ቀጥታ፡

ጀርመን ወደ ጥሎ ማለፉ ገብታለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ አምስት መርሐ ግብር ጀርመን ከመመራት ተነስታ ኮትዲቯርን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

ማምሻውን በቶሮንቶ ስታዲየም በተደረገው የምድብ አምበሉ ፍራንክ ኬሲዬ በ30ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ኮትዲቯር መሪ ሆናለች።

ይሁንና ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው ዴኒስ ኡንዳቭ በ85ኛው እና 94ኛው ደቂቃ ያስቆጠራቸው ጎሎች ጀርመንን አሸናፊ አድርጓል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቱን ተከትሎ የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን በስድስት ነጥብ  ወደ ጥሎ ማለፍ የገባች ሶስተኛ ሀገር ሆናለች።

አሜሪካ እና ሜክሲኮ አስቀድመው ጥሎ ማለፍ የገቡ ሀገራት ናቸው።

ኮትዲቯር በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ኢኳዶር ከኩራሳኦ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሁለቱ ሀገራት በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም