አርእስተ ዜና
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 
May 19, 2024 80
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባውን የሸይካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መርቀው ከፍተዋል። ትምህርት ቤቱ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ እናት ሸይካ ፋጢማ ድጋፍ በአዲስ አበባ የተገነባ ነው። ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምር ሲሆን ለአይነ ስውራን ምቹ የሆኑ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች ላይብረሪና ሌሎችም ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን የያዘ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም 34 ትምህርት ቤቶችን አስገንብቶ አገልግሎት ማስጀመሩን ተናግረዋል።   ትምህርት ቤቶቹ በዋናነት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ መሆኑንም አንስተዋል። ዛሬ ለምረቃ የበቃው አዳሪ ትምህርት ቤቱም እጅግ ዘመናዊና በአይነቱ ልዩ መሆኑን ጠቅሰው ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ከ300 በላይ አይነ ስውራን ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል ብለዋል። መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህ ስራም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በበኩላቸው፣ በጽህፈት ቤቱ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን የኑሮ ጫና ማቃለልን ታሳቢ ያዳረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ሸይካ ፋጢማን ጨምሮ የአዳሪ ትምህርት ቤቱ እንዲገነባ ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። ሸይካ ፋጢማን ወክለው ንግግር ያደረጉትና በሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ የሂዪማንቲ ትምህርት ክፍል ቻንስለር የሆኑት ዶክተር ካሊፋ ሙባረክ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።   የአገራቱ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየሰፋ መሆኑን ጠቅሰው፣ አዳሪ ትምህርት ቤቱም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ እኤአ በ2018 ኢትዮጵያን ከጎበኙ ወዲህ የአገራቱ ግንኙነት ይበልጥ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ መነጽሮችን ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ አዳሪ ትምህርት ቤቱንም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።
ፕሮፌሰር አስፋው አጥናፉ አረፉ
May 19, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምሕርት ቤት የራዲዮሎጂ ትምሕርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ፕሮፌሰር አስፋው አጥናፉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዓርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም አርፈዋል፡፡ ፕሮፌሰር አስፋው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋከልቲ፣ የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ1976 ዓ.ም አግኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ ሐኪምነት አሰብ ሆስፒታል ካገለገሉ በኋላ በራዲዮሎጂ ስፔሽያሊቲ ትምህርት ከመጀመሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች አንዱ በመሆን በ1981 ዓ.ም ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም በ2006 ዓ.ም በቦዲ ኢሜጂንግ ሰብ ሰፔሺያልቲ ፕሮግራም ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ተመራቂዎች መካከል አንዱ በመሆን አጠናቀዋል፡፡ በሰላሳ አምስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ የአገልግሎት ዘመናቸው ብዙ ኃላፊነቶችን ተወጥተዋል፡፡ ለአራት ተርም በራዲዮሎጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትበብር በመፍጠር በትምህርት ከፍሉ የተለያዩ የሰብ ሰፔሻልቲ ትምህርቶች እንዲጀመሩ አድርገዋል፡፡ የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ትምህርት በባችለር ዲግሪ እንዲሰጥ በማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርከተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ የቴሌ ሜዲስን ዩኒት፣ በቀጣይም የኢ-ሄልዝ ማዕከል እንዲቋቋም ያደረጉ ሲሆን በኃላፊነት ደረጃም ሰርተዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ራዲዮሎጂ ማሕበርን ለመመሥረት ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ከመስራቾቹ አንዱ በመሆን የመጀመሪያ የማሕበሩ ፕሬዚደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሰላሳ አምስት በላይ የጥናት ጽሑፎችን ያሳተሙ ሲሆን ባደረጓቸው ጥናቶች በማስተማር፣ በጤና አገልግሎት፣ በማሕበረሰብ አገልግሎት እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ሆነ በሐገር፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በ2010 ዓ.ም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም፣ የተለየያዩ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ ፕሮፌሰር አስፋው ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም ሰኞ፣ ግንቦት 12 ቀን 2016 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በመካኒሳ አቦ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ
May 19, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በኬንያ አቻው ተሸንፎ ከአለም ዋንጫ ማጣሪያው ውጪ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ብሄራዊ ቡድኑ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከኬኒያ አቻው ጋር ናይሮቢ ላይ አድርጎ 3 ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። ውጤቱንም ተከትሎ የኬንያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል። የኬኒያ ብሄራዊ ቡድን በአራተኛው ዙር የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥም ይሆናል። አፍሪካ በዓለም ዋንጫው ሶስት አገራትን የማሳተፍ ኮታ ያላት ሲሆን 12 አገራት በውድድሩ ለመሳተፍ በሶስተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታቸውን በማድረግ ይገኛሉ። አዘጋጇ ዶሚኒካን ሪፐብሊክን ጨምሮ እንግሊዝ ፣ፖላንድ፣ ስፔን፣ ብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ፣ ኒውዝላንድ፣ ጃፓንና ሰሜን ኮሪያ ለዓለም ዋንጫው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። 16 ሀገራት የሚሳተፉበት 8ኛው የፊፋ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ በዶሚኒካን ሪፐብሊክ አስተናጋጅነት ጥቅምት 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የምትሆንበት የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ ምርምሮች እየተደረጉ ነው
May 19, 2024 51
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ የምትሆንበት የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ የምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) "ሳይንስ በር ይከፍታል ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሃሳብ ከግንቦት 10 እስከ 18 ቀን 2016 የሚከናወነውን ስትራይድ ኢትዮጵያ ዓመታዊ ኤክስፖ ትናንት ከፍተዋል፡፡ ኤክስፖው በአይ ሲ ቲ ዘርፍ ትልቅና ተስፋ ሰጭ ጅምር የታየበት መሆኑን ገልጸው፤ ሁነቱ ለቴክኖሎጂ ፈጠራና እድገት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚገልጽ፣ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ዘመን በምታደርገው ጉዞ ያላትን አቅምና ምኞት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገ ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በሳይንስ ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ እንዳሉት፤ የስትራይድ ዓመታዊ ኤክስፖ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ፣ ትብብርና ፈጠራ እንዲሁም የፈጠራ ባህል ግንባታን የሚያጠናክር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን የደረሰችበትን እድገት ከማሳየት ባለፈ በቀጣይ በዘርፉ ላላት ተቀባይነት ምቹ ምህዳር ይፈጥራል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዘርፉ ጥናትና ምርምር በማድረግ መድሃኒት አምርታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንድትችል በር በመክፈት በራስ መተማመን መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፈጠራ ውጤቶችን ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገቢራዊ በማድረግ የኢ ኮሜርስ፣ ስታርትአፕ እና መሰል ተግባራት እንዲዳብሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በቴክኖሎጂ ሰውና ሀሳቡ ተገናኝተዋል ያሉት ዶክተር ባይሳ፤ የሳይንስን መሰረታዊ እውቀት መገንዘብ ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከዋሉ የጥናት ውጤቶች በተጨማሪ ከሌሎች ዓለም ሀገራት ጋር መወዳደር የሚያስችሉ የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ ምርምሮች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም ስራ ላይ ለማዋል የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው፤ በዚህም በዘርፉ ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ እድል በመፍጠርና የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት በመስጠት ብዙ ርቀት መጓዙን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትሉ ይጠናከራል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
May 19, 2024 62
ሚዛን አማን፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ። በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራና የዞንና የክልል የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በፌዴራል መንግስት ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በእዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ በፌዴራል መንግስት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የክልሉን የልማት ተስፋ ያሳደጉ ናቸው። በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ ሎጅ ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል። ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ በክልሉ መንግስት የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገንባታ 62 በመቶ ላይ መድረሱን የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የሚቀሩ ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ የግንባታ ሥራው የተጀመረውና የገበታ ለትውልድ አካል የሆነው የደንቢ ሎጅ የግንባታ ሂደት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፣ የሎጁ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በቀጣይ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት ይሆናል። የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያን እየገነባ ያለው የ"ሳምሶን ቸርነት ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭ" ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኢዮብ ሞላ በበኩላቸው ግንባታውን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ እየተሠራ ነው ብለዋል። የአየር ማረፊያው ግንባታ የህዝብ የልማት ጥያቄ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠውና ግንባታውን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ግብአቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል።  
የሚታይ

ባለፉት ዓመታት በክልሉ ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
May 19, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ መንጌ ወረዳ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የካሻፍ ቱመት መንገዱል ጤና ጣቢያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በዚህ ወቅት አቶ አሻድሊ ሀሰን ባለፉት ዓመታት በክልሉ በጤናው ዘርፍ ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል። በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ጤና ጣቢያ በአዲሱ የጤና ፖሊሲ ስታንዳርድ መሰረት የሚገነባ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። መንግስት መድረስ ባልቻለባቸው አካባቢዎች ስትራቴጂክ የልማት ተግባራትን እያከናወነ ለሚገኘው ለክልሉ ቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምስጋና አቅርበዋል። የመንጌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም መንሱር፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እየመለሰ ይገኛል ብለዋል። በወረዳው ያለውን የጤና ሽፋን ለማሳደግ እና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የግንባታው መጀመር ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። የጤና ጣቢያው ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል። የጤና ጣቢያው ግንባታ ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው ሲጠናቀቅም ከ30ሺህ በላይ የአካባቢውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎችም በጤና ጣቢያው ግንባታ መጀመር እንደተደሰቱ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ኖርዌይ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያከናውነውን ተግባር እንደምትደግፍ አስታወቀች
May 19, 2024 86
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ኖርዌይ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያከናውነውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለመደገፍ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች። ኖርዌይ እኤአ በ2011 ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በደርባን ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጠንካራ አጋርነት መመስረቷ ይታወሳል። በኖርዌይ ኤምባሲ የአየር ንብረት፣ አካባቢና ደን አማካሪ ማሪ ማርቲንሰን ለኢዜአ እንዳሉት ኖርዌይ የኢትዮጵያ መንግስት በአየር ንብረትና በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ የያዘውን ግብ ለመደገፍ እየሰራች ነው። በተጨማሪ አገራቸው በአየር ንብረትና በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የምርምር ማዕከላትን እየደገፈች መሆኗን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ላይ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው በተለይም በደን ጥበቃ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ መንግስት የሚያከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መንግስት ለአረንጓዴ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም ነው የገለፁት። የአየር ንብረት ለውጥ ለብዝሀ ህይወትና ለመጪው ትውልድ ስጋት በመሆኑ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ስለሚገባ ሌሎች አጋር አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ሁለቱ አገራት በዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት ያደረጉት ስምምነት ከ10 አመት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የኖርዌይ የአየር ንብረትና አካባቢ ሚኒስቴር በየካቲት 2016 ዓም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአየር ንብረት ላይ ያለውን አጋርነት እኤአ እስከ 2030 ለማጠናከር መስማማታቸውን አስታውሰዋል። በአለም ላይ ብዝሀ ህይወትን ጠብቀው በማቆየት ስኬታማ ከሆኑ 36 አካባቢዎች ሁለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ለእነዚህ አካባቢዎች ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት። በቀጣይ የኖርዌይ መንግስት በደን ልማት ላይ የሚያደርገው ድጋፍ እንደሚጠናከር አስታውቀዋል፡፡    
ለአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ቀልጣፋና ዘመናዊ የጉምሩክ አሰራር ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ ነው
May 19, 2024 97
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ለአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋና ዘመናዊ የጉምሩክ አሰራር ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። ከአህጉራዊ የንግድ ቀጣናው ጋር በተያያዘ የጉምሩክ እንቅስቃሴን ከማሳለጥ አንፃር ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ኢዜአ የጉምሩክ ኮሚሽንን አነጋግሯል። በጉምሩክ ኮሚሽን የታሪፍና ስሪት አገር ዳሬክተር ካሳዬ አየለ፤ ከአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር በተገናኘ የጉምሩክ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ዘመናዊ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል። የድንበር አስተዳደርና የካርጎ ፍተሻን ኤሌክትሮኒክ ማድረግ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትል ስርአት መዘርጋት ከሚጠቀሱት ዘመናዊ አሰራሮች መካከል ናቸው ብለዋል። በነጻ የንግድ ቀጣናው የዚህ አሰራር ተግባራዊ መሆን ደግሞ በእቃዎች መተላለፍና ግብይት ወቅት በቀላሉ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። በነጻ ንግድ ቀጣናው የሚነግዱ አባል አገራት የሚያቀርቡት ምርት በራሳቸው የተመረተ መሆን ስላለበት በነጻ የንግድ ቀጣና የስሪት አገር ህግ መሰረት የተመረተ መሆኑን ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካ ህብረት መጋቢት 2010 ዓ.ም በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ባደረገው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነበር የተፈረመው። በስምምነቱ መሰረት በመላው አፍሪካ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ምርት ድርሻ እንደሚኖረው ይገመታል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ከዓለም ንግድ ድርጅት ቀጥሎ በርካታ ሀገራት የፈረሙት ሁለተኛው ግዙፍ የንግድ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል።  
ማስታወቂያ
ኢዜአ
Feb 7, 2023 18509
ኢዜአ
ፖለቲካ
በሀረሪ ክልል የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል - ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
May 19, 2024 69
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በቀጣይ ወራት በሚከናወኑ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች በሚመለከት እንደተናገሩት በክልሉ በየዘርፉ እየተሰሩ የሚገኙ አበረታች ስራዎችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በዋናነትም ብቁ፣ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን በመገንባት የመንግስት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በልዩ ትኩረት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል። ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ከማጠናቀቅ አንፃርም ባለፉት ወራት የተከናወኑ አበረታች ስራዎች ማጠናከር እንዲሁም የተጀመሩ የቱሪዝም ልማት ስራዎች እንዲጠናከሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። የሌማት ትሩፋት፣ የከተማ ግብርና ስራዎችን ማጠናከር እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችም የላቀ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል። እንዲሁም ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ላይ የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ርእሰ መስተዳድሩ በተለይም የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር የተጀመረውን ስራ የማጠናከር እና ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድን ስርአት የማስያዝ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ የማስቀጠል እና የማዕድን ሀብትን በአግባቡ የማስተዳደር ስራ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የከተማ ጽዳትና ውበት ስራን የማጠናከር እንዲሁም ለእግረኛ መንገድ አገልግሎት እንዲውሉ ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን ለእግረኛ ምቹ የማድረግ ስራም ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል። ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍና ብልሹ አሰራር የመከላከል እንዲሁም የመንግስት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያን ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል። የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍም በጥናት የተደገፈ ስራ እንደሚሰራ ጠቅሰው የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች እንደሚጠናከሩ ነው የገለፁት። ሕብረብሔራዊ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነትን እና አንድነትን በማፅናት የክልሉን ሰላም የማስጠበቅ ስራም በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል። ዘንድሮ በሀረር ከተማ የማከበረው 26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል - ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶ
May 18, 2024 86
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል እየተሰሩ ባሉ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ዙሪያ የምክር ቤት አመራሮች፣ የባለስልጣኑ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቢሾፍቱ ውይይት አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶ፤ መገናኛ ብዙኃን ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ፣ለህዝብ ተጠቃሚነትና ለልማት መሳካት ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል። በሀገራዊ ለውጡ የዴሞክራሲ ምህዳሩን የማስፋት እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ነጻነት የማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። አሳሪ የነበሩ ሕጎችን ከመለወጥ አንጻር በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸው፤ በዚህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ፣ የፀረ-ሽብር አዋጅ እና የሲቪል ማኅበራትን አዋጅ ለአብነት ጠቁመዋል። በሀገሪቱ የሚዲያ ነፃነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ዘርፉን በሕግና በእውቀት ለመምራት የተለያዩ ሕጎች ወጥተው ተግባራዊ መደረጋቸውንም ጠቁመዋል። መገናኛ ብዙኃን የሕዝብንና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ መስራት እንደሚገባቸው የገለጹት ምክትል አፈ ጉባኤዋ፥ ከሀገር ጥቅም በተጻረረ መልኩ የሚሰሩትን በሕጋዊ መንገድ ማረም እንደሚገባ አሳስበዋል። የሕዝብንና የሀገርን ደኅንነት ለማረጋገጥ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ወጥቶ ተግባራዊ መደረጉንም ጠቁመዋል። የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት አዋጅን አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።   በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የአቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ ኤደን አማረ፤ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚደረግ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ ሀገራዊ የጥናት ሪፖርት አቅርበዋል። በጥናቱ መሠረትም የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በማንሳት፥ ድርጊቱን ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በመድረኩ የተሳተፉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፤ ባለስልጣኑ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል የጀመረውን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡   በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ የሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዜጎች መረጃዎችን በነፃነት የማግኘት መብት አላቸው ብለዋል፡፡ ሆኖም መረጃዎችን የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ ማሠራጨት እና መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡   የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እጸገነት መንግስቱ በበኩላቸው፤ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል የሚረዱ ደንቦችን በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡   በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማሕዲ (ዶ/ር) የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን መከላከል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡ ድርጊቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሀገር በቀል መተግበሪያዎችን ጭምር እስከማዘጋጀት ሊታሰብበት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡   የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው፤ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን መከላከል ለነገው ትውልድ ሰላም የሰፈነባት ሀገር የማስረከብ አካል ነው ብለዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ጨምሮ እርምጃ እስከመውሰድ ድረስ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።      
ታዋቂ ግለሰቦች ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም ለቀጣናው ሰላም መረጋገጥ ገንቢ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል - ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር)
May 18, 2024 81
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ ታዋቂ ግለሰቦች ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ። ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢጋድ የታዋቂ ግለሰቦች ምክር ቤት ስብስባ ዛሬ ተጠናቋል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ፤ የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች በማኅበረሰብ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል። ግለሰቦቹ በማኅበረሰብ ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም እንዳላቸውም ተናግረዋል። ምክር ቤቱ ኢጋድ በሰላም፣ መረጋጋት፣ ቀጣናዊ ትስስር፣ ሕገ-ወጥ ስደትና የድንበር ጉዳዮች ላይ እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን እንዲደግፍ መቋቋሙን አመልክተዋል። ከአንድ ዓመት በፊት ምክር ቤቱ ቢቋቋምም የሚጠበቅበትን ያህል አልሰራም ያሉት ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በስብሰባው የምክር ቤቱን የመፈጸም አቅም ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከሩን ገልፀዋል። በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር በርካታ ሥራዎች ቢከናወኑም አሁንም ብዙ ሥራ እንደሚቀርና ከዚህም አንጻር የምክር ቤቱ ሚናና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው የተናገሩት። ታዋቂ ግለሰቦች ያላቸውን አቅምና በማኅበረሰብ ላይ መፍጠር የሚችሉትን ተጽዕኖ በመጠቀም ሚናቸውን በሚገባ እንዲወጡና ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። ቀጣናው ግጭትን ጨምሮ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ ቢሆንም ለችግሮቹ የማይበገር ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ አመልክተዋል። የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የምክር ቤቱ መቋቋም በግጭትና አለመግባባት ከፍተኛ ጉዳት ላስተናገደው ቀጣናው በጎ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።   የኢጋድ ራዕይ የሆኑት ሰላም፣ ብልጽግናና ቀጣናዊ ትስስር እውን እንዲሆኑ የታዋቂ ግለሰቦችና የአገር ሽማግሌዎች ጉዳይ ቁልፍ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ምክር ቤቱ ለሚያደርጋቸው ሁሉን አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።   የኢጋድ ታዋቂ ግለሰቦች ምክር ቤት ሊቀመንበር ጆን አያቤ ሴ ምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ጸጥታን ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች እንዳሉበት ገልጸው፤ ምክር ቤቱ በቀጣናው ያሉ ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው አንስተዋል። ምክር ቤቱ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት አበክሮ በመሥራት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ እንደሚወጣ ገልፀዋል። የኢጋድ ታዋቂ ግለሰቦች ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አፍሪካውያን ችግሮቻችንን ለመፍታት ወደ ውጭ መመልከት የለብንም ያለ ሲሆን፤ በራሳችን አቅም ለሚገጥሙን ፈተናዎች መፍትሔ ማበጀት አለብን ሲል ገልጿል። ለዚህም አገር በቀል የግጭት አፈታት ሥርዓቶቻችንን መጠቀም እንደሚገባና የአገር ሽማግሌዎችም ከዚህ አኳያ ወሳኙን ሚና እንደሚወጡ ተናግሯል። ምክር ቤቱ ዛሬ ስብሰባውን በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ያደረገ ሲሆን፤ ትናንት የቴክኒክ ስብሰባውን አካሂዷል። ባለፈው ዓመት በተቋቋመው የኢጋድ የታዋቂ ግለሰቦች ምክር ቤት ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ዩጋንዳ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው።  
ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን ለመፍታትና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ለስኬታማነቱ እንሰራለን--የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች 
May 18, 2024 84
ሀዋሳ/ሚዛን ግንቦት 9/2016 (ኢዜአ)-ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን ለመፍታትና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የበኩላችንን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። በሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት፣ የኮሚሽኑ ሥራ ዘመናትን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ነው። ለዘመናት ሳይፈቱ የቆዩ የህዝብ ቅራኔዎችን በመፍታት ለሀገር ዘላቂ ሰላም ግንባታ የጎላ ፋይዳ ስላለው ለስኬቱ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። የኢትዮዽያ የቃል ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንትና የሲዳማ ክልል የሀገር ሽማግሌ መጋቤ ጢሞቲዎስ በራሳ እንደገለጹት፤ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም የሚያሳትፍ በመሆኑ ያደሩ ቁርሾዎችንና የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት ያስችላል። እስከዛሬ ሁሉንም ያካተተ ምክክር ባለመደረጉ ለዘመናት የቆዩ ቅራኔዎች ከስር መሰረቱ እንዲፈቱ መንግሥት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አቋቁሞ ወደተግባራዊ ሥራ መግባቱን አመስግነዋል። ለምክክሩ ስኬታማነት የጋራ ጥረትና ቀና ልቦና እንደሚፈልግ ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ ሁሉንም በማሳተፍ የጀመረው ሥራ ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ለእዚህም ሀገራዊ ምክክር ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አብሮነት ያለውን ፋይዳ ለህብረተሰቡ በማስገንዘብ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። "በውይይትና በምክክር የማይፈታ ችግር የለም" ያሉት መጋቤ ጢሞቲዎስ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነት ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታትና ለሀገራዊ የልማት ጉዞን መፋጠን ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ሁሉም ለስኬታማነቱ እንዲረባረብ አስገንዝበዋል።   በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ብሩክ ባልቻ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፣ በምክክሩ ሁሉም አካል በሚወክለው እንዲሳተፍ መደረጉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ዕድል ይሰጣል። በተለይ እንደ አገር እየተስተዋሉ ላሉ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ስለሚያስችል ለኮሚሽኑ ሥራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። "የኮሚሽኑን ዓላማና ግብ በሚገባ በመረዳት እና ባህላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት ተሳትፏችንን ማሳደግ ይገባናል" ብለዋል። ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካታችነትና አሳታፊነት ዋና መርሁ መሆኑን ከመገናኛ ብዙሀን እንደተረዱ የገለጹት ወይዘሮ ብሩክ፣ "ሀገራዊ ምክክሩ ለሀገር የሚያመጣውን ብሩህ ተስፋ ለኅብረተሰቡ ማስገንዘብ ይገባል" ብለዋል። "ልሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መልካም እድል ይዞ መጥቷል" ያሉት ደግሞ በደቡብ ምእራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል የቤንች ሸኮ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ ቱሪ ኮዛ ናቸው። የምክክር ኮሚሽኑ ለሀገር ሰላምና አንድነትን ያመጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸው፤ "ለነገ ጠንካራና ሰላማዊ ሀገር ለመገንባት ሁሉም ከኮሚሽኑ ጎን መቆም አለበት" ብለዋል። "የሀገራዊ ኮሚሽን መቋቋም በራሱ በጎ ዕድል ነው" ያሉት አቶ ቱሪ፤ በዋና ዋና ሀገራዊ ችግሮች ላይ ተነጋግሮ መፍታት በዜጎች መካከል አንድነትን ለማጽናት አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።   በየአካባቢ ህብረተሰቡ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ቢኖረውም በአግባቡና በተደራጀ መንገድ ጥቅም ላይ ባለመዋሉ ለዘመናት ያልተፈቱ ቅራኔዎች እንዳሉ አስታውሰው፤ "አሁን የተፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ችግሮችን ለማስተካከል በጋራ መስራት አለብን" ብለዋል። በአካባቢያቸው የሚያውቁትን ሀገር በቀል የሰላም እሴቶች እና ባህሎችን በማስተዋወቅና ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለኮሚሽኑ ሥራ የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግሥት የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ምደባና ሽግሽግ መደረጉን ገለጸ
May 18, 2024 79
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልላዊ መንግሥት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የህዝብን ጥያቄ ለመመለስና የመፈፀም አቅምን ያገናዘበ የአመራር ሽግሽግ ማድረጉን አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የተደረገው የአመራር ሽግሽግ እና ምደባ በክልሉ የህዝቦች አብሮነትን ፣ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና አንድነትን ለማጎልበት ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የአመራር ሽግሽጉ በክልል ደረጃ አበረታች ስራዎች ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን በመቅረፍ በቀሪ የምርጫ ዘመን የመንግስትን ተልዕኮዎችን በተሻለ ደረጃ ለመፈፀም ያለመ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። በዚህም መሰረት፦ አቶ ሙክታር ሳሊህ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነጋዎ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢልያስ ዮኒስ የሀረር ከተማ ማዘጋጀ ቤት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዚነት ዩሱፍ የክልሉ ፕብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ነቢላ ማህዲ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ ዳይሬክተር ኮ/ር ረምዚ ሱልጣን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኢ/ር ፈርሃን ዚያድ የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ም/ሥራ አስከያጅ አቶ ዘከሪያ አብዱለዚዝ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሰልሃዲን አብዶሽ ደንብ ማከበር ጽ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር ማአሩፍ አብዲ ከተማ ልማት ፕላን ኢንስቲቲዩት ደ/ር አብዱልሐኪም ኢምራን አ/ወዱዱ ሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲን ምክትል ኮሚሽነር ጃብር አልዬ የመረጃ ዴስክ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድናን አህመድ የሚልሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማህቡብ ሼክ ያሲን በሀል ማዕከል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ለታ በዳዳ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ምክትል ኃላፊ አቶ ኸሊድ ኑሬ የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዳሳ ገመዳ ልቀት ማአከል ( coc ) ዳይሬክተር አቶ ሚልኬያስ አህመድ ህብራት ሥራ ማ/ማ/ማ/ኤጀንሲ ኃላፊ ኮ/ር ረምዚ ሱልጣን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ረመዳና ጀብሪል የወንጀል ምርመር ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አሰፋ ቶልቻ ሐረር ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጀ ዲን አሚር ኑር ወረዳ መስተዳድር አቶ ሼዙ መሀመድ ሴይፋላህ - ዋና አስተዳደሪ አቶ አብዲ አውል - ም/አስተዳደሪ አቶ አፈንዲ አህመድ - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ አባዲር ወረዳ መስተዳድር አቶ አብዱልመጂድ ጋቱር - ዋና አስተዳደሪ አቶ ከዲር አ/ረዘቅ - ም/አስተዳደሪ አቶ መሀመድ አብዲ -ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ጅንኤላ ወረዳ መስተዳድር አቶ ፈትሂ ሀሰን - ዋና አስተዳደሪ አቶ ታረቀኝ ጋሮሞ - ም/አስተዳደሪ አቶ አህመድ አብዱከሪም - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ሸንኮር ወረዳ አስተዳደር አቶ ሳሚ ዩሱፍ ተፈራ - ዋና አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ሰቢት - ም/አስተዳደሪ አቶ ፈራሀን ቶፊቅ - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ አቦከር ወረዳ መስተዳድር አቶ ሱልጣን ሳኒ - ዋና አስተዳደሪ አቶ ሰሚር ሙኽተር - ም/አስተዳደሪ አቶ አቤል አለማየው - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ሐኪም ወረዳ መስተዳድር አቶ ኢብሳ አልዬ - ዋና አስተዳደሪ አቶ መፍቱህ ሸምሱ - ም/አስተዳደሪ አቶ አባስ ዩሱፍ - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ሶፊ ወረዳ መስተዳድር አቶ አህመድ አልዬ - ዋና አስተዳደሪ አቶ ሰሚር አብዱለህ - ም/አስተዳደሪ አቶ ረመዳን አልዪ አሜ - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ድሬ ጠያራ ወረዳ መስተዳድር አቶ መሀመድ ጀማል - ዋና አስተዳደሪ ወ/ሮ ሲነት አብዶሸ - ም/አስተዳደሪ አቶ ያሀያ አ/ሰላም - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሀላፊ ኤረር ወረዳ መስተዳድር አቶ ፉርቃን ሙሳ - ዋና አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ጀማል - ም/አስተዳደሪ አቶ ዲኔ አብዱላ ደውድ - ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ሃላፊ በመሆን ተሹመዋል።      
በዞኑ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን-የካምባታ ዞን ወጣቶች
May 18, 2024 85
ዱራሜ ፤ግንቦት 10/2016 (ኢዜአ )፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በካምባታ ዞን የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ሲሉ የዞኑ ወጣቶች ተናገሩ። በክልሉ ሰላምና ልማት ዙሪያ በዱራሜ ከተማ የተደረገውን ህዝባዊ ውይይት የተሳተፉ ወጣቶች እንደገለፁት፤ በዞኑ እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ስራዎች ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ሂደቱን በማገዝ ረገድ የበኩላችንን እንወጣለን። በምክክሩ ወቅት አስተያየት የሰጠችው የዱራሜ ከተማ ነዋሪዋ ወጣት መሰረት ወሌቦ በዞኑ አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎች በአካባቢው መነቃቃትን እየፈጠሩ ነው ብላለች። የህብረተሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት አኳያ እየተገነቡ የሚገኙ የመንገድና መሰል የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሆን እንደሚደግፉ ተናግራለች። በአካባቢው ለወጣቱ የስራ እድልን ለማመቻቸት የሚረዱ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመልካም ሁኔታ እየተከናወኑ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው ያለው ደግሞ የቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ነዋሪው ወጣት ሰንበቱ አወል ነው። በዞኑ እየታዩ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች ህዝቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ከአስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብሏል። ሆኖም በወረዳው እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ የንፁህ ውሃና የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነት ችግሮች የዞኑ ልማት እንዳይፋጠን እንቅፋት ሊሆኑ ስለሚችሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባም አንስቷል። በወረዳው ሲንከባለሉ የመጡ የመልማትና የእኩል ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች አሁን ላይ መመለስ መጀመራቸውን ያነሳው ደግሞ የአንገጫ ወረዳ ነዋሪው ወጣት በላቸው ወልዴ ነው። ''እነዚህም የልማት ስራዎች በርካቶችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሶ እንዲጠናከሩ በሀሳብና በጉልበት እናግዛለን'' ብሏል። ይሁን እንጂ በአካባቢው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተደራሽ አለመሆን የስራ ፈጠራን ከማጎልበት አኳያ ውስንነት እንዲኖር በማድረጉ ሊታሰብበት እንደሚገባም ጠቁሟል።   የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ዳዊት ለገሰ በበኩላቸው አስተዳደሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን አሳታፊ በሆነ መልኩ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ''እንደ ዞን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የልማት ዘርፎች እየታየ ያለው ከፍተኛ የሆነ መነቃቃትና ስኬት ህዝብና መንግስት በተቀናጀ መንገድ እያደረጉት ያለው ጥረት ውጤት ነው'' ብለዋል። የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅና አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ሁሉ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ የወጣቱ ሀይል እያደረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ ማጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል። የዞኑ አስተዳደር የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት አበክሮ እንደሚሰራም ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።  
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  የልማት ጥያቄዎችን  መመለስ ዋነኛ ትኩረት ሆኖ  ቀጥሏል - ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሀሰን 
May 18, 2024 74
አሶሳ ፤ ግንቦት 10 /2016 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች መመለስ ዋነኛ ትኩረት ሆኖ መቀጠሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን አስታወቁ፡፡ በክልሉ በ400 ሚሊዮን ብር ለሚካሄድ የመንገድ ግንባታ ዛሬ የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱ የልማት ተግባራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ አድርገዋል። አሁንም መሠረተ ልማት ያልተሟላቸው አካባቢዎች እንዳሉ መንግስት በሚገባ ይረዳል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ዛሬ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት አካባቢ አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በተለይም በክልሉ የተፈጥሮ ሀብት በስፋት የሚገኝባቸው አካባቢዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስ አሁንም የክልሉ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ እንደሚቀጥል አቶ አሻድሊ አስታውቀዋል።   ዛሬ ግንባታ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠለት መንገድ ስራው ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን ለእርሻ ኢንቨስትመንት የሚውል ሰፊ ለም መሬት ፣ወርቅና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶችን በበለጠ የማልማት አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል። ግንባታ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠለት በአብራሞ እና ኡራ ወረዳዎች መካከል የሚገኙ አራት ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር መንገድ መሆኑን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚኖረው የመንገዱ ግንባታ በአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ለማጠናቀቅ መታቀዱንና ለማስፈጸሚያው 400 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተመልክቷል። በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንና በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ መሳ አህመድን ጨምሮ ሌሎችም የአመራር አባላትና የአካባቢው ነዋሪዎችም ተገኝተዋል፡፡  
የኢትዮጵያና ታንዛንያን ሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት ይሰራል
May 18, 2024 104
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና ታንዛንያን ሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሁለቱም ወገን በኩል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በታንዛንያ ዋና ከተማ ዶዶማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዲስ ሕንፃ ግንባታ መሠረተ-ድንጋይ አኑረዋል። በታንዛኒያ አዲስ ለሚገነባው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት የታንዛኒያ ፓርላማ አባላትን ጨምሮ የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ምክትል ሚኒስትር፣ የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ማባሩክ ናሶር ማባሩክ፣ በታንዛኒያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሽብሩ ማሞ፣ የዶዶማ ክልል አስተዳደር፣ የዶዶማ ከተማ ከንቲባና ሌሎች በርካታ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት በተገኙበት ተከናውኗል ።   ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ከታንዛንያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። አምባሳደር ብርቱካን ከታንዛንያ አቻቸው አምባሳደር ማባሩክ ናሶር ማባሩክ ጋር በታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዚህ ወቅትም የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በማንሳት ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሁለቱም ወገን በኩል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ከመግባባት ላይ ተደርሷል። በተለይም በኢኮኖሚው ረገድ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ ሀገራቱ በከፍተኛ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። አምባሳደር ብርቱካን የታንዛንያ የኢሚግሬሽን ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሆኑት ዶክተር አና ማካካላ ጋር ውይይት ማካሄዳቸውንና ለኢትዮጵያዊያን በታንዛንያ የመዳረሻ ቪዛ መፈቀዱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አውስተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ወደ ተለያዩ መዳረሻ አገራት ለሚደረግ ህገወጥ ፍልሰት የታንዛንያን ድንበር አቋርጠው በመግባታቸው ምክንያት በጸጥታ አካላት ተይዘው በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የታንዛኒያ መንግሥት በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ የኢሚግሬሽን ኮሚሽነሯ አረጋግጠዋል ።          

ማህበራዊ
ፕሮፌሰር አስፋው አጥናፉ አረፉ
May 19, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምና ትምሕርት ቤት የራዲዮሎጂ ትምሕርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ፕሮፌሰር አስፋው አጥናፉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዓርብ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም አርፈዋል፡፡ ፕሮፌሰር አስፋው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋከልቲ፣ የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ1976 ዓ.ም አግኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ ሐኪምነት አሰብ ሆስፒታል ካገለገሉ በኋላ በራዲዮሎጂ ስፔሽያሊቲ ትምህርት ከመጀመሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች አንዱ በመሆን በ1981 ዓ.ም ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ እንዲሁም በ2006 ዓ.ም በቦዲ ኢሜጂንግ ሰብ ሰፔሺያልቲ ፕሮግራም ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ተመራቂዎች መካከል አንዱ በመሆን አጠናቀዋል፡፡ በሰላሳ አምስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ የአገልግሎት ዘመናቸው ብዙ ኃላፊነቶችን ተወጥተዋል፡፡ ለአራት ተርም በራዲዮሎጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትበብር በመፍጠር በትምህርት ከፍሉ የተለያዩ የሰብ ሰፔሻልቲ ትምህርቶች እንዲጀመሩ አድርገዋል፡፡ የራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ትምህርት በባችለር ዲግሪ እንዲሰጥ በማስቻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርከተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ የቴሌ ሜዲስን ዩኒት፣ በቀጣይም የኢ-ሄልዝ ማዕከል እንዲቋቋም ያደረጉ ሲሆን በኃላፊነት ደረጃም ሰርተዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ራዲዮሎጂ ማሕበርን ለመመሥረት ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ከመስራቾቹ አንዱ በመሆን የመጀመሪያ የማሕበሩ ፕሬዚደንት ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሰላሳ አምስት በላይ የጥናት ጽሑፎችን ያሳተሙ ሲሆን ባደረጓቸው ጥናቶች በማስተማር፣ በጤና አገልግሎት፣ በማሕበረሰብ አገልግሎት እና በአጠቃላይ በዩኒቨርስቲው ሆነ በሐገር፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በ2010 ዓ.ም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም፣ የተለየያዩ አገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡ ፕሮፌሰር አስፋው ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም ሰኞ፣ ግንቦት 12 ቀን 2016 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በመካኒሳ አቦ ቤተ ክርስቲያን መሆኑን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የወጣቶች ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዘላቂ ሠላምን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
May 19, 2024 67
ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ የወጣቶች ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ማህበራዊ ትስስርን በማሳደግ ዘላቂ ሠላምን ለመገንባት የጎላ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የሠላም ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 10ኛው ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና ዛሬ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀምሯል። በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ በሚኒስቴሩ የወጣቶች ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቺስ ኢቲቻ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ብሔራዊ የበጎ ፍቃድ ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው። ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠርና ሀገራዊ እንድነት የማስፈን፣ የፌዴራል ሥርዓቱን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ ግጭቶችን የማስተዳደር እና ቀጠናዊና አህጉራዊ ትብብርን የማጎልበት ተልዕኮውን እየተወጣ መሆኑንም ገልጸዋል። ለዚህም ከ2013 በጀት ዓመት ጀምሮ ለተከታታይ ዘጠኝ ዙር በርካታ ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊዎችን ማሰልጠኑን ጠቁመዋል። ወጣቶቹ በተለያዩ ክልሎች ተሰማርተው ባከናወኗቸው የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱንም ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ማህበራዊ ትስስርን ከማሳደግ፣ ብሔራዊ መግባባት ከመፍጠርና ዘላቂ ሠላምን ከመገንባት አኳያ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ መሆኑንም አስረድተዋል። "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሐሳብ በሚኒስቴሩ የተጀመረው የወጣቶች ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት መርሀ ግብር ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ ነው። መርሃ ግብሩ የወጣቶችን የሀገርና የሕዝብ ፍቅርን ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑንም አቶ ገመቺስ ገልጸዋል። በጎነት ለአብሮነት በሚል ማዕቀፍ የሚሰጠው ስልጠና ባህልን ከመለዋወጥ ባለፈ ለሀገር እሴቶች ትኩረት ስለሚሰጥ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ጂሎ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በሀገሪቱ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ ተግባር ወጣቶች ማህበራዊ እሴቶችን እንዲያዳብሩ ፋይዳው የጎላ ነው። ይህም በሀገር ዘላቂ የሰላም ግንባታ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ከማድረግ በላይ እርስ በእርስ ያላቸውን ማህበራዊ ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ያስችላል ነው ያሉት። በክህሎት፣ በሥነ ምግባር እና በሥራ ፈጠራ ራሳቸውን እንዲያጎለብቱ በማድረግ በኩልም ሚናው የጎላ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በመሆኑም ወጣቶች በበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ መሳተፍ የህሊናና የመንፈስ እርካታ እንደሚያጎናጽፍ አውቀው፣ በዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ መግባባት ሥራዎች ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ አሳስበዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር በሚቆየው ስልጠና ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ከ2ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው። ስልጠናው የወጣቶችን ክህሎት፣ ሥነ ምግባር፣ አመለካከት፣ የአካል ብቃት፣ የሞራል ግንባታ የሚያካትት እንዲሁም አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት እንዲገነዘብ በማድረግ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
May 19, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ መንጌ ወረዳ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የካሻፍ ቱመት መንገዱል ጤና ጣቢያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በዚህ ወቅት አቶ አሻድሊ ሀሰን ባለፉት ዓመታት በክልሉ በጤናው ዘርፍ ጤናማ እና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል። በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋዩ የተቀመጠው ጤና ጣቢያ በአዲሱ የጤና ፖሊሲ ስታንዳርድ መሰረት የሚገነባ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። መንግስት መድረስ ባልቻለባቸው አካባቢዎች ስትራቴጂክ የልማት ተግባራትን እያከናወነ ለሚገኘው ለክልሉ ቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምስጋና አቅርበዋል። የመንጌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም መንሱር፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች እየመለሰ ይገኛል ብለዋል። በወረዳው ያለውን የጤና ሽፋን ለማሳደግ እና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የግንባታው መጀመር ድርሻው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። የጤና ጣቢያው ግንባታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል። የጤና ጣቢያው ግንባታ ከ6 ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው ሲጠናቀቅም ከ30ሺህ በላይ የአካባቢውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የአካባቢው የህብረተሰብ ክፍሎችም በጤና ጣቢያው ግንባታ መጀመር እንደተደሰቱ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አስረኛው ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ 
May 19, 2024 76
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በሰላም ሚኒስቴር የተዘጋጀው 10ኛው ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ተጀመረ። "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሀሳብ ለአንድ ወር የሚሰጠውን ስልጠና ሚኒስቴሩ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑም ተመላክቷል። በስልጠናው ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ከ2ሺህ በላይ ወጣቶቾ እየተሳተፉ መሆኑን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ጀማል ለኢዜአ ገልጸዋል። ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማሕበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ዋና ዓላማ ለወጣቶች የሀገርና የሕዝብ ፍቅርን ከማላበስ ባለፈ ምክንያታዊ እንዲሆኑና የሕይወት መምራት ክሕሎታቸውን ማሳዳግ መሆኑን ጠቁመዋል።   ከእዚህ በተጨማሪ የሥራ ባሕልን፣ ሥነ ምግባር እና የሰላም እሴትን በማጎልበት አገራዊ አንድነትን፣ ብሔራዊ መግባባትን እና ጥልቅ ማሕበራዊ ትስስርን የማስፈን ዓላማ እንዳለው አስረድተዋል። ፕሮግራሙ ለአገራዊ እንድነትና ዘላቂ ሰላም ግንባታ መሳካት ሚናው የጎላ መሆኑንም አቶ ደረጄ ተናግረዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ስለጠናው ውጤታማ እንዲሆን ሚኒስቴሩ በየስልጠና ማዕከሉ ከፍተኛ ባለሙያ በመመደብ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል። የሰላም ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት በዘጠኝ ዙሮች ከ49 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሰልጠን አሰማርቷል። ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ስልጠና ማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ የሚኒስቴሩና የኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።  
ኢኮኖሚ
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 
May 19, 2024 80
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባውን የሸይካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መርቀው ከፍተዋል። ትምህርት ቤቱ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሸክ መሃመድ ቢን ዛይድ እናት ሸይካ ፋጢማ ድጋፍ በአዲስ አበባ የተገነባ ነው። ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምር ሲሆን ለአይነ ስውራን ምቹ የሆኑ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች ላይብረሪና ሌሎችም ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን የያዘ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም 34 ትምህርት ቤቶችን አስገንብቶ አገልግሎት ማስጀመሩን ተናግረዋል።   ትምህርት ቤቶቹ በዋናነት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ መሆኑንም አንስተዋል። ዛሬ ለምረቃ የበቃው አዳሪ ትምህርት ቤቱም እጅግ ዘመናዊና በአይነቱ ልዩ መሆኑን ጠቅሰው ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ ከ300 በላይ አይነ ስውራን ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል ብለዋል። መንግስት በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህ ስራም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በበኩላቸው፣ በጽህፈት ቤቱ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን የኑሮ ጫና ማቃለልን ታሳቢ ያዳረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።   ሸይካ ፋጢማን ጨምሮ የአዳሪ ትምህርት ቤቱ እንዲገነባ ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። ሸይካ ፋጢማን ወክለው ንግግር ያደረጉትና በሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ የሂዪማንቲ ትምህርት ክፍል ቻንስለር የሆኑት ዶክተር ካሊፋ ሙባረክ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን ገልጸዋል።   የአገራቱ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየሰፋ መሆኑን ጠቅሰው፣ አዳሪ ትምህርት ቤቱም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ እኤአ በ2018 ኢትዮጵያን ከጎበኙ ወዲህ የአገራቱ ግንኙነት ይበልጥ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ መነጽሮችን ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ አዳሪ ትምህርት ቤቱንም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረክበዋል።
በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትሉ ይጠናከራል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
May 19, 2024 62
ሚዛን አማን፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ። በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራና የዞንና የክልል የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን በፌዴራል መንግስት ድጋፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በእዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ በፌዴራል መንግስት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የክልሉን የልማት ተስፋ ያሳደጉ ናቸው። በግንባታ ሂደት ላይ ያለው የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የደንቢ ሎጅ ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች መካከል እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል። ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ በክልሉ መንግስት የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ሥራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገንባታ 62 በመቶ ላይ መድረሱን የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ የሚቀሩ ሥራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ የግንባታ ሥራው የተጀመረውና የገበታ ለትውልድ አካል የሆነው የደንቢ ሎጅ የግንባታ ሂደት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፣ የሎጁ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በቀጣይ አምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት ይሆናል። የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያን እየገነባ ያለው የ"ሳምሶን ቸርነት ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭ" ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኢዮብ ሞላ በበኩላቸው ግንባታውን ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለመጨረስ እየተሠራ ነው ብለዋል። የአየር ማረፊያው ግንባታ የህዝብ የልማት ጥያቄ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠውና ግንባታውን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ግብአቶች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠው ወደ ሥራ መገባቱ ይታወቃል።  
በጋምቤላ ክልል የማዕድን ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ረገድ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል - ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ 
May 19, 2024 68
ጋምቤላ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የማዕድን ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ሀብቱን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ። በክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የማዕድን ሀብት ልማት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ የምክክር መድረክ ዛሬ በማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ተካሂዷል። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት ከወሰዳቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎረሞች መካከል የማዕድን ሀብት ልማት አንዱና ዋነኛው ነው። ክልሉም ያለውን የማዕድን ሀብት በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም በወርቅ ማዕድን ላይ ከልማቱ አንስቶ በዝውውሩ ላይ የሚስተዋሉ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ሀብቱን በአግባቡ ለማልማት የተጀመረው ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የማዕድን ዘርፍ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቴንኩዌይ ጆክ በበኩላቸው፤ በክልሉ ሰፊ የማዕድን ሀብት ቢኖርም በሚፈለገው መጠን አልምቶ ከመጠቀም አንፃር ውስንነቶች አሉ ነው ያሉት።   በመሆኑም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የማዕድን ሃብት ልማትን በማጠናከር ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚኖረውን አስተዋፅኦ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል። በተለይም በማዕድን ሀብት ልማቱ ላይ ከክልል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ያለውን አደረጃጀት ወጥ በማድረግ ሀብቱን ከብክነት ለመታደግ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አኳታ ቻም የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳሉት፤ የክልሉን የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለማልማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።   በስራ ዘመኑ የኮንስትራክሽን ማዕድን ሀብት ልማት ላይ ለመሰማራት ፍቃድ ለሚጠይቁ ባለሃብቶች ፈቃድ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑም አመላክተዋል። የማዕድን ሀብቱን ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ለመታደግ እንደ ክልል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል። በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በተዘረጋው የህግ አስከባሪዎች አደረጃጀት አማካኝነት 50 ግለሰቦች ህገ-ወጥ የወርቅ ዝውውር ላይ ሲሳተፉ ተገኝተው በህግ እንዲጠየቁ መደረጉን በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል። በቀጣይ በወርቅ አምራች ወረዳዎች የተጀመረውን የቁጥጥርና የክትትል ስራዎች በማጠናከር ሀብቱን በህጋዊ መንገድ ለማልማት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከር አቅጣጫ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል። በምክክር መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።  
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በአዲስ የስራ ባህል በተቀናጀና በተፋጠነ መልኩ እንደቀጠለ ነው
May 19, 2024 119
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በአዲስ የስራ ባህል በተቀናጀና በተፋጠነ መልኩ መቀጠሉን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የከተማዋ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ ገለጹ። የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንትና በተለይም የቱሪዝም እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ ይታወቃ። በመሆኑም የፕሮጀክቱን ክንውን ክረምቱ ሳይገባ ለማገባደድ ይቻል ዘንድ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳድሩ አስታውቋል። በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክሕሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ፤ በአምስት አቅጣጫዎች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት በተቀናጀና በተፋጠነ መልኩ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፕሮጀክቱ ክንውን አዲስ የስራ ባህል የተፈጠረበት ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው በሁሉም አቅጣጫዎች በተቀናጀና በተቀላጠፈ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል። የልማት ስራን ሌት ከቀን በማከናወን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን እንደሚቻል አዲስ ልምድ የተቀመረበት መሆኑንም ጠቅሰዋል። ከቦሌ መገናኛ ሲኤም ሲ የኮሪደር ልማት ንኡስ ኮሚቴ አስተባባሪ ዶክተር ኤፍሬም ግዛው፤ የኮሪደር ልማቱ የስራ እድል ብቻ ሳይሆን የስራ ባሕልና አስተሳሰብንም የቀየረ ነው ብለዋል።   መንግስት ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ ገንዘብ በመበጀትና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሕዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የመገናኛ ሲኤም ሲ ፕሮጀክት አስተባባሪ ከማል ጀማል፤ የኮሪደር ልማቱ በቅንጅታዊ አሰራር በፍጥነት ከማከናወን ባለፈ የስራ ባሕልን የቀየረ መሆኑን ገልጸዋል።   የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ከ4 ኪሎ ፒያሳና የአድዋ ድል መታሰቢያ፤፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ እስከ መገናኛ ይዘልቃል። ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ እንዲሁም ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ እና በመገናኛ እስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚያካልል መሆኑ ይታወቃል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የምትሆንበት የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ ምርምሮች እየተደረጉ ነው
May 19, 2024 51
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ የምትሆንበት የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ የምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) "ሳይንስ በር ይከፍታል ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል" በሚል መሪ ሃሳብ ከግንቦት 10 እስከ 18 ቀን 2016 የሚከናወነውን ስትራይድ ኢትዮጵያ ዓመታዊ ኤክስፖ ትናንት ከፍተዋል፡፡ ኤክስፖው በአይ ሲ ቲ ዘርፍ ትልቅና ተስፋ ሰጭ ጅምር የታየበት መሆኑን ገልጸው፤ ሁነቱ ለቴክኖሎጂ ፈጠራና እድገት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚገልጽ፣ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ዘመን በምታደርገው ጉዞ ያላትን አቅምና ምኞት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ትኩረቱን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን ላይ ያደረገ ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024 ኤክስፖ በሳይንስ ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ እንዳሉት፤ የስትራይድ ዓመታዊ ኤክስፖ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ፣ ትብብርና ፈጠራ እንዲሁም የፈጠራ ባህል ግንባታን የሚያጠናክር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በሳይንስ ቴክኖሎጂ ፈጠራና ዲጂታላይዜሽን የደረሰችበትን እድገት ከማሳየት ባለፈ በቀጣይ በዘርፉ ላላት ተቀባይነት ምቹ ምህዳር ይፈጥራል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዘርፉ ጥናትና ምርምር በማድረግ መድሃኒት አምርታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንድትችል በር በመክፈት በራስ መተማመን መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፈጠራ ውጤቶችን ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ገቢራዊ በማድረግ የኢ ኮሜርስ፣ ስታርትአፕ እና መሰል ተግባራት እንዲዳብሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በቴክኖሎጂ ሰውና ሀሳቡ ተገናኝተዋል ያሉት ዶክተር ባይሳ፤ የሳይንስን መሰረታዊ እውቀት መገንዘብ ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከዋሉ የጥናት ውጤቶች በተጨማሪ ከሌሎች ዓለም ሀገራት ጋር መወዳደር የሚያስችሉ የቀጣዩን ዘመን ታሳቢ ያደረጉ ምርምሮች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም ስራ ላይ ለማዋል የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው፤ በዚህም በዘርፉ ለወጣቶች ዘላቂ የሥራ እድል በመፍጠርና የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት በመስጠት ብዙ ርቀት መጓዙን ተናግረዋል፡፡
ለአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ቀልጣፋና ዘመናዊ የጉምሩክ አሰራር ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ ነው
May 19, 2024 97
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ለአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋና ዘመናዊ የጉምሩክ አሰራር ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ጠንካራ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። ከአህጉራዊ የንግድ ቀጣናው ጋር በተያያዘ የጉምሩክ እንቅስቃሴን ከማሳለጥ አንፃር ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ኢዜአ የጉምሩክ ኮሚሽንን አነጋግሯል። በጉምሩክ ኮሚሽን የታሪፍና ስሪት አገር ዳሬክተር ካሳዬ አየለ፤ ከአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር በተገናኘ የጉምሩክ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ዘመናዊ አሰራር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል። የድንበር አስተዳደርና የካርጎ ፍተሻን ኤሌክትሮኒክ ማድረግ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትል ስርአት መዘርጋት ከሚጠቀሱት ዘመናዊ አሰራሮች መካከል ናቸው ብለዋል። በነጻ የንግድ ቀጣናው የዚህ አሰራር ተግባራዊ መሆን ደግሞ በእቃዎች መተላለፍና ግብይት ወቅት በቀላሉ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል። በነጻ ንግድ ቀጣናው የሚነግዱ አባል አገራት የሚያቀርቡት ምርት በራሳቸው የተመረተ መሆን ስላለበት በነጻ የንግድ ቀጣና የስሪት አገር ህግ መሰረት የተመረተ መሆኑን ማረጋገጫ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካ ህብረት መጋቢት 2010 ዓ.ም በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ባደረገው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነበር የተፈረመው። በስምምነቱ መሰረት በመላው አፍሪካ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ዓመታዊ ምርት ድርሻ እንደሚኖረው ይገመታል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ከዓለም ንግድ ድርጅት ቀጥሎ በርካታ ሀገራት የፈረሙት ሁለተኛው ግዙፍ የንግድ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል።  
በኦሮሚያ ክልል ችግር ፈች የፈጠራ ውጤቶች እንዲበራከቱ እየተሰራ ነው - የክልሉ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ
May 19, 2024 78
አዳማ ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፡- የፈጠራ ውጤቶች የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እንዲያስችሉ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ። በኦሮሚያ ክልል የተሻለ የንግድ ሃሳቦችና የፈጠራ ባለቤቶች በማቅረብ በውድድር ላሸነፉ ወጣቶች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የክልሉ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ኤባ ገርባ እንደገለፁት አዳዲስ የንግድ ሃሳቦችና የፈጠራ ባለቤቶችን በተገቢው መንገድ ድጋፍ ማድረግ ሲቻል ሀገሪቷ ከውጭ በሚገባ ንግድና ቴክኖሊጂ ጥገኛ አትሆንም ብለዋል። ይህን ታሪክ ለመቀየርም አዳዲስ የንግድ ሃሳቦች የያዙ ኢንተርፕሩነሮችና የፈጠራ ባለቤቶችን መደገፍና ማበረታታት ላይ የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በተለይም በክህሎት የዳበሩ ኢንተርፕሩነሮች በብዛትና በጥራት ለማፍራት፣ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችና ውጤቶችን የማበልፀግ ስራ ላይ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል። በዚህም ከቀበሌ ጀምሮ አዳዲስ የንግድ ሃሳቦችና የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን ወጣቶችና ሴቶች በመለየት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ተጨማሪ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። የቢሮው ምክትል ሃለፊ አቶ ሀብታሙ ካሣ በበኩላቸው ብሩህ ኢትዮጵያ በሚል ከኮሌጆች ጀምሮ መጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጭምር የተሻለ አዳዲስ የንግድ ሃሳቦችና የፈጠራ ቴክኖሎጂ ባለቤቶችን በመምረጥና በማወዳደር የተሻለ ሆኖ ለተገኙት እውቅና መሰጠቱን ተናግረዋል።   በተለይም ወደ ተግባር በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚቀየሩ አዳዲስ ሃሳቦችና የፈጠራ ውጤቶች ማህበረሰቡ ዘንድ ደርሰው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዲፈቱ ብሎም በሀገር ልማትና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸው ነው ብለዋል። በዚህም በግብርና፣ አይሲቲ፣ በዲጂታል ንግድ፣ በማኑፋክቸሪንግና በኢንዱስትሪ የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን የማበልፀግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነትም ጥሬ ስንዴን በቀላሉ በቤተሰብ ደረጃ ፕሮሰስ ለማድረግ፣ የዶሮ መኖ ማቀነባበሪያ፣ የሻይ ቅጠልና ሩዝ ማቀናበበሪያ እንዲሁም የኦክስጂን ማምረቻ ማሽኖች የማበልፀግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምሮ ገልጸዋል። የኦክስጂን ማምረቻ ማሽን በመፍጠር ለውድድር ቀርቦ ያሸነፈው ተማሪ ኢብሳ ታምሩ እንደገለፀው በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የጤና ተቋማት የኦክስጂን ማምረቻ ማሽን እጥረት መኖሩን ጠቅሶ ይሄን ችግር ለመፍታት ማሽኑን መፍጠሩን ተናግረዋል። በዚህም ቴክኖሎጂውን ለሆስፒታሎችና ለጤና ጣቢያዎች በቀላል ዋጋ ከማቅረብ ባለፈ ከውጭ የሚገባውን የኦክስጂን ማምረቻ ማሽን በሀገር ውስጥ ለመተካት ነው ብለዋል። ከደምቢ ዶሎ የመጣው ተማሪ ቢቂላ ተሾመ በበኩሉ በሆቴሎች የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጥና ማስተማር የሚችል ሮቦት በመፍጠር ለውድድር አቅርቦ እውቅና ማግኘቱን ተናግሯል።   በእውቅና ላይ ተመርጠው በውድድሩ ከተሳፉት 112 የፈጠራ ባለቤቶች ውስጥ 49 የሚሆኑት በሀገር ደረጃ በሚካሄደው የአዳዲስ ሃሳቦችና ቴክኖሎጂዎች ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተመርጠዋል።  
 የኢትዮጵያን ቁልፍ የመሠረተ-ልማት ኃብቶች በተሻለ አቅም ለማስተዳደር የሚያስችል አዋጅ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው
May 18, 2024 78
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ቁልፍ የመሠረተ-ልማት ኃብቶች የሳይበር ደኅንነትን በተሻለ አቅም ማስጠበቅና ማስተዳደር የሚያስችል አዋጅ ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ገለጸ። አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የተቋማት የሕግና የሳይበር ሙያተኞችን ጨምሮ ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል። በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የኢንፎርሜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሃኒማል ለማ፤ ከዚህ ቀደም ቁልፍ የአገር ኃብቶችን የሳይበር ደኅንነት የሚያስጠብቅ አዋጅ እንዳልነበረ አስታውሰዋል። በሂደት ላይ የሚገኘው ቁልፍ የመንግሥት መሠረተ-ልማቶችን የሳይበር ደኅንነት ጥበቃ ረቂቅ አዋጅ ሥራ ላይ ሲውል ለዜጎች አገልግሎት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ምኅዳር ይፈጥራል ብለዋል። የአገር ቁልፍ የመሠረተ-ልማት የሳይበር ደኅንነት ጥበቃም ግልጽ የሆኑ የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት የተሻለ የተቋማት የትብብር አቅም ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልፀዋል። ቁልፍ የመሠረተ-ልማት የሳይበር ደኅንነት በማስጠበቅ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ የሳይበር አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠትና የደኅንነት ኃብቶችን ማፍራት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።   በአስተዳደሩ የሳይበር ሕግ ምርምርና ዝግጅት ዲቪዥን ኃላፊ ፍቅረሥላሴ ጌታቸው፤ ረቂቅ አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ቁልፍ የአገር መሠረተ-ልማቶች ተለይተው ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ ያስችላል ብለዋል። በረቂቅ አዋጁ ላይ ቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን የሚያስተዳድሩ ተቋማትና ግለሰቦችን ተግባርና ኃላፊነት በግልጽ በማመላከት የተሻለ አሠራር ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ገልፀዋል። ተቋምትም በአስተዳደሩ የሚወጡ ሕጎችን መነሻ በማድረግ የሚጠቀሙባቸውን የዲጂታል ኃብት ጥበቃ ማድረግ የሚችሉበትን አስገዳጅ አሠራር እንዲከተሉ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ረቂቅ አዋጁንም በማስጸደቅ ቁልፍ የመሠረተ-ልማቶችን የሳይበር ደኅንነት የተጠበቀ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የሚገኘውን የዘርፉን ጥቃት መመከት እንደሚያስችል ገልፀዋል። በቁልፍ የአገር መሰረተ-ልማቶች የሚደረገው አስተማማኝ የሳይበር ደኅንነት ጥበቃ፤ የመንግስትን የዲጂታል አገልግሎት በማሳለጥ የዜጎችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ መስጠት ያስችላል ብለዋል። የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ይዘት፣ ዓላማ፣ ምንነትና የዝግጅት ሂደት የሚዳስስ መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል። በአገር ቁልፍ መሠረተ-ልማቶች ላይ የሳይበር ደኅንነት ሥጋት እየጨመረ መምጣቱ፣ አገራዊ ስታንዳርዶችን ተፈፃሚ የማድረግ፣ የሳይበር ደኅንነት አቅም ኦዲት ለማድረግ፣ ቁልፍ መሠረተ-ልማቶችን ማስጠበቅ የሚያስችል ዝርዝር ሕግ ወጥቶ አለመተግበሩና ተያያዥ ጉዳዮች ለረቂቅ አዋጁ የዝግጅት ሂደት የጥናት መነሻ መሆናቸው ተነስቷል።  
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከአለም ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ
May 19, 2024 54
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን በኬንያ አቻው ተሸንፎ ከአለም ዋንጫ ማጣሪያው ውጪ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ብሄራዊ ቡድኑ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከኬኒያ አቻው ጋር ናይሮቢ ላይ አድርጎ 3 ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። ውጤቱንም ተከትሎ የኬንያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል። የኬኒያ ብሄራዊ ቡድን በአራተኛው ዙር የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥም ይሆናል። አፍሪካ በዓለም ዋንጫው ሶስት አገራትን የማሳተፍ ኮታ ያላት ሲሆን 12 አገራት በውድድሩ ለመሳተፍ በሶስተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታቸውን በማድረግ ይገኛሉ። አዘጋጇ ዶሚኒካን ሪፐብሊክን ጨምሮ እንግሊዝ ፣ፖላንድ፣ ስፔን፣ ብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ፣ ኒውዝላንድ፣ ጃፓንና ሰሜን ኮሪያ ለዓለም ዋንጫው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። 16 ሀገራት የሚሳተፉበት 8ኛው የፊፋ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ በዶሚኒካን ሪፐብሊክ አስተናጋጅነት ጥቅምት 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
May 19, 2024 60
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የሚመራው አዳማ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች 2ቱን ሲያሽንፍ 1 ጊዜ ተሸንፏል። 2 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በነዚህ 5 ጨዋታዎች 4 ጎሎችን ከመረብ ሲያሳርፍ 3 ግቦች ተቆጥረውበታል። አዳማ ከተማ በ38 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና ካለፉት 5 የሊግ ጨዋታዎች 2ቱን ሲያሸንፍ 1 ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። 2 ጊዜ ነጥብ ተጋርቷል። በ5ቱ ጨዋታዎች 5 ግቦችን ሲያስቆጥር 4 ግቦች ተቆጥረውበታል። በዘላለም ሽፈራው የሚሰለጥነው ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ መለያየቱ የሚታወስ ነው። በ25ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ሻሸመኔ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከምሽቱ 12 ሰዓት ይጫወታሉ። ሻሸመኔ ከተማ ባለፉት አመስት የሊግ ጨዋታዎች 4 ጊዜ ሽንፈት ሲያስተናግድ 1 ጊዜ አቻ ወጥቷል። ክለቡ በነዚህ 5 ጨዋታዎች 1 ግብ ብቻ ሲያስቆጥር 6 ጎሎችን አስተናግዷል። በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመራው ሻሸመኔ ከተማ በ13 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ካለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች በ2ቱ ድል ሲቀናው 1 ጊዜ ተሸንፏል። 2 ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በ5ቱ ጨዋታዎች 8 ግቦችን ከመረብ ጋር ሲያገናኝ 7 ጎሎችን አስተናግዷል። በነጻነት ክብሬ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና በ38 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያለውን አዳማ ከተማን በግብ ክፍያ በልጦ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መለያየታቸው አይዘነጋም። በተያያዘም ትናንት በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መቻል ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 2 ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀድያ ሆሳዕና አንድ አቻ ተለያይተዋል።  
አካባቢ ጥበቃ
ኖርዌይ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያከናውነውን ተግባር እንደምትደግፍ አስታወቀች
May 19, 2024 86
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ ኖርዌይ የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያከናውነውን የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለመደገፍ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች። ኖርዌይ እኤአ በ2011 ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ በደርባን ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጠንካራ አጋርነት መመስረቷ ይታወሳል። በኖርዌይ ኤምባሲ የአየር ንብረት፣ አካባቢና ደን አማካሪ ማሪ ማርቲንሰን ለኢዜአ እንዳሉት ኖርዌይ የኢትዮጵያ መንግስት በአየር ንብረትና በብዝሃ ህይወት ጥበቃ ላይ የያዘውን ግብ ለመደገፍ እየሰራች ነው። በተጨማሪ አገራቸው በአየር ንብረትና በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የምርምር ማዕከላትን እየደገፈች መሆኗን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ በብዝሀ ህይወት ጥበቃ ላይ በርካታ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው በተለይም በደን ጥበቃ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ መንግስት የሚያከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መንግስት ለአረንጓዴ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም ነው የገለፁት። የአየር ንብረት ለውጥ ለብዝሀ ህይወትና ለመጪው ትውልድ ስጋት በመሆኑ ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ስለሚገባ ሌሎች አጋር አካላትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ሁለቱ አገራት በዘርፉ ላይ በጋራ ለመስራት ያደረጉት ስምምነት ከ10 አመት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የኖርዌይ የአየር ንብረትና አካባቢ ሚኒስቴር በየካቲት 2016 ዓም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአየር ንብረት ላይ ያለውን አጋርነት እኤአ እስከ 2030 ለማጠናከር መስማማታቸውን አስታውሰዋል። በአለም ላይ ብዝሀ ህይወትን ጠብቀው በማቆየት ስኬታማ ከሆኑ 36 አካባቢዎች ሁለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ለእነዚህ አካባቢዎች ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት። በቀጣይ የኖርዌይ መንግስት በደን ልማት ላይ የሚያደርገው ድጋፍ እንደሚጠናከር አስታውቀዋል፡፡    
የክረምቱ ዝናብ ለግብርናና ተጓዳኝ ሥራዎች መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው - የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
May 18, 2024 64
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች በክረምት ወቅት የሚያገኙት መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ለግብርናና ተያያዥ ሥራዎች መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የበልግ አየር ሁኔታ ትንበያ ግምገማና የመጪው ክረምት የአየር ትንበያ አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዳማ ከተማ ምክክር አካሄዷል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ እንደገለጹት፤ በመጪው የክረምት ወቅት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያኙ የአየር ትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ። ክረምቱ በምድር መቀነት (ኢኩዌተር) አካባቢ ባለው የፓስፊክ ውቅያኖስ በሚከሰተው ከአማካይ በላይ ቅዝቃዜ (ላኒና) ምክንያት መደበኛና ከመደበኛ በላይ እንዲሁም በተወሰኑ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል አመልክተዋል። የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለግብርና፣ ለውሃ ኃብትና ለግጦሽ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።   በመካከለኛና የተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች መደበኛ የሆነ ዝናብ ሲያገኙ በተወሰኑ የአገሪቷ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኢኒስቲትዩቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሰጠው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ አደጋን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው ተግባር መሆኑን ገልጸው ይህ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የብዝሃ ህይወት ሀብቶችን ለሀገርና ህዝብ ጥቅም ለማዋል የዘርፉ ተዋንያን በቅንጅት መስራት አለባቸው - ግብርና ሚኒስቴር
May 16, 2024 106
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2016(ኢዜአ)፦የብዝሃ ህይወት ሀብቶችን ለሀገርና ህዝብ ጥቅም ለማዋል የዘርፉ ተዋንያን በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የብዝሃ ህይወት ቀንን "የእቅዱ አካል እንሁን" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ የሚያከናውናቸውን ስራዎች የሚያሳይ አውደ ርዕይ የተከፈተ ሲሆን የፓናል ውይይትና ሌሎች መርሃ ግብሮችም እስከ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላሉ፡፡ የግብርና ሚኒስትር የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ አማካሪ ታረቀኝ ፅጌ እንዳሉት፤ ብዝሃ ህይወት ሥነ ምህዳርን ለማስቀጠል፣ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠንና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የጎላ አበርክቶ አለው፡፡ ብዝሃ ህይወትን ማንበርና የምድርን ከባቢ መጠበቅ እንዲሁም ዘላቂነትን ማረጋገጥ ለቀጣዩ ትውልድ የተጠበቀችና የለማች አገር ማስረከብ ነው ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ የብዝሃ ህይወት ሀብቶችን ለመጠበቅ ያከናወናቸው ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች የሚበረታቱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ያላትን የብዝሃ ህይወት ሀብቶች ጥቅም ላይ ለማዋል የተተገበሩ የልማት ስራዎች በቂ እንዳልሆኑ አንስተዋል፡፡ በመሆኑም ሀገር ከብዝሃ ህይወት ሀብት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የዘርፉ ተዋንያን ከመንግስት ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አስረደተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መለሰ ማሪዮ በበኩላቸው፤ የብዝሃ ህይወት ሀብቶቻችንን ለመጠበቅና ለማንበር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወንን ነው ብለዋል።   በዚህም 7 የብዝሃ ህይወት ማዕከላት፣ 3 የዕፅዋት አፀዶች፣ ከ30 በላይ የማህበረሰብ ዘረመል ባንኮች እና 28 የደን ዘረመል ባንኮችን በማቋቋም የብዝሃ ህይወት ሀብቶች እየጠበቁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዓለም አቀፉ የብዝሃ ህይወት ቀንም የብዝሃ ህይወት ሀብት ጥበቃ ፖሊሲ አውጭዎች እና ማህበረሰቡን በማስገንዘብ መልካም ተሞክሮዎችን ለመቀመር እድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡      
በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በግንቦት የዝናብ ስርጭቱ ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎች የተመቸ ነው - የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት
May 16, 2024 118
መቀሌ፤ ግንቦት 8 /2016 (ኢዜአ)፡- በአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች በግንቦት የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት ስለሚኖር ቀድመው ለሚዘሩ የአገዳ ሰብሎች የተመቸ ሁኔታን እንደሚፈጥር የክልሉ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ትንበያ አመለከተ። በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትግራይ ክልል ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ አቶ ዳርጌ ፍቃዱ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በአብዛኞቹ የትግራይ አካባቢዎች በግንቦት የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር የአየር ትንበያው አመልክቷል። ''ይህም ቀድመው በያዝነው ወር ለሚዘሩ እንደ በቆሎ፣ ማሽላ ዳጉሳና የበጋ ጤፍ ለመሳሰሉት ሰብሎችና ማሳቸውን በብርእ ሰብሎች የሚሸፍኑ አርሶ አደሮች የማሳ ዝግጅት ለማድረግ የጎላ ጠቀሜታ አለው'' ብለዋል። በቀጣዮቹ ወራትም በክልሉ ሊኖር የሚችለውን የዝናብ መጠንና ስርጭትን እየተከታተሉ ለአርሶ አደሩና ለባለሙያዎች ሳይንሳዊ መረጃ እንደሚያቀርቡ አቶ ዳርጌ ተናግረዋል። እያንዳንዱ አርሶ አደር የተገኘውን የዝናብ ውሃ ወደ ኩሬ በመጥለፍና ወደ ማሳ አስገብቶ እርጥበትን በመቋጠር "ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይጠበቅበታል" ብለዋል። በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበራ ከደነው በበኩላቸው፤ በክልሉ በእርሻ ልማት የሚተዳደር ከ700 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እንዳሉ ጠቁመው፤ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም በእርሻ መሬቱ ላይ እርጥበትን እንዲቋጥር መልዕክት አስተላልፈዋል። አርሶ አደሮቹ ከውሃ ጠለፋና የእርከን ስራዎች ከማካሄድ ጎን ለጎንም ማሳቸውን ቀድመው በሚዘሩ ሰብሎች እንዲሸፍኑ አስገንዝበዋል። ግንቦት ላይ የሚዘንበው ዝናብ ቀድመው ለሚዘሩ የአገዳ ሰብሎች የተመቸ መሆኑን ገልፀው፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የዳጉሳ፣ የማሽላና የበቆሎ የሰብል ዓይነቶችን በመዝራት የእርሻ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የመረጃ ስርጭትን በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት አለም አፍሪካ ትክክለኛ ድምጿን እንድታሰማ ሀገራት ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ
May 16, 2024 113
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2016(ኢዜአ)፦ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በተገናኘ የመረጃ ስርጭት በፍጥነት እየተለወጠ ባለበት አለም አፍሪካ ትክክለኛ ድምጿን እንድታሰማ ለማድረግ ሀገራት ለዘርፉ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ። በአህጉሪቱ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላይ የሚመክረው 3ተኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን በጋና አክራ እየተካሄደ ይገኛል። አፍሪካዊ መረጃዎችን ለአርቴፍሻል አስተውሎት ግብአት በሚሆን መልኩ በማዘጋጀትና የአህጉሪቱን መጪ የቴክኖሎጂ ጉዞ በማፋጠን በኩል ሚዲያው ከፍተኛ ሚና እንዳለው በጉባኤው ተነስቷል። የዘንድሮው ጉባኤ የሚዲያ ነፃነትና የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም ሚዲያውን በኢኖቬሽንና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የማገዝ አጀንዳዎችን መያዙ ተገልጿል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሀገራት የሚወስዱትን መፍትሄዎች ለብዙሃኑ መረጃ የማድረስ ሃላፊነታቸውን ሚዲያዎች እንዲወጡ ማድረግ ላይም ጉባኤው ይመክራል ተብሏል።   በ3ተኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን ላይ የሀገራት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ መሪዎችና ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ኢትዮጵያ በተለይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፎች የምታከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ልምዷን እንደምታካፍል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል- አንቶኒዮ ጉተሬዝ
Apr 15, 2024 1559
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2016(ኢዜአ)፡- አለም ተጨማሪ ጦርነት እንድታስተናግድ እድል ባለመፍጠር በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ ሀገራት በአስቸኳይ ሊያስቆሙት እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አሳሰቡ። ኢራን እስራኤል ከሳምንታት በፊት ሶርያ በሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ጥቃት አድርሳብኛለች በሚል ባሳላፍነው ቅዳሜ ሌሊት መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በቀጣናውና በአለም ሀገራት የተፈጠረውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የጸጥታ ምክር ቤቱን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። በስብሰባውም አለም ተጨማሪ ጦርነት የምታስተናግድበት ምንም አይነት አቅም ስለሌለ ሀገራት በእስራኤልና ኢራን መካከል የሚታየውን አሳሳቢ ሁኔታ በአስቸኳይ ሊያስቆሙት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ችግሩ በቸልታ የሚታይ ከሆነ አስከፊ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸውን ያስነበበው ፍራንስ 24 የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሁኔታውን በአስቸኳይና ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሊያስቆሙት እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም ዘግቧል።
በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ
Apr 8, 2024 2430
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2016(ኢዜአ)፦በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል የባህር ዳርቻ በተከሰተ የጀልባ አደጋ ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። በሞዛምቢክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ናምፑላ ግዛት 130 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹ በግዛቷ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ በመሸሽ ወደ ሌላ አካበቢ ለመሄድ በጀልባ በተሳፈሩበት ወቅት አደጋው እንደተከሰተ የገለጹት ባለስልጣናቱ ጀልባዋ መሸከም ከምትችለው የሰው መጠን በላይ በመጫኗ አደጋው እንደደረሰ አመልክተዋል። በዚህም ህጻናትን ጨምሮ ከ90 በላይ ሰዎች ሕይታቸው እንዳለፈ ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሰዎችን ከአደጋው በሕይወት ማትረፍ እንደተቻለ ያመለከተው ዘገባው ተጨማሪ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስነብቧል። የናምፑላ ግዛት ባለፈው አመት በሞዛምቢክ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል አንዷ መሆኗም በዘገባው ተመላክቷል።
ሐተታዎች
"የዓይን ብሌን" ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ
May 16, 2024 104
በዓይን ብሌን ጠባሳ ብርሃኑን ያጣ ሰው ዳግም ዕይታውን ለማግኘት ሰዎች ከህልፈተ-ሕይወታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን በበጎ ፈቃደኞች ለመለገስ ቃል በገቡት መሰረት ገቢራዊ ሲደረግ ነው። በኢትዮጵያም የበጎ ፈቃደኞች የዓይን ብሌን ልገሳ ከተጀመረ ዓመታትን አስቆጥሯል፤ ብዙዎቹም ዓይን ብሌናቸውን በመለገስ ሰዎችን ባለ ብርሃን አድርገዋል። ከእነዚህ በጎ ፈቃደኖች መካከል ኢዜአ ስምረት ተሾመ እና ነጋ ደምሴን ለአብነት አነጋግሯል። በጎፈቃደኞቹ ይህን ተግባር ሲያስረዱም የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል መግባት የዓይንን ብርሃኑን ያጣ ሰው ዳግም ዕይታውን ማግኘት እንዲችል ማድረግ ነው ። "የዓይን ብሌን መለገስ ለእኔ ምንም አያጎድልብኝም" የምትለን ስምረት ተሾመ እንዲያውም ባደረኩት በጎ ተግባር በፈጣሪም ሆነ በሰው ምስጋና አገኛለሁ ትላለች። ምድር ላይ የተሰጠኝ ዕድሜ እስኪያልቅ የአንድን ሰው የዓይን ብርሃን እንደምመልስ ሳስብ ዘመኔን በደስታ እኖራለሁ ብላለች። ሌላውም እንደኔ የዓይን ብሌን ቢለግስ የእኔን ደስታ ያጣጥማት ስትል በማከል ።   ከሕይወተ ህልይወቴ በኋላ ለማደርገው የዓይን ብሌን ልገሳ በሕይወት እያለሁ ቃል በመግባቴ ትልቅ የህሊና ደስታ እግኝቻለሁ የሚለን ደግሞ ሌላኛው በጎ ፈቃደኛ ነጋ ደምሴ ነው ።   በጎ አድራጊዎች ባደረጉላቸው የዓይን ብሌን ልገሳ ማየት መቻላቸውን ምስክር የሚሁኑን ወጣት መታሰቢያ ንጉሴ እና ወጣት ታሪኩ ሁሴን ናቸው።   ከበጎ ፈቃደኞች በተገኘ የዓይን ብሌን ዕይታቸውን በማግኘታቸው ጤናማ ሕይወትን መምራት እንዲችሉ አድርጎናል ሲሉም አስተያየታቸውን ይገልጻሉ። በተደረገላቸው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው መማርና መሥራት መቻላቸውንም ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ይህን ሲያስረግጡ ፤ በሀገራችን በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት ዕይታቸውን ያጡ ሰዎች በሕክምና የዓይን ብርሃናቸውን ለማግኘት ወረፋ የሚጠባበቁ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን ገልፀዋል። የእነዚህን ሰዎች ዕይታ ለመመለስም የኅብረተሰቡን በጎ ፈቃደኝነት የሚጠይቅ ሰብዓዊ ተግባር መሆኑን በመጠቆም ። እንደ ሀገር ኢትዮጵያውያን ስለ ዓይን ብሌን ልገሳ ያለን ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ቢኖሩትም ከችግሩ ስፋት አንጻር በሚፈለገው ደረጃ ሕብረተሰቡ በቂ ባህል አጎልብቷል ማለት ያዳግታል ሲሉ። አገልግሎቱ ሕብረተሰቡ ስለ ዓይን ብሌን ልገሳ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የተለያዩ ሥራዎች በመሥራት ላይ ይገኛል ብለዋል። የዓይን ብሌን ንቅለ-ተከላ ሕክምናን ለማግኘት የሚሹ ወገኖችን ህልማቸው እውን እንዲሆን ሕብረተሰቡ የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል የመግባት ባህሉን እንዲያጎለብት አቶ ሀብታሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ለእነዚህም ወገኖች የዓይን ብርሃናቸውን ዳግም እንዲያገኙ አገልግሎቱ የዓይን ብሌን የማሰባሰብ ሥራ እና ሕብረተሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ተቋሙ በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት ብርሃናቸውን ላጡ ወገኖች ዕይታቸውን ዳግም እንዲያገኙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዓይን ብሌን የማሰባሰብ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት 300 የሚሆኑ ሰዎችን የዓይን ብሌን ለመለገስ ቃል ለማስገባት እና 195 የዓይን ብሌን ለመሰብሰብ መታቀዱን አውስተዋል። በዚህም 203 የዓይን ብሌን መሰብሰብ እንደተቻለና 288 የኅብረተሰብ ክፍሎች የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም አገልግሎቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት የዓይን ብሌን የማሰባሰብ እና የማኅበረሰቡን ግንዛቤ የሚያጎለብቱ ሥራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።    
ነገረ - አስተውሎት
Apr 24, 2024 500
(በሰለሞን ተሰራ) ሰው በሀሳብ ከሕይወታዊያን ፍጥረት ይለያል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ኑሮውን ቀላል ለማድረግ አስቧል። ሀሳቡም መላ ፈጥሯል። ድንጋይ አፋጭቶ እሳትን አንድዷል። እንስሳትን አላምዶ፣ ሰብልን አባዝቶ፣ መጠለያውን ቀልሶ… ኑረቱን አሳልጧል። ዕለታዊ ተግባሩን ለማቃለል በቁስ ላይ ተመራምሮ አጋዥ ቁስ ፈጥሯል። በሂደትም የኢንዱስትሪን አብዮት አፈንድቷል። በ18ኛው ክፍለ ዘመን በባተው የኢንዱስትሪ አብዮት ዓለም አዲስ ክስተት አስተናግዳለች። ፋብሪካዎች፣ መኪናና አውሮፕላን፣ የእንፋሎትና የኤሌክትሪክ ኃይልና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች ተፈብርከው ምርትና ምርታማነት ጨምሯል። ከተሜነት አብቧል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በሰው ተፈጥረዋል። ሳይንስን ለመፍትሔ-እንከን አውሏል። ቴክኖሎጂን ለሁለንተናዊ ሕይወት ማቃለያ ተጠቅሟል። ጊዜ፣ ጉልበትና ሀሳብን ከፈጠራ ጋር አዋዶ ኑሮና ሕይወት አቅልሏል። ኮምፒዩተር ፈበረከ፤ ኢንተርኔትን ፈጠረ፣ ዓለምን አስተሳሰረ። የተዓምር ዘመን ሆነ። ሰው እያስተዋለ... እያስተዋለ… በረቀቀ ጥበብና ግኝት ዛሬ ከዘመነ-አስተውሎት ደረሰ። ሰው ሰራሽ አስተውሎት!! የዘመኑ ቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) እንደሆነ ይጠቀሳል። ዳሩ የቴክኖሎጂው እምርታ የዘመን ክስተት ሳይሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት ጀምሮ እርሾ ሲያቦካ እንደነበር የዘርፉ ምሁራን ይጠቅሳሉ። ዋረን ማክኩሎች እና ዋልተር ፒትስ ለዛሬው ሰው ሰራሽ አስተውሎት እርሾ የሆነ በነርቭ አውታረ መረብ የሚታገዝ ሒሳባዊ ሞዴል የፈጠሩት በ1943 ዓ.ም ነበር። በ1950 ዓ.ም ደግሞ አለን ተርኒግ እንደ ሰው ማሰብ የሚችል ማሽን ፈለሰፈ። በተመሳሳይ በ1960ዎቹ አጠቃላይ ችግር ፈቺ፣ ሎጂክ ቴዎሪስትና መሰል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞች በልፅገዋል። በ1950 ዓ.ም ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ራሱን ችሎ እንዲጠና ተወሰነ። ለውስብስብ ችግሮች አይነተኛ መፍትሄ መሆኑ ታመነበት። በ1970 እና 80ዎቹ የዘርፉ ሊቃውንት የሰውን ልጅ የመወሰን አቅም የሚተካ የኮምፒውተር ፕሮግራም ለማበልጸግ ጥረት አድርገዋል። በ1990ዎቹ ምርምሮቹ መቀዛቀዝ ጀምረው ነበር። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዳግም አንሰራርቷል። ስልተ ቀመርን (algorithm) የሚረዱ ማሽኖች ስራ ላይ ውለዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጥናት ዘርፍ የሰውን ስራና ሃሳብ በኮምፒዩተር መራሽ ቁሶች መተካት ነው። የሰው ልጅ ፍጥረት የሆኑ ማሽኖች መገንዘብ፣ መማርና ችግሮችን እንዲቀርፉ ማስቻልም ነው። ማሽኖች በሰው ልጅ ምትክ አካባቢን ማመዛዘን፣ መማር፣ ማቀድና መፍጠር፣ መተንተንና እንከኖችን ማምከን እንዲችሉ ማድረግ ነው። የሰውን የማሰብ ኅይል በኮምፒዩተር አዳብሮ በሰውኛ ጥበብ ሕይወትን ማቅለል ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሰው ልጅ ያሉትን የስሜት ህዋሳት ክህሎቶች ለማሽኖች በማስተማር ሰዎች ነገሮችን በቀላሉ እንዲያገኙና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው። በዚህም የኮምፒውተር ሊቃውንት ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝምና አስበው የሚሰሩ ማሽኖች ወደ ስራ እያስገቡ ነው። ለአብነትም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ጥበብ ቤት የሚያጸዱ ሮቦቶች፣ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች፣ ሰው አልባ ጦር መሳሪያዎች፣ የደህነንት ጥበቃ ካሜራዎች፣… በልጽገው ስራ ላይ ውለዋል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው ይህ ቴክኖሎጂ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተስፋም ስጋትም ይዞ መምጣቱ ይነገራል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዛሬ ላይ በሁሉም መስክ ገቢራዊ እየተደረገ ነው። በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ በደህንነት፣ በግብርና ዘርፎች ምርትና አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለመጨመር ቁልፍ አማራጭ ተደርጓል። ቴክኖሎጂው ከዓለም ገበያ ከ350 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድርሻ አለው። አፍሪካም እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ገበያ 10 በመቶ ድርሻ መያዝ ከቻለች እኤአ 2030 አሁን ያለው አህጉራዊ ጥቅል ምርቷ (ጂዲፒ) 50 በመቶ ይጨምራል። ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ዘርፉን የሚመራ ተቋም መስርታለች፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን። ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምህዳር ተጠቃሽ ሀገር ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነው። በቅርቡ የተመረቀው “አስተውሎት” የተሰኘ ፊልም ደግሞ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሰው ልጅ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የማይገባበት ሕይወት እንደሌለ ፊልሙ ያስረዳል። በጤና፣ በማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በመረጃ ፍለጋ፣ በፖለቲካ፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፍለጋና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ የዚህ ቴክኖሎጂ ቁልፍ ሚና ተንጸባርቋል። ዘርፉ ከቅንጦት ይልቅ አስፈላጊነቱ ጨምሯል። ለበሽታ መከላከል፣ ለጤና እንክብካቤ፣ ለትምህርት መሻሻልና ድህነት ቅነሳ ይውላል። ለዚህም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የተመሰረቱ መተግበሪያዎች ፈጠራና አቅም እያደገ መምጣቱ በፊልሙ ተገልጿል። ፊልሙ የኢትዮጵያ የቡና ዛፎችን የበሽታ ስርጭት ለይቶ ለማከም ያለውን ውጤታማነት ያወሳል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የአገራችንን ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሳይበር ደህንነትን ለመጠበቅ፣ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ገበያን ለማስፋት እና ለመሳሰሉት ሥራዎች በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በአሁኑ ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ እየተስፋፉ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማሽን ትራንስሌት ወይም የቋንቋ ትርጉም አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም አንዱን ቋንቋ ወደ ሌላ በመተርጎም አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትም በአንድ መተግበሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን መማር እንዲሁም ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሥርዓትን አበልጽጎ ለተጠቃሚዎች አቅርቧል። መተግበሪያው አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር የሚያስችል ሲሆን ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችለው የመተግበሪያው አካል ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደ መተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ከፊልሙ መገንዘብ ተችሏል። በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የደረሰበትን ልህቀት ያማከሉና ከዘርፉ ውጤት ለማግኘት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተኬደው ርቀት ይበል የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልህቀት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የዘርፉን ውጤቶች የበለጠ ማላቅ ያስፈልጋል። በዓለም የዕለት ተለት እንቅስቃሴ ውስጥ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ በመረዳት ለዘርፉ ምርምሮች የሚደረገውን ድጋፍ የበለጠ ማጠናከር ያሻል። ዓለም የሚሄድበትን ፍጥነት በመመልከት ሀገራችንን የሚመስሉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን ለመተግበር በትኩረት መሥራት ያስፈልጋል።        
ብሩህ ነገን የሰነቁ እንስቶች
Apr 19, 2024 747
የሰው ልጆች ከፍጥረት እስከ ዕለተ ሞት ባሉት የሕይወት ዑደቶች ውስጥ በሚገጥሟቸው መልከ ብዙ ፈተናዎች ሳቢያ ራሳቸውን ለቀቢጸ ተስፋ ይዳርጋሉ፤ ተገደውም ወደ ማይፈልጉት ሕይወት ይገባሉ። በተለይም ሴቶች በሚገጥሟቸው አይነተ ብዙ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ጫናዎች ሳቢያ በበርካታ የህይወት ውጣ ውረድ ወስጥ ያልፋሉ፤ በሂደቱም ለአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት የተዳረጉ በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው ቃልኪዳን በላይነህ (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በወጣትነቷ ትዳር መስርታ፣ልጆችን ወልዳ ለመሳም በቅታለች፡፡ ዳሩ ግን ባለቤቷ በድንገተኛ አደጋ በመሞቱ ምክንያት ህጻን ልጆቿን ይዛ ለአስከፊ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጓን ትናገራለች። በዚህም ራሷንና ልጆቿን ህይወት ለማቆየት ወደ ማትፈልገው የወሲብ ንግድ ሕይወት ውስጥ ለመግባት መገደዷን ነው የገለጸችው፡፡ በህፃንነት ዕድሜ ለአካል ጉዳተኝነት የተዳረገችው ሳምራዊት (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) በበኩሏ በአካል ጉዳተኝነቷ ምክንያት ተንቀሳቀሳ መስራት ባለመቻሏ ከተወለደችበት ገጠራማ ስፍራ ወደ አዲስ አበባ መምጣቷን ትናገራለች፡፡ በአዲስ አበባም ህይወቷን በልመና ስትመራ ቆይታለች፡፡ ሌላኛዋ ባለታሪካችን ሔዋን (በግል ፍላጎቷ ስሟ የተቀየረ) ወደ ማትፈልገው ህይወት ውስጥ ስትገባ የሚያጋጥማት ማህበራዊ ፣ አካላዊ ጥቃት እና ስነልቦናዊ ጫና ቀላል አይደለም ትላለች። እሷም ኑሮን ለማሸነፍ የገባችበት የህይወት መስመር ወደ አላስፈላጊ ሱስ ውስጥ እንድትገባና ለስነ ልቦናዊ ቀውስ እንድትጋለጥ እንዳደረጋት ገልጻለች። መንግስት በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ለመታደግ የሚያስችልና “ለነገዋ” የተሰኘ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል አንዱ ነው፡፡ ማዕከሉ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ሴቶችን በስነ ልቦና የምክር አገልግሎት እና በተለያዩ ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት ብሩህ ነገን ለማቀዳጀት ስራ ጀምሯል። እነ ቃልኪዳን፣ ሳምራዊት፣ ሔዋንና ሌሎች በችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ‘የነገዋ’ የተሰኘውን የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ተቀላቅለው የተሻለ ነገን ለመኖር ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በማዕከሉ በሚሰጣቸው ሙያዊ ስልጠናና የምክር አገልግሎትም ወደ ተረጋጋ መንፈስ እንዲመለሱ፣ የሕይወት ተሞክሮ እንዲቀስሙ፣ ነጋቸውን ለማሳመር እንዲነሳሱ ስለማድረጉም ይናገራሉ። ማዕከሉ በአዲስ አበባ መከፈቱ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች ትልቅ ብስራት መሆኑን ገልጸው፤ መሰል ማዕከላትም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊስፋፋ እንደሚገባ ጠቁመዋል።   “የነገዋ” የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄርጳሳ ጫላ ማዕከሉ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰው፤ 500 ሴቶችን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሰልጣኞች ከማዕከሉ ሲወጡ ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲችሉ የሚያደርግ በልዩ የክህሎት፣ የስነ ልቦና እና የሙያ በአጠቃላይ በ18 አይነት የስልጠና ዘርፎች እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ስፌት፣ ስነ ውበት፣ የምግብ ዝግጅት፣ የከተማ ግብርና፣ የሕጻናት እንክብካቤና ሌሎች ዘርፎች ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር እንደሚያሰለጥን ነው የገለጹት። ከስልጠናው በኋላ ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር ማዕከሉ በትብበር እየሰራ መሆኑም ተናግረዋል፡፡ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማእከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ''እራትም... መብራትም'' የመሆን ጅማሬ
Apr 14, 2024 1894
ሲሳይ ማሞ (ከአሶሳ) ያኔ! 2003 ዓ.ም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ የተነገሩ ተስፋዎች የማየፈቱ ህልሞች ብለን ስንቶቻችን አስበናቸው ይሆን? በአካባቢው ሊኖር ስለሚችለው ታላላቅ ክስተቶች፣ ስለሚፈጠሩት መልካም ነገሮች በሰማንበት ቅጽበት በህልም ዓለም ውስጥ እንዳለን ስንቶቻችን አስበን ይሆን? "አዬ ህልም!?" በሚል ሲደርስ እናየዋለን በሚል ቀናት ቆጥረናል። ያኔ! ነገሮች ሲነሱና ሲተረኩ ስንቶቻችን እንሆን እዚህ ቀን ላይ ደርሰን እናይ ይሆን!? የሚል ሃሳብ በእዝነ ህሊናችን የተመላለሰው? ያኔ! የታላቁ ህዳሴ ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ ኋላ ከ240 በላይ ኪሎ ሜትሮችን የሸፈነ ውሃ ሐይቅ ሰርቶ ተንጣሎ እንደሚተኛ እያለምን መጩውን ዘመን በጉጉት የጠበቅን ስንቶቻችን ነን? ግድቡ ግንባታው ሲገባደድ አገር የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በዘለለ "ከሰው ሰራሽ ሐይቁ በሚወጣ ዓሳ ሌላ የገቢ ምንጭ ይፈጠርላታል፤ በሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ሃይቅ ላይ የጀልባ ትራንስፖርትና የመዋኛ አገልግሎቶች ይጀመራል" የሚሉት መረጃዎችንና ትንታኔዎችን ከመገናኛ ብዙሃኑ ስንሰማ እንደርስ ይሆን? የሚል ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ያልመጣ ቢኖሩ ጥቂቶች ሳይሆኑ አየቀሩም። ያኔ! እንደትንቢት የተነገረው ዛሬ ጊዜው ሲደርስ "ይሆናል" የተባለው ከጊዜ ወደ ጊዜ "እየሆነ" መጣ። ስለታላቁ ግድብ በህልም ደረጃ ሲገለፁ የነበሩ በዕውን ወደማሳየቱ እየተንደረደረ ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ገጠመኜን ጀባ ልበላችሁ! ዕለቱ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከማለዳው 12 ሰዓት ነው፡፡ አፍንጫዋ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሰካች አንድ የሞተር ጀልባ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንጣለለውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለሁለት እየከፈለች ትጓዛለች ከማለት ትበራለች ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ሰው ሰራሽ ሐይቁ ውሃውን እንደልቧ እየቀዘፈች ለመጓዝ አስችሏታልና! ከምዕራብ በኩል የኮርቻ ግድብ (Saddle dam) ተጠማዞ እና በኩራት ደረቱን ገልብጦ ይታያል፡፡ በስተምስራቅ አቅጣጫ ላይ የሚገኘው የግድቡ ሃይቅ ደግሞ ለስለስ ያለ ሃምራዊ ቀለም ለተመላካቹ ያሳያል። የማለዳዋ የፀሐይ ጨረር ያረፈበት የውሃው ክፍል ለእይታ ባያስቸግርም ገና ከማለዳው ከአካባቢው ሞቃታማ አየር ጋር ተዳምሮ ወላፈን የሚመስል ሙቀቱን መርጨት ጀምሯል፡፡ ከፊት ለፊታችን ደግሞ በረጅም ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያቆረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፊት ለፊት ተንጣሎ ይታያል፡፡ የተሳፈርንባት የሞተር ጀልባ ስምንት ያህል መንገደኞችን ይዛለች፡፡ በሰው ሰራሽ ሐይቁ ላይ የሚደረግ ጉዞ ለተጓዡ ሐሴትን ጀልባዋን ለሚዘውራት ከዕለት ገቢ የዘለለ ተድላን እንደሚለግስ አያጠራጥርም። የአካባቢውን ድባብ እየተመለከትን ጉዟችንን ቀጠልን። በጉዞው ቅፅበትም ዓይኖቻችን በአንድ ወጣት አሳ አስጋሪ ላይ አረፉ። ወጣቱ በጀልባዋ ላይ ሆኖ በአንደኛው አቅጣጫ በኩል አጎንብሶ በመንጠቆ ያጠመዳቸውን ግዙፍ አሳዎችን አጥብቆ እየያዘ ወደ ጀልባዋ ይጨምራል። ከአቅሙ በላይ ሆነው ሊያመልጡት የሚታገሉ አሳዎችን ደግሞ በብረት አንካሴ ወገባቸውን እየወጋ ለመያዝ ይታገላል፡፡ ተጠግተን ለመርዳትና አሳዎቹን በመያዝ ለማገዝም ሆነ ሌላ ድጋፍ ለማድረግ አልደፈርንም፡፡ ወጣቱ ግዙፍ አሳዎቹ ጋር የገጠመውን ግብግብ በካሜራ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ግን አልዘነጋሁትም። ወጣቱ ኢትማን መሃመድ ይባላል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የጉባ ወረዳ ነዋሪ ነው፡፡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ላይ አሳ የማስገር ስራ ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል፡፡ “ቤተሰቦቼ እንደነገሩኝ ከ13 ዓመት በፊት ግድቡን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲቀመጥ አሁን በሞተር ጀልባ የምንጓዝበት ሃይቅ ይፈጠራል የሚል እምነት በአካባቢው ነዋሪዎች እሳቤ ውስጥ ፈጽሞ አልነበረም።” ሲል ይናገራል ወጣቱ፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሃይቅ ለእርሱ እና ለሌሎች ከእርሱ ጋር ለተደራጁ 25 ወጣቶች የሥራ እድል በር መክፈቱን አጫወተኝ፡፡ ከታላቁ ግድብ ያገኙት ትሩፋት እርሱ እና የማህበሩ አባላት በአገራቸው ላይ ሰርተው የመለወጥ ተስፋቸውን በእጅጉ እንዳለመለመላቸው አጫውቶኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚገኙ ወንዞች አሳ ቢያመርቱም በህዳሴው ግድብ አማካኝነት ከተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የሚያገኙት ግን በዓይነትም በመጠንም የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ከሐይቁ እስከ 50 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ነጫጭና ሌሎች ዓሳዎችን እያሰገረ መሆኑን በአድናቆት ጭምር ይገልፃል። ማህበሩ በቀን እስከ ሁለት ኩንታል ወይም ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ገደማ ዓሳ ያመርታል፡፡ “የህዳሴው ግድብ የምግብ ዋስትናም ፤ የገቢ ምንጭም ሆኖናል” ሲልም ወጣቱ ሃሳቡን ቋጭቷል። ለሰዓታት በቆየሁበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ የአሳ ማስገር እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት መንፈስ ከገነቡት ግድብ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ጅማሬን ይስተዋላል። ነገሩ እንዲህ ነው! በባህር ዳር ጣና ሃይቅ ላይ ያካበተውን የአሳ መረብ አሰራር እና የሞተር ጀልባ አጠቃቀም ልምድ ለማካፈል ወደ ስፍራው ያቀናው ወጣት የሻምበል ወርቁ በማህበር ተደራጅተው አሳ ለሚያሰግሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወጣቶች ስልጠና ሲሰጥ ማግኘቴ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን መረጃ እውነታነት ያሳያል። “አንዱ ወንድሜ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ይሄም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እኔም ከአማራ ክልል ነኝ፡፡ ሁላችንም እኩል የግድቡ ትሩፋት ተጠቃሚ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በአካል የማንተዋወቀውን ኢትዮጵያውያንን ግድቡ አስተዋውቆናል” ብሎኛል የሻምበል። ሌላው የመንጠቆ አጣጣል ስልጠና ለመስጠት ከአርባምንጭ ተጉዞ ወደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅ መጥቶ ያገኘሁት ደግሞ ወጣት አልማው ደሳለኝ ነው። ''ለአካባቢው ወጣቶች ልምዴን እና ያለኝን ዕውቀት በማካፈሌ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ'' የሚለው ወጣቱ፤ በሃይቁ ላይ የተመለከተው ከፍተኛ የአሳ ሃብት እንደ እርሱ ያሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በመጥቀም ለአገሪቷም የተሻለ ገቢን ሊያመጣ እንደሚችል ያምናል። “ተባብረን በመስራት አገራችንን እንለውጣለን” በማለት ህብረትና አንድነት ከድህነት ለመውጣት የሚያስችል ዘመኑ የሚፈልገው ታላቅ መሳሪያ መሆኑን ያምናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ...ተብለው ሲነገሩ የነበሩ የወደፊት ትልሞች አሁን እውን ሆነው 'ስራን ለሰሪው....ፍፁማዊ የገፅታ ለውጥን ለአካባቢው መልክዓ ምድር እንዲሁም ሰፊ የቱሪዝምና ሌሎች የስራ መስኮችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት የተግባር ጅማሬ እየታየ ነው። በግድብ ግንባታው የመሰረት ድንጋይ ማኖር ወቅት "በይሆናል" ሲባሉ የነበሩ ዕቅዶች እውን ወደ መሆን...ወደ መጨበጥ እየመጡ መሆናቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው። ለኢትዮጵያውያን የ”ይቻላል” ተምሳሌት የሆነው ግድብ ዋነኛ በይበልጥ ሲጠቀስ ከነበረው የኃይል አቅርቦት ባሻገር ለዜጎች ሌላ የስራ መስክ በመፍጠር ' እራትም መብራትም' ሆኖ እስከመጨረሻው ሊዘልቅ እነሆ ውጤቱን እያሳየ ነው። እንግዲህ የነገ ሰው ብሎን ትሩፋቱን በይበልጥ ያሳየን !!  
ትንታኔዎች
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ
May 11, 2024 183
የሽግግር ፍትሕ - የአያሌ ችግሮች መፍቻ (ሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከስተዋል። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገሪቱ ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነት እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ያወጣው መግለጫ እንዳመላከተውም በኢትዮጵያ የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ሥልት ነው። ከአንድ ዓመት በላይ በዝግጅት ሂደት የቆየው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተከትሎ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብርም ተካሂዷል። የሽግግር ፍትሕ ታሪካዊ ዳራ የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ ታሪካዊ መነሻ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1939 እስከ 1945 ከተደረገው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ ፍትሕን ለማስፈን የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 በጀርመን ኑረንበርግ የተሰየመ ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ችሎት የተቋቋመ ሲሆን፤ ችሎቱ የተቋቋመው ዋና የናዚ መሪዎችን የፍርድ ሂደት ለመከታተልና ውሳኔ ለመስጠት ነው። በወቅቱ የናዚ መሪዎች በጦር ወንጀል፣ በሰብዓዊ ጥፋት እንዲሁም ወንጀሎችን ለመፈጸም በማሴር ተከሰዋል። ለአንድ ዓመት የቆየው የፍርድ ሂደትም በናዚ ሰዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ “ታሪካዊ” እና “ታላቅ” የሚል አድናቆትን አግኝቶ ነበር። የጦርነቱም የፍርዱም ተሳታፊዎች “ጨርሶ አይደገምም፤ Never again” የሚል ቃል ገብተው ነበር። በወቅቱ የጃፓን ወታደሮች የፍርድ ሂደት የሚታይበት የቶኪዮ ወታደራዊ ችሎትም ተቋቁሞ ነበር። በኑረንበርግ እና በቶኪዮ የነበሩት ወታደራዊ ችሎቶች ለሽግግር ፍትሕ እሳቤ መጠንሰስ ቁንጮ ማሳያዎች እንደሆኑ ይነገራል። በግሪክ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1945 እና በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983 የቀድሞ ወታደራዊ መንግሥት አባላት የፍርድ ሥርዓትም እንደ ሽግግር ፍትሕ ማሳያ ይጠቀሳሉ። የሽግግር ፍትሕ ዘርፍ እ.አ.አ ከ1980 በኋላ ያለው እሳቤና ተፈጻሚነቱ እያደገ የመጣ ሲሆን፤ እ.አ.አ በ1970 እና 1980ዎቹ ትኩረቱን የሰብዓዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ ላይ አድርጓል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተቀባይነት እንዲያገኝና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎችና ስምምነቶች እንዲቋቋሙ በር ከፍቷል። በወቅቱ የሽግግር ፍትሕ እሳቤ ማዕከል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በፖለቲካ ሽግግር እንዲሁም በሕግና ወንጀል ፍርዶች ወቅት እንዴት ይቃኛሉ? እንዴት ይታያሉ? የሚለው ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ የነበሩ ክርክሮች “ፍትሕ” ለሚለው ዓለም አቀፍ ጽንሰ-ሀሳብ መዳበርና መስፋት አስተዋጽዖ እንደነበረውም ይጠቀሳል። በሂደት የሽግግር ፍትሕ እየሰፋ በተለይም እ.አ.አ በ1980ዎቹ መጨረሻና በ1990 መግቢያ ላይ ዴሞክራሲና የዴሞክራሲ እሳቤዎች ዓለምን እየተቆጣጠሩና ተጽዕኗቸው እየጨመረ ሲመጣ የሽግግር ፍትሕ ከዴሞክራሲ አንጻር መቃኘት ጀመረ። በዚህም የሽግግር ፍትሕ የዴሞክራሲ እሳቤ አንዱ የጥናት ዘርፍ መሆን የቻለ ሲሆን፤ የሽግግር ፍትሕ “ጠባብ ከነበሩ የሕግ ጥያቄዎች ወደ የተረጋጉ የዴሞክራሲ ተቋማት መገንባትና የሲቪክ ተቋማት እንደገና ማደስ ወደሚል ሰፊ የፖለቲካ አመክንዮዎች አድማሱን አስፍቷል” ሲሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕን ማዕቀፍ ከፖለቲካዊ ሂደቶችና ዴሞክራሲያዊ ለውጦች ጋር ያቆራኙ አገራት ከአምባገነናዊ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር ምቹ መደላድል እንደፈጠረላቸው በዘርፉ ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ይጠቅሳሉ። በዴሞክራሲያዊ ሂደት ውስጥ ያሉ የሽግግር ፍትሕ ፈተናዎች በርካታ ናቸው የሚሉት ምሁራን የዴሞክራሲ ሂደቱ ሳይጓተት ላለፉ ቁርሾዎች መፍትሔ መስጠት፣ ግጭቶችን የሚፈታ የዳኝነት ወይም የሦስተኛ ወገን የፍትሕ ሥርዓት መዘርጋት፣ የካሳ ክፍያዎችን መፈጸም፣ ያልሻሩ ቁስሎች እንዲሽሩና የባህል እርቆችን የተሟላ ማድረግ ከፈተናዎቹ መካከል የሚጠቀሱ እንደሆኑ ያነሳሉ። ካናዳ፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ አገራቱን የቆረቆሩ ነባር ዜጎች ይደርስባቸው ለነበረው ጭቆና ምላሽ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕን ተጠቅመውበታል። በአሜሪካም “የዘር ፍትሕ Racial justice” አስመልክቶ በሚደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች የሽግግር ፍትሕ ቋንቋና ሀሳብ ደጋግሞ ይነሳ ነበር። የሽግግር ፍትሕ አንድ የወለደው ሀሳብ ቢኖር የ”እውነት ፈላጊ” ኮሚሽኖች (Truth commissions) ማቋቋም ነው። በአርጀንቲና እ.አ.አ በ1983፣ በቺሊ እ.አ.አ በ1990 እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ በ1995 የ”እውነትን አፈላላጊ” ኮሚሽኖች ተቋቁመዋል። ኮሚሽኖቹ በላቲን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ እስያና ምስራቅ አውሮፓ እንደ ሽግግር ፍትሕ “ምልክት” ይታዩ የነበረ ሲሆን፤ ይሁንና በዩጎዝላቪያ ለተፈጸሙ ወንጀሎች ቀጣናዊ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽን ለማቋቋም ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም በፖለቲካ መሰናክሎች ምክንያት ሳይሳኩ መቅረታቸውን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የዴሞክራሲ ምሁራንና ባለሙያዎች አገራት በሽግግር ፍትሕ ማዕቀፎቻቸው ውስጥ ብሔራዊ ስትራቴጂዎቻቸውን ሲቀርጹ ያለፉ በደሎችንና ቁርሾዎችን እንደ አገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታና ባህርይ መፍታትን በዋናነት ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እንደሚገባ ይመክራሉ። ይህ ቁርሾን የመፍታት ሂደት ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ከሕግ ተጠያቂነት የማምለጥ ዝንባሌን ለማስቀረት፣ በዜጎችና መንግሥታት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማደስና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ይገልጻሉ። የሽግግር ፍትሕ ሰፊ የአስተሳሰብ ማዕቀፍ ዜጎች ሁሌም ኋላቸውን እያዩ ወይም ካለፉ ክስተቶች ጋር ከመጋፈጥ ወደፊት የተሻለ ነገር ይመጣል ብለው ተስፋ እንዲሰንቁ እንደሚያደርግም ይጠቅሳሉ። እ.አ.አ በ2001 በሽግግር ፍትሕ፣ እርቅና ርትዕ ላይ የሚሰራ “ዓለም አቀፍ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል” የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም የተመሠረተ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ግብረ-ኃይል ተቋቁሟል። የሽግግር ፍትሕ በዘላቂ ልማት ግቦች መካከል ግብ 16 “የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አፋጣኝ የፍትሕ ጣልቃ-ገብነት እርምጃዎች በመውሰድ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት” የሚለውን ለማሳካት አጋዥ ነው። የሽግግር ፍትሕ ትርጓሜዎች እንደ ዓለም አቀፉ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል ከሆነ የሽግግር ፍትሕ “ከግጭት የወጡ አገራት በመደበኛ የፍትሕ ሥርዓት በቂ ምላሽ ሊሰጡባቸው የማይችሏቸውን ከፍተኛ፣ የተደራጁና በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡባቸው መንገዶች ናቸው።” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሽግግር ፍትሕ ለፍትሕ ብቻ ትኩረት በማድረግ ፍትሃዊ የኃብትና አገልግሎት ክፍፍል ማድረግ ወይም ለኢ-ፍትሃዊነት ምላሽ መስጠት ሳይሆን “ከአቅም በላይ ለሆኑና ልዩ ባህርይ ላላቸው ፈተናዎች ምላሽ የሚሰጥበት አካሄድና መንገድ ነው” ሲል ይገልፀዋል። የወንጀል ቅጣቶች፣ የእውነት ፈላጊ ኮሚሽኖች መቋቋም፣ ካሳ መክፈል፣ ሰዎች በግጭት ወቅት ያጡትን ወይም የተሰረቁትን ንብረትና ኃብት መተካት፣ በጅምላ መቃብር ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች በክብር ለየብቻ እንዲቀበሩ ማድረግ፣ ይቅርታና ምህረት ማድረግ፣ መታሰቢያዎችን መገንባት፣ በግጭቶቹ ላይ ሳይንሳዊ ምርምር በማድረግ ግጭቶችና በደሎች እንዳይደገሙ በሚያደርግ መልኩ ትምህርቶችን ማስተማርና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ምላሽ የሚሰጡ ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ በሽግግር ፍትሕ ውስጥ ከሚካተቱ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። በሌላ በኩል በሽግግር ፍትሕ በፖለቲካዊ ሽግግር ውስጥ የሕግ የበላይነትን ማስፈን በዚህም ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት የሚደረግ ጉዞን ማፋጠን ያስፈልጋል የሚሉ ምሁራንም አሉ። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት በደሎችን በማከም ሰላምና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር መገንባትን ባለመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ለመተግበር ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ያሉ አለመግባባትና ግጭቶችን ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ትክክለኛ አማራጭ መሆኑ ይገለጻል። የሽግግር ፍትሕ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ የሕግ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ እርቅና ካሳን ጭምር ታሳቢ የሚያደርግ እንደሆነ ተጠቅሷል። በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ መዘርጋት አስፈላጊነት ታምኖበት ሁሉን አቀፍ አካታችና ተመጋጋቢ የሆነ ፖሊሲ ለማዘጋጀት ላለፉት ጊዜያት ሰፊ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ያጋጠሟትን ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ታምኖበታል። የሽግግር ፍትሕ ሰላምና ፍትሕን አስተሳስሮ የመሄድ ጉዳይ እንደሆነና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የማይተካ ሚና እንዳለው እንዲሁም በሂደቱ የይቅርታና ምህረት ጉዳዮችን እንደሚያቅፍ የሕግ ምሁራን ይገልጻሉ። በጦርነት የተጎዱ አካላትን ማቋቋም በሽግግር ፍትሕ እንደሚታይና በዚህም ዘላቂ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ማምጣት እንደሚቻል ያስረዳሉ። የተለያዩ አገራት ከነበሩባቸው በርካታ ቀውሶች ወጥተው ወደ ሰላም የመጡበት ሂደት መሆኑን በማውሳት የዘርፉ ባለሙያዎችን ባካተተ መልኩ በቁርጠኝነት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ምክረ-ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ። የሽግግር ፍትሕ ስልቶች ያለፉ በደሎችን፣ ቁርሾዎችን፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ አለመግባባትና ጥርጣሬን በአግባቡ በመፍታት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ምቹ መደላድል መፍጠር ዋነኛ ዓላማው ነው። ቀደም ሲል ከነበረ አለመግባባት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲላቀቅ በማድረግ ቀጣይነት ያለው አብሮነትና መተማመን መፍጠር የሚያስችል የፍትሕ ማስገኛ ስልትም ነው። አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ አገራት በሽግግር ፍትሕ ስልቶች አልፈው ከነበሩበት ውስብስብ ችግር በመውጣት የተሻለ ሰላም፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነት ማስፈን ችለዋል። ለአብነትም ኮሎምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩጋንዳና ሴራሊዮን ካለፉበት አስከፊ የእርስ በርስ ግጭትና አፓርታይድ ሥርዓት በሽግግር ፍትሕ መፍትሔ በመስጠት የተሻለ ሀገር መገንባት መቻላቸው በማሳያነት የሚቀርብ ነው። በኢትዮጵያም በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት ሊፈቱ የማይችሉ የረዥም ዓመታት ጥፋቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ ታምኖ እየተሰራበት ይገኛል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት በኢትዮጵያ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊነት በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዝግጅት በጥር ወር 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የሚያዘጋጅና ከተለያዩ ተቋማት የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ምህረት መስጠትን፣ የሕግና ተቋማት ማሻሻያ ማድረግን፣ ማካካሻ መስጠትን፣ እውነትን ማፈላለግን እና ተጠያቂነትን ማስፈንም የሽግግር ፍትሕ ሰነዱ ዓላማ አድርጎ የሽግግር ፍትሕ የደረሰበትን ደረጃ ባገናዘበ መልኩ ፖሊሲው ሲዘጋጅ ቆይቷል። ሰላምን በማረጋገጥ፤ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የማኅበረሰብን ትስስር መመለስ ያስፈልጋል የሚለው ጉዳይ ከፖሊሲው የትኩረት አቅጣጫ መካከል የሚጠቀስ ነው። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ከዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ውይይቶች ተደርገዋል። የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ-ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች እንደተካሄዱበት ተልጿል። በተጨማሪም መንግሥት የሽግግር ፍትሕ አማራጮችን አስመልክቶ ሕዝባዊ ውይይቶችን በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች አድርጓል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ጸድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል። በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታውሷል። ሆኖም እነዚህ አሠራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት፣ በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብዓዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል። ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡንና ምክር ቤቱ ግብዓቶችን በማከል ፖሊሲው ከጸደቀበት ቀን እንስቶ ሥራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል። የባለድርሻ አካላት ሚና በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲተገበር የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑ ዕሙን ነው። በፖሊሲው እንደተመላከተውም የሽግግር ፍትሕ ሥራዎችን ተግባራዊ የሚያደርጉ ተቋማት በርከት ያሉ ናቸው፡፡ በዚህ ሂደት የመንግሥት አካላት ሚናቸው ከፍተኛ ሲሆን ለአብነትም የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው። ለምሳሌ የፍትሕ ሚኒስቴር የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓቱን በበላይነት የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፀም ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ትልቅ የቤት ሥራ አለበት፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴርም የአገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት የማስተዳደር፣ የፌዴራል መንግሥት በጀትን የማዘጋጀት፣ የተፈቀደ በጀትን ለሚመለከተው አካል የመላክ፣ አፈጻጸሙን የመገምገም እና የመሳሰሉት ተግባራት እና ኃላፊነቶች ያሉት መሥሪያ ቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚኖሩት ተግባርና ኃላፊነቶች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማኅበረሰቡን የማሳወቅ እና የማንቃት ሥራ እንዲሰሩ እንዲሁም በሽግግር ፍትሕ አተገባበር የቴክኒክ እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስተባበር ይጠበቅበታል። የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ተቋማት የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቋቋሙ ተቋማት ወይም አደረጃጀቶች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ የሰላም እና የፀጥታ ችግር እንዳይገጥማቸው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የተለያዩ የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሕጎችን ቅድሚያ እና ትኩረት በመስጠት ከማጽደቅ፣ ለሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ ትግበራ የሚቋቋሙ ተቋማት ኮሚሽነሮች እና ዳኞች ሹመት ግልፅ በሆነ እና የሕዝብን ተሳትፎ በሚያረጋግጥ ሂደት እንዲከናወን ከማድረግ ወዘተ አኳያ ኃላፊነቱ ከፍተኛ ነው። የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ የሽግግር ፍትሕ አተገባበርን አስመልክቶ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር እና አዎንታዊ ሰላም እንዲገነባ ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ሥራ በመሥራት፣ የሽግግር ፍትሕ ዘላቂ ሰላምን ሊያመጣ በሚችል አግባብ በሁሉም ክልሎች ወጥ በሆነ መንገድ እየተተገበረ ስለመሆኑ በመከታተልና አስፈላጊውንም ድጋፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል። በአጠቃላይ ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት አተገባበር ጋር በተያያዘ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሚና የሚኖራቸው የመንግሥት ተቋማት ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎችም አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። እነዚህ አካላት የሽግግር ፍትሕ ሂደት ትግበራው የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ ተጎጂን ማዕከል ያደረገ እና የፖሊሲውን መርሆዎች ያከበረ መሆኑን በመከታተልና በመደገፍ፤ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለ ሽግግር ፍትሕ ሥርዓት እና ሂደት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የሽግግር ፍትሕ ሥርዓቱ አተገባበር በሕዝብ ተቀባይነት እንዲኖረው በማድረግ፤ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ ይኖርባቸዋል። እንደ መውጫ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በቅርቡ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም መንግሥት የተሟላና ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚያስችል የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ለማዘጋጀት አስቀድሞ የገለልተኛ ሙያተኞች ቡድን በማዋቀር ሲሰራ ቆይቷል። ከ80 በላይ ሕዝባዊ የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ማኅበረሰቡ በስፋት ሃሳብ እንዲሰጥ በማድረግም የተገኙ ግብዓቶችን በፖሊሲው በማካተት እንዲፀድቅ መደረጉ ተገልጿል። የፖሊሲው አጠቃላይ ዓላማ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሠረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር መሆኑ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል። የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲያመጣና ዜጎች ነገን በተስፋ እንዲጠብቁና በአገራቸው ላይ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው በተሟላ መልኩ መተግበር አለበት። ለዚህም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። የሽግግር ፍትሕ ሂደቱና አገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ችግር ወጥታ ወደ ቀጣዩ የእድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር ከማድረግ አኳያ እርስ በርስ የሚመጋገቡ ሲሆን፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ በሚጣጣሙባቸው አጀንዳዎችና ግቦች ላይ በጋራ በመሥራት ሁሉን አቀፍ ውጤት ማግኘትም ይቻላል።
መልከ ብዙው የ"ዳሞታ ተራራ"
Apr 23, 2024 583
የዳሞታ ተራራ ወላይታዎች የሚታወቁበት የራሳቸው የሆነ ባህል፣ ቅርስ እንዲሁም መለያ ምልክት ነው። ዳሞታ የወላይታ የልምላሜ መገለጫና የተፈጥሮ መስህብ ነው። ተራራው በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ በሚገኝ 12 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ32 ምንጮችና በ12 ጅረቶች ታጅቦ በኩራት ተንሰራፍቶ የሚገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ መጠሪያ ነው። ከዚህ የተነሳ የወላይታ ሶዶ ከተማን ተፈጥሮ ካደላት የዳሞታ ተራራ ሞገሷ የተነሳም ተራራው ፀዳሏ ነው ብለው የሚጠሩትም አልጠፉም። የዳሞታ ተራራ ለአካባቢው ነዋሪም ሆነ አካባቢውን ሊጎበኙ ለሚመጡ እንግዳ ተቀባይነቱን በአረንጓዴ የተፈጥሮ መስህቦቹ በማሸብረቅ ውበቱን በመግለፅ የሚያሳይ ተራራ ነው። ተራራውን ወደ ላይ ለሚመለከተው ዳሞታ ብዙ የሚያሳየውና የሚነግረው ታሪክ እንዳለው ያሳብቃል። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የዳሞታ ተራራ ለ800 ዓመታት ገደማ የቆየ ታሪካዊ የመስህብ ስፍራ ነው። በጥቅጥቅ ደኖች፣ በወራጅ ወንዞችና ጅረቶች፣ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ ቁጥር ስፍር በሌላቸው የእፅዋት ዘሮችም የተሸፈነ ነው። በወላይታ ዞን እምብርት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከፍታ ላይ የሚገኘው የዳሞታ ተራራ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 3000 ሜትር እንዲሁም የዙሪያ ልኬቱ ከ68 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነም ይነገራል። በአንድ ወቅት ተራራው በአካባቢ መራቆት፣ በአየር ሚዛን መዛባትና በሌሎች ምክንያቶች ግርማውንና ልምላሜውን እያጣ መጣ። ይህም የወላይታን ህዝብ በማሳሰቡ ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ ልጅ አዋቂ ሳይል ርብርብ በማድረግ ወደ ቀደመ አቋሙና ሙላቱ ለመመለስ ብርቱ ተፈጥሮን የመከላከል ፍልሚያ አደረገ። ፍልሚያውም በአካባቢው ማህበረሰብ አሸናፊነት በመጠናቀቁ ተራራው ልምላሜውን ጠብቆ አሁን የተላበሰውን ግርማ እንዲይዝ በማድረግ ሊያጣው የነበረውን ጥቅጥቅ ደን በመመለስ የመሬት መሸርሸርን ከመከላከልና የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አልፎ ትልቅ የአይበገሬነት ታሪክ እንደፃፈም ይወሳል። ለዚህም ነው ዳሞታን ከወላይታዎች ማህበረሰቡን ከተራራው ለመለየት እንደማይቻልና ጠንካራ ተዛምዶን የመሰረቱ መሆናቸው የሚገለፀው። የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌ አቶ አብርሃም ባቾሬ እንደሚሉትም ዳሞታ በርካታ የቱሪስት መስህቦች፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የሀገር በቀል እፅዋት፣ የዱር እንስሳትና ጥንታዊ የወላይታ ነገስታት መናገሻ ስፍራዎች ባለቤት ነው። የዳሞታ ተራራ ከወላይታ ህዝብ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም ከአሸናፊነት ወኔው ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑም ያነሳሉ። በዙሪያው ዘመናትን ያስቆጠረ የጥቅጥቅ ደንና የነገስታት መኖሪያ እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት የሚገኙበት መሆኑን አንስተው ለወላይታ ሶዶ ከተማም የተለየ ግርማ ሞገስን እንዳላበሳት ተናግረዋል። በዳሞታ ተራራ ዙሪያ የተኮለኮሉት ወንዞችም መነሻቸውን ከተራራው በማድረግ ወደ ታች እየተገማሸሩ ይነጉዳሉ። ወይቦ፣ ቁሊያ፣ ካልቴ ቶቦቤ፣ ሀመሳ፣ ሊንታላ፣ አይከሬ፣ ዋላጫ፣ ጫራቄ፣ ቦልዖ፣ ካዎ ሻፋ፣ ጋዜና ሻፋና ሌሎች ወንዞች ከዚሁ ተራራ ተጎራብተው፣ ከተራራው ያገኙትን መዳኛ ፀበል ለሌሎች ለማቋደስ አየተንደረደሩ ይወርዳሉ። ለአካባቢው ማህበረሰብም ልምላሜያቸውን ያጋባሉ፤ ብርቱውን መሬቱን ምሶ ገበታውን እንዲያበለፅግ ያተጋሉ። ሁሉም ግን የዳሞታ መልዕክተኞች፣ የዳሞታ ተጧሪዎች ናቸው። እንደ አቶ አብርሃም ገለፃ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገደማ የክርስትና ሀይማኖትን በአካባቢው በማስፋፋት ስመ ገናና የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ክርስትናን ለመስበክና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ለመፈጸም ዳሞታ ተራራን ይወጡ እንደነበረ ከልጅነታቸው ይነገራቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ድካም ሲሰማቸው እረፍት የሚያደርጉበት ለመንፈስ ሃሴትን የሚያጎናፅፍ ስፍራ ነው የዳሞታ ተራራ። በዚህ ምክንያት "ጦሳ ፔንጊያ" የእግዜር መተላለፊያ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠውና "ጣዛ ጋሯ" የንጉስ ሞቶሎሚ ቤተ-መንግስት፣ የንጉስ ሞቶሎሚ የጥምቀት ሥፍራ፣ ቆሊ ቦርኮታ፣ ዳጌቾ፣ ቦቄና ሶዶ፣ ጦማ ገሬራና ሌራቶ ጎዳ የተሰኙ ታሪካዊና የሚጎበኙ ስፍራዎች ይጎበኙበታል በዳሞታ ተራራ። ካዎ ሞቶሎሚ፣ ካዎ ዳሞቴ፣ ካዎ ጎቤና ካዎ ጦና የሚባሉ የወላይታ ነገስታት ቤተ-መንግስታቸውን በተራራው አናትና ግርጌ ላይ ይገነቡ እንደነበር አቶ አብርሃም ይናገራሉ። የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዳሞታ ተራራ በወላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያለው መሆኑን ይገልፃሉ። ከተራራው አናት መነሻቸውን የሚያደርጉ ወንዞች የወላይታን ምድር አጥግበው ሰዎችና እንስሳቱን አጠጥተው ወደ ብላቴ እና ኦሞ ወንዝ ይፈሳሉ። የዳሞታ ተራራ ሌላው ጠቀሜታው መሬት እንዳይሸረሸር ቀጥ አድርጎ በዛ ግዝፈቱ ይዟል ይሄም ለመንገድ ደህንነትና የአካባቢውን አየር ተስማሚ ከማድረግ አኳያ አይተኬ ሚና አለው። በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነው የዳሞታ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከዘመናት በፊት ተጀምሮበታል ይላሉ አስተዳዳሪው። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በከፊል ለሶዶ ከተማ የሚያጠጣውን የዳሞታ ተራራ የቱሪስት ማዕከል ለማድረግ ከዩኒቨርስቲና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል። የዳሞታ ተራራ ታሪካዊ ይዘቱን ስንመለከት አካባቢው ቀደም ሲል የነገስታት መናገሻ ቦታ ነበር የሚሉት ደግሞ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ዶክተር አበሻ ሽርኮ ናቸው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከወላይታ ሥርወ-መንግስት መካከል ካዎ ሳቴ ሞቶሎሚና የሌሎች ነገሥታት መናገሻ ስፍራ ስለነበር በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያለው ታሪካዊ ስፍራ ነው። የዳሞታ ተራራ ለአብዛኞቹ በወላይታ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች የስያሜያቸው መነሻ ነው። ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞታ ወይዴ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎችና ሌሎች ቀበሌያት የተራራውን ስም መነሻ ያደረጉ መሆኑ ተራራውን ታሪካዊ ያደርገዋል። እዚሁ ተራራ ላይ ካሉ የተለያዩ መስህቦች መካከል የጥንታዊ ዋሻ "ሞቼና ቦራጎ" ዋሻ አንዱ ነው። ይህ ዋሻ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ የጥንት ሰው መኖሪያ ዋሻ ነበር። ዋሻው በዳሞታ ተራራ ከሚገኙ ከአምስት በላይ ዋሻዎች አንዱ ሲሆን በተራራው በስተምዕራብ አቅጣጫ በኩል የሚገኝና ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች በዚሁ ዋሻ ይኖሩ እንደነበረም ታሪክ ያስረዳል። ሞቼና ቦራጎ ዋሻ ስፋቱ 38 ሜትር፣ የጣሪያው ከፍታ 33 ሜትር፣ የዋሻው ዙሪያ ልኬት ደግሞ 58 ሜትር፣ እንዲሁም በውስጡ ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች የመያዝ አቅም ያለው እንደሆነም መረጃዎች ያመላክታሉ። ሌላው ከዳሞታ ተራራ መስህቦች መካከል አንዱ የሆነውን ደብረ-መንክራት አቡነ ተክለኃይማኖት ገዳም ላስተዋውቃችሁ። ይህ ገዳም ለአቡነ ተክለኃይማኖት መታሰቢያነት በ1887 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ከመመስረቱ ጋር በተያያዘ የተገነባና በዳሞታ ተራራ ምዕራባዊ ራስጌ የሚገኝ የቱሪስት መስህብ ሥፍራ እንደሆነ ነው ዶክተር አበሻ የሚናገሩት። ገዳሙ የአምልኮና የፀበል አገልግሎት እየሰጠ ከአንድ ክፈለ ዘመን በላይ ያስቆጠረ በወላይታ ዞን ካሉ መንፈሳዊ ስፍራዎች አንዱ ሲሆን በውስጡ በርካታ ሐይማኖታዊና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ ጉዞ ከሚደረግባቸው መዳረሻዎች አንዱ ነው። በመሆኑም አካባቢው ለቱሪስት መዳረሻነት፣ ለአካባቢው ልማት ብሎም ለአየር ንብረት ሚዛንን መጠበቅ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።            
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች
Mar 2, 2024 4157
ሞክሼዎቹ - የአድዋ መንገሻዎች (ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ)   የአድዋ አድማስ ዘለል ገድል ሲወሳ የድሉ መገኘት የጦር አበጋዞች ከፊት ይመጣሉ። ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች፣ ባላምባራስ እና ሌሎች ባለማዕረግ አዋጊዎች የድሉ የጀርባ አጥንት መሆናቸው እሙን ነው። ከመላ ሀገሪቷ ጠረፍ ተነቃንቆ ስንቅና ትጥቁን ታጥቆ፣ ድል ሰንቆ እስከ ግማሽ ዓመት ድረስ በባዶ እግሩ የተመመውን የሀገሬው ሰራዊት በቅጡ መርተው አዋግተዋል። ከመነሻ ሰፈር እስከ አድዋ ተረተር፣ ከአምባላጌ ኮረብቶች እስከ መቀሌ ጋራና ቁልቁለቶች፣ ከእንደአባ ገሪማ እስከ ማሪያም ሸዊቶ ሸለቋማ ቋጥኞች፣ ከምንድብድብ መስክ እስከ በገሠሦ አቆበቶች፣ .... ድልና ገድል በደምና በላብ ሲጻፍ የጠላትን የ'ክዱ' ማባባያ የጠሉ፣ ለሀገር ለመሰዋት የቆረጡ ጀግና አዋጊዎች፣ የሀገር ባለውለታዎች ነበሩ። በአድዋ ድል መታሰቢያ 12 የአድዋ ጦር አበጋዞች (ጀኔራሎች) ሀውልት ቆሞላቸዋል። እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ (አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ (አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። ከነዚህ የአገር ባለውለታዎች መካከል ሁለት ስመ ሞክሼ ጀግኖችን እንዘክራለን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስን። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቀዳሚዎች ስምንት ራሶች መካከል ብቸኛው የራስ ቢትወደድ (ከንጉሥነት በታች) ባለማዕረግ ናቸው። በፈረስ ስማቸው አባ-ገድብ ይሰኛሉ። በልጅነታቸው የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ባለሟል ሳሉ ከእስረኛው ምኒልክ ጋር ተዋወቁ። ምኒልክ ከአፄ ቴዎድሮስ አምልጠው ሸዋ ከገቡ በኋላ ከእቴጌ ጣይቱ ብጡል ወንድሞች ራስ ወሌ እና ፊታውራሪ አሉላ ብጡልን ይዘው ከመቅደላ ወደ ሸዋ ተሻገሩ፤ የምኒልክ ሁነኛ ሰው ሆኑ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም በሞት እስኪለዩ ድረስ በክፉም በደጉም ዘመን የአጼ ምኒልክ ከፍተኛ አማካሪና ተወዳጅ መስፍን እንደነበሩ፣ ከጦር ሜዳ እስከ ሽምግልናም ሁነኛ ሰው ሆነው ስለማገልገላችው በታሪክ ድርሳናት ተጠቅሷል። በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ዳሞት(ጎጃም) ተዘዋውረው በተለያዩ ግዛቶች በአስተዳዳሪነት ሰርተዋል። ድሕረ መተማ ጦርነት ምርኮኞች እንዲመለሱ፣ ድንበር እንዲካለል በመስራትም የዲፕሎማሲ ስራቸው ይጠቅሳል። ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከተሳተፉባቸው ደማቅ ታሪኮች መካከል የአድዋ ድል ይጠቅሳል። ጦርነቱ አሀዱ ብሎ የጀመረው ሕዳር 28 ቀን 1888 አምባላጌ ነው። ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው በዚህ ጦርነት ጀኔራል ቶዚሊ የተባለው የጠላት ጦር መሪ የተገደለበት ነው። በዚህ ዐውደ ውጊያ አባ ገድብ አንዱ ወሳኝ የጦር አበጋዝ ነበሩ። በተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደተመዘገበው ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ከግዛታቸው ከዳሞትና አገው ምድር የተውጣጣ ስድስት ሺህ እግረኛ እና ፈረሰኛ ጦር ይዘው አድዋ ዘምተዋል። “አባ ገደብ መንጌ እያለ ኧረ ጐራው አምባ ላጌን ሰብሮ ቶዘሊን አስጐራው” የተባለው ለዚህ ይመስላል። አባ ገድብ ጥቅምት 11 ቀን 1903 ምሸት ከራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው ጋር እየተጫወቱ ካለምንም ህመም ድንገት አርፈው ቅድስት ሥላሴ ተቀበሩ። ራስ ቢትወደድ መንገሻ ልጆቻቸውን ከተለያዩ መኳንንት ጋር በጋብቻ በማጣመር በኢትዮጰያ ታሪክ ተጠቃሽ መሆን ችለዋል። ለአብነትም ዘውዲቱ መንገሻ ጠቅላይ ሚኒስትር መኮንን እንዳልካቸውን፣ አስካለማርያም መንገሻ ልዑል ራስ ኅይሉን አግብተው የልጅ ኢያሱን ባለቤት ሠብለወንጌል ኅይሉን ወልደዋል። ደጃዝማች ጀኔራል አበበ ዳምጠውን ያገቡት ወሰንየለሽ መንገሻ ደግሞ የአልጋወራሽ አስፋወሰን ባለቤት ልዕልት መድፈሪያሽ ወርቅ አበበን ወልደዋል። ሌላው የአድዋ ጀግና የጦር መሪ ራስ መንገሻ ዮሐንስ (አባ ግጠም) ናችው። ትውልዳቸው ትግራይ፣ ዘመኑም 1857 ዓ.ም ነው። የአድዋ ጦር ውሎ ቁልፍ ሰው ራስ መንገሻ የአጼ ዮሐንስ (አባ በዝብዝ) ልጅ ናቸው። አጼ ዮሐንስ በተሰዉበት በመተማው ጦርነት ተሳትፈዋል። አባታቸው ከሞቱ በኋላም የትግራይ አገረ ገዥ ሆነዋል። በአድዋ ዘመቻ 12 ሺህ ጦር አሰልፈው በብርቱ ተዋግተዋል። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከአድዋ ጦርነት ቀደም ብሎ በአጼ ምኒልክ ላይ እንዲያምጹ ኢጣሊያኖች ሲገፋፋቸውና ሲያባብላቸው ቢቆዩም ከስልጣን ሽኩቻ ይልቅ የኢትዮጵያን ነጻነት መርጠዋል። ከአጼ ምኒልክ ጋር ቢኳረፉም በሀገር ሉዓላዊነት ግን አልተደራደሩም። የኢጣሊያ ወራሪ ጦር ትግራይ ሲገባም ራስ መንገሻ የወገን ደጀን ጦር እስኪደርስ ወደራያ አፈግፍገው፣ በአምባላጌ ጦር ሜዳ አንዱ ተሳታፊ የጦር ጀግና ነበሩ። ራስ መንገሻ የትግራይ ሀገረ ገዥ በመሆናቸውም የእርሳቸው እና በስራቸው የነበሩት የራስ አሉላ እንግዳ ጦር በጄኔራል አልቤርቶኔ ከሚመራው ጠላት ሃይል ቀዳሚው ተፋላሚ እንዲሆኑ አድርጎታል። “አይከፈት በሩ መግቢያ መውጫችን በል ተነስ መንገሻ ግጠም በር በሩን ይህን ጎሽ ጠላ ማን አይቀምሰው መንገሻ ዮሐነስ አንተን ገፍተው...” ተብሎ የተገጠመላቸውም ለዚህ ነው። የጠላት መግቢያ በር ዘብ በመሆናቸው። አባ ግጠም በአድዋው ታሪካዊ ጦርነት አሰላለፋቸው ማርያም ሸዊቶ በተሰኘው ተራራ በኩል ሲሆን ከራስ አሉላ፣ ከዋግሹም ጓንጉል ብሩና ከደጃዝማች ሀጎስ ጋር በመሆን ነበር። የጠላትን የመጀመሪያ ጥቃትን ያስተናገዱትም ራስ መንገሻ ዮሐንስ ናቸው። የአድዋ ድል ከተበሰረ በኋላ አጼ ምኒልክ ራስ መንገሻን ሹመውና ሸልመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። አጼ ምኒልክ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማህበረሰቡ በጦርነት ስፍራ በመሆኑ ለደረሰበት ጉዳት 30 ሺህ ብር ድጋፍ ማድራገቸውን የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል የጻፉት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደአረጋይ ተርከዋል። ከአድዋ ድል ከጥቂት ዓመታት በኋላ ራስ መንገሻ በአጼ ምኒልክ ላይ በማመጻቸው ተይዘው በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሕዳር 6 ቀን 1899 ዓ.ም አንኮበር ግዞት ላይ አንዳሉ ማረፋቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ መንገሻ አቲከም ግዛት ከአገው ምድር እመይቴ ተዋበች ጋር ትዳር መስርተው ዕውቁን የትግራይ መስፍን ራስ ሥዩም መንገሻን እንዲሁም ከእቴጌ ጣይቱ የወንድም ልጅ ወይዘሮ ከፈይ ወሌ ብጡል አግብተው አስቴር መንገሻን፣ አልማዝ መንገሻንና ብርሃኔ መንገሻን ወልደዋል፡፡ ለአብነት ያክል የሞክሼዎቹን ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም እና ራስ መንገሻ ዮሐንስ አነሳን እንጂ የዛሬ የ128 ዓመት በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ የጻፉ ጀግኖች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ጀግኖቹን የመሩ የጦር መሪዎችም ብዙና ተጋድሏቸው የገዘፈ ነው። ከ11 ሺህ በላይ የጣሊያንን ሠራዊት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉ፣ 4ሺህ የሚሆኑትን እጅ ያሰጡና የማረኩ እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር እንዲያስረክብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜም ክብር ይገባቸዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። (በአየለ ያረጋል)      
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች 
Mar 2, 2024 2916
ትላንትን ከዛሬ ባስተሳሰረው የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኙ እውነታዎች ለመነሻ እኤአ በ1885 ጀርመን በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አውሮፓውያን መላ አፍሪካን በካርታ ላይ የተከፋፈሉትን በተግባር መሬት ላይ ለመቀራመት ጦራቸውን ሰብቀው፣ ስንቃቸውን ጭነውና ትጥቃቸውን አጥብቀው ያካሄዱት ዘመቻና የወረራ ጉዞ የተገታባት አድዋ እና እለቷ ዛሬ ድረስ በተገፉ ህዝቦች ልብ ታትማ በአዕምሮ ውስጥ ተቀርጻ ትኖራለች። ጣሊያን የኢትዮጵያን መሬት፣ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር ተቆጣጥሮ ሀብቷን ለሮምና ለመላው አውሮፓ ለማቅረብ የቋመጠበት የዘመናት ህልሙ የተኮላሸበት ቦታ ጭምር ናት - አድዋ። ይህ ወራሪ ኃይል ሊቢያን በእጁ ካስገባ በኋላ ጉዞውን በቀይ ባሕር አስመራ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ግብ ነበረው። ጄነራል ባራቴሪ የመደባቸው ጄነራል አልበርቶኒ፣ ጄኔራል አሪሞንዲ እና ጄነራል ቦርሜዳ በግንባር የተሰለፈውን ጦር ሲመሩ የኋላ ደጀንም እንደነበራቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ከ17 ሺህ በላይ የጣሊያን ሠራዊት 66 የሚሆኑ መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና አውቶማቲክ መሳሪያዎችን ታጥቆ የግንባር ሜዳው ላይ ስለመድረሱ "የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው እስካሁኑ ዘመን" በሚል በአንድርዜይ ባርይትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ተጽፎ በዓለማየሁ አበበ የተተረጎመው መጽሐፍ ያስረዳል። የዛሬ የ128 ዓመት፤ ዕለቱም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ዓለም የተደመመበትና ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ የሆነበት ደማቅ ታሪክ በጀግኖች አባቶች ተሰራ። በጦርነቱ የጣሊያን መንግስት የጎመጀውን የኢትዮጵያን መሬት ሊያገኝ ይቅርና ከ11 ሺህ በላይ ሠራዊቱ ሙትና ቁስለኛ ሆኑ። 4ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ለጀግኖች አባቶቻችን እጃቸውን ሰጥተው ተማረኩ። እንዲሁም 56 መድፎች፣ በርካታ መትረየሶች እና ሌሎች አውቶማቲክ መሳሪያዎቹን ለወገን ጦር አስረከበ። የቀረው የፋሽስት ሠራዊትም ተንጠባጥቦ እግሬ አውጪኝ ብሎ ፈረጠጠ። ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ክብር፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት በአውደ ግንባሩ በፈጸሙት የጀግንነት ተጋድሎ ዓለምን ያስደመመና መላውን ጥቁር ሕዝብ ያኮራ ድል ተጎናጽፈዋል። በወቅቱ ነጭን ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ በይቻላል ተክቶ ሌሎችም ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ያነሳሳ ደማቅ የታሪክ አሻራ አኑረዋል። የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር አድርጎ ለመበዝበዝ ቢመጣም ጀግንነት፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፣ እንዲሁም የአልገዛም ባይነት ወኔን የታጠቁ ኢትዮጵያውያን በሶሎዳ ተራሮች ግርጌ ቅስሙን በመስበር የአገራቸውን ክብርና ነጻነት አጽንተዋል። በዚህ አኩሪ ድል ኢትዮጵያ ለበርካታ አገራት በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች። የአድዋ ድል ደግሞ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህዝቦች የጀግንነት ተምሳሌትና የነጻነት ዓርማ እንድትሆን ያስቻለ ታላቅ አፍሪካዊ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአካባቢና በሌሎች ልዩነቶች ሳይነጣጠሉ ለአገራቸው ክብርና ነጻነት በአንድነት ቆመውና መስዋት ከፍለው ያስመዘገቡት የጀግንነት ታሪክ ነው። በዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአፍሪካና ለመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት ምልክት ሆናለች፡፡ የሰው ልጆችን እኩልነት በደም ዋጋ አረጋግጣለች።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋ ድል ደማቅና ታላቅ ቢሆንም በሚመጥነው ልክ መታሰቢያ አልነበረውም። ዛሬ ግን እነዚያ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን በሚመጥን ሁኔታ በአዲስ አበባ ፒያሳ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ” ተገንብቷል። ከአድዋ ድል 128 ዓመታት በኋላ፣ የተሰራው የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ተመርቆ ተከፍቷል። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአምስት ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድነት የተከፈለውን መስዋትነት፣ የአርሶ አደሮችን ተሳትፎ፣ የሴቶችን ተጋድሎ በሚያሳይ መልኩ፣ በአስገራሚ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የታነጸ ነው።   የአድዋ ድል መታሰቢያ የተገነባበት ስፍራ አገር በውጭ ወራሪ ኃይሎች እጅ እንዳትወድቅ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የዓድዋ ጅግኖች የዘመቻቸው መነሻ እንዲሁም ከድል በኋላ ተሰባስበው ደስታቸውን የተጋሩበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። የአድዋ ድል በዓል 7ኛ ዓመት ዳግማዊ ምኒልክ፣ ከአርበኞች፣ ከየአካባቢው ገዢዎች፣ ከውጭ አገር ዲፕሎማቶችና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በደማቅ ሁኔታ በዚሁ ስፍራ አክብረውታል። ስፍራው ዛሬ የታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሳይገነባበት በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ የልማት ስራዎች ቢታጭም ውጤታማ ስራ ሳይሰራበት ቆይቷል። አካባቢው ለረጅም ዘመናት ታጥሮ ሳይለማ በመቆየቱ እጅግ የቆሸሸ፣ ሰዎች ለዝርፊያ የሚዳረጉበት ስፍራ ሆኖ ቆይቷል። ዘመናትን ተሻግሮ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በከተማዋ ከሚገነቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዓይነቱ ልዩ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲሰራበት ተደረገ። የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ በሚስብ ኪነ ህንፃ፤ የኢትዮጵያውያንን ህያው የድል ታሪክ የሚዘክር ሆኖ ተሰርቷል።   የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የኢትዮጵያውያን የድል ብስራት፣ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ኩራት የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ መግቢያ በሮች የራሳቸው የሆነ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። የምሥራቅ ጀግኖች በር፣ የምዕራብ ጀግኖች በር፣ የሰሜን ጀግኖች በር፣ የደቡብ ጀግኖች በር፣ የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር፣ የፓን አፍሪካኒዝም በር ተብለው የተሰየሙ ናቸው። በአራቱም አቅጣጫዎች የተሰየሙ በሮች ተምሳሌትነት በዓድዋ ድል ከአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያውያን በጋራ የተሳተፉበት የጋራ ድላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡   መታሰቢያው በውስጡ ምን ይዟል? በዋናው መግቢያ:- የኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ነጻነት ድል መገለጫ የሆነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሃውልትና የሁሉም ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር ምልክት ይገኛል። የዓድዋ ጦርነት ዘመቻን ያስተባበሩትና የወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና የባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሀውልትም በዚሁ መግቢያ በኩል ይገኛል። ሃውልት የቆመላቸው 12 የጦር መሪዎች:- በመታሰቢያው የአድዋን ጦርነት በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ህዝቦች ድል ያበሰሩ 12 ዋና ዋና የጦር መሪዎች ሃውልት ተቀምጧል፣ እነሱም፤- ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ (አባ ጎራው)፣ ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ (አባ ቃኘው)፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት ተሰማ ጎሹ ( አባ ጠና)፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ አባ ቡላ (አባ ሻንቆ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮቢ (አባ ጠለስ)፣ ራስ ቢተወደድ መንገሻ አቲከም ቢተርፉ (አባ ገድብ)፣ ራስ ወሌ ብጡል ሃይለማሪያም (አባ ጠጣው)፣ ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን (አባ መርከብ)፣ ራስ አባተ ቧያለው ንጉሱ (አባ ይትረፍ)፣ ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ ( አባ ነጋ)፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ (ቁሴ) ዲነግዴ ሁንዱል (አባ መቻል) እና ራስ መንገሻ ዮሃንስ ምርጫ (አባ ግጠም) ናቸው። በስተቀኝ በኩል፤- እስከ 3 ሺ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ የሚገኝ ሲሆን በመጀመሪያው ኮሪደር ላይ ደግሞ ህዝቡ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ሁሉም ልዩነቱን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በመወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እንዲሁም በጀግንነት መፋለሙን የሚሳየዩ ትዕይንቶች በእስክሪኖች ይታያሉ። በክፍሉ መሐል ላይ፤- ጦርነቱ የተጎሰመበት ግዙፍ ነጋሪት የተቀመጠ ሲሆን በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የአድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይገኛል። ከድል መልስ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ጋሻዎች፣ መሳሪያዎች፣ አልባሳት፣ መመገቢያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች፣ ስዕሎች፣ ፎቶዎች ይገኛሉ። ወደ ውስጥ መግቢያ በሆነው በምዕራብ በር ላይ የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አጼ ሚኒሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረውን የምንጭ ውሃ እቴጌ ጣይቱ ብልሃት በተሞላበት መልኩ በኢትዮጵያ ሰራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ማሸነፍ የተቻለበት የጦር እስትራቴጂ የሚዘክር ገንዳ ከእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊት ለፊት ተቀምጦ ይገኛል። የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፤- ጦርነቱ የተካሄደበትን ቦታ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታ ሌላው የአድዋ ድል መታሰቢያ ውበትም ታሪክም ነው፡፡ የአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ መልከዓ-ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ በዚሁ መታሰቢያ መቀመጡ ኢትዮጵያውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነጻነት የከፈሉትን መስዋትነት ያመላክታል። ከተራሮች አጠገብ በጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ ከዋሉ ጣሊያናዊ ስሪት የሆነ "ቶሪኖ 1883" የሚል ጽሁፍ ያለበት መድፍ ይገኛል። በጦርነቱ ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45 ሺህ ፈረሰኞች የሰሩትን ጀብድ ሊወክልና ሊዘክራቸው የሚችል ‘የአድዋ ፈረሰኞች የድል ሀውልት’ ቆሞላቸዋል፡፡ የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው ጣሊያን ለማዳን ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት ተሰባስበው የተመሙበትን የሚወክል ‘የአንድነት ድልድይ’ በሚል ተሰርቷል፡፡ የሁሉንም ተሳትፎ የሚያሳዩ የተለያዩ ሁነቶች በጦርነቱ ወቅት ህዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የነበሩ እንደራሴዎች የሚያሳይ ስዕላዊ በመታሰቢያ የተቀመጠ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የህዝቡን እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾችም ይገኛሉ።   የገበሬዎችና ሴቶች ተሳትፎ የሚያሳዩ ስራዎች በአድዋ ጦርነት ከ120 ሺህ በላይ ገበሬዎች የግብርና ስራቸውን አቋርጠው "አገራችን ተነካች" በማለት ታጥቀው ድል ያጎናጸፉ፣ ለጥቁር ህዝቦች ትልቅ ታሪክ ያስቀመጡ ጀግኖች ናቸው። በዚህ መታሰቢያ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነጻነት ማስታወሻ የኢትዮጵያ ጀግኖችን ጉዞ የሚያሳዩ ምስሎች ይገኛሉ። በጦርነት ወቅት ሴቶች የቤት ሃላፊነትን ከመወጣት በተጨማሪ በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለሰሩት ስራ የተሰየመ ማስታወሻም በአድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። የአሁኑ ትውልድ አሻራ፣- የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተባብረው አፍሪካ በራሷ አቅም መልማት እንደምትችል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊ ተምሳሌት የሆነው የህዳሴ ግድብ ፏፏቴ በመታሰቢያው ይገኛል። ኢትዮጵያውያን ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን-አፍሪካ ሃውልትም ተካቷል።   ሌሎችም የአድዋ ድል መታሰቢያ የአድዋን ጦርነት ሁነቶች ብቻ ሳይሆን ለተለያያዩ ዝግጅቶች የሚሆኑ አዳራሾችን፣ ካፍቴሪያዎችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ሌሎች ለበርካታ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችንን አካቶ የተሰራ ነው። ከ2500 በላይ እንግዶችን መያዝ የሚችል ፓን አፍሪካን አዳራሽ፣ 300 ሰዎች የሚይዝ የአድዋ አዳራሽ፣ 160 ሰዎች የሚይዝ መካከለኛ አዳራሽ፣ 300 ሰው በአንድ የሚያስተናግዱ ሬስቶራንቶች፣ ሁለት ካፍቴሪያዎችና የህጻናት ሙዚየም በውስጡ አካቷል። በሌላ በኩል በአንድ ጊዜ 1000 ተሽከርካሪ መያዝ የሚችሉ ፓርኪንግ፣ ዘመናዊ ጂምና ሌሎችም ተካተዋል። የአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋ ጊዜ የማይሽረው፣ ዘመን የማይለውጠው የጀግንነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን ማሳያ፣ ለነጻነት የታገሉና የተሰዉ ጀግኖች የሚታሰቡበት የታሪክ ማስታወሻ ነው። የአድዋ ድል ትሩፋቶችን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ በየትውልዱ ለማስተማር የሚያግዝ የዘመናት የነጻነት መንፈስን የሚያስተጋባ፣ ለመጪው ትውልድ የሚሻገር እውነት ነው። እናም የአድዋ ድል መታሰቢያ የወል ታሪካችንን የምንገነባበት የማዕዘን ድንጋይ ነው።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 12223
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16572
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 8576
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 9814
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 27855
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22856
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16572
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12632
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 12223
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 11488
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 11257
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 10716
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 27855
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 22856
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 16572
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 12632
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
መጣጥፍ
በአንድነት የመምከር ብሩህ ተስፋ! 
May 13, 2024 160
በአንድነት የመምከር ብሩህ ተስፋ! በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) ሀሳብ ያፋቅራል፤ ሀሳብ ያቃርናል። በማንኛውም ጊዜ የሚነሳ ሀሳብ በውይይት ዳብሮ በሰዎች የሕይወት ኡደት ውስጥ መግባባት፣ መተማመን እና መስማማት የሚሉ መሠረታውያንን ሲያስከትል ሰዎችን ልብ ለልብ በማገናኘት አንድ የማድረግ ኃይሉ ከፍያለ ይሆናል። ያን ጊዜ ሰላምና ፍቅር በአብሮነት ታጅቦ በጋራ ማንነት ይደምቃል። በተቃራኒው ሀሳብ በልዩነት የተወጠረ ከሆነ በጊዜ ሂደት እየከረረ ወዳጅነትን የመበጠስ አቅም ያገኛል። ይህ እንዳይሆን ሀሳቦችን በውይይት ማቀራረብ የመጀመሪያ ጉዳይ የመጨረሻም መፍትሄ ነው። ሰው እንደመልኩ አስተሳሰቡና ግንዛቤው ቢለያይም ዙሮ አንድ የሚሆንበት ሰብዓዊ ፀጋ ተችሮታል። ይህም ከራስ በተጨማሪ የሌሎችንም ሀሳብ አዳምጦ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ የሚያስችል ማስተዋል ነው። ማስተዋል ደግሞ ግራ ቀኝን የመቃኘትና የመመዘን ጥበብ ሲሆን፤ የሌሎችን ሀሳብ ከእውነታ ጋር ለማጤን ይረዳል። መነጋገር በብዝኃ አስተሳሰብ እና ማንነት ውስጥ የመከባበር እሴትን በማጉላት በሕዝቦች መካከል አንድነትንና መቀራረብን ይፈጥራል። ፍቅር ሰብኮ፣ ሰላም ዘርቶ አብሮነትን ለማጨድ የሚያስችል ከጥንትም በማህበረሰቡ ወስጥ ያለው ጥበብ ውይይት ነው። ማህፀነ ለምለሟ ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ከብዝሃ ባህልና እምነት ጋር አቅፋ ይዛለች። ብዝኃነት ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊነት ስሟን በአብሮነት የመኖር ተምሳሌት የሚያስጠራ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሚያዘጋጀው ምቹ ሁኔታ ኢትዮጵያዊያን በችግሮቻቸው ላይ በጋራ ሊመክሩ ነው። በምክክሩም "የኢትዮጵያዊነት ቀለም፣ የአብሮነት መንፈስ፣ የመከባበር እና የሰላም እሴት አብቦ ፍሬው በምድሪቱ እንዲታይ ያደርጋል" የሚል ብሩህ ተስፋን ሰንቀዋል። ለችግሮቻቸው መፍቻ ቁልፍ ውይይት መሆኑን ስለተረዱትም ምክክሩን አጥብቀው ሽተዋል። በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት መምህር እንዳለ ንጉሴ እንደሚሉት፤ በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ችግሮች ሲፈጠሩ ለመፍትሄው አፈ ሙዝ እንጂ ጠረጴዛ አይታሰብም። ለችግሮች መፍትሄ በሀይል ይገኝ ይመስል ከሰላማዊ ውይይት ይልቅ ጉልበትን መርጠው ተመሳሳይ አዙሪት ውስጥ የገቡ አገራት ጥቂት አይደሉም። በዚህም ወደ መፍረስ አልያም ወደ መዳከምና አቅም አልባ የመሆን ደረጃ ላይ የደረሱ አገራት አሉ። ኢትዮጵያ ግን ከዚህ በመሻገር የውይይት ዐውድ በማዘጋጀት ልጆቿ በችግሮቻቸው ላይ በአንድነት እንዲመክሩ ተግታ እየሠራች ነው። ኢትዮጵያዊያንም በአንድነት ተወያይተው ከልዩነቶቻቸው ይልቅ አንድ የሚያደርጓቸውን አጉልተው ለማውጣት ጫፍ ላይ ደርሰዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ደግሞ በአንድ ሀገር ውስጥ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመንና ግልጽነትን ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለው ነው መምህር ንጉሴ የገለጹት። እንደመምህሩ ገለጻ፤ ከውይይቱ እንደ ሀገር ፖሊሲ ሊቀረጽባቸው በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን በገብዓትነት ለመሰብሰብ ይቻላል። በምክክሩ በዋናነት የሰላምም ሆነ የግጭትን ውጤት የሚቀምሰውን ማኅበረሰብ ማሳተፍ ችግሮችን በጋራ የመፍታት ልምድ እንዲዳብር ያደርጋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዚህ ረገድ አካታች መርህን መከተሉ በዜጎች ውስጥ ጥሩ ተስፋ እንዲፈጠር አድርጓል። የሕዝብን ፍላጎት አዳምጦ ምላሽ የሚሰጥ አካልን ፊት ለፊት አስቀምጦ ምክክር መደረጉ ከውይይት ማግስት አዎንታዊ ምላሽ ለማግኘት ያስችላል። በሁሉም ዘንድ ተቀባይነቱ ከፍ ያለ መንግስት የመፍጠር ዕድልን ከማስፋት ባለፈ ልዩነትን የሚያሰፉ ችግሮችን ከስር መሠረቱ የመንቀል አጋጣሚን እንደሚያመጣ ነው መምህር ንጉሴ የገለጹት። የምክክር ኮሚሽኑ ዜጎችን አንድ የሚያደርጉ ጉዳዮችን በማንጸባረቅ የጋራ እሴት የመገንባት ኃላፊነት ተጥሎበታል። ይህ እውን በሚሆነበት ጊዜ የእኔነት ስሜት ተመናምኖ የእኛነት የሚለመልምበት አስተሳሰብ በዜጎች ውስጥ ይሰርጻል ተብሎም ይጠበቃል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነትና በጋራ ሀገር በአንድነት ተባብሮ መስራትና በፍቅር የመኖር እሴት እንዲለመልም ምክክሩ መሠረት ይጥላል። የኢትዮጵያውያን እሴትና የኮሚሽኑ ቅቡልነት! ኢትዮጵያውያን የሀሳብ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት የሚያስችል ባህላዊ እሴት ያላቸው ሕዝቦች ናቸው። ምንም እንኳ ከቦታ ቦታ ቢለያይም እያንዳንዱ ብሔረሰብ ግጭት የሚያስወግድበት ባህላዊ ሥነ ሥርዓት አለው። የአፈጻጸሙ ሂደት ጉራማይሌ ሊሆን ቢችልም እንኳ የሰላም ግንባታ ሂደት መሠረቱ ውይይት ነው። ይሁንና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምዳችን በዘመናት ሽግግር ውስጥ የመደብዘዝ ዕድል ገጥሞታል። ይሁንና ከማኅበረሰቡ ማንነት ውስጥ ጨርሶ ስላልጠፋ ይህ በጎ እሴት አሁን እየታየ ላለው የሰላም እጦት ሁነኛና አስተማማኝ መፍትሄ ስለሚያመጣ ምክክሩ ተቀባይነት አግኝቶ በተስፋ ሊጠበቅ ችሏል። በሌላ በኩል የምክክር ኮሚሽኑ የሚፈጥረው ምቹ ሁኔታ ዜጎች ችግሮቻቸውን ተናግረው ሊደመጡ የሚችሉበት ሰፊ መድረክ በመሆኑ ከሕዝቡ ዘንድ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቷል። መምህር እንዳለ እንደሚሉት፤ ውይይት ለሰላም ግንባታ ብቸኛ አማራጭ ሲሆን፤ መንግስትም የሕዝብን ሀሳብ ለመስማት ዕድል ያገኛል። በእዚህም የምክክር ኮሚሽኑ ተቀባይነት መጉላቱን ነው የገለጹት። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኢትዮጵያውያን በችግሮቻቸው ላይ መክረው ለመግባባት የሚያስችላቸው ነው። የውይይት መድረኩ አንዱ የሌላውን ችግር በመረዳት ሀገራዊ እይታውን የሚያሰፋበት መነጽር ይፈጥርለታል። ለመፍትሄ ከመነሳት በፊት ችግሮችን ማወቅ ይቀድማልና በምክክር ወቅት ኢትዮጵያ ምን መልክ እንዳላት ዋና ዋና ችግሮቿስ ምንድን ናቸው? የሚሉት በተወያዮች በኩል ይንጸባረቃሉ። የተወያዮች ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ውጤታማነት በተወያዮች የሚወሰን ነው። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አደረጃጅቶች ሀሳቦቻችንን ያደርሱልናል ብለው የወከሏቸው ግለሰቦች አሉ። በመሆኑም እነዚህ የህብረተሰብ ተወካዮች ላለመግባባት ምክንያት የሆኑ ዋና ዋና ችግሮችን ለውይይት ይዞ ለመቅረብ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ይህን ሀሳብ የሚያንጸባርቁት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሰቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር አጥናፉ ምትኩ ከማህበረሰብ ተወካዮች በሳል ሀሳብ ይዞ መቅረብ እንደሚጠበቅ ይገልጻሉ። የግል ሀሳብን ሳይሆን የወከሏቸውን ህዝቦች ፍላጎትና አስተሳሰብ ማንጸባረቅ የተወያዮች ግዴታ ነው። በውይይት ወቅትም የራስን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ሀሳብ የማድመጥ ባህልን አጉልቶ ማንጸባረቅ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ተወያዮች ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ የጋራ መፍትሄ የማፍለቅ ሃላፊነትም አለባቸው። የመቻቻል እና የመከባበር ልምድ በውይይት ወቅት ጎልቶ እንዲወጣ ከማድረግ ባለፈ ወደ ማኅበረሰቡ ማዛመትም አስፈላጊ ነው። ያለፈውን በማንሳትና በመቆስቆስ አንዱ ሌላውን የሚከስ ሳይሆን ቁስሉን ለማከም መፍትሄ የሚፈልግ ስብዕናን መላበስ ያስፈልጋል። በእዚህ መንፈስ ለውይይት ከቀረብን ለዘመናት ሳያግባቡን የቆዩ ችግሮችን ፈትቶ እንደ ሀገር ለመሻገር አቅም መፍጠር ይቻላል። የዜጎች ድርሻ ተስፋ የነገ ብርሃን ጮራ ነው፤ ነገን የመመልከት መነጽር። ተስፋ ስኬታማ የሚሆነው ደግሞ ዛሬ በሚሠራው ሥራ ነው። እንጀራ ተጋግሮ ከመበላቱ በፊት ጤፍ ተፈጭቶ መቦካት አለበት። እንጀራ የመብላት ተስፋ ጤፍ ከመዝራት ጀምሮ የማስፈጨትና የማቡካት ሂደትን ይጠይቃል። የምክክር ኮሚሽን ፍሬያማ ውጤት በቅድመ ዝግጅት ምዕራፉ የጠራ ግንዛቤ መያዝና ቀና አመለካከት መላበስን ይጠይቃል። ይሆናል፤ ይሳካል ብሎ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ማድረግና ከአላስፈላጊ ትችት መራቅም እንዲሁ። መምህር አጥናፉ እንዳሉት የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማ ግቡን እንዲመታ በተለይ የአገር ሽማግሌዎች አገር በቀል እውቀቶችን በማቀበል፤ ምሁራን የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመቀመር እና የምርምር ሥራዎችን በማቅረብ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል። አካታችነቱን ተጠቅመው ሀሳብ ለማዋጣትና ለመደገፍ ለዜጎች የተሰጠ እድል በመሆኑ በአገባቡ በመጠቀም ተባብሮ እውን ማድረግ ይገባል። ኢትዮጵያ ብሩህ የአብሮነትና የሰላም ተስፋን በምክክር ኮሚሽኑ ላይ የመጣሏ ምሥጢር የቤት ገበናን በቤት ውስጥ መፍታት የሚችል ቁልፍ ይዞ ስለተነሳ ነው። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሀገር በቀል እውቀቶችን ተንተርሶ ከባዳ ዐይንና ጆሮ የራቀ ሁነኛ መፍትሄን እንካችሁ እያለ ነው። ዜጎችም ለመቀበል እጃቸውን ዘርግተው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ይሄን ደግሞ በየአካባቢው ለኮሚሽኑ እየተደረገ ያለው የህዝብ አቀባበልና ድጋፍ ያረጋግጣል። ኮሚሽኑ አሁን የቀረውን የቅድመ ውይይት ሂደት ጨርሶ ወደዋናው ምክክር ሲገባ ከአንደበት ይልቅ ለጆሮ ቦታ ሰጥቶ በሰከነ መንፈስ ውይይቱን የማስኬድ ኃላፊነት መሸከም ከሁሉም ይጠበቃል። ሰላም !!!
ከፈተናዎች ባሻገር . . . !
May 4, 2024 374
ከፈተናዎች ባሻገር . . . ! (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን ኢዜአ) በዓለም ውስጥ ሆኖ በአንዳች ምክንያት የወደቀ ይነሳል፤ የታመመ ይድናል፤ የፈረሰ ይጠገናል፤ የደከመ ይበረታል፤ የተኛ ወይም ያንቀላፋም ይነቃል። ይህን እውነት ሰው በልቡ ተስፋ አድርጎ ውሎ ያድራል።ነገን ያልማል። "ሲጨልም ይነጋል" እያለ ለራሱ ይጽናናል። መከራ ሲበዛበት "ሊነጋ ሲል ይጨልማል" በሚል አዲስ ተስፋን በውስጡ ይዘራል። ከእነዚህ ተቃራኒ የሰው ልጅ ከህይወት ዑደት ኩነቶች ባሻገር በተለያዩ የእምነት ተቋማት አስተምህሮ ደግሞ የሞተ የሚነሳበት መንፈሳዊ ተስፋ አለ። ይህም ትንሣኤ ይባላል- ከሞት በኋላ የሚኖር ሕይወትን የሚያሳይም መነጽር። "ትንሣኤ" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን፤ ቀጥተኛ ትርጉሙ መነሳት ነው። መነሳት የሚነገረው ለወደቀ፤ ለደከመ እና ለሞተ ነው። እንዲሁም ከነበረበት ከፍ ማለት ቀና ማለት መለወጥና ወደ አዲስ መልካም ነገር መሸጋገርን ያመለክታል። በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትንሣኤ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስን ከሞት መነሳትን መሠረት በማድረግ ነው። ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ የሰው ልጆች ማድረግ ስለሚገባቸው በጎ ምግባራት እርሱ በመተግበር አስተምሯል። የበጎ ተግባራት ውጤት ደግሞ ከሞት በላይ ራስን ከፍ አድርጎ በሕይወት ዙፋን ላይ መቀመጥ እንደሆነ አሳይቷል። ፍቅር እንዲጎለብት ለሌላው መኖርና አልፎም መስዋዕት መሆንን በግልጽ አንጸባርቋል። እርሱ መልካም ነገር አድርጎ "እናንተ እንዲሁ አድርጉ" ብሏል። ለአብነትም ፍቅር በቀዳሚነት የሚጠቀስ ትምህርቱ ነው "እርስ በእርስ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህች ናት" ብሏል። ፍቅሩን ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ በመስጠት ገልጧል። ነገ ምን እንዲያውም ከደቂቃዎችና ሰዓታት በኋላ ምን እንደሚፈጠር በማናውቀው ተገድቦና ተተምኖ በተሰጠን የህይወት ዑደት ውስጥ በምናልፋቸው የትኞቹም ጎዳናዎች ምህረትን፣ ይቅር ባይነትን ይጠየቃል። ለሰው ልጅ ለራሱም ቢሆን ቂምና ቁርሾ ያላደረበት ልብ ያስፈልገዋል። የወደደንን ወይም የሰበሰበንን ሳይሆን ተቃራኒውን የፈጸመብንን የመውደድና ፍቅርን በተግባር የማሳየት ልምምድ እንዲኖረን ያስተምራል። ይህም ከራሳችን ጀምሮ ለአካባቢያችን ሁሉ ሰላምና መረጋጋትን ይፈጥራል። ሌላው የተግባር ትምህርቱ ትህትና ነው። የሰው ልጆችን ለማክበር ራሱን ዝቅ አድርጓል። የደቀ መዛሙራቱን እግር ተንበርክኮ አጥቧል። "እናንተም እንዲሁ ለሌሎች አድርጉ" ሲልም አስተምሯል። የዚህ ዓይነቱ ተግባር ዛሬም በኢትዮጵያውያን እሴት ውስጥ ይስተዋላል። በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፉ መጥቷል። ቤታችን የወላጆቻችንን አልፎም የመጣን እንግዳ እግር ማጠብ የመልካም ሥነ ምግባር ምገለጫችን ሆኖ ቆይቷል። ይህ እርስ በርስ መከባበር እያጠነከረ ይመጣል፤ ውሎ ሲያድርም በስነ ምግባር የታነጸ የጠንካራ ማህበረሰብ መገለጫም ይሆናል። ትህትና ከአንገትን ጎንበስ ብሎ ሰላምታ መሰጣጣት ብቻ አይደለም። ሌሎች የተሻሉ እንዲሆኑ ማሰብን ያካተተ ከልብ የሚፈልቅ ተግባር ነው። በትዕቢት አውቃለሁ ባይነት ሳይሆን ራስን ዝቅ በማድረገ መንፈስ የተገዛ ማንነት ማዳበርን ይጠይቃል። ድርጊት የሀሳብ ውጤት ነው። ስለሆነም እርስ በርሳችን ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ እንዲሁም በስራ ቦታችን ካሉ ባልደረቦቻችንን ከልብ በመነጨ ትህትና መቀበልና ማስተናገድ አልፎም መታዘዝ ይጠበቅብናል። ይህ ነው የትህትና ጥቅ እሴቱ። በጎነት፣ ፍቅር፣ ትህትና፣ ለጋስነትና ቅንነትን የሰው ልጅ ገንዘቡ ቢያደርግ ሞትን አሸንፎ ይከብራል። ከመውደቅ ባሻገር መነሳት አለ። ከጨለማ በኋላ ብርሃን ይኖራል። ይህም ከጽልመትና ከአስቸጋሪ ነገሮች አልፈን ብርሃን ማየት እንደሚቻል የጸና ተስፋ በመያዝ ነጋችንን ማየት ይኖርብናል። ትንሣኤ ደስታ ነው፥ ከድቅ ድቅ ጨለማ በኋላ የሚገኝ ልዩ ብርሃን፤ ከመቃብር በላይ የሚገኝ ሐሴት ነው። የትላንት መከራ ላይ የታነጸ ጽኑዕ ደስታ፤ የትላንት መልካም ነገርን መነሻ አድርጎ የሚገኝ ክብር ነው። የሰው ልጅ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ነገን ተስፋ አድርጎ ጠንክሮ መስራት ከቻለ መልካም ነገር ሁሉ ማግኘት ይችላል። ዛሬም ዓለም ብዙ ውጣ ውረዶችን ታስተናግዳለች። እንደ አገር ኢትዮጵያ ብዙ ችግሮች እያጋጠሟት ነው። ችግሮቹና መከራው ማብዛቱ የነገን ትንሣኤ ለማምጣት ነው። ከፈተናዎች ባሻገር ድል አለ፤ ትንሣኤ ይገለጻል። ለዚህም ነው ምንም ፈታኝ ነገር ቢኖር፣ ችግሮች ቢደራረቡም ተግቶ ሰርቶ ወደ ብርሃኑ መውጣት ይቻላል የምን ለው። የትንሣኤ በዓል ከበዓል ባሻገር በበጎ እይታ በመቃኘት፣ በፍቅር በመታነጽና የቅንነት ጎዳናን በመያዝ ለአገር እና ለራሳችን ክብርን ለመጎናጸፍ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት መሆን አለበት።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም