አርጀንቲና ግብጽን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
አርጀንቲና ግብጽን በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018 (ኢዜአ)፦ የ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የ16ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ አርጀንቲና ግብጽን ከ2 ለ 0 መመራት ተነስታ 3 ለ 2 አሸንፋለች።
ማምሻውን በአትላንታ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ያስር ኢብራሂም በ15ኛው እና ሙስጠፋ ዚኮ በ67ኛው ደቂቃ ለግብጽ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሙስጠፋ ዚኮ በ58ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል በቪዲዮ የታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ጥፋት በመሰራቱ ተሽሯል።
ክርስቲያን ሮሜሮ በ79ኛው፣ ሊዮኔል ሜሲ በ83ኛው እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ በ93ኛው ደቂቃ የአርጀንቲናን ግቦች አስቆጥረዋል።
አርጀንቲና ከውድድሩ ከመሰናበት ጫፍ ደርሳ ውጤቱን በመቀልበስ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች።
በሩብ ፍጻሜው ከኮሎምቢያ እና ስዊዘርላንድ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
ኮሎምቢያ እና ስዊዘርላንድ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በቢሲ ፕሌስ ቫንኩቨር ስታዲየም ይጫወታሉ።