ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ
Oct 26, 2025 55
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤቨርተንን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ሚኪ ቫን ደቬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፓፔ ሳር ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኤቨርተን በአዲሱ ስታዲየሙ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል። ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ17 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።
ኢትዮጵያ መድን ከወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ፒራሚድስ ጋር አቻ ወጥቷል
Oct 26, 2025 56
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ከግብጹ ፒራሚድስ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል። ማምሻውን ካይሮ በሚገኘው ጁን 30 ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊስተን ማዬሌ በ12ኛው ደቂቃ ፒራማድስን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል። ብሩክ ሙሉጌታ 83ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ግብ ኢትዮጵያ መድን አቻ ሆኗል። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ይቀላቀላል። ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። የግብጹ ፒራሚድስ ክለብ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ባለቤት ነው።
በተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ደርቢ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን አሸነፈ
Oct 26, 2025 54
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ እና ጁድ ቤሊንግሃም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ፌርሚን ሎፔዝ ለባርሴሎና ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኪሊያን ምባፔ በ52ኛው ደቂቃ የፍጹም ቅጣት ምት ስቷል። የባርሴሎናው አማካይ ተጫዋች ፔድሪ በ100ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ነጥቡን ወደ 27 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ባርሴሎና በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦችን በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል
Oct 26, 2025 95
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦች በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ ገለጹ። በባህር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 11ኛው ከፍተኛ ደረጃ ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። "አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ፎረም፤ በአፍሪካ ሠላምና ደህንነት ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች፣ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በትኩረት መክሯል። አፍሪካ በኢኮኖሚ እንዴት ራሷን መቻል አለባት? ምን ዓይነት እርምጃዎች ያስፈልጋሉ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ በአፍሪካ ያሉ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ አካታች ሥርዓት መዘርጋት ለነገ የሚባሉ ጉዳዮች እንዳልሆኑ በፎረሙ በሰፊው ምክክር ተካሂዶበታል። የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ በፎረሙ መዝጊያ ላይ እንዳሉት፤ 11ኛው የጣና ከፍተኛ ደረጃ ፎረም ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል። የፎረሙ መሪ ሀሳብ አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት እንደ አህጉር ልንነጋገርበት የሚገባ ወቅቱን የጠበቀ ጽንሰ ሀሳብ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ዲጂታል የሚደረገው ሽግግር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በፍትሃዊነት እና ዘላቂነት ተደራሽ ማድረግ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። ዓለም በፍጥነት እየተለወጠች መሆኑን አስታውሰው፤አፍሪካም እየተለወጠ ላለው የዓለም ሥርዓት የሚመጥን እንቅስቃሴ ማድረግ አለባት፤ ለዚህ ደግሞ በጣና ፎረም የሚቀርቡ ምክረ ሀሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ከአፍሪካ አገራት በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። አፍሪካ ለማሳካት ያስቀመጠቻቸው ውጥኖች ያለ ወጣቶች ተሳትፎ እውን ሊሆን እንደማይችል አመልክተው፤በአፍሪካ በሁሉም መስክ የሚከናወኑ ተግባራት ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በፎረሙ ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ልዩ መልዕክተኞች ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
Oct 26, 2025 73
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን 1 ለ0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል። በኤሜሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ኤቤሬቺ ኤዜ ከእረፍት በፊት በ39 ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከፓላስ አርሰናልን የተቀላቀለው ኤዜ የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ጎሉንም በቀድሞ ክለቡ ላይ ማስቆጠር ችሏል። አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በ22 ነጥብ መምራት የቻለ ሲሆን ከተከታዮቹ ጋር ያለውንም የነጥብ ልዩነት ማስፋት አስችሎታል። በሌሎች የዛሬ መርሃ ግብር ጨዋታዎች ወደ ቪላ ፓርክ ያቀናው ማንችስተር ሲቲ በተመሳሳይ በአስቶን ቪላ 1ለ0 ተሸንፏል። በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቮልቭስ በበርንሌይ 3ለ2 ፤በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው ቦርንማዝ ደግሞ ኖቲንግሃምን 2ለ0 ያሸነፉበት ጨዋታ የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች ናቸው።
ፖለቲካ
የአካባቢያችንን ሠላምና አንድነት አጠናክረን ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንሰራለን-የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች
Oct 26, 2025 96
ወልዲያ፤ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ):- የአካባቢያቸውን ሠላምና አንድነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 118ኛው የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ ቀን በዓል ዛሬ በወልዲያ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በመድረኩ ላይ ከተገኙት ነዋሪዎች መካከል አቶ አበባው ወደደኝ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለሀገር ዳር-ድንበር መከበር መስዋዕትነት የሚከፍል መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ታጥቆ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ጽንፈኛ ቡድን አደብ በማስገዛት የአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ማስጠበቁን ገልጸው፣ ሰላሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። የወልዲያ ከተማና አካባቢው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ በተለያየ መንገድ ሲያደርጉት የነበረው እገዛ ማጠናከር እንዳለበትም ገልጸዋል። "ህዝቡ ለሠራዊቱ የተለመደ ደጀንነቱን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል" ያሉት ደግሞ ሌላው የበዓሉ ተሳታፊና የከተማው ነዋሪ አቶ ቢሆነኝ ካሣው ናቸው። የህዝብን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ ላለውና የአገር ዘብ ለሆነው መከላከያ ሠራዊታችን የምናደርገው ድጋፍና የምንሰጠው ፍቅር በቀጣይም ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የዛሬው በዓልም ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡትን በቁርጠኝነት በመታገል የአካባቢያችንን ሠላም ለማስጠበቅ ዳግም ቃል የምንገባበት መሆን አለበት ብለዋል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኢትዮጲስ አያሌው የቀደሙ አባቶቻችን ያቆዩልንን የፍቅርና የአንድነት እሴት የአሁኑ ትውልድም አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። ይህ እሴት ተጠናክሮ በከተማው የልማት እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ህብረተሰቡ ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም ሌት ተቀን እየተጋ ያለውን የመከላከያ ሠራዊት በመደገፍ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አክሊሉ አበበ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባሩ የሀገርና የህዝብ ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን አንሰተዋል። "ሠራዊቱን የሚያስጨንቀው የህዝብ ሠላም ሲታወክና የአገር ሉኣላዊነት ሲደፈር ነው፤ ለዚህም ሠራዊታችን ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ የህዝብ ሠላምና የሀገርን ዳር ድንበር ጭምር ያስከብራል" ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ሠራዊቱ የባዳዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተላላኩ ያሉ የጥፋት ቡድኖችን እያሳደደና እየደመሰሰሰ ይገኛል ብለዋል።
በዓሉ ህዝቦች ባህላቸውን በአደባባይ እንዲገልጹና እንዲያስተዋውቁ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ ነው-- የፌዴሬሽን ምክር ቤት
Oct 26, 2025 124
አዳማ፤ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ)፡-የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ህዝቦች ባህላቸውን በአደባባይ አውጥተው እንዲያስተዋውቁ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለፀ። ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት የተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ያተኮረና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው ። በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ እንደገለፁት በዓሉን በየዓመቱ ከማክበር ባለፈ በፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት አስተምህሮ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ዜጎች በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤና አረዳድ እንዲኖራቸው እንዲሁም የህዝቦች አንድነትና አብሮነት እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የዛሬው መድረክም በዓሉን በማስመልከት የፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት አስተምህሮን ይበልጥ ለማስረፅ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ግልጽነትና ለመፍጠርና በቀጣይ በየደረጃው የሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን ለማሳካት ያለመ ነው ብለዋል። በዚህም በፌዴራልና በክልል ደረጃ ባሉ ተቋማት እንዲሁም በዞኖች፣ በወረዳዎችና ከተሞች ላይ በፌዴራሊዝምና ህገመንግስት አስተምህሮ ላይ ለህብረተሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ ማስረጽ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የተሳካ ለማድረግም ከፌዴራል ጀምሮ በክልል፣ በዞንና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የግንዛቤ መፍጠር ሥራዎች በተከታታይ እንደሚከናወኑም ተናግረዋል። በዓሉ የባህል ልውውጥና ትውውቅ እንዲሁም የህዝቦች ግንኙነትና ትስስር የሚጠናከርበት ከመሆኑ ባለፈ ባህሎቻቸውን በአደባባይ የሚያሳዩበት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት አስተምህሮ ማዕከል ዳይሬክተር ሃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ናቸው። በመድረኩ ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ ፌዴራሊዝም የህዝቦች ውክልና በተግባር የሚገለፅበት ነው ብለዋል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የፌዴራል ስርዓቱን ከማጠናከር አንፃር በርካታ አካታችና ሚዛናዊ የሆኑ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። በዓሉ የህዝቦች ባህል፣ ማንነትና ትስስር ይበልጥ ጎልቶ የሚወጣበት መሆኑንም ተናግረዋል። በዓሉ "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከበር ታውቋል።
በኢትዮጵያ የፉክክርና የምክክር ሚዛኑን የጠበቀ ጤናማና የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ነው-አቶ አደም ፋራህ
Oct 26, 2025 124
ባህር ዳር፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የፉክክርና የምክክር ሚዛኑን የጠበቀ ጤናማና የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር የመገንባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለፁ። የአማራ ክልል መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛል። አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ እንደገለጹት፥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ በምክክርና በፉክክር ላይ መሰረት ያደረገ የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት እየተገነባ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ጠንካራ ህገ መንግስት እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ሌሎች የህግ ማዕቀፎች፣ተቋማዊ አደረጃጀቶችና ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ገልፀዋል። እንዲሁም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ አማራጭ ሀሳባቸውን በነፃነት ለህዝብ የሚያደርሱበት ምህዳር መመቻቸቱንም አክለዋል። በተጨማሪም እርስ በእርሳቸው የሚመካከሩበት የሚወያዩበትና የሚነጋገሩበት እንዲሁም ገዥውን ፓርቲ የሚሞግቱበት አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሯል ነው ያሉት። ፓርቲዎች ህግና ስርዓት አክብረው የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር እና ለሰላምና መረጋጋት መስፈን መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። በአማራ ክልል ፅንፈኛ ቡድኖች በህዝብ ላይ እያደረሱ ያለውን በደል ለማስቆምም ፓርቲዎች በትብብር በመስራት ለዳበረ ፖለቲካዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሀገራችን የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። በዚህ ለዳበረ የፖለቲካ ልምምድ ሰላማዊ አማራጭን በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አዎንታዊ ሚናቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይሁን እንጂ በኋላ ቀር አካሄድ የፖለቲካ ስልጣንን በሀይል ለመያዝ ፋላጎቱ ያላቸው ፅንፈኛ ቡድኖች በክልሉ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ የሚስተዋለውን ችግር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሰለጠነ አግባብ በመነጋገር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ሁሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፥ የጋራ ምክር ቤቱ የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት በመገንባት በኩል ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። በዚህም ፓርቲዎች በመመካከርና በመነጋገር የሚገጥሙ ችግሮችን በሰለጠነ አግባብ በትብብር መፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይህም በሀገሪቱ በምክክርና በፉክክር የተመሰረተ ጤናማ የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር እንዲገነባ የጋራ ምክር ቤቱ እየሰራ ነው ብለዋል። ምክር ቤቱ በጋራ ለጋራ ህዝባችን የምንወያይበት መድረክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ሲሉም አብራርተዋል። በመድረኩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር ኃላፊነቱን በላቀ ብቃት እየተወጣ ነው
Oct 25, 2025 198
ድሬዳዋ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር ኃላፊነቱን በአኩሪ ጀግንነትና በላቀ ብቃት እየተወጣ መሆኑን የኢፌዴሪ አየር ኃይል የሶስተኛ አየር ምድብ ስታፍ አስተባባሪ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዱላ ደበጭ አስታወቁ። በድሬዳዋ የሶስተኛው አየር ምድብ አመራሮች እና አባላት 118ኛውን የሠራዊት ቀን " የማትደፈር ሀገር፣ የማይበገር ሠራዊት" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ዛሬ ማክበር ጀምረዋል። ቀኑ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ በልማት ተግባራት ፣ በፓናል ውይይት እና በፅዳት ስራዎች ነው የተከበረው። በዚህ ወቅት የሶስተኛው አየር ምድብ ስታፍ አስተባባሪ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዱላ ደበጭ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የሰራዊት ቀን የእርስ በእርስ ትስስርና አንድነትን ይበልጥ በሚያፀኑ እና በሚያልቁ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። የዘንድሮው በዓል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበትና የባሕር በር የማግኘት ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብት የዜጎች ሁሉ አጀንዳ በሆነበት ማግስት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። ሠራዊቱ የሀገርን ሉአላዊነትና ብሔራዊ ጥቅሞች የማስከበር ኃላፊነቱን በታላቅ ብቃት፣ በአኩሪ ጀግንነትና ቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ኮሎኔሉ አስታውቀዋል። በቀጣይም ሀገራችንን ከታሪካዊ ጠላቶቻችንና ባንዳዎች በአስተማማኝ መንገድ የመጠበቁን ተልእኮ በላቀ ብቃት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የሶስተኛ አየር ምድብ የሰራዊት ስነምግባር ዋና ክፍል ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጌታቸው ማሞ በበኩላቸው ፤ በምድቡ መከበር የጀመረው በዓል ሰራዊቱ አገራዊ ተልዕኮውን የመወጣት ዝግጁነቱን ከማጠናከር ባሻገር በማህበራዊ ልማት ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል። ሰራዊቱ ለየትኛውም ፈተና ሳይበገር የአገርን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መንገድ እየጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሎኔል ጌታቸው፤ ሰራዊቱ በሁሉም መስክ ራሱን በማዘመን የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር፣ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት መወጣቱን ቀጥሏል ብለዋል ።
በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀቶችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል- ምሁራን
Oct 25, 2025 212
ዲላ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀቶችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሰላም ሚኒስቴርና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር "ስለ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በዲላ ከተማ አካሄዷል። መድረኩ "ሰላም ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን በባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ምሁራን የውይይት መነሻ ፅሁፎችን አቅርበዋል። በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በብዝሃ ባህል የተዋበች ለሰላም እሴት ግንባታ መሰረት የጣሉ ባህሎችና ልማዶች መገኛ መሆኗን አጽንኦት ሰጥተዋል። "ማህበረ ባህላዊ እሴቶች ለአንድነታችን ያላቸው ሚና" በሚል መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት በአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን፤ ኢትዮጵያ በብዝሃ ባህል የተዋበች ለሰላም እሴት ግንባታ መሰረት የጣሉ ባህሎችና ልማዶች ያሏት ድንቅ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። በተለይ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰላም ከታች የሚጀመር የህዝቦች ትስስር ውጤት መሆኑን አለመገንዘብ በሀገር መንግስት ግንባታ ላይ ጫና ማሳደሩን አስረድተዋል። የመደመር መንግስት ሀገራዊ ወረቶችን ደምሮ ለላቀ ልማትና ሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት እያኖረ መሆኑን ገልጸው ሀገር በቀልና የካበቱ የሰላም ግንባታ አቅሞችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ብለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለው ሰላም የህዝቦችን ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ጸጋዎችን እንድንጠቅም አቅም ፈጥሯል ያሉት ደግሞ "በሰላምና ልማት ቁርኝት" ላይ ሃሳብ ያቀረቡት በክልሉ ምክትል ርእስ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ናቸው። በክልሉ ከ1 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለግብርና ልማት በማዋል የቡና፣ የቅመማ ቅመምና የቅባት እህሎች ከምግብ ፍጆታ አልፈው ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። ለዚህም በክልሉ የሚገኙ ብዝሃ ባህልና የሰላም እሴቶች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን አንስተው ይህንንም በማጠናከር ብልጽግናን እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ ሰላም ለቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ያለው ፋይዳ" በሚል ርዕስ ሀሳብ ያቀረቡት ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁኔታዎች ክትትል ዳይሬክተር ጄኔራል ዘሩባቤል ጌታቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው የአፍሪካ ቀንድ ትስስር ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በውሃ፣ በኃይል ልማትና በግብርና ምርቶች አቅርቦት ድርሻዋ የጎላ መሆኑን አንስተው ይህንኑ የሚመጥን የመሪነት ሚናን ለማጠናከር የውስጥ አቅም ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። በቀጣናው ያለውን የምጣኔ ሃብት ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የኢትዮጵያ ሚና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ርእሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
Oct 25, 2025 145
ጋምቤላ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በጋምቤላ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። በጋምቤላ ክልል የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅምን እና የአገልግሎት ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ የአመራሮች ሽግሽግ ተደርጓል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ፤ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና የሕዝብን የመገልገል ፍላጎት መሰረት በማድረግ ብቁና ጠንካራ የአመራር አደረጃጀት መፍጠር ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በዚሕም መሰረት በክልሉ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ በማስፈለጉ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ሽግሽግ መደረጉን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት የነበረውን የመፈፀም አቅም መሰረት በማድረግ ብቃትን መሰረት ያደረገ የአመራር ሽግሽግና አዲስ ምደባ ጭምር መደረጉን ነው የገለጹት። በዚህም መሰረት በክልሉ ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሰላምን ለማጽናት እንሰራለን - የወልዲያ ከተማ ነጋዴዎች
Oct 25, 2025 157
ወልድያ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፡- በሰላም ወጥተን ለመግባትና ሰርተን ለመኖር የሚስፈልገን ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል እንሰራለን ሲሉ የወልዲያ ከተማ የንግድ ማሕበረሰብ አባላት ገለጹ። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር "ሰላም ለሁሉም! ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ተወያይተዋል። ከውይይቱ ተሳታፊ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት መካከል አቶ ቢሰጠኝ አዲሱ በወቅቱ እንዳሉት፤ ነጋዴው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ለመስራትና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሰላም መኖር ወሳኝ ነው። የፅንፈኛው ቡድን የጥፋት ተላላኪዎች ነጋዴውንና አርሶ አደሩን በመዝረፍ፣ የትምህርትና የጤና ተቋማትን በማውደምና ሰውን በማገት ሃብትና ቁስ በማካበት ችግር ሲፈጥሩብን ቆይተዋል ብለዋል። የጥፋት ተላላኪዎችን እኩይ ሴራ ለማምከን ከመንግስት ጎን ተሰልፈን በቁርጠኝነት በመስራት ለውጥ አምጥተናል ይህንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል። ችግርን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የውይይት መድረክ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ጫኔ ዓለሙ ናቸው። ጽንፈኛው ቡድን በፈጠረው ችግር ተንቀሳቅሰው ለመስራትና ነግደው ለማትረፍ ሲቸገሩ እንደቆዩ አስታውሰው፤ በቀጣይም የሚያስፈልገን ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል ተሳትፏችንን ይበልጥ እናጠናክራለን ሲሉ ገልጸዋል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ፤ ጽንፈኛ ቡድኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ እገዛ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የመከላከያ ሠራዊታችን ለመላው ሕዝባችን ሰላምና ደህንነት ውድ ህይወቱን እየሠጠ ነው ያሉት ደግሞ በ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ- ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አክሊሉ አበበ ናቸው። ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት የሕዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ጽንፈኛውን እያሳደደና እየደመሰሰ ከአካባቢው እያጸዳ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህንኑ ተግባር ዳር በማድረስ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረትም የወልዲያና አካባቢው የንግዱ ማሕበረሰብ እያደረገ ያለውን እገዛ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ ነው- ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
Oct 25, 2025 156
አዳማ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ( ዶ/ር) ገለጹ። በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በፌዴራል ተቋማት የአደረጃጀት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ( ዶ/ር)፤ በበጀት ዓመቱ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት መሰረት የሆኑ በርካታ ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተዋል። የትራንስፖርት ዘርፉም ለሀገር ማንሰራራት ትልቅ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዘርፉ የአሰራር ለውጦች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት ይገኛል ብለዋል። በተለይም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የአፈር ማዳበሪያን በማጓጓዝ የትራንስፖርት ዘርፉ ትልቅ አሻራ እያኖረ መሆኑን አንስተው የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ሂደት የአሽከርካሪዎችን የሙያዊ ብቃት የማጎልበት፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ማስቀረትን ጨምሮ ሌሎችም ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል። የትራንስፖርት ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አመራር እና አባላት በዘርፉ የተገኘው ውጤት የበለጠ እንዲጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታና በፓርቲው የትራንስፖርት ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው፤ ስልጠናው የተዘጋጀው የፓርቲው አመራርና አባላት የሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤና አረዳድ እንዲኖራቸው ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል። ስልጠናው ከመደመር እሳቤ እስከ መደመር መንግስት መፅሐፍ ላይ በማተኮር ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ይህም የፓርቲው አመራር እና አባላት የፓርቲውን የአሰራር ደንቦችና መመሪያዎች ተገንዝበው እንዲፈጽሙ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
ፖለቲካ
የአካባቢያችንን ሠላምና አንድነት አጠናክረን ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንሰራለን-የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች
Oct 26, 2025 96
ወልዲያ፤ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ):- የአካባቢያቸውን ሠላምና አንድነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም እንደሚሰሩ የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 118ኛው የመከላከያ ሠራዊት የምስረታ ቀን በዓል ዛሬ በወልዲያ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በመድረኩ ላይ ከተገኙት ነዋሪዎች መካከል አቶ አበባው ወደደኝ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለሀገር ዳር-ድንበር መከበር መስዋዕትነት የሚከፍል መሆኑን ገልጸዋል። በአካባቢያቸው ታጥቆ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ጽንፈኛ ቡድን አደብ በማስገዛት የአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ማስጠበቁን ገልጸው፣ ሰላሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። የወልዲያ ከተማና አካባቢው ህዝብ ለመከላከያ ሠራዊቱ በተለያየ መንገድ ሲያደርጉት የነበረው እገዛ ማጠናከር እንዳለበትም ገልጸዋል። "ህዝቡ ለሠራዊቱ የተለመደ ደጀንነቱን ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏል" ያሉት ደግሞ ሌላው የበዓሉ ተሳታፊና የከተማው ነዋሪ አቶ ቢሆነኝ ካሣው ናቸው። የህዝብን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ ላለውና የአገር ዘብ ለሆነው መከላከያ ሠራዊታችን የምናደርገው ድጋፍና የምንሰጠው ፍቅር በቀጣይም ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የዛሬው በዓልም ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የጥፋት ተልዕኮ ያነገቡትን በቁርጠኝነት በመታገል የአካባቢያችንን ሠላም ለማስጠበቅ ዳግም ቃል የምንገባበት መሆን አለበት ብለዋል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኢትዮጲስ አያሌው የቀደሙ አባቶቻችን ያቆዩልንን የፍቅርና የአንድነት እሴት የአሁኑ ትውልድም አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ብለዋል። ይህ እሴት ተጠናክሮ በከተማው የልማት እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ህብረተሰቡ ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም ሌት ተቀን እየተጋ ያለውን የመከላከያ ሠራዊት በመደገፍ የድርሻውን ይወጣል ብለዋል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አክሊሉ አበበ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባሩ የሀገርና የህዝብ ሠላምን ማስጠበቅ መሆኑን አንሰተዋል። "ሠራዊቱን የሚያስጨንቀው የህዝብ ሠላም ሲታወክና የአገር ሉኣላዊነት ሲደፈር ነው፤ ለዚህም ሠራዊታችን ውድ ህይወቱን ጭምር እየከፈለ የህዝብ ሠላምና የሀገርን ዳር ድንበር ጭምር ያስከብራል" ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ሠራዊቱ የባዳዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተላላኩ ያሉ የጥፋት ቡድኖችን እያሳደደና እየደመሰሰሰ ይገኛል ብለዋል።
በዓሉ ህዝቦች ባህላቸውን በአደባባይ እንዲገልጹና እንዲያስተዋውቁ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ ነው-- የፌዴሬሽን ምክር ቤት
Oct 26, 2025 124
አዳማ፤ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ)፡-የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ህዝቦች ባህላቸውን በአደባባይ አውጥተው እንዲያስተዋውቁ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለፀ። ዘንድሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በማስመልከት የተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ያተኮረና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው ። በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ትግሉ መለሰ እንደገለፁት በዓሉን በየዓመቱ ከማክበር ባለፈ በፌዴራሊዝምና ህገ መንግስት አስተምህሮ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ዜጎች በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ግንዛቤና አረዳድ እንዲኖራቸው እንዲሁም የህዝቦች አንድነትና አብሮነት እንዲጠናከር በማድረግ ረገድ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የዛሬው መድረክም በዓሉን በማስመልከት የፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት አስተምህሮን ይበልጥ ለማስረፅ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ግልጽነትና ለመፍጠርና በቀጣይ በየደረጃው የሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን ለማሳካት ያለመ ነው ብለዋል። በዚህም በፌዴራልና በክልል ደረጃ ባሉ ተቋማት እንዲሁም በዞኖች፣ በወረዳዎችና ከተሞች ላይ በፌዴራሊዝምና ህገመንግስት አስተምህሮ ላይ ለህብረተሰቡ ተገቢውን ግንዛቤ ማስረጽ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የተሳካ ለማድረግም ከፌዴራል ጀምሮ በክልል፣ በዞንና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የግንዛቤ መፍጠር ሥራዎች በተከታታይ እንደሚከናወኑም ተናግረዋል። በዓሉ የባህል ልውውጥና ትውውቅ እንዲሁም የህዝቦች ግንኙነትና ትስስር የሚጠናከርበት ከመሆኑ ባለፈ ባህሎቻቸውን በአደባባይ የሚያሳዩበት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የፌዴራሊዝምና ህገ መንግሥት አስተምህሮ ማዕከል ዳይሬክተር ሃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር) ናቸው። በመድረኩ ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ ፌዴራሊዝም የህዝቦች ውክልና በተግባር የሚገለፅበት ነው ብለዋል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የፌዴራል ስርዓቱን ከማጠናከር አንፃር በርካታ አካታችና ሚዛናዊ የሆኑ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። በዓሉ የህዝቦች ባህል፣ ማንነትና ትስስር ይበልጥ ጎልቶ የሚወጣበት መሆኑንም ተናግረዋል። በዓሉ "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከበር ታውቋል።
በኢትዮጵያ የፉክክርና የምክክር ሚዛኑን የጠበቀ ጤናማና የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ነው-አቶ አደም ፋራህ
Oct 26, 2025 124
ባህር ዳር፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የፉክክርና የምክክር ሚዛኑን የጠበቀ ጤናማና የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር የመገንባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለፁ። የአማራ ክልል መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛል። አቶ አደም ፋራህ በመድረኩ እንደገለጹት፥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ በምክክርና በፉክክር ላይ መሰረት ያደረገ የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት እየተገነባ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ጠንካራ ህገ መንግስት እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ሌሎች የህግ ማዕቀፎች፣ተቋማዊ አደረጃጀቶችና ምቹ ነባራዊ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ገልፀዋል። እንዲሁም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ አማራጭ ሀሳባቸውን በነፃነት ለህዝብ የሚያደርሱበት ምህዳር መመቻቸቱንም አክለዋል። በተጨማሪም እርስ በእርሳቸው የሚመካከሩበት የሚወያዩበትና የሚነጋገሩበት እንዲሁም ገዥውን ፓርቲ የሚሞግቱበት አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሯል ነው ያሉት። ፓርቲዎች ህግና ስርዓት አክብረው የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር እና ለሰላምና መረጋጋት መስፈን መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። በአማራ ክልል ፅንፈኛ ቡድኖች በህዝብ ላይ እያደረሱ ያለውን በደል ለማስቆምም ፓርቲዎች በትብብር በመስራት ለዳበረ ፖለቲካዊ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሀገራችን የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። በዚህ ለዳበረ የፖለቲካ ልምምድ ሰላማዊ አማራጭን በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አዎንታዊ ሚናቸውን እየተወጡ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይሁን እንጂ በኋላ ቀር አካሄድ የፖለቲካ ስልጣንን በሀይል ለመያዝ ፋላጎቱ ያላቸው ፅንፈኛ ቡድኖች በክልሉ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ የሚስተዋለውን ችግር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሰለጠነ አግባብ በመነጋገር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ሁሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ በበኩላቸው፥ የጋራ ምክር ቤቱ የዳበረ የፖለቲካ ስርዓት በመገንባት በኩል ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። በዚህም ፓርቲዎች በመመካከርና በመነጋገር የሚገጥሙ ችግሮችን በሰለጠነ አግባብ በትብብር መፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይህም በሀገሪቱ በምክክርና በፉክክር የተመሰረተ ጤናማ የዳበረ የፖለቲካ ምህዳር እንዲገነባ የጋራ ምክር ቤቱ እየሰራ ነው ብለዋል። ምክር ቤቱ በጋራ ለጋራ ህዝባችን የምንወያይበት መድረክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ሲሉም አብራርተዋል። በመድረኩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር ኃላፊነቱን በላቀ ብቃት እየተወጣ ነው
Oct 25, 2025 198
ድሬዳዋ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- የመከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር ኃላፊነቱን በአኩሪ ጀግንነትና በላቀ ብቃት እየተወጣ መሆኑን የኢፌዴሪ አየር ኃይል የሶስተኛ አየር ምድብ ስታፍ አስተባባሪ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዱላ ደበጭ አስታወቁ። በድሬዳዋ የሶስተኛው አየር ምድብ አመራሮች እና አባላት 118ኛውን የሠራዊት ቀን " የማትደፈር ሀገር፣ የማይበገር ሠራዊት" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ዛሬ ማክበር ጀምረዋል። ቀኑ በስፖርታዊ ውድድሮች፣ በልማት ተግባራት ፣ በፓናል ውይይት እና በፅዳት ስራዎች ነው የተከበረው። በዚህ ወቅት የሶስተኛው አየር ምድብ ስታፍ አስተባባሪ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዱላ ደበጭ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የሰራዊት ቀን የእርስ በእርስ ትስስርና አንድነትን ይበልጥ በሚያፀኑ እና በሚያልቁ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። የዘንድሮው በዓል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበትና የባሕር በር የማግኘት ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብት የዜጎች ሁሉ አጀንዳ በሆነበት ማግስት መከበሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። ሠራዊቱ የሀገርን ሉአላዊነትና ብሔራዊ ጥቅሞች የማስከበር ኃላፊነቱን በታላቅ ብቃት፣ በአኩሪ ጀግንነትና ቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ኮሎኔሉ አስታውቀዋል። በቀጣይም ሀገራችንን ከታሪካዊ ጠላቶቻችንና ባንዳዎች በአስተማማኝ መንገድ የመጠበቁን ተልእኮ በላቀ ብቃት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የሶስተኛ አየር ምድብ የሰራዊት ስነምግባር ዋና ክፍል ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጌታቸው ማሞ በበኩላቸው ፤ በምድቡ መከበር የጀመረው በዓል ሰራዊቱ አገራዊ ተልዕኮውን የመወጣት ዝግጁነቱን ከማጠናከር ባሻገር በማህበራዊ ልማት ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል። ሰራዊቱ ለየትኛውም ፈተና ሳይበገር የአገርን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት በአስተማማኝ መንገድ እየጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሎኔል ጌታቸው፤ ሰራዊቱ በሁሉም መስክ ራሱን በማዘመን የሀገርን ሉአላዊነት የማስከበር፣ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት መወጣቱን ቀጥሏል ብለዋል ።
በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀቶችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል- ምሁራን
Oct 25, 2025 212
ዲላ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል እውቀቶችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሰላም ሚኒስቴርና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር "ስለ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በዲላ ከተማ አካሄዷል። መድረኩ "ሰላም ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን በባህላዊ እሴቶች ዙሪያ ምሁራን የውይይት መነሻ ፅሁፎችን አቅርበዋል። በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በብዝሃ ባህል የተዋበች ለሰላም እሴት ግንባታ መሰረት የጣሉ ባህሎችና ልማዶች መገኛ መሆኗን አጽንኦት ሰጥተዋል። "ማህበረ ባህላዊ እሴቶች ለአንድነታችን ያላቸው ሚና" በሚል መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት በአውስትራሊያ የዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን፤ ኢትዮጵያ በብዝሃ ባህል የተዋበች ለሰላም እሴት ግንባታ መሰረት የጣሉ ባህሎችና ልማዶች ያሏት ድንቅ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። በተለይ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሰላም ከታች የሚጀመር የህዝቦች ትስስር ውጤት መሆኑን አለመገንዘብ በሀገር መንግስት ግንባታ ላይ ጫና ማሳደሩን አስረድተዋል። የመደመር መንግስት ሀገራዊ ወረቶችን ደምሮ ለላቀ ልማትና ሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት እያኖረ መሆኑን ገልጸው ሀገር በቀልና የካበቱ የሰላም ግንባታ አቅሞችንና የአብሮነት መገለጫ እሴቶችን በማካበት ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ብለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለው ሰላም የህዝቦችን ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ጸጋዎችን እንድንጠቅም አቅም ፈጥሯል ያሉት ደግሞ "በሰላምና ልማት ቁርኝት" ላይ ሃሳብ ያቀረቡት በክልሉ ምክትል ርእስ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ናቸው። በክልሉ ከ1 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለግብርና ልማት በማዋል የቡና፣ የቅመማ ቅመምና የቅባት እህሎች ከምግብ ፍጆታ አልፈው ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። ለዚህም በክልሉ የሚገኙ ብዝሃ ባህልና የሰላም እሴቶች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን አንስተው ይህንንም በማጠናከር ብልጽግናን እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ ሰላም ለቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ያለው ፋይዳ" በሚል ርዕስ ሀሳብ ያቀረቡት ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁኔታዎች ክትትል ዳይሬክተር ጄኔራል ዘሩባቤል ጌታቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው የአፍሪካ ቀንድ ትስስር ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ በውሃ፣ በኃይል ልማትና በግብርና ምርቶች አቅርቦት ድርሻዋ የጎላ መሆኑን አንስተው ይህንኑ የሚመጥን የመሪነት ሚናን ለማጠናከር የውስጥ አቅም ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል። በቀጣናው ያለውን የምጣኔ ሃብት ትስስርና የጋራ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የኢትዮጵያ ሚና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በክልሉ ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ርእሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
Oct 25, 2025 145
ጋምቤላ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በጋምቤላ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። በጋምቤላ ክልል የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅምን እና የአገልግሎት ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ የአመራሮች ሽግሽግ ተደርጓል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ፤ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና የሕዝብን የመገልገል ፍላጎት መሰረት በማድረግ ብቁና ጠንካራ የአመራር አደረጃጀት መፍጠር ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በዚሕም መሰረት በክልሉ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ በማስፈለጉ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ሽግሽግ መደረጉን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት የነበረውን የመፈፀም አቅም መሰረት በማድረግ ብቃትን መሰረት ያደረገ የአመራር ሽግሽግና አዲስ ምደባ ጭምር መደረጉን ነው የገለጹት። በዚህም መሰረት በክልሉ ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ሰላምን ለማጽናት እንሰራለን - የወልዲያ ከተማ ነጋዴዎች
Oct 25, 2025 157
ወልድያ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ)፡- በሰላም ወጥተን ለመግባትና ሰርተን ለመኖር የሚስፈልገን ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል እንሰራለን ሲሉ የወልዲያ ከተማ የንግድ ማሕበረሰብ አባላት ገለጹ። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር "ሰላም ለሁሉም! ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ተወያይተዋል። ከውይይቱ ተሳታፊ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት መካከል አቶ ቢሰጠኝ አዲሱ በወቅቱ እንዳሉት፤ ነጋዴው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ለመስራትና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሰላም መኖር ወሳኝ ነው። የፅንፈኛው ቡድን የጥፋት ተላላኪዎች ነጋዴውንና አርሶ አደሩን በመዝረፍ፣ የትምህርትና የጤና ተቋማትን በማውደምና ሰውን በማገት ሃብትና ቁስ በማካበት ችግር ሲፈጥሩብን ቆይተዋል ብለዋል። የጥፋት ተላላኪዎችን እኩይ ሴራ ለማምከን ከመንግስት ጎን ተሰልፈን በቁርጠኝነት በመስራት ለውጥ አምጥተናል ይህንን ማጠናከር ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል። ችግርን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የውይይት መድረክ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ጫኔ ዓለሙ ናቸው። ጽንፈኛው ቡድን በፈጠረው ችግር ተንቀሳቅሰው ለመስራትና ነግደው ለማትረፍ ሲቸገሩ እንደቆዩ አስታውሰው፤ በቀጣይም የሚያስፈልገን ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል ተሳትፏችንን ይበልጥ እናጠናክራለን ሲሉ ገልጸዋል። የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ፤ ጽንፈኛ ቡድኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት እየተደረገ ባለው እንቅስቃሴ ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ እገዛ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የመከላከያ ሠራዊታችን ለመላው ሕዝባችን ሰላምና ደህንነት ውድ ህይወቱን እየሠጠ ነው ያሉት ደግሞ በ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ሥነ- ልቦና ግንባታ ኃላፊ ኮሎኔል አክሊሉ አበበ ናቸው። ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት የሕዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ጽንፈኛውን እያሳደደና እየደመሰሰ ከአካባቢው እያጸዳ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህንኑ ተግባር ዳር በማድረስ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረትም የወልዲያና አካባቢው የንግዱ ማሕበረሰብ እያደረገ ያለውን እገዛ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ ነው- ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
Oct 25, 2025 156
አዳማ ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ( ዶ/ር) ገለጹ። በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በፌዴራል ተቋማት የአደረጃጀት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ( ዶ/ር)፤ በበጀት ዓመቱ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት መሰረት የሆኑ በርካታ ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተዋል። የትራንስፖርት ዘርፉም ለሀገር ማንሰራራት ትልቅ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዘርፉ የአሰራር ለውጦች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት ይገኛል ብለዋል። በተለይም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የአፈር ማዳበሪያን በማጓጓዝ የትራንስፖርት ዘርፉ ትልቅ አሻራ እያኖረ መሆኑን አንስተው የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ዘመናዊ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች እየታዩ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ሂደት የአሽከርካሪዎችን የሙያዊ ብቃት የማጎልበት፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ማስቀረትን ጨምሮ ሌሎችም ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል። የትራንስፖርት ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አመራር እና አባላት በዘርፉ የተገኘው ውጤት የበለጠ እንዲጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታና በፓርቲው የትራንስፖርት ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው፤ ስልጠናው የተዘጋጀው የፓርቲው አመራርና አባላት የሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤና አረዳድ እንዲኖራቸው ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል። ስልጠናው ከመደመር እሳቤ እስከ መደመር መንግስት መፅሐፍ ላይ በማተኮር ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ይህም የፓርቲው አመራር እና አባላት የፓርቲውን የአሰራር ደንቦችና መመሪያዎች ተገንዝበው እንዲፈጽሙ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
ማህበራዊ
በክልሉ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች መዳረሻ በማድረግ የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው
Oct 26, 2025 143
ደሴ፣ ጥቅምት16/2018 (ኢዜአ):-በአማራ ክልል ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች መዳረሻ በማድረግ የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ የጡሩሲና መስጊድ እና ሐሪማ የመልሶ ግንባታ ተጠናቆ ተመርቋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ መልካሙ ፀጋዬ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መስህቦችን በማልማት ለጎብኚዎች መዳረሻ በማድረግ የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች የተጎዱ ቅርሶችን መልሶ በመገንባት፣ በመጠገንና በማደስ የዘርፉ ልማት ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። በዛሬው እለት ለምረቃ የበቃው የጡሩሲና መስጅድና ሐሪማ ግንባታም ከዚሁ ጋር የተገናኘ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ መሰል የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሃብቶችን የማልማትና የሀገር ሀብት ሆነው እንዲቀጥሉ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል። በክልሉ በሁሉም መስኮች ልማትን በማስቀጠልና ሰላምን በማፅናት ለእድገትና ማንሰራራት በጋራ መትጋት ይገባል ብለዋል። በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አህመድ አሊ፣ የቱሪዝም ሀብቶችን የመጠበቅ፣ የማልማትና የገቢ ምንጭነታቸውን የማሳደግ ሥራ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የጡሩሲና መስጅድና ሐሪማ በመንግስትና በህብረተሰቡ ትብብር ታሪካዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ የመልሶ ግንባታ ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል። በምረቃ ሥነ ስርአቱ ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
99 ጊዜ ደም በመለገስ አርአያነትን ያሳዩ የሕይወት አድን ጀግና!
Oct 26, 2025 73
የፐብሊክ ሰርቪስ ባስ ሹፌር የሆኑት አቶ ሙላት አስራት ለበጎ ተግባር ከፍ ያለ አመለካከት አላቸው። "ሰው ማገልገል ክብር ነው፤ የተቸገረን መርዳት የሕሊና እርካታ ያስገኛል" የሚለው የሕይወት መርሃቸው ነው። በዚህም መርሕ ተጉዘው በበጎ ተግባራቸው ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሕይወት ተስፋ ሆነዋል። የዚህ ታሪክ መንደርደሪያ አቶ ሙላት የ99 ጊዜ የደም ልገሳ በማድረግ ላሳዩት አርአያነት በ27ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የጤና ሚኒስቴር በልዩ ተሸላሚነት ዕውቅና የሰጣቸው መሆኑ ነው። አቶ ሙላት ቀን ከሌት በሹፌርነት ከማገልገል በተጨማሪ፣ 99 ጊዜ ደም በመለገስ ለወገኖቻቸው በመስጠት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ችለዋል። ይህ አስገራሚ ተግባራቸው የማይነጥፍ ደግነታቸውን ያሳያል። አዲስ አበባ ከተማ ተወልደው ያደጉት አቶ ሙላት፣ የደም ልገሳን ልማድ የጀመሩት ገና በወጣትነታቸው እንደሆነ ይናገራሉ። "ገና የቀይ መስቀል ክበብ አባል ሆኜ የጀመርኩት የተቀደሰ ተግባር ዛሬም ቀጥሏል" የሚሉት አቶ ሙላት፤ ይህን የጀመሩት ደም መለገስ የሌሎችን ሕይወት ለመታደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ መሆኑን በመገንዘብ እንደሆነ ያስረዳሉ። የደም ልገሳን አስፈላጊነት ተረድተው ወደ ተግባር ከተሰማሩ በኋላ ከ28 ዓመታት በላይ ያለማቋረጥ በማካሄድ ታላቅ በጎነት ፈጽመዋል። በነዚህ ሁሉ ዓመታት ውስጥ ደም የመለገስ ልምዳቸው ለጤናቸው ምንም ዓይነት እክል አለመፍጠሩን ያወሳሉ። "ግድ የላችሁም ደም ለግሱ፤ ምንም ጤናችሁ ላይ ጉዳት አያደርስም፤ እኔም ምስክር ነኝ" ሲሉ ወጣቶችን ያበረታታሉ። አዎ ለ99 ጊዜ ደም በመለገስ ያሳዩት ልዩ የበጎ ተግባር አገልግሎት፣ ቀኑን ጠብቆ ዕውቅና ሲሰጣቸው ስሜታቸው ልዩ ነበር። በጉባኤው ተሳታፊዎችም አቶ ሙላት ለሕይወት አድን ተግባር ባሳዩት ልዕለ-በጎነት ልዩ ቦታ ሰጥተው አመስግነዋቸዋል። "ፈጣሪ ዕድሜና ጤና እስኪሰጠኝ ድረስ ደም መለገሴን አላቆምም" ሲሉ ለበጎ ተግባር ያላቸውን የማይለወጥ ቁርጠኝነት ያረጋገጡት አቶ ሙላት፣ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለሰዎች እንደሚኖሩም ገልጸዋል። ወጣቶች የእርሳቸውን መልካም ተግባር በመከተል ደም እንዲለግሱም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። "የበጎነት መንፈስ የሚታየው በገንዘብ ልገሳ ብቻ ሳይሆን የራስን የሰውነት ክፍል በመስጠትም ጭምር ነው" የሚለውን አባባል ያስመሰከሩ እውነተኛ የሕይወት አድን ጀግና ናቸው አቶ ሙላት አስራት።
ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ነው
Oct 26, 2025 101
ሳጃ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):-ሀገር በቀል ዕውቀቶችና እሴቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከየም ዞን ጋር በመተባበር በየም ባህላዊ መድኃኒት እውቀት እና አጠቃቀም ዙሪያ የተዘጋጀ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በወቅቱ እንዳሉት ኢትዮጵያ በርካታ ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ዕሴቶችና ትውፊቶች ያሏት ሀገር ናት ። ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ እሴቶችና ትውፊቶች የህዝቦች አጠቃላይ ህይወትና የኑሮ ዘይቤ ምሶሶ መሆናቸውን አንስተዋል ። በሀገሪቱ ያሉ ዕምቅ ሀገር በቀል ዕውቀቶችና ትውፊቶችን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የማልማትና የማስተዋወቅ እንዲሁም ተገቢውን ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ። ቀደምት አባቶች ጠብቀው ያቆዩት የየም ባህላዊ የመድሀኒት ዕውቀት ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ሚኒስቴሩ እውቀቱ ለትውልድ እንዲተላለፍ በትብብር እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል ። በዚህ እረገድ ሌሎች ባለድርሻዎችም ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር) በየም ዞን ውስጥ ካሉት ዕሴቶች መካከል አንዱ የሆነው የመድሃኒት ቅመማ እውቀትን ለመጠበቅና ለማሳደግ በተቀናጀ መንገድ እየሰራን ነው ብለዋል ። በተለይም በባህል መድኃኒት ቅመማ ረገድ ያለው እውቀት ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ የተለያዩ ጥረቶች እንደሚደረጉ አስታውቀዋል ። የየም ባህላዊ መድኃኒት ለቀማና ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትን ለማሳደግና ለማዳበር ከተለያዩ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሽመልስ እጅጉ ናቸው። በየአመቱ ጥቅምት 17 በቦር ተራራ የሚካሄደው የመድሀኒት እጽዋት ለቀማ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር እረገድም ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል ። እውቀቱና ትውፊቱ ተጠብቆ እንዲቆይና ለቀጣይ ትውልድ እንዲሸጋገር የመሰነድና ሌሎች የምርምር ስራዎችን ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል። በመድረኩ በዞኑ የሚገኙ የሀገር በቀል ዕውቀቶችን፣ የባህላዊ መድኃኒት እውቀትና አጠቃቀም የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ከጅማ፣ ከወልቂጤ፣ ዋቸሞና ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ምሁራን እና ከተለያዩ አካላት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል ። በየም ባህላዊ መድኃኒት እውቀትና አጠቃቀም ዙሪያ ሲምፖዚየም እንዲሁም በባህል መድኃኒት ለቀማና ቅመማ ጋር በተያያዘ የተዘጋጀ የፎቶ ኤግዝብሽን ምልከታ ተደርጓል። በመድረኩ የፌደራልና በየደረጃ ያሉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
በድሬዳዋ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Oct 26, 2025 59
ድሬዳዋ፣ ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ አስተዳደር በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ። በአስተዳደሩ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ያስገነቧቸው 80 ቤቶች ዛሬ ተመርቀው ለችግረኛ ቤተሰቦች ተሰጥተዋል። ቤቶቹን መርቀው ለችግረኞችና ለአረጋዊያን ቁልፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፈትህያ አደን፣ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአስተዳደሩ ምክር ቤት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው። ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በበጎ ፍቃድ ሥራዎች እርስ በርስ ለመደጋገፍ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እያስገኙ ናቸው። በተለይም የማህበረሰቡን ችግሮች በማቃለል እና ተጨባጭ መፍትሄ በማምጣት የጎላ አበርክቶ አላቸው ብለዋል። ዛሬ ተመርቀው ለችግረኞች የተላለፉት ቤቶች የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው ይሄ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በበጋ ወራትም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በቅንጅት የሚሰራው ሥራ የሚበረታታና በሌሎቹም የልማት መስኮች ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል። በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሳተፉ ተቋማት በአጭር ጊዜ መኖሪያ ቤቶችን በጥራት ገንብተው ለችግረኞች በማስተላለፋቸው አመስግነው ይሄ የመደጋገፍ ባህል ይበልጥ ማስፋትና ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። "በበጎ ፍቃድ ሥራ በመሳተፍ የዜጎችን ችግሮች መፍታት ደስታና እርካታ ያጎናፅፋል" ያሉት ደግሞ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አስተባባሪው የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ ናቸው። በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ300 ሺህ በላይ የአስተዳደሩ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ 14 ዓይነት የበጎ ፍቃድ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን አስታውቀዋል። በልማት ስራው ከ90 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን አስታውሰው ከሁለት ሳምንት በኋላ ደግሞ በዚሁ መርሃግብር የተገነቡ ሌሎች ቤቶች ተመርቀው ይተላለፋሉ ብለዋል። ዛሬ የቤት ባለቤት የሆኑት አረጋዊያን በበኩላቸው የተመረቁትን ቤቶች የዘመናት ጥያቄያቸውን የሚፈቱና የተሻለ ህይወት ለመኖር የሚያስችሉ መሆኑን ተናግረዋል። በተመሳሳይ በአስተዳደሩ በ14 ሚሊዮን ብር የተገነባው ዳዊት ዘመናዊ የአረጋውያን መጦሪያ ማዕከልም ተመርቋል።
ኢኮኖሚ
የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦችን በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል
Oct 26, 2025 95
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦች በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ ገለጹ። በባህር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 11ኛው ከፍተኛ ደረጃ ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። "አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ፎረም፤ በአፍሪካ ሠላምና ደህንነት ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች፣ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በትኩረት መክሯል። አፍሪካ በኢኮኖሚ እንዴት ራሷን መቻል አለባት? ምን ዓይነት እርምጃዎች ያስፈልጋሉ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ በአፍሪካ ያሉ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ አካታች ሥርዓት መዘርጋት ለነገ የሚባሉ ጉዳዮች እንዳልሆኑ በፎረሙ በሰፊው ምክክር ተካሂዶበታል። የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ በፎረሙ መዝጊያ ላይ እንዳሉት፤ 11ኛው የጣና ከፍተኛ ደረጃ ፎረም ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል። የፎረሙ መሪ ሀሳብ አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት እንደ አህጉር ልንነጋገርበት የሚገባ ወቅቱን የጠበቀ ጽንሰ ሀሳብ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ዲጂታል የሚደረገው ሽግግር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በፍትሃዊነት እና ዘላቂነት ተደራሽ ማድረግ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። ዓለም በፍጥነት እየተለወጠች መሆኑን አስታውሰው፤አፍሪካም እየተለወጠ ላለው የዓለም ሥርዓት የሚመጥን እንቅስቃሴ ማድረግ አለባት፤ ለዚህ ደግሞ በጣና ፎረም የሚቀርቡ ምክረ ሀሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ከአፍሪካ አገራት በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። አፍሪካ ለማሳካት ያስቀመጠቻቸው ውጥኖች ያለ ወጣቶች ተሳትፎ እውን ሊሆን እንደማይችል አመልክተው፤በአፍሪካ በሁሉም መስክ የሚከናወኑ ተግባራት ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በፎረሙ ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ልዩ መልዕክተኞች ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የኮሪደር ልማቱ መዲናዋን ውብ ከማድረግ ባሻገር የንግድ እንቅስቃሴውን በእጀጉ አነቃቅቷል - ነዋሪዎች
Oct 26, 2025 81
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የኮሪደር ልማቱ መዲናዋን ውብ ከማድረግና የትራንስፖርት መጨናነቅን ከማስቀረቱ ባሻገር የንግድ እንቅስቃሴውን በእጅጉ ማነቃቃቱን ነዋሪዎች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተዋል። በሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመንት እና ፉሪ የተካሔደው የኮሪደር ልማት በከተማዋ በሁለተኛው ዙር ከተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች መካከል አንዱ ነው። የኮሪደር ልማቱ 16 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 589 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፤ በካዛንቺስና አካባቢው ከተካሔደው የኮሪደር ልማት ቀጥሎ በርዝመቱ ሁለተኛ ደረጃ የሚይዝ ነው። የኮሪደር ልማቱን አስመልክቶ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አቶ ሀብታሙ ግርማ እንደሚሉት፤ የኮሪደር ልማቱ በአካባቢ የነበረውን ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ቀይሮታል። በተለይም ልማቱ በተሰራበት መንገድ ላይ የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያስቀረ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድን ከአውራ ጎዳና የለየና የንግድ እንቅስቃሴውን የተሻለ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኮሪደር ልማቱ አካባቢውን ለዓይን ማራኪ ከማድረጉ ባሻገር የእግረኛና የተሽከርካሪ መጨናነቅን ማስቀረቱን የገለጹት ደግሞ አቶ ዳንኤል ኩማ ናቸው። መንግስት ለልማት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሰረተ ልማቶቹ እውን መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በመስራት ለውጥ እንደሚመጣ በተጨባጭ እንድናይ አድርጎናል ብለዋል። አቶ አለሙ አርጋው በበኩላቸው፤ የኮሪደር ልማቱ በሌሎች አገሮች እያየን የምናደንቃቸውን ውብ ከተሞች በራሳችን አገር እንድናይ አድርጓል ነው የሚሉት፡፡ በልማቱ የተሰሩት የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ መናፈሻዎችና ሌሎች የመዝናኛ ቦታዎች ከተማዋን በእጅጉ እንደቀየሯት ተናግረዋል። ወጣት እየሩስ ፋንታው በበኩሏ በኮሪደር ልማቱ ዘመናዊ መንገዶች መገንባታቸው በአካባቢው ያለው የትራንስፖርት ምልልስ የተሳለጠ እንዲሆን ማስቻሉን ጠቅሳለች። በአካባቢው የተካሔደው የኮሪደር ልማት የስራ እድል እንደፈጠረላት የተናገረችው ደግሞ ወጣት ሀገሪቱ ፈቃደ ናት።
በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን የተረጂነት አስተሳሰብን ማስቀረት የሚያስችል የልማት ስራ እየተከናወነ ነው
Oct 26, 2025 170
አሶሳ፤ጥቅምት 16/2018(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመሸፈን የተረጂነት አስተሳሰብን ማስቀረት የሚያስችል የልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስካለች አልቦሮ ገለጹ። የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ አቡራሞ እና ሆሞሻ ወረዳዎች የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እያለማ የሚገኘውን ሰብል ጎብኝተዋል። የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስካለች አልቦሮ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት መንግሥት ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የጀመረው ኢንሼቲቭ በክልሉ በስፋት እየተከናወነ ነው። የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ኢንሼቲቩን ወደ ተግባር በመቀየር የተለያዩ የሰብል ዓይነቶችን በማልማት የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተያዘውን ግብ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል። ክልሉ ለግብርና ልማት ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ራስን ከተረጂነት ማለቀቅ እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባም አፈጉባዔዋ አስገንዝበዋል። በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም እየተከናወነ የሚገኘው የግብርና ስራ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢንሼቲቩ ከተያዘለት ዓላማ በተጨማሪ የአካባቢውን የሥራ ባህል የሚቀይርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ መሆኑን ጠቅሰዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዘንድሮው ዓመት 1 ሺህ 756 ሄክታር ማሳ በበቆሎ፣ ማሽላ፣ አኩሪ አተር እና ሌሎች ሰብሎች እየለማ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሐመድ አብዱላዚዝ ናቸው። ከዚህ ውስጥም ኮሚሽኑ በራሱ አቅም በአቡራሞ እና ሆሞሻ ወረዳዎች ላይ 270 ሄክታር ማሳ እያለማ መሆኑን አብራርተዋል። በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን በተጀመረው እንቅስቃሴ የተለያዩ ወረዳዎች ወደ ስራ መግባታቸውንና ይህም ለኮሚሽኑ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ለገበያ መረጋጋት ሚናቸውን እየተወጡ ነው-ሸማቾችና ነጋዴዎች
Oct 26, 2025 68
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱት የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የተለያዩ የምርት ዓይነቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ለገበያ መረጋጋት ሚናቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ። መንግሥት በቅዳሜና እሁድ ገበያዎችና ተግባራዊ ባደረጋቸው የተለያዩ ኢኒሼቲቮች የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣የዋጋ ንረትን በመቆጣጠርና ገበያን በማረጋጋት እንዲሁም የኑሮ ጫናን በማቃለል የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል። የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ዋነኛ ዓላማም ሸማቾች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ማስቻል ሲሆን፤ ገበያዎቹ ምርቶቹን ከአርሶ አደሮች፣ ከፋብሪካዎች ወይም ከሸማቾች የኅብረት ሥራ ማህበራት በቀጥታ በመረከብ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ኢዜአ በመዲናዋ በሚገኙ የተለያዩ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ሸማቾችና ነጋዴዎች በገበያዎቹ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በእሁድ ገበያ ያነጋገርናቸው ወይዘሮ ሽታ ደመላሽ የሚፈልጉትን ምርት በበቂና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በአካባቢያቸው መከፈታቸው ለግብይት የሚያስፈልገውን ጊዜና የትራንስፖርት ወጪ እንደቆጠበላቸው ገልጸዋል። ሌላኛው ሸማች አባቡ አሰፌ በበኩላቸው፤ የገበያዎቹ በቅርብ ርቀት ተደራሽ መሆን ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የፈለጉትም ምርት እንዲያገኙ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ገበያዎቹን የበለጠ በማስፋፋት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ገልጸዋል። አቶ መለሰ ባዬ በበኩላቸው፥የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በእሁድ ገበያ ላይ በመሳተፍ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የሚያቀርቡ ነጋዴዎች በበኩላቸው፤ ከኅብረት ሥራ ማህበራት እና ከአቅራቢዎች በቂ ምርት እያመጡ ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እየሸጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ከነጋዴዎቹ መካከል ምትኩ ፋንታሁን እንደሚሉት፤ መንግሥት የንግድ ቦታዎችን በነጻ ከማመቻቸቱ ባሻገር ምርቶችን ከአቅራቢዎች በቀላሉ በማግኘት ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ አስችሏቸዋል። ይህም ምርቶችን በበቂ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ለማቅረብ ጥሩ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። ሌላኛዋ ነጋዴ ገነት ዋቅጅራ፤ ለሸማቾች በርካታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ መሆኑን ጠቅሳ ፤ ኅብረተሰቡ በመገበያያ ቦታዎቹ በመገኘት የሚፈልገውን ምርት እየገዛ መሆኑን ተናግራለች።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የዲጂታልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ ነው- ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Oct 25, 2025 193
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት በተሰጠው ትኩረት የዲጂታልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ4ኛው ዙር ሰመር ካምፕ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶችን አስመርቋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሠላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፣የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት በዲጂታል ዘመን ወቅቱን የዋጀ በክህሎት መር እውቀት የሠለጠነ ዜጋን ማፍራት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል። የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሳይበር ደህንነት እና ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቁ ወጣቶችን በተከታታይ የማሰልጠንና የማሰማራት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት በሰው ኃብት ልማት በተለይ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የሳይበር ጥቃትን በብቃት የሚከላከልና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ህልምን የሚያሳካ የዲጂታል አርበኛ የሆነ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ በዲጂታል ዘርፉ ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል እያደረገች ላለው ሽግግር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የበቃ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል። የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ዋና ዓላማ በዘርፉ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ክህሎት በማሳደግ እና በዘርፉ ለሀገር የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ወቅቱን የሚመጥን ብቁ፤ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሳይበር ታለንት ስልጠና አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር በመፍጠር እና በተቋሙ የሚሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እውቅና እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የፈጠራ ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዝ የሥራ ፈጣሪዎች አቅም ማጎልበቻ ማዕከል ከፍቶ ወደ ስራ ማስገባቱንም ገልጸዋል። በዚህም በሰመር ካምፕ የፈጠራ ስራ ያላቸው ታዳጊዎች በማዕከሉ ውስጥ የፈጠራ ስራቸውን ማስፋትና ወደ ገበያ የሚያቀርቡበትን ዕድል ከመፍጠር ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በሰመር ካምፑ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች በበኩላቸው በቆይታቸው የተለያዩ ክህሎቶችን ማግኘታቸውን ገልጸው በቀጣይ ሀገራቸውን በዲጂታል ዘርፎች ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል። ወጣት አሌክሳንደር ሳሙኤል የኢ-ለርኒንግ ስርዓት ማበልጸጉን በማንሳት፥ የጀመረው ሥራ የትምህርት ስርዓቱን በዲጂታል ለማሳለጥ ዓላማ ያለው ነው ብሏል። ሌላው ወጣት ኬና ቶልቻ በበኩሉ በቆይታው በኤሮስፔስ ዘርፍ ስልጠና መውሰዱን በመግለፅ፥ በድሮን ኦፕሬሽን ላይ እውቀት መቅሰሙን ጠቁሟል። ወጣት ባስሌል መስፍን በበኩሉ በሶፍትዌር ማበልፀግ ስልጠና እንደወሰደ ጠቅሶ፥ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን የህዝብ ትራንስፖርት አጠቃቀም የሚያሳልጥ መተግበሪያ መስራታቸውን ገልጿል።
የታዳጊዎችና ወጣቶችን የፈጠራና ክህሎት አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Oct 25, 2025 95
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):- በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ የሆነ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት የታዳጊዎችንና የወጣቶችን የፈጠራና የክህሎት አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ4ኛው ዙር ሰመር ካምፕ በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶችን አስመርቋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሠላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት በዲጂታል ዘመን ወቅቱን የዋጀ በክህሎት መር እውቀት የሠለጠነ ዜጋን ማፍራት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሳይበር ደህንነት እና ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቁ ወጣቶችን በተከታታይ የማሰልጠንና የማሰማራት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራ ለመስራት በሰው ኃብት ልማት በተለይ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች አቅም ለማጎልበት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል እያደረገች ላለው ሽግግር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የበቃ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ብለዋል። የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ዋና ዓላማ በዘርፉ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ክህሎት በማሳደግ እና በዘርፉ ለሀገር የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ወቅቱን የሚመጥን ብቁ፤ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የሳይበር ታለንት ስልጠና አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።
አጀንዳ 2063ን ለማሳካት የአህጉሪቱን ወጣቶች የፈጠራ አቅም ማጎልበት ይገባል - ምክትል ሊቀ-መንበር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ
Oct 22, 2025 312
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018(ኢዜአ):- የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት ቴክኖሎጂና ፈጠራን ከአጀንዳ 2063 ጋር ማቀናጀትና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የኢኖቬሽን ፌስቲቫል በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ፌስቲቫሉ "የአፍሪካ ህብረት ወጣቶችን የአህጉራዊ ኢኖቬሽን መሪ የማድረግ ተግባር" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሚካሄድ ሲሆን ኢኖቬተሮች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የግሉ ዘርፍ መሪዎች እና የወጣት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፌስቲቫሉ ለሀገር በቀል የኢኖቬሽን መፍትሄዎች እውቅና በመስጠት ስራዎችን የበለጠ ማላቅ ላይ ትኩረት የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ ፈጠራንና ቴክኖሎጂን ከአጀንዳ 2063 ጋር በማቀናጀት የበለፀገች አፍሪካን ለመገንባት መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡ አፍሪካን ለመለወጥና ለማሳደግ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ፈጠራን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የአህጉሪቱ የፈጠራ ችሎታ፣ የዲጂታል ለውጥ እና የሥራ ፈጠራ ዋና አንቀሳቃሽ ኃይሎች ወጣቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አህጉሪቱ በፈጠራ ዘርፍ የያዘችውን ግብ ማሳካት የሚችሉት ወጣቶች በመሆናቸው አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሴቶች፣ የጾታ እና ወጣቶች ዳይሬክተር ፕሩደንስ ንግዌንያ በበኩላቸው ወጣቶችና ሴቶች የአፍሪካን የፈጠራ ምህዳር መሠረት መጣል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ አፍሪካ በፈጠራ ዘርፍ ማሳካት የምትፈልገውን ለውጥ እውን ለማድረግ በወጣቶችና ሴቶች የፈጠራ አቅም ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ የፌስቲቫሉ ተሳታፊ ወጣት ትመር ብርሃኔ አፍሪካዊያን በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ዘርፍ ያለንን ዕውቀት በየጊዜው ማላቅ አለብን ስትል ተናግራለች፡፡ ወጣት አሜን ቢኒያም በበኩሏ የምንፈልጋትን አፍሪካ እውን ለማድረግ ፈጠራን እና ቴክኖሎጂን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ጠቅሳ ለዘርፉ የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር የተያዘው ግብ ስኬታማ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝባለች፡፡ የኢኖቬሽን ፌስቲቫሉ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት፣ አካታችና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ራዕይ አቀጣጣይ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
የማር ጥራት ፍተሻን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለማካሄድ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው
Oct 22, 2025 244
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ)፦የማር ምርትን የጥራት ፍተሻ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ለማካሄድ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ፍተሻውን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም ለማካሄድ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነት መርሃ ግብር ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ የማር ምርት አቅም ቢኖርም በሚፈለገው ልክ የውጭ ምንዛሬ እየተገኘበት አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ለዚህ ደግሞ የማር ጥራት ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፍተሻ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ድሪባ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የማር ምርት ጥራትን ለማስጠበቅ የጸረ ተባይ ቅሪት ፍተሻ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ አቅም ለማካሄድ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው። ለዚህም ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ለፍተሻ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ዝግጁ መደረጋቸውን አብራርተዋል። ፍተሻውን ለማከናወን ክህሎት ያለው ባለሙያ ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ ከውጭ በመጣ አሰልጣኝ ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም በማር ላይ የሚገኘውን የጸረ ተባይ ቅሪት ፍተሻ የሚደረገው ናሙና ወደ ውጭ ተልኮ መሆኑን አስታውሰው፤ አሁን ላይ ፍተሻውን ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑን ጠቁመው፤ ተወዳዳሪ ለመሆን መሰል የላብራቶሪ አቅም መገንባቱ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል። የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት ረገድም ፍተሻው በሀገር ውስጥ መካሄዱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምግብና መጠጥ ፍተሻ ላቦራቶሪ ሲኒየር አናሌቲካል ኬሚስት ብሩክ ስለሺ በበኩላቸው፤ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በሌሎች ምርቶች ላይም የጸረ ተባይ ቅሪትን መፈተሽ የሚያስችል አቅም ለመገንባት ያስችላል ብለዋል። በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰለሞን መንገሻ በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የላቦራቶሪ አቅም እንዲገነባ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለላቦራቶሪ የሚያስፈልጉ የተለያዩ መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን ገልጸው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች የሥራ ላይ ስልጠና እንዲሰጡ እየተደረገ ነው ብለዋል። ለማር ምርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ተደራሽ መደረጋቸውን የገለጹት አስተባባሪው፤ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸው ሀገራት ልምድ ተቀምሮ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
ስፖርት
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ
Oct 26, 2025 55
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤቨርተንን 3 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ሚኪ ቫን ደቬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፓፔ ሳር ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኤቨርተን በአዲሱ ስታዲየሙ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል። ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ17 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።
ኢትዮጵያ መድን ከወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ፒራሚድስ ጋር አቻ ወጥቷል
Oct 26, 2025 56
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ከግብጹ ፒራሚድስ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል። ማምሻውን ካይሮ በሚገኘው ጁን 30 ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊስተን ማዬሌ በ12ኛው ደቂቃ ፒራማድስን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል። ብሩክ ሙሉጌታ 83ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ግብ ኢትዮጵያ መድን አቻ ሆኗል። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ኢትዮጵያ መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ይቀላቀላል። ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው። የግብጹ ፒራሚድስ ክለብ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ባለቤት ነው።
በተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ደርቢ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን አሸነፈ
Oct 26, 2025 54
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ እና ጁድ ቤሊንግሃም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ፌርሚን ሎፔዝ ለባርሴሎና ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። ኪሊያን ምባፔ በ52ኛው ደቂቃ የፍጹም ቅጣት ምት ስቷል። የባርሴሎናው አማካይ ተጫዋች ፔድሪ በ100ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ነጥቡን ወደ 27 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ባርሴሎና በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
Oct 26, 2025 73
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን 1 ለ0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል። በኤሜሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ኤቤሬቺ ኤዜ ከእረፍት በፊት በ39 ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል። በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከፓላስ አርሰናልን የተቀላቀለው ኤዜ የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ጎሉንም በቀድሞ ክለቡ ላይ ማስቆጠር ችሏል። አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በ22 ነጥብ መምራት የቻለ ሲሆን ከተከታዮቹ ጋር ያለውንም የነጥብ ልዩነት ማስፋት አስችሎታል። በሌሎች የዛሬ መርሃ ግብር ጨዋታዎች ወደ ቪላ ፓርክ ያቀናው ማንችስተር ሲቲ በተመሳሳይ በአስቶን ቪላ 1ለ0 ተሸንፏል። በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቮልቭስ በበርንሌይ 3ለ2 ፤በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው ቦርንማዝ ደግሞ ኖቲንግሃምን 2ለ0 ያሸነፉበት ጨዋታ የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች ናቸው።
አካባቢ ጥበቃ
እምቦጭን በዘላቂነት ለመከላከል የህብረተሰብ ተኮር ሥራ ውጤት እያስገኘ ነው
Oct 26, 2025 101
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-እምቦጭን በዘላቂነት ለመከላከል የህብረተሰብ ተኮር ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ ሞቱማ መቃሳ ገለጹ፡፡ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ ሞቱማ መቃሳ ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውን ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ለማከናወን የውኃ ሀብቷን መጠበቅ ወሳኝ ነው። ስለሆነም መንግስት በአገሪቷ የልማት እቅዶች ውስጥ የውኃ አስተዳደርና ጥበቃን ቅድሚያ ሰጥቶ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ለአብነትም በአገሪቷ ውስጥ ምን ያህል የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ ሀብት እንዳለ በትክክል የመለየትና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ይህን ሀብት ለየትኞቹ የልማት ዘርፎች በምን ያህል መጠንና ጥራት ለማዋል እንደሚቻል የውኃ አቅም ልየታ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የውኃ ሀብት አስተዳደርና ጥበቃ ስራ ከፍ ብሎ እንዲመራ ሚኒስቴሩ መዋቅራዊ ማሻሻያ ማድረጉንም አመልክተዋል። ከፍተኛ ትኩረት ከሚሹ የውኃ አካላት ጥበቃ ጉዳዮች መካከል አንዱ በእምቦጭ አረም ምክንያት የሚከሰተውን ችግር ማቃላል መሆኑን አመልክተዋል። እምቦጭ በፍጥነት የሚስፋፋና በየጊዜው ተመልሶ የሚመጣ መሆኑን ያወሱት አቶ ሞቱማ፤ በዘላቂነት ለማቃለል በየጊዜው አስቸጋሪ ፈተና መሆኑን አንስተዋል። ይህንን ችግር መፍትሄ ለመስጠት ሚኒስቴሩ በትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝም አብራርተዋል። ይህን ዘላቂ ችግር ለማቃለል ህብረተሰብን ያማከለ አሰራር ተቀይሶ በመተግበር ላይ እንደሚገኝና ውጤትም እየተገኘበት እንደሆነም አስታውቀዋል። በጣና ሐይቅና በሌሎች የውኃ አካላት ላይ የእምቦጭ አረምን ችግር ለመፍታት ከተጀመሩ ሥራዎች በተጨማሪ ህብረተሰብ ተኮር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ሞቱማ ተናግረዋል። የውኃ ሀብት ጥበቃና አስተዳደር የሀገር ጉዳይ በመሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋን ማደግና የፓርኮች ልማት አዕዋፍትንና የዱር እንስሳትን ከስደት ታድጓል
Oct 26, 2025 75
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተከናወነው ሥራ የደን ሽፋን ማደግና የፓርኮች ልማት አዕዋፍትንና የዱር እንስሳትን ከስደት እየታደገ መምጣቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ገለጹ። የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን 16ኛውን ዓለም አቀፍ የስደተኛ አዕዋፍ ቀንን "ለአዕዋፍት የተመቸ ማህበረሰብ እና ከተማ እንፍጠር" በሚል መሪ ሃሳብ በአቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ አክብሯል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ቀኑን ማክበር ያስፈለገው ለህብረተሰቡ ስለ እንስሳት ሀብት ጥበቃ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው። አዕዋፋትና የዱር እንስሳት በመኖሪያ አካባቢያቸው በሚደርስ መራቆት ምክንያት ለስደት እንደሚዳረጉ ተናግረው፤ በዚህም ኢትዮጵያ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ሳታገኝ መቆየቷን ገልጸዋል። የአዕዋፍት እና የዱር እንስሳት ስደት ችግርን ከስር መሰረቱ ለመፍታት የጥበቃ ቦታዎችን ማልማትና ማስፋፋት እንደሚገባ ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአገር ደረጃ የደን ሽፋን ማደጉን ያወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህም ለዱር እንስሳት ምግብና መጠለያ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው አብራርተዋል። የአካባቢ ጥበቃ እያደገ በመምጣቱ ሐይቆችም ወደ ድሮ ይዞታቸው መመለሳቸውን አመላክተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ፓርኮችን የመጠበቅ እና አዳዲስ የጥበቃ ስፍራዎችን የማልማት ተግባራት በስፋት ማከናወናቸውን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የአዕዋፋት እና የዱር እንስሳት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አመልክተው፤ የፓርኮችን ይዞታ በማሻሻልና ያሉትን በመጠበቅ ተሰደው የቆዩ የዱር እንስሳት ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማስቻሉንም አስታውቀዋል። የዱር እንስሳት ለአደጋ ተጋላጭነት በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን አንስተዋል። በመርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር፣ ባለድርሻ አካላት፣ አርቲስቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና የባለስልጣኑ ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ውብ ሐረርን ለትውልድ ለማሻገር …
Oct 26, 2025 100
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡- ሰሞኑን በሳንፍራንሲስኮ በተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ነፃ ለማድረግ የተጀመረው ኢንሼቲቭ እያስገኘ ላለው ውጤት ዕውቅና ተሰጥቷል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሐረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ለአሁኑ ነዋሪ ብሎም ለመጪው ትውልድ ጽዱ፣ ውብ እና ምቹ ሐረርን ለማንበር ያለሙ ስምምነቶች ተፈርመው እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል። ከእነዚህ ስምምነቶች አንዱ ‘ኪዩቢክ ፕላስቲክ ፕራይቬት’ የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት እና የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2024 የተፈራረሙት አንዱ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ የውል ስምምነት መሠረትም፤ ቤት ለቤት እና ከድርጅቶች የሚሰበሰቡ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ደረቅ ቆሻሻዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማዋ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ እስከ 48 በመቶ ያህሉ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ በንፋስ ምክንያት እየተበተነ አካባቢን እንደሚበክል አስገንዝበው፤ ይህን ከማስቀረት አልፎ ከየቤቱና ድርጅቶች የሚወጣው የፕላስቲክ ቆሻሻ ተለይቶ ‘ፕሮሰስ’ ተደርጎ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ከፕላስቲኩ በሚሠራ ጡብ የቤት ግንባታ እንደሚከናወን ተናግረዋል። ለአብነትም ከ500 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ፕላስቲክና ፕላስቲክ ነክ ቆሻሻ ወደ ፕሮሰስ በማስገባት፤ በሐረር ከተማ ጁገል አካባቢ ቤተ መጻሕፍት መገንባቱን አረጋግጠዋል። ከዚህ በመነሳት ወጪ ቆጣቢ ስለሆነ ለሌሎች ቤቶች ግንባታ እንደሚውልም በጥናት መረጋገጡን ጠቅሰዋል። የሚሰበሰበው የፕላስቲክ ቆሻሻ በበዛ ቁጥር እንደገና የሚሰጠው ጥቅምም በዚያው ልክ ያድጋል ብለዋል። ሕብረተሰቡን የማስተማር ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው፤ በተለይ ሴቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በሚሰበስቡት ፕላስቲክ ልክ ገንዘብ እየተከፈላቸውም መሆኑን ነው የገለጹት። እስካሁንም ከ600 በላይ ሴቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል። ቆሻሻን በአግባቡ በመሰብሰብ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል እየተደረገ ባለው ጥረት በሐረር ከተማ በየአካባቢው ይታይ የነበረው የፕላስቲክነክ ደረቅ ቆሻሻ መቀነሱን አረጋግጠዋል። አሁን እየተገኘ ያለው ውጤት በቀጣይ ብዙ ለመሥራት ዐቅም እንደሚሆንም አመላክተዋል። ለዚህ ጥሩ ጅማሮም ሐረርን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ነጻ ለማድረግና ፕላስቲክ ቆሻሻን እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል እየተደረገ ላለው ጥረት በሳንፍራሲስኮ የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ዕውቅና ሰጥቶናል ብለዋል። ከዕውቅናው በፊት የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በሐረር ተገኝተው ግምገማ ማድረጋቸውንም አውስተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህም በአንድ ወቅት መጥተው መጎብኘታቸውን እና ወደ ሌሎች ከተሞችም መስፋት ያለበት ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን መግለጻቸውን ተናግረዋል። ሕብረተሰቡም ፕላስቲክን ከሌሎች ቆሻሻዎች ጋር ቀላቅሎ ከመጣል ተቆጥቦ በአግባቡ እንዲወገድ የማድረግ ልምዱ እየዳበረ መሆኑን አንስተው፤ለነዋሪ ምቹና ጽዱ ሐረርን ለማንበር በሚደረገው ጥረት የሕብረተሰቡ ሚና እንዲጠናከር ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የባዮ ኢነርጂ ልማት እና የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል
Oct 24, 2025 163
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የባዮ ኢነርጂ ልማት እና የታዳሽ ኃይል ልማትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን አስታወቀ። በኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ የባዮ ኢነርጂ ልማት ለማምረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተደርጓል። ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ጌታቸው እና መቀመጫውን እንግሊዝ አገር ያደረገው ሰንበርድ ባዮ-ኢነርጂ አፍሪካ ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ቤኔት ተፈራርመውታል። ሰንበርድ ባዮ-ኢነርጂ አፍሪካ በአህጉሪቱ ግዙፍ የባዮ-ፊውል አምራች ኩባንያ ነው። ኩባንያው ግብርናን መሰረት ያደረገ የባዮ ኢነርጂ ልማት፤ የአቪዬሽን ነዳጅ፣ ለትራንስፖርት የሚሆን ታዳሽ ኃይል፣ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ባዮ ፊውል ያመርታል ተብሏል። የተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል አማራጭ ላይ የጀመረችውን ስራ የበለጠ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ጌታቸው በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዘላቂ የኢነርጂ ልማት የሚያጠናክር ነው። ስምምነቱ ከውጪ የሚገባውን ነዳጅ ለመቀነስና የኢነርጂ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ፕሮጀክቱ የግብርና ልማትን ለማገዝ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን የኢነርጂ ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን እገዛ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። የሰንበርድ ባዮ-ኢነርጂ አፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ቤኔት በበኩላቸው፤ ኩባንያቸው በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ውጤታማ ተግባር እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ድርጅቱ በዛምቢያና ሴራሊዮን በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ላይ መሰማራቱን አስታውቀው ያለውን ልምድ በመጠቀም በኢትዮጵያ ውጤታማ ስራ እንደሚያከናውን አረጋግጠዋል። የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ አቶ ከድልማግሥት ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ስምምቱ በሀገሪቱ ከብክለት የጸዳ ትራንስፖርት ለመተግበር እየተደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስቴሩ ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ለአህጉሪቷ ለዘላቂና አስተማማኝ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው
Oct 24, 2025 176
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ):-ለአህጉሪቷ አስተማማኝና ዘላቂ የምግብ ሥርዓት ግንባታ አባል ሀገራት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ የአባል አገራት በግብርና፣ በእንስሳት፣ በዓሳ ሀብት፣ በገጠር ልማት፣ በውሃ፣ በአካባቢ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በስብሰባው የሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም የማላቦ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2014 እስከ 2025) መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የሚተገበረው የካምፓላ አጀንዳ (እ.ኤ.አ 2026 እስከ 2035) ጸድቋል፡፡ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አባል ሀገራት የራሳቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም የግብርና ግብዓቶችንና ምርጥ ዘርን መጠበቀ እንዲሁም ብዝሃ ህይወትን ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውሃ ኃብትን ከማሳደግ አኳያም ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ - ኒፓድ የግብርና፣ የምግብ ዋስትና እና የአካባቢ ዘላቂነት ዳይሬክተር ኤስቴሪን ፎታቦንግ የካምፓላ አጀንዳ (2026–2035) በአፍሪካ የግብርና-ምግብ ሥርዓቶች ላይ የለውጥ ምዕራፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ ከአጀንዳው ግቦች መካከልም ዘላቂ የምግብ ምርትን፣ አግሮ-ኢንዱስትሪያላይዜሽንን እና ንግድን ማጠናከር፣ ለግብርና-ምግብ ሥርዓት ለውጥ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስን ማሳደግ ብሎም የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚሉ እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ልማት ኤጀንሲ የካምፓላ አጀንዳ ስትራቴጂ እንዲሳከ ምቹ ሁኔታዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡ የዩጋንዳ ግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እና የአምስተኛው የአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ እና የአካባቢ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ተወካይ ፍሬድ ብዊኖ ክያኩላጋ የካምፓላ አጀንዳ የእንስሳት ሃብትን ማሳደግ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡ በዚህም ለእንስሳትና ለዓሳ እርባታ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የእንስሳት መኖ ማሳደግ፣ ለእንስሳት ጤና እንዲሁም የዘረመል መሻሻልም ከትኩረት መስኮች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ የካምፓላ አጀንዳ የአፍሪካ ግብርና ልማት መርሃ ግብር ታላላቅ ግቦች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ
Oct 24, 2025 135
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 14/2018(ኢዜአ)፦11ኛው የጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጥቅምት 14 እስከ 16/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው 11ኛው ጣና ፎረም በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት፣የዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የጣና ፎረም "አፍሪካ በተለዋዋጩ የዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች በአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ለሶስት ቀናት የሚመክር ይሆናል። የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ተሳታፊ ሙያተኞች በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮችና በአፍሪካዊ መፍትሔዎች ልምድና ዕውቀታቸውን የሚያካፍሉበት ዝግጅትም ተጠባቂ የፎረሙ የመርሃ ግብር አካል ነው። በፎረሙ ላይ በመሪዎችና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ልዩ መልዕክተኞች ምክክር እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በቀጣናው መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል የተጀመሩ የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢጋድ
Oct 20, 2025 333
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) በቀጣናው የሚታየውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር የጀመራቸውን የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ። የኢጋድ ሶስተኛው የሰራተኛ፣ ስራ እና የሰራተኛ ፍልሰት የሚኒስትሮች ስብሰባ ዛሬ በኬንያ ናይሮቢ ተጀምሯል። “በኢጋድ ቀጣና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሰራተኛ ፍልሰት እና የሰዎች ዝውውር ህጋዊ ማዕቀፍን ማሻሻል” የስብሰባው መሪ ቃል ነው። በስብሰባው ላይ የኢጋድ አባል ሀገራት የሰራተኛ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎች፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(አይኤልኦ)፣ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት(አይኦኤም)፣ የአውሮፓ ህብረትና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል። በኢጋድ ቀጣና የሰራተኛ፣ ስራ እና የሰራተኛ ፍልሰት ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በቀይ ባህር መስመር ያለውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ይካሄዳል። በስብሰባው ላይ ከኢጋድ ቀጣና ውጪ የሚገኙ ዜጎች አባል ሀገራትን በነጠላ የመግቢያ ቪዛ መጎብኘት የሚያስችላቸውን የቪዛ ኢኒሼቲቭ ይፋ ይደረጋል። ኢኒሼቲቩ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርና ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ማሳለጥ እንዲሁም ቱሪዝምን የማሳደግ ፋይዳ እንዳለው ኢዜአ ከኢጋድ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በአውሮፓ ህብረት የፋይናንስ ድጋፍ የሚተገበረው ነጻ የሰዎችና የቁም እንስሳት እንቅስቃሴ የህግ ማዕቀፍ ሁለተኛ ምዕራፍ ይፋ ይሆናል። ማዕቀፉ ህጋዊ የፍልሰት መንገዶች ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ትስስርን የማሳካት ግብ ያለው መሆኑንም አመልክቷል። ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰንሰለትን መበጣጠስ፣ በፍልሰት በሌላ ሀገር የሚገኙ ዜጎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ላይ ምክክር ያደርጋሉ። በውይይቱ ማብቂያ ሀገራት የጋራ መግለጫ እንደሚያወጡ የሚጠበቅ ሲሆን ደህንነቱ የተጠበቀ መደበኛ ፍልሰት፣ ጠንካራ የሰራተኛ አስተዳደር ስርዓት መፍጠርና ለሰዎች ዝውውር የተቀናጀ ቀጣናዊ ምላሽ መስጠት ላይ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እንደሚገልጹ ተጠቁሟል። ኢጋድ በቀጣናው የሚታየውን መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር የጀመራቸውን የጋራ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክቷል። ዜጎች ህጋዊ አማራጮችን እንዲከተሉና የኢኮኖሚ ፈተናን ጨምሮ ለሌሎች ገፊ ምክንያቶች ዘላቂ መፍትሄ መስጠት በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልጿል። ስብሰባው ጥቅምት 10 እና 11 በባለሙያዎች፣ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚኒስትሮች ደረጃ ይካሄዳል።
የአፍሪካ ሀገራት ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በቁርጠኝነት ሊተገብሩ ይገባል- የአፍሪካ ህብረት
Oct 19, 2025 337
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 8/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ሀገራት ሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) አፈጻጸም ውጤታማነት ለማሳደግ በትኩረት እንዲሰሩ የአፍሪካ ህብረት አሳሰበ። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ መደበኛ ስብስባ ከጥቅምት 11 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። በስብሰባው ላይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎች እና የልማት አጋሮች ይሳተፋሉ። የአፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቮች አፈጻጸም መገምገም እና ዘርፉ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከር የስብሰባው አላማ ነው። እ.አ.አ በ2023 በአዲስ አበባ የተካሄደውን አምስተኛው የልዩ ኮሚቴ ስብሰባ ውጤቶች ግምገማ ይደረጋል። የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) የማላቦ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025) ስኬቶች እና የካዳፕ የካምፓላ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035) አፈጻጸም ላይ ውይይት ይካሄዳል። የስርዓተ ምግብን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት ስርዓት መዘርጋት፣ የበካይ ጋዞችን ልህቀት መቀነስ እና ዘላቂ የውሃና ተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደርን ማጠናከር ሌሎች የምክክር አጀንዳዎች ናቸው። በአፍሪካ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ዘላቂ እድገትን ማምጣት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሀሳቦች ይቀርባሉ። ውይይቱ እ.አ.አ በ2026 በአዲስ አበባ የሚካሄዱትን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባና የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንደሚያዘጋጅ ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ 2063 ለማሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ዘርፎች መሆናቸውን አመልክቷል። ህብረቱ የግብርና እና የገጠር ልማት የበለጠ ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል። የህብረቱ አባል ሀገራት የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርቧል። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ጥቅምት 11 እና 12 እንዲሁም ጥቅምት 14 በሚኒስትሮች ደረጃ እንደሚከናውን ኢዜአ ከህብረቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የክህሎቶች ልማት፤ የአፍሪካ ቀጣይ የእድገት ምዕራፍ እና ግንባር
Oct 15, 2025 619
አፍሪካ የተስፋ እና የበረከት አህጉር ብቻ አይደለችም የዓለም ቀጣይ የእድገት ዳርቻ እና ማዕከል ጭምር እንጂ። ህዝቧ እ.አ.አ በ2024 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተሻግሯል፤ እ.አ.አ በ2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከአንድ ትውልድ በኋላ ባለንባት ምድር ላይ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ ከአፍሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል። በጣም አስገራሚው ነገር ከ60 በመቶ በላይ አፍሪካውያን እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆን ይህም አፍሪካን ወጣቷ አህጉር አድርጓታል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ወጣት ትልቅ የስነ ህዝብ ትሩፋት ነው። ይህን አቅም ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካን የዓለም ክህሎት መፍለቂያ፣ የፈጠራ እና ኢኖቬሽን ማዕከል ማድረግ ይቻላል። ይሁንና የስነ ህዝብ ትሩፋት ብቻውን ልማት እንዲረጋገጥ አያስችልም። እውነተኛው ፈተና ያለው ይህን የተትረፈረፈ የሰው ሀብት በክህሎት የዳበረ፣ ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ራሱን ብቁ ያደረገ እና መፍጠር ወደ ሚችል የስራ ኃይል መቀየር ላይ ነው። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የሰው ኃይል “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር” የሚያስችል ዋንኛ ምሰሶ እንደሆነ ያስቀምጣል። ይህ አህጉራዊ ማዕቀፍ በእውቀት እና ሁሉን አቀፍ እድገት አማካኝነት የበለጸገች፣ የተሳሰረች እና ራሷን የቻለች አህጉርን የመፍጠር ራዕይን አንግቧል። አፍሪካ የሰው ሀብት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ሀብቶች ባለጸጋም ናት። አፍሪካ የዓለማችን 30 በመቶ የማዕድን ሀብት የሚገኝባት አህጉር ናት። ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ፕላቲኒየም እና ሌሎች ውድ ማዕድናትን በስፋት ይገኙበታል። ማዕድናቱ አሁን ዓለም ላለችበት አረንጓዴ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሚባሉ ናቸው። የዓለማችን 60 በመቶ ያልታረሰ መሬት ያለው በዚችሁ አህጉር ነው። ይህ እርሻ የማያውቀው መሬት የዓለምን የምግብ ስርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የመቀየር አቅም አለው። ከ10 ቴራ ዋት በላይ የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት አፍሪካ ከአህጉር አልፋ የኢንዱስትሪ እና ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በኃይል የማመንበሽበሽ አቅም አለው። የኢኮኖሚ ማዕበሉም ወደ አፍሪካ ያደላ ይመስላል። እ.አ.አ 2021 ገቢራዊ መሆን የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና 55 ሀገራትን የሚያስተሳስር እና 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ተጠቃሚን በአንድ ማዕቀፍ ስር የሚያሳባስብ ነው። በአህጉር ደረጃ ዓመታዊ ጥቅል ምርቱ (ጂዲፒ) 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል። አህጉራዊ የንግድ ማዕቀፉ በሙሉ አቅሙ ሲተገበር የአፍሪካ ሀገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ መጠን 50 በመቶ እንደሚጨምረው የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትን የሚያፋጥንና አህጉሪቷ ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ ልካ መልሳ ያለቀላቸውን ምርቶች በከፍተኛ ወጪ ከመግዛት ተላቃ ጥሬ ምርቶቿን በከፍተኛ ጥራት ወደ ማምረት ያሸጋግራታል። ይህ ትልቅ የኢኮኖሚ ትስስር እድል አፍሪካውያን በጋራ እንዲለሙ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያሳድጉ እና የእውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ እንዲሁም ጠንካራ እና የማይበገር ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እነዚህ ሁላ ተስፋ ሰጪ አቅሞች የሚቃረን አንድ የማይካድ ሐቅ አፍሪካ ውስጥ አለ ይህ እውነት የአፍሪካን የእድገት አቅም በሚፈለገው መልኩ የሚመግብ የክህሎቶች እና የስራ ክፍተት ነው። በየዓመቱ በአፍሪካ ከ10 እስከ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች ወደ ስራ ይገባሉ። ይሁንና በአህጉሪቷ በዓመቱ የሚፈጠረው መደበኛ ስራ 3 ሚሊዮን ብቻ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ የቅርብ ጊዜ ሪፖርት ከሆነ ከአፍሪካ ወጣቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ገደማው ስራ አጥ (Unemployment) ወይም ከአቅም በታች ሰራተኝነት (Underemployment) ውስጥ ነው። ይህ ስራ አለማግኘት ያለው በአፍሪካ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢነርጂ፣ ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን እና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚገኙ ኩባንያዎች ክህሎት ያለው ሰው አጠረን እያሉበት ባሉበት ወቅት መሆኑ ትልቅ ጥያቄን ያስነሳል። በትምህርት ስርዓቱ እና በገበያው ፍላጎት መካከል እንዴት እንደዚህ አይነት አለመጣጣም ሊመጣ ቻለ? የሚል። በትምህርት እና በኢንዱስትሪው መካከል ባለው ያለመተሳሰር ችግር ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ 130 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ምርታማነት (productivity) ታጣላች። እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ፈተናው የአቅም ሳይሆን ትምህርት እና ስራን፣ ፖሊሲ እና ተግባርን እና ስልጠናን ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያስተሳሰር መስመር አለመዘርጋቱ ነው። በአፍሪካ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት እየሰሩ ያሉት ከኢንዱስትሪው ርቀው ነው ማለት ይቻላል ይህም ተመራቂዎች የስራ ገበያው የሚፈልገውን ክህሎት እና አቅም እንዳይታጠቁ አድርጓል። ሌላኛው ፈተና በአፍሪካ የተንሰራፋው ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ ነው። አንዳንድ ጥናቶች የአፍሪካን ኢ-መደበኛ የኢኮኖሚ ድርሻ እስከ 85 በመቶ ያደርሱታል። ይህም ዜጎች ክህሎታቸውን እንዳያሳድጉ እና የብቃት ማረጋገጫን እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል። የአፍሪካን ክህሎት ምህዳር በመቀየር የኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የስራ እድል ፈጠራን ማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ ላይ የጋራ ትብብርን ማጠናከር አበይት ትኩረቱ ያደረገ ሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። “አፍሪካውያንን የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማት የሚያፋጥኑበትን ክህሎቶች ማስታጠቅ” የሳምንቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሁነቱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው። በሁነቱ መክፈቻ ላይ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የአባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የልማት ተቋማት አመራሮች፣ መምህራን፣ ኢኖቬተሮች፣ የወጣት ተወካዮች እና የልማት አጋሮች ተሳትፈውበታል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክህሎቶች ለሀገራዊ ግቦችና ለአህጉራዊ የ2063 የልማት አጀንዳዎች መሳካት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ናቸው። ኢትዮጵያ ለክህሎት ልማት በሰጠችው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው ብለዋል። ክህሎት መር የፖሊሲ እርምጃችን ወጣቶች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ የስራ ፈጣሪነት ባህልን በንቃት እያስተዋወቀ መሆኑን ተናግረዋል። ተመራቂዎች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እና እድገት እንዲያመጡ የሚያስፈልጋቸውን ስልጠና፣ ምክር እና የገንዘብ ድጋፍ እያመቻቸ መሆኑን አመላክተዋል። በስልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ትብብር የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው የህዝባችንን አቅም ወደ ውጤታማ፣ አሳታፊ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ የሥራ ኃይል መለወጥ አለብን ብለዋል። ክህሎት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የክህሎት ልማት ለአሳታፊ ዕድገትና ለተገቢ የሥራ ዕድሎች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዕቅድ አካል መሆኑን ጠቁመዋል። አባል ሀገራት ሀገራዊ ለውጦችን ከአህጉራዊ ፍላጎቶች ጋር ለማጣጣም በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የተሻለ፣ ፈጣን እና ይበልጥ አሳታፊ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለውን የለውጥ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል። የፖሊሲ ወጥነትን እና ቀጠናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል። የአፍሪካ ክህሎት ክፍተትን መሙላት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ለክህሎት ልማት መጠቀም እና በአጀንዳ 2063 አማካኝነት ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ ላይ ውይይት ይደረጋል። በሳምንቱ የሚኒስትሮች እና የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረኮች፣ የክህሎት አውደ ርዕዮች እና የገበያ ትስስር ሁነቶች እንዲሁም የወጣቶች እና የስራ ፈጣሪዎች ፎረም እንደሚካሄድ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ፎረሙ የአፍሪካ ኢኖቬተሮች የስራ ውጤቶች ይቀርቡበታል። የክህሎቶች ሳምንት ተሳታፊዎቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና በኢኖሼሽን ማዕከላት ውስጥ ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው የሚገኙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎች ይጎበኛሉ። ሳምንቱ እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የአፍሪካ ክህሎት ልማት አስመልክቶ የጋራ አቋም መገለጫ እና የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ለአህጉሪቷ የኢንዱስትሪ እና ክህሎት አጀንዳ ተጨባጭ አሻራ የሚያሳርፍ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል። የመጀመሪያው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት እ.አ.አ ኦክቶበር 2024 በጋና አክራ መካሄዱ የሚታወስ ነው። የአፍሪካ ክህሎቶች ፈተናዎች ክፍተቶች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ እንዲሁም ምህዳሩን ለመቀየር አህጉሪቷ በዘርፉ አብዮት ያስፈልጋታል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህን የስነ ህዝብ ትሩፋት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ክህሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል መቀየር ይገባል። ይህን ለማድረግ የተቀናጀ እና አህጉር አቀፍ ጥረት ያስፈልጋል። የሁለተኛው የአፍሪካ ክህሎቶች ሳምንት ስኬት የሚለካው በንግግሮች እና በጋራ መግለጫዎች ሳይሆን ራዕዮቹን በአፍሪካ ትምህርት ተቋማት፣ ስልጠና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎች በተጨባጭ በመቀየር እና ውጤት በማምጣት ነው። በዚህ ረገድም መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአፍሪካን የክህሎት ልማት መጻኢ ጊዜ በውድድር፣ በፈጠራ እና አሳታፊነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊገነቡ ይገባል። አፍሪካ ወጣቶቿ በክህሎት እና በእውቀት ከታጠቁ አፍሪካ የተለመቻቸውን ግዙፍ እቅዶች እና ትላልቅ ውጥኖች ባጠረ ጊዜ እንዲሳኩ ያስችላል።
ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ በሀገሩ ህልሙን እውን ያደረገው ወጣት...
Oct 9, 2025 607
ሐረር ፤መስከረም 29/2018 (ኢዜአ)፦በሐረር ከተማ ተወልዶ ያደገው ነስረዲን አህመድ፤ በውጭ ሀገር ሰርቶ መለወጥን በማሰብ ከአመታት በፊት ወደ አረብ ሀገር ለመሄድ እንቅስቃሴ ጀመረ። የመጓዝ እቅዱም ተሳካለትና በዱባይ ለስምንት ዓመታት በስራ ላይ ማሳለፉን ያስታውሳል፤ በበረሃው ምድር ሌት ተቀን በስራ እየደከመ ህይወቱን ሊለውጥለት የሚችል ገንዘብ ለመያዝ ቢጥርም ባሰበው ልክ ሊሳካለት አልቻለም። በመሆኑም ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ ሰርቶ የመለወጥ ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይውል ሳያድር ወደ ስራ ገባ። ከበረሃው ንዳድ ወጥቶ በሀገሩ ሰርቶና አልምቶ መለወጥን የሰነቀው ነስረዲን በሀረር የንብ ማነብ ስራን ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንደሆነው ያስታውሳል። በምንሰራበት የስራ መስክ ሁሉ በትጋት ሌት ከቀን መስራት ከቻልን የማናሳካው ነገር አይኖርም የሚለው ወጣቱ አሁን በሀገሩና በወንዙ በስኬት መንገድ ላይ መሆኑን ይናገራል። የነስረዲን የንብ ማነብ ስራ የተጀመረው በጥቂት ቀፎዎች የነበረ ቢሆንም በስድስት ወራት ውስጥ ግን 50 ቀፎዎች ማድረስ መቻሉን ያስታውሳል። በሀገሬ ህልሜ እውን እየሆነ ነው የሚለው ወጣቱ የንብ ማነብ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ላይ የንብ ቀፎዎቹን 300 ሲያደርስ ለ30 የአካባቢው ወጣቶችም የስራ እድል ፈጥሯል። በአረብ ሀገር የቆየባቸውን ዓመታት በቁጭት የሚያስታውሰው ነስረዲን መልፋትና መድከም ከተቻለ በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል እኔ ጥሩ ማሳያ ነኝ ይላል። ከአረብ ሀገር የአመታት እንግልት በኋላ ወደ ሀገሬ ተመልሼ የስኬት መንገድን ጀምሬያለሁ በቀጣይም ጠንክሬ እሰራለሁ ብሏል። በቀጣይ ከንብ ማነብም ባለፈ የማር ማቀነባበርያ አነስተኛ ኢንዱስትሪ የማቋቋም ትልም እንዳለው ተናግሮ ለዚህም እንደሚተጋ አረጋግጧል። በዚሁ የልማት ፕሮጀክት ላይ የስራ እድል የተፈጠረለት ወጣት ሸዊብ መሀመድ፤ ከዚህ ቀደም ያለምንም ስራ ተቀምጦ መሽቶ ይነጋ እንደነበር አስታውሶ አሁን እያገኘ ባለው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየረዳ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት በድሪ ሙሳም፤ በነስረዲን ጥረት እርሱን ጨምሮ ብዙ ወጣቶች ስራ የተፈጠረላቸው በመሆኑ ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆኑን አንስቶ በቀጣይ እርሱም የራሱን ተመሳሳይ ስራ ለመጀመር ማቀዱን ገልጿል። በሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የንብ እርባታ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢብሳ ዩስፍ፤ የነስረዲን ጥረትና የአጭር ጊዜ ስኬት ለሌሎች ወጣቶችም ጥሩ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ የማር ምርታማነትን ለማጎልበት በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ የንብ መንደር በመመስረት ዘርፉን የማጎልበት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የአፍሪካ መምህራን፤ የአህጉሪቷ መጻኢ ጊዜ ቀራጺዎች
Oct 3, 2025 813
አፍሪካ በወጣቶች የታደለች ሀገር ናት። ከአህጉሪቷ ህዝብ መካከል ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ25 ዓመት በታች መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜን የሚወስነውን ወጣት ማን ያስተምረዋል? የሚለው ጥያቄ ቁልፍ ነው። ይህ ጥያቄ ከመማሪያ ክፍሎች እና መጻሕፍት ባለፈ የአፍሪካ ልማት አበይት አጀንዳ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። በዓለም ደረጃ ትልቅ የእድገት እና የልማት ሞተር የሆነውን ወጣት በብዛት የያዘችው አፍሪካ ትውልዱን የሚቀርጽ መምህራን ውጪ ህልሟን ማሳካት የሚታሰብ አይሆንም። የአፍሪካ ህብረት በአህጉር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እ.አ.አ በ2030 በትንሹ 15 ሚሊዮን አዲስ መምህራን እንደሚያስፈልጉ አስታውቋል። ይህን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እና ጠንካራ ሪፎርሞችን ማድረግ ይጠይቃል። አፍሪካ የትምህርት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል፣ የመምህራንን ቁጥር ለመጨመር እና በትምህርት ዘርፍ የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት 90 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል ሲል ህብረቱ ገልጿል። ጉዳዩ ከትምህርት ባለፈ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ያለው ነው። መምህራን የእያንዳንዱ ክህሎት፣ ስራ እና ኢኖቬሽን የሀሳብ መሐንዲስ ናቸው። የአፍሪካ መጻኢ ጊዜ የመወሰን አቅም አላቸው። በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የመምህራን ትምህርት ስርዓታቸው ላይ ማሻሻያ እያደረጉ ይገኛል። የአፍሪካ መዲና የሆነችው ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ በርካታ ሪፎርሞችን እያደረገች ሲሆን ከዚህ ውስጥ አንዱ የመምህራንን አቅም መገንባት እና የብቃት ደረጃን ማሳደግ ይገኝበታል። የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሄራዊ የመምህራን ልማት ንቅናቄ በማድረግ መምህራን በተለያዩ የትምህርት እርከኖች አቅማቸውን እንዲጎለብት ተከታታይ ስልጠና እንዲያገኙ እያደረገ ነው። በአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም አማካኝነንት ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ መምህራን የዲጂታል ክህሎታቸው በማዳበር እና ተከታታይ የብቃት ምዘና በማድረግ አቅማቸውን እየተገነባ ይገኛል። በነዚህ ስራዎች የትምህርት ውጤት ላይ አበረታች መሻሻሎች ታይተዋል። መንግስት የሰለጠነ መምህራንን ቁጥር ማሳደግን የሪፎርሙ አካል አድርጎ እየሰራ ነው። ጋና የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆችን ወደ ዩኒቨርስቲ በማሳደግ ሙያዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ እየሰራች ትገኛለች። ኬንያ ብቃት ላይ የተመሰረተ የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ የመምህራን መማር ማስተማር የበለጠ ተግባር ተኮር እና ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የጀመረችው ተግባር ተጠቃሽ ነው። ሩዋንዳ የስርዓተ ትምህርት አሰራሮቿን ከመምህራን ስልጠና ጋር በማጎዳኘት የመምህራን እጥረትን ለመቀነስ እና ክህሎታቸውን ለማሳደግ እየሰራች ነው። ለትምህርት ዘርፍ የሚመደበው በጀት በቂ አለመሆን፣ የተማሪ እና ክፍል ጥምርታ አለመመጣጠን፣ የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር በሚፈለገው ደረጃ አለማደግ፣ የዲጂታል ክህሎት ማነስ እና ከፍላጎት አንጻር በቂ የሰለጠነ መምህራን አለመኖር የአህጉሪቷ የትምህርት ዘርፍ ፈተናዎች ናቸው። የፓን አፍሪካ የመምህራን ትምህርት ኮንፍረንስ በያዝነው ሳምንት በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሄዷል። "በአፍሪካ የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ኮንፍረንስ የትምህርት ሚኒስትሮች፣ የመምህራን ማህበራት ተወካዮች፣ ምሁራን፣ የግሉ ዘርፍና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተሳትፈዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በኮንፍረንሱ ላይ ባደረጉት ንግግር ትምህርት ለሰው ሃብት ልማትና ለምጣኔ ሀብት ቁልፍ ሚና አለው ብለዋል። በአፍሪካ የሚፈለገውን ልማትና ዕድገት ለማምጣት የትምህርት ተደራሽነት ላይ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሪፎርሞችን ተግባራዊ ማድረጓንና በዚህም ውጤት መገኘቱን አንስተዋል። የመምህራንን አቅም ለመገንባት የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት በኩልም የተሻለ ስራ መሰራቱን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ የጠቀሱት። የትምህርት ጥራትና የመምህራን እጥረት ላይ እንደ አህጉር አሁንም ያልተፈታ ችግር መኖሩን ጠቁመው፤ ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አባል ሀገራቱ ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባንያንኪምቦና በበኩላቸው በአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ሳይንስና ፈጠራን የበለጠ ለማዳበር የመምህራንን አቅም ማሳደግ ወሳኝ ነው ብለዋል። ለዚህም ለመምህራን አቅም ግንባታ የተለያዩ ኤኒሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ የአፍሪካ የ2063 የልማት ዕቅዶች ዕውቀት መር በሆነ መንገድ ቢተገበሩ ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል። የአፍሪካ መምህራንን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከፈጣንና ተለዋዋጭ ቴክኖሎጂ ጋር መላመድ እንደሚገባም ነው ያነሱት። በአፍሪካ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን የበለጠ ለማሳደግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከወቅቱ ጋር ማዛመድ ይገባል ብለዋል። በኮንፍረንሱ ላይ መምህራንንና ትምህርትን የተመለከቱ የተለያዩ አህጉራዊ ስትራቴጂዎች ይፋ ተደርገዋል። የአፍሪካ የትምህርት ስትራቴጂ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚተገበር) የአፍሪካ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ስትራቴጂ፣ የአፍሪካ ሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ እንዲሁም የአፍሪካ የትምህርት የክህሎት ልማት የድርጊት መርሃ ግብር ይፋ ሆነዋል። በተጨማሪም የአፍሪካ መምህራትን ማህበረሰብ የአሰራር ማዕቀፍ ወደ ትግበራ ገብቷል። ይፋ የሆኑት ስትራቴጂዎች እና የአሰራር ማዕቀፎች የመምህራን ትምህርት፣ ሙያዊ ልህቀት፣ መሰረተ ትምህርት፣ ዲጂታል ክህሎቶች እና ኢኖቬሽን ተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ መዋቅራዊ ለውጦችን የማምጣት ግብ እንዳላቸው የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል። በኮንፍረንሱ ላይ የ2025 የአፍሪካ መምህራን ሽልማት የተካሄደ ሲሆን የዘንድሮው የዓለም የመምህራን ቀን በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተከብሯል። አህጉራዊው ሁነት በአፍሪካ የመምህራን ድምጽ የበለጠ ጎልቶ እንዲሰማ የማድረግ ፣ የትምህርት ኢንቨስትመንት መጠን እንዲያድግ እና የባለድርሻ አካላት ትብብርን የማጠናከር አላማ እንዳለው ተገልጿል። የመምህራንን አቅም ማሳደግ የአፍሪካ የትምህርት ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ አበይት ትኩረቶች መካከል አንደኛው መሆኑን ህብረቱ በመረጃው አመልክቷል። ህብረቱ እ.አ.አ 2024 የትምህርት ዓመት ብሎ በመሰየም የሰጠው ስትራቴጂካዊ ትኩረት የዚሁ ማሳያ ነው። የፓን አፍሪካ ኮንፍረንሱ የመምህራን ትምህርት የአፍሪካ የልማት አጀንዳ አበይት ትኩረት መሆኑ በግልጽ ታይቶበታል። የመምህራንን እጥረትን መቀነስ ብዙ መምህራንን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን ስልጠና ጥራት ያለው፣ ነባራዊ እውነታን ያገነዘበ እና መጻኢውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል። የአፍሪካ መንግስታት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የመምህራን ትምህርት ስርዓትን መቀየር ትኩረታቸውን ባደረጉበት በአሁኑ ወቅት የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ የቀና የሚያደርገውን አፍሪካዊ ማን ያስተምራል? የሚለው ጥያቄ ተስፋ የሚሰጥ ምላሽ ያገኛል። የሰለጠነ፣ በክህሎት የዳበረ እና የኢኖሼሽን እውቀቱ ያደገ መምህር ለአፍሪካ ቀጣይ ጉዞ መቀናት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።
"ያሆዴ"- ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት
Sep 28, 2025 892
(በማሙሽ ጋረደው - ከኢዜአ ሆሳዕና ቅርንጫፍ) የሀዲያ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል የሆነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው። ለማህበራዊ የህይወት አመራር ጉልህ አስተዋጾም ስላለውም በሀዲያዎች ዘንድ በየዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል፡፡ "ያሆዴ" ያለፈውን አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲስ ዘመን የሚቀበሉበት፤ የመጻኢ ተስፋ ብስራትና የልምላሜ ምልክትም ጭምር ተደርጎም ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በዓሉ ሲቀርብ የሀዲያ ተወላጆችና የበዓሉ ተሳታፊዎች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ከያሉበት ወደአካባቢው በመምጣት ይሰባሰባሉ፡፡ በዘንድሮ የያሆዴ በዓልም የሀድያ ተወላጆች የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ በተዘጋጀ ስፍራ (ነፈራ) ተሰባስበው በዓሉን በድምቀት አክብረውታል፡፡ በበዓሉ አከባበር ያለፈው ዓመት ስኬትም ይገመገማል፤ በአዲሱ ዓመትም የተሻለ ተሰርቶ ስኬት እንዲመዘገብ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ይካሄዳል። ሊተገበር የሚችል ዕቅድም ይታቀዳል፡፡ በግልና በቤተሰብ የመጡ ስኬቶች በጋራ በመሆን ይገመገማሉ። የበረቱና ውጤት ያስመዘገቡም እንዲበረታቱ ይደረጋል። ለዚህም ነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው የሚባለው። ሰዎች እንዲሰሩና ስኬት እንዲያስመዘግቡ የሚያበረታታ እሴት አለው። የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፋን ቦጋለ እንደሚሉት የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል "ያሆዴ" ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት ነው፡፡ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የበዓሉ መቃረብን የሚያበስሩት ታዳጊ ልጆች ናቸው። ልጆቹ የዋሽንት (ገምባቡያ) ድምጽ ማሰማት ከጀመሩ በጉጉት የሚጠበቀውን የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል መድረሱ ምልክት ነው። በዓሉ ሀድያዎች አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበት ወቅት ነው። በዓሉ የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት በመሆኑም የተለየ ትርጉምና ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ በዓሉ ሲከበር በተለያዩ ምክንያቶች ተራርቀው የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ከያሉበት ይሰባሰባሉ። በዓሉ በአማረ መልኩ እንዲከበርም ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸው የሥራ ድርሻቸውን ያከናውናሉ። አባውራዎች ለበዓሉ ሠንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ በቱታ ወይም በቅርጫ ቡድናቸው አማካኝነት እየቆጠቡ ይቆያሉ። እንዲሁም ለእንስሳት የሚሆን የግጦሽ ሳር የሚያበቅል ቦታ ከልለው ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ የሚሆነበት ምክንያት ደግሞ በዓሉ በሚከበርበት ሰሞን የሰው ልጅ ይቅርና እንስሳትም መጥገብ አለባቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ እማውራዎች ከበዓሉ ሦስትና አራት ወራት አስቀድመው እንሰት በመፋቅ ቆጮና ቡላ ያዘጋጃሉ። በተጨማሪም ከአካባቢው እናቶች በጋራ በመሆን (ዊጆ) የተሰኘ የቅቤ እቁብ በመግባት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ማጠራቀም ይጀምራሉ፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ ለአተካናና ለሥጋ መብያ ናቀሮ ወይም ዳጣን እንዲሁም የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት ድርሻ የእናቶች ነው፡፡ ለበዓሉ የቤት ውስጥና የውጭ ግርግዳን በቀለምና በተለያዩ ጌጣጌጦች የማስዋብ ሃላፊነት ደግሞ የልጃገረዶች ነው። ወጣት ወንዶች ከነሀሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚያሳዩዋቸውን ግንድ በመቁረጥ ለምግብ ማብስያ እንዲውል ፈልጠው ያዘጋጃሉ። በሀዲያዎች አጠራር ለችቦ የሚሆን እንጨት ወይም ጦምቦራ ከጫካ ለቅመው አስረው እንዲደርቅም ያስቀምጣሉ፡፡ ለበዓሉ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት በዓሉ በስኬትና በድምቀት እንዲከበር ጠቀሜታው የጎላ ነው። በዚህም ያሆዴ ከተናጠል ይልቅ ትብብርን የሚያጠናክር ነው ማለት ይቻላል። እሴቱ በትብብር መድመቅ እንደሚቻልም የሚያሳይ ነው። ይህን ሀሳብ የሚጋሩት አቶ መስፍን የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በምንም ሁኔታ መነጣጠል የማይቻል ትስስርን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ይገልጻሉ። ሀገራዊ አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክር ዘመናትን የተሻገረና ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ባህላዊ እሴት ያለው መሆኑንም ይናገራሉ። በዓሉ ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀረው አባውራዎች በቅርጫ ማህበራቸው አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ የእርድ በሬ ይገዛሉ። በዚህ ወቅት ገንዘብ ማዋጣት ያልቻሉ የቅርጫ አባላት እህል በሚደርስበት ወቅት ለመክፈል ተስማምተው በሬውን በዱቤ እንዲገዙ ይደረጋል፡፡ ይሄም የሚሆነው በያሆዴ በዓል አንዱ ሲበላ ሌላው ተመልካች መሆን ስለሌለበት ነው። እርስ በርስ መጨካከን እንዳይኖርና በዓሉን በአብሮነት ሁሉም ተደስቶ ማክበር እንዲችል ለማድረግ ነው። ከበዓሉ ዕለት በፊት ያለው የመጨረሻ ገበያም የእብድ ገበያ (መቻዕል ሜራ) የሚል ስያሜ አለው። ይሄ ሥያሜ ያገኘው በዓሉ ሲቃረብ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚፈጠረውን ውጥረት ታሳቢ በማድርግ ነው፡፡ በዚህ የእብድ ገበያ ህብረተሰቡ መገበያየት የሚጀምረው ጠዋት ማለዳ ጀምር ሲሆን የግብይት ሂደቱ የሚጠናቀቀው ደግሞ እኩለ ቀን ላይ ነው፡፡ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለመግዛትና የያሆዴ በዓል ከተከበረ በኋላ ለአንድ ወር ገበያ ስለማይቆም ይህን ታሳቢ ያደረገ ግብይት ለመፈጸም የግብይት ሂደቱ ጥድፊያ የበዛበት ሆኖ ይታያል። ያሆዴ በዓል መከበር የሚጀምረው በአተካን ሂሞ ወይም በአተካና ምሽት ሲሆን ይህም ከበዓሉ አንድ ቀን በፊት ያለው ምሽት ነው። ስያሜውን ያገኘው "አተካና" ከተሰኘና በያሆዴዎች ዘንድ ለክብር እንግዳ እና በዘመን መለወጫ ከሚዘጋጅ ምግብ ነው። አተካና ከወተት፣ ከአይብ፣ ከቡላ፣ ከቅቤና ከሌሎች የቅመማ ቅመም ውጤቶች የሚዘጋጅ ምግብ ሲሆን በጣም ጣፋጭና የምግበ ፍላጎትን የሚጨምር ምግብ ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ይሄንን የተለየ ምግብ ተሰባስቦ በአብሮነት በመመገብ በደመቀ መልኩ በዓሉን ማክበር ይጀምራል፡፡ የአካባቢው አባቶች በወጣቶች የተዘጋጀ የማቀጣጠያ እንጨት (ሳቴ) ይዘው ትልቅ በሚባሉ አባውራ ቤት ደጃፍ ወደ ተዘጋጀው የችቦ ደመራ (ጦምቦራ) ቦታ ይመጣሉ:: የሀገር ሽማግሌች አዲሱ ዓመት የብርሃን ዓመት እንዲሆን፤ ለሀገርና ለህዝቦቿ ሰላም እንዲጸና፤ አብሮነት እንዲጠናከር፣ ሰላምና ፍቅር እንዲነግስ ፈጣሪያቸውን ከተማጸኑ በኋላ ችቦውን በእሳት ይለኩሳሉ፡፡ ችቦው ከተለኮሰ በኋላ የአካባቢው ወጣቶች ተሰባስበው ያሆዴ …ያሆዴ! …ያሆዴ! በማለት እየጨፈሩ ያነጋሉ ይጨፍራሉ:: በሀድያዎች ዘንድ "ያሆ" ማለት የአዲስ ዓመት መግባትን ተከትሎ ማብሰሪያ ጭፈራ ሲሆን "ኤዴ" ማለት ደግሞ አገናኝ ማለት ነው፡፡ በያሆዴ በዓል የእርድ ሥነ ስርዓት ለማከናወን ነዋሪዎች የሚሰበሰቡበት ስፍራ "ነፈራ" የሚል ስያሜ አለው። የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ሰፋ ያለ ቦታ ሰሆን በተለያዩ የጥላ ዛፎች የተዋበና ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀም ነው። በእለቱ ለእርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኋላ የባህል ሽማግሌዎች የበሬውን ሻኛ በሰርዶ ሳር ለጋ ቅቤ ይቀባሉ፤ ወተትም ያፋሱበታል፡፡ ይህ ባህላዊ ሥነ ስርዓት ጋቢማ የሚባል ሲሆን (የመልካም ምኞት) መግለጫ ስነ ስርዓትም ነው፡፡ ይህም ሥነስርአት በሚከናወንበት ወቅትም "ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሀገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን " እያሉ በአባቶች ምርቃት ከተካሄደ በኋላ የእርድ ስነ ስርዓት ይከናወናል፡፡ የእርድ ሥነ ስርዓቱ የተከናወነበት ቤት እማወራ አስቀድመው ባደረጉት ዝግጅት መሰረት ቅቤ፤ (ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ) እንዲሁም ከታረደው የበሬ ሥጋ አርዚ ማራ (ቅምሻ) ይወሰድና ክትፎ ከተዘጋጀ በኋላ በጋራ እየበሉ እየተጫወቱ ይውላሉ፡፡ በዚህም በቅርጫ ሥጋው ላይ ከሚሳተፉት የቤተሰብ አባላት ውጪ በአካባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችም ጭምር አብረው በመብላት በመጠጣት በዓሉን በአንድነት ያሳልፋሉ፡፡ ቀሪውን የቅርጫ ሥጋም አባላቱ ተከፋፍለው ወደ እየቤታቸው ይወስዱታል፡፡ በዓሉ አብሮ የመብላት፣ የመጠጣት፣ የመጠያየቅ፣ ችግርንና ግጭትን በጋራ ተወያይቶ የመፍታት፣ መፈቃቀርና መተሳሰብን የሚፈጥር፣ አቅመ ደካሞችና የተቸገሩ የሚረዱበት የአብሮነት መገለጫ በመሆኑ በተለየ መልኩ ይከበራል፡ ከእርድ ሥርዓቱ በኋላ በማግስቱ ልጆች አደይ አበባ (ዘራሮ) ይዘው ወደ ወላጆቻቸው እየጨፈሩ ይመጣሉ። የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባላሉ። ከስጋውም፣ ከቦርዴውም፣ ከአተካናውም እንዲመገቡ ያደረጋል። ይህ ስነ ስርዓትም ሚክራ ይባላል። በያሆዴ የዘመን መለወጫ በዓል ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ሥጋና አደይ አበባ ጭምር ይዘው ይሄዳሉ። በዓሉ ያላገቡ ወጣቶች የሚተጫጩበትና ለአዲስ ህይወት ጅማሬ የሚያበስሩበት በመሆኑን የተለየ ድባብ አለው፡፡ የያሆዴ በዓል ካሉት እሴቶች አንዱ የህብረተሰቡን የአካባቢ ልማት ተሳትፎ ማበረታታት ተጠቃሽ መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን ዕሴቱ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው ለማህበረሰብ ጥቅም እንዲውሉ ጭምር አቅም እየሆነ መምጣቱን ነው የሚናገሩት።ይህ የአብሮነት ማስተሳሰሪያና የማህበራዊ መስተጋብር መጋመጃ የሆነው በዓል እሴቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል መስራት ይገባል። እሳቸው እንዳሉት በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም መምሪያው ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ዕሴቱን የመሰነድና ምርምሮች ማካሄድን ጨምሮ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 1362
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ 7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 1927
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 2758
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 2892
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር። ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው። የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 668
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 507
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 6352
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 4829
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የአፍሪካ የግብርና፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ፤ እድሎች እና ፈተናዎች
Oct 20, 2025 434
አፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማሳካትና እንድትበለጽግ የጀመረችው ጉዞ ወሳኝ መዕራፍ ላይ ይገኛል። የአህጉሪቱን የመለወጥ ትልም ባሏት እምቅ ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ላይ የተመረኮዘ ነው። ተዝቆ የማያልቀው የአፍሪካ ብዝሃ ሀብት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግና አይበገሬ አቅም መገባንት የሚያስችሏትም ጭምር ናቸው። ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የውሃ ሀብቶቿ እና ብዝሃ ከባቢ የአየር ንብረቷ ከሀብቶቿ መካከል ይጠቀሳሉ። ግብርና አሁንም የአፍሪካ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው። ዘርፉ ለአህጉሪቱ 35 በመቶ የሚጠጋ አጠቃላይ ጥቅል ሀገራዊ ምርት(ጂዲፒ) አስተዋጽኦ ያደርጋል። 60 በመቶ ህዝብም በግብርና ስራ እንደሚተዳደር የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) ሰነድ ያሳያል። ከዚህም ውስጥ አብዛኞቹ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። ሴቶች በግብርናው ዘርፍ ካለው የሰው ኃይል የ50 በመቶ ድርሻው ይወስዳሉ። የአፍሪካ ህዝብ 60 በመቶ ድርሻ የያዘው ወጣት በግብርና ንግድ፣ እሴት መጨመርና የኢኖቬሽን ስራዎች ያለው ተሳትፎ እያደገ መጥቷል። የዓለም 60 በመቶ ያልለማ መሬት ያለው በአፍሪካ ነው። ሰፊ የውሃ ሀብቶችና እያደገ ያመጣው ብሉ ኢኮኖሚ(የባህር እና ሌሎች የውሃ ሀብቶች) ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ እድገትን የሚያረጋግጡ ናቸው። የመሰረተ ልማቶች ተደራሽነት ማደግ፣ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችና ኢኖቬሽንን የተመረኮዙ የፋይናንስ አማራጮችን መስፋት ግብርናን የምግብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ለኢንዱስትሪ ልማት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ንግድ መሳለጥ ትልቅ አቅም መሆን ይችላል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና በግብርና ምርቶችና አገልግሎቶች ያለውን አህጉራዊ የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ ነው። የንግድ ቀጣናውን በሚገባ መጠቀም ከተቻለ እ.አ.አ በ2030 የግብርና ንግድ ልውውጡን በ30 በመቶ ማሳደግ እንደሚቻል ጥናቶች ያመለክታሉ። ግብርናው የተጠቀሱት ጥንካሬዎች ያሉት ቢሆንም ረጅም ጊዜ የዘለቁ መዋቅራዊ ፈተናዎች አብረውት ዘልቀዋል። የግብርና ምርቶች ላይ የሚፈለገውን ያህል እሴት አለመጨመር፣ የቴክኖሎጂ አጠቀቃምና የምርታማነት ውስንነት፣ የመሰረተ ልማቶች እና ሎጅስቲክስ በበቂ ሁኔታ አለመሟላት፣ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ክፍተቶች ከአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተፈጥሯዊ አደጋዎች እንዲሁም እያደገ ከመጣው ህዝብ ጋር ተዳምሮ ግብርናውን እየፈተነው ይገኛል። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ማጠንጠኛ የሆነው ጉዳይ የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት(ካዳፕ) ነው። እ.አ.አ በ2003 የአፍሪካ ህብረት በሞዛምቢክ ባደረገው ስብሰባ የግብርና የምግብ ዋስትና ድንጋጌን አጽድቋል። ይህ ማዕቀፍ የማፑቶ ድንጋጌ ስያሜን በማግኘት የካዳፕ ትግበራ በይፋ እንዲጀመር አድርጓል። የማፑቶ ድንጋጌ እ.አ.አ በ2014 በማላቦ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025 የተተገበረ) በአዲስ መልክ የታደሰ ሲሆን የተለያዩ ቃል ኪዳኖችን በውስጡ ይዟል። ይህም በካዳፕ አማካኝነት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ከአጠቃላይ ዓመታዊ ጥቅል ምርታቸው(ጂዲፒ) ቢያንስ ስድስት በመቶውን ለግብርናው ዘርፍ እንደሚመድቡና በየሀገራቱ በዘርፉ በየዓመቱ በአማካይ ስድስት በመቶ እድገትን የማሳካት ግብ አለው። ረሃብን ማጥፋት፣ ድህነትን በግማሽ መቀነስ፣ የማይበገር አቅም መገንባትና የጋራ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ሌሎች ግቦች ናቸው። ካዳፕ የአፍሪካ ሀገራት በስርዓተ ምግብ ያላቸውን ኢንቨስተመንት በማሳደግ፣ በአፍሪካ የእርስ በእርስ የግብርና ንግድን በማሳደግና የፖሊሲ መሰናሰልን በመፍጠር ቁልፍ ሚና ተወጥቷል። ይሁንና የተመዘገቡት ውጤቶች ያልተመጣጠነ ልዩነት የሚታይባቸው ናቸው። የ2023 የካዳፕ የግምገማ ሪፖርት እንደሚያሳየው የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የማላቦ ግቦችን ማሳደግ የሚያስችል መንገድ ላይ እንዳልሆኑ ያስቀምጣል። ይሁንና 26 ሀገራት በተቀመጡ ግቦች መመዘኛ መሻሻል እንዳሳዩ ይገልጻል። ኢትዮጵያ፣ ብሩንዲ፣ ካሜሮን፣ ግብጽ፣ ማሊ፣ ጋና እና ጋምቢያ የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ። አብዛኞቹ ሀገራት በግብርና ኢንቨስትመንት፣ ምርታማነት እና የፖሊሲ ትግበራ ላይ ፈተናዎች እንዳሉበት ሪፖርቱ አመልክቷል። ሀገራት የሰነዱን ትግበራ ማፋጠንና ተቋማዊ ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስቧል። የማላቦ ድንጋጌ ወደ መገባደዱ ላይ የሚገኝ ሲሆን የካዳፕ ቀጣዩ ምዕራፍ የካምፓላ ድንጋጌ ነው። ይህ የትግበራ ምዕራፍ ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035 የሚቆይ ነው። የካምፓላ ድንጋጌ ከማፑቶ እና ማላቦ ድንጋጌዎች ትምህርቶችን በመውሰድ የግብናውን እድገት ማላቅ ግቡ አድርጎ ይዟል። የካምፓላ አጀንዳ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ አረንጓዴ እድገት እና አይበገሬነት ያላቸውን ሚና በማንሳት መስኮቹ ስርዓተ ምግብን ዘላቂና አካታች የማድረግ ግብን ማሳካት እንደሚያስችሉ አመልክቷል። በዚህ ማዕቀፍ እ.አ.አ 2050 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ህዝብ ይኖራታል ተብሎ የሚጠበቀውን አፍሪካን በራስ አቅም የመመገብ ውጥን የያዘ ነው። ይሁንና የግብርና ምርታማነት ከዓለም አቀፍ አማካይ የምርታማነት ምጣኔ አንጻር ሲታይ አሁንም ወደ ኋላ ቀረት ያለ ነው። ይህም አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች የተገደበ የፋይናንስ አቅርቦት ማግኘታቸው እንዲሁም የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው አለመደረጉ የችግሩ አብይ መንስኤ ሆኖ ይጠቀሳል። የአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የከባቢ አየር ብክለት ፈተናዎቹ እንዲበረቱ አድርጓል። ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ የበይነ መንግስታት ፓናል(IPCC) አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እርምጃዎችን በፍጥነት ካልወሰደች እ.አ.አ በ2050 የግብርና ምርታማነቷ ከ20 እስከ 30 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ገምቷል። ከ250 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ደህንነቱ ያልተረጋገጠ እና ንጽህናው ያልተጠበቀ የውሃ አቅርቦት ፈተና ውስጥ ይገኛሉ። በህዝብ ቁጥር መጨመር፣ በከተሜነትና ኢንዱስትሪ መስፋፋት ምክንያት ንጹህ የውሃ አቅርቦትን የማግኘት ጉዳይ የበለጠ ሊስፋ እንደሚችል ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩና ፈተናዎች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለአባል ሀገራት የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል። የህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር የስራ ክፍሉ(DARBE) አማካኝነት የአፍሪካን ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና ኢኒሼቲቮች የተናበቡና የጋራ ግብ ያላቸው እንዲሆኑ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል። የአቅም ግንባታ፣ የቴክኒክ እና የፖሊሲ ድጋፍም የሚያደርግ ሲሆን ብሄራዊ እቅዶች ከአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሰነዶችና የአጋርነት ማዕቀፎች ጋር የተጣጠሙ መሆናቸውን ያረጋገጣል። የስራ ክፍሉ ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች ጋር አጋርነቶችን የማጠናከር ስራ ያከናውናል። ግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬነት እንዲሁም የተፈጥሮ እና የብሉ ኢኮኖሚ ሀብቶች በዘላቂነት መጠቀም ላይ የተቀናጁ አሰራሮችን መፍጠር ላይም ይሰራል። የዘርፉ አጠቃላይ ስራዎች አካል የሆነው ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል። በስብሰባው ላይ ሚኒስትሮች፣ ባለሙያዎችና የልማት አጋሮች ይሳተፋሉ። የአፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቮች አፈጻጸም መገምገምና ዘርፉ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከር የስብሰባው አላማ ነው። እ.አ.አ በ2023 በአዲስ አበባ የተካሄደውን አምስተኛው የልዩ ኮሚቴ ስብሰባ ውጤቶች ግምገማ ይደረጋል። የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም(ካዳፕ) የማላቦ ድንጋጌ(ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2025) ስኬቶች እና የካዳፕ የካምፓላ ድንጋጌ (ከእ.አ.አ 2026 እስከ 2035) አፈጻጸም ላይ ውይይት ይካሄዳል። የስርዓተ ምግብን ማጠናከር፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት ስርዓት መዘርጋት፣ የበካይ ጋዞችን ልህቀት መቀነስና ዘላቂ የውሃና የተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደርን ማጠናከር ሌሎች የምክክር አጀንዳዎች ናቸው። በአፍሪካ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ በማሻሻል ዘላቂ እድገትን ማምጣት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክረ ሀሳቦች ይቀርባሉ። ውይይቱ እ.አ.አ በ2026 በአዲስ አበባ የሚካሄዱትን የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባና የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንደሚያዘጋጅ ተመላክቷል። የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር አጀንዳ 2063 ለማሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ዘርፎች መሆናቸውን አመልክቷል። ህብረቱ የግብርና እና የገጠር ልማት የበለጠ ማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክቷል። የህብረቱ አባል ሀገራት የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራምን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲተገብሩም ጥሪ አቅርቧል። ስድስተኛው የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ጥቅምት 11 እና 12 እንዲሁም ጥቅምት 14 በሚኒስትሮች ደረጃ እንደሚያከናውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አፍሪካ ወደ ዘላቂ ግብርና፣ የገጠር ልማት፣ ውሃ አስተዳደር እና አካባቢ ጥበቃ እያደረገች ያለው ጉዞ አንገብጋቢ አጀንዳና ሽግግሩን ለማፋጠን ወሳኝ ሚና አለው። አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፋይናንስ ማነቆ፣ መሰረተ ልማቶች እና የፖሊሲ የመፈጸም አቅም ውስንነትን ጨምሮ የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩባትም እድሎቿ ፈርጀ ብዙ ናቸው። በርካታ ያልለማ መሬት፣ ሰፊ የውሃ ሀብት፣ ወጣቶች እና የብሉ ኢኮኖሚ ሀብቶች በአፍሪካ ዘላቂ የግብርና እድገት ለማረጋገጥና ሁሉን አቀፍ ስርዓተ ምግብ ለመገንባት የሚያስችል ነው። ለአርሶ አደሮች በቂ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ አቅማቸውን መገንባት ቁልፍ ጉዳይ ነው። ሀገራት ብሄራዊ ፖሊሲዎቻቸውን ከአህጉራዊ ማዕቀፎች ጋር ማጣጣም ይኖርባቸዋል። ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት የአሰራር ማዕቀፍ መዘርጋት ይገባል። የተፈጥሮ ሀብትን በሚገባ መጠቀም፣ በኢኖቬሽን ላይ መዋዕለ ንዋይን ፈሰስ ማድረግና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር የምግብ ዋስትናዋን ያረጋገጠች፣ አረንጓዴ እና የበለጸገች አህጉር መገንባት ይቻላል።
ኢሬቻ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ማንሰራራት!
Oct 3, 2025 1019
ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ሰዎች በክረምት ወቅት ከሚከሰት መለያየትና መራራቅ በኋላ ዳግም የሚገናኙበት፣ በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት ዕለት ነው። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። ኢሬቻ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ጥብቅ ቁርኝት የሚገለጽበት የገዳ ስርዓት አንዱ አካል ነው፡፡ የኢሬቻ እሴቶች ጠንካራ ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት የሚያግዙ ናቸው። አንድነት፣ ወንድማማችነት፣ አብሮነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ዕርቅ እና ሌሎችም ተጠቃሽ የመልካም እሴቶች መገለጫ ነው። በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የገዳ ስርዓት አንዱ እሴት ኢሬቻ ሲሆን፤ ለሀገር ማንሠራራትና ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መሠረት ይሆናል፡፡ ኢሬቻ አብሮነት የሚጸናበት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴት ይበልጥ የሚጎላበት፣ አሰባሳቢ ትርክት የሚጎለብትበት፣ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት ማሰሪያ ከፍ ያለ በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ በጋራ የሚያከብሩትና የዓለም ቱሪስቶች የሚታደሙበት ሲሆን፤ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትና የኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ጎልቶ የሚታይበት ነው፡፡ የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል አከባበር ሀገራዊ ማንሰራራት በተግባር የተረጋገጠበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተመርቆ ዓለም የኢትዮጵያን መቻል በተግባር ባየበትና ሌሎች ለሀገር ማንሰራራት ዕውን መሆን መሠረት የሚጥሉ ትላልቅ ሀገራዊ ኘሮጀክቶች ይፋ በተደረጉበት ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ በዓሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመላው ኢትዮጵያዊያንን ሕብረት የሚንጸባረቅበት ሆኖ በተለያዩ አከባቢዎች በድምቀት እየተከበረም ይገኛል፡፡ በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ። Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Hayyee! Waaqa Uumaa, Waaqa Uumamaa ፍጥረትን የፈጠርክ ፈጣሪ Gurraacha garaa garbaa የእውነትና የሰላም አምላክ! Dogoggora nu oolchi ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ሁሉ ጠብቀን! Dacheef nagaa kenni ለምድራችን ሰላም ስጥ! Laggeenif nagaa kenni ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! Olota keenyaaf nagaa kenni ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! . . . Loowan keenyaaf nagaa kenni " ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!" በማለት ይመረቃል። ሕዝቡም ይሁንልን ይደረግልን ሲል "አሜን! አሜን! አሜን!” ይላል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 25 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ " ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት " በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል። የክራምት ወራት እንዳበቃ የሚከበረው "ኢሬቻ መልካ" Irreecha Birraa (በውኃ ዳርቻ የሚከበር) ሲሆን፤ በዓመቱ አጋማሽ ላይ "ኢሬቻ ቱሉ" Irreecha Arfaasaa ደግሞ በተራራማ ቦታ ይከበራል። ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ነው። የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመምጣቱ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ይህ ከማህበራዊ መስተጋብር አኳያም ሰዎች የሚሰባሰቡበትና የሚገናኙበት ነው። ከባዱ የክረምት ወቅት አልፎ ብርሃን (ብራ) ስለደረሰ ለዚያ ምልክት ይሆን ዘንድ የለመለመ እርጥብ ሣር ይዘው ወደ ወንዝ በመውረድ ንጹህ ውሃ ውስጥ እየነከሩና እየረጩ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ኢሬቻ ቱሉ የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ አብሮነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። ኢሬቻ ምድርን እና ሰማይን ለፈጠረው "ዋቃ" "Waaqa" ምስጋናውን ለማድረስ የሚከበር ሲሆን፤ በዕድሜ ልዩነት ሳይገደብ ለዘመናት በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ሲከበር ቆይቷል። በዝናባማው የክረምት ወቅት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቆ የቆየው ዘመድ አዝማድ በኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ ይገናኛል፤ ይጠያየቃል፤ ናፍቆቱንም ይወጣል። አባቶች ክረምት በለሊት ይመሰላል ይላሉ። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ደግሞ ውበት ነው፤ መታያና መድመቂያም ነው። ለዚህ ነው በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ሁሉም ውብ የባህል ልብሱን በመልበስ በደስታ በዓሉን ለማክበር የሚመጣው። ሕዝቡ በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሥፍራ የሚሄደው በተናጠል ሳይሆን በሕብረትና በአንድነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው የሚባለው። ኢሬቻ የወንድማማችነትና የአንድነት አርማ ሲሆን፤ የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ፣ የህብረ ብሔራዊ አብሮነት ማስተሳሰሪያም ጭምር ነው፡፡ በኢሬቻ ልዩነት የለም፤ ፀብ የለም፤ ክፋት የለም፤ ይልቁንም ምስጋና ይበዛል፤ ፍቅር ይሰፍናል፤ አብሮነት ያብባል፣ አንድነት ይጸናል። ኢሬቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት ነው። የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚወጣው ታዳሚም እንደ እርጥብ ሣር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ የበዓሉን ስነ-ስርዓት ያከናውናል። ይህን የሚያደርገውም "ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያፀደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመሰግንሃለን" በማለት የፈጣሪን መልካምነት ለማሳየት ነው። በሌላ በኩል እርጥብ ሣር የልምላሜ ምልክት በመሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫም ስለሆነም ነው በኢሬቻ በዓል እርጥብ ሣር የሚያዘው። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር እንዲህ እያሉ ያመራሉ። ኦ ያ መሬሆ…………………መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ኡማ ሁንዳ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ለፋ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ መልካ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ እያሉ ያመራሉ። የሁሉ ፈጣሪ፣ ምድርን የፈጠርክ፣ ወንዙን የፈጠርክ . . . ምስጋና ለአንተ ይሁን በማለት ያመሰግናሉ፤ ይዘምራሉ። የኢሬቻ በዓል ሥነ-ሥርዓት በአባመልካ ተከፍቶ በአባ ገዳዎች ተመርቆ ከተጀመረ በኋላ መላው ሕዝብ በአንድነት ሥርዓቱን ያከናውናል። ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው፣ የሁሉም ማጌጫ፣ መድመቂያ እና የአብሮነት መገለጫ ነው። የበዓሉ ታዳሚዎች ከዋዜማው ጀምሮ በሆረ ፊንፊኔና በሆረ ሀርሰዲ በመሰባሰብ፤ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችን በማዜምና ምስጋና በማቅረብ አድረው በነጋታው ዋናውን የምስጋና በዓልም ያከናውናሉ፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎች የደስታና የምስጋና ምልክት የሆነውን ባህላዊ ነጫጭ ልብስ ለብሰው፣ ባህልን የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ሁነቶችን በመከወን ልዩ ልዩ ዜማዎችን በማዜም፣ ግጥሞችን በማቅረብ፣ ወደ ፈጣሪ በመጸለይ እና ምስጋና በማቅረብ ሥርዓቱን ያከናውናሉ፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች የሚታወቁበትን ባህላዊ ልብስ በመልበስ በቋንቋቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን በአንድነት ያከብራሉ። ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር በርካታ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ከማቀራረብና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ከመገንባት ረገድ ትልቅ አስተዋጾኦ ያለው ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ በዓላት ላይ ለመታደም ወደ አገር ቤት ይመጣሉ። የውጭ አገራት ጎብኚዎችና እንግዶችም በትዕይንቱ ይታደማሉ። ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ አገር የመጡ ልዑካን በበዓሉ ላይ በመታደም የበዓሉን ትልቅነት እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት መገለጫ መሆኑን መመስከራቸው ይታወሳል። አያሌ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ያሉት ይህ የምስጋና በዓል እውነተኛ ወንድማማችነት የሚታይበት፣ አንድነት የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚጠናከርበት፣ ሰላምና ተስፋ የሚታወጅበት አገራዊ እሴት ነው። በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ምግቦችና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ኢሬቻና መሰል የአደባባይ በዓላትን እንደመልካም የገበያ አማራጭ ይጠቀሙባቸዋል። የኢሬቻ በዓል ለቱሪዝም ፍሰት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው፤ በርካታ የባህር ማዶ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የሚታደሙበት በዓል ነው፡፡ በዓሉ ትልቅ የቱሪዝም መስህብ ሲሆን፤ ዘርፉን በማጠናከር እና ብሔራዊ ልማትን በማሳደግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚናንም የሚጫወት ነው፡፡ ኢሬቻ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች በስፋት የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ ነው። በእርግጥም ይህንን ውብ የጋራ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነውና በምስጋና እንደጀመርን በምስጋናና ምርቃት እንሰነባበት። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ከመጥፎ ነገር ጠብቀን! ንጹህ ዝናብ አዝንብልን! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ!