አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን 1 ለ0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል።
በኤሜሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግብ ኤቤሬቺ ኤዜ ከእረፍት በፊት በ39 ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከፓላስ አርሰናልን የተቀላቀለው ኤዜ የውድድር አመቱ የመጀመሪያ ጎሉንም በቀድሞ ክለቡ ላይ ማስቆጠር ችሏል።
አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን በ22 ነጥብ መምራት የቻለ ሲሆን ከተከታዮቹ ጋር ያለውንም የነጥብ ልዩነት ማስፋት አስችሎታል።
በሌሎች የዛሬ መርሃ ግብር ጨዋታዎች ወደ ቪላ ፓርክ ያቀናው ማንችስተር ሲቲ በተመሳሳይ በአስቶን ቪላ 1ለ0 ተሸንፏል።
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ቮልቭስ በበርንሌይ 3ለ2 ፤በአስደናቂ ብቃት ላይ የሚገኘው ቦርንማዝ ደግሞ ኖቲንግሃምን 2ለ0 ያሸነፉበት ጨዋታ የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብሮች ናቸው።