ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸኑ ሀገራዊ እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል - ሚኒስትር መሐመድ እንድሪስ
Dec 18, 2025 25
ባህር ዳር፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸኑ ሀገራዊ እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እንድሪስ ገለጹ። በባህር ዳር ከተማ "ማህበራዊ ሀብቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን" በሚል መሪ ሃሳብ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ እየተካሄደ ነው።   የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እንድሪስ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ኢትዮጵያ አብሮነትን የሚያጎለብቱና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችሉ የዳበሩ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት። እነዚህን ሀገራዊ አሴቶችን በመጠበቅና በማዳበር ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መስራት እንደሚገባ ገልጸው ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ድርሻ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። "ሀገር በእድገት ጎዳና ጸንታ የምትዘልቀው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ባህላዊ እሴቶችን ይበልጥ ማሳደግ ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር ነባር ባህላዊ የግጭት መፍቻ እሴቶችን ለማልማትና ለማደራጀት በሚከናወኑ ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል።   መንግስት ግጭቶች በምክክር እንዲፈቱ ትናንትም ዛሬም እየሰራና ለሰላምም እጁን ዘርግቶ ይገኛል ሲሉም አክለዋል። ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ የዛሬው መድረክም የህብረተሰቡ የሽምግልና እሴቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል። "የክልሉ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ተባብሮና ተከባብሮ የመኖር የዳበረ እሴት ያለው ነው" ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ናቸው።   የክልሉ መንግስት ለሽምግልና ስርዓት መጎልበት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በክልሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የክልሉ ህዝብ ሰላምን አጥብቆ ከመሻት ባለፈ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት የዳበረ እሴት ያለው ቢሆንም በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ባዳዎች ጥምረት የግጭት ማዕከል እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል። መንግስት ግጭቱ በሰላም እንዲቋጭ የሰላም እጁን መዘርጋቱን ገልጸው እስካሁን በተደረገው ጥረት የታጠቁ ሃይሎች የሰላም አማራጩን ተቀብለው መምጣታቸውን ተናግረዋል። በክልሉ እስካሁን ለመጣው ለውጥ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ የክልሉ መንግስት ለሽምግልና ስርዓት መዳበር አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በምክክር መድረኩ ላይም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ሥራ ሃላፊዎች፣ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በክልሉ የፍትህ አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል
Dec 18, 2025 17
አዳማ ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ የፍትህ አካላት ገለጹ። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች በፈትህ ስርአቱ ውስጥ የሚኖራቸውን እገዛ ማጠናከርን ያለመ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ምድብ ቋሚ ችሎት አስተባባሪ ረታ በቀለ፤ የፍትህ ስርአቱን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ሂደት የመንግስትና ባለደርሻ አካላት ጥረት እንዳለ ሆኖ በተለየም የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የፍትህ አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የማህበረሰብ መሪዎችና አጠቃላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ማሞ ቱሲ፤ በበኩላቸው ለፍትህ ስርአቱ ጥራትና ፍትሃዊነት የሁሉም አካላት ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም ደግሞ ለፍትህ ስርአቱ መስፋት፣ ሚዛናዊና ተአማኒ አገልግሎት ለመስጠት የማህበረሰብ መሪዎች የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል። በመሆኑም ለተሻለ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ የህብረተሰቡ ተሳትፎና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ከመድረኩ የሳታፊዎች መካከል የምስራቅ ሸዋ ዞን ሀገረስብከት የስብከተ ወንጌል ሃላፊ አባ ሃይለገብሬኤል ተስፋ፤ ሁላችንም የትክክለኛ ፍትህ አጋዦች መሆን አለብን ብለዋል። የአዳማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሃላፊ ሼህ ማሕሙድ ሁሴን፤ በየትኛውም አጋጣሚና በምንም ሁኔታ እውነትን ብቻ መናገርና መመስከር የግድ መሆኑን ገልጸዋል። የሀሰት ምስክርነትና በመዋሸት ፍትህ እንዲዛባና ሰዎች እንዲጎዱ ማድረግ በፈጣሪም ዘንድ የሚያስጠይቅ መሆኑን አንስተው ለትክክለኛ ፍትህ አጋዥ ሆነን እንገኝ ብለዋል። በመድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል።  
ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ የሆነው የምክክር ሂደት ለስኬት እንዲበቃ የድርሻችንን እንወጣለን-የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች
Dec 18, 2025 17
አርባምንጭ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ):- የምክክር ሂደት ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በይፋ ስራ ከጀመረ በኋላ ከዝግጅት ምእራፍ ተነስቶ የምክክር ምእራፍ እስከሚደርስ ድረስ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ሀገር ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ አጀንዳቸውን እንዲያቀርቡና እንዲመክሩ በማድረግ ስኬታማ ስራ መስራቱም ይታወቃል። በሀገር ጉዳይ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ ሁሉም መክሮ የጋራ መፍትሄ ለመሻትም የምክክር ኮሚሽኑ በ11 ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊዎችን ለይቶ አጀንዳቸውን ተቀብሏል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር ሂደቱ ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ከሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ ሰዲቃ ስሜ፤ የግጭትና ጦርነት ውጤቱ ኪሳራ እንጂ አንዳችም ትርፍና የሰላም መፍትሄ የማያመጣ በመሆኑ ለንግግርና ምክክር ቦታ መስጠት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በሀገር ጉዳይ ላይ በመምከር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ ያለው የምክክር ኮሚሽን ስኬታማ መሆን የሚችለው ሁላችንም ስናግዘውና ስንደግፈው ብቻ ነው ብለዋል። የምክክር ሂደቱ በሀገራችን የግጭትና አለመግባባት ምክንያቶች ሁነው የዘለቁትን ችግሮች በመለየት በዘላቂነት የምንፈታበት መልካም ዕድል ስለመሆኑ አንስተዋል። በመሆኑም እኛ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር ሂደት ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን በፅኑ በማመን ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ሌላኛው የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ ተፈራ ኦይቻ፤ በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ መክሮ ችግሮችን መፍታት ለሀገርና ለትውልድ የማሰብ የአስታዋይነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ እድል በመጠቀም በሀገራችን ጉዳዮች ላይ መክረን ሰላምን፣ አብሮነትንና ሀገራዊ አንድነትን ማጥበቅ አለብን ብለዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራው በዜጎች መካከል ያሉ መሠረታዊ ልዩነቶችን በምክክር በመፍታት በዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት የፀናች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማውረስ እንደሚረዳ እምነታቸውን ገልጸዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሰላምና ልማትን ማምጣት መሆኑን በአግባቡ የተገነዘብን በመሆኑ እስካሁን እያገዝነውና እየደገፍተው መጥተናል ያሉት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ አቶ አዳሙ ኪሮ ናቸው። በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አንስተው በምክክሩ የሚታሰበው ስኬት እንዲመጣ ሁላችንም የድርሻችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በይፋ ከተቋቋመ ጀምሮ ከዝግጅት ምእራፍ ተነስቶ በምክክር ምእራፍ እስካሁን በርካታ ተግባራትን ማከናወኑ ይታወቃል።    
በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተችሏል
Dec 18, 2025 32
ባህርዳር፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የመስኖ እና ሆርቲካልቸር ልማት ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አቶ ይበልጣል ወንድምነው፤ በክልሉ የበጋ መስኖ ልማት እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በክልሉ የምርት አማራጮችን በማስፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በዚህም የበልግና መኸር ምርትን ጨምሮ የበጋ መስኖ ልማት በስፋት እየተከናወነ ስለመሆኑ አንስተው ዘንድሮ በበጋ መስኖ 502 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ከተያዘው እቅድ እስካሁን 268 ሺህ 100 ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል ብለዋል። ከመስኖ ልማቱ 190 ሺህ ሄክታሩ የስንዴ ሰብል መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ ሌላው በተለያዩ ሰብሎች የለማ መሆኑን ገልጸዋል። በመስኖ ልማቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረው ከልማቱ ከ47 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የመስኖ ልማቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ገበያን ለማረጋጋት የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል። ‎በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዘውዱ ክፍሌ፤ በመስኖ ለማልማት ካዘጋጁት 2 ሄክታር መሬት ግማሹን በስንዴ ዘር መሸፈናቸውን ገልጸዋል። ‎በቀጣይም ቀሪውን መሬት በሌሎች ሰብሎችና የአትክልት ልማት ለመሸፈን እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል። ‎በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓንጓ ወረዳ አርሶ አደር ተመስገን ሽታሁን፤ በዘመናዊ የመስኖ ልማት ታግዘው ማከናወን ከጀመሩ ወዲህ የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ዘንድሮ የተሻለ ዝግጅት አድርገው እያለሙ መሆኑን አንስተው ጥሩ ምርት ሊያገኙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት በመስኖ በ1ኛ እና 2ኛ ዙር ከለማው መሬት 46 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱ ታውቋል።  
በነቀምቴ የከተማ ግብርና ሥራ ስርአተ ምግብን ለማሻሻልና ገበያን ለማረጋጋት ጉልህ አስተዋጾ አድርጓል
Dec 18, 2025 33
ነቀምቴ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዘኤ)፡-የከተማ ግብርና የአርሶ አደሩን ሥርአተ ምግብ ለማሻሻልና ገበያን ለማረጋጋት ጉልህ አስተዋጾ ማድረጉን የነቀምቴ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የነቀምቴ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ ከድር በከተማዋ 1ሺህ 144 ሄክታር መሬት በአትክልትና ሰብል መልማቱን ገልጸዋል። በተለይ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቱ የአርሶ አደሩን ስርአተ ምግብ ከማሻሻል ባለፈ ለአካባቢው ገበያ መረጋጋት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማ ግብርና በኢኒሼቲቭ የተተገበሩት የወተት ልማት፣ የከብት ማድለብና የዶሮ እርባታ ሥራዎች የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደጉንም ጠቁመዋል። የከተማ ግብርና ሥራ ነዋሪዎች ባላቸው አነስተኛ ቦታ አትክልት በማልማትና እንስሳትን በማርባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ገበያ እያረጋጉ መሆኑን አክለዋል። በነቀምቴ ከተማ በልማቱ እየተሳተፉ ካሉ ነዋሪዎች መካከል የሶርጋ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ተመስገን ስጦታው ባላቸው አንድ ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኞችን በማልማትና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አርሶ አደሩ በፍራፍሬ ልማት ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደጉ ለሥራቸው መስፋፋት ጉልህ ሚና መጫወቱንም ጠቁመዋል። በዚህም ቀደም ብለው የተከሏቸው የፍራፍሬ ችግኞች ፍሬ መስጠት እንደጀመሩና የአካባቢውን ገጽታ መቀየራቸውን አክለዋል። የከተማ ግብርና ሥራ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እያገዘ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ቶሎሳ ቂናጢ ናቸው። እሳቸውም በጓሮ እትክልት ልማት በመሰማራት ቤተሰባቸውን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ከመቻላቸው በለፈ ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል። በከተማ ግብርና ሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከግብርና ባለሙያዎች ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ግብአት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።    
የሚታይ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ተሸጋግራለች
Dec 18, 2025 55
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ መሸጋገሯን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ። “የኢትዮጵያ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ተመርቋል። ዘጋቢ ፊልሙ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግብርናን በማዘመንና ራስን ለመቻል የምታደርገውን ስኬታማ ተግባር በሚገባ የሚያሳይ መሆኑ በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።   ታሪኩ የተዋቀረው በኢትዮጵያ 'የስንዴ አብዮት' ዙሪያ ሲሆን፤ በኦሮሚያ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች ላይ ያተኮረ ነው። በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ገጸ ባህሪው ዮሐንስ፥ ግዙፍ የጭነት ተሽከርካሪን እያሽከረከረ የሀገርን ቀለብና የወደፊት ተስፋ የሆነውን ምርት በሚያጓጉዝበት ወቅት ከእውነተኛ ገበሬዎችና ባለሙያዎች ጋር ይገናኛል። በአፍሪካ ታላቅ የስንዴ አምራች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ይህንን ጥልቅ የሆነ ትራንስፎርሜሽን በምታከናውንበት በዚህ ወቅት ይህ ታሪክ ከስኬቱ ጀርባ ያለውን የሰው ልጅ ጥረትና ጥንካሬ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይም ነው።   ዘጋቢ ፊልሙ ማራኪ የሆኑ የመልክዓ ምድር ዕይታዎችን ከጥልቅ የታሪክ አወቃቀር ጋር በማዋሃድ፣አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከሚተገብሩባቸው እርሻዎች ጀምሮ ምርቶቹ እስከሚደርሱበት የከተማ ማዕከላት ድረስም ያስቃኛል። ፊልሙ ስለ ስንዴ ምርት ብቻ የሚተርክ ሳይሆን ስለ ጽናት፣ ስለ ፈጠራ እና ራሷን ችላ ለአፍሪካ የጋራ ብልጽግና አርአያ ለመሆን በመገስገስ ላይ ስላለች ሀገር የሚተርክ ድንቅ የኪነ-ጥበብ ሥራ ነው።   የዘጋቢ ፊልሙ ታሪክ የሚያተኩረው በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ላይ በዚህም ኢትዮጵያ ለዓመታት ለስንዴ ግዥ የምታወጣው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እና ይህን ለመቀየር የፖለቲካ ቁርጠኝነት የታከለበት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንዴት እንደተጀመረ እና አርሶ አደሩ እንዴት በኩታ ገጠም እርሻ እንደተሰለፈ የሚያስቃኝ ነው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከጠባቂነት ወጥታ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችበት ድንቅ ስኬትም የሚያስቃኝ ነው። ዘጋቢ ፊልሙ ጥራቱን ጠብቆ የተሰራ ሲሆን ለዓይን የሚማርኩ የኢትዮጵያ እርሻዎች፣ የአዝመራ አሰባሰብ ሂደቶች እና የአርሶ አደሩ የደስታ ስሜትንም ያካተተ ነው። ዘጋቢ ፊልሙ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የደረሰችበትን ድንቅ ስኬት እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማየት መነሳሳት የሚፈጥሩበትም ነው። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ተሸጋግራለች። ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የስንዴ ምርት ከውጭ ስታስገባ መቆየቷን ገልጸው፤ ይህንን ታሪክ ለመቀየርና ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ከመቻል አልፋ ለሌሎች እንድትተርፍ ለማስቻል የተቀረጸው ስትራቴጂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። በቁርጠኝነት ተግባራዊ የተደረገው የኩታ ገጠም እርሻ አሠራር ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ጠቁመው፥በአሲዳማነት የተጠቁ በርካታ ሄክታር መሬቶችን በኖራ በማከም ወደ ምርት እንዲገቡ የማድረግ ሥራዎችም ለውጤታማነቱ ትልቅ ሚና መጫወታቸውን አስረድተዋል። ረግረጋማ የሆኑ የደጋ ቦታዎችን በቴክኖሎጂ በማድረቅ ለምርት እንዲውሉ ማድረግ ሌላኛው መሠረት መሆኑን ጠቅሰው፥ በበርካታ ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለሀገር ውስጥ ብሎም ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን ወደ ውጪ እንድትልክ ማስቻሉን ገልጸዋል። ዘጋቢ ፊልሙ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ድልን በመረጃና በምስል ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ወጣቶች ወደ ግብርናው ዘርፍ በስፋት እንዲገቡ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የግብርና ብድር አስጀመረ
Dec 18, 2025 82
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘላቂ ግብርናን ለመደገፍና የገጠር ኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበት ለአርሶና አርብቶ አደሮች የግብርና ብድርን በይፋ አስጀምሯል። የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ በወቅቱ የብድር አገልግሎቱ የአነስተኛ ባለ-ይዞታ አርሶና አርብቶ አደሮች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።   አገልግሎቱ አርሶ አደሮች በግለሰብ ደረጃም ሆነ ተደራጅተው ከግብርና ግብዓቶች እስከ ማሽነሪዎች ግዥ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑን ገልጸዋል። ለእንስሳት ምርታማነት አርብቶ አደሮች የተለያዩ ግብዓቶች ለማሟላት ዕድል የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል። አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተመላክቷል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የግብርና ፋይናንስ በማሳደግ የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡   መንግስት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉትን በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ አካታች የሆነ የፋይናንስ ተደራሽነትን በገጠር ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸው፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፋ ያደረገው የብድር አገልግሎት አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ባንኩ ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ የጀመረው አገልግሎት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑንም አመልክተዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ግብአት ሽፋንን በማሳደግ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል ተችሏል - ጤና ሚኒስቴር
Dec 18, 2025 65
አሶሳ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ግብአት የሆነውን ኦክስጂን ሽፋን በማሳደግ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ማሻሻል መቻሉን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገር አቀፍ የህክምና ኦክስጂን የምክክር ዐውደ ጥናት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ክልሎች ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ሆስፒታሎች ስራ አስኪያጆች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።   የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ አክሞ ማዳን የሚያስችል የጤና አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ በመተግበር ላይ ይገኛል። ይህም ጥራቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ከመሆኑም በተጨማሪ መሠረታዊ የህክምና መሳሪያዎች ተደራሽ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት የነበረውን ሶስት የኦክስጂን ማዕከል በአሁኑ ሰዓት ወደ 85 በማድረስ ዜጎች ህክምናውን በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ በኦክስጂን እጥረት የሚከሰተውን ሞት መቀነስ ተችሏል ብለዋል።   የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በበኩላቸው፤ በአሶሳ ሆስፒታል የተተከለው የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከል ከሆስፒታሉ በተጨማሪ በክልሉ ጤና ተቋማት ምርቱን በማቅረብ ህብረተሰቡ የተቀላጠፈ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ አስችሏል ብለዋል። የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።
የአየር ኃይል የምስረታ በዓል ተቋሙ የደረሰበትን ደረጃ በሚያሳይ መልኩ ይከበራል
Dec 18, 2025 89
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡- 90ኛው የኢፌዲሪ አየር ኃይል የምሰረታ በዓል አየር ኃይሉ የደረሰበትን ደረጃ በሚያሳይ እና በሚመጥን መልኩ እንደሚከበር የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ ገለጹ። የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን የተመለከተ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።   የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ በዚሁ ወቅት አየር ኃይል ረጅም እድሜ ካላቸው ተቋማት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። የበዓሉ ዓላማ አየር ኃይሉ ያለፋቸውን ተጋድሎዎች እና የተከፈለውን ዋጋ ለመዘከርና ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ተቋሙ ቀዳሚ አየር ኃይል ለመሆን እያከናወነ ያለውን ስራ ለማሳየት መሆኑን ጠቁመዋል። አየር ኃይል የኢትዮጵያን ነጻነት አስጠብቆ ዛሬ ላይ ማድረሱን ጠቅሰው፤ ከለውጡ ወዲህ ራሱን በሰው ኃይል፣ በትጥቅ እንዲሁም በመሰረተ ልማት ማደራጀቱን ጠቁመዋል። 90ኛው የኢፌዲሪ አየር ኃይል የምስረታ በዓል አየር ኃይሉ የደረሰበትን ደረጃ በሚያሳይ መልኩ እንደሚከበር ጠቁመዋል። በበዓሉ የተለያዩ ሀገራት የሚሳተፉበት የአየር ላይ ትርኢት፣ የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች ኮንፈረንስና የአቪዬሽን ኤክስፖ እንደሚካሄድ አመላክተዋል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር በበኩላቸው፤ አየር ኃይል የሀገር ኩራት እና የህዝብ መከታ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያን የነጻነት ታሪክ አጽንተው ካቆሙ ተቋማት መካከል አንዱ የአየር ኃይል መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪም የተለያዩ የሰው ሰራሽ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ህዝብን ከአደጋ የጠበቀ ተቋም መሆኑን ጠቁመዋል። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ባደረገው ሪፎርም አቅሙን በማሳደግ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ሌት ተቀን በሚስጠበቅ ላይ የሚገኝ የሀገር ሀብት የሆነ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የኢትዮጵያና ህንድ ስትራቴጂክ አጋርነት ያላቸውን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት በሚገባ እንዲጠቀሙ ትልቅ እድል ይፈጥራል
Dec 18, 2025 84
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያና ህንድ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት ማሳደጋቸው ያላቸውን አህጉራዊ ሚናቸውን በመጠቀም የታዳጊ ሀገራትን ፍላጎት ለማስከበር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የረጅም ዘመን ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማደጉ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በምክር ቤት ንግግራቸው ህንድና ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት ማደጉ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።   የምክር ቤት አባል ነጃት ግርማ (ዶ/ር) ሁለቱ ሀገራት የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል። ይህን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ለህዝቦቻቸው የጋራ ብልጽግና ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ማንሳታቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው የምክር ቤት አባሉ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያና ህንድ ቀደምት የስልጣኔ ባለቤት እንደመሆናቸው የቀጣይ ዕጣ ፋንታቸው በእጃቸው ላይ ነው ብለዋል። የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት ማደጉ በምንም ሁኔታ የማይናወጥ ወዳጅነት መመስረት ያስችላቸዋል ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝትም የሀገራቱ ግንኙነት የበለጠ መጠናከሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል።   አጋርነቱ በዓለም አቀፍ መድረኮች እርስ በእርስ ለመደጋገፍ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የገለፁት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን አህጉራዊ ተጽዕኖ በመጠቀም የታዳጊ ሀገራትን ፍላጎት ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያና ህንድ ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን እ.ኤ.አ በ1948 የጀመሩ ሲሆን፣ አሁን የደረሱበት የስትራቴጂክ አጋርነት ደረጃ ለሁለቱ ህዝቦች የጋራ ብልጽግና አዲስ ተስፋ የሰነቀ መሆኑ ተመላክቷል።
ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት ድጋፋችንን እናጠናክራለን
Dec 17, 2025 140
ሰቆጣ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፡-የአካባቢያቸው ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመሆን ሲያደርጉ የቆዩቱን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጋዝጊብላ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ "ሁሌም ለሰላም ዘብ እንቆማለን" በሚል መሪ ሃሳብ በሰላም ግንባታ ዙሪያ በጋዝጊብላ ወረዳ አስ ከተማ ዛሬ ተወያይተዋል።   ውይይቱ የተካሄደው የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችና የብሔረሰብ አስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት ነው። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ተስፋዬ ወሰን፤ ቀደም ሲል ፅንፈኛው በአካባቢው ታዳጊ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ እንዲስተጓጎሉ በማደረግ ጭምር በደል መፈፀሙን አስታውሰዋል። በአካባቢው ሕግ በማስከበር ሰላምን እንዲሰፍን በተከናወኑ ሥራዎች የበኩላቸውን ሲወጡ መቆየታቸውንና በዚህም ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።   በቀጣይም የአካባቢያቸው ሰላም በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጠል ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ነው የገለጹት። ሌላው ተሳታፊ ወይዘሮ መሰሉ አታላይ ፤ "አጥፊዎችን በማጋለጥ ለሰላም ዘብ እንቆማለን " ብለዋል። ችግሮች በውይይትና በሰላም እንዲቋጩ የሚደግፉ መሆኑን ገልጸው፤ በጫካ የቀሩ የመንግስትን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ተቀብለው በመምጣት የበደሉትን ሕብረተሰብ እንዲክሱ የእናትነት ሚናቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። በየደረጃው ያለው የፀጥታ ሃይል ለሕዝብ ሰላም መስፈን ሲባል ዋጋ እየከፈለ ነው፤ እኛም ከጎኑ በመሆን እያገዝን ነው ያሉት ደግሞ አቶ አረጋ ሳሙኤል ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአካባቢያቸው የሰፈነውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በሚከናወኑ ሥራዎች እያደረጉት ያለውን እገዛ ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። የጽንፈኛውን እኩይ ተግባር ለመመከት ሕዝቡ አምርሮ በመታገል ሲያደርግ የቆየውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተነገሩት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሰተዳደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ ናቸው። የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪና የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን ፤ የጋዝጊብላ ወረዳ ሰላም ፀንቶ እንዲቀጥል የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች እገዛቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል እንዳመለከቱት፤ ጽንፈኛው የታሪካዊ ጠላቶችን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፈፀም ቢሞክርም በሕግ ማስከበር እርምጃ ማምከን ተችሏል። መንግስት ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደሰላም የመጡ እንዳሉ አንሰተው፤ የሰላምን አማራጭ በማይቀበሉት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ሕብረተሰቡ ሰላምን ለማፅናት ሲያደርግ የቆየውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል። በውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር ይሰራሉ
Dec 17, 2025 145
አዲስ አበባ፤ታኅሣስ 8/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገለጹ። የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር በሰላም ግንባታና ግጭትን አስቀድሞ መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።   ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር ስለሚያደርገው ጥረት ገለጻ አድርገዋል። የአውሮፓ ኅብረት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ እና ገንቢ ሚናም ማድነቃቸውን ሚኒስቴሩ ለኢዜአ የላከው መረጃ አመላክቷል። አምባሳደሯ በበኩላቸው፥ የተጀመሩ የጋራ ግቦችን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። አክለውም፥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጉዞ ቀጣይነት ያለው እንዲሁም የተጠናከረ ትብብር ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የጋራ ትርክትን በመገንባት ሂደት ድጋፋችንን እናጠናክራለን 
Dec 17, 2025 149
ሆሳዕና ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ መንግሥት የጋራ ትርክትን በመገንባት ሂደት እያደረገ ላለው ጥረት ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ በከተማው የቦብቾ ቀበሌ ነዋሪው አቶ አለማየሁ ኤልያስ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ መንግሥት የጋራ ትርክትን በመገንባት ፈጣን ሀገራዊ እድገት ለማስመዝገብ እያደረገ ያለው ጥረት ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።   አሁን ላይ በመደመር መንግሥት ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበባቸው መሆኑን ጠቁመው የበለፀገች ሀገርን ለመገንባት አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ሁሉም በተሰማራበት መስክ ጠንክሮ መስራት አለበት ነው ያሉት። መንግሥት ሌብነትን የሚፀየፍ ትውልድ በመፍጠር ፈጣን እድገት እንዲረጋገጥ ትርጉም ያለው ስራ እየሰራ ይገኛል ያሉት ደግሞ በከተማው የሄጦ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ መሰረት አቢዮ ናቸው፡፡   እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የሚያስደስቱና የነገው ትውልድን ተስፋ የሚያለመልሙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡   የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አበበ አያልቅበት በበኩላቸው፤የጎሰኝነትና ዘረኝነት አመለካከት በመውጣት በሀገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ማስቀጠልና በተሰማራንበት የስራ መስክ በትጋት በመስራት ውጤታማነታችንን ማላቅ ይጠበቅብናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ እና ህንድ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገሩ የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ የሚያጸና ነው 
Dec 17, 2025 198
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እና ህንድ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሸጋገሩ የሀገራቱን ትስስር ማስፋትና ማጠናከር የሚያስችል እርምጃ መሆኑን የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነትና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የሀገራቱ የሁለትዮሽ የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመረው ህንድ ከቅኝ ግዛት ነጻ በወጣችበት ማግስት እንደሆነም አውስተዋል።   ኢትዮጵያ እና ህንድ በባህል እና በትምህርት ያላቸው ትብብር የህዝብ ለህዝብ ቁርኝታቸው ይበልጥ እንዲጠብቅ ማድረጉን ነው የገለጹት። የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊየን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃጨርቅ እና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ኩባንያዎቹ ከ75 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል መፍጠራቸውንም በንግግራቸው ጠቁመዋል። ሀገራቱ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብራቸውን ማጠናከር የሚችሉባቸው በርካታ እድሎች እንዳሉም ነው ያነሱት። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።   የሁለቱን ህዝቦች በምግብ ዋስትና፣ በጤና እና አቅም ግንባታ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አንስተዋል። ሁለቱ ሀገራት ግብርና፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች እርስ በእርስ በመማማር የጋራ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚቻል አመልክተዋል። ህንድ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ እድገት አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ አመስግነው ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል።
የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ያጠናክራል
Dec 17, 2025 112
ድሬዳዋ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራውን እንደሚያጠናክር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ገለጹ። የአስተዳደሩ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አብዲ ሙክታርን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አድርጎ መርጧል።   በዚሁ ጊዜ አፈ-ጉባኤው ባደረጉት ንግግር አስፈፃሚው አካል የህዝብ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በፍጥነት፣ በጥራትና በላቀ መልኩ ለመፈፀም መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል። የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ምክር ቤቱ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።   ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው የቀረቡለትን አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። በዚህም መሠረት፦ 1/ ወይዘሮ ሌሊሴ አህመድ - የድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ 2/ አቶ ብሩክ ወርቅነህ - የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም 3/ አቶ ፉአድ መሐመድ - የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን የተጣለባቸውን የህዝብ ኃላፊነት በታማኝነትና በቁርጠኝነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
ሕንድ ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
Dec 17, 2025 172
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 8/2018(ኢዜአ)፡- ሕንድ ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡   በንግግራቸውም፤ የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙነት በርካታ ዓመታትን ማስቆጠሩን ጠቁመው፤ ታሪክና ባህል የሚጋሩ ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል። በመሆኑም በቀጣይ ሕንድ ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በተለይም በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሳይበር ሴኩሪቲ፣ በዐቅም ግንባታ፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ሀገራቸው ፍላጎት እንዳላትም አመላክተዋል። በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታ ዘርፍም የሕንድና ኢትዮጵያ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም መሠረት በይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።   ከዓድዋ ድል ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያውያን ቅኝ ላለመገዛት በልበ ሙሉነትና በአንድነት ያደረጉት ተጋድሎና ያገኙትን ድል አድንቀዋል። ኢትዮጵያ አሁንም በቀጣናው ያላትን የሰላምና መረጋጋት ሚና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድንቀዋል። በዓለም መድረኮችም ሕንድና ኢትዮጵያ ያላቸውን ድምፅ በማስተባበር ለታዳጊ ሀገራት መብት መከበር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ማህበራዊ
ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸኑ ሀገራዊ እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል - ሚኒስትር መሐመድ እንድሪስ
Dec 18, 2025 25
ባህር ዳር፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸኑ ሀገራዊ እሴቶችን ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ እንድሪስ ገለጹ። በባህር ዳር ከተማ "ማህበራዊ ሀብቶቻችን ለዘላቂ ሰላምና ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን" በሚል መሪ ሃሳብ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ እየተካሄደ ነው።   የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እንድሪስ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት ኢትዮጵያ አብሮነትን የሚያጎለብቱና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችሉ የዳበሩ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት። እነዚህን ሀገራዊ አሴቶችን በመጠበቅና በማዳበር ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መስራት እንደሚገባ ገልጸው ለዚህም የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች ድርሻ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። "ሀገር በእድገት ጎዳና ጸንታ የምትዘልቀው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ባህላዊ እሴቶችን ይበልጥ ማሳደግ ላይ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር ነባር ባህላዊ የግጭት መፍቻ እሴቶችን ለማልማትና ለማደራጀት በሚከናወኑ ተግባራት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል።   መንግስት ግጭቶች በምክክር እንዲፈቱ ትናንትም ዛሬም እየሰራና ለሰላምም እጁን ዘርግቶ ይገኛል ሲሉም አክለዋል። ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ የዛሬው መድረክም የህብረተሰቡ የሽምግልና እሴቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል። "የክልሉ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ተባብሮና ተከባብሮ የመኖር የዳበረ እሴት ያለው ነው" ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ናቸው።   የክልሉ መንግስት ለሽምግልና ስርዓት መጎልበት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በክልሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የክልሉ ህዝብ ሰላምን አጥብቆ ከመሻት ባለፈ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት የዳበረ እሴት ያለው ቢሆንም በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ባዳዎች ጥምረት የግጭት ማዕከል እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል። መንግስት ግጭቱ በሰላም እንዲቋጭ የሰላም እጁን መዘርጋቱን ገልጸው እስካሁን በተደረገው ጥረት የታጠቁ ሃይሎች የሰላም አማራጩን ተቀብለው መምጣታቸውን ተናግረዋል። በክልሉ እስካሁን ለመጣው ለውጥ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ የክልሉ መንግስት ለሽምግልና ስርዓት መዳበር አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በምክክር መድረኩ ላይም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ሥራ ሃላፊዎች፣ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በክልሉ የፍትህ አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል
Dec 18, 2025 17
አዳማ ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ የፍትህ አካላት ገለጹ። የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች በፈትህ ስርአቱ ውስጥ የሚኖራቸውን እገዛ ማጠናከርን ያለመ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ምድብ ቋሚ ችሎት አስተባባሪ ረታ በቀለ፤ የፍትህ ስርአቱን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ሂደት የመንግስትና ባለደርሻ አካላት ጥረት እንዳለ ሆኖ በተለየም የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የፍትህ አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የማህበረሰብ መሪዎችና አጠቃላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል። የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ማሞ ቱሲ፤ በበኩላቸው ለፍትህ ስርአቱ ጥራትና ፍትሃዊነት የሁሉም አካላት ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም ደግሞ ለፍትህ ስርአቱ መስፋት፣ ሚዛናዊና ተአማኒ አገልግሎት ለመስጠት የማህበረሰብ መሪዎች የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል። በመሆኑም ለተሻለ የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ የህብረተሰቡ ተሳትፎና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ከመድረኩ የሳታፊዎች መካከል የምስራቅ ሸዋ ዞን ሀገረስብከት የስብከተ ወንጌል ሃላፊ አባ ሃይለገብሬኤል ተስፋ፤ ሁላችንም የትክክለኛ ፍትህ አጋዦች መሆን አለብን ብለዋል። የአዳማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሃላፊ ሼህ ማሕሙድ ሁሴን፤ በየትኛውም አጋጣሚና በምንም ሁኔታ እውነትን ብቻ መናገርና መመስከር የግድ መሆኑን ገልጸዋል። የሀሰት ምስክርነትና በመዋሸት ፍትህ እንዲዛባና ሰዎች እንዲጎዱ ማድረግ በፈጣሪም ዘንድ የሚያስጠይቅ መሆኑን አንስተው ለትክክለኛ ፍትህ አጋዥ ሆነን እንገኝ ብለዋል። በመድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች ተሳትፈዋል።  
ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ የሆነው የምክክር ሂደት ለስኬት እንዲበቃ የድርሻችንን እንወጣለን-የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች
Dec 18, 2025 17
አርባምንጭ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ):- የምክክር ሂደት ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በይፋ ስራ ከጀመረ በኋላ ከዝግጅት ምእራፍ ተነስቶ የምክክር ምእራፍ እስከሚደርስ ድረስ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ሀገር ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ አጀንዳቸውን እንዲያቀርቡና እንዲመክሩ በማድረግ ስኬታማ ስራ መስራቱም ይታወቃል። በሀገር ጉዳይ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ ሁሉም መክሮ የጋራ መፍትሄ ለመሻትም የምክክር ኮሚሽኑ በ11 ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊዎችን ለይቶ አጀንዳቸውን ተቀብሏል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር ሂደቱ ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ከሀገር ሽማግሌዎቹ መካከል አቶ ሰዲቃ ስሜ፤ የግጭትና ጦርነት ውጤቱ ኪሳራ እንጂ አንዳችም ትርፍና የሰላም መፍትሄ የማያመጣ በመሆኑ ለንግግርና ምክክር ቦታ መስጠት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። በሀገር ጉዳይ ላይ በመምከር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እየሰራ ያለው የምክክር ኮሚሽን ስኬታማ መሆን የሚችለው ሁላችንም ስናግዘውና ስንደግፈው ብቻ ነው ብለዋል። የምክክር ሂደቱ በሀገራችን የግጭትና አለመግባባት ምክንያቶች ሁነው የዘለቁትን ችግሮች በመለየት በዘላቂነት የምንፈታበት መልካም ዕድል ስለመሆኑ አንስተዋል። በመሆኑም እኛ የሀገር ሽማግሌዎች የምክክር ሂደት ለሀገር ዘላቂ ሰላም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን በፅኑ በማመን ለስኬታማነቱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። ሌላኛው የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ ተፈራ ኦይቻ፤ በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ መክሮ ችግሮችን መፍታት ለሀገርና ለትውልድ የማሰብ የአስታዋይነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ እድል በመጠቀም በሀገራችን ጉዳዮች ላይ መክረን ሰላምን፣ አብሮነትንና ሀገራዊ አንድነትን ማጥበቅ አለብን ብለዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራው በዜጎች መካከል ያሉ መሠረታዊ ልዩነቶችን በምክክር በመፍታት በዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት የፀናች ሀገር ለመጪው ትውልድ ለማውረስ እንደሚረዳ እምነታቸውን ገልጸዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሰላምና ልማትን ማምጣት መሆኑን በአግባቡ የተገነዘብን በመሆኑ እስካሁን እያገዝነውና እየደገፍተው መጥተናል ያሉት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ አቶ አዳሙ ኪሮ ናቸው። በመሆኑም ይህንን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አንስተው በምክክሩ የሚታሰበው ስኬት እንዲመጣ ሁላችንም የድርሻችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በይፋ ከተቋቋመ ጀምሮ ከዝግጅት ምእራፍ ተነስቶ በምክክር ምእራፍ እስካሁን በርካታ ተግባራትን ማከናወኑ ይታወቃል።    
በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ግብአት ሽፋንን በማሳደግ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል ተችሏል - ጤና ሚኒስቴር
Dec 18, 2025 65
አሶሳ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ግብአት የሆነውን ኦክስጂን ሽፋን በማሳደግ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ማሻሻል መቻሉን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገር አቀፍ የህክምና ኦክስጂን የምክክር ዐውደ ጥናት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ክልሎች ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ሆስፒታሎች ስራ አስኪያጆች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።   የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬህይወት አበበ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ አክሞ ማዳን የሚያስችል የጤና አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ በመተግበር ላይ ይገኛል። ይህም ጥራቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ከመሆኑም በተጨማሪ መሠረታዊ የህክምና መሳሪያዎች ተደራሽ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት የነበረውን ሶስት የኦክስጂን ማዕከል በአሁኑ ሰዓት ወደ 85 በማድረስ ዜጎች ህክምናውን በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ በኦክስጂን እጥረት የሚከሰተውን ሞት መቀነስ ተችሏል ብለዋል።   የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በበኩላቸው፤ በአሶሳ ሆስፒታል የተተከለው የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከል ከሆስፒታሉ በተጨማሪ በክልሉ ጤና ተቋማት ምርቱን በማቅረብ ህብረተሰቡ የተቀላጠፈ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ አስችሏል ብለዋል። የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።
ኢኮኖሚ
በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተችሏል
Dec 18, 2025 32
ባህርዳር፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የመስኖ እና ሆርቲካልቸር ልማት ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አቶ ይበልጣል ወንድምነው፤ በክልሉ የበጋ መስኖ ልማት እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በክልሉ የምርት አማራጮችን በማስፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። በዚህም የበልግና መኸር ምርትን ጨምሮ የበጋ መስኖ ልማት በስፋት እየተከናወነ ስለመሆኑ አንስተው ዘንድሮ በበጋ መስኖ 502 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ከተያዘው እቅድ እስካሁን 268 ሺህ 100 ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል ብለዋል። ከመስኖ ልማቱ 190 ሺህ ሄክታሩ የስንዴ ሰብል መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ ሌላው በተለያዩ ሰብሎች የለማ መሆኑን ገልጸዋል። በመስኖ ልማቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረው ከልማቱ ከ47 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝ ጠቁመዋል። የመስኖ ልማቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ገበያን ለማረጋጋት የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል። ‎በሰሜን ጎጃም ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዘውዱ ክፍሌ፤ በመስኖ ለማልማት ካዘጋጁት 2 ሄክታር መሬት ግማሹን በስንዴ ዘር መሸፈናቸውን ገልጸዋል። ‎በቀጣይም ቀሪውን መሬት በሌሎች ሰብሎችና የአትክልት ልማት ለመሸፈን እየተዘጋጁ መሆኑን ተናግረዋል። ‎በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የጓንጓ ወረዳ አርሶ አደር ተመስገን ሽታሁን፤ በዘመናዊ የመስኖ ልማት ታግዘው ማከናወን ከጀመሩ ወዲህ የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ዘንድሮ የተሻለ ዝግጅት አድርገው እያለሙ መሆኑን አንስተው ጥሩ ምርት ሊያገኙ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት በመስኖ በ1ኛ እና 2ኛ ዙር ከለማው መሬት 46 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱ ታውቋል።  
በነቀምቴ የከተማ ግብርና ሥራ ስርአተ ምግብን ለማሻሻልና ገበያን ለማረጋጋት ጉልህ አስተዋጾ አድርጓል
Dec 18, 2025 33
ነቀምቴ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዘኤ)፡-የከተማ ግብርና የአርሶ አደሩን ሥርአተ ምግብ ለማሻሻልና ገበያን ለማረጋጋት ጉልህ አስተዋጾ ማድረጉን የነቀምቴ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የነቀምቴ ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ግርማ ከድር በከተማዋ 1ሺህ 144 ሄክታር መሬት በአትክልትና ሰብል መልማቱን ገልጸዋል። በተለይ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቱ የአርሶ አደሩን ስርአተ ምግብ ከማሻሻል ባለፈ ለአካባቢው ገበያ መረጋጋት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማ ግብርና በኢኒሼቲቭ የተተገበሩት የወተት ልማት፣ የከብት ማድለብና የዶሮ እርባታ ሥራዎች የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደጉንም ጠቁመዋል። የከተማ ግብርና ሥራ ነዋሪዎች ባላቸው አነስተኛ ቦታ አትክልት በማልማትና እንስሳትን በማርባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ገበያ እያረጋጉ መሆኑን አክለዋል። በነቀምቴ ከተማ በልማቱ እየተሳተፉ ካሉ ነዋሪዎች መካከል የሶርጋ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ተመስገን ስጦታው ባላቸው አንድ ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኞችን በማልማትና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አርሶ አደሩ በፍራፍሬ ልማት ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደጉ ለሥራቸው መስፋፋት ጉልህ ሚና መጫወቱንም ጠቁመዋል። በዚህም ቀደም ብለው የተከሏቸው የፍራፍሬ ችግኞች ፍሬ መስጠት እንደጀመሩና የአካባቢውን ገጽታ መቀየራቸውን አክለዋል። የከተማ ግብርና ሥራ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እያገዘ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ቶሎሳ ቂናጢ ናቸው። እሳቸውም በጓሮ እትክልት ልማት በመሰማራት ቤተሰባቸውን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ከመቻላቸው በለፈ ለገበያ በማቅረብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል። በከተማ ግብርና ሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከግብርና ባለሙያዎች ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ግብአት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።    
በከተሞቹ የሰፈነው ሰላም ለመሰረተ ልማትና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አስችሏል
Dec 18, 2025 38
ባህር ዳር፤ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦በአካባቢያቸው ሰላም መስፈኑ ለመሰረተ ልማትና ኢንቨስትመንት ትኩረት ሰጥተው በመስራት ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ እንዳስቻላቸው የደሴና የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደሮች ገለጹ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት በከተማው የሰፈነው ሰላም ዘንድሮ ከ200 በላይ አልሚ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲወስዱ አስችሏል። በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት ውስጥ ከ160 በላይ የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ የግንባታ ስራቸውን አጠናቀው ማሽን ከውጭ እያስገቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም 18 ኢንዱስትሪዎች በያዝነው በጀት ዓመት ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ በተደረገ የተጠናከረ ድጋፍ እስካሁን አራቱ ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል ብለዋል። ወደ ማምረት ከተሸጋገሩት ውስጥም የምግብ ማቀነባበሪያ፣ የፕላስቲክና ሌሎች ፋብሪካዎች እንደሚገኙበት አቶ በድሉ ጠቁመዋል። ደብረ ብርሃን ከተማ ለአዲስ አበባ ባላት ቅርበትና ሰላም የሰፈነባት በመሆኑ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፤ ከተማ አስተዳደሩም የሚመጡ ባለሃብቶች በፍጥነት የሚስተናገዱበት አሰራር ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በወተት ልማት፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ፣በመኖ ማቀነባበርና በሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ለመሰማራት ለሚመጡ ባለሃብቶች በራቸው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል። በተመሳሳይ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፥ በደሴና አካባቢው ሰላም በመረጋገጡ ከተማ ለቱሪዝም፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል። በዚህም የመጀመሪያውን ዙር የኮሪደር ልማት በስኬት ገንብቶ በማጠናቀቅ ሁለተኛው ዙር መጀመሩን ጠቁመው፥ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ሰላም በመስፈኑ በእያንዳንዱ ቀን በከተማዋ የተለያዩ ስብሰባዎች እየተካሄዱ መሆኑንና በዚህም ደሴን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። በኮሪደር ልማቱ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ራሱን፣ ቤተሰቡንና ሀገሩን እንዲጠቅም ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም አስረድተዋል። እንደ ከንቲባዎቹ ገለጻ፥ በከተሞቹ በልማት ተጨባጭ ውጤት ሊመጣ የቻለው ጽንፈኛው ሃይል የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርገውን ሙከራ ከህብረተሰቡና ከጸጥታ አካሉ ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ በማክሸፋቸው ነው።
ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ተሸጋግራለች
Dec 18, 2025 55
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ መሸጋገሯን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ። “የኢትዮጵያ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ተመርቋል። ዘጋቢ ፊልሙ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግብርናን በማዘመንና ራስን ለመቻል የምታደርገውን ስኬታማ ተግባር በሚገባ የሚያሳይ መሆኑ በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።   ታሪኩ የተዋቀረው በኢትዮጵያ 'የስንዴ አብዮት' ዙሪያ ሲሆን፤ በኦሮሚያ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች ላይ ያተኮረ ነው። በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ገጸ ባህሪው ዮሐንስ፥ ግዙፍ የጭነት ተሽከርካሪን እያሽከረከረ የሀገርን ቀለብና የወደፊት ተስፋ የሆነውን ምርት በሚያጓጉዝበት ወቅት ከእውነተኛ ገበሬዎችና ባለሙያዎች ጋር ይገናኛል። በአፍሪካ ታላቅ የስንዴ አምራች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ይህንን ጥልቅ የሆነ ትራንስፎርሜሽን በምታከናውንበት በዚህ ወቅት ይህ ታሪክ ከስኬቱ ጀርባ ያለውን የሰው ልጅ ጥረትና ጥንካሬ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይም ነው።   ዘጋቢ ፊልሙ ማራኪ የሆኑ የመልክዓ ምድር ዕይታዎችን ከጥልቅ የታሪክ አወቃቀር ጋር በማዋሃድ፣አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከሚተገብሩባቸው እርሻዎች ጀምሮ ምርቶቹ እስከሚደርሱበት የከተማ ማዕከላት ድረስም ያስቃኛል። ፊልሙ ስለ ስንዴ ምርት ብቻ የሚተርክ ሳይሆን ስለ ጽናት፣ ስለ ፈጠራ እና ራሷን ችላ ለአፍሪካ የጋራ ብልጽግና አርአያ ለመሆን በመገስገስ ላይ ስላለች ሀገር የሚተርክ ድንቅ የኪነ-ጥበብ ሥራ ነው።   የዘጋቢ ፊልሙ ታሪክ የሚያተኩረው በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ላይ በዚህም ኢትዮጵያ ለዓመታት ለስንዴ ግዥ የምታወጣው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እና ይህን ለመቀየር የፖለቲካ ቁርጠኝነት የታከለበት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንዴት እንደተጀመረ እና አርሶ አደሩ እንዴት በኩታ ገጠም እርሻ እንደተሰለፈ የሚያስቃኝ ነው። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከጠባቂነት ወጥታ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ የጀመረችበት ድንቅ ስኬትም የሚያስቃኝ ነው። ዘጋቢ ፊልሙ ጥራቱን ጠብቆ የተሰራ ሲሆን ለዓይን የሚማርኩ የኢትዮጵያ እርሻዎች፣ የአዝመራ አሰባሰብ ሂደቶች እና የአርሶ አደሩ የደስታ ስሜትንም ያካተተ ነው። ዘጋቢ ፊልሙ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት የደረሰችበትን ድንቅ ስኬት እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ተሞክሮ በማየት መነሳሳት የሚፈጥሩበትም ነው። የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ችላ ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ተሸጋግራለች። ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የስንዴ ምርት ከውጭ ስታስገባ መቆየቷን ገልጸው፤ ይህንን ታሪክ ለመቀየርና ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን ከመቻል አልፋ ለሌሎች እንድትተርፍ ለማስቻል የተቀረጸው ስትራቴጂ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቅሰዋል። በቁርጠኝነት ተግባራዊ የተደረገው የኩታ ገጠም እርሻ አሠራር ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ጠቁመው፥በአሲዳማነት የተጠቁ በርካታ ሄክታር መሬቶችን በኖራ በማከም ወደ ምርት እንዲገቡ የማድረግ ሥራዎችም ለውጤታማነቱ ትልቅ ሚና መጫወታቸውን አስረድተዋል። ረግረጋማ የሆኑ የደጋ ቦታዎችን በቴክኖሎጂ በማድረቅ ለምርት እንዲውሉ ማድረግ ሌላኛው መሠረት መሆኑን ጠቅሰው፥ በበርካታ ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ለሀገር ውስጥ ብሎም ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን ወደ ውጪ እንድትልክ ማስቻሉን ገልጸዋል። ዘጋቢ ፊልሙ የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ድልን በመረጃና በምስል ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ወጣቶች ወደ ግብርናው ዘርፍ በስፋት እንዲገቡ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በሚዛን አማን ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋይን እንግልት አስቀርቷል
Dec 18, 2025 36
ሚዛን አማን፤ታኅሳሥ 9/2018 (ኢዜአ)፦መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋይን እንግልት ያስቀረ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተማዋ ኢዜአ ያናገራቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዳሉት፥ አገልግሎቱ አንድ ጉዳይ ለማስፈጸም በተለያዩ ቢሮዎች ሲኬድ ይባክን የነበረ ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ አስችሏል። በሚዛን አማን ከተማ ባለፈው ጥቅምት ወር ወደሥራ የገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስመልክቶ ኢዜአ ካነጋገራቸው ተገልጋዮች መካከል አቶ ኪዳኔ ኮይንስ እንዳሉት፥ አገልግሎቱ መንግሥት ለሕዝብ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ተግባራዊ ምላሽ የሰጠበት ነው። የማዕከሉ ሥራ መጀመሩ ከዚህ ቀደም አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም ሲገጥማቸው የነበረን እንግልት በማስቀረት ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከጥሩ መስተንግዶ ጋር ለማስፈጸም እያስቻላቸው በመሆኑ አገልግሎቱ እንዲጠናከር ጠይቀዋል። "ከመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጊዜና ጉልበት የቀነሰ ፈጣን አገልግሎት አግኝቺያለሁ" ሲሉ የተናገሩት ደግሞ ሌላዋ ተገልጋይ ወይዘሮ አመለወርቅ ኃይሉ ናቸው። "በቴክኖሎጂ ተደግፎ ያለውጣ ውረድና ቀጠሮ አገልግሎት የማግኘት ሥርዓት መዘርጋቱ ተጠቃሚ አድርጎናል፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ" ያሉት ተገልጋዩዋ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በሌሎች አካባቢዎችም መስፋፋት አለበት ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎትን በዝምድናና በእጅ መንሻ የመፈጸም ብልሹ አሠራርን ጭምር እንዳስቀረ የተናገሩት ደግሞ አቶ አዲሱ ገብረጊዮርጊስ የተባሉ ተገልጋይ ናቸው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመዲን አወል እንደገለጹት፣ ማዕከሉ ለአገልግሎት ክፍት ከሆነበት ጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ ከ4 ሺህ 800 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት ሰጥቷል። በማዕከሉ 35 አገልግሎቶች በዘጠኝ የክልልና የፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጡ ጠቅሰው ተግባሩን ለማጠናከር የዳታቤዝ እና መሰል የቴክኖሎጂ ሥራዎች ማስፋፊያ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። የመሶብ አገልግሎትን በክልሉ ለማስፋፋት በተቀመጠው ግብ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ 10 መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ግንባታ ሥራ መጀመሩንም አቶ አህመዲን ጠቁመዋል። በመደመር መንግሥት ለማሳካት ከተያዙ የአንድ ግቦች መካከል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሽ ሲሆን በዚህም በእያንዳንዱ ከተማ አንድ ማዕከል በመገንባት ብልሹ አሠራርን ለማስቀረት ትኩረት ተሰጥቷል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅማችንን አሳድጓል-ተማሪዎች
Dec 18, 2025 46
ጅግጅጋ፣ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅማቸውን እንደጨመረላቸው በጅግጅጋ ስልጠናውን የወሰዱ ተማሪዎች ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢንሼቲቭ በመላው ሀገሪቷ የተጀመረው የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በቴክኖሎጂ የበቃና ተወዳዳሪ የሰው ሀይልን ለማፍራት አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመው ሀገር አቀፍ ስልጠና ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግም አበርክቶው የላቀ ነው። ስልጠናውን የሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የመንግስት ሰራተኞች እና ወጣቶች በንቃት እየተከታተሉ መሆናቸውም ታውቋል። በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማም በርካታ ተማሪዎችና መምህራን ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን ፤ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የእድሉ ተጠቃሚዎች ስልጠናው የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን ማሳደጉን ተናግረዋል። በከተማው የካህ ቁጥር አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሙስጠፌ ሀሰን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በበይነ መረብ ወስዶ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ሰርተፊኬት ማግኘቱን ገልጿል። በስልጠናውም በራሱ ላይ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎቱን እንዳሳደገው ተናግሯል። የመጀመሪያዎቹን ሁለት ኮርሶች ከጨረስኩኝ በኋላ ሌሎች 20 ተማሪዎችን የፕሮግራሙን ጠቀሜታ በማስረዳት ማስመዝገቡን የተናገረው ተማሪ ሙስጠፌ፤ በተለይም ወጣቶች ይህንን ነጻ የትምህርት ዕድል መጠቀም እንዳለባቸው ተናግሯል። ተማሪ አስማ አሊ በበኩሏ፥ ከኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዳታ አናሊሲስ ሰርተፊኬት ማግኘቷን ገልጻለች። ይህንን ስልጠና ከመውሰዷ በፊት እና ዛሬ ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን አንስታ፤ ስልጠናው የተማሪዎችን እውቀትና ክህሎታቸውን እንደሚያሳድገው ተናግራለች። የኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ወጣቶች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ ያላቸውን እውቀት ለሀገራቸው ዲጂታል እድገት እንዲያበረክቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጻለች። ተማሪ አቡበከር መሀመድ ሀሰን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወሰደ መሆኑን ገልፆ፥ በተለይ ዳታ አናሊሲስ ላይ ትኩረት መስጠቱን ተናግሯል። ስልጠናው ከዲጂታል ዓለም ጋር መጓዝ እንደሚያስችል ተናግሮ፤ከራሱ አልፎ ለሌሎች ተማሪዎችም ድጋፍ መስጠት እንዲችል ማገዙን ገልጿል። የካህ ቁጥር አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ከድር ረሺድ በበኩላቸው፥ ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በ2017 በትምህርት ቤቱ መጀመሩን ተናግረው ይህንን ስልጠና ተማሪዎች እንዲወስዱ ትኩረት አድርገን ሰርተናል ብለዋል። ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት እድል ውስን እንደነበር ገልጸው፥በአሁኑ ወቅት እድሉ በቤታችሁ ድረስ በመምጣቱ ወጣቶች እድሉን መጠቀም አለባችሁ የሚል ምክር አስተላልፈዋል። በትምህርት ቤቱ በአንዴ 40 ተማሪ ማስተናገድ የሚችል አይሲቲ ላብ ክፍል መኖሩን ገልጸዉ፥ ተማሪዎች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማስፋት በቤት ሆነው በአለም ዙሪያ ያለውን ሥራ መስራት የሚያስችላቸውን አቅም እንደሚፈጥርላቸውም ገልጸዋል።
አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች ማስቀጠል የሚያስችለን አቅም ፈጥረናል
Dec 18, 2025 72
ሰመራ፣ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ):- አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ የተጀመሩትን ሥራዎች ማስቀጠል የሚያስችል አቅም መፍጠራቸውን የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት ስርዓት የዲጂታል ብልፅግና አተገባበር አውቶሜሽን ላይ ለአመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና በሰመራ መሰጠቱ ይታወሳል። በሰልጠናው ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አመራሮች ተሳትፈዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ አመራሮች እንዳሉት ስልጠናው በተቋማት የዲጂታል አሰራርን የተከተለ የተናበበና የተቀናጀ ሪፖርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ሰጥቷቸዋል። በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስትራተጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብይ አበባው እንዳሉት ለዲጀታል ስራ መሠረታዊ የሆኑ ክህሎቶችና የሰው ኃይልን ከማሟላት ጀምሮ የተከናወኑ ሰፋፊ ተግባራት አሉ።   በዚህ ስልጠናም የተጀመሩትን ስራዎች ለማጠናከር በግብአትነት የሚያገለግሉ ግንዛቤዎች ተገኝተዋል ብለዋል። በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስትራተጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አንተነህ አየለ በበኩላቸው ከክልል እሰከ ቀበሌ የሚያስተሳስር ዲጂታል ስርዓት እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።   በዚህ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር እና ልውውጥ ደግሞ ስራዎችን ቀልጣፋና ቀላል ከማድረግ ባሻገር ጊዜና ሃብት መቆጠብ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆኑን አስረድተዋል።   በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስትራቴጂክ ስራ አመራርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከበደ እንዳሉት በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ከማሟላት ጀምሮ፣ 8 ሶፍትዌሮችን በማበልፀግ ተግባራዊ ማድረግ እንደተቻለ አመልክተዋል።   ስልጠና ከሰጡ አመራሮች መካከል የኢትዮጵያ ስታስቲክሰ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ሜሮን ከፈለው (ዶ/ር) እንዳሉት የዲጂታል አሰራር ስራዎችን ለማቀላጠፍ በእጅጉ ያግዛል። የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች፣ በየክልሉ እና በየተቋማቱ በእየተሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀላፊ አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር በበኩላቸው እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የዲጂታል አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል። ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጊዜና ወጪን በመቆጠብ ባሻገር የኢትዮጵያ ኮደርሰ ስልጠና ላይ ያለውንም ክፍተት የሚሞላ መሆኑን ጠቅሰዋል።  
መሶብ የአንድ ማዕከል ፈጣንና የተሻለ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል - ተገልጋዮች
Dec 17, 2025 141
ሐረር፤ ታህሳስ 8/2018 (ኢዜአ)፡- መሶብ የአንድ ማዕከል ፈጣንና የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስቻላቸው መሆኑን ተገልጋዮች ገለጹ። በሀገር ደረጃ ከተነደፉ የተቋማት ማሻሻያ ፕሮግራሞች ውስጥ አንዱ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ነው። ከዚህ ውስጥም የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና የፌዴራል ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ወይዘሮ አልማዝ መሰለ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፍጥነትና በዘመናዊ አሰራር እንዲገለገሉ ያስቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል።   ከተጠቃሚዎች መካከል አቶ ሙሉጌታ ታዬ፤ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመገልገል መምጣታቸውን ጠቁመው የመጡበትን ጉዳይ በ5 ደቂቃ መጨረሳቸውን ተናግረዋል። አገልግሎቱም ቀደም ሲል ይታይ የነበረውን እንግልትና የተወሳሰበ የአሰራር ችግር የፈታ በመሆኑ መደሰታቸውን ጠቁመው፤ እንዲህ ያሉ የዘመኑ አሰራሮች በሌሎችም መጠናከር እንዳለባቸው ተናግረዋል።   ቀደም ሲል አገልግሎት ለማግኘት ሰልፍ መጠበቅና እንግልት የሚስተዋልበት አሰራር ይታይ ነበር ያሉት ደግሞ አቶ ከሊፍ መሀመድ ናቸው።   መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማህበረሰቡ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲያገኝ በማድረግ ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ ረገድ እያበረከተልን የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ደሊል ሙሳ በበኩላቸው፤ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ እንግልትን ያስቀረ መሆኑን ጠቁመው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አገልግሎት እያገኘን ነው ብለዋል።   የአገልግሎቱ ወደ ስራ መግባት ከዚህ በፊት የነበረን ውጣ ውረድና ያልተገባ ወጪን ያስቀረ ስለመሆኑ ጠቁመው መንግስትም ይህን አሰራር በመዘርጋቱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል። የሐረሪ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ አክራም መሀመድ እንደገለጹት፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አሰራርን መሰረት ያደረገ ነው ።   የማህበረሰቡን የአገልግሎት ጥያቄ በመመለስ ጥራትና ቅልጥፍናን በመጨመርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በማስቀረት የአገልግሎት እርካታን ማሳደግ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል። የሐረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ጆርዳን ይስሃቅ በበኩላቸው፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመጀመሪያው ዙር በሰባት ተቋማት ወደ 26 አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።   በሁለተኛው ዙር ደግሞ የመጀመሪያውን ጨምሮ 50 የሚደርሱ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ጠቁመው ማዕከሉ የተገልጋይ መረጃ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን እያስቻለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ስፖርት
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
Dec 18, 2025 57
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 9/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይካሄዳሉ። ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ መቻል ከድሬዳዋ ከተማ ይጫወታሉ። መቻል በሊጉ ባደረጋቸው 12 ጨዋታዎች ስምንት ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ተሸንፏል። ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 20 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሰባት ጎሎችን አስተናግዷል። ቡድኑ በ26 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ድሬዳዋ ከተማ በውድድር ዓመቱ ካከናወናቸው 12 ጨዋታዎች መካከል አራቱን ሲያሸንፍ ሰባት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይቷል። 12 ግቦችን ሲያስቆጥር 18 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ድሬዳዋ በ13 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ጨዋታው መቻል ተከታታይ ድሎችን ለማስመዝገብ፣ ድሬዳዋ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው። በሌላኛው መርሃ ግብር ሸገር ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በሊጉ 11 ጨዋታዎችን አድርጎ ስምንት ጊዜ ሲያሸንፍ ሶስት ጊዜ ተሸንፏል። በጨዋታዎቹ 18 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 10 ጎሎችን አስተናግዷል። አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሸገር ከተማ በ24 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቦሌ ክፍለ ከተማ በሊጉ ባካሄዳቸው 12 ጨዋታዎች 12 ጨዋታዎች አምስቱን ሲያሸንፍ ሁለት ሽንፈት አጋጥሞታል። በአምስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይቷል። 13 ግቦችን በጨዋታዎቹ ላይ ሲያስቆጥር 10 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ በ20 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ማንችስተር ሲቲ ለካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ
Dec 18, 2025 72
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን ቸርኪ በ32ኛው እና ሳቪኒዮ 67ኛው ደቂቃ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። በጨዋታው ማንችስተር ሲቲ በተጋጣሚው ላይ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል። የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ አብዱኮዲር ኩሳኖቭ በ16ኛው ደቂቃ ላይ በብሬንትፎርዱ ኬቨን ሻደ የሰራው ጥፋት በቢጫ ካርድ መታለፉ አጨቃጫቂ ነበር። ሻደ የመጨረሻ ሰው ሆኖ በተሰራው ጥፋት ኩሳኖቭ በቀይ ካርድ መውጣት ነበረበት የሚል ተቃውሞ ብሬንትፎርዶች ቢያሰሙም ውሳኔው ሳይቀለበስ ቀርቷል። በካራባኦ ዋንጫ በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት (ቫር) የሚተገበረው ከግማሽ ፍጻሜ አንስቶ ነው። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ሲቲ ለካራቦኦ ግማሽ ፍጻሜ ሲያልፍ ከእ.አ.አ 2021 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።   በሌላኛው መርሃ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፏል። ዮአን ዊሳ እና ሉዊስ ማይሊ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሳሳ ሉኪች ለፉልሃም ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። የወቅቱ የካራባኦ ዋንጫ አሸናፊ ኒውካስትል ዩናይትድ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ የግማሽ ፍጻሜ ድልድል ወጥቷል። ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከአርሰናል እና ክሪስታል ፓላስ አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ። አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ በዚህ ሳምንት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በመርሃ ግብር መደራረብ በመራዘሙ ምክንያት በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ይካሄዳል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ 
Dec 17, 2025 85
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ልደታ ክፍለ ከተማ አርባ ምንጭ ከተማን 4 ለ 2 አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄለን እሸቱ፣ ረድኤት ዳንኤል እና ሰብለወንጌል ወዳጆ በጨዋታ፣ ቃልኪዳን ጥላሁን በፍጹም ቅጣት ምት ለልደታ ክፍለ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል። መሰረት ማቴዎስ እና ፍሬህይወት በድሉ ለአርባ ምንጭ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ውጤቱን ተከትሎ ልደታ ክፍለ ከተማ በስምንት ነጥብ ደረጃውን 13ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል። በሊጉ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ በተመሳሳይ ስምንት ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ማለት ወራጅ ቀጠና ገብቷል። ዛሬ በተደረጉ የ13ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 2 ለ 0፣ ሲዳማ ቡና ይርጋ ጨፌ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የኮንሶዎች እርከን ሥራ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ጉልህ አስተዋጾ እያበረከተ ነው
Dec 18, 2025 44
ካራት ፤ ታህሳስ 9/2018(ኢዜአ)፡-በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የኮንሶዎች እርከን ሥራ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ጉልህ አስተዋጾ ያበረከተ ሀገር በቀል እውቀት መሆኑ ተገለጸ፡፡ የኮንሶ መልክአ ምድር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በ2003 ዓ.ም በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ የሚታወስ ነው። መልክአ ምድሩ በ23 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈና በውስጡ በርካታ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን የእርሻ እርከኖች፣ ጥብቅ ደኖች፣ ኩሬዎችና መንደሮች ይገኙበታል፡፡   የኮንሶ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ገንዘቤ ኮራ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበው የኮንሶዎች እርከን ሥራ ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ ያለ ሀገር በቀል አውቀት ነው። ባህላዊ የእርከን ሥራው የኮንሶ ማህበረሰብ የታታሪነት ምልክት መሆኑን ገልጸው፣ ማህበረሰቡ አስቸጋሪ መልክአ ምድርን ጭምር በማልማት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ያሳየበት እንደሆነም ተናግረዋል። የእርከን ሥራው ኮንሶዎች ትውልድን የተሻገረ ቅርስና ተፈጥሮን ለመጠበቅ የዘየዱት ሃገር በቀል እውቀት ሲሆን የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ የዝናብ ውሃን ወደመሬት በማስረግ ለምርትና ምርታማነት ማደግ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። እንደ ሃላፊዋ ገለጻ በአካባቢው ከአዝርዕት ሰብሎች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ ቦሎቄ እና ዳጉሳን እንዲሁም የጓሮ አትክልቶች በተለይ በመኸርና በበልግ ወቅቶች በስፋት ይመረታሉ። በጥምር ግብርና የሚተዳደሩት ኮንሶዎች ተፈጥሮን ጠብቀው በስፋት ለሚያከናውኑት የእንስሳት እርባታ ስራም ከሰብል ተረፈ ምርት በተጨማሪ የመኖ ዛፎችን እንደሚያለሙም ተናግረዋል።   የኮንሶ ዞን ህዝብ የባህል አባት ካላ ገዛኸኝ ወልዳዊት በበኩላቸው የኮንሶዎች ባህላዊ የእርከን ሥራ የህዝቡ የአኗኗር ዘይቤ መገለጫና የሀገር በቀል ዕውቀት ውጤት ነው ብለዋል። የጥንት ኮንሶዎች የስልጣኔ ምልክት የሆነው የእርከን ሥራ ከአካባቢው የአየር ጸባይ ጋር እንዴት ተስማምቶ መኖር እንደሚቻል ትውልድ የተማረበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የእርከን ሥራው አፈር እንዳይሸረሸር እንዲሁም ለምነትና እርጥበቱ ተጠብቆ እንዲቆይ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። የኮንሶ ማህበረሰብ ባህላዊ የእርከን ሥራ ከመኖሪያ መንደር ጀምሮ እስከ አርሻ ማሳ በጥንቃቄ የሚሠራ የህልውና መገለጫ ነው ያሉት ደግሞ አቶ ሮባ ለሚታ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ናቸው።   ያለን ትልቁ ሀብት መሬት ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው እርከን ሥራም መገለጫችን ነው ብለዋል። የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ መጠበቅ ካልተቻለ ትውልድ የማስቀጠል ጉዳይ አደጋ እንደሚገጥመው ገልጸው፣ "ከአባቶች የተረከብነውን ቅርስ ጠብቀን ለልጆቻችን እናስተላልፋለን" ብለዋል። የኮንሶ የመሬት አቀማመጥና የአየር ጸባይ ምቹ ባይሆንም አባቶች እርከን በመስራትና በባህላዊ ኩሬ ውሃ በማቆር ተፈጥሮን ተቋቁሞ መኖር የሚቻልበትን ዘዴ እንዳስተማራቸው ገልጸዋል፡፡ የኮንሶ ማህበረሰብ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ያለውን ጠቀሜታ ቀድሞ መገንዘቡን የገለጹት አቶ ሮባ፣ በዚህም የተፋሰስ ሥራ በማከናወን ለምርታማነት መረጋገጥ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። የኮንሶዎች ሀገር በቀል ዕውቀት ውጤት የሆነው የእርከን ሥራ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አካባቢዎችም በስፋት እየታየ ነው።    
በአማራ ክልል የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ እየተከናወነ ነው
Dec 17, 2025 148
‎ባህር ዳር ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት፤ የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል።   ‎በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በ9 ሺህ 206 ተፋሰሶች ላይ በ456 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ቀጥሏል ብለዋል። የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራው ‎እስከ መጪው መጋቢት ወር የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ የልማት ስራ ላይ ከ4 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች የሚሳተፉ መሆኑን አንስተው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎም መጠናከር አለበት ብለዋል። ‎በበጋው የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የማሳና የጋራ ላይ እርከን፣ የውሃ ማፋሰሻና መቀልበሻ ቦዮች እንዲሁም ከ6 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ የውሃ ማስረጊያ ስትራክቸሮች የሚከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።   ‎በክልሉ የልማት ስራው ከሚከናወንባቸው አካባቢዎች መካከል ‎የደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አራጋው ወንዴ እና በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ዙሪያ ነዋሪ አርሶ አደር የሱፍ ይመር፤ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ መሰረታዊ ጉዳይ አድርገን እየሰራን ነው ብለዋል። ‎በዚህ የልማት ስራ የእርሻ መሬትና የአፈር ለምነት እንዲሻሻልና ምርታማነት እንዲጨምር ከማድረግ ባለፈ በተፋሰሶቹ የእንስሳት መኖ ማግኘት እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል። ‎በክልሉ ባለፈው ዓመት በ8 ሺህ 400 ተፋሰሶች ላይ የበጋ ወራት የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ስራ መከናወኑ ታውቋል።
በክልሉ ለዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ሥራ ዝግጅት እየተደረገ ነው
Dec 17, 2025 82
ቦንጋ ፤ ታህሳስ 8/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዘንድሮ ከ272 ሺህ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ለሚከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ። በክልሉ የመሬትና የውሃ ሀብትን መጠበቅ፣ ማልማትና በላቀ ደረጃ አቀናጅቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ውብሸት ዘነበ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡ በየዓመቱ የሚከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ የአፈር ለምነትን ለመመለስና የውሃ ሀብትን ለማበልፀግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ምርትና ምርታማነት መጨመሩን ያነሱት አቶ ውብሸት፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ የለሙ አካባቢዎች ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደፈጠሩም ገልጸዋል። ዘንድሮም ልማቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። በክልሉ ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት በሚከናወነው የአፈርና ውሃ ልማትና ጥበቃ ሥራ ከ1 ሚሊዮን 305 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ መታቀዱንም ጠቁመዋል፡ የዘንድሮ የበጋ ወቅት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ በ1ሺህ 210 ተፋሰሶች በሚገኝ 272 ሺህ 250 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚከናወንም አቶ ውብሸት አስታውቀዋል። ለሥራው ውጤታማነት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፣ ለልማቱ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ማሟላት እንዲሁም የልማቱ ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍሎችን መለየትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት ምን አሉ?
Dec 17, 2025 188
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከማንሞሃን ሲንግ በኋላ ኢትዮጵያን የጎበኙ ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ህንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የልማት አጋርነት ማሳደግን ያለመ ነው። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በፓርላማ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በአድዋ ድል መታሰቢያም የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት በስፋት ዘግበውታል። ዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎቹ ሮይተርስ እና አሶሲዬትድ ፕሬስ ጉብኝቱን ከ"ጂኦ-ፖለቲካዊ" አንጻር ተመልክተውታል። በተለይ ህንድ በኢትዮጵያ ያላትን የአምስት ቢሊዮን ኢንቨስትመንት አጉልተዋል። አልጀዚራ ትኩረቱን ያደረገው ህንድ በ"ደቡባዊው ዓለም" (Global South) ላይ ያላትን ተጽዕኖ ለማሳደግ በምታደርገው ጥረት ላይ ነው። እንዲሁም የኢትዮጵያና የህንድ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳም በስፋት አንስቷል። ቢቢሲ እና ፍራንስ 24 ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለየት ያለ አቀባበል ትልቅ የዲፕሎማሲያዊ መቀራረብ ምልክት መሆኑን ዘግበውታል። የአፍሪካ ሚዲያዎች በበኩላቸው የናሬንድራ ሞዲን ጉብኝት "የአፍሪካ-ህንድ" ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ አድርገው ዘግበዋል። አፍሪካ ኒውስ እና ዘ ኢስት አፍሪካን ጉብኝቱ በአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መደረጉን በማንሳት፣ ህንድ ከአህጉሪቱ ጋር ያላትን ወታደራዊ፣ የጤና እና የቴክኖሎጂ ትብብር እንደሚያጠናክረውም ገልጸዋል። የደቡብ አፍሪካው ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የናይጄሪያ እና ሌሎች የአፍሪካ መገናኛ ብዙሃን ህንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ኢትዮጵያን እንደ መግቢያ በር (Anchor) መጠቀሟን እና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚኖረውን ተምሳሌትነት ዘግበዋል። እንደ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ (The Times of India) ፣ ኤንዲቲቪ (NDTV) እና ኤኤንአይ (ANI) ያሉ የህንድ መገናኛ ብዙሃን የሞዲን ጉብኝት ከፍተኛ ሽፋን ሰጥተውታል። የዘገባዎቹ ዋንኛ ትኩረት በኢትዮጵያ ፓርላማ ስላደረጉት ንግግር እና ስለተደረገላቸው ልዩ የክብር ሽልማት ነው። በሌላ በኩልም የዲጂታልና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተደረጉ ስምምነቶችን በዝርዝር አቅርበዋል። አጠቃላይ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ትኩረት ታሪክ፣ ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ የደቡብ ለደቡብ ትብብር ላይ ያጠነጠኑ ናቸው። የኢትዮጵያ እና ህንድ የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ መሸጋገሩንም በመገናኛ ብዙሃኑ በስፋት ተነስቷል። ኢትዮጵያ እና ህንድ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት እና ብሪክስን ጨምሮ በሌሎች የባለብዙወገን መድረኮች ላይ የደቡባዊውን ዓለም ድምፅ ለማሰማት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸው በዘገባዎቹ በስፋት ተንጸባርቋል።  
የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል
Dec 4, 2025 667
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2018(ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሚዲያ ሽልማት ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ተከናውኗል።   በዕውቅና መርሃ ገብሩ የኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ሚኒስትሮችና ተወካዮች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሽልማቱ ለአፍሪካ ጋዜጠኝነት፣ ብሮድካስት ሚዲያ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ዘገባዎች እውቅና የሰጠ ነው። በአፍሪካ ሚዲያ ምህዳርን በመቅረጽ ሚናቸውን የተወጡ ጋዜጠኞች ተሸልመዋል። ምርጥ የዜና ዘገባ፣ ምርጥ ቃለ መጠይቅ፣ ምርጥ ዶክመንተሪ፣ ምርጥ ወቅታዊ ፕሮግራም፣ ምርጥ አፍሪካ ተኮር የመዝናኛ ፕሮግራምና ምርጥ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን በመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ እና ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው።   አፍሪካ ተኮር ምርጥ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ምርጥ የወቅታዊ ጉዳይ የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ እና ምርጥ አጭር የማህበራዊ ሚዲያ ተንቀሳቃሽ ምስል የማህበራዊ ሚዲያ ሽልማት የተሰጠባቸው ዘርፎች ናቸው። ሁሉም እጩዎች 2000 ዶላር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በእያንዳንዱ ዘርፍ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች የስድስት ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝተዋል። የምርጦች ምርጥ የይዘት ፈጣሪዎች አሸናፊም "The Golden Alkebulan" የተሰኘ ልዩ በወርቅ የተለበጠ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በሽልማቱ ላይ ከ40 ሀገራት በላይ የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ከ800 በላይ ስራዎችን ማቅረባቸውን ተገልጿል። የአፍሪካ ሕብረት ብሮድካስቲንግ፣ የፓትሪስ ሉሙምባ ፋውንዴሽን፣ የክዋሜ ንክሩማህ ፋውንዴሽን፣ የምዋሊሙ ኒዬሬሬ ፋውንዴሽን፣ የኬኔት ካውንዳ ሌጋሲ ፋውንዴሽን፣ የሲሱሉ ፋውንዴሽን ለማኅበራዊ ፍትህ፣ የፒኤልኦ ሉሙምባ ፋውንዴሽንና የሩስያው አር ቲ ሚዲያ የሽልማቱ አጋር ናቸው።
ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው - የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች
Dec 1, 2025 550
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ ነው ሲሉየምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ገለጹ። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን ትርክት በመቀየር ትልቅ ሚና የሚወጣ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ መካሄዱ ይታወቃል። የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት አሸናፊዎች እና ተሳታፊ ጋዜጠኞች ዛሬ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በሴት ጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ ከሆኑት መካከል ዩጋንዳዊቷ ጋዜጠኛ አይባሬ ሲንደሬላ ኢትዮጵያ በዜጎቿ አስተዋጽኦ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቃለች። በበርካታ ሀገራት ዜጎች ከሚከፍሉት ታክስ ተጨባጭ ውጤቶችን እምብዛም ሲያዩ አይስተዋልም ያለችው ጋዜጠኛዋ ኢትዮጵያ በግልጽነትና በጠንካራ ራዕይ የህዝብን ሀብቶች አሻጋሪ ብሄራዊ ፕሮጀክት መቀየሯን ተናግራለች። የአፍሪካ መሪዎች ከሕዳሴ ግድብ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን ሊወስዱ ይገባል ብላለች። የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አዘጋጅ አሻ ሃሚሲ አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግሮች ያለ ምንም ጣልቃ ገብነት መፍታት እንዳለባቸው ገልጻለች። ሕዳሴ ግድብ ዜጎች ለሀገራቸው መስዋዕትነት እንደሚከፍሉ የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው ያለችው አሻ ይህም በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለ መተማመንና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ላይ መስራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላከት ነው ብላለች። ግድቡ አፍሪካውያን ለጋራ ራዕይ ከቆሙ ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየ እንደሆነም ተናግራለች። በኢጋድ ሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ካሸነፉት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ደቡብ ሱዳናዊው የፊልም ባለሙያ እና ተራኪ ጋብርኤል ጋትሉዋክ ዋል ኬት በበኩሉ ህዳሴ ግድብ አፍሪካ ያላትን አቅም በተግባር ያሳየ ነው ሲል ተናግሯል። ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የመሰለ ግዙፍ ፕሮጀክት ካሳካች ሌሎች ሀገራትም ይህን ፈለግ ተከትለው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይችላሉ ብሏል። አፍሪካውያን ሀገራቸውን በራሳቸው መገንባት እንደሚችሉ ማመን አለባቸው ያለው ኬት የራሳቸውን ዕጣ ፈንታ ሌሎች እንዲወስኑላቸው መፍቀድ የለባቸውም ሲልም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ለሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያን እና በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የከፈሉትን መስዋዕትነት አንስተዋል። ሕዳሴ ግድ የአፍሪካ የስኬት ተምሳሌት ፕሮጀክት እንደሆነ ገልጸው ከግድቡ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ይህም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክርና የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ራዕይ የሆነውን የበለጸገች እና የተሳሰረች አፍሪካን የመፍጠር ራዕይን እንደሚደግፍም ተናግረዋል። ግድቡ የአፍሪካን ትርክት የመቀየር ትልቅ ኃይል ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል አምባሳደሩ።
የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል
Nov 21, 2025 890
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 12/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ዓለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችና የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ላይ የዌብናር ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ወሳኔ ሰጪዎች፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የገንዘብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የልማት ዕቅድ ክፍል ኃላፊ ኦዬባንኬ አበጂሪን፤ የምንፈልጋትን አፍሪካ ዕውን ለማድረግ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። የአፍሪካ ሀገራት የ2030 ዘላቂ የልማት አጀንዳና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አፈፃጸም ሂደትን የሚከታተል የሪፖርት ሥርዓት መኖሩንም ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2017 የተጀመረው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት ክትትል ሥርዓትም የአህጉሪቷን ዘላቂና ቁልፍ የልማት ማዕቀፎች አፈፃጸም የሚገመገምበትን መድረክ በማመቻቸት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። እ.ኤ.አ የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርት መድረክም የአህጉሪቷ ልማት በሳይንስና ማስረጃ የተመሰረቱ የመፍትሔ አፈፃጸሞችን ያመላከተ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሪፖርቱም የአፍሪካ ዕድገት በጤና፣ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በውቅያኖስ ጥበቃና ዓለም አቀፍ ሽርክና ጋር በአፍሪካ ሀገራት እ.ኤ.አ የ2030 ዘላቂ የልማት ግብና የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ወሳኝ አካል መሆኑን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትም በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የትብብር ሥርዓትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የ2025 የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ሪፖርትም ወሳኝ የአፈፃጸም ግኝቶችን በማረም የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦችን በሚገባ ለመተግበር አቅም እንደሚፈጥር አስረድተዋል። በመድረኩም የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት ግቦችና አጀንዳዎች የአፈፃጸም ስኬት ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚችል ተግባቦት መፈጠሩን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካትም አዲስ ዓለም የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል። መድረኩም ብሔራዊና ቀጣናዊ የልማት ስኬት አፈፃጸም የአሰራር ስርዓቶችን በመፈተሽ ዕድሎችን በማስፋት የአህጉሪቷን ዘላቂ የልማት አጀንዳዎ ማሳካት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሐተታዎች
መልካምነት ይከፍላል..!!!
Dec 11, 2025 377
መልካምነት ይከፍላል...!!! በማስረሻ ሀብታሙ (ኢዜአ-ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) መልካም ስነ ምግባርና ባህሪ ከራስ ባለፈ ቤተሰብን ያኮራል፤ ከዚህ ከፍ ሲልም ለማህበረሰብ ግንባታና ለሀገር የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው። ሌብነትና ሙስናን ለመከላከልም እንዲሁ አስተዋጾ አለው። በመልካም ስነምግባር ታንጾ ያደገ ሰው በላቡና በወዙ ጥሮ ግሮ ያፈራውን እንጂ የሌሎች የሆነን ሀብትና ንብረት አይመኝም። ዛሬ የራሱ ያልሆነውን ንብረት በሀሰት ምሎና ተገዝቶ ለመውሰድና ለመክበር የሚጥር ሰው በበዛበት በዚህ ዘመን ላይ ወድቆ ያገኙትን ንብረት ለባለቤቱ ለመመለስ "ገንዘብ የጣለ" እያለ በአደባባይ ባለቤቱን የሚያፈላለግ ሰው ሲገጥም ግርምትን ከማጫር ባለፈ እንዲህ አይነት ሰውም አለ ወይ? ያስብላል።   ነገሩ የተከሰተው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ነው። በአካባቢው ባህልና እምነት የሰው ገንዘብም ሆነ ንብረት ያለአግባብ መውሰድ "ጎሜ" ወይም እንደ "ሀጥያት" ተደርጎ ይቆጠራል። በኮሻሌ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በዚህ ባህልና እምነት ውስጥ ያደጉ ቢሆንም በቤተሰባቸው በመልካም ስነ ምግባር ታንጸው ማደጋቸው አሁን ላላቸው ታማኝነትና ቅንነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል። አርሶ አደሩ ታማኝነታቸውን በተግባር ጭምር በማሳየታቸው ከመንግስት ጭምር እውቅና ተችሯቸዋል። ነገሩ እንዲህ ነው አንድ ቀን ገበያ ውለው ሲመለሱ በመንገዳቸው ላይ ተጠቅልሎ የታሰረ ነገር ይመለከታሉ። መሬት ወድቆ ያገኙት ነገር እስሩን ፈትው ሲያዩ በርከት ያለ የገንዘብ ኖት ነው። ለማመን እያቃታቸው ገንዘቡን መቁጠር ጀመሩ። በላስቲክ የተጠቀለለው ብር 30 ሺህ ነበር። የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ይዞ ወደ ቤት መግባት የህሊና እዳ መስሎ ስለታያቸው አማራጭ ያሉትን አደረጉ፡፡ የገንዘቡ ትክክለኛ ባለቤት ከተገኘ በሚል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" እያሉ በአደባባይ ጽምጻቸውን ከፍ አድርገው መጠየቅ ጀመሩ። የሰማቸው ሁሉ ግራ ስለተጋባ ቀረብ ብሎ ሊጠይቃቸው ይቅርና ጤነኛ ሰውም አድርጎ አላያቸውም። የገንዘቡ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ትክክለኛ ሰውም ባለመገኘቱ ልፋታቸው ድካም ብቻ ሆነ። የያዙትን 30 ሺህ ብር ይዘው ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተገደዱ። በአካባቢው የገበያ ቀን በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ነው። እናም የገንዘቡን ባለቤት ለማግኘት እስከ ሳምንት ድረስ መቆየት ግድ ሆኖባቸው። ባለቤቱ ይገኛል ወይስ አይገኝም በሚል ሀሳብ ሳምንቱን አሳለፉ። ቀጣይ የገበያ ቀን ሲደርስም ገንዘቡን እንጨት ላይ አስረው በማንጠልጠል "ገንዘብ የጠፋበት! ገንዘብ የጠፋበት" አያሉ በገበያ ስፍራ በመዘዋወር ዳግም የጠፋበትን ሰው ማፈላለግ ጀመሩ። ገንዘቡ የእኔ ነው፤ ጠፍቶብኛል እያለ የሚመጣ ሰው ቢበዛም ትክክለኛውን የገንዘብ መጠንና ምልክቱን የሚጠራ ሰው አለመኖሩ ግን ፍለጋቸውን አድካሚ አድርጎታል። የገንዘቡን ባለቤት አግኝተው እስኪያስረክቡ ድረስ ተስፋ አልቆረጡም፤ “ገንዘብ የጠፋበት፣ ገንዘብ የጠፋበት...” እያሉ ገበያውን ከዳር ዳር ዞሩ። የኋላ ኋላ ግን ድካማቸው በከንቱ አልቀረም። በስተመጨረሻ ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ከእነምልክቱ እና ቦታው የሚናገር አንድ ግለሰብ ተገኘ።   ከገንዘቡ ባለቤት ጋር ከተወያዩ በኋላ ገንዘቡ ወድቆ ወዳገኙበት ስፍራ ይዘው በመሄድ የያዙትን ገንዘብ መሬት ላይ ጥለው ራሱ ባለቤቱ ምሎ እንዲያነሳ ያደርጋሉ። በእዚህ ሁኔታ ወደቆ ያገኙትን ገንዘብ በታማኝነት ያስረከቡት አቶ ሴዳ ለዚህ መልካም ተግባራቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ እውቅና ተችሯቸዋል። የእሳቸው መልካም ተግባር መረጃ የደረሰው ኮሚሽኑም የአርሶ አደሩን አርአያነት ለሌላው ለማስተማር አፈላልጎ ያገኛቸዋል፡፡ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ሲያከብር በማጠቃለያው ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በተገኙበት የእውቅና ምስክር ወረቀትና የ15 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቶላቸዋል፡፡   የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አብደላ ከቤተሰብ ጀምሮ በትምህርት ቤቶች በዜጎች ስነ ምግባር ላይ አበክሮ መስራት እንዲህ ያሉ ዜጎችን በብዛት ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጹት። ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሲበራከቱ ደግሞ ሀገርና ህዝብን የሚጎዳውን ሙስና ለመከላከል ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል፡ እንደ አርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ የሚገነባው ከቤት ጀምሮ በሚሰራ ሥራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ኮሚሽኑ ትውልድን በስነ-ምግባር ለማነጽ የጀመረውን ስራ ለማጠናከር በሚሰራው ሥራ እንደ አርሶ አደሩ ያሉ ታማኞች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። በክልሉ የተቋቋመው የጸረ ሙስና ግብረ ኃይልም በጸረ ሙስና ትግሉ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡም ታማኝነትን ባህሉ ከማድረግ ባለፈ የጸረ ሙስና ትግሉን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም ነው ያሳሰቡት። የአርሶ አደር ሴዳ ጋርዜ መልካም ተግባርና ታማኝነትም ለብዙዎች ምሳሌ ይሆናል። በተለይ ያለፉበትን ለማግኘትና በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ሰዎች ከእሳቸው መልካም ተግባር ሊማሩ ይገባል። የሰው ሀብት ወስዶ ከመክበር ይልቅ በታማኝነት ከምናቆየው ንጹህ ህሊና ይበልጥ አትራፊ እንሆናለን። ለሰዎች መልካም መስራት ክብርና ዋጋ የሚያሰጥ መሆኑንም የእኚህ አርሶ አደሩ ተሞክሮ ያሳያልና እንደእሳቸው ለሰራነው መልካም ተግባር ዋጋ እንዲከፈለን ታማኝነትን የህይወታችን መርህ ማድረግ አለብን። መልካምነት ቢቆይም እንኳ በራሱ ይከፍላልና።  
ለቀጣናዊ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ልህቀት እውቅና የሚሰጠው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት
Nov 28, 2025 743
የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተጀመረው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አማካኝነት ነው። ሽልማቱ የኢጋድ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ እና ተቋማዊ አቅምን የማጠናከር ጥረቶች አካል ነው። በኢጋድ ቀጣና በጋዜጠኝነት የላቀ ስራ ላከናወኑ የሚዲያ ባለሙያዎች በሽልማቱ እውቅና ይሳጣቸዋል። ሽልማቱ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ እና ሌሎችም ተጓዳኝ መድረኮችን የሚሸፍን ነው። የሚዲያ ስራው በቀጣናው በተለይም የድርቅ አይበገሬነት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ልማት ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል። ዓመታዊው የኢጋድ ሽልማት የቀጣናዊ ተቋሙ አባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ በግላቸው የሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና የፎቶ ጋዜጠኞች ጨምሮ አጠቃላይ የሚዲያ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው። በተጨማሪም የቀጣናውን ጉዳይ የሚሸፍኑ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞችም ይሳተፉበታል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስራቸውን በእንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በኢጋድ አባል ሀገራት በሚገኙ ቋንቋዎች ያቀርባሉ። ከተለያዩ ሙያዎች የተወጣጡ የውሳኔ ሰጪ ወይም ገምጋሚ ቡድን ተቋቁሙ ስራዎቹን በመመዘን አሸናፊዎችን ይለያል።   የመጀመሪያው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2023 በጅቡቲ ነበር። “የድርቅ ተጽእኖዎችን መቋቋም የሚያስችል ትብብር መፍጠር” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። መሪ ሀሳቡ በድርቅ፣ አይበገሬ አቅም መገንባት፣ የውሃ አስተዳደር እና ቀጣናዊ ትብብር ያተኮረ ነው።   ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመንት፣ ጦማር (ብሎግ) እና የፎቶ ጋዜጠኝነት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። በመጀመሪያው ሽልማት ላይ ከቀጣናው 105 ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን 14 ባለሙያዎች በዘርፎቹ ተመርጠው ተሸልመዋል። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ተቋሙ ሚዲያን ለግንዛቤ መፍጠር እና ቀጣናዊ ትብብር እንደ መሳሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ በወቅቱ ገልጾ ነበር። በድርቅ እና በምግብ ዋስትና ላይ ያሉ የጋራ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚዲያ ሚና ወሳኝ እንደሆነም አመልክቷል። ሁለተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት የተካሄደው እ.አ.አ በ2024 በኬንያ ናይሮቢ ነው። “የተስፋ ትርክቶች፤ የቀጣናውን መጻኢ ጊዜ ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ሁሉን አቃፊ ማድረግ” የሽልማቱ መሪ ሀሳብ ነው። ሽልማቱ በሰላም፣ ደህንነት፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ መጻኢ ጊዜን መፍጠር፣ ቀጣናዊ ትብብር እና መረጋጋት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ ህትመት፣ ፎቶግራፍ፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የእድሜ ዘመን ተሻላሚ ከሽልማት ዘርፎቹ ውስጥ ናቸው። ለ2024ቱ ሽልማት 318 የሚዲያ ባለሙያዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን 18 የሚዲያ ባለሙያዎች በዘርፎቹ ሽልማት አግኝተዋል። ሁለተኛው ሽልማት ከመጀመሪያው በዘርፎች እና በተሳታፊዎች ብዛት መሻሻል የታየበት ነበር። ይህም ሚዲያ በቀጣናዊ ሰላም፣ ደህንነት እና ቀጣናዊ ትስስር ላይ ያላቸውን ሚና የሚያሳይ ነው። ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መጥቷል። ሽልማቱ ነገ ህዳር 20 እና 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከናወን ነው። ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ነው። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያና የአፍሪካ ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ባንክ (አፍሪኤግዚም ባንክ) ለፕሮግራሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቋል። የዚህ ዓመት ሽልማት በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና የሚሰጥ ነው። የሁለት ቀን ሁነቱ የአየር ንብረት ጠንካራ ዘገባዎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት እንዲሁም ቀጣናዊ ትብብር ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የ2025 የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በ10 ዘርፎች የሚከናወን ነው። የህትመት ጋዜጠኝነት፣ የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፣ የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፣ ዲጂታል ሚዲያ፣ ፎቶግራፈር፣ ሀገር በቀል ዘገባ፣ የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ/ የይዘት ቀራጭ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና የእድሜ ዘመን ሽልማት የሽልማት ዘርፎቹ ናቸው። 400 የሚሆኑ የኢጋድ አባል ሀገራት ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ማስገባታቸውን ጠቁመው፤ ከዚህ ውስጥ 94 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መሆናቸውን ኢጋድ አስታውቋል። ሽልማቱ በቀጣናው ገንቢ ሚና ያለው ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሚዲያ አዋርድ ማስተናገዷም ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬቶች ዕውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚዲያ ሽልማት ውድድሩ ላይ በርካታ የኢጋድ አባል ሀገራት የመገናኛ ብዙሃን ሙያተኞች እንደሚሳተፉም ገልጿል። የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ በአዲስ አበባ መካሄዱም በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን ገጽታ ለመገንባት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው። የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቁ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዘገባዎች እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ብዝሃ ድምጾች እንዲሰሙ በማድረግ፣ ለዴሞክራሲ እሴቶች መጎልበት እና ዘላቂ ልማት የበኩሉን ሚና ይወጣል።  
 የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አዘጋጅነት
Nov 14, 2025 940
ለረጅም አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ምሰሶ ሆና ቆማለች። በሀገራት መካከል የግንኙነት ድልድል እና የአንድነት መልዕክተኛ መሆን ችለላች። ከምስረታው አንስቶ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት። የአፍሪካ መዲና በመባል የምትጠራው አዲስ አበባ በርካታ ድርድሮች፣ የሰላም ውይይቶች እና አህጉራዊ ውሳኔዎች የተላለፈባቸው ሁነቶች ተስተናግደውባታል። ውሳኔዎቹ የአፍሪካ ቀጣና ፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ ናቸው። የኢትዮጵያ የመሪነት ሚና ከዲፕሎማሲውም የተሻገረ ነው። ሀገሪቷ የገባችውን ቃል ከተግባር ጋር በማጣጣም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚለኩ ውጤቶችን እያስመዘገብች ትገኛለች። የተራቆቱ መሬቶች ወደ ነባር ይዞታቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የታዳሽ ኃይል አማራጮቿን በማስፋት ለአረንጓዴ ልማት እና እድገት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታለች። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው አረንጓዴ አሻራ ሚሊዮኖችን ከዳር እስከ ዳር በማነቃነቅ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ከችግር ተናገሪነት ወደ ተጨባጭ መፍትሄ አመንጪነት ሽግግር በማድረግ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ምሳሌ የሚሆን ተግባር አከናውናለች። ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ደረጃ ያላትን ተአማኒነት እና ተቀባይነት እንዲያድግ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በከባቢ አየር ጥበቃ ቁርጠኝነት እና አቅምን በማጣመር ለውጥ አምጥታለች። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገኘችው እምነት እና የመሪነት ሚና ውጤት የሚያሳይ ተጨማሪ ሃላፊነት ከሰሞኑ ከብራዚል የደን ከተማ ቤለም ተሰምቷል። 30ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 30) በቤለም እየተካሄደ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በአንገብጋቢ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች እና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ እየመከሩ ይገኛል። በጉባኤው ላይ እየተሳተፈች የምትገኘው ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 የሚካሄደውን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የገቡትን ቃል በተግባር ለመቀየር ቁርጠኝነት ባነሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር መፈጸሟን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳላት ገልጸው የዳበረ የትራንስፖርት አገልግሎት ከብዙ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫነት ጋር ሲደመር የዝግጁነት አቅሟን በላቀ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አመልክተዋል። ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ልምዱም አቅሙም እንዳላት ገልጸው፣ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ናይጄሪያም ጉባኤውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርባ ነበር። የኢትዮጵያ የኮፕ 32 የማስተናገድ ፍላጎት ከአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። የወቅቱ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀመንበር የሆነችው ታንዛንያ የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጻለች። የአፍሪካውያን ውሳኔ ከቃል ባሻገር ኢትዮጵያ የአህጉሪቷን የአየር ንብረት የቅድሚያ ትኩረቶች የማራመድ እና የመወከል አቅም አላት ብለው ይሁንታ የሰጡበት ነው። ይህ ጠንካራ እምነት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ሁሉን አፍሪካውያን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እና አህጉሪቷን ያማከለ ውሳኔዎች በዓለም መድረክ እንዲተላለፍ እያደረገች ያለውን ጥረት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግም ነው። በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ አፍሪካውያን ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስናግድ ድጋፍ በመስጠታቸው አመስግነው፤ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ አበክራ እንደምትሰራ ተናግረዋል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ኢትዮጵያ መሰል አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን በብቃት ማስተናገድ እንደምትችል የሚያመላክት ነው ብለዋል። አዲስ አበባ እንግዶቿን በሚመጥን ደረጃ ጉባዔውን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደሩ፥ ለኢትዮጵያ ጥያቄ ሌሎች ሀገራትም ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ የኮፕ 32ን ለማስተናገድ መመረጧ በድንገት የመጣ ጉዳይ አይደለም። በተግባር የተረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የመሪነት ሚና፣ አረንጓዴ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እያከናወነች ያለቻቸው ስራዎች እና የፖለቲካ ቁርጠኝነቷ፣ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ድምጽ እና ምልክት መሆኗ ከቃል ባለፈ በተጨበጠ ስራ መታየቱ፣ ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የማስተናገድ ውጤታማነቷ እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነቷ ድምር ውጤቶች እንጂ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታስተናግድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠን ክብር ይሰማናል ብለዋል። አፍሪካ በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በብራዚል በአንድ ድምጽ ተናግራለች፤ ዓለምም አዳምጧል ብለዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2027 በአዲስ አበባ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ለደገፉ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች ምሥጋና አቅርበዋል። በሰው ልጆች ኑሮ በጣም አንገብጋቢ ከሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ለመቅረፍ እንዲቻል የጋራ ጥረቶችን ለመምራት ዕድሉን ስላገኘንም አመሥጋኞች ነን ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህን ትልቅ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ላይ ያላትን ቁርጠኛ ርምጃ፣ አመራር ብሎም ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ የዳበረ ዐቅም ያሳያል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በምታስተናግደው የኮፕ 32 መድረክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ ርምጃን የሚያበረታታ ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት ለማምጣት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማዘጋጀቷ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ መድረኮች ኢትዮጵያ ያላትን የአየር ንብረት የመሪነት ሚና የበለጠ ያሳድጋል። የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራ የሚያስፈልጋትን ፋይናንስ ለማግኘት እና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማጠናከር መልካም አጋጣሚን ይፈጥርላታል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የጉባኤው ተሳታፊዎች የቱሪዝም መስህቧቿንና መዳረሻዎቿን ሲጎበኙ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ ያድጋል ይህም ኢኮኖሚውን በመደገፍ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በአፍሪካ ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ተጽእኖ ፈጣሪን ጉባኤው በማስተናገድ በኩል ጉልህ አበርክቶ የሚኖረው ሲሆን ዘላቂ የሆነ የከባቢ አየር ትብብርን ለመፍጠር ያስችላል። ለኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ማስተናገድ ከክብር ባሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ሰው ለሚኖርባት ምድር ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር የምታሳይበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ጠንካራ የከባቢ አየር ጥበቃ ኢኒሼቲቮች፣ የማይበገር ዲፕሎማሲ እና የነገ አረንጓዴ እድገት ህልሟ ከጉባኤው ጋር ተዳምረው የተፈጥሮ ጠበቃነቷን እና የዓለም ትብብር ተምሳሌትና መሪነቷን የበለጠ ያሳድጉታል። ኢትዮጵያ እና ህዝቧቿ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአየር ንብረት የረጅም ጊዜ ፈተናዎች እንዲፈቱ ከአፍሪካ ብሎም ከመላው ዓለም ጋር ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እና ቁርጠኛ ናት።
" መሬት እና ፍትህ" - የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የእድገት ጉዞ
Nov 11, 2025 963
መሬት በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው። መሬት ከአፍሪካውያን የአኗኗር ዘይቤ፣ ማንነት፣ ባህል እና ማህበራዊ መስተጋብር ጋር የተቆራኘ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከቅኝ ግዛት ዘመን በፊት የአፍሪካ በርካታ ማህበረሰቦች መሬት በልማዳዊ እና ባህላዊ ስርዓት ያስተዳድሩ ነበር። የቤተሰብ ጎሳዎች ወይም ማህበረሰቦች መሬት የመጠቀም፣ የማስተዳደር እና ባህላዊ መንገዶች በሰጣቸው መብት ሲያስተላልፉ ቆይተዋል። በእንደዚህ አይነት ስርዓት ውስጥ መሬት ከሀብት ባለፈ ከማህበራዊ ግንኙነቶች፣ መንፈሳዊ መስተጋብሮች እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በጋራ የማስተዳደር ኃላፊነት ጋር ትስስር አለው።   በቅኝ ግዛት ዘመን የአውሮፓ ኃይሎች በስምምነቶች፣ በአዋጆች እና ኃይል በመጠቀም መሬት የቁጥጥር፣ የብዝበዛ እና ሀብትን የመንጠቂያ መሳሪያ አድርገውታል። መሬት ፖሊሲ ኃይልን ማጠናከሪያ እና የኢኮኖሚ ብዝበዛ መንገድ ሆኗል። አፍሪካውያን በልማዳዊ እና ባህላዊ መንገዶች የነበራቸውን የመሬት መብቶች በመንጠቅ ከአፍሪካ ውጪ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የሰፈራ ፕሮግራም ማካሄጃ እንዲሆኑ በር ከፍቷል። በዚህም ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀብት ሲበዘበዝ ቆይቷል። ሀገር በቀል ማህበረሰቦች ከመሬታቸው የመፈናቀል እና የመገለል ሰለባ ሆነዋል። በቅኝ ገዢዎች የወጡ የመሬት ፖሊሲዎች፣ የመሬት ምዝገባ እና የመሬት አስተዳደር ስርዓት የአፍሪካ መሬት ተጠቃሚዎችን መብት የነፈገ ነበር። የቅኝ ግዛት የቀረጸው የመሬት አስተዳደር ስርዓት አፍሪካውያንን ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትን ያሳጣ ነው።   የአፍሪካ ሀገራት ከነጻነታቸው በኋላ እኩልነት ያልተረጋገጠባቸውን የመሬት መብቶች እና ስርዓቶች ወርሰዋል። ሀገራት የመሬት ፖሊሲዎቹን አሁን ያሉ የልማት ግቦችን፣ የፍትህ ፍላጎቶች እና ወቅታዊ የአስተዳደር ማዕቀፎች ባማከለ ሁኔታ የመቀየር ስራ በማከናወን ላይ ናቸው። በቅኝ ግዛት ዘመን የመሬት መብታቸውን ላጡ ዜጎች በተለይም ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመለሰላቸው ይገኛል። ይሁንና የቅኝ ግዛት የመሬት ቅድሚያ መጥፎ፣ በሀገራት ብሄራዊ ህግ ውስጥ ያሉ የተደባለቁ የህግ ማዕቀፎች (ለምሳሌ ልማዳዊ ህጎች ከመደበኛ ህጎች ጋር መደባለቅ) እና የተቋማት የአስተዳደር ስርዓት አለመናከር በአፍሪካ ፍትሃዊ እና እኩልነት የመሬት ስርዓት የማስፈን ጉዞ ላይ ጋሬጣ ሆኗል። ዛሬ ላይ አፍሪካ አጀንዳ 2063 እና ዘላቂ ልማት ግቦች እየተገበረች ትገኛለች። የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች አንኳር ምሰሶ ተደርገው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሬት ነው። እኩል የመሬት መብት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ የአጀንዳ 2063 ሰነድ ያስረዳል። የአፍሪካ ህብረት ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በመተባበር በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ማዕቀፎች እና የህግ አሰራሮችን በመቅረጽ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የመሬት ህጎችን የተሰናነሰኑ እንዲሆኑና የተቋማት አቅምን እንዲያጠናክሩ ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው።   “የመሬት አስተዳደር፣ ፍትህ እና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ለዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ ከህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኮንፍረንሱን ያዘጋጁት የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) በጋራ በመተባበር ነው። ከአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ እና የአካባቢ ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ እና ለነባራዊ እውነታዎች ምላሽ የሚሰጡ የመሬት ፖሊሲ ምርጥ ተሞክሮዎች በኮንፍረንሱ ላይ እየቀረቡ ይገኛል። ህዳር 1 በነበረው የጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸኃፊ ክላቨር ጋቴቴ በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ስብሰባ በወሳኝ ወቅት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።   አፍሪካውያን ያላቸውን ሰፊ የመሬት ሀብት በቅኝ ግዛት አሰራሮች ሳቢያ በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው በአፍሪካ መሬት ዛሬም የግጭትና የኢ-ፍትሐዊነት መገለጫ ሆኗል ብለዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር በሴቶች፣ በወጣቶችና በዝቅተኛ አርሶ አደሮች ዘንድ ኢ-ፍትሐዊነትን በማንገስ ሰፊ የኢኮኖሚ ልዩነት መፍጠሩን ገልጸዋል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ስብሰባ ከአፍሪካ ሕብረት 2025 "የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን" መሪ ሀሳብ ጋር የተጣጣመ መሆኑን አንስተው፤ ዓላማው አፍሪካውያን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ብለዋል። የአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የካሳ ጥያቄ ያለፈውን ማስመለስ ሳይሆን አሁን ባለው የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል። አፍሪካ 65 በመቶ ያልታረሰ መሬት፣ ከዓለም ኢንዱስትሪ ሁለት በመቶ ብቻ ድርሻ ያላት፣ ለአየር ንብረት ለውጭ ተፅዕኖ ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች የሆነ አህጉር መሆኗን አንስተዋል። በአፍሪካ የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን በማዘመን ፍትሐዊነትን ማስፈን ጊዜው አሁን ነው ያሉት ዋና ጸኃፊው፣ ሴቶችን ወጣቶችና ዝቅተኛ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዜጎችና ዳያስፖራ ዳይሬክተር አምር አልጆዋሊ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ የአህጉሪቱን መፃኢ ጊዜ ለመቀየር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።   በአፍሪካና ዘርዓ አፍሪካውያን ላይ የደረሰው በደል ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት ገልጸው፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ለሕብረቱ መሪ ሀሳብ ትግበራ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመሬት አስተዳደር የፍትሐዊነት ምልክት መሆኑን በማንሳት፤ የመሬት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መስፈን አለበት ብለዋል። የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 በማሳካት አካታች ብልፅግናና ሰላምን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። ሕብረቱ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ ግልፅ አሰራር እንዲሰፍን ለአባል ሀገራት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል። ስድስተኛው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። ውጤታማ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመሬት አስተዳደር ስርዓት መገንባት፣ ተቋማዊ አቅምን መፍጠር እና የቁጥጥርና ክትትልን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የቅኝ ግዛት አሻራዎች እና ወቅታዊ የኢ-ፍትሃዊነት ጉዳዮች በመሬት ባለቤትነት እና አስተዳደር ያሳደሯቸውን ተጽእኖዎች ለመፍታት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ይገልጻሉ። በመሬት ፖሊሲ ቀረጻ፣ ትግበራ እና ቁጥጥር አቅምን መገንባት፣ የእውቀት ሽግግርን ማሳደግ እና የፖሊሲ ቁርጠኝነትን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ምላሽ የመቀየር ጉዳይም አጽንዖት የሚሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ህብረቱ ገልጿል።   በአህጉራዊ ኮንፍረንሱ ላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት፣ የህብረቱ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የፖሊሲ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ትውልደ አፍሪካውያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል። የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኮንፍረንስ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሁነት ነው። የመሬት ፖሊሲ ጉባኤው አፍሪካውያን ፍትሃዊ እና ዘላቂ የመሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነታቸውን እያሳዩበት የሚገኝ መድረክ ነው። ጉባኤው አፍሪካውያን ከባለፈው ታሪክ በመማር ፖሊሲ፣ ጥናት እና የማህበረሰብ ድምጾችን በማቀናጀት ረገድ ያለው ፋይዳ ወሳኝ ነው። ጉባኤው የመሬት ፍትህን የማስፈን፣ አይበገሬነትን የመገንባት እና ለሁሉም አፍሪካውያን የጋራ ብልጽግና የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ በመደገፍ ረገድ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ትንታኔዎች
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ 
Dec 8, 2025 498
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።  
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3007
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ  7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 2947
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 3846
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 2383
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 1530
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 7348
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 5834
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 58424
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 52970
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 33642
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 31170
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 26891
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 25674
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 25235
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 25188
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 58424
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 52970
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 33642
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 31170
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ እና የህንድ ዘመን አይሽሬ እና ድንበር  ተሻጋሪ ወዳጅነት 
Dec 16, 2025 234
በሙሴ መለስ (ኢዜአ) ኢትዮጵያ እና ህንድ ረጅም ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አላቸው። በዚህም የስልጣኔ እሴቶችን ይጋራሉ። ሁለቱ ሀገራት የንግድ ትስስር ከፈጠሩ ከ2000 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠሩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እና ህንድ ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መሰረት የሀገራቱ ታሪካዊ ወዳሽነት እንደሆነም ይወሳል። ኢትዮጵያ እና ህንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1948 ነው። እ.አ.አ በ1950 ሳርዳት ሳንት ሲንግ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህንድ አምባሳደር በመሆን ተሹመዋል። በወቅቱ ኢትዮጵያ እና ህንድ በየሀገራቱ ኤምባሲ በመክፈት የዲፕሎማሲ ትብብሩን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ገልጸዋል። ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እ.አ.አ በ1956 እና በ1958 በህንድ ያደረጓቸው ጉብኝቶች ከኢትዮጵያ መሪዎች ጉብኝቶች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። እ.አ.አ 1960 ዎቹ ማብቂያ እና 1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የህንድ ፕሬዝዳንቶች የነበሩት ሳርቬፓሊ ራድሃክሪሽናን እና ዛኪር ሁሴን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝቶችን አድርገዋል። እ.አ.አ በ2011 ከአንድ ዓመት በፊት ህይታቸው ያለፈው የቀድሞው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ በኢትዮጵያ ያደረጉት የስራ ጉብኝትም ተጠቃሽ ነው። የቀድሞው የህንድ ፕሬዝዳንት ራም ናት ኮቪንድ እ.አ.አ በ2017 የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ በጉብኝታቸው ህንድ እና ኢትዮጵያ በንግድ፣ ኮሙኒኬሽን እና የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር የሚያስችሉ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። ደቡብ አፍሪካ እ.አ.አ በ2023 ባዘጋጀችው 15ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከነበራቸው ተሳትፎ ጎን ለጎን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። የሀገራቱ መሪዎች በወቅቱ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ የወጣቶች ክህሎት ማጎልበት እና በሕዝብ ለሕዝብ ልውውጥ ዙሪያ ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ተወያይተዋል። በወቅቱ ህንድ ባዘጋጀችው የሁለተኛው “Voice of Global South Summit” በተሰኘው ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተሳትፎ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2016 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንደራ ሞዲ በህንድ አጠቃላይ ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈውም ነበር። የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንደራ ሞዲም የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ን የደስታ መግለጫ መልዕክት በመቀበል በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸው ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት እንደሚያድግ መግለጻቸውም ይታወሳል። ህንድ እና ኢትዮጵያ በአፍሪካና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላቸውን አጋርነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል። በዚህም ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ትብብር ከፍተኛ ትኩረት እንደምትሰጥም ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ያስታወቁት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 20ኛው የቡድን 20 አባላት ሀገራት ጉባኤ ከነበራቸው ተሳትፎ ጎን ለጎን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ትርጉም ያለው እና ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። ህንድ የቡድን 20 አባል ሀገር መሆኗ የሀገራቱን የባለብዙ ወገን ትብብር የበለጠ የሚያጠናክር ነው። ከእ.አ.አ 2021 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ሀገራቱ የሁለትዮሽ እና የባለዙወገን ትብብራቸውን የሚያጠናክሩ ተከታታይ ውይይቶችን አድርገዋል። በወቅቱ የህንድ የትምህርት፣ ንግድ፣ ልማት፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ያደረጓቸው ጉብኝቶች የሀገራቱ ግንኙነት የበለጠ እየጠነከረ መምጣቱን የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ድጋፍ ያደረገች ሲሆን በብዝሃ ወገን ማዕቀፉ ሁለቱ ሀገራት በትብብር እየሰሩም ይገኛሉ። ኢትዮጵያ እና ህንድ በተለያዩ ጊዜያት በአየር ትራንስፖርት፣ ኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት፣ መከላከያ፣ ተደራራቢ ታክስን የማስቀረት፣ ንግድ፣ ኮሙኒኬሽን ሳይንስ፣ባህል፣ ትምህርት እና የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ማቋቋምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መስራት የሚያስችሏቸው የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። እ.አ.አ ፌብሩዋሪ 2025 ኢትዮጵያ እና ህንድ በመከላከያና ደህንነት ዘርፍ የተፈራረሙት የሁለትዮሽ ስምምነት ቁልፍ የሚባል ነው። እ.አ.አ በ2023/24 በወጣ መረጃ የኢትዮጵያ እና ህንድ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ ምጣኔ 271 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ኢትዮጵያ አተር፣ ቅመማ ቅመሞች፣ የቆዳ ውጤቶች እና የከበሩ ድንጋዮችን ወደ ህንድ ትልካለች። ከህንድ ደግሞ ማሽነሪዎች፣ የመድኃኒትት ምርቶች እና የብረታ ብረት ውጤቶችን በዋናነት ታስገባለች። ህንድ የኢትዮጵያ ዋንኛ የኢንቨስትመንት አጋር ከሚባሉ ሀገራት መካከል ትጠቀሳለች። ከ500 በላይ የህንድ ኩባንያዎች በጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና አገልግሎት ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ። ህንድ መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ አቅርቦት ታደርጋለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፣ ጤና እና መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከሁለቱ ሀገራት አበይት የትብብር መስኮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ሞዲ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከማንሞሃን ሲንግ በኋላ ኢትዮጵያን የጎበኙ ሁለተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ህንድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የልማት አጋርነት ማሳደግን ያለመ ነው። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ከሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ የጉብኝታቸው መርሃ ግብር ያሳያል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶች እና የጉብኝት ልውውጦች የኢትዮጵያ እና የህንድን ግንኙነት የበለጠ የሚያጸኑ ናቸው። ኢትዮጵያ እና ህንድ በታዳሽ ኃይል፣ ፋርማሲዩቲካል፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና ግብርና ማቀነባበሪያን ጨምሮ በአዳዲስ መስኮች ትብብራቸውን የማጠናከር ጽኑ ፍላጎት አላቸው። የሁለቱ ሀገራት ትብብር ከእርስ በእርስ ግንኙነት ባለፈ የአፍሪካ እና ህንድ እንዲሁም የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። ከ2000 ዓመት በፊት የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት ወደ ጠንካራ እና ጽኑ ትብብር ተቀይሯል። በማይናወጥ መሰረት ላይም ቆሟል። የበለጠ ጥልቀቱ እየጨመረ የመጣው የሀገራቱ ግንኙነት በጋራ ብልጽግና፣ ስትራቴጂካዊ ትስስር፣ ዘላቂ ልማት እና የሀገራቱን ዜጎች ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ አጠናክሮ ለመቀጠል የጋራ ቁርጠኝነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።  
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ
Dec 3, 2025 826
በአረንጓዴ ልምላሜ ያጌጠው - የቤንቾች ቀዬ (በቀደሰ ተክሌ) -ከሚዛን ቅርንጫፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የቤንች ምድር የሰጡትን የሚያበቅል ክረምት ከበጋ የማይጠወልግ ልምላሜን የታደለ ክልል ነው። በቤንች ሸኮ ዞን ባሉ የተለያዩ ወረዳዎች ደን የሚመስልና በመኖሪያ መንደሮች የሚታየው አብዛኛው አረንጓዴ ስፍራ ለምግብነት የሚያገለግሉ ፍራፍሬዎች፣ ቅጠሎችና ስሮችን የያዘ ነው። የቤንቾች ቤት ዙሪያው በአረንጓዴ ተፈጥሮ ያጌጠ ነው። የቤታቸው ሞገስ፤ የምግብ ዋስትናቸውም ጭምር ነው። ከዚህ ከፍ ሲል ደግሞ ቤንቾች ነፋሻማ አየር እየማጉ የመኖር ልምድን ያጎናጸፋቸው ይኸው አፈር ቆፍረው ዘር ተክለው ያበቀሉትና የተንከባከቡት አረንጓዴ ሀብት ነው። ከአንድ አርሶ አደር ማሳ እንሰት፣ ሙዝ፣ ጎደሬ፣ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ማየት የተለመደ ነው።   እግር ጥሎት ወደ ቀዬያቸው ያመራ እንግዳ ከፍራፍሬዎቹ የደረሰ ካለ ተቆርጦ ይሰጠዋል። በተጨማሪም ከብቶች፣ በጎችና ዶሮዎች የገቢ ምንጮቻቸው ናቸው። ወደ ቤታቸው ዘልቆ የገባ ሰው "ኪዥ" የተሰኘና የቤንች እናቶች ከወተት የሚያዘጋጁትን ''ጎደሬ'' ተብሎ ከሚጠራ የስራ ስር ምግብ ጋር ያጣጥማል። ቤንቾች በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እንዲሁም ሌሎች የሰብል ዓይነቶችን ያለማሉ። ማር፣ ቡና፣ ኮረሪማ እና ሌሎች የተፈጥሮ ቅመማ ቅመሞችም ቤንቾች ከገበያ ገዝተው የሚያመጡት ሳይሆን ከማሳቸው የሚያፈሩት ነው። የተቀናጀ እርሻን ባህል ያደረጉት ብርቱ የቤንች አርሶ አደሮች ወደ ገበያ አውጥተው የሚሸጡት እንጂ የሚገዙት የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። የፋብሪካ ውጤቶችን ለመግዛትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ከጓዳቸው ሞልቶ የተረፈውን ወደ ገበያ አውጥተው በመሸጥ ገበያን ያረጋጋሉ። በጠንካራ የእርሻ ባህላቸውም ምክንያት ልጆቻቸው የበሰለ ምግብን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፍራፍሬዎችንም ከጓሮና ከጫካ ቆርጠው ስለሚመገቡ ረሀብን አያውቁም።   የቤንቾች ቤት ዙሪያ ውብና ጽዱ ነው። ለዚህ ደግሞ ሴቶቹ የቤታቸውን ግድግዳ በተፈጥሮ ቀለም ከማስዋብ ጀምሮ ይጠበቡበታል። በቤንቾች ዘንድ የአንድ አርሶ አደር ጉብዝና የሚለካው በቤቱ ነው። ይህም የቤቱ ዙሪያ ያለው ውበትና የቤቱ ጥንካሬ ብቻም ሳይሆን ገላጣ መሆን አለመሆኑም ጭምር ከግምት ውስጥ ይገባል። አባዎራው በማሳው ላይ የሰብል ስራውን ያከናውናል። ልጆችና እማውራዋ ደግሞ ይኮተኩታሉ ያርማሉ። ከዚህም በተጨማሪ የቤንች እናት ጎደሬና ሌሎች የጓሮ አትክልቶችን የማልማት ኃላፊነት አለባት። የቤታቸው ዙሪያና ቀዬው በሙሉ በአረንጓዴ ልምላሜ አጊጦ የሚታይበት ምስጢሩ ይሄው ነው። ከርቀት ደን መስሎ የሚታየው አረንጓዴው ቀዬአቸው የገቢ ምንጭም በመሆኑ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ነውም ማለት ይቻላል። የሌማት ትሩፋት እሳቤ ቀድሞ የገባቸው ቤንቾች ማር አይገዙም፤ ለእንቁላል ሸመታም ገበያ አይወጡም። ወተት ቢያምራቸው በትኩሱ፤ ከዛም አለፍ ሲል በባህላዊ መንገድ እርሾ ጨምረው የሚያዘጋጁት "ኪዥ" የተሰኘ የወተት ውጤትን እንደ አይብም እንደ እርጎም አደርገው ይጠቀሙታል። የትኛውንም መልክዓ ምድር በሚስማማው የሰብል ዓይነት መሸፈን ያውቁበታል። መሬቱ ረግረጋማ ከሆነ ለጎደሬ፤ ዳገታማ ሆኖ ለማረስ የሚያስቸግር ከሆነ ደግሞ ለሙዝ ልማት ያውሉታል።   የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ሥራ የሚሠራው በጓሮ ነው። ይህም ሁሉን ከአንድ ጓሮ ለማግኘት በመጣር የሚመጣ ነው። ይህም ካልሆነ ደግሞ አስተማማኝና ቋሚ ምርት ማሳ ላይ አልያም ጎተራው ላይ ማኖር ያስፈልጋል። እንደ ቤንቾች በቤተሰብ ደረጃ ምግብን በራስ አቅም ለመቻል የሚደረገው ጥረት እንደሀገር ሲጠናከር ለውጡ ቀጣይነት ባለው መልኩ ይፋጠናን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አብዛኛው አርሶ አደር ነው። ይሁን እንጂ ጾሙን የሚያድር ሰፊ መሬት እንዳለ መረጃዎች ያመለከታሉ። አንድም መሬት ጾም እንዳያድር በየአካባቢው ስራዎች ቢጀመረም ውጤቱ ቀሪ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው። ዛሬም በምርት እጥረት የኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች ይስተዋላሉ። በእነዚህ መሬቶች ላይ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ከተማ ቁጭ ማለትን የሚሻ ትውልድ ማየት የተለመደ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች እጃቸው ብርቱ በመሆኑ እነዚህ ችግሮች በስራ አሽንፈዋል። ይህም በምግብ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ በኢኮኖሚም እንዲረጋጉ አድርጓቸዋል።   ለሀብት ምንጭ የሆነን ማሳ ለቆ ከተማ በመዋል የሚገኝ ነገር አይኖርም። በከተማም ሆነ በገጠር ለመለወጥ እንደ ቤንቾች ብርቱ እጆች ያስፈልጋሉ። ካልተሰራ ገቢ ሳይሆን ወጪ እያደገ ወዳልተገባ መንገድ ለመሄድ ምክንያት ይሆናል። ለችግርም ሆነ ሰርቶ የመለወጥ ዕድሉ የሚወሰነው በምርጫችንና ለሥራችን በምንሰጠው ትኩረት ነው። እንደ ቤንች ሸኮ ዞን አርሶ አደሮች ሰርቶ ለመለወጥና ራስን ለመቻል በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየር ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ። ሰላም!
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም