ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ባርሴሎና ለሩብ ፍጻሜ አልፏል
Mar 18, 2026 105
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ኒውካስል ዩናይትድን 7 ለ 2 ረምርሟል። ማምሻውን በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊኒያ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። ማርክ በርናል እና ፌርሚን ሎፔዝ በጨዋታ ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ቀሪዎቹን ጎሎች ለባርሴሎና ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አንቶኒ ኢላንጋ ለኒውካስል ግቦቹን አስቆጥሯል። በመጀመሪያ አጋማሽ ተመጣጣኝ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ ባርሴሎና በሁለተኛው አጋማሽ ፍጹም የበላይነት ወስዷል። ባርሴሎና በሁለተኛው 45 አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል። የስፔኑ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል። የአምስት ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቡድኑ ስምንት ውስጥ ሲገባ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው። በሩብ ፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አሸናፊ ጋር ይገናኛል። ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል። በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ፣ ባየር ሙኒክ ከአትላንታ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል
Mar 18, 2026 112
አርባ ምንጭ ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል፡፡ በዛሬው ዕለትም የተለያዩ ተቋማት 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚገመት የምግብ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። የተለያዩ ተቋማት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ኦርቢስ ኢንተርናሽናል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች አደረጃጀቶች እንዲሁም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለተጎጂዎች ያመጡትን ድጋፍ ዛሬ ለጋሞ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል። ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ሙላቱ ገብሬ፤ ከተቋሙና ከሠራተኞች በተሰበሰበ ገንዘብ የንፁህ ውሃና የንፅህና መጠበቂያዎችን ማስረከባቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ክልል ወጣቶች አደረጃጀት የወላይታ ዞን፣ የሶዶ ከተማና የአሪ ዞን መዋቅር አባላትና በጎ ፈቃደኞችም አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዋዳ እንደገለፁት፤ አደጋው ከተከሰተበት እለት ጀምሮ የተለያዩ አደረጃጀት አባላት በነፍስ አድንና ሌሎች ተግባራት ሲሳተፉ ቆይተዋል። የዛሬ የተደረገው የምግብና የዓይነት ድጋፍ በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች ባሉ የወጣት አደረጃጀቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለተጎጂዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚውል ግምታቸው 1 ሚሊዮን ብር የሆነ የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። የፋብሪካው ኮርፖሬት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ማናጀር አቶ አብርሀም ዘሪሁን፤ በወገኖች ላይ በደረሰ አደጋ የፋብሪካው ሠራተኞችና አመራሮች በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ለተጎጂዎች አፋጣኝ ድጋፍ የሚሆንና ግምታቸው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ብርድልብሶችን ዛሬ ማበርከታቸውን ገልፀው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ፤ የተጎዱ ወገኖች ከደረሰባቸው ችግር ፈጥነው እንዲያገገሙ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ምላሽ እየሰጡ ያሉ አካላትን አመስግነዋል። በቀጣይ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረው ጥረት ሁሉም ከጎናቸው በመሆን እንዲረባረብም ጥሪ አቅርበዋል።
ለዒድ አልፈጥር በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
Mar 18, 2026 135
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9 /2018 (ኢዜአ)፦ ለ1447ኛውን የዒድ አልፈጥር ረመዳን በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት፡- ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች (ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች በተመሣሣይ ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮክ መብራት ላይ፤ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)፤ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ለውስጥ ወደ ጋዜቦ አደባባይ ለሚመጡ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)፤ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ ሳንጆሴፍ መብራት ለሚመጡ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ) ሲሆን ለሌሎች ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)፤ ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)፤ ከልደታ ፀበል ውስጥ ለውስጥ ወደ አሹ ስጋ ቤት የሚያስወጣው (ልደታ ፀበል ላይ)፤ ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)፤ ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት (ፈረሰኛ ፖሊስ ካምፕ መብራት ላይ)፤ ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ (ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ)፤ ከበርበሬ በረንዳ ወደ ድሮ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ቃና ዘገሊላ ዳቦ ቤት መስቀለኛ ላይ)፤ ከመርካቶ አካባቢ በተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ (ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ላይ)፤ ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ወደ አገር አስተዳድር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ)፤ ከ4 ኪሎ አደባባይ ወደ ውጭ ጉዳይ ለሚሄዱ (4 ኪሎ አደባባይ ላይ)፤ ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ሴቶች አደባባይ ላይ)፤ በበዓሉ እለት ማለትም ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ እንደሚሆኑ አመልክቷል። ከበዓሉ ዋዜማ ምሽቱ ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች ጋር ለምታደርገው ድርድር ውጤታማነት የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች
Mar 18, 2026 181
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች ጋር የምታደርገውን ድርድር ለማጠናቀቅ በምታደርገው ጥረት የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጥሪ አቀረቡ። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ እና ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (China Exim Bank) የልዑካን ቡድን ጋር በጋራ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ የገንዘብ ድጋፍ አማራጮች ዙሪያ ነው። በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ የቡድን 20 (G20) የጋራ ማዕቀፍ የዕዳ ሽግሽግ (debt restructuring) ሂደት አስመልክቶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ምክክር ተደርጓል። ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ ቻይና የአበዳሪዎች ኮሚቴ (OCC) ሰብሳቢ በመሆን ላሳየችው አመራርና በዕዳ ሽግሽግ ሂደቱ ወቅት ላደረገችው ገንቢ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ሂደቱ አሁን ላይ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የተጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል። አያይዘውም፣ ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች(commercial creditors) ጋር የምታደርገውን ድርድር በማጠናቀቅ በኩል የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመላክቷል።
የክልሉ ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Mar 18, 2026 276
ደቡብ ኢትዮጵያ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርዳቸውን ወስደዋል። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ሕዝቡ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ሚናውን መወጣት አለበት ብለዋል። መንግሥት ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምርጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡም ከወዲሁ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለበት አንስተዋል። ሌላው በወቅቱ የምርጫ ካርድ የወሰዱት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዞኑ ሕዝብ በአስቸጋሪ የፈተና ወቅት ላይ ቢገኝም ቀጣይ ዕጣ ፈንታው ላይ የሚወስንበትን ካርድ በመውሰድ ለምርጫው መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል በዞኑ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
ፖለቲካ

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ
Mar 18, 2026 200
ሀዋሳ ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፡-የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላላ ምርጫው ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንገኛለን- ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም በጠቅላላ ምርጫው ለመሳተፍና ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት ምርጫ ዜጎች መብታቸውን በመጠቀም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሚናቸውን የሚወጡበት ዕድል በመሆኑ ተመዝግበው ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደዋል፡፡ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል የውቅሮ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ተገኝ በቀለ ባለፉት ጊዜያት በተካሄዱ ምርጫዎች እንደተሳተፉና ለዘንድሮ ምርጫም ካርድ ወስደው መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሚናቸውን የሚወጡበት እድል ነው ብለዋል። በመሆኑም ቤተሰቦቻቸውና የአካባቢያቸው ነዋሪዎች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየቀሰቀሱ መሆኑን የገለጹት አቶ ተገኝ በመገናኛ ብዙሃን የሚደረግ የፓርቲዎችን ክርክር እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ የምርጫ ሂደት በቴክኖሎጂ መታገዙ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ለማካሄድ ያግዛል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። በተለይ ወጣቱ የምርጫ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት የጠቀሱት አቶ ተገኝ፣ ሃገርን በተሻለ መምራት የሚችል ፓርቲን በእውቀት ላይ ተመስርቶ መምረጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመምረጥ እንደተዘጋጀች የገለጸችው ወጣት ፍሬህይወት ኪሮስ በበኩሏ የምርጫ ካርድ ወስዳ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ክርክር እየተከታተለች መሆኗን ተናግራለች። ለሴቶች ተጠቃሚነት የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ እንደምትመርጥና ሴቶችም በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግራለች። በሚኖሩበት አካባቢ ዜጎች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ድርሻቸውን እንዲወጡ በመቀስቀስ እየተሳተፉ መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ የማነህ ናቸው፡፡ በቀደሙት ምርጫዎች የተለያየ ተሳትፎ እንደነበራቸው ገልጸው በመራጭነት መሳተፍ የዜግነት ግዴታም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እየደረጉት ያለው ክርክርም ህዝቡ የተሻለውን ፓርቲ ለይቶ እንዲመርጥ እድል እየፈጠረ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በአስተዳደሩ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በላቀ መልኩ ሊወጡ ይገባል
Mar 18, 2026 170
ድሬዳዋ፤ መጋቢት 9/2018(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አሰተዳደር የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በላቀ መልኩ ሊወጡ እንደሚገባ በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ኢብራሂም ዩሱፍ ገለጹ። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲካሄድ የሚጠበቅብንን እንወጣለን-የፖለቲካ ፓርቲዎች የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመገናኛ ብዙኃን እና ለማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያዎች በምርጫ ሥነ-ምግባር ዙሪያ የአቅም ግንባታ መድረክ አካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአስተዳደሩ ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ኢብራሂም ዩሱፍ በወቅቱ እንዳሉት፤ ዘንድሮ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል። ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ በማገዝ በኩል የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመው፤ ትክክለኛ መረጃን በፍትሐዊነት ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ሥልጠናውም ባለሙያዎች በዕውቀት በመታገዝ ሁሉንም አካላት በእኩልነት እንዲያገለግሉ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ብሩክ ወርቅነህ፤ የሚዲያ ባለሙያዎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መዳበር የድርሻቸውን እንዲወጡ ሥልጠናው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በምርጫ ወቅት ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ፣ ትክክለኛና ታማኝነተ ያለው መረጃን በፍጥነት ለሕዝብ ማድረስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በሥልጠናው የተሳተፉ ጋዜጠኞች በበኩላቸው፤ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። የምርጫ ሕግና ደንብን እንዲሁም ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በማክበር በንቃት እንደሚሠሩም አስታውቀዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር እና ቅስቀሳ አማራጭ ሀሳቦች የሚቀርቡበት ሊሆን ይገባል - ምሁራን
Mar 18, 2026 156
ሚዛን አማን፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ) ፡-የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያካሂዱት ክርክር እና ቅስቀሳ አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦች የሚቀርብበት ሊሆን ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ። ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በግንቦት ወር መጨረሻ ለማካሄድ የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ሥራዎችን እያከናወነች ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክርና ቅስቀሳ መርሃ ግብርም እየተካሄደ ነው። በዚህ መሰረትም የተለያዩ ሀገር አቀፍና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሀንና በተለያዩ አማራጮች ያሏቸውን አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦች በማንሳት ክርክርና ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው። በዚህ ዙሪያ ኢዜአ ያነጋገራቸው በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንደገለጹት ምርጫ የአንድ ሀገር ትልቁ የዴሞክራሲ ሥርአት መገለጫ መሆኑን ገልጸው፤ ፍትሐዊና፣ ነጻ፣ ተአማኒና አካታች እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫ ወቅት በሚያደርጓቸው ክርክሮችና ቅስቀሳዎች ለመመረጥ ያስችለናል ያሏቸውን የፖሊሲ አማራጮች ህዝብን ባከበረ መልኩ ማቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በተለይ ብሔራዊ አንድነትን የሚያስጠብቁ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር፣ በመከባበርና በመቻቻል አማራጭ ሃሳባቸውን አቅርበው የህዝብን ስነ ልቦና በጠበቀ መልኩ መከራከር እንዳለባቸው መክረዋል። በዩኒቨርሲቲው የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት መምህር ሙሉቀን አየለ በበኩላቸው እንዳሉት በቅድመ ምርጫ ወቅት የሚከናወኑ የክርክርና የቅስቀሳ ሂደቶች የፓርቲዎች ማንነት የሚለይበት ነው። በመሆኑም መንግሥት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ፣ ሲከራከሩና የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የመራጩን ሕዝብ ሞራልና ሥነ ልቦና ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል። የምርጫ ሥነ ምግባርን በመከተልና የተሻለ አማራጭ ሀሳብ በማቅረብ የነገዋን ኢትዮጵያ አጉልቶ ማሳየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤቱን በጸጋ ለመቀበል ሚዛናዊ አቋም ይዘው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏቸውን የፖሊሲ አማራጮች የምርጫ ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ ከፍ አድርገው ማዘጋጀትና ማቅረብ አለባቸው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ቢመርቅ በሪሁን ናቸው። ምርጫ የውድድር ሜዳ ሊሆን የሚችለው ተነጻጻሪ የሆኑ ጠንካራ ሀሳቦች ሲቀርቡበት መሆኑን ጠቅሰው፣ ፓርቲዎች በተሻለ መልኩ ለመሥራት መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ሀሳብ ማቅረባቸው መራጩ ሕዝብ የሚፈልገውን ለመምረጥ ያስችለዋል ብለዋል። ፓርቲዎች ለአንድ ሀገር እንደመሰራታቸው መጠን መከባበርና መቻቻልን መርህ አድርገው ሊንቀሳቀሱ ይገባል ያሉት መምህሩ፣ የመመረጥ ዕድላቸውን ለማስፋት የምርጫ ሕግና ሥርዓትን መከተል እንዳለባቸው አክለዋል። ብሔራዊ አንድነትን በሚያስጠብቁ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ሊሰሩ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል። እስካሁን በመገናኛ ብዙሀን ለክርክር የተመቻቸው መድረክ በአንጻራዊነት የተሻለ መሆኑን ገለጸው አካታችነትን በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንገኛለን- ተፎካካሪ ፓርቲዎች
Mar 18, 2026 153
ባህር ዳር፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፡- በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ለ7ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲዎች የክርክር መድረኮች በተለያዩ ሚዲያዎች በመካሄድ ላይ ሲሆን መራጮችም ድምፃቸውን ለመስጠት የሚያስችላቸውን ካርድ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። የምርጫ፤ ሂደት ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊነቱ የሚታየው በሂደቱ በመሆኑ ፓርቲዎች በነፃነት ሃሳባቸውን እያራመዱ ፖሊሲና ስትሬቴጂያቸውን ለህዝብ እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። ለሀገርና ህዝብ ሊጠቅም ይችላል የሚለውን ፓርቲ ለመምረጥም ዜጎች የፓርቲዎችን ሃሳቦች በመከታተል እየመዘኑ ስለመሆኑ ይናገራሉ። በመሆኑም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደትና ዝግጁነታቸውን በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን አነጋግሯል። ጠቅላላ ምርጫውን ለማካሄድ ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን በመጠቀም ፖሊሲና ስትራቴጂያቸውን እንዲሁም ማንፌስቷቸውን ለህዝብ በማስተዋወቅ ለፉክከሩ መቅረባቸውን ገልጸዋል። የፓርቲ አመራሮቹ በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንገኛለን እስከ ፍፃሜው ድረስም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እመቤት ከበደ፤ ፓርቲያቸው በምርጫው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ከማስተዋወቅ ባለፈ የበቁና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን እጩዎችን ማቅረቡን አንስተዋል። አብን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሰላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲ መሆኑን አንስተው፤ በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንገኛለን ብለዋል። የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ (አዲሃን) ስራ አስፈፃሚ አባል አዲሱ ጉልላት፤ በዘንድሮው ምርጫ የምርጫ ህግና ደንቡን በማክበር ለመፎካከርና ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም የፓርቲውን ፖሊሲና ፕሮግራሞች ለመራጩ ህዝብ የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በኢትዮጰያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የባህር ዳር ምርጫ ወረዳ አስተባባሪ ሃይለማርያም ብርሃኑ፤ በምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር በማድረግ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አሻራችንን ለማኖር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። በፓርቲው የተዘጋጁ አማራጭ ፖሊሲዎችን እንዲሁም እጩዎችን ለመራጩ ህዝብ በማቅረብ የማስተዋወቅ ስራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል። በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች የቅድመ ምርጫ ተግባራት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
በጠቅላላ ምርጫው የዞኑን የመልማት ጸጋዎች በመለየት አማራጭ ሃሳቦችን ይዘን ቀርበናል- የፖለቲካ ፓርቲዎች
Mar 18, 2026 183
ዲላ ፤መጋቢት 9/2018((ኢዜአ) :- በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የዞኑን የመልማት ጸጋዎች በመለየት አማራጭ ሃሳቦችን ይዘው መቅረባቸውን በጌዴኦ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። በቀጣይ ግንቦት 24 በሚካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ፣ ጌህዴድ፣ ኢዜማና ነዕፓን ጨምሮ ሌሎችም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እንደገለፁት፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የዞኑን የመልማት ጸጋዎች በመለየት አማራጭ ሃሳቦችን ይዘው ቀርበዋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የጌዴኦ ዞን ሴቶች ክንፍ ሃላፊ ወይንሸት በዛብህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሳታፊ፣ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጌዴኦ በሃገር በቀል እውቀቱ አካባቢውን መጠበቅ የኑሮው መሰረቱ መሆኑን አንስተው ይህም ጎልቶ እንዲወጣና የአርሶ አደሩን ኑሮ እንዲያሻሽል በማኒፌስቷቸው በግልጽ ለይተው ለመወዳደር እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በምርጫው በሰላማዊ መንገድ ከመሳተፍ ባለፈ የዞኑን የመልማት ጸጋዎችን በመለየት አማራጭ ሀሳቦችን ይዘው መቅረባቸውን ያነሱት ደግሞ የጌዴኦ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ግርማ ሐጌ ናቸው። ዞኑ በጥምር ግብርናና በተለያዩ እጽዋቶች የተዋበ በመሆኑ ከእርሻ ልማት ውጭ በሆኑ የግብርና ልማት ሥራዎች በተለይ በንብ ማነብ ረገድ ያለውን አቅም መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዞኑ የሚታወቅበትን የአካባቢ ጥበቃ ጸጋ እንዲጎለብት ለማድረግ በማኒፌስቷቸው አካተው ለመወደደር መቅረባቸውን ገልጸዋል። የጌዴኦ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የዞኑ ተወካይ አቶ መስከረም ተዘራ በበኩላቸው የዞኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየሰራን ነው ብለዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ፓርቲዎች የተሻለ ሃሳብ ለህዝብ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የበኩሉን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል። በፓርቲ ደረጃ ያለ ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት የሚመጣ እድገት የለም የሚል ጽኑ አቋም ይዘው እየሰሩ መሆናቸውን አቶ መስከረም አንስተዋል። በተለይ በዞኑ ለሰላም እሴት መጎልበት ትልቅ ድርሻ ያላቸው ባህላዊ እሴቶች እንዲተዋወቁ በማኒፌስቷቸው ለይተው እየሰሩ መሆኑንም አክለዋል።
ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻችን እንወጣለን - ሲቪክ ማህበራት
Mar 18, 2026 140
ሰቆጣ፤ መጋቢት9/2018 (ኢዜአ) ፡-የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻችን እንወጣለን ሲሉ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት ገለፁ። ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ትግበራ ላይ ትገኛለች። ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪክ ማህበራት ሚና የላቀ መሆኑ ይታወቃል። የሲቪክ ማህበራቱ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ በማውጣትና የታዛቢነት ሚናቸውን ለመወጣት እያደረጉት ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። የአማራ ወጣቶች ማህበር የዋግ ኽምራ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት ወንድሙ ገብረ እግዚአብሄር እንደገለጸው የማህበሩ አባላት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ እየሰሩ ነው። የማህበሩ አባላት ከወገኝተኝነት በፀዳ መልኩ በሰላም ማስጠበቅና ምርጫው ሰላማዊ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጿል። የክልሉ ወጣቶች ማህበርና የፌደራል ወጣቶች ካውንስል ለማህበሩ በሰጡት ውክልና መሰረትም 170 ወጣቶች በታዛቢነት ለማሳተፍ የልየታ ስራ ማከናወናቸውን አስረድቷል። በታዛቢነት ለተለዩ የማህበሩ አባላት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው በስልጠናው በሚያገኙት እውቀትና ባላቸው ልምድ በመጠቀም ለምርጫው ስኬት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግሯል። ወጣቱ የመራጭነት ካርድ በማውጣት በምርጫው የሚኖረውን ተሳትፎ የበለጠ እንዲያሳድግ ማህበሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አመልክቷል። የብሔረሰብ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር ሊቀ መንበር መምህር ከፍያለው አስፋው በበኩላቸው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መምህራን የበኩላቸውን ሚና ይወጣሉ ብለዋል። መምህራን በጠቅላላ ምርጫው በመራጭነት ከመሳተፍ በተጨማሪ የታዛቢነት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል 11 የማህበሩ አባላት መለየታቸውን አስረድተዋል። "7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የበኩላችንን ሚና እየተወጣን ነው" ያሉት ደግሞ የብሔረሰብ አስተዳደሩ የአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን ሰብሳቢ አቶ ኪሮስ ቸኮለ ናቸው። የፌዴሬሽኑ አባላትም የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ የፖለቲካ ፓርቲን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ ማውጣታቸውን አስረድተዋል። በጠቅላላ ምርጫውም የፌዴሬሽኑ 50 አባላት በገለልተኝነት የታዛቢነት ሚና እንዲወጡ መለየታቸውንም አቶ ኪሮስ ገልፀዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቦርዱ ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ/ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።
በምርጫው የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ከወዲሁ የምርጫ ካርድ ወስደናል- የሐረር ከተማ ነዋሪዎች
Mar 18, 2026 176
ሐረር፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)∶−በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ካርድ ከወዲሁ መውሰዳቸውን የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያካሄድ ይታወቃል። በከተማዋ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርዳችንን ወስደናል ሲሉ ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡት የከተማው ነዋሪዎች መካከል የምርጫ ካርድ ስወስድ የመጀመርያዬ ነው ያለችው ወጣት አለምፀሃይ አበራ አንዷ ናት፤ የዜግነት መብቴን በመጠቀም የምርጫ ካርድ በመውሰዴ ደስተኛ ነኝ ብላለች። በጠቅላላ ምርጫውም ለሰላም፣ ለልማትና ለዕድገት የሚሰራ ፓርቲ እንደምትመርጥ የተናገረችው ወጣት አለምጸሃይ ወጣቶችም በምጫው የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉና ከወዲሁም የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ የበኩሏን እየተወጣች ነው። አቶ ደምመላሽ ለማ እንዳሉት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በጉጉት ስጠብቀው ነበር በዚህም “በምርጫዬ” አማካይነት የምርጫ ካርድ ተመዝግቤ ወስጃለሁ። ምርጫ የዲሞክራሲ መብት መገለጫ ነው፤ ለአገርና ለህዝብ ይጠቅማል ይበጃል የምንለውን የምንመርጥበት ነው ብለዋል። ይህንን መብት ሁሉም የምርጫ ካርድ በመውሰድ መጠቀም እንደሚገባና ዕድሜው ለመራጭነት የደረሰ ሁሉ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በንቃት መሳተፍ እንዳለበት አስተያየት ሰጥተዋል። ምርጫ ለሰላም፣ ለልማትና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ በመሆኑ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን የተናገሩት ደግሞ አቶ ኬይሩ ከሊል ናቸው። በዚህም ኢትዮጵያን በልማት ሊያሳድግና ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ የሚያደርስ ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት አቶ ኬይሩ እድሜው ለምርጫ የደረሰ ዜጋ ከወዲሁ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ መክረዋል። አቶ አደም ሙመድ በበኩላቸው ለአገርና ለህዝብ ይጠቅማል፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ያሻግራል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ካርድ በመውሰዳቸውን መደሰታቸውን ተናግረዋል። ምርጫ ለሰላምና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ዕድሜው ለመራጭነት የደረሰ ሁሉ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በንቃት መሳተፍ አለበት ሲሉም አመልክተዋል።

ማህበራዊ
በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል
Mar 18, 2026 112
አርባ ምንጭ ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ቀጥሏል፡፡ በዛሬው ዕለትም የተለያዩ ተቋማት 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚገመት የምግብ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። የተለያዩ ተቋማት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ኦርቢስ ኢንተርናሽናል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች አደረጃጀቶች እንዲሁም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለተጎጂዎች ያመጡትን ድጋፍ ዛሬ ለጋሞ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል። ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ሙላቱ ገብሬ፤ ከተቋሙና ከሠራተኞች በተሰበሰበ ገንዘብ የንፁህ ውሃና የንፅህና መጠበቂያዎችን ማስረከባቸውን ገልጸዋል። በደቡብ ክልል ወጣቶች አደረጃጀት የወላይታ ዞን፣ የሶዶ ከተማና የአሪ ዞን መዋቅር አባላትና በጎ ፈቃደኞችም አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዋዳ እንደገለፁት፤ አደጋው ከተከሰተበት እለት ጀምሮ የተለያዩ አደረጃጀት አባላት በነፍስ አድንና ሌሎች ተግባራት ሲሳተፉ ቆይተዋል። የዛሬ የተደረገው የምግብና የዓይነት ድጋፍ በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች ባሉ የወጣት አደረጃጀቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለተጎጂዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚውል ግምታቸው 1 ሚሊዮን ብር የሆነ የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። የፋብሪካው ኮርፖሬት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ማናጀር አቶ አብርሀም ዘሪሁን፤ በወገኖች ላይ በደረሰ አደጋ የፋብሪካው ሠራተኞችና አመራሮች በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ለተጎጂዎች አፋጣኝ ድጋፍ የሚሆንና ግምታቸው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ብርድልብሶችን ዛሬ ማበርከታቸውን ገልፀው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ፤ የተጎዱ ወገኖች ከደረሰባቸው ችግር ፈጥነው እንዲያገገሙ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ምላሽ እየሰጡ ያሉ አካላትን አመስግነዋል። በቀጣይ ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረው ጥረት ሁሉም ከጎናቸው በመሆን እንዲረባረብም ጥሪ አቅርበዋል።
ለዒድ አልፈጥር በዓል ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
Mar 18, 2026 135
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9 /2018 (ኢዜአ)፦ ለ1447ኛውን የዒድ አልፈጥር ረመዳን በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት፡- ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች (ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች በተመሣሣይ ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮክ መብራት ላይ፤ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)፤ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ለውስጥ ወደ ጋዜቦ አደባባይ ለሚመጡ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)፤ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ ሳንጆሴፍ መብራት ለሚመጡ ለከባድ ተሽከርካሪዎች (አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ) ሲሆን ለሌሎች ተሽከርካሪዎች (ጥላሁን አደባባይ ላይ)፤ ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች (ቡልጋሪያ መብራት ላይ)፤ ከልደታ ፀበል ውስጥ ለውስጥ ወደ አሹ ስጋ ቤት የሚያስወጣው (ልደታ ፀበል ላይ)፤ ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ)፤ ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት (ፈረሰኛ ፖሊስ ካምፕ መብራት ላይ)፤ ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ (ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ)፤ ከበርበሬ በረንዳ ወደ ድሮ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ቃና ዘገሊላ ዳቦ ቤት መስቀለኛ ላይ)፤ ከመርካቶ አካባቢ በተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ (ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ላይ)፤ ከቴዎድሮስ አደባባይ በቸርችል ወደ አገር አስተዳድር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ)፤ ከ4 ኪሎ አደባባይ ወደ ውጭ ጉዳይ ለሚሄዱ (4 ኪሎ አደባባይ ላይ)፤ ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች (ሴቶች አደባባይ ላይ)፤ በበዓሉ እለት ማለትም ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ እንደሚሆኑ አመልክቷል። ከበዓሉ ዋዜማ ምሽቱ ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ
Mar 18, 2026 75
ጎንደር፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ለ200 ወገኖች ማዕድ አጋርቷል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ተከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፤ የመደጋገፍና የመተጋገዝ እሴቶች እየዳበሩ በመምጣታቸው ብዙዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አስተዳደሩ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራቱን ገልጸዋል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሼህ መሐመድ ኢብራሂም፤ ከተማ አስተዳደሩ በአሉን ምክንያት በማድረግ የእምነቱ ተከታዮች ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የረመዳን ወር ከሁሉም በላይ የእምነቱ ተከታዮች በጾምና በጸሎት መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑበት ቅዱስ ወር መሆኑን ጠቁመው በአሉ የህዝብ ሙስሊሙ የአብሮነትና የአንድነት የጋራ ማሳያ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ማዕድ ከተጋሩት መካከል ወይዘሮ ረህመት መሃመድ እና አቶ ሰይድ ጀማል፤ ከተማ አስተዳደሩ የኢድ በዓልን አስመልክቶ ላደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል።
በሆሳዕና ከተማ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ
Mar 18, 2026 81
ሆሳዕና፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳዕና ከተማ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ አቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ። አቅመ ደካማ ወገኖች በበኩላቸው ድጋፉ በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል። በሆሳዕና ከተማ የአል ፈትህ መስጊድ የዘካተል ፊጥር አስተባባሪ ኡስታዝ ሙበሽር ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ ወገኖች የምግብ ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉ በተለይ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢድ አልፈጥር በዓልን ያለምንም ሀሳብ ሳይቸገሩ ተደስተው እንዲያሳልፉ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡ ከታላቁ የረመዳን ጾም ጅማሮ አንስቶ ከእምነቱ ተከታዮች ዘካ ሲሰበሰብ እንደነበር አስታውሰው የዛሬው ድጋፍም የዚሁ አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተለይ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉትን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ በዘካ ሲሰበሰብ መቆየቱን ጠቅሰው፣ ዛሬም ለበዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል። ይህም ኢድ አልፈጥር በዓልን ሁሉም ተደስቶ በአብሮነት እንዲያከብር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው የገለጹት። ድጋፍ ከተደረገላቸው ወገኖች መካከል በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ወርቂቴ ያሲን እንደገለጹት፤ በአቅም ውስንነት ምክንያት ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ማሟላት አቅቷቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅንጬ፣ ዘይትና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን ማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ የተደረገላቸው ድጋፍ በዓሉን በደስታና በአብሮነት ለማሳለፍ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች ጋር ለምታደርገው ድርድር ውጤታማነት የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች
Mar 18, 2026 181
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች ጋር የምታደርገውን ድርድር ለማጠናቀቅ በምታደርገው ጥረት የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጥሪ አቀረቡ። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ እና ከቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ (China Exim Bank) የልዑካን ቡድን ጋር በጋራ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላይ ሊኖሩ በሚችሉ የገንዘብ ድጋፍ አማራጮች ዙሪያ ነው። በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ የቡድን 20 (G20) የጋራ ማዕቀፍ የዕዳ ሽግሽግ (debt restructuring) ሂደት አስመልክቶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ምክክር ተደርጓል። ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ ቻይና የአበዳሪዎች ኮሚቴ (OCC) ሰብሳቢ በመሆን ላሳየችው አመራርና በዕዳ ሽግሽግ ሂደቱ ወቅት ላደረገችው ገንቢ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ሂደቱ አሁን ላይ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የተጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል። አያይዘውም፣ ኢትዮጵያ ከንግድ አበዳሪዎች(commercial creditors) ጋር የምታደርገውን ድርድር በማጠናቀቅ በኩል የቻይና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመላክቷል።
ጣልያን በማቴይ እቅድ የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ መሰረተ ልማቶች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች
Mar 18, 2026 185
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9 /2018 (ኢዜአ)፦ ጣልያን የኮይሻ ኃይል ማመንጫን ጨምሮ በማቴይ እቅድ (Mattei Plan) የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ መሰረተ ልማቶች ለመደገፍ ጽኑ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት እንዳላት አስታወቀች። በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በስትራቴጂካዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከጣልያኑ የማቴይ ዕቅድ (Mattei Plan) ግብረ ኃይል ጋር በሮም ውይይት አድርጓል። ውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን በኢትዮጵያ የልማት አጀንዳ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ ባላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርጓል። ፕሮጀክቶቹ የኮይሻ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ የግንባታ ፕሮጀክት እና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ልማት ናቸው። እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የኢነርጂ አቅም እና የአቪዬሽን መሠረተ ልማት በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጡና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚደግፉ ታምኖበታል። በውይይቱ ላይ የጣልያን ወገን በማቴይ እቅድ ጥላ ሥር ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ገልጿል። ይህም ፈጠራ የታከለባቸው የፋይናንስ ዘዴዎችን በመጠቀም እና በመንግሥትና በግል ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ተግባራዊ እንደሚሆን ተመልክቷል። በውይይቱ የተሳተፈው የጣልያን ግብረ ኃይል ከጣልያን የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር፣ የጣልያን የኤክስፖርት ክሬዲት ኤጀንሲ (SACE)፣ የጣልያን መንግስት የፋይናንስ ተቋም (CDP) እና የጣልያኑ የግንባታ ኩባንያ ዊ ቢውልድ ግሩፕ (Webuild Group) የተወጣጡ ከፍተኛ ተወካዮችን ያካተተ ነው። በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች ለኮይሻ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ዝግጅት፣ ተጨማሪ ሀብትን ማሰባሰብ እና የፋይናንስ መዋቅሩን ማሳለጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል። በተጨማሪም ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የተቀናጀ የፋይናንስ አማራጮችን (blended finance) በመጠቀም የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ሃሳብ ተለዋውጠዋል። የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ፕሮጀክቶቹ በአገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የረዥም ጊዜ የልማት ግቦችን ለመደገፍ ያላቸውን አስፈላጊነት አስገንዝበዋል። ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጣልያን ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለው ቀጣይነት ያለው አጋርነት እና ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ሁለቱም ወገኖች የፕሮጀክቶቹን ግንባታ ለማፋጠን እና የተገቡ ቃሎችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በቴክኒክ ረገድ በቅርበት አብሮ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ባንኮችንና በኢንዱስትሪ ዞኖች የሚያለሙ ባለሃብቶችን ትብብር የሚያጎለብት መመሪያ ተግባራዊ ተደርጓል
Mar 18, 2026 94
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የግልና የመንግስት ባንኮችንና የኢንዱስትሪ ዞን አልሚ ባለሃብቶችን የወጪ ንግድና ተኪ ምርት አቅም የሚያሳድግ የትብብር መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ። የፋይናንስ ተቋማት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ማጠናከር የሚያስችል የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመድረኩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ፓርክ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹም ከተማ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያሳልጥ የኢንዱስትሪ ዞኖች ተገንብተዋል። በአሁኑ ወቅትም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን፣ ሁለት መካከለኛ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንና አንድ የአይ.ሲ.ቲ ፓርክን እያስተዳደረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ቀደም ባሉት ዓመታት በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዞኖች የተሰማሩ ባለሃብቶች አብዛኞቹ ከውጭ የመጡ እንደነበር አስታውሰዋል። የሀገር ውስጥ አልሚ ባለሃብቶችን ለማበረታታት በተከናወኑ ተግባራት አሁን ላይ በኢንዱስትሪ ዞኖች ከተሰማሩ 250 ባለሃብቶች ውስጥ 65 በመቶ የሚሆኑት የሀገር ውስጥ አልሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀገር ውስጥ አልሚ ባለሃብቶች የኢንዱስትሪ ዞኖች የተሟላላቸውን መሰረተ ልማቶች በመጠቀም ማልማት የሚችሉበትን አቅም እያሳደጉ መሆኑንም አስረድተዋል። የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ምርታማነት ለማስቀጠል መሰረተ ልማት፣ የፋይናንስ አቅርቦትና ተወዳዳሪነትን የሚያስቀጥልና ጊዜ ቆጣቢ የፋይናንስ ሥርዓት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም በልዩ የኢኮኖሚ ዞን አዋጁ በኢንዱስትሪ ዞኖች የሚያለሙ ባለሃብቶችና ሁሉም ባንኮች መስፈርቱን አሟልተው በትብብር መሥራት የሚያስችል ዕድል መፍጠር እንደተቻለ አንስተዋል። የውጭ ባለሃብቶች የራሳቸውን ካፒታል ይዘው እንደሚመጡ ገልጸው፤ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ግን በባንኮች ሊደገፉ ይገባል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ ቀደም በኢንዱስትሪ ዞኖች አገልግሎት መስጠት የሚችለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንደነበር አስታወሰው፤ መመሪያው አቅም የላቸው ባንኮች መስፈርቱን አሟልተው መግባት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል፡፡ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጁና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ የግልና የመንግሥት ባንኮችንና በኢንዱስትሪ ዞኖች የሚያለሙ ባለሃብቶችን ትብብር እንደሚያጎለብት ተናግረዋል። በኢንዱስትሪ ዞኖች እያለሙ ያሉ ባለሃብቶችና ባንኮች የምርታማነትንና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያስቀጥል ጠንካራ ትብብር መገንባት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል። የኢንዱስትሪ ዞኖች በተኪና ወጪ ንግድ ምርት፣ በሥራ ዕድልና ቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የትብብር አቅምን ማሳደግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ የኃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማሟላት በትኩረት እየሰራች ነው-ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)
Mar 18, 2026 119
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የኃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማሟላት በትኩረት እየሰራች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ኃብት በመጠቀም በካይ ያልሆኑ የኃይል ምንጮችን ለማልማት የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ነድፋ እየሰራች የምትገኝ ሲሆን የውሃ ኃይል፣ የንፋስና ፀሐይ ኃይል እንዲሁም የጂኦተርማል ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከምትጠቀመው አጠቃላይ የኃይል ምንጭ ውስጥ ከ96 በመቶ በላይ የሚሆነው በካይ ካልሆኑና ታዳሽ ከሆኑ ምንጮች የሚገኝ ነው። ይህም ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ኢነርጂ ልማት ረገድ ቀዳሚ ተጠቃሽ ሀገር እንድትሆን ያደርጋታል ብለዋል። የውሃ ኃይል (Hydro) ትልቁን የኃይል ድርሻ የሚይዝ መሆኑን ጠቅሰው፥ የፀሐይና የንፋስ ኃይል ቴክኖሎጂዎችም በስፋት ወደ ስራ እየገቡ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ይህ ስኬት መንግስት ሀብቱን ወደዚህ ዘርፍ ለማዞር ባሳለፈው ፖሊሲ ተኮር ውሳኔ የተገኘ መሆኑን ጠቁመው፥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዚህ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ ትልቁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ መንግስት የዜጎችን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት በአረንጓዴ ኢነርጂ ልማት ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ከሁሉም የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የሚገኘው አጠቃላይ የኃይል መጠን ከ10 ጊጋ ዋት በላይ መድረሱ ከፍተኛ ሀገራዊ አቅም መፈጠሩን ያሳያል ብለዋል። የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስና የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥ ከነዳጅ ነፃ የሆኑ አማራጮችን ማስፋፋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አሳስበው በየደረጃው የታቀዱ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ የተጀመረው ስራ ይጠናከራል
Mar 18, 2026 169
ባሕር ዳር፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ዘመኑን በሚመጥን መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ተደራሽ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። ''ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ትውውቅ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄዷል። ፍኖተ ካርታው በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተመልክቷል። ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የሕዝብ የመገልገል ፍላጎት መሠረት ያደረገ ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር ነው። ፍኖታ ካርታው በክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘና ሥርዓትን በመገንባት ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥን ለማረጋገጥ ያግዛል። በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኛውን የማስፈጸም አቅም ማሳደግ፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት እንዲሁም ነፃ፣ ገለልተኛና ዲጂታል የሥራ አካባቢን መፍጠር ዋና ዋና የሪፎርሙ አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። ተቋማትም ፍኖተ ካርታውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የአገልግሎት ጥራትን፣ ፍጥነትን፣ ፍትሐዊነትንና እርካታን በሚያረጋግጥ መልኩ ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። ለዚህም ሲቪል ሰርቫንቱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ፣ በላቀ ብቃት፣ ዕውቀትና ክህሎት ታግዞ ሪፎርሙን ሊተገብር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለማሻገር የሚያስችል የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል። ፖሊሲው ሀገራዊ ዕውቀትንና ልምድን መሠረት ያደረገ በመሆኑ በፍጥነት ለውጥ ለማስመዝገብ እንደሚያስችል ጠቁመዋል። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በ36 ማዕከላት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ ይህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ ቀደም ሲል በተቋማት ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተግባራዊ በተደረገባቸው ከተሞች የሕዝብ እርካታን 97 በመቶ ማድረስ መቻሉን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ይህንን ውጤት ለማስፋት የሪፎርም ፍኖተ ካርታውን በላቀ ትብብር መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል። በመድረኩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ትግበራ ከሚገቡ የተለያዩ የክልል ተቋማት ጋር የሰነድ ርክክብ ተከናውኗል።
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ አፍሪካን በልኳ ለዓለም የሚያስረዳ ትርክት መገንባት ያስችላል
Mar 17, 2026 171
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ አፍሪካን በልኳ ለዓለም የሚያስረዳ ትርክት መገንባት የሚያስችል መሆኑን የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያስመዘገበቻቸው ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ ዓለም የመሰከረላቸው ድሎችን ለማስተዋወቅ ያግዛልም ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በመጭው ሚያዚያ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ በመንግሥታቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና የሌሎች አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የነደፈች፣ አህጉራዊ የመተላለፊያ በር በመሆኗ አዲስ አበባ ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ተመራጭ ያደርጋታል። በዚህም በቀጣይ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በሚካሄደው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በንቃት መሳተፍ በሚችሉባቸው ዕድሎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካን ገንቢ ትርክት ለመገንባት በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እጅ ነው። አፍሪካ የትርክት ተጎጂ መሆኗን ገልጸው፤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የአፍሪካ ትርክትን ለመቀየር የተቋቋመ አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑን ተናግረዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ መነሻው ኢትዮጵያ መዳረሻው አፍሪካ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ገልጸዋል። አፍሪካ የራሷን በጎ ትርክት ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በማስተባበር መሪ ተዋናይ ሆኖ ይሰራል ብለዋል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎች የጎላ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያውያን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን መልካም ገጽታ እንዲገነቡና ትብብር እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያስመዘገበቻቸው ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ ዓለም የመሰከረላቸው ድሎችን ለማስተዋወቅ ገንቢ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተሾመ ተክሉ፤ ኢትዮጵያ የቅርስ፣ የታሪክና የባህል ባለቤት መሆኗን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅና ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም ሀብት አውጥቶ ማሳየት ሳይቻል መቆየቱን ያወሱት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። የማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ከተቻለ ሀገራዊ የቱሪዝም ሀብትን ለዓለም ማሳየት የሚያስችል መድረክ ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን የቱሪዝም ሀብት ሲያስተዋውቁ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስቴር ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በሩ ክፍት ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማየት ለሚፈልጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል። የኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገመዳ ኦላና፤ ጉባኤው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን ገፅታ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የእርስ በእርስ ትብብራቸውን በማጠናከር አህጉራዊ አንድነትን መፍጠር ያስችላል ብለዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በበኩላቸው፤ ሁነቱ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት ብሎም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለመገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ መዘጋጀቱ የሀገራችንን ገጽታ ለመገንባት የቱሪዝም ሃብታችንን ለማስተዋወቅ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የጉባዔው አዘጋጆች ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ለሁነቱ መሳካት በትብብር ለመስራትና የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአፍሪካን ትርክት በጋራ ለመቅረፅ ገንቢ ሚና አላቸው
Mar 17, 2026 220
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአፍሪካን ትርክትና ህልም በጋራ ለመቅረፅ ገንቢ ሚና እንዳላቸው የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ ገለጹ። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ በመጭው ሚያዚያ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስብሰባ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አፍሪካ የራሷን ትርክት መገንባት የሚያስችሉ፣ የደንበኞችን እምነት የሚያሳድጉ፣ ብራንድ ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸው ስብሰባውን አስፈላጊ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ በመንግሥታቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና የሌሎች አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የነደፈች፣ አህጉራዊ የመተላለፊያ በር በመሆኗ አዲስ አበባ ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ተመራጭ ያደርጋታል። በዚህም በቀጣይ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በሚካሄደው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በንቃት መሳተፍ በሚችሉባቸው ዕድሎች ዙሪያ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር ውይይት ተደርጓል። የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካን ገንቢ ትርክት ለመገንባት በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እጅ ነው። አፍሪካ የትርክት ተጎጂ መሆኗን ገልጸው፤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የአፍሪካ ትርክት ለመቀየር የተቋቋመ አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑን ተናግረዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ መነሻው ኢትዮጵያ መዳረሻው አፍሪካ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ገልጸዋል። ማህበራዊ ሚዲያዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎቹ የጎላ መሆኑን አመልክተው፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያውያን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን መልካም ገጽታ እንዲገነቡና ትብብር እንዲፈጥሩ ተናግረዋል። በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተሾመ ተክሉ፤ ኢትዮጵያ የቅርስ፣ የታሪክና የባህል ባለቤት መሆኗን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅና ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም ሀብት አውጥቶ ማሳየት ሳይቻል መቆየቱን ያወሱት መሪ ስራ አስፈፃሚው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። የማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ከተቻለ ሀገራዊ የቱሪዝም ሀብትን ለዓለም ማሳየት የሚቻልበት መድረክ ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን የቱሪዝም ሀብት ሲያስተዋውቁ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በሩ ክፍት ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማየት ለሚፈልጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል። ኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገመዳ ኦላና በበኩላቸው፤ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን ገፅታ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የእርስ በእርስ ትብብራቸውን በማጠናከር አህጉራዊ አንድነትን መፍጠር ያስችላል ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ከፍተኛ የተደማጭነት ሚና በማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የድንች ምርታማነትን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
Mar 17, 2026 212
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የድንች ምርታማነትን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከአየርላንድ የድንች ምርምር እና ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ብሔራዊ የድንች ምርምር ልማት አውደ ጥናት አካሒዷል። ድንች በኢትዮጵያ በአነስተኛ መሬትና በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ በመሆኑ ለምግብ ዋስትና እና ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የድንች አምራች ለመሆን የሚያስችል እምቅ አቅም ያላት ሲሆን፣ በተለይም የተሻሻሉ ዝርያዎች መጨመር ምርታማነቱን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረው ይገኛል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በተወካያቸው ፕሮፌሰር አሊ መሐመድ አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ግብርና ለምግብ ሉዓላዊነት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ተኪ የሌለው ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረትም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል። ድንች ከአገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ አማራጭ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው ለምርቱ እሴት በመጨመር ረገድ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ በበኩላቸው፤ ምርታማነትን ማሳደግ የኢንስቲትዩቱ ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ምርምሮች የተሻሻሉ የድንች ዝርያዎችን ቁጥር ወደ 45 ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አማካይ የድንች ምርታማነት በሄክታር 230 ኩንታል መድረሱን ተናግረው ምርቱ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ የሚቆይበትን ቴክኖሎጂ ማስፋፋትና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን እሴት የመጨመር ሥራ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ ምክትል የተልዕኮ ኃላፊ ፈርጋን ሪያን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በድንች ምርታማነት ላይ እያሳየችው ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ አገራቸው በግብርናው ዘርፍ ያላትን አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ስፖርት
ባርሴሎና ለሩብ ፍጻሜ አልፏል
Mar 18, 2026 105
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ኒውካስል ዩናይትድን 7 ለ 2 ረምርሟል። ማምሻውን በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊኒያ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። ማርክ በርናል እና ፌርሚን ሎፔዝ በጨዋታ ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ቀሪዎቹን ጎሎች ለባርሴሎና ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አንቶኒ ኢላንጋ ለኒውካስል ግቦቹን አስቆጥሯል። በመጀመሪያ አጋማሽ ተመጣጣኝ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ ባርሴሎና በሁለተኛው አጋማሽ ፍጹም የበላይነት ወስዷል። ባርሴሎና በሁለተኛው 45 አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል። የስፔኑ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል። የአምስት ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቡድኑ ስምንት ውስጥ ሲገባ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው። በሩብ ፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አሸናፊ ጋር ይገናኛል። ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል። በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ፣ ባየር ሙኒክ ከአትላንታ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ የሚገቡ ቀሪ አራት ክለቦች የሚለዩባቸው ጨዋታዎች ይደረጋሉ
Mar 18, 2026 121
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መርሐ- ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ባርሴሎና ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በካምፕ ኑ ስታዲየም ይጫወታሉ። ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንት በፊት በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ጨዋታ የሚያሸንፈው ቡድን ሩብ ፍጻሜውን ይቀላቀላል። ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ ምሽት አምስት ላይ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቡድኖች ከሳምንት በፊት በራምስ ፓርክ ስታዲየም ተገናኝተው ጋላታሳራይ 1 ለ 0 አሸንፏል። ሊቨርፑል ወደ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት ከአንድ ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ጋላታሳራይ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት ስምንት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል። ባየርሙኒክ አተላንታን ምሽት አምስት ላይ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ያስተናግዳል። የጀርመኑ ቡድን በመጀመሪያው ጨዋታ 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነው። አተላንታ በሂሳባዊ ስሌት ሩብ ፍጻሜ የመቀላቀል እድሉ እጅጉን የጠበበ ነው። ምሽት አምስት ላይ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አትሌቲኮ ማድሪድ በመጀመሪያው ጨዋታ 5 ለ 2 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። የስፔኑ ክለብ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት ቅርብ ነው። በአንጻሩ በውጤት ማጣት ቀውስ የሚገኘው ቶተንሃም ውጤቱን የመቀልበስ ከፍተኛ ዳገት ይጠብቀዋል። ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ሪያል ማድሪድ፣ ፒኤስጂ፣ አርሰናል እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ተጋጣሚዎቻቸውን በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብተዋል።
ሴኔጋል ያሸነፈችው የአፍሪካ ዋንጫ ተነጥቆ ለሞሮኮ ተሰጠ
Mar 18, 2026 196
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ውጤት ተሽሮ ዋንጫው ለሞሮኮ እንዲሰጥ መወሰኑን አስታወቀ። ውሳኔው ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል። አህጉራዊው የእግር ኳስ የበላይ አካል ከውሳኔው ላይ የደረሰው የፍጻሜውን ጨዋታ ውጤት ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ መሆኑን የካፍ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አስታውቋል። ሞሮኮ ባስተናገደችው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በፍጻሜው ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፋ ሴኔጋል ዋንጫውን ማንሳቷ የሚታወስ ነው። በፍጻሜው ጨዋታ ለሞሮኮ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት በመቃወም የሴኔጋል ተጫዋቾች ለ15 ደቂቃ ያህል ሜዳ ጥለው መውጣታቸው የውድድሩን ህግ አንቀጽ 84 (Article 84) የሚጥስ ሆኖ መገኘቱን ካፍ ገልጿል። የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FRMF) ያቀረበውን ይግባኝ ለመመርመር የተሰበሰበው የካፍ የይግባኝ ሰሚ ቦርድ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ቀደም ብሎ ያስተላለፈውን ውሳኔ በመሻር ዋንጫውን ከሴኔጋል ተነጥቆ ለሞሮኮ እንዲሰጥ ወስኗል። በዚሁ መሰረት ቦርዱ የ1 ለ 0 ውጤቱን በመሻር ሞሮኮ የ3 ለ 0 የፎርፌ ውጤት እንድታገኝ መደረጉን አመልክቷል። ይህ ውሳኔ ሞሮኮ ከ50 ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫን ለሁለተኛ ጊዜ እንድታነሳ አስችሏታል። ሴኔጋል ለሁለተኛ ጊዜ ያነሳችው የአፍሪካ ዋንጫ ተነጥቃለች። ካፍ ያስተላለፈው ውሳኔ አስገራሚ፣ ታሪካዊ፣ ያልተጠበቀ እና አወዛጋቢ በሚል በእግር ኳስ አፍቃሪን ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ ካፍ ያሳለፈውን ውሳኔ ኢ-ፍትሐዊ እና ተቀባይነት የሌለው ሲል ገልጾታል። ውሳኔው የአፍሪካን እግር ኳስ ገጽታ ያበላሸ ነውም ብሏል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔው እንዲታይ ወደ ዓለም አቀፍ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) እንደሚወስድ አመልክቷል።
ሪያል ማድሪድ ፒኤስጂ እና አርሰናል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ
Mar 17, 2026 194
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል። ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል። ቪኒሺስ ጁኒየር በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ለማድሪድ ግቦቹን አስቆጥሯል። አርሊንግ ሃላንድ ለሲቲ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። የማንችስተር ሲቲ አምበል በርናንዶ ሲልቫ በ20ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። የ15 ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሪያል ማድሪድ በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። በሌላኛው መርሐ ግብር ፒኤስጂ ቼልሲን 3 ለ 0 አሸንፏል። በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክቪቻ ክቫራስኬሊያ፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ሴኒ ማዩሉ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በድምር ውጤት 8 ለ 2 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሰናል ባየር ሌቨርኩሰንን 2 ለ 0 አሸንፏል። ኤበሬቺ ኤዘ እና ዴክላን ራይስ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምር ውጤት 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል። ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ስፖርቲንግ ሊዝበን ቦዶ ግሊምትን 5 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 5 ለ 3 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
አካባቢ ጥበቃ
ለሀገራዊ የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ትግበራ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት መጠናከር አለበት
Mar 18, 2026 92
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ስኬታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ባለስልጣኑ የፍኖተ ካርታውን ትግበራ ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ባለስልጣኑ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም ፅዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለውጥ የሚያመጡ የህግና አሰራር ስርዓት ወደ ተግባር በማስገባት ለሌሎች ሀገሮች ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ግቦችን ለማሳካትና ወደ ሰርኩላር ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ማፋጠን የሚያስችለው ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ በ2017 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን አስታውሰዋል። ፍኖተ ካርታው ፅዱ ኢትዮጵያን በመፍጠር ሂደት ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል(Recycling) ባህልን የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በማጎልበት፣ ለተሻለ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠርና አዳዲስ የስራ እድሎችን በመክፈት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል። የአካባቢ ጥበቃ ስራ በአንድ ተቋም ብቻ ውጤታማ ማድረግ ስለማይቻል የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል። በዚህም ወደ ሰርኩላር ኢኮኖሚ የሚደረገው ሽግግር እንዲፋጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በተጠናከረ ተሳትፎ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከተቋማቱ ጋር የተደረገው ስምምነት በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማከናወን፣ የህግና አሰራር ማሻሻያዎች፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን በቴክኖሎጂና በዕውቀት መደገፍ እንዲሁም የጋራ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በቅንጅት መስራት ከሚከናወኑ ሥራዎች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ ስምምነቱን ከተፈራረሙ ተቋማት መካከል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን እንደገለጹት በባለስልጣኑ የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ግንባታዎች በመልሶ መጠቀም የተዘጋጁ የሀገር ውስጥ ግብዓቶችን እንዲጠቀሙ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሃሰን መሃመድ በበኩላቸው የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ፖሊሲ ጋር የሚቀናጅ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አለበል ደሴ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የፖሊሲ ፋይዳ ያላቸው ሀገራዊ ጥናቶችን በመለየት ፖሊሲ አውጪውን የማማከር ስራ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ ለፍኖተ ካርታው ትግበራ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሳባ ዘሪሁን በበኩላቸው በዚህ ስራ ባለድርሻ እንደመሆናችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአዲስ አበባ ኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትምህርት የሚሰጥ ነው
Mar 18, 2026 90
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የዛምቢያና ኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች ገለጹ። በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ መዲናዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ለነዋሪዎችና ጎብኝዎች ምቹ የእንቅስቃሴ ምኅደር ፈጥረዋል። በመዲናዋ በአጭር ጊዜ የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን በማስገኘት ልምድና ተሞክሮ እየተቀሰመባቸው ይገኛል። በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማትም ከተማዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ነዋሪዎችን ምቹና የአረንጓዴ ከባቢ በማጎናጸፍ በ75 የኢትዮጵያ ከተሞች እየተተገበረ ይገኛል። የዛምቢያና የኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካዊያን ማዕከልነቷን በተግባር ያረጋገጡ የልማት ውጤቶች ተገኝተዋል። በመዲናዋ በአጭር ጊዜ የተገነቡ አስደናቂ የልማት ውጤቶችም ከተማዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ምቹ የከተሜነት ምኅዳር እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል። በዛምቢያ የአካባቢና የገጠር ልማት ሚኒስቴር የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ባለሙያ ብሬን ሲያካበያ፤ አዲስ አበባ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተጎሳቆለና እርጅና የተጫጫነው ገፅታ እንደነበራት አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የተገነባው የኮሪደር ልማት ነዋሪዎች ምቹና ፅዱ የአረንጓዴ ከባቢን ያጎናጸፈ አስደናቂ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል። የመዲናዋ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውም ውብ የከተሜነት ገፅታን በመፍጠር ልዩ ድምቀት እንደፈጠሩ ተናግረዋል። በህዝብና በአመራር ቁርጠኝነት ተገንብተው የተጠናቀቁት የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶችም ሀገራቸውን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትልቅ ትምህርት መሆኑን አንስተዋል። የኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ባለሙያ መሎሰም ቡሊ በበኩላቸው፣ ከተሜነት የአንድ ሀገር የዕድገትና ስልጣኔ መገለጫ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ የተገኙ ተምሳሌታዊ የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ዜጎች ዘመናዊ የከተሜነት አኗኗር ሥርዓት እንዲጎናጸፉ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የመዲናዋ አስደናቂ የከተማ ውበት፣የአረንጓዴና ቆሻሻ አያያዝ የልማት ስኬቶች የአፍሪካን የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት የመቀነስ ግብ ያገናዘቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ አህጉራዊ አጀንዳዎችን የሚያሳካና ትምህርት የሚቀሰምበት መሆኑን አንስተዋል።
በአሪ ዞን ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የጎርፍ እና የናዳ ቅድመ መከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው
Mar 18, 2026 93
ጂንካ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ለጎርፍ እና ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ማኅበረሰቡን በማሳተፍ አደጋን ቅድመ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስራት አበበ እንደገለጹት፤ በአሪ ዞን የሚገኙ አራት ወረዳዎች በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው ተራራማና ተዳፋት በመሆናቸው በተደጋጋሚ ለናዳ አደጋ ተጋላጭ ናቸው። በተመሳሳይ በዞኑ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ደግሞ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ባለፈው ዓመት ወቅት በዎባ አሪ ወረዳ በተከሰተ የአፈር መንሸራተት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወሱት ኃላፊው፤ በዘንድሮው ዓመትም በደቡብ አሪ ወረዳ ወሰት ቀበሌ መሰል አደጋ መከሰቱን ተናግረዋል። ዘንድሮ የተከሰቱት አደጋዎች ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸሩ በእጅጉ የቀነሱት ማኅበረሰቡን በማሳተፍ በተከናወኑ የመከላከል ሥራዎች መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅትም የበልግ ዝናብን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ለጊዜው ከአካባቢው የማውጣት ሥራ እየተሰራ ነው። በከተሞች በቆሻሻ የተደፈኑ የፍሳሽ ቦዮችን የማጽዳት ተግባር፤ ያልተጠበቀ የወንዝ ሙላት ለሰውና ለእንስሳት ሕይወት መጥፋት ምክንያት እንዳይሆን ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየሰሩ ነው ብለዋል። የደቡብ አሪ ወረዳ የወሰት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኃይሉ ከማይ በሰጡት አስተያየት፤ አካባቢያቸው ለናዳ ተጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። አደጋ እንዳይደርስባቸውም ለጊዜው ከአካባቢው በመራቅ ራሳቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሌላኛው የአስተያየት ሰጪ የባካ ዳውላ አሪ ወረዳ የሴኔጋል ቀበሌ ነዋሪ አቶ ማርቆስ አዲሱ በበኩላቸው፤ በአካባቢው በተከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ ቀደም ሲል ይከሰት የነበረውን ናዳ መከላከል መቻላቸውን ገልጸዋል። ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ ስፍራዎች ችግኞችን በመትከል አፈሩ እንዳይሸረሸር ጥበቃ እያደረግን ነው ያሉት አቶ ማርቆስ፤ በዚህም አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል መቻሉን አረጋግጠዋል።
አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ ለደን ልማት በተሰጠው ትኩረት የደን ሽፋን ጨምሯል
Mar 17, 2026 225
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ ለደን ልማት የተሰጠው ትኩረት ሀገራዊ የደን ሽፋኑ እንዲያድግ ማስቻሉን የኢትዮጵያ የደን ልማት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን 14ኛው የዓለም የደን ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እንደነበር አስታውሰው፤ በዚህም የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በዕጅጉ ቀንሶ እንደነበር አስረድተዋል። ለአብነትም ከአስር ዓመት በፊት በየዓመቱ ዘጠና ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት ደን ይጨፍጨፍ ነበር ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አሁን ላይ ወደ ሃያ ሰባት ሺህ ሄክታር ዝቅ እንዲል መደረጉን ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለደን ልማት የተሰጠው ትኩረት በመስኩ ትልቅ ውጤት እንዲመጣ ማስቻሉን አብራርተዋል። ከሀገራዊ ለውጡ በፊት 17 ነጥብ 2 በመቶ የነበረው የደን ሽፋን አሁን ላይ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል። 14ኛው የዓለም የደን ቀንም በኢትዮጵያ በዘርፉ የተገኙ ስኬቶች ከማጉላት ባለፈ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ይበልጥ በማጠናከር ለላቀ ውጤታማነት የሚመከርበት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የደን ሽፋን እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ውጤቶች እየተገኘ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የውኃ አቅርቦት እንዲሻሻል፣ የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ ማስቻሉንም ገልጸዋል። ይህም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ከማገዝ ባለፈ ብዝሃ ህይወት እንዲጠበቁ አወንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። በተለይም ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመቀነስ ረገድ የኢትዮጵያ የደን ኃብት ከፍ ያለ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል በሚደረገው ጥረትም ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተችና ለዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጠቃሽ ማሳያ ነው ብለዋል። 14ኛው የዓለም የደን ቀን "ደን ለኢኮኖሚ" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 178
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 160
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 161
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ደኅንነት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 5, 2026 193
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የኢጋድ የሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ውይይቱን ያደረጉት የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) በመወከል ነው። ውይይቱ ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው። ሁለቱ ወገኖች የጋራ የተግባር ምላሽ ለመስጠት እና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 2665
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 303
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 351
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 337
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 14, 2026 1302
ከየካቲት 29 - መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ኢትዮጵያ • ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተመልክተዋል። ማዕከሉ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል • በተመሳሳይ በድሬዳዋ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማኅበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። • የድሬዳዋ የኮሪደር ልማትንም የጎበኙ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬዳዋ ዕውን እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል። • ከድሬዳዋ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር መርሐ-ግብር ያከናወኑት ባለፈው ሳምንት ነው። • በድሬዳዋ የሚገኘውን እመርታ ቤተ-መጻሕፍትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል። ቤተ-መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ ለ1 ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። • በሳምንቱ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ሥራ ተመልክተዋል። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ፤ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ ዕቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል። • የቁንድዶ ተራሮችንም ጎብኝተዋል። • በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከልም ተመልክተዋል። ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር ዐቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል። • በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ናሲኦል ዋሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። • ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር አካሂደዋል። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሹመት መስጠታቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌ/ጄኔራል አሥራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድን እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች አድርገው የሾሙት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካቸው ጋር በጅቡቲ የቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጊሌ በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝታቸውን ቀጥለውም ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚሁ ወቅትም ከፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ✍️ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጋር መምከራቸው • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል። በዚሁ ወቅትም የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት የመደመር መንግሥት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል። • ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዳይሬክተር ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) ጋር በዲጂታል ልማት ያለ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ እና ትብብራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይም የታደሙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምኅሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ኅያው የሕይወት ስንቅ ነው ብለዋል። ✍️ የመሬት ናዳና ጎርፍ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ • ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ የዜጎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል። ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። • ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ያስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። እስካሁንም በአደጋው ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስና መልሶ ለማቋቋም ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገኑ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ✍ ምክር ቤቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማወጁ • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማስመልከት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ዐውጇል። በዚህም መሠረት ትናንት የጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ዐበይት_ጉዳዮች #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 387
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር
Feb 24, 2026 494
(በአየለ ያረጋል) ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፤ ኢትዮጵያና እስራኤል። የሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረው ግንኙነት አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች የተጠናከረ ሆኖ ይገኛል። የሀገራቱ ግንኙነት ግን እንደየስርዓተ መንግስታቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባህሪ መልኩን እየለዋወጠ እና ውጣ ውረዶችን እያለፈ የተሻገረና ጠንካራ መሆኑም ይታወቃል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪካዊ ገጽታ፦ ሃገራቱ የግንኙነታቸው ትርክት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በንግሥተ ሳባ እና በንጉሥ ሰለሞን ዘመነ መንግስት እንደሆነ አፈ ታሪክ ያስረዳል። ይህ አፈ-ታሪካዊ እርሾ ከኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ጋርም ቀጥሏል። በመካከለኛው እና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ሃይማኖትና ንግድ ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አስተሳስሯል። በተለይም ዴር ሱልጣንን ጨምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት መኖር የሁለቱን ሀገራት ባህላዊ ተጋምዶሽ አጎልብቷል። ይህ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ከእስራኤል ሀገረ መንግስት ዳግም መመስረት በኋላም በዘመናዊት ኢትዮጰያ ታሪክም ቀጥሏል። የኢትዮ እስራኤል ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፦ የዘመናዊ የኢትዮ-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተወጠነው በአውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ1956 ሲሆን በ1961 ይፋዊ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል። በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግስት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ ጥቅምን ያማከለና የወቅቱን የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አድርጓል። በንጉሳዊ ስርዓተ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ሌሎች የልማት ቴክኒካል ድጋፍ የደረሰ ወዳጅነት ነበራቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በእስራኤለና አረቦች ጦርነት ሳቢያ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል። ያም ሆኖ በግልጽም ሆነ የህቡዕ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ይወሳል። መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በደርግ መንግስት መጨረሻ ዓመታት (በአውሮፓውያኑ 1989) የኢትዮ-እስራኤል ይፋዊ ግንኙነት ዳግም ተጀምሯል። የ"ኦፕሬሽን ሙሴ" (1984) እና "ኦፕሬሽን ሰለሞን" (1991) የተሰኙ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የማጓጓዝ ተልዕኮዎችም በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ስምምነት የተካሄዱ መሆናቸውን ልብ ይሏል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም) ጀምሮ ደግሞ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጥሏል። በፈረንጆቹ 1992 ኢትዮጵያ በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፍታለች። በፈረንጆቹ 2003 ኢትዮጵያና እስራኤል የኢንቨስትመቶች ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1996 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2004) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አሪኤል ሻሮን ጋር ያደረጉት ታሪካዊ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሳድጎታል። ጉብኝቱን ተከትሎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ያጠናከሩ የተለያዩ ስምምነቶች ተደርገዋል። በተለይም በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከፍ ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትና ፀረ ሽብር ጉዳዮች እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥና የድንበር ጥበቃ ቴክኖሎጂ በትብብር ለመስራት መሰረት ጥለዋል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአዲስ አበባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም መክረዋል። በተመሳሳይ በፈረንጆቹ በ2017 የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ጎብኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በየራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ቆመዋል። በዓለም አቀፍ መድረኮች አንዳቸው ለሌላው ድምጽ በመስጠት ተደጋግፈዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ለብሔረታዊ ጥቅሞቿ መጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እስራኤል አሉታዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይልቁንም እስራኤል ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ እንደ መግቢያ ሁነኛ በር አድርጋ ትቆጥራለች። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮ-አስራኤል ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴካዊ አጋርነት አድጓል። በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በእስራኤል ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ደግሞ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ እንዲታደስ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ታሪካዊ የተሰኘውን ምክክር አድረገዋል። መሪዎቹ በሰጡት ገለጻም በአምስት ነጥቦች ላይ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በውሃ፣ በመስኖ፣ በጤና እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ መፈራረማቸውን አውስተው ነበር። በግብርና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምተው እንደነበርም እንዲሁ። ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ፦ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ልማት በመለወጥ የንግድና ኢንቨስመንት ግንኙነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አከናውነዋል። የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እየጎለበተ መጥቷል። ለአብነትም የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል። በማዕድን ዘርፍ (በፖታሽ)፣ በማምረቻ ዘርፍ( በጨርቃጨርቅ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች) እንዲሁም በጤናና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ ነው። በተለይም በግሪን ሃውስ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በፋርማሲዩቲካል (የመድኃኒት) ዘርፎች ሁነኛ ተሳትፎ አድርገዋል። በተመሳሳይ በንግድ ልውውጥ ረገድ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ እስራኤል በስፋት ትልካለች። በአንጻሩ እስራኤል የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የግብርና ግብዓቶችን (ማዳበሪያና ኬሚካሎች)፣ የሕክምና መሣሪያዎችን እና የደህንነት ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረቅ አካባቢ ግብርና ስመጥር የሆነችው እስራኤል በዘርፉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት አጋር ስትሆን በዘመናዊ መስኖ፣ የአቮካዶና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት እርባታ እና የወተት ምርታማነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች በጎ ተሳትፎ ታደርጋለች። በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወዳጅነት መጠናከር ቤተ-እስራኤላውያን እንደ ድልድይ አገልግለዋል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ160 ሺህ በላይ መሰረታቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላዊያን ዜጎች አሉ። እነዚህ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ሁነኛ ድልድይ ሆነዋል። በተለይም በእስራኤል የሰለጠኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በማስቻል በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በንግድ ስራ ረገድ ውጤታማ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ፈጥጠሯል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸውን ከፍ አድርጎታል። የፕሬዝዳንት ሔርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሃገራት የጸና ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጎለብት እንደሚሆን ይጠበቃል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ የሚያጠናክሩበት ምቹ ሁኔታም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1208
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3694
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2476
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8268
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6753
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 559
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ። እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል። የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል። በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል። ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል። በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡
ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት
Feb 26, 2026 516
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያደርሰዋል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት አዘርባጃን እ.አ.አ በ1991 ነጻነቷን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። የሀገራቱ ግንኙነት ከእ.አ.አ 1990ዎች መግቢያ አንስቶ እያደገ መጥቷል። አዘርባጃን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ኤምባሲ የከፈተች ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር እንዲጠናከር በር ከፍቷል። በቱርክዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስራ የሚሸፍን ሲሆን ፖለቲካ፣ ትምህርት እና ባህል ሀገራቱ ካላቸው የትብብር መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል በባለብዙ ወገን መድረክ በገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) መድረክ በትብብር እየሰሩ መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2019 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 18ኛው የገለልተኛ ሃገራት ንቅናቄ (ናም) ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ 120 አባል ሃገራትን ያቀፈና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓለም ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። በሀገራቱ መካከል ተከታታይ የሆኑ የባህል ልውውጥ መድረኮች ተካሄደዋል። ለዚህም እ.አ.አ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአዘርባጃን የትምህርት እድል አግኝተው ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢኮኖሚ አንጻር እ.አ.አ በ2017 በአዘርባጃን የተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ፎረም ተጠቃሽ ነው። በወቅቱ ጨርቃጨርቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በወቅቱ ሀገራቱ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ምጣኔ ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ባለስልጣናት መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እያደጉ መጥተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአዘርባጃን ጉብኝት ማድረጋቸወ ይታወሳል። ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም እንዲሁ። ምክክሩ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍና በትብብር መንፈስ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም በወቅቱ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር በነበራቸው ውይይት የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ መክረዋል። በውይይቱም በመረጃ፣ በፀጥታና ደህንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም መስማማታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ2017 በወቅቱ የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኤልማር ማማድያሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቋሚነት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ማኅበራዊ ፈጠራ ተቋም ሊቀ መንበር ኦልቪ ሜዲዬቭ የብሔራዊ ቤተመንግሥት እና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል። ኦልቪ ሜዲዬቭ በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ የተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን የምትልካቸው ምርቶች ብዝኀነትን ለማሳደግና ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ሰሊጥ፣ የተቆላ ቡና፣ ተልባ፣ የፍየል እና የበግ ሥጋን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ንግድ ትብብር ላይ ያተኮረው ሶስተኛ የኢትዮ-አዘርባጃን የውይይት መድረክ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ከውይይቱ በኋላ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል። 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) በህዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን መካሄዱ ይታወቃል። በጉባኤው ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጋለች። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑክ ከአዘርባጃን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ሀገራቱ በአካባቢ ጥበቃ፣ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገራቱ መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደረጉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ትምህርት እና ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ እንደሚታይ አንስቷል። የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝትም የዚሁ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጉብኝት በመሪ ደረጃ የሚደረግ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር የቅርብ ዓመታት ውይይቶች እና ጉብኝቶች ማሳያ ናቸው።