ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
በድሬዳዋ አስተዳደር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቷል
Oct 6, 2026 29
ድሬዳዋ፣ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት መስጠቱን የአስተዳደሩ ከንቲባ አብዱላሂ አደን አስታወቁ። የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ የውሃ፣ የመንገድ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ከንቲባ አብዱላሂ አደን በወቅቱ እንደገለፁት፤ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቷል። ዘላቂ ሰላምና ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ለዚህም ቀደም ብለው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ከማጠናቀቅ ጎን ለጎን አዳዲስ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ይሸጋገራሉ ብለዋል። ሰው ተኮር የልማት እና የመልካም አስተዳደር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው በጀት እና ጊዜ ለማጠናቀቅም ነዋሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት እንደሚሰራ አንስተዋል። በተለይም በገጠር እና በከተማ የትምህርት እና የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል። የካቢኔ አባላቱም የቢሮ የስራ እንቅስቃሴዎችን፣ የወረዳ እና የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ እና የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታትን ተመልክተዋል።
የተጀመረው ሁለንተናዊ እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመደመር መንግስት ጎን በመሰለፍ የድርሻችንን እንወጣለን
Oct 6, 2026 40
ደሴ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦በመላው ሀገሪቱ የተጀመረው ሁለንተናዊ እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመደመር መንግስት ጎን በመሰለፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ ነዋሪ ሼህ መሐመድ ሰይድ፤ በዘንድሮው ምርጫ ድምፃቸውን የሰጡት የመደመር መንግሥት ሰላምን ለማፅናትና ልማትን ለማጠናከር ሙሉ እምነት ስላላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። መንግሥት ባለፉት ዓመታት ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ ያሳየውን አስደናቂ ብቃት አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ከአዲሱ የመደመር መንግሥት ጎን እንደሚቆሙም ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት፣ የባሕር በር፣ ሰው ተኮር ልማቶችና ሌሎች ኢንሼቲቮችን አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገሪቱን እድገት እውን ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራትም የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ይመር አሊ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በየመስኩ ያስመዘገበው የልማት ውጤትና አፈጻጸም ዳግም ድምፃችንን እንድንሰጠው አድርጎናል ብለዋል። በደሴ ከተማ በኮሪደር ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በከተማ ግብርናና በሌሎች የልማት ሥራዎች እምርታ እየተመዘገበ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በተመሠረተው ምክር ቤት ቀርበው ባስቀመጡት ቀጣይ አቅጣጫ መሠረት የሚከናወኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት እንዲሳኩ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል። መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት፣ ሙስናን ለመከላከልና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ አሠራርን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት የሚደገፍ ነው ያሉት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ሥርካለም አበበ ናቸው። ለዘላቂ ሰላምና ልማት፣ የወል ትርክትንና ሌሎችንም እሴቶች በማጎልበት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩም ጠቁመዋል። በተለይም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሰላምን ለማፅናትና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት መንግሥት እየተከተለው ያለውን አቅጣጫ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኘው ስኬት በበጋውም ተጠናክሮ ይቀጥላል
Oct 6, 2026 50
ገንዳውኃ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኘውን ስኬት በበጋ ወራትም በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ይጠናከራል ሲል የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። በምዕራብ ጎንደር ዞን የክረምት በጎ ፈቃድ ማጠናቀቂያና የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ተካሂዷል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም አረጋ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል እየሆነ መጥቷል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካማ ወገኖችን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ መምጣቱን ጠቁመው፣ አገልግሎቱ የወጣቶችና የሴቶች የልማት ተሳትፎ እያደገ እንዲመጣ ማስቻሉንም ተናግረዋል። በከልሉ በክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች አስተዋጽኦ ላደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበው፣ የበጎ ፍቃድ ተግባራት በበጋ ወቅትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በጎነት ጊዜን፣ ቦታን፣ ብሔርን እና ቀለምን የማይለይ የማህበረሰባችን መገለጫ እሴት ነው። በዚህም በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶችን በበጋ ወራትም ለማስቀጠል አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግሥት እማኘው በበኩላቸው፤ በክረምቱ ከ240 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ300 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዞኑ ነዋሪዎች ከ434 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አስገንዝበዋል። በክረምቱ በበጎ ፈቃደኞች ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች መካከል 240 የአቅመ ደካማ ቤቶችን መጠገንና በአዲስ የመገንባት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል እንዲሁም 521 ዩኒት ደም የመለገስና ሌሎች የልማት ሥራዎችን የማከናወን ሥራዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል። የተገኘውን ተሞክሮ በማስቀጠል በበጋ ወራትም ከ120 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ182 ሺህ በላይ ዜጎችን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል። የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪ ወጣት አድኖ በበኩሉ፤ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ የተለያዩ የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በበጋው ወራትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጸው፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናን በኩታ ገጠም በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል
Oct 6, 2026 102
ዲላ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናን በኩታ ገጠም በማልማት ምርታማነቱን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ገለጸ። በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ በኩታ ገጠም አሠራር የተከናወነ የቡና ልማትና የምርት ዝግጅት የመስክ ምልከታ ተካሄደ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ብሩ በወቅቱ እንዳሉት፣ የልማቱ ዋና ዓላማ ያረጁ የቡና ዝርያዎችን በተሻሻሉ ተክሎች በመተካት የአርሶ አደሮችን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው። የኩታ ገጠም አሠራሩ በሄክታር ከ19 ኩንታል በላይ ምርት ማስገኘት መቻሉን አቶ አማኑኤል ጠቅሰው፣ ይህም ከክልሉ አማካይ የምርት መጠን ከእጥፍ በላይ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የኩታ ገጠም የቡና ልማትን በማስፋት በሁሉም አካባቢዎች ምርታማነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝና የመስክ ምልከታውም የዚሁ አካል መሆኑን አብራርተዋል። በዞኑ ከ2 ሺህ 500 ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም አሠራር በቡና ልማት መሸፈኑን የገለጹት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል ወርቁ ናቸው። በዞኑ ያረጁ የቡና ተክሎችን በመንቀል በተሻሻሉ ዝርያዎች በኩታ ገጠም የማልማቱ ሥራ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የጥምር ግብርና ልማትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተያዘው የምርት ዘመንም ከ38 ሺህ ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የምርት ማሰባሰብና የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በወናጎ ወረዳ ቱማታ ጭራቻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ወጋየሁ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ቡናን በኩታ ገጠም ማልማታቸው የምርት መጠንና ጥራትን ከማሻሻል ባሻገር የሥራ ባህላቸውን እንደቀየረው ጠቅሰዋል። የኩታ ገጠም ልማቱ ዘመናዊ አሠራርን ይዞ በመምጣቱ የመጀመሪያ ምርታቸውን በሁለት ዓመት ውስጥ ማግኘት መቻላቸውን ያነሱት አርሶ አደር ወጋየሁ፣ ይህም ከዚህ ቀደም አምስት ዓመታት ይወስድ የነበረውን ያስቀረ መሆኑን ተናግረዋል። ልማቱ ከቡና እርሻ ባሻገር ለዶሮና ንብ እርባታ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸውም አክለው ገልጸዋል። በመስክ ምልከታው የክልሉ እና ከጎፋ ዞን የመጡ የዘርፉ አመራሮች፣ አምራቾችና አቅራቢዎች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ለዘላቂ ሀገር ግንባታ እንዲውሉ ይደረጋል - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Oct 6, 2026 58
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦችን መሬት በማውረድ ለዘላቂ ሀገር ግንባታ እንዲውሉ ይደረጋል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። የሙስናን አረንቋ የማድረቅ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል። ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል። ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄዱ ይታወቃል። በዚህም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን በመሰየም ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ ሀገራዊ ስትራቴጂክ ግቦችን ለማሳካት የሐሳብ ጥልቀት፣ የእውቀት ደርዝና የሥራ ተነሳሽነት ወሳኝ ኃይሎች ናቸው ብለዋል። በዚህም ኢትዮጵያን በጸና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት በማስቀጠል ዜጎች ለሀገር ብልፅግና በጋራ መንፈስ እንዲተጉ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የነፍጥ አዙሪትንና የአመጽ የፖለቲካ ውርስ በዘላቂነት ለማስቀረት የፖለቲካ ልምምዳችን በሰላም፣ በንግግርና በመደማመጥ ላይ እንዲመሠረት መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አመልክተዋል። የሀገራዊ የምክክር ምክረ ሐሳቦችና የውይይት ውጤቶች ለፖለቲካ ልምምድና ለዘላቂ ሀገር ግንባታ ያላቸው ፋይዳ ተገንዘቦ በዳበሩ ሀገራዊ ሐሳቦች ወደ መሬት እንዲወርዱ ይደረጋል ብለዋል። የኢትዮጵያን ፖለቲካና ማኅበራዊ ንቃት ከፍ በማድረግ ልዩነቶችን በማጥበብ ሰላምና ዕድገት የሰፈነባት ተምሳሌታዊ ሀገር የሚገነባ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ተቋማትን በቁጥጥር ሥርዓት በማጠናከርና ሠራተኞችን በሥነ ምግባር በማብቃት የሙስናን አረንቋ የማድረቅ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል። ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ፣ በኮሪደር ልማት እና በግብርና እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎችን በማስፋት የሕዝብን ተሳትፎ ማዕከል ያደረገ የኢኮኖሚ እድገት ግስጋሴ እንደሚረጋገጥም አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫ ሁለንተናዊ ኃይልን በማጠናከር በቴክኖሎጂ ራስን መቻልን፣ መከላከልን ማሳደግና የውስጥ ጥንካሬን መገንባት መሆኑንም አክለዋል። ጠንካራ የተቋም ግንባታ፣ሰላማዊ የፖለቲካ ውይይት እና ሁለንተናዊ ኃይልን ማጠናከር የሀገሪቱን የነገ ዕድገት እውን የሚያደርጉ አንጡራ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ፖለቲካ

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በተወሰዱ እርምጃዎች የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ያነሷቸው ነጥቦች
Oct 6, 2026 110
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በተወሰዱ እርምጃዎች የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ያነሷቸው ነጥቦች፦ ኢትዮጵያ የግብርና ሥርዓት ይሻሻል ዘንድ በሥራ ላይ ያዋልናቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂና ግብዓቶች፣ የመስኖ መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት በተጨባጭ የተከናወኑ ሥራዎች የአምራች ኢንዱስትሪ አቅማችን ከፍ ማለትና የማዕድን ዘርፍ ልማት መስፋፋት፣ የወጪ ንግድና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በእጅጉ ማደጉ የቱሪዝም መዳረሻዎች መበልጸጋቸውና ኢትዮጵያን የሚጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር መጨመር የዲጂታል መሠረተ ልማት አውታር መስፋፋትና የአገልግሎት ዘርፍ እመርታ ማሳየታቸው በጥቅሉ የኢትዮጵያ አማካይ ኢኮኖሚ ምጣኔ በከፍተኛ መጠን እንዲያድግ ከፍተኛ ሚናና አበርክቶ ነበራቸው።
አዲሱ የኦሮሚያ ክልል የዞን አደረጃጀት መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት ለማስፈን ያስችላል
Oct 6, 2026 88
አዳማ ፤መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የዞን አደረጃጀት በየመስኩ የህዝብ ጥያቄዎችን በመመለስ መልካም አስተዳደርን በዘላቂነት ያሰፍናል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውን የአዳማ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ ፤ ታላቅ ርዕይ የአዳማ ከተማ ባህል ፍርድ ቤት ዳኛና የሀገር ሽማግሌ ጠሃ ሀምዳ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የክልሉ መንግሥት ያወጣውና የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ያጸደቀው አዲሱ የዞን አደረጃጀት በሕዝብ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት ምቹ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል። አሁን የተተገበረው አዲሱ የዞኑ አደረጃጀት ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት በር ከፋች ነውም ብለዋል። የመደመር መንግሥት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ይበልጥ ለማስፋፋት አደረጃጀቱ ምቹ መሆኑንም የሀገር ሽማግሌው ተናግረዋል። በተለይ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ውስንነቶችን አርሞ በቁርጠኝነት ለመጓዝ አዲሱ የዞን አደረጃጀት ወሳኝ መሆኑንና አስታውሰዋል። በአደረጃጀቱ የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የታለመለትን ግብ እንዲመታ እንደ ሀገር ሽማግሌ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉም ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል። ዞኖቹን እንዲያስተዳድሩ የተሰየሙ አመራሮች ህብረተሰቡን በማሳተፍ በልዩ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ከሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ እንደሚችሉ የገለጹት ደግሞ ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ ጥላሁን ራጎ ናቸው። "አዲሱ አደረጃጀት ህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝና በህዝብ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት ስላለን ለተግባራዊነቱም ከመንግሥት ጎን እንቆማለን" ብለዋል። በተለይ አደረጃጀቱ ለህዝብ የቅሬታ ምንጭ የነበረውን የሠላም እጦት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመከላከል መልካም አስተዳደርን እንደሚያሰፍን እምነታቸውን ገልጸዋል። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች መሰረተ ልማቶችን በጥራት እና ባጣረ ጊዜ እውን ለማድረግ አዲሱ የዞን አደረጃጀቱ አይነተኛ መሳሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። የሀገር ሽማግሌ ግርማ ሰንበቶ በበኩላቸው በኦሮሚያ ክልል የተዘረጋው አዲስ የአስተዳደር መዋቅር የመንግስትና ህዝብ የተደመረ አቅምን በማቀናጀት ህብረተሰቡን ያማከለ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። በመደመር መንግሥት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በየአካባቢው የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን አስታውሰው፣ በዚህ ሂደት ያጋጠሙ ውስንነቶችን ነቅሶ በማውጣት በቀጣይ የተሻለ ሥራ ለማከናውን አዲሱ የዞን አደረጃጀት የተሻለ ምህዳር ይፈጥራል የሚል አምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ከአዲሶቹ የዞን አስተዳዳሪዎች ለዘላቂ ሠላም መረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው በመስራት የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎት ማርካት ይኖርባቸዋል ሲሉም አክለዋል።
በመደመር መንግስት የተያዙ እቅዶችና የተነሱ ትልሞች የሀገርን እድገትና የህዝብን ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ ናቸው
Oct 6, 2026 120
ወልዲያ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ) ፡-በመደመር መንግስት የተያዙ እቅዶችና የተነሱ ትልሞች የሀገርን እድገትና የህዝብን ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ መሆናቸው ተመላከተ። የመደመር መንግስት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ የተመሰረተ መሆኑን ተከትሎ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚከናወኑ አበይት ተግባራትን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የዓለምን፣ የአፍሪካንና በተለይም የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚገባውን ዝግጁነት አንስተዋል። በሀገር ብሄራዊ ጥቅምና አጠቃላይ የዲፕሎማሲ አቅጣጫን በተመለከተ፣ በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ የግብርና ልማትና ዲጅታላይዜሽን እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን አንስተዋል። በዚህ ረገድ አዲስ የተመሰረተው የመደመር መንግስት የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ከትናንት መልካም የሆኑትን በመውሰድ እሴት በመጨመር በቀጣይ የተሻለች ሀገር እንገነባለን ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ሃሳቦች ያልዳሰሱት ጉዳይና ያላመላከቱት የወደፊት ትልም የለም ብለዋል። በመሆኑም በመደመር መንግስት የተያዙ እቅዶችና የተነሱ ትልሞች የሀገርን እድገትና የህዝብን ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ አሸናፊ ሰማሁ፤ እንደ ሀገር ባለፉት ጥቂት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችና ተጨባጥ ውጤቶች ለቀጣይ ብሩህ ተስፋ የሰነቁ ስለመሆናቸው አንስተዋል። ከዚህ በመነሳት የመደመር መንግስት ቀጣይ ትኩረት ለሰላምና የህግ የበላይነት መከበር ቅድሚያ በመስጠት በሁሉም ረገድ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ሊያስቀጥል ይገባል ብለዋል። በተለይም በግብርና ልማት፣ በቱሪዝም፣ በዲጅታላይዜሽንና የአገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አንፃር የተመለከትናቸው ጅምሮች ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄያችን ምላሽ እንዲያገኝ የማድረግ ጥረትም የጋራ አጀንዳችን ሆኖ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግን ማናቸውንም የባንዳነት እንቅስቃሴም አጥብቀን መታገል ይኖርብናል ነው ያሉት። ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ሀብታሙ ባቡ፤ የመደመር መንግስት በፈተና ውስጥም ሆኖ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያመጣው ለውጥና ያስመዘገበው ስኬት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በጠቅላላ ምርጫው አሸናፊ በመሆን መንግስት የመሰረተው ብልጽግና ፓርቲ ሀገር የመምራት እድል ማግኘቱ እነዚህን ስኬቶች ለማስቀጠልና እድገቷን ለማረጋገጥ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት፣ የኮሪደር ልማት፣ የግብርና ልማት፣ የቱሪዝም ዘርፍና ሌሎችም የሀገር እመርታዎች መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ስኬት ሊሰራ ይገባል ብለዋል። አዲሱ መንግስት በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ በአገልግሎት ዘርፍና ሌሎችም ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል። ሌሎች አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ገነት ሙልጌታ አዲሱ መንግስት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው የሰላም ጉዳይ መሆን እንዳለበት አንስተው፤ ለዚህም ሁላችንም ባለቤት ሆነን መስራት አለብን ብለዋል።
አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ያደርጋል
Oct 6, 2026 100
አምቦ/ጊምቢ፤ መስከረም 26/2019(ኢዜአ) ፡-የኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ ያደረገው አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ የሚያደርግ መሆኑን የአምቦና የጊምቢ ከተሞች ነዋሪዎች ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአምቦና የጊምቢ ከተሞች ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ አዲሱ አደረጃጀት ሥልጣንን ወደ ታች በማውረድ የአገልግሎት ማዕከላትን ወደ ወረዳና ቀበሌ ደረጃ ለማውረድ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። ይህም የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች በቅርበትና በፍጥነት ለመፍታት እንደሚያስችልም ነዋሪዎቹ አክለዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የአምቦ ከተማ ነዋሪው አቶ አለሙ አበበ፤ አደረጃጀቱ ከዚህ ቀደም በዞኖች ብዛት ይባክን የነበረውን የመንግሥት በጀት ለማስቀረት ይረዳል ብለዋል። ነዋሪው የሚፈልገውን አገልግሎት ለማግኘት ያወጣ የነበረውን አላስፈላጊ ጉልበትና ወጪ በማስቀረት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው ያለ ምንም እንግልት እንዲያገኝ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል። በመደመር እሳቤ የተጀመሩና በኦሮሚያ ክልል ተግባራዊ የተደረጉ አሠራሮች ክልሉን በምግብ ራስን ከመቻል አልፎ ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ እንዳበቁት ሁሉ፣ አዲሱ አደረጃጀትም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ በየነ ጫላ በበኩላቸው፤ ዞኖችን በአዲስ መልክ የማደራጀቱ ውሳኔ የመንግሥት አካላትን ቅንጅታዊ አሠራርና ብቃት የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ተመሳሳይና ተደጋጋሚ አሠራር ያላቸውን ተቋማት በአንድ የተቀናጀ መዋቅር ሥር በማምጣት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል ያለውን የሥራ ቅንጅትና አፈጻጸም እንደሚያሳድገው ጠቁመዋል። ወይዘሮ ወርቅነሽ አጀማ የተባሉ ነዋሪ በተመሳሳይ፤ አዲሱ የዞኖች መዋቅር የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ቀደም ሲል የነበሩ የአስተዳደርና የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። አደረጃጀቱ ብልሹ አሠራሮችን በማስቀረት የክልሉን ዞኖች በተሻለ ሁኔታ ለመምራት፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስና ውስጣዊ የአሠራር ግድፈቶችን በብቃት ለመቆጣጠር ያስችላል ብለዋል። የጊምቢ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ኤብሴ ታዬ፤ አዲሱ የዞን አደረጃጀት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች እንዲፋጠኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ተግባራዊ የተደረገው የዞኖች አደረጃጀትም ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አክለዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ አብዲሳ ተፈሪ በበኩላቸው በክልሉ መንግሥት የተወሰደው የዞኖች አደረጃጀት እርምጃ ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል። የላሎ አሳቢ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘሮ መሠረት ጎቤና፤ ዞኖች በአዲስ መዋቅር እንዲደራጁ መደረጉ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ከዚህ ቀደም 21 የነበሩትን ዞኖች ወደ 6 ዞኖች በአዲስ መልክ እንዲደራጁ ማድረጉ ይታወቃል።
ምክር ቤቶቹ የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራ በብቃት በመወጣት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋገር ይጠበቅባቸዋል - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Oct 6, 2026 155
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ምክር ቤቶቹ የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራ በብቃት በመወጣት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋገር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄዱ ይታወቃል። በዚህም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤዎቻቸውን በመሰየም ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው እንደገለጹት፤ የታላቁ ህዝብ ምክር ቤት የመንግስት ስልጣን መሰረቱ እና ምንጩ የሰፊው ህዝብ የይሁንታ ድምጽ መሆኑ የሚረጋገጥበት ሕያው ምስክር ነው። የህዝብ ምክር ቤት አባላት የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የሚደነግጓቸው ህጎች በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የስልጣን ፍኖት በህዝብ የይሁንታ ድምጽ እና ተቀባይነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አመልክተው፤ ሕዝብ የጣለባችሁ ሀገራዊና ህዝባዊ ሀላፊነት በእጅጉ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ስለዚህ የህዝቡ ይሁንታ ከአመኔታ ጋር ታላቅ አደራን መስጠቱን እንደሚያረጋግጥ አመልክተው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ሀላፊነት በታላቅ አስተዋይነት፣ ጥበብ፣ ብልሃትና ታታሪነት እንደምትወጡት ያምናል ብለዋል። ሁለንተናዊ ዝግጅታችሁ ይህንን አደራ የሚመጥን ብቻ ሳይሆን ከፍ ወደአለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ጭምር ሊሆን ይገባል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው። የምክር ቤት አባላቱ ቀዳሚ ትኩረት መልካም አስተዳደርን የሚያዘምን፣ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በይበልጥ ከፍ የሚያደርግ፣ ምርት እና ምርታማነትን የሚያሳድግ፣ የኑሮ ውድነትን የሚገራ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ይበልጥ የሚያስፋፋ፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን በስፋት የሚዘረጋ፣ የህዝብን ሰላም እና ደህንነት የሚያጸና መሆን እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀላፊነት ነው - ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
Oct 6, 2026 136
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስጠበቅና ብልፅግናን ማረጋገጥ የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀላፊነት ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄዱ ይታወቃል። በዚህም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን በመሰየም ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ተሰይመዋል። በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ መርሐ ግብር ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር፤ ሀገሪቱ በየዘመኑ ሲንከባለል የመጣው የአመፅ ፖለቲካ ተግባር የሚያከትምበት እና የልማትና የሰላም ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ላይ ደርሳለች፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምና የተረጋግቶ የመኖርን ዋጋ በጥልቅ የሚያውቅ፣ የጦርነትን ክፋትና አጉዳይነት በጉልህ የሚረዳና የሚጠየፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፉትና በታከቱ እሳቤዎች ሕዝብን ወደ አመፅ አዙሪት ለማስገባት የሚደረጉ ማናቸውም ሙከራዎች መደምደሚያቸው መቃረቡንም አስገንዝበዋል። የሁከት ኃይሎች በየጊዜው የጋረጧቸውን ፈተናዎች መንግስት በትዕግስት፣ በስክነት፣ በብርታት እና በጥብቅ ኃይል ጭምር ማምከን መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያን የሚመጥናት ጎዳና ዕድገት፣ ብልጽግና እና አንድነት በመሆኑ መንግስትና ማህበረሰቡ የሴራንና የግጭት ነጋዴዎችን አምርረው እንደሚታገሉ አረጋግጠዋል። የታላቅ ሀገርና የነባር ስልጣኔ ባለቤት የሆነ ህዝብ መገለጫ ሀገርን ማጽናት፣ ሉዓላዊነትን ማስከበር እና ሰላምን መጠበቅ በመሆኑ የተጀመሩት የምርት ጉዞዎች ያላንዳች ማወላወል እንደሚቀጥሉ በስራና በትጋት ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። የኢትዮጵያዊነት እሳቤ በየእያንዳንዱ ጋሬጣ የሚደናቀፍ አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ታላቁን ሀገራዊ ርዕይ እና አቅም ከፍ አድርጎ በማየት ላይ ያተኮረ መሆን እንደሚገባው አመልክተዋል። በዚህ መንገድ የተጀመሩ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕይታዎች የታላቅነት ሀሳብ የወለዳቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ምንጊዜም ከእውነት እና ከታሪክ ትክክለኛ ጎን የሚሰለፍ አስተዋይ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ መንግስት ይህንኑ እሴት ያከብራል፣ ይጠብቃል ብለዋል። ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ሰላም መጠበቅ እንዲሁም ብልፅግናዋን ማረጋገጥ የመንግስት ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንኑ ጥሪት ጠብቆ የማቆየት፣ የማስቀጠል እና የማሻሻል የጋራ ሀላፊነት መሆኑን አመልክተዋል።
የኢትዮጵያን የታላቅነት መንገድ የሚያስፉ አስተማማኝ ተቋማት እየተገነቡ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
Oct 6, 2026 109
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የታላቅነት መንገድ የሚያስፉ አስተማማኝ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት እየተገነቡ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገልጸዋል። ሰባተኛው የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ማካሄዱ ይታወቃል። በዚህም የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎቻቸውን በመሰየም ሥራቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ተሰይመዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በምክር ቤቶቹ የጋራ መክፈቻ መርሐ ግብር ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በውስጥና በውጭ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በመቋቋም ጠንካራ ተቋማትን እየገነባች ነው ብለዋል። በስትራቴጂክ እይታ የሚመሩ ጠንካራ ተቋማት ግንባታ ተግባራትም በሕዝብ አንድነት ላይ የተመሰረተ ታላቅ ሀገራዊ ስኬትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች መሆኑ ገልጸዋል። መንግሥት የኢትዮጵያን የትልቅነት መንገድ የሚያስፉ ዘላቂና ሁለንተናዊ ተቋማትን በማደራጀት የላቁ አቅጣጫዎችንና ተግባራትን ቀይሶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በዚህም የኢትዮጵያን የታላቅነት መንገድ የሚያስፉ አስተማማኝ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት እየተገነቡ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደትም ማህበራዊ እሴቶችን በማስተሳሰርና በሃሳብ የበላይነት በማመን ሕብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያንና ጠንካራ ወንድማማችነትን ለማረጋገጥ መሰረት እንደጣለ አንስተዋል።

ማህበራዊ
በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኘው ስኬት በበጋውም ተጠናክሮ ይቀጥላል
Oct 6, 2026 50
ገንዳውኃ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገኘውን ስኬት በበጋ ወራትም በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ይጠናከራል ሲል የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። በምዕራብ ጎንደር ዞን የክረምት በጎ ፈቃድ ማጠናቀቂያና የበጋ ወራት የበጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ተካሂዷል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም አረጋ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ባህል እየሆነ መጥቷል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት አቅመ ደካማ ወገኖችን በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል። በተጨማሪም በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ መምጣቱን ጠቁመው፣ አገልግሎቱ የወጣቶችና የሴቶች የልማት ተሳትፎ እያደገ እንዲመጣ ማስቻሉንም ተናግረዋል። በከልሉ በክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች አስተዋጽኦ ላደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበው፣ የበጎ ፍቃድ ተግባራት በበጋ ወቅትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በጎነት ጊዜን፣ ቦታን፣ ብሔርን እና ቀለምን የማይለይ የማህበረሰባችን መገለጫ እሴት ነው። በዚህም በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶችን በበጋ ወራትም ለማስቀጠል አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግሥት እማኘው በበኩላቸው፤ በክረምቱ ከ240 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ300 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዞኑ ነዋሪዎች ከ434 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አስገንዝበዋል። በክረምቱ በበጎ ፈቃደኞች ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች መካከል 240 የአቅመ ደካማ ቤቶችን መጠገንና በአዲስ የመገንባት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ችግኞችን የመትከል እንዲሁም 521 ዩኒት ደም የመለገስና ሌሎች የልማት ሥራዎችን የማከናወን ሥራዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል። የተገኘውን ተሞክሮ በማስቀጠል በበጋ ወራትም ከ120 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ182 ሺህ በላይ ዜጎችን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል። የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪ ወጣት አድኖ በበኩሉ፤ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ የተለያዩ የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን በበጋው ወራትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጸው፡፡
ሆስፒታሉ በመደበኛና በዘመቻ በሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው
Oct 6, 2026 84
ባህር ዳር፤ መስከረም 26/2019(ኢዜአ)፡-የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህሙማንን ህይወት ለመታደግ በዘመቻ የቀዶ ህክምና እንዲያገኙ ማድረጉን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብይ ፍሰሃ ገለጹ። ከአሜሪካ፣ ከሀንጋሪ፣ ከፖርቹጋል፣ ከስፔንና ሌሎች አገራት የተውጣጡ ሀኪሞች በዘመቻው ተሳታፊ ሆነዋል። "የኦፕሬሽን ኢንተርናሽናል" የበጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች ቡድን በፈለገ ህይወት ሆስፒታል በዘመቻ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና እየሰጠ ይገኛል። የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብይ ፍሰሃ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዘመቻው በተራዘመ ቀጠሮ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ህሙማንን ህይወት ለመታደግ ሁለንተናዊ ጥረት እያደረገ ነው። በዘመቻው ከአንገት በላይ፣ የጽንስና ማህፀን አጠቃላይ ቀዶ ህክምና በከፍተኛ ባለሙያዎች በነፃ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሆስፒታሉ ከውጭ ሀገራት ሀኪሞች ጋር በመተባበር በሚሰጠው ህክምና ህሙማን ፈጣን የቀዶ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስትና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር የሰውበላይ ምንአለ በበኩላቸው፤ ለሰባት ቀናት በዘመቻ በሚካሄደው የቀዶ ህክምና በተራዘመ ቀጠሮ ላይ የነበሩ ከ100 በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። ቡድኑ ከፍተኛ የቀዶ ህክምናውን በነጻ ከመስጠቱ ባሻገር ለሆስፒታሉ ዘመናዊ የህክምና ማሽኖችን፣ መድኃኒቶችንና ሌሎች ግብአቶችን በእርዳታ ማበርከቱን አስረድተዋል። ከቡድኑ አባላት መካከል ከሀንጋሪ የመጡት ዶክተር ኖቫክ አንድራስ (Novak Andras) እንደገለጹት፤ የአንጀት፣ የፊንጢጣና ሌሎች በሽታዎች ለሚሰቃዩ ወገኖች የቀዶ ጥገና ህክምና እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። በዘመቻው ባለቤታቸው ከፍተኛ የእንቅርት በሽታ በቀዶ ህክምና ተወግዶላቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ይርጋለም ተገኘ ናቸው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ህክምናውን ለማግኘት እንደሞከሩ አመልክተው የቀዶ ህክምናው በዘመቻ መካሄዱ ባለቤታቸው ከሕመም እንዲያገግሙ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል እስከ 15 ሚሊዮን ለሚጠጋ ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት አለበት
Oct 5, 2026 297
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሁሉም ዜጎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶች አባቶችና እናቶች ለሀገር እድገትና አንድነት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። በጫካ የሚገኙ የታጠቁ አካላት ይህንን ታሪካዊ እድል በመጠቀም ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቅሬታ ያላቸው ወገኖችም የይቅርታን መንፈስ ተላብሰው በሀገር ግንባታ ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔራዊ ጥቅም ላይ በጋራ የመቆም እና በአማራጭ ሀሳቦች የመፎካከር ባህልን ማሳደግ እንዳለባቸውም ጠቁመዋል። አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ መዘጋጀት እንዳለበት ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፤ የዛሬ ወጣቶች በሩቅ አሳቢነት ነጋቸውን እንዲቀርጹ አሳስበዋል። የትናንት ወጣቶች ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአብዮታዊ የትግል ስልትና ከባንዳነት ልምምድ በመራቅ የተጣሉትን ለማስታረቅና የሸሹትን ለመመለስ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሀገር አባቶችና እናቶችም ለነገዋ ኢትዮጵያ ታላቅነትና ስልጣኔ በመጸለይ ታሪካቸውን ማውረስና ትውልዱን መገንባት እንደሚገባቸው ገልጸዋል። "ትናንት አልፏል፤ ነገም ገና አልደረሰም፤ ዛሬ ግን ምቹ ሆኖ ቀርቧል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬን በትጋት በመስራት ትናንትን ማስተካከል እና የፈለግነውን ዓይነት ብሩህ መንገድ መቅረጽ እንደሚቻል አስገንዝበዋል። ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኖረው ቆይታ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመጠየቅና ከመደገፍ ባሻገር የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ የህዝቡን ህይወት ምን ያህል እንደለወጡና የመደመር ስልጣኔን ምን ያህል እንዳሳኩ በቅርበት እንዲከታተልና እንዲመራም አደራ ብለዋል።
ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኩል ስንራመድ ብቻ ነው
Oct 5, 2026 292
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፦ ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኩል ስንራመድ ብቻ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምርጫ አካሂደን፣ በህጋዊ ምርጫ እምነት ጥለው፣ በድምጻቸው መንግስት ለማጽናት በተግባር ለታመኑ ዜጎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል። ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ፣ የዲሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ያሳለፍነው ምርጫ እንደማንኛውም ህዝባዊ ምርጫ ተካሄደ ተብሎ ብቻ የሚገለጽ የሰርክ ኹነት አልነበረም ብለዋል። ዜጎች በምርጫው ፈቃዱን ሊሰጥ የቻለው በብዙ ውዥንብሮች መካከል አልፎ እንደነበርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል። በየጫካው የሸመቁበት፣ በየሚዲያው እያዋከቡት፣ በአሉባልታ እያስፈራሩት፣ በብዙ ፈተናዎች መካከል አልፎ ህልውናውን ለማጽናት ህዝቡ ፈቅዶ መርጧል ብለዋል። አጠቃላይ ሂደቱ የዴሞክራሲ ባህል መሰረቱ እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ አሳይቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ወደፊት ታሪክ በደማቅ ብዕር እንደሚጽፈው፣ ትውልድም ደጋግሞ እንደሚዘክረው ጥርጥር የለኝም በማለት ገልጸዋል። ማንኛውም ምርጫ አሸናፊ እና ተሸናፊ ፓርቲ ሊኖረው ይችላል፤ ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል። ሀገራችን የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች መሻገር የምንችለው በወንድማማችነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን እኪል ስንራመድ ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፤ ዛሬ ዘመኑ ተቀይሯል ነገሮች እንደ ድሮ አይደሉም ብለዋል። ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ ዓለምአቀፋዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እንደሚለዋወጡ ጠቅሰው፤ ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ወዲህ የዓለም ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መልኮች በፈጣን ለውጥ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። ዓለም በጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎቿ ምክንያት መልክ እና ጠባይዋ መቀያየሯን ጠቁመው፤ አይገመቴነት የዘመኑ ዋነኛ መገለጫ እየሆነ ነው፤ ቋሚ አሰላለፍ ማየት ብርቅ ሆኗል ብለዋል። የባለብዙ ዓለም ዋልታ ሊወለድ በሚታገልበት በዚህ ወቅት ጎራ መርጦ ማንም እንደማይቆምና የትኛውም ፖለቲካዊ እሳቤ በዓለም ላይ እንደሚነግስ ከግምት በዘለለ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይቻልም አስገንዝበዋል። ታሪክ ወደ የትኛው አዲስ ምዕራፍ እንደሚያደርሰን በግልጽ በማይታወቅበት መንታ መንገድ ላይ እንገኛለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲስ ነገር ዕዳም፣ ምንዳም አለው፤ ዕዳ እና ምንዳው ግን ለሁሉም እኩል አይደለም ነው ያሉት። መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው፣ የሚመጣውን አዲስ ነገር ከወዲሁ ገምተው፣ በጥንቃቄ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ መሆኑን ጠቁመው፤ በአንጻሩ ዘግተው እና ተዘናግተው ለሚቆዩ ደካሞች ዕዳው እልፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የሀገራችን አርሶ አደርም «መጪው ክረምት የሚጠቅመው ላረሰው ገበሬ ነው» እንደሚል ገልጸው፤ ከሁለቱ አማራጮች ለሀገራችን የሚበጀውን መንገድ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቁ አደራ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢኮኖሚ
በድሬዳዋ አስተዳደር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቷል
Oct 6, 2026 29
ድሬዳዋ፣ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት መስጠቱን የአስተዳደሩ ከንቲባ አብዱላሂ አደን አስታወቁ። የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኙ የውሃ፣ የመንገድ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ከንቲባ አብዱላሂ አደን በወቅቱ እንደገለፁት፤ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቷል። ዘላቂ ሰላምና ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ለዚህም ቀደም ብለው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ከማጠናቀቅ ጎን ለጎን አዳዲስ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ይሸጋገራሉ ብለዋል። ሰው ተኮር የልማት እና የመልካም አስተዳደር ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው በጀት እና ጊዜ ለማጠናቀቅም ነዋሪዎችንና ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት እንደሚሰራ አንስተዋል። በተለይም በገጠር እና በከተማ የትምህርት እና የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል። የካቢኔ አባላቱም የቢሮ የስራ እንቅስቃሴዎችን፣ የወረዳ እና የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ እና የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታትን ተመልክተዋል።
የተጀመረው ሁለንተናዊ እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመደመር መንግስት ጎን በመሰለፍ የድርሻችንን እንወጣለን
Oct 6, 2026 40
ደሴ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦በመላው ሀገሪቱ የተጀመረው ሁለንተናዊ እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመደመር መንግስት ጎን በመሰለፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደሴ ከተማ ነዋሪ ሼህ መሐመድ ሰይድ፤ በዘንድሮው ምርጫ ድምፃቸውን የሰጡት የመደመር መንግሥት ሰላምን ለማፅናትና ልማትን ለማጠናከር ሙሉ እምነት ስላላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። መንግሥት ባለፉት ዓመታት ሜጋ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ ያሳየውን አስደናቂ ብቃት አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ከአዲሱ የመደመር መንግሥት ጎን እንደሚቆሙም ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት፣ የባሕር በር፣ ሰው ተኮር ልማቶችና ሌሎች ኢንሼቲቮችን አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገሪቱን እድገት እውን ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራትም የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። አቶ ይመር አሊ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በየመስኩ ያስመዘገበው የልማት ውጤትና አፈጻጸም ዳግም ድምፃችንን እንድንሰጠው አድርጎናል ብለዋል። በደሴ ከተማ በኮሪደር ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በከተማ ግብርናና በሌሎች የልማት ሥራዎች እምርታ እየተመዘገበ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በተመሠረተው ምክር ቤት ቀርበው ባስቀመጡት ቀጣይ አቅጣጫ መሠረት የሚከናወኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግባራት እንዲሳኩ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል። መንግሥት በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት፣ ሙስናን ለመከላከልና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ አሠራርን ለማስፈን የሚያደርገው ጥረት የሚደገፍ ነው ያሉት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ሥርካለም አበበ ናቸው። ለዘላቂ ሰላምና ልማት፣ የወል ትርክትንና ሌሎችንም እሴቶች በማጎልበት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩም ጠቁመዋል። በተለይም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሰላምን ለማፅናትና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት መንግሥት እየተከተለው ያለውን አቅጣጫ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናን በኩታ ገጠም በማልማት ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል
Oct 6, 2026 102
ዲላ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናን በኩታ ገጠም በማልማት ምርታማነቱን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ገለጸ። በጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ በኩታ ገጠም አሠራር የተከናወነ የቡና ልማትና የምርት ዝግጅት የመስክ ምልከታ ተካሄደ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ብሩ በወቅቱ እንዳሉት፣ የልማቱ ዋና ዓላማ ያረጁ የቡና ዝርያዎችን በተሻሻሉ ተክሎች በመተካት የአርሶ አደሮችን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው። የኩታ ገጠም አሠራሩ በሄክታር ከ19 ኩንታል በላይ ምርት ማስገኘት መቻሉን አቶ አማኑኤል ጠቅሰው፣ ይህም ከክልሉ አማካይ የምርት መጠን ከእጥፍ በላይ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም የኩታ ገጠም የቡና ልማትን በማስፋት በሁሉም አካባቢዎች ምርታማነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝና የመስክ ምልከታውም የዚሁ አካል መሆኑን አብራርተዋል። በዞኑ ከ2 ሺህ 500 ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም አሠራር በቡና ልማት መሸፈኑን የገለጹት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል ወርቁ ናቸው። በዞኑ ያረጁ የቡና ተክሎችን በመንቀል በተሻሻሉ ዝርያዎች በኩታ ገጠም የማልማቱ ሥራ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የጥምር ግብርና ልማትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በተያዘው የምርት ዘመንም ከ38 ሺህ ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የምርት ማሰባሰብና የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በወናጎ ወረዳ ቱማታ ጭራቻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ወጋየሁ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ቡናን በኩታ ገጠም ማልማታቸው የምርት መጠንና ጥራትን ከማሻሻል ባሻገር የሥራ ባህላቸውን እንደቀየረው ጠቅሰዋል። የኩታ ገጠም ልማቱ ዘመናዊ አሠራርን ይዞ በመምጣቱ የመጀመሪያ ምርታቸውን በሁለት ዓመት ውስጥ ማግኘት መቻላቸውን ያነሱት አርሶ አደር ወጋየሁ፣ ይህም ከዚህ ቀደም አምስት ዓመታት ይወስድ የነበረውን ያስቀረ መሆኑን ተናግረዋል። ልማቱ ከቡና እርሻ ባሻገር ለዶሮና ንብ እርባታ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸውም አክለው ገልጸዋል። በመስክ ምልከታው የክልሉ እና ከጎፋ ዞን የመጡ የዘርፉ አመራሮች፣ አምራቾችና አቅራቢዎች ተገኝተዋል፡፡
የተጀመሩ የልማት ኢኒሼቲቮችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ሥራ ይጠናከራል
Oct 6, 2026 118
ሮቤ፣መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ የተጀመሩ የልማት ኢኒሼቲቮችን በማጠናከር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ሥራ እንደሚጠናከር የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳደር ገለጸ። በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ኢድሪስ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በዞኑ አጋርፋ ወረዳ በመገኘት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን በመስክ ተመለከቱ። አቶ አህመድ ከጉብኝቱ በኋላ ስለ አዲሱ አደረጃጀት፣ በመሬት ላይ ስለሚታዩ ነባራዊ ሁኔታዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለኢዜአ አስተያየት ሰጥተዋል። አስተዳዳሪው በወቅቱ በሰጡት አስተያየት፣ የክልሉ መንግሥት የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል ተግባራዊ ያደረጋቸው የልማት ኢኒሼቲቮች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተለይም በኩታ ገጠም አሠራር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የግብርና ሥራዎች የአርሶ አደሩን ምርታማነትና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን በመስክ ምልከታቸው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በአርሶ አደሩ ምርት ላይ ተጨማሪ እሴት በመፍጠር በተደራጀ መልኩ ወደ ገበያ እንዲቀርቡና አርሶ አደሩ ከምርቱ የተሻለ ጥቅም እንዲያገኝ የሚያስችሉ የፓስታና ማካሮኒ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የሚበረታቱና በቀጣይም ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል። የተጀመሩትን የግብርናና ሌሎች የልማት ኢኒሼቲቮች በተሻለ መልኩ በማጠናከር የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። የክልሉ መንግሥት ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ያደረገው የቀበሌና የወረዳ አደረጃጀት ሕዝቡ በአስተዳደር ሥርዓቱ የበለጠ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉንም አቶ አህመድ አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልኩ ተግባራዊ የተደረገው የዞን አደረጃጀት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥና ከዚህ ቀደም የተጀመሩ መልካም ሥራዎችን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። አደረጃጀቱ ነዋሪው ከአካባቢው ሳይርቅ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝና የልማት ተሳትፎውን እንዲያጠናክር እንደሚያግዝም ተናግረዋል። በክልሉ ከዚህ ቀደም በላይኛው የአደረጃጀት እርከን አካባቢ ተከማችቶ የነበረው የውሳኔ ሰጪነት ተግባር በተጠና መልኩ በየደረጃው ወደ ተደራጁ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌዎች ተደራሽ እንዲሆን ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አመልክተዋል። በተለይም የገጠርና የከተማ ትስስርን ማጠናከር፣ የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠንና የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በአምስት ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ከተያዙ ቁልፍ ግቦች መካከል መሆናቸውነ አቶ አህመድ አብራርተዋል።።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲው የሳይንስ ባህል ግንባታን የሚያጠናክሩ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል
Oct 5, 2026 150
አዲስ አበባ፤ መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታዳጊዎች ላይ በትኩረት በመስራት የሳይንስ ባህል ግንባታን የሚያጠናክሩ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ገለፁ። ዩኒቨርሲቲው የዲጂታላይዜሽን ዘርፉን የሚመሩ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዩኒቨርሲቲው የታዳጊዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት የሚያሳድጉ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። ዩኒቨርሲቲው በክረምት ወቅት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን አንስተው፤ ባለው የስቴም ማዕከልም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የተማሩትን በተግባር የሚያዩበትና የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ተማሪዎች የሚጎበኙት የሳይንስ ሙዚየምም የሳይንስ ክህሎትን ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የልህቀት ማዕከላት ፈጠራን የሚያበረታቱ በመሆናቸው በተማሪዎችና መምህራን የተሰሩና ወደ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገሩ የፈጠራ ስራዎች መኖራቸውን አስረድተዋል። የዩኒቨርሲቲው የኢኖቬሽንና ኢንኩቤሽን ማዕከልም የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብና ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያሉ ተሰጥኦ ያላቸውን ሰዎች ሀሳብ ወደስታርት አፕ ለመቀየር ብሎም ሀብት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል። በስኬት የተጠናቀቀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ ለማድረግ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ትግበራም ለምርምር ተቋማት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፣ ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት አብርሃም ደበበ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሳይንስ ባህል ግንባታ ላይ ለዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። የስቴም ትምህርቶችን ከዚህ ቀደም ከዘጠነኛ ክፍል ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው፤ የሳይንስ ባህል ግንባታውን ወደታችኛው የትምህርት ደረጃ ለማስፋት በማሰብ በአሁኑ ወቅት ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች መካተታቸውን አስረድተዋል። በቅርቡም የማህበረሰብ ትምህርት ቤት መክፈቱ ከመዋዕለ ህፃናት ጀምሮ ተማሪዎች ሳይንስና ቴክኖሎጂን እንዲገነዘቡ የሚያስችል ነው ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለውን የሳይንስ ሙዚየም ተማሪዎችን እንደላቦራቶሪ እገዛ እያደረገ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የዲጂታላይዜሽን ዘርፉን የሚመሩ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ጋር በመተባበር በሰው ኃይል ልማት ላይ እየሰራ ነው ብለዋል።
ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል
Oct 3, 2026 185
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። የአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ዜጎች ተገቢው የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው በማድረግ ስራ እና ሀብትን በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማጠናከር ተግባራዊ የተደረገ ፕሮግራም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ5 ሚሊየን የኮደርስ መርሐ ግብር ወደ 7 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ስዩም መንገሻ እንደገለጹት፤ በዲጂታል ኢትዮጵያ የስኬት ጉዞ በዋናነት ትልቁ የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ማጎልበት ነው። የኮደርስ ስልጠና የዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሲጀመር አምስት ሚሊዮን ዜጎችን ስልጠና እንዲወስዱ መታቀዱን አንስተው፤ ከታቀደው በላይ ለማሳካት በመቻሉ ሰባት ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ ዜጎች ቁጥር 5 ነጥብ 4 ሚሊየን መድረሱን ገልጸው፤ በዚህም ክህሎታቸውን ማሳደግና በኦን ላይን የስራ እድል ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበታቸውን ተናግረዋል። የኮደርስ ስልጠናው መሰረታዊ ነው፤ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ መንደርደሪያ፣ መስፈንጠሪያ ነው ሲሉም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድጉ ተግባራትን እያከናወነች መሆን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ዲጂታላይዜሽን በማስፋፋት ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶች ተጨባጭ ለውጦች መገኘታቸውንም ገልጸዋል። የዲጂታል ክህሎት ሀገርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ግብዓት በመሆኑ በዘርፉ ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለጹት። የኢትዮ ኮደርስ ዜጎች የዲጂታል ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸው፤ በቀጣይም እንደዚሀ አይነት ስልጠናዎች በላቀ ደረጃ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርትአፕ ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርት አብይ ታደሰ በበኩሉ በኢትዮ ኮደርስና በሌሎች ኢኒሼቲቮች ስታርት አፖችን መደገፍ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። የኮደርስ ስልጠና መሰረታዊ ክህሎትን ለማስጨበጥና የስራ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በኤ. ይ ዘርፍ የወጣቶችን ክህሎት የሚያዳብሩ ወደ ስታርት አፕ እንዲገቡ የሚያስችሉ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ነው የገለጸው። ወጣቶች በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ክህሎታቸውን ማሳደጋቸው ለስራ ፈጠራና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል። በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይበር ሴኪዩሪቲ ኦዲተር ማርታ ሀዲስ አራቱንም ኮርሶች መውሰዳቸውንና በዘርፉ የነበራቸውን እውቀት ለማዳበር እንደጠቀማቸው ገልጸዋል። ኢኒሼቲቩ ለወጣቶች በጣም ትልቅ እድል ነው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን፣ ክህሎትን ለማሳደግ ከወቅቱ ጋር ለመራመድ መሰረታዊ ስልጠና ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሰው ሰራሽ የታገዙ ስራዎች እየተስፋፉ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ኮርሶቹ ለቀጣይ የስራ እድሎችና ሙያን ለማሳደግ መሰረት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ ነው
Oct 1, 2026 331
አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2019(ኢዜአ)፡-የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ባላት ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በሁሉም መስክ የሀገርን ማንሰራራት የሚያበስር እመርታዊ ውጤት እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የ50 ዓመታት የምርምር፣ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ጉዞን እና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ለሦስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ማጠናቀቂያም የኢትዮጵያ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ማበልፀጊያ ኢንስቲትዩት የቡራዩ ተሰጥኦ ልማት ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን አስመርቋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችን በማሰልጠን የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል የሰው ኃይል እያፈራ ነው። በትምህርት ቤቱ ሥልጠና የሚሰጣቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችም ከፍተኛ የማሰብ፣ የማገናዘብና የመተንተን አቅማቸውን ታሳቢ ባደረጉ መስፈርቶች ተመልምለው የሚሰለጥኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ታዳጊዎች የፈጠራ ክህሎትና ልዩ ተሰጧቸውን በማበልጸግ ችግር ፈቺ የመፍትሔ ውጤቶችን የሚያፈልቁበት ወሳኝ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ተመራቂዎችም በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው ንድፈ ሃሳብን ከተግባር ተኮር ያቀናጀ ዕውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላትም ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያበለጽጉበትን ዕድል በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው፤ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ተፈጥሯዊ ተሰጥኦቸውን በተግባር ልምምድ የታገዘ ሥልጠና የሚያገኙበትን የዕውቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ማክዳ ወርቅሸት፤ ትምህርት ቤቱ ልዩ ተሰጥኦቸውን የሚያበለጽጉበትን ወሳኝ ትምህርትና ሥልጠና ዕድል ሰጥቶናል ብላለች። የሥልጠና ቆይታቸውም የልዩ ተሰጥኦ ዕውቀትና ክህሎታቸውን በማበልጸግ ከዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነትን እንደሚያጎለብትላቸው ገልጻለች። የኢትዮጵያ ዲጂታል ልማት የቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጧቸውን የምናጎለብትበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሮልናል ያለው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት በተሻለ አበበ ነው። በአሁኑ ወቅት የክረምት ሥልጠናዎችና ልዩ ልዩ የፈጠራ ማሳያ መድረኮች በርካታ ዕድሎችን በመፍጠር ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጿል። ወጣቶችም የኢንተርኔት አክሰስንና አዳዲስ ዕድሎችን በመጠቀም የራስን ጥረት ማዕከል በማድረግ አዳዲስ ሶፍትዌሮችን በማልማት ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።
በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው
Oct 1, 2026 244
ሸገር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላቱ ለኢሬቻ በዓል አከባበር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በሚገኘው የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው። የዲያስፖራ አባላቱ በኢንስቲትዩቱ በተከናወኑ የዲጂታል ልማት ስራዎቹ መደመማቸውንም ገልጸዋል። ከአሜሪካ የመጡት ዶክተር ተመስገን ሻሾ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመለከቱት ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለተተኪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው። "ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተደገፈች ያለችበት ወቅት በመሆኑ፣ ሀገራችን ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከውጭ ይገቡ የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የጀመረችው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ነው" ብለዋል። በተለይም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲደገፉና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ያደነቁት ዶክተር ተመስገን፤ አሁን የተጀመሩት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በተሻለ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ተመስገን፤ በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራቸው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ከደቡብ አፍሪካ የመጡት አቶ ኡመር ኡስማን በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወኑት ተግባራት ትውልዱ በሀገሩ ሰርቶ እንዲለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል። በኦሮሚያ ክልል በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ አስተማማኝ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአስተማማኝ የዕድገት መስመር ላይ የምትገኝ መሆኗን በመጠቆም፣ ዲያስፖራው በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ሌንሴ ለሜሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳሉት፤ ጉብኝቱ በየዓመቱ በኢሬቻ ሳምንት በክልሉ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት ባህል አካል ነው። አክለውም በኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ለነገዋ ሀገር ተስፋ የሚሆኑበትን አሰራር መመልከታቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከፍተኛ የዕውቀት ብቃት (IQ) ያላቸውን ተማሪዎች በማፍራት ሀገራቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን ያብራሩት አቶ አሚን፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በሀገራችን እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ በተግባር በማሳየት አባላቱ ሀገራቸውን በዕውቀትም ሆነ በኢንቨስትመንት ለመደገፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
ስፖርት
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩ ሆነች
Oct 6, 2026 96
አዲስ አበባ፤መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦አትሌት ትዕግስት አሰፋ የ2026 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች። የዓለም አትሌቲክስ በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ 10 የዓለም ምርጥ አትሌት እጩዎችን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ከሴት እጩ አትሌቶች መካከል ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ትገኛለች። አትሌት ትዕግስት ከዚህ ቀደም በእ.አ.አ በ2023 እና በ2025 የዓለም አትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት እጩ እንደነበረች የሚታወስ ነው። አትሌቷ በቅርቡ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በጉዳት ተፈትና 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለም ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች ። እንዲሁም በ2026 የለንደን ማራቶን በ2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በማጠናቀቅ የሴቶች ብቻ ማራቶን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲሸልስን በድጋሚ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ
Oct 3, 2026 292
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊ ሰለሞን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት በአጠቃላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። እሙሽ ዳንኤል ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታገናኝ ቱሪስት ለማ፣ ቤተልሄም መንተሎ፣ ቤተልሄም በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና የሲሸልሷ አሻንታ ማሪ በራሷ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል። ሀገራቱ ከቀናት በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ 16 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የበላይነቱን አሳይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛል። የወዳጅነት ጨዋታዎቹም የዚህ ዝግጅት አካል ናቸው። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል
Oct 3, 2026 208
አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታውን ዛሬ ያከናውናል። ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል። በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅቱን እያደረገ ነው። ቡድኑ የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። ሁለቱ ቡድኖች ከጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አከናውነዋል። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ ተካሄደ
Oct 1, 2026 272
ቢሾፍቱ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ተካሂዷል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ጅራታ ሌሊሳ (ከሸገር) 1ኛ፤ አትሌት ለሚ ተሾመ (ከሸገር) 2ኛ፤ አትሌት አቤል ቼቤት (ከኡጋንዳ) 3ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል። እንዲሁም በሴቶች አትሌት ብርነሽ ደሴ (ከፀዳይ ባንክ) 1ኛ በመውጣት የ2019 የ2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ ባደረጉት ንግግር፣ ኢሬቻ ፍቅርንና አንድነትን በማጠናከር ለብሔራዊ መግባባት መሠረት በመጣል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ይህንን በስፖርት በማስደገፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የመግባባት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ እናሳድጋለን ብለዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ ሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሀገሪቱን ቱሪዝም እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የቢሾፍቱ ከተማም ከምንጊዜውም በላይ ዘንድሮ የኢሬቻ እንግዶችን ለመቀበል በኮሪዶር ልማት አጊጣ እየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል።
አካባቢ ጥበቃ
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 197
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን እያጎለበተ ነው
Oct 1, 2026 210
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን በማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል። በተለይም የከተሞችን ሁለንተናዊ ጽዳትና ውበት ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምኅዳር ድኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የጽዱ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ ምኅዳርን በማጎናጸፍ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻና መሰል ውጤታማ የልማት ሥራዎችን የሚያፋጥን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንም የሕብረተሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጽዱ ኢትዮጵያን ግብ የሚያሳካ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ባህልን የሚያጎለብት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያው ዙር "ውበት ይንቃ፤ ብክለት ይብቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የብክለት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ "ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ባህልን ማጠናከር የሚያስችል መሰረት መጣል እንደተቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም ለ3 ወራት የሚቆይ 3ኛ ዙር ''የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል። በየዓመቱ የሚካሄዱት የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የማኅበረሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማጎልበት ተቋማት በብክለት መከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው ብለዋል። መርሐ ግብሩም የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትና መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ በውጤታማነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይም ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥና ብክለትን ለመከላከል የተቀናጁ የአካባቢ የጽዳትና ውበት ጥበቃ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የኤልኒኖ ክስተት ተጽዕኖዎችን ለመከላከል መዘጋጀት ይገባል
Sep 29, 2026 266
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ ክስተት የሚያመጣቸውን መልካም እድሎች ለመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኤልኒኖ ክስተት ከጥቅምት ወር ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጠnነከረ ይሄዳል። ኤልኒኖ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች እንዲሁም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ የደቡብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እና ስርጭት እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ከጥቅምት ጀምሮ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት በተለይም ለሱማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ ለጉጂ፣ ለቦረና፣ ለሲዳማ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም ዝናብ ከወዲሁ የመስኖ ስራዎችንና የተለያዩ የግብርና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለአርብቶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በማሻሻል በእንስሳት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ህንድ ውቅያኖስም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቀ ይገኛል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኤልኒኖ ክስተት እና የህንድ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመር በአንድ ጊዜ በሚጣመሩበት ወቅት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አማራ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከመደበኛ በላይ በሚኖረውና ተደጋጋሚነት ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በዋቢ ሸበሌ እና በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት እድሉ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል ከወዲሁ በዋቢ ሸበሌ፣ በኦጋዴን እና በገናሌ ዳዋ አካባቢዎች የተቀናጀ የወንዝ አመራር ስርዓትን መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው የበጋ ወቅት ከመደበኛ በላይ የሚኖረው የዝናብ መጠን ያለው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ለማህበረሰቡ ተደጋጋሚነት ያለው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀጣናው የታዳሽ ኃይል ማዕከል
Sep 27, 2026 502
ኢትዮጵያ በውሃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል ሀብቶቿ ለታዳሽ ኃይል ልማት እጅግ ግዙፍ አቅም ያላት ሀገር ስትሆን፤ የመደመር መንግስት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በብቃት በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማልማት ረገድ ያከናወነው ስራ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ከራሷ አልፎ ለጎረቤት አገራት በማዳረስ ቀጣናውን በኢነርጂ የማስተሳሰር ስትራቴጂካዊ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። እንደ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ ላሉ አገራት የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የምስራቅ አፍሪካን አገራት በኢነርጂ በማስተሳሰር በጋራ ማደግ እንደሚገባ ያሳየ ነው።ይህ የሃይል ትብብር የአፍሪካን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ እና በቀጣናው የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት ሆኖ ቀጥሏል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 942
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1050
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 948
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1127
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፋ ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግባለች
Oct 6, 2026 133
የታላቋ ሀገር ፤ ታላቅ መንግሥት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፋ ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግባለች። ትናንት በይፋ የተመሰረተው የመደመር መንግሥትም ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በነፃና በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሰጡት ድምፅ የቆመ፣ የሕዝብን አደራና እምነት ሙሉ በሙሉ የተረከበ ታላቅ መንግሥት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር፡ "ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ፣ የዲሞክራሲ ባህልም የሚፈተነው በምርጫ ወቅት ነው፤ ያሳለፍነው ምርጫ እንደማንኛውም ህዝባዊ ምርጫ ተካሄደ ተብሎ ብቻ የሚገለጽ የሰርክ ኹነት አልነበረም" ብለዋል። ዜጎች በምርጫው ፈቃዳቸውን ሊሰጡ የቻሉት በብዙ ውዥንብሮች መካከል አልፈው እንደነበር ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በየጫካው የሸመቁበት፣ በየሚዲያው እያዋከቡትና በአሉባልታ እያስፈራሩት እንኳን ሳይበገር ህዝቡ በብዙ ፈተናዎች መካከል አልፎ ህልውናውን ለማጽናት ፈቅዶ መምረጡን አስታውሰዋል። አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባህል መሰረቱ እየጠነከረ መምጣቱን በግልጽ የሚሳይ ከመሆኑም በላይ ወደፊት በደማቅ ብዕር የሚጻፍ ታሪክ ነው። ዜጎች የመረጡት መንግሥት የመመሥረቱ ጉዳይ የምርጫ ሂደት ማጠቃለያ ብቻ ሳይሆን የሀገር ሉዓላዊነትና የሕዝብ ውሳኔ ሰጪነት ማረጋገጫ ነው። ዜጎች የመረጡት መንግሥት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያደርጋቸው ማንኛቸውም ውሳኔዎች የሕዝቡን ፍላጎትና ብሔራዊ ጥቅምን መሠረት ያደረጉ ናቸው። የዜጎች የምርጫ ተሳትፎ የመንግሥት ህጋዊነት ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገርን በጋራ የመገንባትና የሉዓላዊነት ባለቤት የመሆን ትልቅ ማሳያ ነው። የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት የሕዝብን ዘላቂ ተስፋና ሀገራዊ እድገት እውን ያደረጉ በርካታ ታላላቅ የመሠረተ ልማት፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሴክተር ስኬቶችን ማበሰር የቻለ ነው። በተለይም የሕዝብን የዘመናት ጥያቄዎችን የመለሱ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅና በውጤታማነት በማጠናቀቅ አቅሙን ለዓለም አሳይቷል። የገበታ ለሀገር፣ የገበታ ለትውልድ እና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለዜጎች ምቹ የኑሮ ሁኔታንና የሥራ ዕድልን ፈጥረዋል። በስንዴ ምርት የተመዘገበው ራስን የመቻልና ለውጭ ገበያ የማቅረብ ስኬት፣ ሀገራዊ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተደረገ ትልቅ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያውያን የጋራ አቅምና የፅናት ምልክት የሆነው የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ለፍጻሜ በመቃረብ ለሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይልና የኢኮኖሚ ማነቃቂያ በመሆን ላይ ይገኛል። በተለየ ሁኔታ ይህ መንግሥት የሕዝብንና የሀገርን የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በፅናት እየሠራ ይገኛል። ኢትዮጵያ በባሕር በርና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያላትን ፍትሐዊና ተፈጥሯዊ ፍላጎት በግልጽ ብሔራዊ ጥቅም አድርጎ በማስቀመጥ፣ በበሰለና በጠንካራ ዲፕሎማሲ ሀገራዊ መብቷን ለማስከበር የሚያደርገው ጥረት የሉዓላዊነታችንና የከፍታችን ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብቷን በማስከበር፣ ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር በቀጣይነትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ ውይይት በማድረግ ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን አከናውናለች። በሕዝብ ድጋፍና በተመዘገቡት ታላላቅ የልማት ስኬቶች ታግዞ፣ በመደመር እሳቤ ሀገራዊ አንድነትን እያጠናከረ ያለው ይህ መንግሥት፣ የታላቋን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በማስከበርና የወደፊት ብሩህ ተስፋዋን ይገነባል።
በሀገር ግንባታ ላይ እየጎለበተ የመጣው የወጣቶች ተሳትፎ
Oct 5, 2026 110
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተከናወኑ ሀገራዊ ሂደቶች ወጣቶች በፖለቲካና በምርጫ፣ በሀገራዊ ምክክር፣ በቴክኖሎጂ እና በሥራ ፈጠራ፣ በስፖርት፣ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በሰላም ግንባታና በበጎ ፈቃደኝነት የሚያሳዩት ተሳትፎ እየጎላ መጥቷል። ይህ ሁኔታ ወጣቶች በሀገራዊ ልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ውስጥ ሀሳብ የሚያመነጩ፣ በውሳኔዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚሳተፉና በዛው ልክ ተጠቃሚነታቸውንም እያረጋገጡ የሚሄዱ የዛሬ ተዋናዮች የነገ ደግሞ ተረካቢዎች መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል። ለዚህ ደግሞ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በቅርቡ በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የታየው ሰፊ የወጣቶች ተሳትፎ ነው። በምርጫው ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈዋል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሰፊውን ድርሻ ወጣቶች ሊይዙት እንደሚችልም ይታመናል። የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከሚጎለብትባቸው ሂደቶች መካከል ምርጫ አንዱ ነው። በዚህ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ ወጣቶች በተመራጭነት፣ በመራጭነት፣ በምርጫ አስተባባሪነትና አስፈጻሚነት፣ በፖለቲካዊ ውይይቶችና በተለያዩ የሕዝብ ተሳትፎ መድረኮች ላይ በንቃት መሳተፋቸው ወጣቶች በሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ አሳይተዋል። ይህም ወጣቶች የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደቱን ከሩቅ የሚመለከቱ ሳይሆኑ በሂደቱ ውስጥ በቀጥታ የሚሳተፉ ዜጎች መሆናቸውን ያሳያል። ሀገራዊ ምክክር፤ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ የታየበት ሀገራዊ ሁነት የወጣቶች ተሳትፎ በምርጫ ብቻ ሳይወሰን በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በግልጽ ተንጸባርቋል። በሀገራዊ ምክክሩ ከተካተቱ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ወጣቶች ዋነኞቹ ነበር። ባገኙት ዕድልም የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተመለከቱ በርካታ አጀንዳዎችን በማቅረብ ተሳትፏቸውን አጠናቀዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዓላማ በጋራ የሚያገናኙ ጉዳዮችን በውይይት መለየት፣ በልዩነቶች ላይ መነጋገርና በሀገር ደረጃ መግባባት የሚፈጥሩ መፍትሔዎችን ማፈላለግ ነው። በዚህ ሂደት ወጣቶች መሳተፋቸው በዲሞክራሲያዊ ውይይትና በሰላማዊ የሀሳብ ልውውጥ ውስጥ ያላቸውን ሚና ያሳያል። በመሆኑም ሀገራዊ ምክክር ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበትና ሀሳባቸውን የሚያንጸባርቁበት መድረክ መፈጠሩን ያሳያል። ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጠራ የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ተሳተፎ እና ተጠቃሚነት በግልጽ ካሳየባቸው ዘርፎች መካከል የቴክኖሎጂ ዘርፍ አንዱ እና ዋነኛው ነው። በዚህ ዘርፍ ላይ የወጣቶች ተጠቃሚነት በቴክኖሎጂ ፈጠራም የታጀበ ነው። የዲጂታል ዘመኑ ለወጣቶች አዳዲስ የተሳትፎ መድረኮችን ፈጥሯል። በኮዲንግ፣ በሶፍትዌር ልማት፣ በዲጂታል አገልግሎት፣ በፊንቴክ፣ በኢ-ኮሜርስና በሌሎች የቴክኖሎጂ ዘርፎች ወጣቶች አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅና መፍትሔዎችን በማቅረብም ጭምር። መንግሥት የወጣቶችን በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሳደግ ካለው መሻት የተነሳ የ5 ሚሊየን ኮደሮች ፕሮግራም ነድፎ በመተግበር ውጤት አስመዝግቧል። ወጣቶችን በኮዲንግና በዲጂታል ክህሎት ለማብቃት የተሄደበት ርቀት እና የተመዘገበው ውጤት ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። ይህ ተሳትፎ ወጣቶች ቴክኖሎጂን ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ቴክኖሎጂን ወደ መፍጠር እንዲሸጋገሩ፣ ችግሮችን የሚፈቱና ሥራ የሚፈጥሩ ምቹ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂን ለስራ ዕድል ፈጠራ ወጣቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በዚህም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መጥቷል። ወጣቶች ቴክኖሎጂን ለግብርና፣ ለአግሮ-ቢዝነስ፣ ለማምረቻው ዘርፍ፣ በኢ-ኮሜርስ እና ለአገልግሎት ዘርፎች ዕድገት በማዋል በኩል የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱም ናቸው። ይህም የወጣቶች ሚና ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነትና ወደ ንቁ ኢኮኖሚያዊ ተዋናይነት እየተሸጋገረ መምጣቱን ያመለክታል። ስፖርት፤ የወጣቶች ተሳትፎ ሌላው መድረክ የመደመር መንግሥት በአእምሮም በአካልም የጎለበተ ትውልድ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት የሚኖረውን አበርክቶ በውል በመረዳቱ ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሆኑ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል። እየሰራም ይገኛል። ስፖርት ወጣቶች ሀገራዊ ተሳትፏቸውን የሚያጎለብቱበት እና ሀገራቸውን በዓለም የውድድር መድረኮች ላይ የሚወክሉበትና የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው። የስፖርት ተሳትፎ ከውድድርና ውጤት ባለፈ የቡድን ሥራ፣ የመከባበር፣ የደንብ ማክበርና የሰላማዊ ውድድር እሴቶችን የሚያጎለብት በመሆኑ ለዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታም አስተዋጽኦ አለው። ባህልና ኪነ-ጥበብ፤ የወጣቶች የሀሳብ መግለጫ ወጣቶች በባህልና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ እያሰፉ ነው። በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በቲያትር፣ በስዕልና በሌሎች የፈጠራ ዘርፎች የሚሳተፉ ወጣቶች የራሳቸውን ሀሳብና እይታ ለማህበረሰቡ እያቀረቡ የሌሎችንም እየወሰዱ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የራሳቸውን ጠጠር እንዲያኖሩ ዕድል የሚፈጥሩ አውዶች ናቸው። ኪነ-ጥበብ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ፣ ልዩነቶችን ለማቀራረብና የጋራ እሴቶችን ለማጠናከር ከሚያገለግሉ መድረኮች አንዱ በመሆኑ፣ የወጣቶች በዚህ ዘርፍ መሳተፍ ለሀገራዊ ማንነትና ለማህበራዊ ትስስር ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ነው። ሰላም ግንባታና በጎ ፈቃደኝነት፤ ለማህበረሰብ ተሳትፎ የወጣቶች ሀገራዊ ተሳትፎ በሰላም ግንባታና በበጎ ፈቃደኝነትም ጭምር ይገለጻል። በተለያዩ የሰላም ማስፈን፣ የማህበረሰብ ውይይት፣ የአካባቢ ጥበቃና ማህበራዊ ድጋፍ ሥራዎች ወጣቶች በበጎ ፈቃድ የሚሳተፉባቸው ዘርፎች ናቸው። ይህ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ለሀገር ጉዳይ መቆም እንደሚችሉ ያሳያል። በጎ ፈቃደኝነት በተለይ የዜግነት ተሳትፎን በተግባር የሚያሳይ መስክ ነው። ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለማህበረሰቡ በማበርከት የጋራ ችግሮችን በጋራ መፍታት እንደሚቻል በተግባር ያሳያሉ። ይህም የዜጎችን ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎን የሚያጠናክር ነው። ይህ ሁለንተናዊ የወጣቶች ተሳትፎ ለሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውጤታማነት አይነተኛ ሚና አለው። የመደመር መንግስት በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ሂደት ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገር ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ ተጠቃሚነታቸውንም እንዲያረጋግጡ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ወጣቶች ይህን ትልቅ ዕድል በመጠቀም ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከመጠቀም ባለፈ ለሀገር የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። ይህን ዕድል በሚገባ ከተጠቀሙበት የኢትዮጵያ ወጣቶች የነገ ተስፋ ብቻ ሳይሆኑ በዛሬው የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ አሻራቸውን ማኖር ያስችላቸዋል። የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ብቻ ሳይሆን በሀገራዊ ልማት፣ በሰላም፣ በማህበራዊ ትስስርና በፈጠራ ዘርፎች እየሰፋ የመጣ ግልጽ እውነታ ነው። ይህን ተሳትፎ በተጠናከረ መንገድ ለማስቀጠል ዛሬ የሚመሰረተው የመደመር መንግስት ግልጽ አቅጣጫ ይከተላል።
የታላቅ ሕዝብ ድምጽ - የጠንካራ ሀገረ መንግሥት መሠረት
Oct 5, 2026 199
ታላቅነት መታወቂያዋ፣ ግዙፍ ሕዝብ ጌጧ፣ አርቆ አሳቢ ርዕይ ደግሞ የጉዞዋ ኮከብ የሆነላት ኢትዮጵያ፣ በየዘመናቱ እንደ ተራራ የተደቀኑባትን መሰናክሎች ሁሉ ተሻግራ የልማትና የብልፅግና ጉዞዋን በጽናት ዘልቃለች። ዛሬም የጀመረቻቸውን ሀገራዊ የዕድገት ርምጃዎች አጠናክራ ለመቀጠል በታሪክ ማዕዘን ላይ ቆማለች። ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያሸጋግራትን መሪ የመምረጥ ባለቤትነትና ሥልጣን ለሕዝብ የተረጋገጠበት፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም የዚህ ሀገራዊ ጉዞ ጉልህና ወሳኝ ምዕራፍ ሆኖ በታሪክ ማኅደር ሰፍሯል። 👉 የታላቅ ሕዝብ ውሳኔ ትልቅነት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተከናወነው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው፣ ይበጀናል ላሉት ፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነጻነት ሰጥተዋል። በምርጫው 42 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል። ይህ ተሳትፎም ምርጫውን በአገር ውስጥ የፖለቲካ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ከተመዘገበባቸው ምርጫዎች ተርታ አሰልፎታል። የምርጫው ስኬት በቁጥር ብዛት ብቻ አይለካም። ዜጎች የአየር ንብረት ተጽዕኖና የጊዜ ገደብ ሳይበግራቸው እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ይህም ሕዝቡ ለሀገራዊ ዕጣ ፈንታው ያለውን ጥልቅ የኃላፊነት ስሜት፣ ትዕግሥትና ጽናት በተግባር የመሰከረበት፣ የታላቅነቱንም ምስክር ለዓለም ያሳየበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው። የሕዝቡን ድምጽ ተከትሎም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 ወንበሮችን በማግኘት የአብዛኛውን ሕዝብ ይሁንታ በማግኘት ማሸነፉን ይፋ አድርጓል። 👉 ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ተወካዮቹን የመምረጡ ዋና ዋና ጥቅሞች ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ተወካዮቹን መምረጡ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ እንደ ዓለት የጸና መሠረት ነው። የመንግሥት ጥንካሬ ምንጩ የሕዝብ ድጋፍና ይሁንታ ነው። የዜጎችን ይሁንታ ያገኘ መንግሥት ተቋማትን ለመገንባት፣ ሕግን ለማስከበርና ሀገራዊ አንድነትን ለማጽናት የሚያስፈልገውን ሞራላዊና ሕጋዊ መሠረት ይጨብጣል። ከፍተኛ የመራጮች ተሳትፎ የመንግሥትን ሕጋዊ ተቀባይነት ያጎላል፤ መንግሥትም "ሕዝብ የሰጠኝ አደራ ነው" ብሎ በሙሉ ልብ ፖሊሲዎቹን ይተገብራል፤ ዜጎችም ለወጡ ሕጎችና ውሳኔዎች ይበልጥ ይተባበራሉ። ምርጫው የዴሞክራሲን ባህል በሕዝብ ልብ ውስጥ ይተክላል። ዜጎች ድምጻቸው ወሳኝ መሆኑን በዓይናቸው ሲያዩ፣ የሥልጣን ምንጭ ሕዝብ መሆኑን በልምድ ይገነዘባሉ። ይህ ልምድ ለመጪዎቹ ምርጫዎች ጠንካራ ፋና ሆኖ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ የሥልጣን ሽግግርን አገራዊ ባህል ያደርጋል። ከልዩ ልዩ ክልሎች፣ ማኅበረሰቦችና ሃይማኖቶች የተውጣጡ ዜጎች በአንድ ቀን፣ ለአንድ ዓላማ ወደ ምርጫ ጣቢያ መትመማቸውም "የጋራ ሀገር፣ የጋራ ዕጣ ፈንታ" የሚለውን ፅኑ ስሜት ያጎለብታል። በመሰረቱ በካርዱ የመረጠ ዜጋ የመረጠውን መንግሥት የመከታተል፣ የመጠየቅና የመተቸት ሞራላዊ መብት ይጎናጸፋል። መንግሥትም ለመረጠው ሕዝብ የመመለስ ኃላፊነት ይሸከማል። ይህ የጋራ ተጠያቂነት የጤናማ የመንግሥትና የሕዝብ ግንኙነት የጀርባ አጥንት ነው። ግጭትና አለመግባባት በምርጫ ሳጥን ሲፈታም የሥልጣን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መልስ ያገኛል፤ ይህም ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ዋስትና ነው። በመጨረሻም ብዙ ሕዝብ የተሳተፈበት ምርጫ የሀገርን ዓለም አቀፍ ገጽታና ተዓማኒነት ያንጻል። ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ አጋሮች፣ ለኢንቨስተሮችና ለልማት ተባባሪዎች ያላትን ተዓማኒነት ከፍ ያደርጋል፤ የተረጋጋችና በሕዝብ ድጋፍ የምትመራ አገርም ለኢንቨስትመንትና ለትብብር ተመራጭ ናትና። 👉 ከሕዝቡ ጠቀሜታ አኳያ ምርጫ ለሕዝቡ የመብት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የጥቅሙም መሣሪያ ነው። ሕዝብ ሕልሙን፣ ፍላጎቱንና ምኞቱን እውን ያደርግልኛል ብሎ ያመነውን ፓርቲ መምረጡ ተገቢውን ምላሽ እንደሚያገኝ በማመን ነው። አሸናፊው ፓርቲም የሕዝብን ጥያቄዎች የመመለስ ቃል በትከሻው ላይ ይሸከማል። በዚህም ሕዝብ ፍላጎቱን የሚያስቀድም መንግሥት ያገኛል። መንገድ፣ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ የሥራ ዕድልና የኑሮ ውድነትን የመሳሰሉ የዕለት ተዕለት ጥያቄዎች በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የመንግሥት ዕቅድ እምብርት እንዲሆኑ ድምጽ ተሰጥቷል። ይህም የልማትና የአገልግሎት ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበትን በር ይከፍታል። ድምጹ ዋጋ እንዳለው ያየ ዜጋ ተስፋውና ተሳትፎው ይለመልማል። ዛሬ የሚጣሉ ጠንካራ ተቋማዊ መሠረቶችም ለልጆቻችንና ለመጪው ትውልድ የተረጋጋችና የበለጸገች አገር ቅርስ ሆነው ይተላለፋሉ። 👉 የመደመር መንግሥት ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የሰጠው ድምጽ ውጤትን ከማብሰር ያለፈ፣ ከባድ አደራ የተሸከመ ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ማግኘቱ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጠለት ብልፅግና ፓርቲ፣ የተመሰረተው መንግሥት ይህንኑ የሕዝብ አደራ በመሸከም ነው። ለሕዝቡ ቃል የገባውን በተግባር የሚተረጉምበትን ፍኖተ ካርታ የሚያሳይበት ነው። ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ እና የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥም ተከታታይ ድሎችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው። ከድሎቹ ቀዳሚው የትውልድ ቃል ኪዳን የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም፣ ገንዘብና ጥረት የገነቡት ይህ ግድብ ተጠናቅቆ ተመርቋል። በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ ሆኖም ለአገር ብርሃንን፣ ለሕዝብ ተስፋን፣ ለቀጣናውም የትብብር ዕድልን ይዞ ቆሟል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ ተሰልፈው ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአገርን ገጽታ ቀይረዋል። ስንዴን ከውጭ በማስገባት ትታወቅ የነበረች አገር፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ራሷን ወደ መቻል መንገድ ገብታለች። በኮሪደር ልማት የአዲስ አበባና የሌሎች ከተሞች ገጽታ ተለውጧል፤ ሕዝብም በንጹህ፣ ውብና ለኑሮ ምቹ አካባቢ የመኖር መብቱን እያጣጣመ ነው። በቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ለመገንባትና ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተጀመሩ ርምጃዎችም የአገሪቱን የነገ ከፍታ ያበስራሉ። ሕዝብ አብላጫ ድምጹን የሰጠው ይህንን የስኬት ጉዞ አይቶ፣ ከዚህ የበለጠ ያደርሰናል ብሎ በማመን ነው። ስለዚህ የዛሬው ድምጽ ለፓርቲው ከዕውቅና ባለፈ፣ የጀመራቸውን ሥራዎች ወደ ከፍታ ለማድረስ የሚጓዝበት ስንቅ ነው። የተገኙት ድሎች የመጨረሻ መዳረሻ ሳይሆኑ ለቀጣይ ታላቅ ርምጃ የተቀመጡ መሠረቶች ናቸው። ፓርቲውም ይህንን የድል ጉዞ ሳይቋረጥ የማስቀጠል፣ ከፍ የማድረግና የማላቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት። የተመሰረተው የመደመር መንግሥት ሕዝብ በድምጹ በሰጠው ይሁንታ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ሥራዎች ሳይቆራረጡ እንዲቀጥሉ፣ ግልጽ የአምስት ዓመት የአመራር አቅጣጫም እንዲኖር ያስችላል። ከሕዝብ፣ አደራ የተረከበው መንግሥት ሕዝቡ ያስቀመጠውን አደራ ወደ ተጨባጭ ውጤት የሚለውጥበት ጊዜ ይመጣል። በኑሮ ማሻሻያ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በፍትሐዊ ተጠቃሚነት የተገቡ ቃሎች ወደ ተግባር ይለወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሕዝብ እምነቱን አብላጫ ድምጽ በመስጠት ያረጋገጠው ፓርቲም ይህንን እምነት በውጤት የመመለስ ድርብ ኃላፊነት አለበት። ጠንካራ ሀገር ከመገንባት አኳያም፣ ሕዝባዊ ይሁንታ ያለው መንግሥት፣ ጠንካራ ተቋማትና ንቁ ዜጋ ሲገናኙ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ይገነባል። ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ መርጧል፤ አሁን ደግሞ ምርጫው የዘራውን ተስፋ በሥራ የማጽናት ኃላፊነት ብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት ነው። ያለፉት ድሎች ለቀጣዮቹ ስኬቶች መወጣጫ ደረጃ ሆነው፣ ሕዝብና መንግሥት በመተማመን ላይ የተመሠረተ የጋራ ጉዞ ሲያደርጉ፣ ኢትዮጵያ ታላቅ ሕዝቧን እና ታላቅ ርዕይዋን የሚመጥን ከፍታ ላይ ትደርሳለች።
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 163
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ አየር ኃይል - የማድረግ አቅም ዳርቻ
Oct 5, 2026 130
በብዙ መውጣትና መውረድ፣ ውስጥ አልፏል። በውድ መስዋዕትነት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አስከብሯል። በሁለት አሳዛኝና አስገራሚ አጋጣሚዎች የመፍረስ አደጋ ተደቅኖበት ነበር፤ አሳዛኙ በጣሊያን ወረራ ወቅት ወድሞ ከጥቅም ውጭ መሆኑ ነው። ሁለተኛውና አስገራሚው ነገር ደግሞ በ1983 ዓ.ም መንበረ ስልጣኑን በሀይል የተቆጣጠረው ጸረ ኢትዮጵያው ሕወሓት የባህር ኃይሉን ሙሉ በሙሉ በመበታተን የአየር ኃይሉን በማዳከም ለሀገሩ ያለውን ጥላቻ የገለጠበት የታሪክ አጋጣሚ ነው። የመፍረስ አደጋዎችን በማለፍ የማንሰራራት ዘመንን ዋጅቷል። የቀጣናው የሰላም ዘብ፣ የደህንነት ዋስትና መሆኑን በጀግንነት እያሳየ ድፍን 90 ዓመታትን ተሻግሯል፤ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር ኃይል። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ “ኢሕአዴግ ሀገሪቱን ሲቆጣጠር በጠቅላላ ነው የተበተነው፤ ኢትዮጵያ መልሳ ማግኘት የማትችላቸው ንብረቶች ወደ ጎረቤት ሀገር ተበትነዋል።” ብለዋል። ሕገወጡ ሕወሓት ምድረ በዳ ያደረገው አየር ሀይል ዛሬ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግሮ ድል የማብሰር ምልክት ሆኗል። የጠንካራና አይበገሬ ተቋማት፣ የሉዓላዊነት ዋስትና የድል አድራጊነት አውራ ሆኗል። “ሰማዩ የእኛ ነው” በሚል መሪ ሀሳቡ እንደ ስሙ እያደረ ነው። የቀጣናው አስተማማኝ የሰላም ዘብ ነው የኢትዮጵያ አየር ኃይል። የአውሮፕላን አብራሪዎችና ቴክኒሻኖችን ማሰልጠኛ ማዕከል፣ ለሌሎች የሚተርፍ የጥገና አቅም ገንብቷል፤ መለዋወጫዎችን ያመርታል። ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የታጠቁ የሰማይ ላይ ንጉሶችን አፍርቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሰው ልጅ የማድረግ አቅምና ብቃት የታየበት፣ የዳበረ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ የዋለበት የቴክኖሎጂም፣ የምርምርም፣ የውጊያም፣ የሰላምም ተቋም ሆኗል። ነገን መዋጀት፣ ኢትዮጵያን ማፅናትና ማስቀጠል የግብሩ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ልጆች የጀመሩት ለውጥ በትናንሽ ሙከራዎች ሸብረክ የማይል በጽኑ መሰረተ ላይ የመገንባቱ ማረጋገጫ ማህተም ጭምር። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በ1928 ዓ.ም ሲቋቋም የመጀመሪየው አዛዣ ሻለቃ ሚሽካ ባቢቼፍ ነበሩ። የመጀመሪያዋ የጦር አውሮፕላን ደግሞ "ንስረ ተፈሪ" /Nessre Tafari/ የተሰኘችው ባለሁለት ክንፍ የፈረንሳይ ስሪት Potez 25-ናት። ኢትዮጵያ ከብዙ የዓለም ሀገራት በፊት ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ባንክና መሰል ዘመናዊ የመንግስት አገልግሎት ስትጀምር የኢፌዴሪ አየር ኃይል አንዱ ነበር። የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት አርማ፣ የሉዓላዊነትና የደህንነት ማረጋገጫ ማህተም መሆኑን በሰማይ ላይ ነግሦ በተግባር አረጋግጧል፤ እያረጋገጠም ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ የአየር ክልል በአስተማማኝነት በመጠበቅ የሰማይ ንግሥናውን ተቆናጧል። የኢትዮጵያ የታላቅነት ማንፀሪያ ሆኖም ያገለግላል። ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ “90 ዓመታትን በተሻገረው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ታሪክ ውስጥ የሀገርን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል፤ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል በደምና በአጥንታቸው ሀገር ያጸኑ ጀግኖቻችንን አፍርቷል” ብለዋል። የለውጡ መንግሥት አየር ኃይሉን ከመፍረስ ታድጎ በውጊያ መሰረተ ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታና ትጥቅ በማሟላት ኢትዮጵያን የሚመጥን ተቋም ገንብቷል። የኢፌዴሪ አየር ኃይልን በሁሉም ረገድ በማዘመንና ሁለንተናዊ ብቃቱን በማሳደግ የመከላከያ ሠራዊቱ ጠንካራ ክንድ፣ የሉዓላዊነት ዘብ፣ የኢትዮጵያውያን ኩራት ማድረግ ተችሏል። አየር ኃይል ከ1969 – 1970 ዓ.ም በተካሄደው የእናት አገር ጥሪ /የኦጋዴን ጦርነት/ የእብሪተኛውን የዚያድ ባሬ ወራሪ ጦር ግብዓተ መሬት በማፋጠን የፈጸመው ጀብዱ በዓለም ወታደራዊ ኢላማና ስኬት ታሪክ እጅግ አስደናቂ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። እንደነ ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ባሉ ወደር የለሽ የአየር ላይ ቀዛፊዎች በቁጥር የላቀና ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶችን የታጠቀው የሶማሊያ አየር ኃይል ላይ የአየር የበላይነት በመውሰድ መቅሰፍት አውርደውበታል። ይህ ኢትዮጵያውያን በኩራት የሚናገሩለት ገናና ታሪክ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል እንደ ታሪኩ ማደር የሚያስችለው ቅኝት ውስጥ ገብቷል፤ በጠላቶች የተቃጣበትን የመፍረስ አደጋ በጣጥሶ ወጥቷል። የአባቶቹ ልጅ መሆኑን አሳይቷል። ዛሬ እጅግ በረቀቁና በቴክኖሎጂ በዳበሩ የጦር ጄቶችና ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅሙን ገንብቷል። በጠላት ላይ ኢላማውን የጠበቀ ከፍተኛ አደጋ መፍጠር የሚችሉ ምስጉን ባለሙያዎችን አፍርቷል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው እንደሚሉት፤ የአየር ኃይል የጥገና፣ የማምረትና የቴክኖሎጂ አቅም በአፍሪካውያን ጭምር የተመሰከረለት አስደናቂ ለውጥ ውጤት አምጥቷል። በአፍሪካ ካሉ ትልልቅ የአቬዬሽን ኢንዱስትሪዎች አንዱ ሆኗል፤ በዕውቀት በቴክኖሎጂና ራስን በመቻል አቅም ልቆ ተገኝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይል “የኢትዮጵያን አንድነትና ነጻነት ሊገዳደሩ የሚፈልጉ ሀይሎች አቅሟን አይተው እንዲገቱ፤ ከሞከሩም እንዲቀጡ የማድረግ ሀገራዊ አቅም ገንብቷል። ጥቁር አንበሳ ማሸነፍ እንጂ መሸነፍ አያውቅም፤ እናም አትሞክሩት፤ ሰላምን ማጽናት እንፈልጋለን ደፍሮ የሚሞክር ካለ ግን ግብዓተ መሬቱን እናፋጥናለን።” በማለት ኢትዮጵያ ግዙፍ ተቋም መገንባቷን አብስረዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ላይ የተደረገው ስር ነቀል ሪፎርም የኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥገና፣ የሰው አልባ አውሮፕላን ምርት፣ የመለዋወጫና ሌሎች የማምረቻ ፋብሪካዎች አቅም በፍጥነት አድጓል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል የማድረግ አቅም ጨምሯል፤ የትብብር ስምምነት በመፈራረም በጋራ ለመስራት የሚፈልጉ ሀገሮችም ተበራክተዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፤ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስከብር አየር ኃይል መገንባት እንደሚቻል የተረዳነው፣ ዐይናችንን የገለጥነው፣ ወደ ተግባር የገባነው ከሪፎርሙ በኋላ ነው ይላሉ። ሪፎርሙ ቴክኖሎጂ እንዲታጠቅና እንዲያለማ፣ ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀም በማድረግ ብዙ ሀብት እንዲያፈራ የማይገለጹ አቅሞችን እንዲገነባ ማድረጉንም አንስተዋል። “የማምረት አቅማችን ከአምናው ዘንድሮ ጨምሯል” የሚሉት ምክትል አዛዡ፤ በቀን ከ20 ያልበለጡ ምርቶችን ከማምረት አሁን 350 ተሸጋግሯል፤ አንዳንድ መለዋወጫዎችን በቀን እስከ 3 ሺህ 500 የማምረት አቅም ገንብቷል፤ በኢትዮጵያ አየር ኃይል እርካታ የሚባል ነገር የለም፤ አይፈቀድምም። በድል ላይ ድል መጎናጸፍ፤ የኢትዮጵያን ሀያልነት ማወጅ የግቡ መዳረሻ ነው። ስሙ በተነሳ ቁጥር ከኢትዮጵያ ውድቀት ጋር የሚቆራኘው ሕገ ወጡ ሕወሓት፤ ኢትዮጵያ ባህር በር አልቦ፣ ዜጎቿን የመልክዓ ምድር እስረኛ አድርጓል። ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አድማስ ተሻጋሪ ነው፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ አይወሰንም፤ ህንድ ውቅያኖስ ይደርሳል፤ መሰረታዊ፣ ታሪካዊና ህጋዊ የባህር በር ባለቤትነቷ ምላሽ ማግኘት አለበት። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚመጠን አቅም ለመገንባት ሌት ተቀን መትጋት ደግሞ የአየር ኃይል አድማስ ተሻጋሪ የዘወትር ግብር ነው። ኢትዮጵያን የመታደግ፣ ኢትዮጵያን የማኩራት፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በአጭር ጊዜ የመፈጸም ብቃት ተቋማዊ አርማው ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር አስቀጥሏል። ኢትዮጵያ “ማህጸን ለምለም ናት” የሚለውን በገቢር እየኖረ ሰማዩን እያሰሰ አውሮፕላኑ እየተንደቀደቀ … የኢትዮጵያውያንን ልብ እያሞቀ … ቀጥሏል፤ ንሥርነቱን በተግባር እየገለጠ ወዳጆቹን እያስደመመ፣ ጠላቶቹን እያኮሰመነ ይቀጥላል።
ከፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት
Oct 5, 2026 108
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ)፡- ከፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ ኢትዮጵያ ረጅም የፖለቲካ ታሪክ ያላት ሀገር ብትሆንም፣ ይህ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች በፖለቲካዊ መገለል፣ በአለመተማመን፣ በአለመግባባትና በግጭት የተቆራረጠ መንገድ አልፏል። የፖለቲካ ስርዓቱ ውስጥ የሀገሪቱ ህዝቦች፣ ክልሎችና የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች በእኩልነት እንዲሳተፉ የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠርም ብዙ ፈተናዎች አልፈዋል። ከብዙ ልፋት በኋላ በሀገሪቷ የመጣው ለውጥ የተሻለ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት፣ ምህዳሩን በማስፋትና ልዩነቶችን በሃሳብ ክርክር ለመፍታት የሚያስችል አዲስ የፖለቲካ አውድ ፈጥሯል። ይህም ከቆየው የፖለቲካ ስብራት ወደ ማንሰራራት የሚወስድ መልካም እድሎችን ይዞ የመጣ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የፖለቲካ ተሳትፎ በመስፋቱ የፖለቲካ አውዱ የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት ማድረግ አስችሏል። የሀገር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ፣ የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት እንዲሆን የሚያስችል የፖለቲካ አውድ መፈጠር አስችሏል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተወሰኑ ክልሎች “አጋር” እየተባሉ በሀገራቸው ጉዳይ እንዳይወስኑ እና እኩል ተሳታፊ እንዳይሆኑ ተገድበው ቆይተዋል። አሁን ላይ ግን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ እኩል ተሳትፎና ድምጽ እንዲኖራቸው ተደርጓል። በዴሞክራሲ ሥርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚኖራቸው ሚና መንግሥትን መቃወም ብቻ አይደለም። አማራጭ ፖሊሲዎችን ማቅረብ፣ ለህዝብ የተሻለ አማራጭ ማቅረብና በሀገር ጉዳይ ላይ ገንቢ ሚና መጫወትም ይጠበቅባቸዋል። በዚህ ረገድ ባለፉት ጥቂት አመታት በሃሳብ የበላይነት የሚመራና ክርክር የሚደረግበት እድል መኖሩ በተግባር ታይቷል። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም በመንግሥት አመራር ውስጥ ሀላፊነት ተሰጥቷቸው ተቋማትን የመምራትና ህዝብን የማገልገል ዕድል ማግኘት ችለዋል። በአንድ ሀገር ውስጥ የፓርቲዎች እንዲሁም የመንግስት መምጣትና መሄድ የማይቀርና የተለመደ ነው፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ግን ከግለሰቦችና ከፓርቲዎች በላይ ቆመው ለህግ፣ ለፍትሕና ለህዝብ ጥቅም መስራት አለባቸው። በመሆኑም በኢትዮጵያ መሰረቶች በመጠናከራቸው የዴሞክራሲ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ የታቸለበት እድል ተፈጥሯል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር እድገትና የሀገረ መንግስት ግንባታ በአንድ ፓርቲ ወይም በአንድ መንግሥት ብቻ የሚጠናቀቅ አይደለም። የሁሉም ዜጎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የክልሎች፣ የዴሞክራሲ ተቋማትና የሲቪክ ማህበራት የጋራ አጀንዳ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል።
የኢትዮጵያ የፅናት ጉዞ እና የካይሮ የጥፋት እጆች
Oct 4, 2026 362
ታሪክ ደጋግሞ እንደሚያስተምረን፤ የኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት እና በቀጣናው ላይ የሚኖራት አዎንታዊ ተፅዕኖ ማደግ በካይሮ የፖለቲካ ሊሂቃን ዘንድ እንደ ስጋት ሲቆጠር ኖሯል።የዓባይን ውሃ በብቸኝነት የመቆጣጠር የቆየ ስትራቴጂ የምትከተለው ግብፅ፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም እና በኢኮኖሚ ጠንካራ ሀገር ሆና እንዳትወጣ ለማድረግ ያልፈነቀለችው ድንጋይ፣ ያልተጠቀመችበት የጂኦፖለቲካዊ ሴራ አልነበረም። ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያን በውስጥ ባንዳዎች እና ቅጥረኞች በፋይናንስና በመሳሪያ በመደገፍ ሀገሪቱን ለማዳከም የተሄደባቸው መንገዶች በሙሉ በኢትዮጵያውያን አይበገሬነት እና በሉዓላዊነት ላይ ባላቸው የማይናወጥ ጽናት ምክንያት መና ቀርተዋል። በቅርቡ ደግሞ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ እና ወደ ሥራ መግባት፣ ያንን የቆየውን የቅኝ ግዛት ውል እና "እኔ ብቻ ልጠቀም" የሚለውን አግላይ እሳቤ ላይመለስ አክሽፎታል። በቀጥታ ወታደራዊ ግጭት ወይም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢትዮጵያን ማንበርከክ ያልቻለችው ካይሮ፣ አሁን ላይ የስልት ለውጥ በማድረግ የውክልና ጦርነት ስትራቴጂን በሰፊው ማካሄድ ጀምራለች። ለዚህ እኩይ አላማዋ ደግሞ በአስመራ የሚገኘውን የሻዕቢያ አስተዳደር እንደ ፈጻሚ አካል መጠቀም ከጀመረች ሰነባብታለች። ሁለቱን ወገኖች ያገናኛቸው የጋራ ፍላጎት ልማት ወይም የህዝቦች እድገት ሳይሆን፤ "ኢትዮጵያን የማዳከም፣ የማተራመስ እና በቀጣናው አቅም አልባ የማድረግ" እኩይ ግብ ነው። የዚህ ያልተቀደሰ ጋብቻ ዋና ስትራቴጂ፡ኢትዮጵያ ሁልጊዜም በውስጥ ግጭትና አለመረጋጋት እንድትጠመድ ማድረግ። ሀገሪቱ ትኩረቷን እና ሀብቷን ወደ ጸጥታ ማስከበር እንድታዞር በማድረግ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን አቅም ማዳከም።የሀገሪቱን የመከላከል አቅም ለመበታተን በተለያዩ አቅጣጫዎች የጸጥታ ስጋት መፍጠር ናቸው። በአሁኑ ወቅት ይህ ጣልቃ ገብነት በግልጽ በሚታይ ደረጃ ላይ ደርሷል። የኤርትራ ሠራዊት የውስጥ ታጣቂዎችን በመደገፍ፣ በቀጥታ በጦርነት በመሳተፍ የጸጥታ ስጋት በመፍጠር እና የፌደራል መንግሥቱን ለማዳከም እየሰራ ይገኛል። ይህም ግብፅ በስተጀርባ ሆና በገንዘብ፣ በመሳሪያ እና በዲፕሎማሲ የምታግዘው ግልጽ የውክልና ጦርነት አካል ነው። ነገር ግን ታለቋ ኢትዮጵያ የሉዓላዊነቷን ወሰን እና የብሔራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ማናቸውንም አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ሴራዎች በዝምታ እንደማትመለከት በተግባር እያሳየች ትገኛለች። የውስጥ ሰላሟን ከመጠበቅ ጎን ለጎን፣ የውጭ ኃይላትን ድብቅ ሴራ የሚያከሽፉ ጠንካራ የዲፕሎማሲ እና የመከላከል እርምጃዎችንም ወስዳለች። በብሔራዊ ደህንነት ላይ አደጋ በሚደቅኑ ተግባራት ላይ በቀጥታ የተሳተፉ 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከሀገር እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን፤ በአስመራ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተደርጓል።በተመሳሳይ ሁኔታ ከግብፅ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና ድብቅ ጣልቃ ገብነት በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ሀገር ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ጠንካራ መልዕክት አዘል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። ከዲፕሎማሲያዊ ውሳኔዎቹ ባሻገር፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው የገቡትን እና በካይሮ እና በአስመራ የተላኩትን የሻዕቢያ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም የውስጥ ቅጥረኞችን የማጽዳት ስራንም በተሳካ ሁኔታ እያከናወነች ትገኛለች። ኢትዮጵያን በታሪክ አጋጣሚ ሁሉ በቀጥታ ወታደራዊ ወራራ ለመፈጸም ተደጋጋሚ ሙከራ አድርጋ ያልተሳካላት ግብጽ አስመራን እየላከች የሄደችበት የሴራ ቀመር ዛሬ ላይ መንቀሳቀስ የሚችል አይደለም። ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ አይደለችም። የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ የውስጥ ድክመቷን ተደግፎ የፈለጉትን ሴራ የሚያስኬዱባት ደካማ ሀገር አይደለችም። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የናይልን የውሃ ፖለቲካ የበላይነት በቋሚነት ቀይሮታል። ሀገሪቱ በቀጣናው የኢነርጂ እና የኢኮኖሚ ማዕከል ሆና ብቅ ብላለች።የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዘመናዊ የውጊያና የቴክኖሎጂ አቅም በመታጠቅ የሀገርን ሉዓላዊነት በጽኑ መደብ ላይ ገንብቷል፤ ማንኛውንም የውስጥና የውጭ ስጋት በከፍተኛ አቅም የመመከት፤ ሲያስፈልግም የማጥቃት ሙሉ ብቃት አለው። በመሆኑም ካይሮ እና አስመራ በጋራ የሸረቡት የማተራመስና የውክልና ጦርነት ሴራ የዛሬዋን ኢትዮጵያ አዲስ እውነታና ቁርጠኝነት ባላገናዘበ ስሁት ስልት ላይ የተመሠረተ ነው። ቀደም ሲል በታሪክ አጋጣሚዎች በውስጥ ባንዳዎችና በውጭ ጠላቶች የተጎነጎኑ ጥምረቶች ሁሉ በኢትዮጵያውያን አይበገሬነት መና እንደቀሩት ሁሉ፣ አሁንም በካይሮ ታቅዶ በአስመራ የሚፈጸመው እኩይ ድራማ የታሰበበት ግብ ሳይደርስ በጽኑ የኢትዮጵያ ክንድ የሚከሽፍ እና የትም የማይደርስ መሆኑ የማይቀር ሀቅ ነው።
ለአፍሪካ ተምሳሌት ከሆነ ምርጫ እስከ መንግሥት ምሥረታ
Oct 4, 2026 446
✍️ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ የአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በግጭትና በተቋማዊ ድክመት የተፈተነ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ምርጫን በሰላም ማካሄድ፣ የሕዝብን ድምፅ ማክበር፣ ውጤትን በተቋማዊ መንገድ ማስተናገድ እና ወደ ሕጋዊ መንግሥት ምሥረታ መሸጋገር እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዚህ ረገድ ለአፍሪካ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ ጠንካራና ገለልተኛ ተቋማት መፍጠሯን፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነጻነት ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መምረጣቸውን፣ በዚህም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የቋመጡ አካላትን ሴራ ማክሸፋቸውን አሳይቷል። ኢትዮጵያ ነገ የምትጀምረው አዲስ ምእራፍ ከሕዝብ ድምፅ ወደ ሥልጣን፣ ከሥልጣን ወደ አደራ፣ ከአደራ ወደ ተግባር የሚወስድ የዴሞክራሲ ሂደት ነው። ከእያንዳንዱ ድምፅ ጀርባ አንድ ዜጋ አለ፤ ከእያንዳንዱ ዜጋ ጀርባ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ ሕልም፣ አንድ ተስፋ እና አንድ የነገ ርዕይ አለ። ሕዝቡ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ከ52 ሺህ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰልፎ ድምፁን ሲሰጥ በካርዱ ላይ የሰፈረውን የመረጠውን ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገሩ የሚያስበውን ተስፋ ነው። ኢትዮጵያውያን መንግሥታቸውን መርጠዋል። አዲሱ መንግሥት ደግሞ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ነገ በይፋ ሥራውን ይጀምራል።ኢትዮጵያውያን ጓጉተው ሲጠብቁት የነበረው ቀን ደርሷል።ጨበክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት ምስረታ ተካሂዷል። በነገው ዕለት ደግሞ ነገ አዲሱ የፓርላማ የሥራ ዘመን መክፈቻና የመንግሥት ምስረታ ይካሄዳል። የዚህ መንግስት ምስረታ ጉዞ የጀመረው ግንቦት 24 በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው። ሕዝብ ድምፁን ሲሰጥ ሥልጣንን ብቻ አይሰጥም፤ አደራ ይሰጣል። መንግሥት ሲመሠረትም የሚያገኘው የሥልጣን ወንበር ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እምነትን የሚሸከም ከባድ ኃላፊነት ነው። ኢትዮጵያ በነገው ዕለት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝብ በድምፁ ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ መንግሥት ምሥረታ በማሸጋገር አዲስ ምዕራፍ ትጀምራለች። ይህም ኢትዮጵያ በሰላማዊ፣ በሕጋዊና በተቋማዊ መንገድ የመንግሥትን ሥልጣን የምታሸጋግር ሀገር መሆኗን የምታሳይበት ታሪካዊ ክስተት ነው። በኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግርና የልዩነት አፈታት ሁልጊዜ በሰላማዊ የሀሳብ የበላይነትና በዴሞክራሲያዊ ፉክክር አልተመራም። የኃይል አማራጭ ብዙ ጊዜ ተሞክሯል። ይህም ብዙ ችግር ወልዷል። ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግርን አባክኗል። ሀገርን በአብዮት ፍዳ ደፍቋታል።ዛሬ ግን በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ መሠረት ላይ የዴሞክራሲ ድልድይ ፈጥሮ የተካሄደው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይህን የቆየ የፖለቲካ መጥፎ ልማድ በመሻገር ሀገሪቱ ወደ ሰለጠነ የሀሳብ ፖለቲካና ወደ ዘመናዊ የመንግሥት ግንባታ እየተሻገረች መሆኗን አሳይቷል። የዚህ ለውጥ ትልቁ መሠረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተሳትፈዋል። ምርጫው እንዳይሳካ በጠላት የተሞከሩ ከባድ ፈተናዎችን አልፈው፣ ማስፈራሪያና እንግልትን በጽናት ተሻግረው ከማለዳ እስከ እኩለ ሌሊት ተሰልፈው፣ ቁርና ሐሩር ሳይበግራቸው ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መርጠዋል። ሕዝቡ ለመረጠው መንግሥት የሰጠው ባዶ ካርድ ሳይሆን የሚፈጸም አደራም ነው። ኢትዮጵያ ነገ የምትጀምረው አዲስ ምእራፍ ከሕዝብ ድምፅ ወደ ሥልጣን፣ ከሥልጣን ወደ አደራ፣ ከአደራ ወደ ተግባር የሚወስድ የዴሞክራሲ ሂደት ነው። ከእያንዳንዱ ድምፅ ጀርባ አንድ ዜጋ አለ፤ ከእያንዳንዱ ዜጋ ጀርባ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ ሕልም፣ አንድ ተስፋ እና አንድ የነገ ርዕይ አለ።ሕዝቡ ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ከ52 ሺህ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰልፎ ድምፁን ሲሰጥ በካርዱ ላይ የሰፈረውን የመረጠውን ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሳይሆን ስለ ሀገሩ የሚያስበውን ተስፋ ነው። “የትኛው ፖሊሲ የተሻለ ነው? የትኛውን አቅጣጫ እመርጣለሁ? ምን ዓይነት መንግሥት እፈልጋለሁ? ለልጆቼ ምን ዓይነት ኢትዮጵያን አስረክባለሁ?” የሚሉ ጥያቄዎችን አስቦ ነው ድምፅ የሰጠው። በዚህ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች መሳተፋቸውም ይህንን የሕዝብ ምርጫ ለመወሰን ሰፊ የፖለቲካ አማራጭ ፈጥሯል። ስለዚህ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሸናፊነት በአንድ ፓርቲ ድል ብቻ የሚጠቃለል አይደለም። የዴሞክራሲ ሂደቱ ራሱ አሸናፊ ሆኗል። ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ናት። ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ ሥልጣን ሽግግር ሁልጊዜ በሰላማዊ የሀሳብ ውድድር የተመራ አልነበረም። የኃይል አማራጭ ብዙ ጊዜ በዴሞክራሲ የሚመራ ፖለቲካ ውሳኔን ተክቷል። ሰባተኛው ምርጫ ግን አዲስ መንገድ አሳይቷል። ሥልጣን በኃይል ሳይሆን በሕዝብ ፈቃድና ምርጫ እንደሚመጣ አረጋግጧል። ይህም ለአፍሪካ ቀንድና ለመላው አፍሪካ ምሳሌ ሆኗል። የአፍሪካ ቀንድ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካዊ ውጥረት፣ በግጭትና በተቋማዊ ድክመት የተፈተነ አካባቢ ነው። በዚህ አካባቢ ምርጫን በሰላም ማካሄድ፣ የሕዝብን ድምፅ ማክበር፣ ውጤትን በተቋማዊ መንገድ ማስተናገድ እና ወደ ሕጋዊ መንግሥት ምሥረታ መሸጋገር እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዚህ ረገድ ለአፍሪካ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ ነው። ኢትዮጵያ ጠንካራና ገለልተኛ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ መፍጠሯን፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነጻነት ይበጀናል ያሉትን መንግሥት መምረጣቸውን፣ በዚህም በኃይል ሥልጣን ለመያዝ የቋመጡ አካላትን ሴራ ማክሸፋቸውን አሳይቷል። ምርጫው እንዳይሳካ ብዙ የሴራ ድር በጠላትና በባንዳ ተተብትቦ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ “ምርጫው ራሱ የጠላት ኢላማ ነበር” ምክንያቱም የምርጫው መሳካት የሚያሳፍራቸው ብዙ የስሁት መንገደኞች ነበሩ፤ ከግጭት የሚያተርፉ የደም ነጋዴዎችም ነበሩ፣ በኃይል ሥልጣን መናጠቅ የሚመኙ ከንቱ ሕልመኞችም ነበሩ።ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ለፕሮፓጋንዳም ሆነ በጠላት ለተደቀነባቸው አፈሙዝ ሳይበገሩ ድምፅ ሰጥተዋል። ከማለዳ እስከ እኩለ ሌሊት በጽናት ተሰልፈው ሀገርን ለማሻገር ይበጀናል ያሉትን መርጠዋል። በዚህም ጠላት ሲያፍር ኢትዮጵያ ግን አሸንፋለች። ይህ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የፖለቲካ ባህል ላይ ትልቅ ለውጥ ነው። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሌላኛው ድል የሚለካው በውጤቱ ብቻ አይደለም፤ በፖለቲካዊ ተሳትፎ ስፋትና በአካታች ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ባሳረፈው ጉልህ አሻራም ጭምር ነው።በዚህ ምርጫ ከ42 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩዎች በምርጫ ሜዳው ተሳትፈዋል። ይህም የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ለተለያዩ ሐሳቦች፣ አማራጮችና የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች በር የከፈተ መሆኑን ያሳያል። የዚህ ምርጫ ልዩ ገጽታ ግን በተወዳዳሪዎቹ ቁጥር ብቻ አይወሰንም። ከዚያ በላይ፣ ገዥው ፓርቲ ለተፎካካሪዎች የበለጠ የመወዳደሪያ ዕድል እንዲፈጠር ያደረገው ውሳኔ በራሱ ግዙፍ የፖለቲካ ትርጉም አለው። ብልፅግና ፓርቲ 15 በመቶ የምክር ቤት ወንበሮችን በሚያስገኙ የምርጫ ክልሎች ላይ እንዳይወዳደር መወሰኑ፣ ለሌሎች ፓርቲዎች የተለየ የፉክክር ሜዳ የፈጠረ እርምጃ ነበር። በሌላ አገላለጽ፣ ገዥው ፓርቲ የራሱን የምርጫ ዕድል በመገደብ ሌሎች የፖለቲካ ድምፆች ወደ ምክር ቤቱ እንዲገቡ ተጨማሪ ቦታ ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን ውሳኔ ሲያብራሩ፣ ዓላማው ብዙ ድምፆች ወደ ፓርላማ እንዲገቡና አካታች ዴሞክራሲ እንዲጠናከር ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። በእርግጥም ይህ አንዱ የዴሞክራሲ ጥንካሬ መለኪያ ነው። ይህ ውሳኔ በምርጫ ወቅት የተወዳዳሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ የተደረገ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገሪቱን ፓርላማ የተለያዩ የሕዝብ ሐሳቦች የሚወከሉበት የበለጠ ውክልና ያለው መድረክ ለማድረግ የተወሰደ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው። ምርጫው የአንድን ፓርቲ ድል ብቻ ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ ሂደት ብዝሃ ድምፆች እንዲሰሙ ዕድል የፈጠረ ነው። በዚህ ረገድ የሰባተኛው ምርጫ ዋና ትርጉም ከምርጫ ውጤቱ በላይ ነው። 15 በመቶውን የምርጫ ሜዳ ለሌሎች ተወዳዳሪዎች መተው ደግሞ የአካታችነት መርህን በተግባር ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ሆኗል። ይህ በየትኛውም አፍሪካ ሀገር ያልተደረገ ነው። ብዙ ድምፆች ወደ ፓርላማ ሲገቡ፣ ዴሞክራሲም የበለጠ ይሰፋል። ይህም የሰባተኛው ምርጫ ከውጤቱ በላይ የሚታይበት ሌላኛው ድል ነው። አዲስ የሚመሠረተው መንግሥትም የበርካታ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የሚሳተፉበት አካታች መንግሥት ነው። የምርጫ ድል የመንግሥት አደራ ነው። የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ ድምፅ አግኝቶ መንግሥት የመመሥረት ሕጋዊ መብት አግኝቷል። ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በሆነው የ501 የምርጫ ክልሎች ውጤት መሠረትም 438 የፌዴራል ፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፏል። ግን የምርጫ ድል የምክር ቤት ወንበርን በማሸነፍ ቢጀምርም በዚህ አያበቃም። ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር መፈጸም ቅቡልነትን ያጸናል። ይህም ነገ የሚመሠረተው መንግሥት የሚጠብቀው ትልቁ ኃላፊነት ነው። ሕዝቡ መርጧል። አሁን ደግሞ አዲሱ መንግሥት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ነገ በይፋ ሥራውን ይጀምራል። በመንግሥት ምሥረታው ከመራጩ ወደ ተመራጩ የሚሸጋገረው የአደራ ኪዳንም ይህ ነው። ቅቡልነት ያለው ሕጋዊ መንግሥት በምርጫ ይመሠረታል። የሚጸናው ግን በሥራ ውጤቱ ነው። የጠንካራ መንግሥትነት መለያውም በሕዝብ የተጣለበትን እምነትና አደራ የሚወጣ፣ ጠንካራ ተቋማትን የገነባ፣ ሕግን ያስከበረ፣ ተፎካካሪ ሐሳቦች የሚደመጡበት እና የሕዝብን ጥያቄ በተጨባጭ ውጤት የሚመልስ መንግሥት ሲሆን ነው። ስለዚህ ነገ የሚመሠረተው መንግሥት በምርጫ ማኒፌስቶው የገባውን ቃልና በሕዝብ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት የአምሥት ዓመት ጉዞውን በተግባር የሚጀምር መሆን አለበት። ይህ እንደሚሆን ደግሞ ብዙ እርሾዎች አሉት። አሁን የተመረጠው መንግሥት ባለፉት አምሥት ዓመታት ለሕዝብ ቃል ገብቶ ባሳካቸው ድሎች ዳግም ዕድል የተሰጠው ነው። በምግብ ራስን የመቻል ግብን በማሳካት ተረጅነትን አስቀርቷል። ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሕዝብ ቃል በገባው መሠረት አሳክቷል። ሕዝብን ያማረረውን የሌብነትና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ ከሰው ንክኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል የመሶብ አገልግሎትን በመላ ሀገሪቱ አስጀምሯል። የኑሮ ውድነትን ለማቃለልም ምርትና ምርታማነትን በብዙ እጥፍ በማሳደግ እና የተበላሸ የገበያ ሰንሰለትን በማስተካከል ወሳኝ ለውጥ አምጥቷል። ታላቋን ኢትዮጵያን የሚመጥኑ የክብርና የሉዓላዊነቷ ዘብ የሆኑ የጸጥታና ደህንነት ተቋማትን ገንብቷል። በታላቅ ርዕይ በመመራትም ኢትዮጵያን ከኩስመና የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ወደ ተደማጭና ተፅዕኖ ፈጣሪ ከፍታ አሸጋግሯታል። በቱሪዝም ልማት የኢትዮጵያን መልክ አድምቋል።በከተሞች ኮሪደር ልማት ጉስቁልናን አስወግዶ ከተሞችን ውብ የመዝናኛ፣ የሥራና የምቹ መኖሪያ ማዕከል እያደረገ ይገኛል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ከቀደሟት እኩል እንድትራመድ እያደረገ ይገኛል። ማዕድኗን ገልጣ ወደ ሀብት እንድትቀይር በውጤት የታጀበ መንገድን ጀምሯል። በኢንዱስትሪ ረገድም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ስትራቴጂክ ምርቶች እንድትተካ ጠንካራ መሠረት ጥሏል። የሕዝብን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስም ባለፉት ዓመታት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቤቶች ከመገንባት ባለፈ በሚቀጥሉት አምሥት ዓመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተጨማሪ ቤቶችን እንደሚገነባ በማብሰር ወደ ሥራ ገብቷል። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያን ለዘመናት ከኖረችበት ውስብስብ የመከራ አዙሪት ተላቃ ጠንካራ ብሔራዊ መግባባትና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲኖራት ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የገባውን ቃል በተግባር ፈጽሟል። አራት ዓመት ተኩል የፈጀ ሀገራዊ ምክክር በማካሄድ በወሳኝ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ኢትዮጵያውያን መግባባት ላይ እንዲደርሱ በማድረግ አዲስ ታሪክ ጽፏል። እንዲሁም ኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገቷን የሚመኙትም ሆኑ የማይመኙትን የምታጓጓ ሀገር እንድትሆን አስችሏል። ይህ ጉዞ በአዲሱ መንግሥት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሰላምን ማጽናት፣ ሕግን ማስከበር፣ ለሌብነት የማይመች አሠራርን ማጠናከር፣ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት፣ የኑሮ ውድነትን መግራት፣ የሕዝብን ኑሮ በተጨባጭ መለወጥ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ መሻቶች ማሳካትና ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አካታችነትን ያረጋገጠችና ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ያረጋገጠች የአፍሪካ ተምሳሌት ሀገርን መገንባት ለአዲሱ መንግሥት ከሕዝብ የተሰጡ አደራዎች ናቸው። መንግሥት አደራውን እንዲወጣ ደግሞ የሕዝብ፣ የግሉ ዘርፍ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ መገናኛ ብዙኃንና የእያንዳንዱ ተቋም የተደመረ ትጋት ወሳኝ ነው። ይህ ከተሳካ፣ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ የምርጫ ባህል ብቻ ሳይሆን በሕጋዊ የሥልጣን መሠረት፣ የሕዝብን አደራ በመወጣት፣ በአካታች መንግሥትና በልማት ድል የአፍሪካ ሞዴል መሆኗን በተግባር ታረጋግጣለች።
ልዩ ዘገባዎች
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 163
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 131
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 135
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
Oct 5, 2026 142
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ የዛሬው እለት ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ ታሪኳ ሌላ አዲስ ምዕራፍ የምትከፍትበት ታሪካዊ እለት ነው። በግንቦት ወር የተካሄደው ምርጫ፣ የሕዝብ ድምፅና ውሳኔ ወደ ተጨባጭ የመንግሥት ምስረታ የተሸጋገረበት ወቅት ላይ ይገኛል። የሕዝብ ድምፅ ድምር ውጤት መንግስት የሚመሰረትበትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጽኑ መሰረት የያዘበት አዲስ የታሪክ ምእራፍ ተከፍቷል። የምርጫ ሂደት በራሱ የሚጠናቀቀው የምርጫ ውጤት በመገለጹ ብቻ ባለመሆኑ የሕዝብ ውሳኔ በተቋማት በኩል ተግባራዊ ሲሆንና የሕዝብን የልማትና የአገልግሎት ፍላጎት ማስተናገድና ምላሽ መስጠት የሚችል መንግስት ሲመሰረት ነው። በዚሁ መሰረትም ባሳለፍነው ሳምንት ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ክልሎች የመንግሥት ምስረታ ሂደታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ ገብተዋል። በዛሬው እለት ደግሞ የፌዴራል መንግስት የሚመሰረትበት፤ አዲሱ ፓርላማ ሥራውን በይፋ የሚጀምርበትና አዲስ የፌዴራል መንግሥት የሚመሠረትበት ታሪካዊ እለት ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የተለያዩ የፖለቲካ ሥርዓቶችንና የለውጥ ወቅቶችን አሳልፋለች። በእያንዳንዱ ዘመን የሀገሪቱ ፖለቲካ በሕዝቡ ፍላጎት፣ በሀገራዊ ጥቅምና በዘመኑ ተግዳሮቶች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ የታየበት አጋጣሚ የበዛ ነበር ማለት ይቻላል። የዛሬው የመንግስት ምስረታ ግን ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፃቸውን በነፃነት የሰጡበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ድምር ውጤት ነው። በመሆኑም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የቆዩ የፖለቲካ ስብራቶችን በማከም የኢትዮጵያን የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚተልምና ቀጣይ መዳረሻዋን የሚወስን ይሆናል። ታላቋን ኢትዮጵያ ለመምራት ትልቅ ርዕይ የሰነቀ መንግስት የግድ በመሆኑ እንደ ሀገር የተያዙ እቅዶችን በተደመረ አቅም በማሳካት እድገትና ማንሰራራቷን ማስቀጠል ይገባል። በመሆኑም አዲሱ መንግሥት በምርጫ ወቅት ለህዝብ የገባውን ቃል በማክበር ለተግባራዊነቱ መትጋት ይጠበቅበታል። የህዝብን አደራ በአግባቡ በመወጣት ቃልን በተግባር መፈፀም የግድ ይላል። የዜጎች የሥራ ዕድል፣ የኑሮ ውድነት፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ፣ የልማት ፍላጎት፣ የፍትሕ አገልግሎትና የመንግሥት ተጠያቂነት የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎች ናቸው። ፓርላማውም ሕግ ከማውጣት ባሻገር የመንግሥትን አፈጻጸም መከታተል፣ ተጠያቂነትን ማረጋገጥና የዜጎችን ድምፅ ወደ ፖሊሲና የሕግ አቅጣጫ መቀየር ይጠበቅበታል። በዚህ መልኩ የሚቀጥለው ፓርላማ የዴሞክራሲ ሥርዓቱን በማጠናከር የህዝብ የልማት መሰረቶች ተጠናክረው የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል። የሕዝብ ድምፅ የሥልጣን ምንጭና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት የሚያኖር መሆኑ ይታወቃል። በህዝብ ድምጽ የተሰጠ ሃላፊነት ደግሞ ተጠያቂነት ጭምር ያለበት አደራ ነው። በመሆኑም አዲሱ መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለዘላቂ ሰላምና ልማት፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የህግ የበላይነት መስራት ይጠበቅበታል።
መጣጥፍ
ኢትዮጵያ እና ቡና
Sep 30, 2026 362
ኢትዮጵያ- ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የተገኘውና በዓለም ላይ የተስፋፋው ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ በብዛት የሚጠጣ ተፈለጊና ተወዳጅ ምርት በመሆን የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሮት ይገኛል። በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ የአርሶ አደሮች የዓለምን 80 በመቶ ቡና እንደሚያመርቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ ቪትናም እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ አገሮች ሲሆኑ ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በመሆኑም የቡናን ዓለም አቀፍ ግብይትና ተፈላጊነት እንዲሁም የተጠቃሚዎች ብዛት መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 1 የዓለም የቡና ቀን አድርጎ ሰይሞታል። በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያው የዓለም የቡና ቀን እ.ኤ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመከበር ላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቡና ለኢትዮጵያዊያን የገቢ ምንጭ ብሎም የባህል መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ፣ የአብሮነት ማሳያ፣ የማኅበራዊ ትስስርና የውይይት መድረክም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በልዩ ልዩ የጣዕም የሚገለጽና በእጅጉም ተፈላጊ ምርት በመሆኑ በተለይም በአርሶ አደሮች ህይወትና አጠቃላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው። በአንዳንድ አካባቢዎች ቡና ተፈልቶ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ዙር የመጠጣት ልምድም አለ። ምንም እንኳን አጠራራቸውና ከእያንዳንዱ ዙር ጋር የሚያያዙ ትርጓሜዎች በአካባቢው ባህል መሠረት የሚለያይ ቢሆንም የመጀመሪያው “አቦል”፣ ሁለተኛው “ቶና” እንዲሁም ሶስተኛው “በረካ” እየተባለ ይጠራል። የዚህ የቡና ስነ ስርአት ዋነኛ ዓላማ በተደጋጋሚ መጠጣት ሳይሆን በአንድነት መቆየትን፣ ለሌላው ጊዜ መስጠትንና የማኅበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ የባህል ምልክቶች ናቸው። ከቡናው ጋር የሚቀርብ (የቡና ቁርስ) እንደየ ሁኔታው ፋንዲሻ፣ ቆሎ፣ ዳቦ ወይም ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦች የሚቀርቡ ሲሆን እጣን አጭሶ በመመራረቅ የሚጠጣም ይሆናል። በዘመናዊው ዓለም ቡና የንግድ፣ የሥራና የመዝናኛ አካል ሆኗል። በቡና ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎችና በዘመናዊ የቡና ማቅረቢያ ሥፍራዎች ሰዎች ይገናኛሉ። ሆኖም በኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩ ትርጉም ከጣዕምና ከንግድ በላይ ይዘልቃል። ከቤት እስከ ጎረቤት ፤ ከታሪክ እስከ ትውልድ የቆየ ትስስር ያለው የኢትዮጵያን ልዩ መገለጫ ባህል ነው። የቡና ባህላዊ ሥነ ሥርዓትን በማስተዋወቅ እንዲሁም የቡና ታሪክን ከተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮ በማሳየት የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርስ ለዓለም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡና የባህል ይዘቱ እንዳለ ሆኖ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆን ለእድገትና ማንሰራራት ሁነኛ መሰረት እየሆነ ይገኛል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቡና ቀን የቡና ዘርፍ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማድረግ “ቡና የዘላቂ መፍትሄ አካል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።
የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ
Sep 29, 2026 258
ጋምቤላ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ የጋምቤላ ክልል በሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውሃ ሀብት፣ ደኖች፣ የሣር ምድሩና በዱር እንስሳትና ብዝሃ ሕይወት እምቅ ሃብት ያለው መሆኑ ይታወቃል። የአኙዋሃና የማጃንግ የተፈጥሮ ሃብቶች ለልዩ የቱሪዝም መስህቦች ሆነው ይጠቀሳሉ። በተለይም ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በሰፊ የሳር ሜዳዎች፣ በውሃ አካላትና በተለያዩ የዱር እንስሳት የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ነው። የዱር እንስሳት ጉብኝት፣ የአዕዋፍ እይታ፣ የተፈጥሮ ጉዞና አጠቃላይ የኢኮ-ቱሪዝም ሃብት ፓርኩ የታደለ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወንዞችና ረግረጋማ መሬቶች፣ የደን ሃብት ከሰዎች አኗኗርና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ጋር በማሰናሰል የቱሪዝም ሃብት ማድረግ ተችሏል። በመሆኑም ጋምቤላ ያለውን የተፈጥሮና የባህል እምቅ ሃብት በዘላቂነት በማልማት፣ የተፈጥሮ ጥበቃን ከቱሪዝም ልማት ጋር በማስተሳሰር ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት አዲስ አቅም መፍጠር እየተቻለ ነው። የባዮስፌር ሪዘርቭ ዋና ዓላማ ተፈጥሮን ከሰው ልጅ የኢኮኖሚና የኑሮ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የዘላቂ ልማትና የምርምር ከባቢን መፍጠር በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና የማጃንግ የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ሊመዘገብ ችሏል። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ምድር ያካለለ ሲሆን በውስጡ በርካታ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ። በጥብቅ ደኑ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ የዕፅዋት፣ ከ327 የሚልቁ የአእዋፍ፣ ከ86 በላይ አጥቢና ተሳቢ የእንስሳት ዝርያዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ የተፈጥሮ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውና ተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ፣ የዱር እንስሳት ሃብት ኮሪደር እና የዘላቂ ልማት ማዕከል ነው ማለት ይቻላል። የአካባቢው ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር ተስማምቶ በመኖር የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ለትውልድ ጠብቆ በማቆየት ረገድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው። በ225 ሺህ 490 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የማጃንግ የተፈጥሮ ደንም በውስጡ 550 የዕፅዋት ዝርያዎች፣ 33 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች እንዲሁም 130 የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዝቅተኛና ከፍተኛ መልክአ ምድርን አካቶ የያዘው ጥብቅ የተፈጥሮ ሃብቱ በተለይም ለንብ ማነብና ለፍራፍሬ ልማት እጅግ ተመራጭ አካባቢ ነው። የጋምቤላ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለምግብ ዋስትና እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ ወሳኝ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።