ቀጥታ፡

በሆሳዕና ከተማ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ    

ሆሳዕና፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦በሆሳዕና ከተማ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ አቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ።

አቅመ ደካማ ወገኖች በበኩላቸው ድጋፉ በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል። 

በሆሳዕና ከተማ የአል ፈትህ መስጊድ የዘካተል ፊጥር አስተባባሪ ኡስታዝ ሙበሽር ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ1 ሺህ ለሚበልጡ ወገኖች የምግብ ድጋፍ ተደርጓል። 


 

ድጋፉ በተለይ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የኢድ አልፈጥር በዓልን ያለምንም ሀሳብ ሳይቸገሩ ተደስተው እንዲያሳልፉ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡

ከታላቁ የረመዳን ጾም ጅማሮ አንስቶ ከእምነቱ ተከታዮች ዘካ ሲሰበሰብ እንደነበር አስታውሰው የዛሬው ድጋፍም የዚሁ አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉትን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ በዘካ ሲሰበሰብ መቆየቱን ጠቅሰው፣ ዛሬም ለበዓል መዋያ የሚሆን ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል። 

ይህም ኢድ አልፈጥር በዓልን ሁሉም ተደስቶ በአብሮነት እንዲያከብር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው የገለጹት። 

ድጋፍ ከተደረገላቸው ወገኖች መካከል በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ወርቂቴ ያሲን እንደገለጹት፤ በአቅም ውስንነት ምክንያት ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ማሟላት አቅቷቸው እንደነበር ገልጸዋል፡፡


 

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅንጬ፣ ዘይትና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን ማግኘታቸውን ጠቅሰው፣ የተደረገላቸው ድጋፍ በዓሉን  በደስታና በአብሮነት ለማሳለፍ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም