ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን ከወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ፒራሚድስ ጋር አቻ ወጥቷል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ከግብጹ ፒራሚድስ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ማምሻውን ካይሮ በሚገኘው ጁን 30 ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊስተን ማዬሌ በ12ኛው ደቂቃ ፒራማድስን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል።

ብሩክ ሙሉጌታ 83ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ግብ ኢትዮጵያ መድን አቻ ሆኗል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ሐሙስ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ መድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ይቀላቀላል።

ኢትዮጵያ መድን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የዘንድሮው የመጀመሪያው ነው።

የግብጹ ፒራሚድስ ክለብ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ ባለቤት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም