ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የኃይማኖት ተቋማት የነገ ተስፋን የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 174
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦የኃይማኖት ተቋማት አብሮነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን የነገ ተስፋ የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ''የኃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግስት ዕይታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ጋር የማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩም የመደመር መንግስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ምልከታ የሚዳስስ የመነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል። የመድረኩ ተሳታፊ አባቶችና የእምነቱ ተከታዮችም መንግስት ቤተ-ክርስቲያኗ በምታቀርባቸው ጥያቄዎች ላይ ለሚሰጠው አፋጣኝ ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ኃይማኖታዊ ዕሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በማድረግ አስደናቂ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በመዲናዋ የተገነቡ ስኬታማ የልማት ሥራዎችም የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ አዲስ አበባ ውብ ገጽታ እንድትላበስ ማድረጉን ተናግረዋል። በቀጣይነትም በአዲስ አበባ ዘላቂ የልማትና ሰላም ግንባታ ሥራ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። በተነሱ ጉዳዮች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመዲናዋ አስደናቂ የልማት ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለሚቀርቡ ጉዳዮችም ከተማ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በፍትሀዊነት እያስተናገደ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ጽንፈኝነትና አክራሪነትን በመታገል ለአዲስ አበባና ኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ስኬት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የማይተካ ሚና እየተጫወተች እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የመደመር መንግስትም ቤተክርስቲያኗ ትውልድን በመቅረጽ፣ ቅርስና ታሪክን በመጠበቅ ለሀገር ግንባታ ላበረከተችው አስደናቂ አስተዋጽኦ ዕውቅና እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በቀጣይም የእምነት ተቋማት ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረፅ ለሀገር ዘላቂ ልማትና ሰላም ግንባታ የሚኖራቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ከተማ አስዳደሩም የእምነት ተቋማት የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በፍትሐዊነት ምላሽ በመስጠት የመዲናዋን ዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ የማፋጠን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኃይማኖት ተቋማት የዜጎችን ሕብረብሔራዊ አንድነት በማጠናከር የኢትዮጵያን የነገ ተስፋ የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ድህነትን ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ የእምነት ተቋማት ዘላቂ ልማትና ሰላምን በመገንባት ወሳኝ ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው
Mar 16, 2026 96
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ወንዞችን አረንጓዴ በማልበስና የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን አባላት ሀገራት ተወካዮች ገለፁ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን አባል ሀገራት ተወካዮች የአዲስ አበባን የወንዝ ዳርቻ ልማት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የመዲናዋን የወንዞች ዳርቻ በማልማት ከቆሻሻ መጠራቀሚያነት አውጥቶ ወደ ሕዝብ መዝናኛነትና የከተማ ውበት አካል እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን አድንቀዋል። በተለይም የወንዝ ዳርቻዎችን አረንጓዴ በማልበስ የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር የማስተሳሰር ረገድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት እንደሚሆን ገልጸዋል።   የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ፌሊክስ ሞሲ ንጋምላጎሲ፥ የአፍሪካ ከተሞች የታቀዱ፣ ሳቢ እና የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ አዲስ አበባ በአርዓያነት የምትጥቀስ ናት ብለዋል። በተለይም አሁን ላይ በአዲስ አበባ እየታዩ ያሉ ለውጦች ከተማዋን ለሰዎች መዝናኛና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተመራጭ እያደረጓት መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ካሉ የልማትና የከተማ ውበት ስራዎች ልምድ እንዲቀስሙና ትምህርት እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚምባብዌ የመጡት ቺቶ ፊሪ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ የሕዝብ መዝናኛ ፓርኮች በስፋት ተገንብተው መመልከታቸውን በአድናቆት ጠቅሰዋል።   ይህም ለከተማዋ ድምቀት ከመሆኑ ባለፈ ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች ምቹ የመንቀሳቀሻ ከባቢን የሚፈጥር ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ለእግረኛ መንገድ የተሰጠው ትኩረት ለጤና እጅግ ተስማሚ የሆነውን የእግር ጉዞ ባህል እንደገና ለማነቃቃት ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም ነው የተናገሩት።   ከሞዛቢክ የመጡት ማኑኤል ቻጉሎ፤ ከ15 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጎብኝተው እንደነበር በማስታወስ፤ አሁን ድጋሚ ሲመጡ አዲስ አበባ አስድናቂ ለውጥና ዕድገት አስመዝግባ እንዳገኟት ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ልምድ የሚቀሰምበት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቷን ጠቅሰዋል።
የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Mar 16, 2026 103
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (አዜአ)፦ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በምክር ቤቱ የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ኢንተርፕራይዞችንና የመዳረሻ ሀገራትን በማስፋት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ ለ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በተያዘው ዕቅድ መሰረት በብዝኅ ኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባላትም፤ ባለፉት ስድስት ወራት የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራትንና የቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ፤ የኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እየተቻለ ነው ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ፤ የመዳረሻ ሀገራትን በማስፋት ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱም በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ወቅት ሕጋዊ ግዴታቸውን በማይወጡ ኤጄንሲዎች ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ዜጋ በማፍራት ለሥራ ገበያው ዝግጁ የሆነ የሰው ሃይል እያቀረቡ ነው ያሉት ደግሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ናቸው። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ግንባታን በማጠናቀቅ ዕውቀትና ክህሎትን ያጣመሩ ዜጎች ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት እያከናወነ ነው ብለዋል። በቀጣይም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅምን የበለጠ በማጠናከር ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ተጠቃሚነትን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
የሚታይ

ኢትዮጵያ እና ጣልያን አጋርነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 16, 2026 301
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ጣልያን ያላቸውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ እና ጣልያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ያለመ ጉብኝት በጣልያን ሮም እያደረገ ይገኛል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከጣልያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ኤድሞንዶ ቺሬሊ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ጣልያን የኢኮኖሚ ትብብር፣ የልማት አጋርነት፣ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንትና ቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያላቸውን ትስስር ማስፋት ላይ ያተኮረ ነው። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።   በተጨማሪም የኢኮኖሚ መረጋጋትን ዘላቂ ለማድረግ፣ የኢንቨስትመንት ምህዳርን ለማሻሻልና ሁሉን አካታች እድገትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። የጣልያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ኤድሞንዶ ቺሬሊ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን በቀጣናው መረጋጋት ያላትን ሚና አንስተዋል። ምክትል ሚኒስትሩ ጣልያን በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አማካኝነት የኢትዮጵያን የልማት የትኩረት መስኮች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና ጣልያን ያላቸውን የረጅም ጊዜ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ቤተክርስቲያኗ በከተማችን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 141
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (አዜአ)፡- በታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በከተማችን ሁለንተናዊ የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሐይማኖት ተቋማት በመደመር መንግሥት ዕይታ በሚል መሪ ሐሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት አባቶችና አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የዛሬዋን ኢትዮጵያ በመገንባት ረገድ ከሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ጋር በመሆን ወሳኝ ሚና አበርክታለች ሲሉም ገልጸዋል።   ቤተክርስቲያኗ በሀገረ መንግሥት ግንባታ፤ ጥንታዊ ቅርሶችን፣ ታሪኮችንና ትውፊቶችን ጠብቆ ለትውልድ በማሸጋገር፣ ትውልድን በማነጽ፣ ግብረ-ገብነትንና ሰብዓዊ ርኅራኄን በማስተማር፣ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም በልማት ተሳትፎ የጎላ ድርሻ ስትወጣ ቆይታለች ብለዋል ከንቲባዋ። በውይይቱም በታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታትም ቤተክርስቲያኗ በከተማችን ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ፣ የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ላይ እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦ አንስተናል ነው ያሉት። ለሕዝቦች ትስስር መጎልበት፣ ለሰላም፣ ለኢትዮጵያ ብልፅግና እና ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ ለመቆም መግባባት ላይ ደርሰናልም ብለዋል። በውይይት መድረኩ የተነሱ አንዳንድ ያጋጠሙ ክፍተቶችን በትብብር ለማረም የሚያስችል ምቹ መደላድል የፈጠረ ውጤታማ መድረክ ነበር ሲሉም ገልጸዋል። መድረኩ በየክፍለ ከተማው ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶች ማጠቃለያ መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህም የመንግሥትን እና የሐይማኖት ተቋማትን ሚና ብሎም ድርሻ በግልጽ ለይቶ ያስቀመጠ መሆኑንም አመላክተዋል። የኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶችና አመራሮች ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎና ገንቢ ሐሳብም አመስግነዋል።
