ቀጥታ፡

ቶተንሃም ሆትስፐርስ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኤቨርተንን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኔዘርላንዳዊው ተከላካይ ሚኪ ቫን ደቬን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፓፔ ሳር ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኤቨርተን በአዲሱ ስታዲየሙ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ17 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኤቨርተን በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም