ቀጥታ፡

በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።

"መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል።

ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል።

በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል።

የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም