ምድረ ገነት ሽሬ እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ምድረ ገነት ሽሬ እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ምድረገነት ሽሬ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ዳንኤል ዳርጌ እና ደሳለኝ ከተማው የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ደሳለኝ ከተማው በ96ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ለቡድኑ ወሳኝ ሶስት አስገኝታለች።
ናትናኤል ዳንኤል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ምድረ ገነት ሽሬ በ26 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ24 ነጥብ ከነበረበት 11ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 አሸንፏል።ደስታ ዋሚሾ በ79ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ወደ አሸናፊነት መንገድ የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና በ27 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ሰባተኛ ድሉን አሳክቷል።
በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።