ቀጥታ፡

አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት እና አትሌት ቢቂሌ አንበሴ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፤ ጥር 17፣ 2018 (ኢዜአ)፦ የመጀመሪያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ዛሬ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

በወንዶች አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት አሸንፏል።

ገመቹ ዲዳ እና አትሌት አሊ ቃሲም ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

አትሌት ቢቂሌ አንበሴ በሴቶች ውድድር አሸናፊ ሆናለች።

ጉተኒ ሻንቆ ሁለተኛ ስትወጣ  ሰውሀረግ ሃይማኖት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በውድድሩ ላይ ወንድ 109፣ ሴት 64 በአጠቃላይ 173 አትሌቶች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል። 

ፌደሬሽኑ ለአትሌቶች የ366 ሺህ ብር ሽልማት ያበረከተ ሲሆን ለውድድሩ ማስኬጃ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም