የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የኮፕ 32 ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 30 ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የኮፕ 32 ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 30 ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የኮፕ 32 ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከ30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 30) ፕሬዝዳንት አምባሳደር አንድሬ አራንሃ ኮሪያ ዶ ላጎ እና ከቡድናቸው ጋር ውይይት አድርገዋል።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) አስተናጋጅ ለመሆን በምታደርገው ዝግጅት ላይ፣ ከቀደምት አዘጋጅ ሀገራት ልምድ መቅሰም ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል።
በዚህም መንፈስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የኮፕ 32 ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 30 ፕሬዝዳንት አምባሳደር አንድሬ አራንሃ ኮሪያ ዶ ላጎ እና ከቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
የውይይቱ ዓላማ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ጉባኤ ከማዘጋጀት ጋር የተያያዙ ዕውቀቶችን እና የተወሰዱ ትምህርቶችን መለዋወጥ መሆኑን ተመላክቷል።