ሪያል ማድሪድ ፒኤስጂ እና አርሰናል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ - ኢዜአ አማርኛ
ሪያል ማድሪድ ፒኤስጂ እና አርሰናል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል።
ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ቪኒሺስ ጁኒየር በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ለማድሪድ ግቦቹን አስቆጥሯል።
አርሊንግ ሃላንድ ለሲቲ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የማንችስተር ሲቲ አምበል በርናንዶ ሲልቫ በ20ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
የ15 ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሪያል ማድሪድ በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ፒኤስጂ ቼልሲን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክቪቻ ክቫራስኬሊያ፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ሴኒ ማዩሉ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በድምር ውጤት 8 ለ 2 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አርሰናል ባየር ሌቨርኩሰንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ኤበሬቺ ኤዘ እና ዴክላን ራይስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምር ውጤት 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ስፖርቲንግ ሊዝበን ቦዶ ግሊምትን 5 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 5 ለ 3 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።