ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያን መረቁ

‎አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  '‘ዲጂታል ለልህቀት'’ በሚል ስያሜ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ፣ በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ዛሬ በይፋ መርቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል ሲሉም ገልጸዋል።

‎‎ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነውም ብለዋል።


 

ይህን ስኬት እንድናጠናክር፣ ተሞክሯችንን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንድንጓዝ በማለት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም