ቀጥታ፡

በክልሉ ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ርእሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ

ጋምቤላ፤ ጥቅምት 15/2018(ኢዜአ):-  በጋምቤላ ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።

በጋምቤላ ክልል የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅምን እና የአገልግሎት ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ የአመራሮች ሽግሽግ ተደርጓል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ፤ የልማት እቅዶችን ለመፈፀምና የሕዝብን የመገልገል ፍላጎት መሰረት በማድረግ ብቁና ጠንካራ የአመራር አደረጃጀት መፍጠር ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

በዚሕም መሰረት በክልሉ የአመራር ሽግሽግ ማድረግ በማስፈለጉ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስና ለሕዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ሽግሽግ መደረጉን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት የነበረውን የመፈፀም አቅም መሰረት በማድረግ ብቃትን መሰረት ያደረገ የአመራር ሽግሽግና አዲስ ምደባ  ጭምር መደረጉን ነው የገለጹት።

በዚህም መሰረት በክልሉ ብቁና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም