በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በማስተሳሰር መጪው ትውልድን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል - ኢዜአ አማርኛ
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በማስተሳሰር መጪው ትውልድን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በማስተሳሰር መጪውን ትውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር እስካሁን የተካሄዱ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ከምልከታው በኋላም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በክልሉ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ፍራፍሬ እና የደን ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሚተከሉ ችግኞችም በምግብ ራስን ለመቻል የሚያግዙ እና ለእንስሳት መኖነት የሚውሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በማስተሳሰር መጪውን ትውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ነው የገለጹት።