የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘመን የተሻገረ የነጻነትና የአንድነት አርማ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘመን የተሻገረ የነጻነትና የአንድነት አርማ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ ፤ጥር 17/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘጠኝ አሥርት ዓመታት የታተመ የማይበገር የአየር ክልልን የማስጠበቅ ፅናት፣ በሰማይ ላይ የተጻፈ የሉዓላዊነት ታሪክ፣ ዘመን የተሻገረ የነጻነትና የአንድነት አርማ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡
ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም፤ የጀግንነት አሻራውን የሚያሳርፍበት፣ ብቃቱን የሚለካበትና የሀገርን ኩራት የሚያውጅበት ሰፊ የመጫወቻ ሜዳው ነው ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት።
ሰማዩ የኛ ነው የሚል መርሁን በኩራት ለዘጠና ዓመታት አውጇል። 90 ከቁጥር በላይ ነው የምንለው በምክንያት ነውም ብለዋል፡፡