ቀጥታ፡

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል

አዲስ አበባ፤ ጥር 17/2018 (ኢዜአ)፦‎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እንዳልካቸው ጥበቡ እና የሀዲያ ሆሳዕናው ቃለአብ ውበሸት በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ደስታ ዋሚሾ ለሀዲያ ሆሳዕና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ16 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሀዲያ ሆሳዕና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ20 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም