ቀጥታ፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ

ጎንደር፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ለ200 ወገኖች ማዕድ አጋርቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ተከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፤ የመደጋገፍና የመተጋገዝ እሴቶች እየዳበሩ በመምጣታቸው ብዙዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።


 

በዚህም አስተዳደሩ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራቱን ገልጸዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሼህ መሐመድ ኢብራሂም፤ ከተማ አስተዳደሩ በአሉን ምክንያት በማድረግ የእምነቱ ተከታዮች ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራቱ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


 

የረመዳን ወር ከሁሉም በላይ የእምነቱ ተከታዮች በጾምና በጸሎት መንፈሳዊ ተግባራትን ያከናወኑበት ቅዱስ ወር መሆኑን ጠቁመው በአሉ የህዝብ ሙስሊሙ የአብሮነትና የአንድነት የጋራ ማሳያ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

ማዕድ ከተጋሩት መካከል ወይዘሮ ረህመት መሃመድ እና አቶ ሰይድ ጀማል፤ ከተማ አስተዳደሩ የኢድ በዓልን አስመልክቶ ላደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም