በተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ደርቢ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ደርቢ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ እና ጁድ ቤሊንግሃም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፌርሚን ሎፔዝ ለባርሴሎና ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ኪሊያን ምባፔ በ52ኛው ደቂቃ የፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።
የባርሴሎናው አማካይ ተጫዋች ፔድሪ በ100ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ነጥቡን ወደ 27 ከፍ በማድረግ መሪነቱን አጠናክሯል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ባርሴሎና በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።