ቤተ እምነቶች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር አለባቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 160
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-ቤተ እምነቶች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የሃይማኖት ተቋማት ለሕዝቦች ትስስር መጎልበት፣ ለልማትና ሰላም ያላቸውን አዎንታዊ ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግሥት ዕይታ” በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።   በመድረኩ የመደመር መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያለው ምልከታ ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የማይተካ ሚና መጫወቷን ገልጸዋል። እንዲሁም ትውልድን በመቅረጽ፣ቅርስ እና ታሪኮችን ጠብቃ ማቆየቷን ተናግረዋል። የመደመር መንግሥት ለዚህ እውቅና እንደሚሰጥ ገልጸው፤ እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል። የቤተ እምነቶች ትልቁ ሀላፊነት የሰላም አምባሳደርነት መሆኑን ገልጸው፤ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸው አመላክተዋል።   እምነትን ሽፋን ያደረጉ ህገወጥ ድርጊቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው፤ የማምለኪያ ስፍራዎችን በተመለከተም ችግሮችን በመፈተሽ በፍትሀዊነት ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተጨባጭ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለመፍታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም ጠቁመዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ኢትዮጵያ እና ጣልያን አጋርነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 16, 2026 301
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ጣልያን ያላቸውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ እና ጣልያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ያለመ ጉብኝት በጣልያን ሮም እያደረገ ይገኛል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከጣልያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ኤድሞንዶ ቺሬሊ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ ኢትዮጵያ እና ጣልያን የኢኮኖሚ ትብብር፣ የልማት አጋርነት፣ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንትና ቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያላቸውን ትስስር ማስፋት ላይ ያተኮረ ነው። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።   በተጨማሪም የኢኮኖሚ መረጋጋትን ዘላቂ ለማድረግ፣ የኢንቨስትመንት ምህዳርን ለማሻሻልና ሁሉን አካታች እድገትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል። የጣልያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ኤድሞንዶ ቺሬሊ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን በቀጣናው መረጋጋት ያላትን ሚና አንስተዋል። ምክትል ሚኒስትሩ ጣልያን በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አማካኝነት የኢትዮጵያን የልማት የትኩረት መስኮች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና ጣልያን ያላቸውን የረጅም ጊዜ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።
ወጣቶች በጠቅላላ ምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Mar 16, 2026 198
ባህር ዳር፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-ወጣቶች በመጪው ጠቅላላ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ረገድ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበራት ፌዴሬሽን አስታወቀ። በጠቅላላ ምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበራት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ግርማ አቸነፍ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደ ሲቪክ ማህበር የሚጠበቁ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ወጣቶች የምረጡኝ ቅስቀሳዎችን በትኩረት በመከታተል ይበጀኛል፤ ይጠቅመኛል ብለው ያመኑበትን ፓርቲ እንዲመርጡ የግንዛቤ ፈጠራ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።   ፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የታዛቢነትና የአስተባባሪነት ህጋዊ ሰርቲፊኬት ወስዶ ወደ ተግባራዊ ስራ መግባቱንም አረጋግጧል። መንግስትና ሃገር የሚፀናው በዲሞክራሲያዊ ምርጫ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ወጣቱ የምርጫ ካርድ በነቂስ እንዲያወጣ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድቷል። ወጣቱ ፓርቲዎች የሚያቀርቡትን አማራጭ ሃሳብ መዝኖ የሚጠቅመውን ከመለየት ባለፈ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የግንዛቤ ማጎልበት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ወጣቱ ኃይል ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚኖረው ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሶ፤ የምርጫ ካርድ ከማውጣት ባለፈ ዘላቂ ሰላምና ልማት ያመጣልኛል የሚለውን ፓርቲ እንዲመርጥም አስገንዝቧል። ወጣት ጥላሁን አበበ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆን በመጪው ምርጫ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ለመሆን ከወዲሁ ለመራጭነት የሚያበቃውን የምርጫ ካርድ መያዙን ገልጿል። ምርጫው በማንኛውም መለኪያ ሰላማዊና አሳታፊ እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣ ጠቁሞ፤ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸውን አማራጭ ፖሊሲዎች በማመዛዘን ለመምረጥ መዘጋጀቱን ተናግሯል። በያዘችው የመራጭነት ካርድ የወጣቱን ፍላጎትና ጥያቄ በአግባቡ ተረድቶ ምላሽ ይሰጣል ብላ ላመነችበት ፓርቲ ድምጿን ለመስጠት መዘጋጀቷን የገለፀችው ደግሞ ወጣት ፋሲካ አማረ ናት። ፓርቲዎች እያደረጉት ባለው የምረጡኝ ቅስቀሳ አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለመረዳት እንደቻለች ጠቅሳ፤ ይህም የተሻለ ጠቃሚ አጀንዳ ያለውን ለመለየት እንዳገዛት ተናግራለች። ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የራሷን ኃላፊነት ለመወጣት መዘጋጀቷንም አረጋግጣለች።
በጠቅላላ ምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን
Mar 16, 2026 242
ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ):- በጠቅላላ ምርጫው በንቃት በመሳተፍ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን ሲሉ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን ገለጹ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ የመራጮች ምዝገባና ሌሎች የቅድመ ምርጫ ተግባራትን እያከናወነ ነው፡፡ መጪው ምርጫን አስመልክተው ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራን እንዳሉት፤ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታው የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ተዘጋጅተናል። በዩኒቨርስቲው የሒሳብ መዝገብ አያያዝ እና የፋይናንስ ትምህርት ክፍል መምህርት ትዕግስት ደቻሳ፤ ምርጫ ሴቶች ዴሞክራሴያዊ መብታቸውን የሚጠቀሙበት በመሆኑ ተሳትፏቸውን ማጠናከር ይኖርባቸዋል ብለዋል። ሴቶች በሀገሪቱ በምርጫ እኩል ተሳትፎ የሚያደርጉበት ስነ- ምሕዳር የተፈጠረ በመሆኑ እድሉን በመጠቀም የሚፈልጉትን ፓርቲ ወደ ስልጣን ማምጣት ይገባቸዋል ነው ያሉት። በምርጫው የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸውን ጠቅሰው በሀገሪቱ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ስኬት የበኩላቸውን ለመወጣት ማቀዳቸውን አስረድተዋል። ዕድሜያቸው ለምርጫ የደረሰ ሁሉም ሴቶች በድምፃቸው መሪዎቻቸውን የመወሰን ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ያሉት ደግሞ የዩኒቨርስቲው የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ትምህርት መምህርት ኃይማኖት አዱኛ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ የምርጫ ክርክሮች ፓርቲዎች እንደ ሀገር ይዘው የመጡትን አማራጭ ለማወቅ እድል የፈጠረ በመሆኑ ድምፃቸውን ይበጀኛል ለሚሉት ፓርቲ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል። ሴቶች ተሳትፏቸውን በማጠናከር ለሀገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሳለጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ የሚጠበቅብንን እንወጣለን ነው ያሉት። በዩኒቨርቲው የወላይትኛ ትምህርት ክፍል መምህርት አሪፏ ኮራ በበኩላቸው፤ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሴቶች ተሳትፎ የላቀ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ሴቶች በቁጥራቸው ልክ በሁሉም ዘርፎች ከተሳተፉ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመልክተው በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት ለመሳተፍ የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ጠቁመዋል። በድምጽ መስጫ ወቅትም ለሰላምና ልማት ይበጃል ያሉትን ፓርቲ ወደ ስልጣን ለማምጣት መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት።  
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 1793
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ምርጫው ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን - የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
Mar 14, 2026 727
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን ሲል የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ። ፓርቲው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አስታውቋል። የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወዴፓ) የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ ፓርቲው በመርሃ ግብሩ እጬዎችን የማስተዋወቅና ለምርጫው እያደረጉት ያለውን ዝግጅት አስተዋውቋል። በዚህም የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመወዳደሪያ ምልክት ቁልፍ መሆኑን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ፓርቲው የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ"ከውሀ ወደ ውሀ" በሚል መሪ መልዕክት መሰየሙን ገልጿል፡፡   የፓርቲው ፕሬዚዳንት ነፃነት ጣሰው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወዴፓ) የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩሉን ይወጣል ብለዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንደተሳካ ሁሉ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄን ምላሽ ለማስገኘት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል። ስለሆነም የወሎ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በነቃ ተሳትፎ ከመንግሥት ጎን ለመቆም ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ ነው
Mar 14, 2026 441
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ገለፁ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከሴቶች ክንፍና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ''ፍትሀዊ ውክልና ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ'' በሚል መሪ ሃሳብ የሴቶች ቀንን አክብሯል።   በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ፤ በኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ሚና በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በሚቀርጿቸው ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነትና ተሳትፎ ማሻሻል እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትም የሴቶችን ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ለማጠናከር አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።   የጋራ ምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እፀገነት ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ባለድርሻ አካላት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ለማጎልበት በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀቶችም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት ማረጋገጥ የሚያስችል ምቹ ምኅዳር መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።   የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ነቢሃ መሀመድ፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ የሴቶች ተሳትፎና ውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ዕድገት እያስመዘገበ ነው ብለዋል። በቀጣይም የሴቶችን የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔ ሰጪነት ድርሻ ለማሻሻል የመጡ ለውጦችን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።   የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ነሲም አሊ፤ የምርጫ ሂደት ፍትሕዊነትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል። ቦርዱም የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችል የማበረታቻ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
በክልሉ ችግሮችን በውይይትና በምክክር በመፍታት ጠንካራ ሥርዓት ለመገንባት በጋራ መስራት ይገባል - አቶ ከፍያለው ተፈራ
Mar 14, 2026 401
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል አሁን ያሉ ችግሮችን በውይይትና በምክክር በመፍታት ጠንካራ ሥርዓት ለመገንባት በጋራ መስራት እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ገለጹ። በክልሉ ዘላቂ ሰላም ማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ ምሁራን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ወጣቶች ተገኝተዋል። የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተመዘገበበት የልማት ስራ ተከናውኗል። በተለይም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ ከሰላም አንጻር በክልሉ የተስተዋለው ችግር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማት ሥራዎችን በሚፈለገው ፍጥነት ለማስኬድ እንቅፋት መፍጠሩን አንስተዋል። "ችግሮችን በውይይትና በምክክር በመፍታት ጠንካራ ሥርዓት ለመዘርጋትና ልማትን ለማፋጠን በጋራ መቆም ይገባል" ብለዋል። ለዚህም ኃላፊነቱ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት መሆኑን አስገንዝበዋል። በልማትና ሰላም ላይ አተኩሮ ከሚሰራ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የመጡት ገረሱ ቱፋ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የመነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል። እሳቸውም ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን እያንዳንዱ ዜጋ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለውና ሰላም ለልማት መሰረት መሆኑን አስረድተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት ለማከናወን ሰላም ቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት አንስተዋል። ማንኛውም ችግር ዘመኑን በሚመጥን መልኩ በሰለጠነ ውይይትና በንግግር ብቻ መፈታት ይኖርበታል ያሉት ተሳታፊዎቹ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ወጣቶች ለሰላም ግንባታው ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አመልክተዋል።  

ማህበራዊ
የኃይማኖት ተቋማት የነገ ተስፋን የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ ናቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 174
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦የኃይማኖት ተቋማት አብሮነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን የነገ ተስፋ የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ''የኃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግስት ዕይታ” በሚል መሪ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ጋር የማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል። በመድረኩም የመደመር መንግስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ያለውን ምልከታ የሚዳስስ የመነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል። የመድረኩ ተሳታፊ አባቶችና የእምነቱ ተከታዮችም መንግስት ቤተ-ክርስቲያኗ በምታቀርባቸው ጥያቄዎች ላይ ለሚሰጠው አፋጣኝ ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአደባባይ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ኃይማኖታዊ ዕሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በማድረግ አስደናቂ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በመዲናዋ የተገነቡ ስኬታማ የልማት ሥራዎችም የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ አዲስ አበባ ውብ ገጽታ እንድትላበስ ማድረጉን ተናግረዋል። በቀጣይነትም በአዲስ አበባ ዘላቂ የልማትና ሰላም ግንባታ ሥራ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። በተነሱ ጉዳዮች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመዲናዋ አስደናቂ የልማት ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለሚቀርቡ ጉዳዮችም ከተማ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በፍትሀዊነት እያስተናገደ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ጽንፈኝነትና አክራሪነትን በመታገል ለአዲስ አበባና ኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ ስኬት በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የማይተካ ሚና እየተጫወተች እንደሚገኝ ገልጸዋል።   የመደመር መንግስትም ቤተክርስቲያኗ ትውልድን በመቅረጽ፣ ቅርስና ታሪክን በመጠበቅ ለሀገር ግንባታ ላበረከተችው አስደናቂ አስተዋጽኦ ዕውቅና እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በቀጣይም የእምነት ተቋማት ትውልድን በመልካም ሥነ-ምግባር በመቅረፅ ለሀገር ዘላቂ ልማትና ሰላም ግንባታ የሚኖራቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ከተማ አስዳደሩም የእምነት ተቋማት የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በፍትሐዊነት ምላሽ በመስጠት የመዲናዋን ዘላቂ ሰላምና ልማት ግንባታ የማፋጠን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የኃይማኖት ተቋማት የዜጎችን ሕብረብሔራዊ አንድነት በማጠናከር የኢትዮጵያን የነገ ተስፋ የሚያለመልሙ የልማትና ሰላም ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ድህነትን ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብ የእምነት ተቋማት ዘላቂ ልማትና ሰላምን በመገንባት ወሳኝ ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
ተማሪዎችን በእውቀትና በሥነ ምግባር የማነጽ ግንባር ቀደም ኃላፊነታችንን እየተወጣን ነው-የጎንደር ከተማ መምህራን 
Mar 16, 2026 135
ጎንደር ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦ተማሪዎችን በእውቀትና በሥነ ምግባር የማነጽ ግንባር ቀደም ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ በጎንደር ከተማ የሚገኙ መምህራን ገለጹ፡፡ ሴቶች ጠንክረን ከሰራን በማንኛውም መስክ ስኬታማ መሆን እንችላለን-ተመራቂ የሕክምና ባለሙያዎች የአማራ ክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች "ለሰላም ዘብ እቆማለሁ፤ የልማት አርበኛ እሆናለሁ" በሚል መሪ ሀሳብ ከከተማዋ መምህራን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።   ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል መምህር ብሩክ አንዳርጌ እንደገለጹት፤ በእውቀት የተገነባና በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ በማፍራት በኩል የመምህራን ተሳትፎና ጥረት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ መምህራን የእውቀት አባት እንደመሆናችን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትኩረት በመስጠት በእውቀትና በስነምግባር የታነጻ ዜጋ ለማፍራት በቁርጠኝነት እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል። ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ መምህር ታድሎ ጸጋ በበኩላቸው፤ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲኖር ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ለአካባቢው ሰላም መጠናከር ከመንግስት ጋር በመተባበር እንሰራለን ብለዋል። "የሰው ሃብት ልማት ለአንድ ሀገር እድገት መፋጠን አበርክቶው ከፍተኛ ነው" ያሉት መምህር ታድሎ ይህንን ለማሳካት በትምህርት ጥራት፣ አግባብነትና ተደራሽነት ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። በትውልድ ግንባታና ቀረጻ ላይ የመምህራንና የትምህርት ቤቶች ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት ደግሞ መምህር ሰለሞን ታደለ ናቸው፡፡ ተማሪዎች ነገ ለሀገርና ለህዝብ ጠቃሚ እንዲሆኑ በትምህርት ቆይታቸው በቂ እውቀትና ክህሎት በማስጨበጥ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት እየሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል። መንግስት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና የትምህርት ግብአቶችን በማሟላት በኩል እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም ነው የገለጹት።   የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) በመድረኩ እንደገለጹት፤ በክልሉ የሰፈነው ሰላም ከትምህርት ገበታ ተለይተው የቆዩ በርካታ ህጻናትን ወደ ትምህርት ለመመለስ አስችሏል። የመማር ማስተማር ስራው ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲከናወን መምህራን ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ሰላምን ማስቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ፣ የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻልና ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን በመፍጠር ረገድ ውጤት ተመዝግቧል ያሉት ደግሞ የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡   ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን በአዲስ በመገንባት፣ የትምህርት ግብአቶችን በማሟላትና የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር በማካሄድ ውጤታማ ተግባር ለማከናወን መቻሉን አስረድተዋል፡፡ የዛሬው የውይይት መድረክ ዓላማም የከተማው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የልማት እቅዶችም እንዲሳኩ በማድረግ በኩል መምህራን የነበራቸውን የላቀ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥል ለማስቻል ነው ብለዋል። በመድረኩ ላይ ከጎንደር ከተማ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሰ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና መምህራንን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት አመራሮች ተሳትፈዋል።
ቤተክርስቲያኗ በከተማችን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 141
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (አዜአ)፡- በታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በከተማችን ሁለንተናዊ የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሐይማኖት ተቋማት በመደመር መንግሥት ዕይታ በሚል መሪ ሐሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የሐይማኖት አባቶችና አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የዛሬዋን ኢትዮጵያ በመገንባት ረገድ ከሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ጋር በመሆን ወሳኝ ሚና አበርክታለች ሲሉም ገልጸዋል።   ቤተክርስቲያኗ በሀገረ መንግሥት ግንባታ፤ ጥንታዊ ቅርሶችን፣ ታሪኮችንና ትውፊቶችን ጠብቆ ለትውልድ በማሸጋገር፣ ትውልድን በማነጽ፣ ግብረ-ገብነትንና ሰብዓዊ ርኅራኄን በማስተማር፣ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በማጠናከር እንዲሁም በልማት ተሳትፎ የጎላ ድርሻ ስትወጣ ቆይታለች ብለዋል ከንቲባዋ። በውይይቱም በታሪክ ብቻ ሳይሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታትም ቤተክርስቲያኗ በከተማችን ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ፣ የልማት እና የብልፅግና ጉዞ ላይ እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦ አንስተናል ነው ያሉት። ለሕዝቦች ትስስር መጎልበት፣ ለሰላም፣ ለኢትዮጵያ ብልፅግና እና ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ ለመቆም መግባባት ላይ ደርሰናልም ብለዋል። በውይይት መድረኩ የተነሱ አንዳንድ ያጋጠሙ ክፍተቶችን በትብብር ለማረም የሚያስችል ምቹ መደላድል የፈጠረ ውጤታማ መድረክ ነበር ሲሉም ገልጸዋል። መድረኩ በየክፍለ ከተማው ሲካሄዱ የቆዩ ውይይቶች ማጠቃለያ መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህም የመንግሥትን እና የሐይማኖት ተቋማትን ሚና ብሎም ድርሻ በግልጽ ለይቶ ያስቀመጠ መሆኑንም አመላክተዋል። የኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን አባቶችና አመራሮች ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተሳትፎና ገንቢ ሐሳብም አመስግነዋል።
ቤተ እምነቶች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር አለባቸው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Mar 16, 2026 160
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-ቤተ እምነቶች ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የሃይማኖት ተቋማት ለሕዝቦች ትስስር መጎልበት፣ ለልማትና ሰላም ያላቸውን አዎንታዊ ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የሃይማኖት ተቋማት በመደመር መንግሥት ዕይታ” በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።   በመድረኩ የመደመር መንግሥት ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያለው ምልከታ ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የማይተካ ሚና መጫወቷን ገልጸዋል። እንዲሁም ትውልድን በመቅረጽ፣ቅርስ እና ታሪኮችን ጠብቃ ማቆየቷን ተናግረዋል። የመደመር መንግሥት ለዚህ እውቅና እንደሚሰጥ ገልጸው፤ እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል። የቤተ እምነቶች ትልቁ ሀላፊነት የሰላም አምባሳደርነት መሆኑን ገልጸው፤ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር እንዳለባቸው አመላክተዋል።   እምነትን ሽፋን ያደረጉ ህገወጥ ድርጊቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ጠቁመው፤ የማምለኪያ ስፍራዎችን በተመለከተም ችግሮችን በመፈተሽ በፍትሀዊነት ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተጨባጭ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለመፍታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም ጠቁመዋል።
ኢኮኖሚ
የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል
Mar 16, 2026 103
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (አዜአ)፦ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በምክር ቤቱ የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም፤ ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ኢንተርፕራይዞችንና የመዳረሻ ሀገራትን በማስፋት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ ለ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በተያዘው ዕቅድ መሰረት በብዝኅ ኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባላትም፤ ባለፉት ስድስት ወራት የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራትንና የቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ፤ የኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ እየተቻለ ነው ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ፤ የመዳረሻ ሀገራትን በማስፋት ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በሂደቱም በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ወቅት ሕጋዊ ግዴታቸውን በማይወጡ ኤጄንሲዎች ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዕውቀትና ክህሎት የበለጸገ ዜጋ በማፍራት ለሥራ ገበያው ዝግጁ የሆነ የሰው ሃይል እያቀረቡ ነው ያሉት ደግሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ናቸው። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ግንባታን በማጠናቀቅ ዕውቀትና ክህሎትን ያጣመሩ ዜጎች ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት እያከናወነ ነው ብለዋል። በቀጣይም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅምን የበለጠ በማጠናከር ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ተጠቃሚነትን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ970 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድ ግንባታና ጥገና ተከናውኗል
Mar 16, 2026 82
ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ስምንት ወራት ከ970 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአዲስ መንገድ ግንባታ፣ ጥገና እና ተያያዥ ተግባራት መከናወናቸውን የዞኑ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ አስታወቀ። የኮሪደር ልማት ዘመናዊ ከተሜነትን በማስፋፋት ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል እያደረገ ነው መምሪያው ባለፉት ስምንት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ማናየ አዳነ እንደገለጹት፤ የመንገድና ትራንስፖርት ዘርፉ ለአገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለማህበራዊ ትስስር የጀርባ አጥንት መሆኑን በመገንዘብ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ከመንግስት፣ ከረድኤት ድርጅቶችና ከማህበረሰቡ በተገኘ ከ970 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ከተከናወኑ ተግባራት መካከል 652 ኪሎ ሜትር መንገድ የጥገና ሥራ፣ ከ11 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታ እና 30 ኪሎ ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይና ሌሎች ግንባታና ጥገና መካሄዱን ገልጸዋል። እነዚህ የግንባታና የጥገና ሥራዎች በጎዛምን፣ በማቻከል፣ በደብረ ኤሊያስ፣ በሰዴ፣ በባሶ ሊበንና በሌሎችም ወረዳዎች መከናወናቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።   የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አባተ በበኩላቸው፤ መንግስት ህብረተሰቡንና ባለሀብቶችን በማስተባበር ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል። በተለይም በትራንስፖርት ስምሪት ላይ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችንና ሙስናን ለማስወገድ የዲጂታል አሰራርን መተግበር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በፌዴራልና በክልል መንግስት ድጋፍ ተጨማሪ የ200 ኪሎ ሜትር መንገድና የሰባት ድልድዮች ግንባታ በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።
በቅርቡ የጸደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለብዝሃ ቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል
Mar 16, 2026 93
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-በኢትዮጵያ በቅርቡ የጸደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለኪነ ጥበብ ቱሪዝም ትኩረት በመስጠት ለብዝሃ ቱሪዝም ዕድገት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው በሰዓሊ ተገኔ ኩንቢ በጣሊያን ቬንስ በሚካሄደው 61ኛው የቬኒስ ቢየናሌ የኢትዮጵያን ፓቪሊዮን "የዝምታ ቅርጾች" የተሰኘ አውደ ርዕይ ዙሪያ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን እና የኤግዚቢሽኑ አዘጋጅ ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የምትሳተፍበት የቬኒስ ቢየናሌ በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊና ታዋቂ ዝግጅቶች አንዱ ነው።   በኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ ለብዝሃ ቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት በመስጠት አዳዲስና ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስፋፋት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል። ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚኖረውን አበርክቶ ማሳደግ የሚያስችል የቱሪዝም ፖሊሲ መፅደቁንም ገልጸዋል። አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ብዝሃ ቱሪዝምን ለማሳደግ ታሪካዊና ባህላዊ የቱሪስት መስህቦችን፣ ኢኮ-ቱሪዝም፣ ጂኦ ቱሪዝም፣ የቡና ቱሪዝም፣ ኮንፍረንስ ቱሪዝም እና የአርት/የኪነ ጥበብ ቱሪዝም ዘርፎችን አካቷል ብለዋል። ኢትዮጵያ በጣሊያን ቬኒስ ከተማ በሚካሄው ዓለም አቀፍ ዝግጅት የኢትዮጵያ ፖቪሊዮን "የዝምታ ቅርጾች" በማዘጋጀት የኪነ ጥበብ ስራዎቿን የምታስተዋውቅበት መድረክ መሆኑን ገልፀዋል። ይሄውም አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ለብዝሃ ቱሪዝም የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው፤ ኤግዚቢሽኑ ዓለም አቀፍ የሥዕል ሥራዎችን ውድድር ያለፉ አርቲስቶች ቀርበው የሀገራቸውን ገፅታ የሚገነቡበትና የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው ብለዋል። መድረኩ የኢትዮጵያን የኪነ ጥበብ ሥራዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን በማንሳት፤ የኢትዮጵያን ልዩ የሙዚቃ፣ ስዕልና ቴአትር ጥበብ እንደሚያሳይ ገልጸዋል።   የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ ኢትዮጵያ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ባላት ዕምቅ አቅም ልክ ተጠቃሚ አልነበረችም ብለዋል። ይሁን እንጂ ከለውጡ ወዲህ ባለው የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ኪነ ጥበብ ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ ያዘጋጀው አውደ ርዕይ "ዝምታ" የኢትዮጵያን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያቀርብ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በስዕልና ቅርፃ ቅርፅ ዘርፍ ያሉ ሰዎች በስፋት እንዲሳተፉ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ስኬታማ ስራ ነውም ብለዋል። አውደ ርዕዩ የኢትዮጵያ አመለካከትና ፈጠራ የተገለጠበት ድንቅ ዝግጅት መሆኑን ገልጸዋል።   "የዝምታ ቅርጾች" አውደ ርዕይ አዘጋጅ ሰዓሊ ተገኔ ቁንቢ፤ ዝምታ ባዶ ሳይሆን በውስጡ የታመቀ ሀሳብ ያለው ነው ብለዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ነጠላ የኢኮኖሚ አተያይን ወደ ብዝኅ ዘርፍ በማሸጋገር እመርታዊ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው
Mar 16, 2026 80
