ቀጥታ፡

የኢድ አልፈጥር በዓልን የተቸገሩትን በመርዳት ማክበር ይገባል

አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ ህዝብ ሙስሊሙ 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን የተቸገሩትን በመርዳትና በመደጋገፍ ማክበር እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  አስገነዘበ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን በመግለጫቸው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። 

ረመዳን የአብሮነት፣ የመደጋገፍ፣ የመረዳዳት የጋራ እሴቶች የሚጠናከሩበት ወር መሆኑን አንስተዋል።

በጾሙ የተለመዱት ኢስላማዊ መልካም ስነ-ምግባራት ከረመዳን በኋላም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በዚህም ህዝበ ሙስሊሙ ኢድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና ለተቸገሩ በማካፈል መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም