ቀጥታ፡

በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ሐረር ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):-በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሂደትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በከተማና በገጠር ወረዳዎች በሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ፈተናውን እየወሰዱ ያሉ ተማሪዎችን አበረታተዋል።

ተማሪዎቹም በፈተናው  የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።


 

ርዕሰ መስተዳድር በወቅቱ በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በሐረሪ ክልል የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአጠቃላይ 2 ሺህ 678 ተማሪዎች እየወሰዱ ይገኛሉ።

ፈተናው በክልሉ ከተማና ገጠር በሚገኙ 10 የመፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ በበይነመረብ  እየተሰጠ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም