ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በተፋሰስ ልማት ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደር እና በተፋሰስ ልማት ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው
ነቀምቴ ፤ ጥር 14 /2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደርና በተፋሰስ ልማት ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የውኃ ሀብትን በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው።
ኢትዮጵያ የምትከተለው ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውኃ ሀብት አጠቃቀምና አስተዳደርም የልማት እንቅስቃሴን ለማፋጠን ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በውኃ ሀብት አስተዳደርና በተፋሰስ ልማት ስራዎች እየከናወነች ያለው ሥራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን በመግለጽ።
በሌላ በኩል ሚኒስቴሩ በተፋሰስ ልማትና በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
ከውሃ ሀብት በተጨማሪ የኢነርጂ ሀብትን በአግባቡ መለየትና ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም አንስተዋል።
በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፌዴራልና የክልሎች እንዲሁም ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።