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ነጠላ የኢኮኖሚ አተያይን ወደ ብዝኅ ዘርፍ በማሸጋገር እመርታዊ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ መሆኑ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ትብብር "ኢትዮጵያ - አዲሲቷ የኢንቨስትመንት መዳረሻ" በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።   ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን እያሳደገ ነው በውይይቱ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃ-ፅዮን፤ ሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያን ውስን የኢኮኖሚ አተያይ ወደ ብዝኅ ዘርፍ የልማት አቅጣጫ ማሸጋገር አስችሏል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም የነጠላ ዘርፍ ኢኮኖሚን በብዝኅ አተያይ በመቀየር አስተማማኝ የዕድገት ምኅዳር እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል። ይህም የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችና የልማት አቅሞች በብዛትና በጥራት የሚስፋፉበትን ምቹ የዕድገት መደላድል መፍጠር እንዳስቻለ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስትመንት ፍሰትና ተወዳዳሪነትን እያሳደገ ነው ብለዋል።   የኢንቨስትመንት ዘርፍ ስኬቶች ተገማችና ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ምኅዳር በመፍጠር በተኪ ምርትና በሥራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹም ከተማ በበኩላቸው፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እመርታዊ የፖሊሲና የአሰራር ምኅዳር እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮችም የምርታማነት አቅምን በማሳደግ በሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚኖራቸውን ድርሻ በማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ኢትዮጵያን ምቹ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል እያደረጋት ይገኛል ያሉት ደግሞ የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሞቱማ ተመስገን ናቸው፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮችም ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚሸጋገሩበትን አስቻይ ምኅዳር በመፍጠር ጥራትና ብቃት ያላቸው አልሚዎች መዋለ ነዋያቸውን ፈሰስ የሚያደርጉበትን ዕድል እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡   የሞሐን ግሩፕ ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሀርሽ ኮታሪ፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአልሚ ባለሃብቶችን ትርፋማነት በማሻሻል ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ መፍጠሩን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ በሀገራዊ ለውጡ ማግስት የመገናኛ ብዙኅን የኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ የሚገልጡበትን ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።   በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ሥራ የጀመረው የፐልስ ኦፍ አፍሪካን (POA) ጨምሮ የህዝብና የንግድ መገናኛ ብዙኅን የሀገርን የዕድገት ዕድሎች እያስተዋወቁ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በቀጣይም መገናኛ ብዙኅን በተለያዩ የቋንቋ አማራጮች ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት የሚያበረክቱትን ጉልህ አስተዋጽኦ ለማስቀጠል የመረጃ ሰጪ ተቋማት ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል። የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙ ለቴክኖሎጂ ትልቅ ትኩረት የሰጠ እና የኢትዮጵያን የእድገት ግስጋሴ የሚያፋጥን አቀጣጣይ ሞተር መሆኑን ተናግረዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በጎንደር ከተማ በዲጂታል የተደገፈ የአድራሻ ስርዓት ትግበራ ተጀመረ
Mar 16, 2026 80
ጎንደር፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፡- በጎንደር ከተማ የዲጂታል የአድራሻ ስርዓት ትግበራ መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ስማርቲ ሲቲ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬተር ይልቃል ሙሉአለም (ዶ/ር ) ለኢዜአ እንደተናገሩት በቴክኖሎጂው የትግበራ ሂደት በከተማው ለሚገኙ 1 ሺ 500 የመኖሪያና የንግድ ተቋማት ዲጂታል የቤት ቁጥር መስጠት ተጀምሯል፡፡ የዲጂታል አድራሻ ስርአቱ ነዋሪዎች የቤት መለያ ቁጥራቸውን ብቻ በማሳወቅ የአንቡላንስና የእሳት አደጋ ጥሪዎችን ጨምሮ የውሃ፣ የቴሌና የመብራት የጥገና አገልግሎቶችን በቤታቸው ሆነው የሚያገኙበት የዲጂታል የአሰራር ስርአት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የከተማውን የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች በዲጂታል አድራሻ ስርአቱ በመታገዝ የቱሪዝም ስፍራዎችን የመዝናኛና ማረፊያ ሆቴሎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ቴክኖሎጂው ይበልጥ አጋዥ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በከተማው የመሬት አስተዳደር ስርአቱን በዲጂታል ማዘመን እንዲቻል በተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችም በአሁኑ ወቅት ከ600 ሽህ በላይ የመሬት ይዞታ መረጃዎችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ወደ ሲስተም የማስገባት ስራ ተከኗውኗል ብለዋል፡፡ የከተማው የመሬት አስተዳደር ስርአት ዲጂታላይዝ በመደረጉም በአሁኑ ወቅት የቤትና የቦታ ባለይዞታዎች የዲጂታል ካርታ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዘመናዊ አሰራር መዘርጋት እንደተቻለም አብራርተዋል፡፡ የዲጂታል ካርታ አሰራር መጀመሩ በዘርፉ ይታይ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የመሬት ወረራንና ብልሹ አሰራርን ከመሰረቱ ለመቅረፍ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ የከተማው ገቢዎች፣ የንግድና ገበያ ልማት መምሪያዎችም ወደ ዘመናዊ ዲጂታል የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአት የሚሸጋገሩበትን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በከተማው መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎትን ለመጀመር ግንባታው እየተፋጠነ ለሚገኘው የማእከሉ ህንጻም የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን የመዘርጋት ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡ በማእከሉ ለተመደቡ ሰራተኞችም የዲጂታል አውቅትና ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሀገር የተጀመረው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ኢንሼቲቭ በዲጂታል ቴክኖሎጂው ዘርፍ እመርታዊ ለውጥና እድገት ለማስመዝገብ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የዲጂታል አድራሻ ስርአት ትግበራውን እያከናወነ የሚገኘው ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር እንደሆነም አመልክተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በምርምር የወጡ ምርታማ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ ነው
Mar 15, 2026 84
ጎንደር ፤መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፡- የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ የሰብልና የፍራፍሬ ዝርያዎችን በማላመድ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ በዩኒቨርሲቲው የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዳንኤል ንጉሴ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኮሌጁ ሥር በተቋቋሙት አራት የምርምር ጣቢያዎች የግብርና ምርምር ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ በዚህም በሽታን፣ ተባይንና የዝናብ እጥረትን በመቋቋም ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ የሩዝ፣ የሽንብራና የቢራ ገብስ ዝያዎችን በምርምር በማውጣት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።   በምርምር የወጡት የሰብል ዝርያዎችም የአካባቢውን ስነ ምህዳር መሰረት ያደረጉና ምርታማነታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ በለሳ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በምዕራብና ምስራቅ ደንቢያ ወረዳዎች በሩዝ ሰብል ከ30 ኩንታል በላይ፣ በሽንብራ ደግሞ እስከ 25 ኩንታል ምርት በሄክታር የሚሰጡ ናቸው ብለዋል። ይህም እስካሁን ከነበረው የአካባቢው የሰብል ዝርያ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የምርት ጭማሬ የሚያስገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል። በፍራፍሬ ልማት ዘርፍም በጎርጎራ አካባቢ ባቋቋመው የምርምር ጣቢያ በመታገዝ የሙዝ፣ የአቮካዶ፣ የማንጎና የፓፓያ ዝርያዎችን በስፋት የማላመድ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡   ኮሌጁ በአዳዲስ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦች ላይ የተመሰረቱ የምርምር ስራዎችን በማከናወን የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አዲስ ስርአተ ትምህርት በመቅረጽ በዲግሪ መርሃ ግብር የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዩኒቨርሲቲው ሥር የግብርና ኮሌጁ ባቀረበልኝ የተሻሻለ የሽንብራ ዘር ተጠቅሜ በማልማት ከራስ ፍጆታ ያለፈ ምርት በማምረት ተጠቃሚ መሆን ችያለሁ ያሉት የምእራብ በለሳ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ታምራት በየነ ናቸው፡፡ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ጣሰው በላይ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ያቀረበላቸውን የሩዝ ዝርያ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት 20 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ የሩዝ ዝርያው ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ ከመሆኑም በላይ በሽታንና የዝናብ እጥረትን በመቋቋም የተሻለ ምርት የሚሰጥ መሆኑን በተግባር ሞክሬ አረጋግጫለሁ ብለዋል፡፡
በአዳማ ከተማ በሦስት ክፍለ ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ ስራ ጀመረ
Mar 14, 2026 99
አዳማ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ሦስት ክፍለ ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ ስራ ጀመረ። የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ታስቦ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በአዳማ ከተማ በሚገኙ አባገዳ፣ ቦሌ እና ዳቤ ክፍለ ከተሞች በይፋ ስራ ጀምረዋል። በማስጀመሪያ ስነ-ሥርዓቱ የተገኙት የፌዴራል ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ(ዶ/ር) እንዳሉት የማዕከሉ ወደ ስራ መግባት በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የነበረውን ችግር እየቀረፈ ነው።   በአዳማ የተጀመረው ተሞክሮ በፌዴራልና በክልሎችም ለማስፋፋት እንደ ምሳሌ የሚወሰድ በመሆኑ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የመሶብ አገልግሎት መልካም አስተዳደርን ከማስፈን ባለፈ ዜጎች ከመንግሥት የሚፈልጉትን አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል መሆኑን ጠቅሰው በአዳማ የተጀመረው ማዕከላቱን የማስፋፋት ስራ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፣ በክልሉ በመጀመሪያው ዙር አገልግሎቱ በተጀመረባቸው ከተሞች ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል። አሁን እየተካሄደ በሚገኘው በሁለተኛው ዙር ማዕከላቱን አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ደግሞ አዳማን ጨምሮ በ26 የክልሉ ከተሞች አገልግሎቱ ስራ ጀምሯል ነው ያሉት።   አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ፣ የመልካም አስተዳደር ችግርንና እንግልትን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል። በሦስተኛ ዙር መርሃ ግብር ደግሞ አገልግሎቱን ወደ 60 ከተሞች ለማስፋፋት የታቀደ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎት የሚያገኝበትን ስርዓት ለመዘርጋት ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። አዳማ ከተማ አገልግሎቱን ቀድማ በማስፋፋት ለክልሉ ምሳሌ ሆናለች ያሉት አቶ አወሉ የህዝቡን የአገልግሎት እርካታ ለማረጋገጥ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ገልጸዋል። በቀጣይም ዜጎች ካሉበት ሆነው በቀጥታ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የሚሰራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው በከተማ ደረጃ ከ130 በላይ አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል እየተሰጡ መሆኑን ገልጸዋል። ዛሬ በተመረቁት ሦስት ክፍለ ከተሞች ደግሞ 110 የሚሆኑ አገልግሎቶች ለህዝቡ ክፍት መሆናቸውን ጠቅሰው ይህም የዜጎችን እርካታ ከመጨመር ባለፈ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ያስችላል ብለዋል።
የፋይዳ የመመዝገብ አቅምን የሚያሳድጉ ሶስት ሺህ አዳዲስ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ወደ ሥራ ሊገቡ ነው
Mar 14, 2026 120
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የመመዝገብ አቅምን የሚያሳድጉ ሶስት ሺህ አዳዲስ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን (ባዮሜትሪክ ኪቶች) በቅርቡ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። እስከ አሁን የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 38 ሚሊየን መድረሱም ተገልጿል። የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰባት ሺህ መመዝገቢያ መሳሪያዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ለማቀላጠፍም ተጨማሪ ሶስት ሺህ የባዮሜትሪክስ ኪቶች ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመካከለኛው ሲስተም ጋር የማናበብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። እነዚህ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ የምዝገባ አቅምን እንደሚያሳድጉ ጠቁመው፤ በአሁኑ ወቅት በሳምንት እስከ አንድ ሚሊየን ዜጎችን መመዝገብ የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም አክለዋል። እስከአሁን ባለው ሂደት የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 38 ሚሊየን መድረሱን አስታውቀዋል፡፡ ዜጎች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት በጣም ባጠረ ጊዜ የፋይዳ መለያ ቁጥራቸው በእጅ ስልካቸው እንዲደርሳቸው እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ መሆኑን ጨምረው ጠቅሰዋል። ምዝገባው በስፋት ተደራሽ እንዲሆን ከባንኮች፣ በኢትዮ-ቴሌኮም ቅርንጫፎች፣ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዲጂታል ሥርዓቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፤ ከባንኮች፣ ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና ከትምህርት ተቋማት ጋር የማስተሳሰር ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በተለይም ህጻናት በትምህርትና በጤና የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ የፋይዳ መታወቂያ እንዲመዘገቡ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ፋይዳን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ያስገቡ ተቋማት አገልግሎታቸውን ማዘመን መቻላቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የማጭበርበር ሙከራዎችን በመከላከል በኩል ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የባንክ ተጠቃሚዎች በፋይዳ አማካኝነት የብድር አገልግሎት የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንና ተቋማት የደንበኞቻቸውን ማንነት በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ አገልግሎታቸውን እንዲያዘምኑ ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡ ከፋይዳ ዋና ዋና ዓላማዎችና ጥቅሞች መካከል ዲጂታል ኢኮኖሚን መገንባት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ ደህንነትና አመኔታ፣ የፋይናንስ አካታችነት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ስፖርት
አካባቢ ጥበቃ
የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው
Mar 16, 2026 96
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ወንዞችን አረንጓዴ በማልበስና የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን አባላት ሀገራት ተወካዮች ገለፁ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን አባል ሀገራት ተወካዮች የአዲስ አበባን የወንዝ ዳርቻ ልማት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የመዲናዋን የወንዞች ዳርቻ በማልማት ከቆሻሻ መጠራቀሚያነት አውጥቶ ወደ ሕዝብ መዝናኛነትና የከተማ ውበት አካል እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን አድንቀዋል። በተለይም የወንዝ ዳርቻዎችን አረንጓዴ በማልበስ የአካባቢ ጥበቃን ከቱሪዝም ጋር የማስተሳሰር ረገድ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት እንደሚሆን ገልጸዋል።   የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ፌሊክስ ሞሲ ንጋምላጎሲ፥ የአፍሪካ ከተሞች የታቀዱ፣ ሳቢ እና የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ አዲስ አበባ በአርዓያነት የምትጥቀስ ናት ብለዋል። በተለይም አሁን ላይ በአዲስ አበባ እየታዩ ያሉ ለውጦች ከተማዋን ለሰዎች መዝናኛና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተመራጭ እያደረጓት መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ካሉ የልማትና የከተማ ውበት ስራዎች ልምድ እንዲቀስሙና ትምህርት እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ከዚምባብዌ የመጡት ቺቶ ፊሪ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ የሕዝብ መዝናኛ ፓርኮች በስፋት ተገንብተው መመልከታቸውን በአድናቆት ጠቅሰዋል።   ይህም ለከተማዋ ድምቀት ከመሆኑ ባለፈ ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች ምቹ የመንቀሳቀሻ ከባቢን የሚፈጥር ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ለእግረኛ መንገድ የተሰጠው ትኩረት ለጤና እጅግ ተስማሚ የሆነውን የእግር ጉዞ ባህል እንደገና ለማነቃቃት ትልቅ ዕድል መፍጠሩንም ነው የተናገሩት።   ከሞዛቢክ የመጡት ማኑኤል ቻጉሎ፤ ከ15 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጎብኝተው እንደነበር በማስታወስ፤ አሁን ድጋሚ ሲመጡ አዲስ አበባ አስድናቂ ለውጥና ዕድገት አስመዝግባ እንዳገኟት ተናግረዋል። ከዚህም ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ልምድ የሚቀሰምበት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቷን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው
Mar 16, 2026 140
አዲስ አበባ፤መጋቢት 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማስተባበር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታከናውነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን ተገለጸ፡፡ ለዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ማጋሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ዙሪያ የምታወራውን በተግባር የምትፈጽም አገር መሆኗን አስመስክራለች። ባለፉት ዓመታት የተተከሉ 48 ቢሊዮን ችግኞች ስኬት ምንጩ የአመራሩና የሕዝቡ ቁርጠኝነት መሆኑን ጠቅሰው መርሃ-ግብሩ ለቀጣዩ ትውልድ ብልጽግና ጠንካራ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ አባላት በኢትዮጵያ ቆይታቸው እነዚህን ተጨባጭ ልምዶች ወደ አገራቸው ይዘው እንደሚሄዱና ኢትዮጵያም ከሌሎች አገራት ልምድ ለመጋራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። የዛምቤዚ ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ፌሊክስ ሞሲ ንጋምላጎሲ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎችን በመተግበር ረገድ ያላትን አህጉራዊ መሪነት በተግባር ማሳየቷን ገልጸዋል።   በተለይም ህዝብን በማስተባበር ረገድ የታየው ስኬት ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ትልቅ ትምህርት እንደሚሆን ጠቁመዋል። ዋና ጸሐፊው አያይዘውም ኢትዮጵያ በግዙፍ መሠረተ ልማቶች ያስመዘገበችውን ስኬት አድንቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ ግቤ 3 እና ኮይሻ ባሉ ፕሮጀክቶች የኃይል ዋስትናንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ለአፍሪካ በተግባር አሳይታለች ብለዋል፡፡ በዛምቤዚ ተፋሰስ ውስጥ እንደ ካሪባ እና ካቦራ ባሳ ያሉ ግድቦች ቢኖሩም፣ አሁንም ጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውኃ ሀብት መኖሩን የጠቀሱት ዋና ጸሐፊው፤ የኢትዮጵያ ታላላቅ የመሠረተ ልማት ተሞክሮዎች ለተፋሰሱ አገራት ትልቅ መነሳሻ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።    
ለ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የላቀ ሀገራዊ ራዕይን በሚያሳካ መልኩ ዝግጅት እየተደረገ ነው
Mar 15, 2026 237
አዲስ አበባ፤መጋቢት 6/2018 (ኢዜአ)፡-ለ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የላቀ ሀገራዊ ራዕይን በሚያሳካ መልኩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረ ሲሆን፤ መርሃ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክሏል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፋኖሴ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለዘንድሮው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዙር የችግኝ ዝግጅት ተጠናቋል። ለስኬታማነቱም በርካታ ቁልፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው፤ ሰባት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዕቅድ መዘጋጀቱን አብራርተዋል። በዚህም እስካሁን ከስድስት ቢሊዮን በላይ ችግኞች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ከችግኞቹ መካከልም 40 በመቶው ሀገር በቀል የደን ችግኞች ሲሆኑ፤ ቀሪው 60 በመቶው ደግሞ እንደ ፍራፍሬ እና የእንስሳት መኖ ያሉ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ናቸው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ 110 ሺህ የችግኝ ጣቢያዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑ ጠቅሰው፤ ከሰባት ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን የመሬት ይዞታ በዲጂታል ጂኦ-ሪፈረንስ ክትትል የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም በአንድ ጀምበር በሚከናወነው ተከላ ላይ የቴክኖሎጂው አጠቃቀም ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡ መርሃ ግብሩ በርካታ ትልልቅ ግቦችን ያነገበ ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል፣ የምግብ ዋስትና፤ ኢኮኖሚና ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ብቻ ሳይሆን የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የተፋሰስ ልማትን እና የአፈርና ውሃ ጥበቃን ያካተተ ሁለንተናዊ የልማት ስትራቴጂ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ ነው
Mar 14, 2026 116
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ የልማት አጀንዳ መሆኑን በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ገለጹ። አምባሳደር አኒል ኩመር ራይ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ችግኞችን በመትከል የካርቦን ልቀትን መቀነስ የሚያስችል ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል። ከብክለት ነፃ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮችን በማስፋት በኩልም ለአየር ንብረት ተፅዕኖ የማይበገር አረንጓዴ የኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ እየወሰደች እንደምተገኝም አንስተዋል። የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬት በምሳሌነት የሚወሰድ የልማት አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አስተማማኝ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታም ለሌሎች የአፍሪካ እና የዓለም ሀገራት ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል። ሕንድም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አስተማማኝ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። በቅርቡ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ መያዣዎች ላይ የእግድ ውሳኔ መተላለፉ ለአካባቢ ደኅንነትና ሥነ-ምኅዳር ጥበቃ ጉልህ ፋይዳ ያለው ወሳኝ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም ሕንድ በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ሥርዓት ያላትን ልምድና ተሞክሮ በማጋራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 145
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።   በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 145
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ደኅንነት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 5, 2026 180
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የኢጋድ የሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ውይይቱን ያደረጉት የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) በመወከል ነው። ውይይቱ ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው። ሁለቱ ወገኖች የጋራ የተግባር ምላሽ ለመስጠት እና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 1793
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ 
Mar 2, 2026 292
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል።   የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል።   የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 339
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።      
   የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 327
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን።   የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው።   የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።   የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት።   የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 14, 2026 1274
ከየካቲት 29 - መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ኢትዮጵያ • ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተመልክተዋል። ማዕከሉ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል • በተመሳሳይ በድሬዳዋ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማኅበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። • የድሬዳዋ የኮሪደር ልማትንም የጎበኙ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬዳዋ ዕውን እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል። • ከድሬዳዋ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር መርሐ-ግብር ያከናወኑት ባለፈው ሳምንት ነው። • በድሬዳዋ የሚገኘውን እመርታ ቤተ-መጻሕፍትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል። ቤተ-መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ ለ1 ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። • በሳምንቱ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ሥራ ተመልክተዋል። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ፤ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ ዕቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል። • የቁንድዶ ተራሮችንም ጎብኝተዋል። • በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከልም ተመልክተዋል። ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር ዐቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል። • በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ናሲኦል ዋሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። • ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር አካሂደዋል። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሹመት መስጠታቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌ/ጄኔራል አሥራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድን እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች አድርገው የሾሙት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካቸው ጋር በጅቡቲ የቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጊሌ በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝታቸውን ቀጥለውም ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚሁ ወቅትም ከፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ✍️ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጋር መምከራቸው • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል። በዚሁ ወቅትም የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት የመደመር መንግሥት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል። • ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዳይሬክተር ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) ጋር በዲጂታል ልማት ያለ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ እና ትብብራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይም የታደሙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምኅሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ኅያው የሕይወት ስንቅ ነው ብለዋል። ✍️ የመሬት ናዳና ጎርፍ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ • ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ የዜጎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል። ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። • ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ያስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። እስካሁንም በአደጋው ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስና መልሶ ለማቋቋም ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገኑ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ✍ ምክር ቤቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማወጁ • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማስመልከት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ዐውጇል። በዚህም መሠረት ትናንት የጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ዐበይት_ጉዳዮች #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 374
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር
Feb 24, 2026 480
(በአየለ ያረጋል) ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፤ ኢትዮጵያና እስራኤል። የሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረው ግንኙነት አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች የተጠናከረ ሆኖ ይገኛል። የሀገራቱ ግንኙነት ግን እንደየስርዓተ መንግስታቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባህሪ መልኩን እየለዋወጠ እና ውጣ ውረዶችን እያለፈ የተሻገረና ጠንካራ መሆኑም ይታወቃል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪካዊ ገጽታ፦ ሃገራቱ የግንኙነታቸው ትርክት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በንግሥተ ሳባ እና በንጉሥ ሰለሞን ዘመነ መንግስት እንደሆነ አፈ ታሪክ ያስረዳል። ይህ አፈ-ታሪካዊ እርሾ ከኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ጋርም ቀጥሏል። በመካከለኛው እና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ሃይማኖትና ንግድ ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አስተሳስሯል። በተለይም ዴር ሱልጣንን ጨምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት መኖር የሁለቱን ሀገራት ባህላዊ ተጋምዶሽ አጎልብቷል። ይህ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ከእስራኤል ሀገረ መንግስት ዳግም መመስረት በኋላም በዘመናዊት ኢትዮጰያ ታሪክም ቀጥሏል። የኢትዮ እስራኤል ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፦ የዘመናዊ የኢትዮ-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተወጠነው በአውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ1956 ሲሆን በ1961 ይፋዊ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል። በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግስት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ ጥቅምን ያማከለና የወቅቱን የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አድርጓል። በንጉሳዊ ስርዓተ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ሌሎች የልማት ቴክኒካል ድጋፍ የደረሰ ወዳጅነት ነበራቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በእስራኤለና አረቦች ጦርነት ሳቢያ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል። ያም ሆኖ በግልጽም ሆነ የህቡዕ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ይወሳል። መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በደርግ መንግስት መጨረሻ ዓመታት (በአውሮፓውያኑ 1989) የኢትዮ-እስራኤል ይፋዊ ግንኙነት ዳግም ተጀምሯል። የ"ኦፕሬሽን ሙሴ" (1984) እና "ኦፕሬሽን ሰለሞን" (1991) የተሰኙ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የማጓጓዝ ተልዕኮዎችም በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ስምምነት የተካሄዱ መሆናቸውን ልብ ይሏል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም) ጀምሮ ደግሞ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጥሏል። በፈረንጆቹ 1992 ኢትዮጵያ በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፍታለች። በፈረንጆቹ 2003 ኢትዮጵያና እስራኤል የኢንቨስትመቶች ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1996 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2004) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አሪኤል ሻሮን ጋር ያደረጉት ታሪካዊ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሳድጎታል። ጉብኝቱን ተከትሎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ያጠናከሩ የተለያዩ ስምምነቶች ተደርገዋል። በተለይም በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከፍ ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትና ፀረ ሽብር ጉዳዮች እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥና የድንበር ጥበቃ ቴክኖሎጂ በትብብር ለመስራት መሰረት ጥለዋል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአዲስ አበባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም መክረዋል። በተመሳሳይ በፈረንጆቹ በ2017 የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ጎብኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በየራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ቆመዋል። በዓለም አቀፍ መድረኮች አንዳቸው ለሌላው ድምጽ በመስጠት ተደጋግፈዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ለብሔረታዊ ጥቅሞቿ መጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እስራኤል አሉታዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይልቁንም እስራኤል ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ እንደ መግቢያ ሁነኛ በር አድርጋ ትቆጥራለች። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮ-አስራኤል ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴካዊ አጋርነት አድጓል። በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በእስራኤል ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ደግሞ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ እንዲታደስ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ታሪካዊ የተሰኘውን ምክክር አድረገዋል። መሪዎቹ በሰጡት ገለጻም በአምስት ነጥቦች ላይ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በውሃ፣ በመስኖ፣ በጤና እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ መፈራረማቸውን አውስተው ነበር። በግብርና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምተው እንደነበርም እንዲሁ። ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ፦ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ልማት በመለወጥ የንግድና ኢንቨስመንት ግንኙነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አከናውነዋል። የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እየጎለበተ መጥቷል። ለአብነትም የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል። በማዕድን ዘርፍ (በፖታሽ)፣ በማምረቻ ዘርፍ( በጨርቃጨርቅ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች) እንዲሁም በጤናና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ ነው። በተለይም በግሪን ሃውስ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በፋርማሲዩቲካል (የመድኃኒት) ዘርፎች ሁነኛ ተሳትፎ አድርገዋል። በተመሳሳይ በንግድ ልውውጥ ረገድ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ እስራኤል በስፋት ትልካለች። በአንጻሩ እስራኤል የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የግብርና ግብዓቶችን (ማዳበሪያና ኬሚካሎች)፣ የሕክምና መሣሪያዎችን እና የደህንነት ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረቅ አካባቢ ግብርና ስመጥር የሆነችው እስራኤል በዘርፉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት አጋር ስትሆን በዘመናዊ መስኖ፣ የአቮካዶና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት እርባታ እና የወተት ምርታማነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች በጎ ተሳትፎ ታደርጋለች። በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወዳጅነት መጠናከር ቤተ-እስራኤላውያን እንደ ድልድይ አገልግለዋል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ160 ሺህ በላይ መሰረታቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላዊያን ዜጎች አሉ። እነዚህ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ሁነኛ ድልድይ ሆነዋል። በተለይም በእስራኤል የሰለጠኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በማስቻል በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በንግድ ስራ ረገድ ውጤታማ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ፈጥጠሯል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸውን ከፍ አድርጎታል። የፕሬዝዳንት ሔርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሃገራት የጸና ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጎለብት እንደሚሆን ይጠበቃል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ የሚያጠናክሩበት ምቹ ሁኔታም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1195
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል።   ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር።   ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ።   ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ   ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ   ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።   ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው።   መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 3683
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2462
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8258
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6741
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60599
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54532
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35101
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32685
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 27801
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 26910
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26430
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26110
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 60599
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 54532
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35101
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 32685
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 539
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ።   እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል።   የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል።   በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል።   ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል።   በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡
ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት
Feb 26, 2026 497
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያደርሰዋል።   ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት አዘርባጃን እ.አ.አ በ1991 ነጻነቷን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። የሀገራቱ ግንኙነት ከእ.አ.አ 1990ዎች መግቢያ አንስቶ እያደገ መጥቷል። አዘርባጃን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ኤምባሲ የከፈተች ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር እንዲጠናከር በር ከፍቷል። በቱርክዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስራ የሚሸፍን ሲሆን ፖለቲካ፣ ትምህርት እና ባህል ሀገራቱ ካላቸው የትብብር መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።   የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል በባለብዙ ወገን መድረክ በገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) መድረክ በትብብር እየሰሩ መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2019 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 18ኛው የገለልተኛ ሃገራት ንቅናቄ (ናም) ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ 120 አባል ሃገራትን ያቀፈና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓለም ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። በሀገራቱ መካከል ተከታታይ የሆኑ የባህል ልውውጥ መድረኮች ተካሄደዋል። ለዚህም እ.አ.አ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአዘርባጃን የትምህርት እድል አግኝተው ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢኮኖሚ አንጻር እ.አ.አ በ2017 በአዘርባጃን የተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ፎረም ተጠቃሽ ነው። በወቅቱ ጨርቃጨርቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በወቅቱ ሀገራቱ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ምጣኔ ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ባለስልጣናት መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እያደጉ መጥተዋል።   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአዘርባጃን ጉብኝት ማድረጋቸወ ይታወሳል። ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም እንዲሁ። ምክክሩ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍና በትብብር መንፈስ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም በወቅቱ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር በነበራቸው ውይይት የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ መክረዋል። በውይይቱም በመረጃ፣ በፀጥታና ደህንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም መስማማታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው ይታወሳል።   እ.አ.አ በ2017 በወቅቱ የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኤልማር ማማድያሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቋሚነት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ማኅበራዊ ፈጠራ ተቋም ሊቀ መንበር ኦልቪ ሜዲዬቭ የብሔራዊ ቤተመንግሥት እና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል። ኦልቪ ሜዲዬቭ በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል።   የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ የተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን የምትልካቸው ምርቶች ብዝኀነትን ለማሳደግና ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ሰሊጥ፣ የተቆላ ቡና፣ ተልባ፣ የፍየል እና የበግ ሥጋን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡   በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ንግድ ትብብር ላይ ያተኮረው ሶስተኛ የኢትዮ-አዘርባጃን የውይይት መድረክ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ከውይይቱ በኋላ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል። 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) በህዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን መካሄዱ ይታወቃል። በጉባኤው ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጋለች። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑክ ከአዘርባጃን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ሀገራቱ በአካባቢ ጥበቃ፣ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገራቱ መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደረጉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ትምህርት እና ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሻሉ።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ እንደሚታይ አንስቷል። የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝትም የዚሁ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጉብኝት በመሪ ደረጃ የሚደረግ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር የቅርብ ዓመታት ውይይቶች እና ጉብኝቶች ማሳያ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም