ቀጥታ፡

ቱኒዚያ ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ስድስት መርሐ ግብር ጃፓን ቱኒዚያን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፋለች።

ማለዳ ላይ በሞንቴሬይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አያሴ ኡዳ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ዳይቺ ካማዳ እና ጁንያ ኢቶ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ካማዳ በዓለም ዋንጫው 1000ኛ ጨዋታ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል።

በጨዋታው ጃፓን በተጋጣሚዋ ላይ የተሻለ ብልጫ ነበራት። 

በአንጻሩ ቱኒዚያ ደካማ የጨዋታ እንቅስቃሴ አድርጋለች።

1000ኛውን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና የጃፓን ልዕልት ሂሳኮ በስታዲየም በመገኘት ተከታትለውታል።

በውድድሩ ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው  ቱኒዚያ ከዓለም ዋንጫው የተሰናበተች ሶስተኛ ሀገር ሆናለች።

ቱኒዚያ በስዊድን የ5 ለ 1 ሽንፈት ካስተናገደች በኋላ አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን በማሰናበት የቀጠረቻቸው ፈረንሳዊ አሰልጣኝ ሀርቬ ሬናርድ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ሽንፈት አስተናግደዋል።

ቱርኪዬ እና ሀይቲ ሌሎች ከዓለም ዋንጫው መሰናበታቸውን ያረጋገጡ ሀገራት ናቸው።

ድል የቀናት ጃፓን በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ትናንት ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ ኔዘርላንድስ ስዊድንን 5 ለ 1 አሸንፋለች።

በመጨረሻው የምድቡ መርሐ ግብር ቱኒዚያ ከኔዘርላንድስ፣ ጃፓን ከስዊድን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም