ቀጥታ፡

የክልሉ ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ደቡብ ኢትዮጵያ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርዳቸውን ወስደዋል። 


 

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ሕዝቡ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ሚናውን መወጣት አለበት ብለዋል።


 

መንግሥት ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምርጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡም ከወዲሁ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለበት አንስተዋል።


 

ሌላው በወቅቱ የምርጫ ካርድ የወሰዱት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዞኑ ሕዝብ በአስቸጋሪ የፈተና ወቅት ላይ ቢገኝም ቀጣይ ዕጣ ፈንታው ላይ የሚወስንበትን ካርድ በመውሰድ ለምርጫው መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል 

በዞኑ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም