የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የራስን ተፈጥሯዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ታሪካዊ ሃብት ምላሽ የማስገኘት ምክንያታዊ የሕልውና ጉዳይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የራስን ተፈጥሯዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ታሪካዊ ሃብት ምላሽ የማስገኘት ምክንያታዊ የሕልውና ጉዳይ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 17/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የራስን ተፈጥሯዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ታሪካዊ ሃብት ምላሽ የማስገኘት ምክንያታዊ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ምሁራነ ገለጹ።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቂያና የጋራ ትርክት መገንቢያ መሆኑንም የተናገሩት።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ የህልውና ጥያቄ መሆኑ ይታወቃል።
በኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራንም፤ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን እንድታጣ የተደረገችበት ታሪካዊ ሴራ የሚያስቆጭ መሆኑንም ገልጸዋል።
የባህልና ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ማንነትና ስልጣኔ ከቀይ ባሕር ባለቤትነት ጋር በእጅጉ ጥብቅ ቁርኝት አለው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም የራስን ተፈጥሯዊ፣ ሕጋዊ፣ መልክዓ-ምድራዊና ታሪካዊ ሃብት ምላሽ የማስገኘት ምክንያታዊ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን ምላሽ የማስገኘት ቀጣናዊና አሕጉራዊ ሰላምና ደኅንነትን በማስጠበቅ ለፍትሐዊ የጋራ ተጠቃሚነትና ዕድገት መሠረት እንደሚሆን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያንም የሀገራቸውን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብሩ ጽኑ ህዝቦች መሆናቸውን የዓድዋ ድል ሕያው ምስክር መሆኑን አስታውሰዋል።
የጋራ ተግባቦት ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ዓይነተኛ ሚና አለው ያሉት ምሁሩ፤ አሰባሳቢ ትርክት ግንባታም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ለማስገኘት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ በመተባበር ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም መከበር መስራት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።
በአሁኑ ወቅትም የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን ምላሽ ለማስገኘት የሚደረገው ጥረት የሀገርን ዕድገትና ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ ወሳኝ ብሔራዊ አጀንዳ መሆኑንም አስረድተዋል።
በውጪ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ ጋሻው አይፈራም(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ታሪክና ስልጣኔ ከባሕር በር ባለቤትነት ጋር የተሰናሰለ ነው ብለዋል።
ለአብነትም ከአክሱም ዘመነ መንግሥታት ጀምሮ ለበርካታ ሺህ ዘመናት ያህል ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ወሰንና የግዛት መዳረሻ አካል ሆኖ እንደቆየ አስታውሰዋል።
በታሪካዊ ጠላቶች ሴራ እና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በቅጡ ባልተገነዘቡ ውስን ቡድኖች አማካኝነት ኢትዮጵያ ከተፈጥሯዊ የባሕር በር ወሰኗ እንድትገለል መደረጉን አስታውሰዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕጋዊ፣ ሥነ-ልቦናዊ፣ መልክዓ-ምድራዊ እና ፍትሕዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ትክክለኛና ምክንያታዊ ጥያቄ መሆኑን ተናግረዋል።