ቀጥታ፡

ባርሴሎና ለሩብ ፍጻሜ አልፏል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ኒውካስል ዩናይትድን 7 ለ 2 ረምርሟል።

ማምሻውን በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊኒያ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።



ማርክ በርናል እና ፌርሚን ሎፔዝ በጨዋታ ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ቀሪዎቹን ጎሎች ለባርሴሎና ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አንቶኒ ኢላንጋ ለኒውካስል ግቦቹን አስቆጥሯል።

በመጀመሪያ አጋማሽ ተመጣጣኝ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ ባርሴሎና በሁለተኛው አጋማሽ ፍጹም የበላይነት ወስዷል።

ባርሴሎና በሁለተኛው 45 አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

የስፔኑ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል።

የአምስት ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቡድኑ ስምንት ውስጥ ሲገባ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው።

በሩብ ፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አሸናፊ ጋር ይገናኛል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል።

በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ፣ ባየር ሙኒክ ከአትላንታ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም