ቀጥታ፡

የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ጥቅምን በተግባር ስላየነው አጠናክረን እንቀጥላለን - አርሶአደሮች

አሶሳ፤ ጥር 14/2018 (ኢዜአ) የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ጥቅምን በተግባር በማየታቸው ተግባሩን አጠናክረው መቀጠላቸውን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቡልድግሉ ወረዳ አርሶአደሮች ተናገሩ።

በምዕራብ ወለጋ ዞን በ 487 ተፋሰሶች ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ እየተከናወነ ነው

የተፋሰስ ልማት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሰረት ሆኗል- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ


 

አርሶአደ ሂድር ኡስማን እንዳሉት፤ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ዘላቂ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም እንዲኖር ከማድረግ በተጨማሪ የአካባቢውን የአየር ንብረት በማስተካከል ሚናው የጎላ ነው።


 

ወይዘሮ ማርታ ዋቅቶላ በበኩላቸው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ መሠራት ከጀመረ ወዲህ በጎርፍ የሚወሰደው ለም አፈር በመቀነሱ ምርታማነታቸው እንዲጨምርና የአካባቢው ሥነ-ምኅዳርም መጠበቁን ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ፀጋን የማልማትና የመጠበቅ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ


 

ከዚህ በፊት የተከናወነው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግ በደን እንዲሸፈኑ ማስቻሉን ያስረዱት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጭ ቢራቱ ፉፋ ናቸው።

ቀደም ሲል ከተሠራው የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ተጠቃሚነታቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም አካባቢን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ ተግባር ስለሆነ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አርሶ አደሮቹ ለኢዜአ ገልጸዋል።


 

ክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አብዱልከሪም ሙሳ፤ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ሥነ-ምኅዳር ይጠብቃል፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በደለል እንዳይሞላ ይረዳል ብለዋል።

ስለዚህ አርሶአደሩ ተሳትፎውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘንድሮው በክልሉ 57 ሺህ ሔክታር በላይ ማሳ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን መታቀዱን አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም