ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዓላማ ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ማጠናከር ነው
Feb 20, 2026 75
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዓላማ የዘመናት ሥብራትን ለመጠገንና ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ማጠናከር ነው። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የምትታተመው "ነጋሪ" መጽሔት፤ "ምክክር ለሀገር ክብር" በሚል ርዕስ የሀገራዊ ምክክሩን የዘመናት ሥብራትን ለመጠገን፣ የኮሚሽኑ አራት የክዋኔ ምዕራፎች፣ አካታችነትና ተሳትፎ እንዲሁም ተግዳሮቶችና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ዳሥሣለች። በዚህም ኢትዮጵያ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮችንና ጫፍ የረገጡ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት እና ለትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር መጀመሯ ተብራርቷል። እንዲሁም የታሪክ አረዳድ ልዩነትን በተመለከተ በሀገር ግንባታ ታሪክ፣ በሰንደቅ ዓላማና በሕገ-መንግሥት ላይ ያሉ አለመግባባቶችን በምክክር ለመፍታት መታቀዱም ተጠቁሟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጡትን ማብራሪያ በመጥቀስ፤ ምክክሩ የዘመናት ሥብራትን ለመጠገንና ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ለማጠናከር ማለሙን መግለጻቸውን ነጋሪ አብራርታለች። መንግሥት ለውጤታማነቱ ቁርጠኛ መሆኑንም ማረጋገጣቸውን ነጋሪ ተመልክታለች። በዐዋጅ ቁጥር 1265/2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራዎቹን በአራት ዋና ዋና ምዕራፎች ከፋፍሎ እያከናወነ እንደሚገኝም በመጽሔቱ ተመላክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የሚሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል። በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ዜጎችም ሐሳባቸው እንዲደመጥ የማረሚያ ቤት ታራሚዎችን የማሳተፍ እንቅስቃሴ መከናወኑ ተመላክቷል። ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ውስብስብ ችግር ወጥታ የጋራ መግባባትና ዘላቂ ሰላም የምታሰፍንበት "ወርቃማ ዕድል" መሆኑን መጽሔቷ አፅንኦት ሰጥታለች ።
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የመረጃና የመዝናኛ ይዘቶችን መመልከት የሚያስችላቸውን ቴሌስትሪም የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ
Feb 20, 2026 33
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የመረጃና የመዝናኛ ይዘቶችን መመልከት የሚያስችላቸውን ቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ። በዚህ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ቴሌስትሪም በመዝናኛ፣ ትምህርት፣ ጤና እና በተለያዩ ዘርፎች ይዘትን በማዘጋጀትና ለሚሊዮኖች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎቱም ሃሳብ ያላቸው አካላት ይዘት በመፍጠር የሚያስተላልፉበት "ብሔራዊ የዲጂታል ይዘት መድረክ" መሆኑን አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ 98 በመቶ መረጃ የሚተላለፈው በሳተላይት መሆኑን በመጥቀስ፤ የዲጂታል መረጃ ተጠቃሚዎች ሁለት በመቶ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በዲጂታል አማራጭ የቀረበው የቴሌስትሪም አገልግሎት ምስሎችን በ4k፣ 8k እና በHD ጥራት በማሳየት የሚያድግና የሚሰፋ የቴሌኮም አገልግሎት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በየጊዜው የሁሉንም ዜጎች የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝ አንስተዋል። የቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት ደንበኞችም የአገልግሎት ክፍያዎችን ባሉበት ቦታ በቴሌ ብር መፈጸም እንደሚችሉ አስረድተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም 108 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ከ87 ሚሊዮን ደንበኞች 50 ሚለዮን የሚሆኑት የብሮድባንድ ተጠቃሚ በመሆናቸው የቴሌስትሪም አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለሳተላይት ክፍያ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ከማዳን ባለፈ ያልተቆራረጠ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል። የቴሌስትሪም ምርቶችን በዘመን ገበያ በማዘዝ በኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከላት ማግኘት እንደሚቻል ገልጸዋል።
የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የመስኖ አውታሮችን በመጠቀም ምርታማነትና ተጠቃሚነታቸውን አሳድገዋል
Feb 20, 2026 30
ሀዋሳ፣ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡-በመንግስት የተዘረጉ የመስኖ አውታሮች ዓመቱን ሙሉ በማልማት ምርታማነታቸውን በማሳደግ የተሻለ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የወረዳው አርሶ አደሮች መንግስት በአካባቢያቸው የዘረጋላቸውን የመስኖ ልማት አውታር በመጠቀም ገቢያቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው የገላልቻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሲራቴ ገላ አካባቢያቸው ቆላማ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከዚህ በፊት የክረምት ዝናብን ብቻ ጠብቀው በቆሎ ያመርቱ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ በዓመት አንዴ የሚያመርቱት የበቆሎ ምርት ከቤት ውስጥ ፍጆታና አነስተኛ ገቢ ከማስገኘት ባለፈ የተሻለ ተጠቃሚ ሳያደርጋቸው መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት መንግስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በመቆፈሩና የመስኖ አውታር በመዘርጋቱ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ ማምረት በመቻላቸው በኑሯቸው ላይ ትልቅ ለውጥ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡ የጃራ ሂእኔሳ ቀበሌ አርሶ አደር እንዳለ እንግዳ በበኩላቸው አነስተኛ የውሃ ጉድጓድ መሳቢያ ሞተር ተጠቅመው በሚያወጡት ውሃ በዓመት ሦስት ጊዜ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ መስኖ በመጀመሩ እሳቸውን ጨምሮ የአካባቢው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ዓመቱን ሙሉ ማምረት መጀመራቸውን ገልጸው፣ መንግስትም የውሃ መሳቢያ ሞተርን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን ማድረጉን ተናግረዋል። በዓመት ሦስት ጊዜ ጥቅል ጎመንና ሌሎች አትክልቶችን እንደሚያመርቱ ገልፀው በአንድ ዙር እስከ 300 ሺህ ብር ገቢ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በክልሉ የመስኖ ልማት ሥራ በአብዛኛው ከወንዞች፣ ጅረቶችና አነስተኛ ጉድጓዶች ውሃ በሞተር በመሳብ እንደሚከናወን ጠቅሰዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በቆላማና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች በቅርብ ጊዜያት ብቻ 6ሺህ ሄክታር መሬት የሚያለሙ የተለያዩ የመስኖ ፕሮጀክቶች ዕውን መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ሀዋሳ ዙሪያና ሎካ አባያ ያሉ ወረዳዎች ከዚህ በፊት በዓመት አንድ ጊዜ በቆሎ ከማምረት ወጥተው ዓመቱን ሙሉ ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይህም አርሶ አደሩን የተሻለ ተጠቃሚ አድርጓል ያሉት ኃላፊው ልማቱ የአካባቢውን ገበያ በማረጋጋትም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አመልክተዋል። በዘንድሮው በጋ በመስኖ ለማልማት ከታቀደው 80 ሺህ ሄክታር መሬት እስካሁን ድረስ 73 ሺህ ሄክታሩ መልማቱንም ተናግረዋል፡፡
የቡና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Feb 20, 2026 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ የቡና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማህበር 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ሀገሪቱ በዘርፉ የጀመረችው የጥራትና የብዛት ምርት የማሳደግ ባህል ለውጭ ምንዛሬ ግኝት መጠናከር ትልቅ አቅም እየሆነ ነው። ለዚህም እንደ ማሳያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የቡና ምርት የሶስት እጥፍ እድገት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። ቀደም ሲል በሄክታር ስድስት ኩንታል የነበረው የቡና ምርት በአሁኑ ወቅት ወደ አሥር ኩንታልና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማህበር ከባለስልጣኑ ጋር በመቀናጀት የዘርፉን ተዋንያን በማሰልጠንና የስራ እንቅስቃሴው በእውቀትና በክህሎት እንዲመራ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በያዝነው በጀት ዓመት ከቡና ሽያጭ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት የታቀደውን ግብ ለማሳካት ማህበሩ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቡና ንግድ ስርአቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ ባለድርሻ አካላት ምርታቸውን በወቅቱ ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸውና ዋጋ ሲተምኑም ዓለም አቀፍ ገበያን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ጉባኤው የኢትዮጵያን አረንጓዴ ወርቅ ይበልጥ ለማዘመንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ማህበሩ ባካሄደው 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፣ ባለፉት ጊዜያት የቡና አመራረት ዘዴን በቴክኖሎጂና በምርምር ለማገዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ ስራ ተከናውኗል ብለዋል። አርሶ አደሮች የተሻሻሉና ምርታማ የቡና ዝርያዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰው፤ በቡናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አቅራቢዎችና ላኪዎች በንግድ ሂደቱ ውስጥ በቀላሉ የሚገናኙበትና መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ የቡና ልማት ስራው በዘመናዊ የእርሻ ዘዴዎች እንዲደገፍ በማድረግ ረገድ ማህበሩ ጉልህ ሚና መጫወቱ ጠቅሰዋል፡፡ 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤው በዋናነት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም፣ በቀጣይም የቡና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የማህበሩ አባላት አቶ ፈጠነ የኋላሸት እና አቶ ደግፌ ኢድሉ በበኩላቸው የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በጋራ በመሆን የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በመትከል ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ ለዘርፉ እድገት የሚያደረጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ጠቁመዋል፡፡
አስቻይ ፖሊሲና ህጎችን በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Feb 20, 2026 43
ሀዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- አስቻይ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊስና ህጎችን በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ። "ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፣የሚዲያ አስተዳደርና ቁጥጥር በኢትዮጵያ" በሚል ርእስ ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ውይይት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በወቅቱ እንደገለጹት የሃሳብ ነጻነት በአለም አቀፍ ህጎችና ህገ-መንግስቱ ውስጥ የተካተተ መረጃ የማግኘትና ለሌሎች መብቶች ጥበቃ የሚያደርግ መብት ነው። በዚህም እንደ ሀገር አስቻይ ፖሊሲዎችና ህጎችን በማውጣትና በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የ2012ቱ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲና እሱን ተከትለው የወጡ አዋጆችና ህጎች ከዚህ ቀደም የነበሩ አሳሪ ህጎችን በመሻር ለሚዲያ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓቱ ምቹ መደላድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በተለይም ግልጽና ቀላል የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የሚዲያውን ምህዳር በቁጥርና በዓይነት ማስፋት መቻሉን ጠቅሰው በሀገሪቱ 310 የሚደርሱ መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። የጋራ የቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋትም በርካታ ተቋማትና የሙያ ማህበራትን ያሳተፉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የሀሳብ ነጻነትን የሚገድቡ ሀሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች እንዲወገዱ የሚያደርግ አዋጅ በማውጣት ችግሩን የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በውይይቱ የጸደቁ ህጎች ተግባራዊነት፣ በወጡ ዝርዝር ህጎችና በመገናኛ ብዙሃን አገልግሎት አሰጣጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መነሳታቸውን ገልጸዋል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናትና የጋዜጠኝነት ተባባሪ ፕሮፌሰር መልሰው ደጀኔ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ለማንኛውም እድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሃገር የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲን ተከትለው የወጡ ህጎችና አዋጆችን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ምህዳሩን እንዲያሰፉ መጠቀም ይገባል ብለዋል። መገናኛ ብዙሃንም ራሳቸውን በራሳቸው መቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተቋማዊ አንድነት በመፍጠር አቅማቸውን ማጎልበትና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንዲረጋገጥ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተናግረዋል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊና ቀጠናዊ ፋይዳ ባላቸውና የፖሊሲ ግብዓት በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዘለቀ አርፍጮ (ፕ/ር) ናቸው የዛሬው የፖሊሲ ውይይት ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ስድስት ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀት የሃሳብ የበላይነትን የማረጋገጥና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የማጎልበት ተግባር እንደሚጠናከርም ገልጸዋል። በመድረኩ ሁለት የመወያያ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ፖለቲካ
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዐርማ ተመረቀ
Feb 20, 2026 66
ሐዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነው የዕዙ ዐርማ የምረቃ መርሐ-ግብር ተከናውኗል። ዐርማውን የመረቁት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው። እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የዕዙን የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በሐዋሳ ከተማ ተከፍቷል። በሌላ በኩል የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የመጽሐፍ ምረቃ እንደሚከናወን ይጠበቃል። የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigital
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ -ርዕይ በሐዋሳ ተከፈተ
Feb 20, 2026 58
ሐዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- በሀገር መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነ የዕዙን የዓመታት ጉዞና ትጥቅ የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በሐዋሳ ከተማ ተከፍቷል። የፎቶ ዐውደ-ርዕዩን መርቀው የከፈቱት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ናቸው። በዚሁ ዝግጅት ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብዳታ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል። በተጨማሪም የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ነዋሪዎች ታድመዋል። የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አካል የሆነው የመጽሐፍ ምረቃ እንደሚከናወንም ተጠቁሟል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመጽሐፉ ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል::
ለመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ የቁሳቁስ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው
Feb 20, 2026 76
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ሥራዎችን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አስጎብኝቷል። በጉብኝቱ ወቅት የቦርዱ የሎጂስቲክስ ኃላፊ አቶ መላኬ አሉላ እንደገለጹት፤ ቁሳቁሶችን ለየምርጫ ጣቢያዎቹ የመለየትና የመደልደል ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የዝግጅት ሥራው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ 52 ሺህ 720 የምርጫ ጣቢያዎችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ለእያንዳንዱ ጣቢያ ተደራሽ የሚደረጉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቅሬታ አፈታት መመሪያዎች እና መረጃ ሰጭ ፖስተሮች በዝርዝር ተለይተው እየተዘጋጁ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በሂደቱ ላይ የጥራት ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምርጫ ቁሳቁሶቹ በወረቀትና በሰው ኃይል ለሚከናወነው ምዝገባ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የምዝገባ ሂደት ለማከናወን የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ያካተቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው
Feb 20, 2026 72
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን አስታወቀ። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚጠበቅባቸውም ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ይፋዊ መርሃ-ግብር ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የመራጮች ምዝገባም የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። ምርጫ የዲሞክራሲ ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናከርና ዜጎች ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚያገለግሉትን መሪዎች የሚመርጡበት ነው። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አባይነህ ጉጆ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ውሳኔ ሰጪነት በሚጠይቁ አበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በቀጥታ ማሳተፍ ይገባል። አካል ጉዳተኞች ህገ-መንግስቱ የሰጣቸውን መብቶች ከሚያረጋግጡባቸው ሁነቶች መካከል አንዱ ምርጫ መሆኑንም አንስተዋል። ቀደም ባሉት ምርጫዎች የምርጫ ጣቢያዎች ለአካል ጉዳተኛው ምቹ ያለመሆን፣ የግንዛቤ እጥረትና በታዛቢነት የመሳተፍ ዕድል አነስተኛ እንደነበር አስታውሰዋል። ፌዴሬሽኑ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የህግ ማዕቀፎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራ ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ማከናወኑን ጠቅሰው፤ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ታዛቢነት እንዲሳተፉ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በምርጫው የሚተገበሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አካል ጉዳተኞችን ከግምት ያስገቡ እንዲሆኑና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ ከምርጫ ቦርድ ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አካል ጉዳተኞች በመራጭነትና ዕጩ ተመራጭነት ብሎም በአጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፕሮግራም እና ማኒፌስቶ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽና ግልጽ በሆነ መንገድ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።
ጠቅላላ ምርጫው ስኬታማ እንዲሆን የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል- የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች
Feb 20, 2026 65
ቀብሪደሃር/ጎዴ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል ሲሉ በሶማሌ ክልል የቀብሪደሃርና ጎዴ ከተማ የሚኖሩ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተናገሩ፡፡ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች እንዳሉት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ይወጣሉ። በቀብሪደሃር ከተማ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ሁሴን መሀመድ፤ ምርጫው ነፃና ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ የላቀ ድርሻና ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል። በዚህም ህዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ የማድረግ ስራ ከሁሉም አካላት ጋር በመቀናጀት እያከናወኑ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ዜጋ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባም አመልክተዋል። ምርጫው የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ማረጋገጫ ነው ያሉት ደግሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አብዱላሂ ዑመር ናቸው። በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ምርጫው በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲከናወን በቅንጅት እየሰራን ነው ብለዋል። የጎዴ ከተማ ነዋሪ ወጣት ከድር ኢብራሂም በበኩሉ፣ ምርጫው ነፃና ሰላማዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት መዘጋጀቱንም ተናግሯል። ወጣቶች በጠቅላላ ምርጫው በመሳተፍ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ የማንቃት ሥራ እየሰሩ መሆኑን የገለፀው ደግሞ ወጣት በሺር ኦዶዋ ነው። በተለይ ምርጫው ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አረጋግጧል።
ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዓይነተኛ ሚና አለው
Feb 20, 2026 72
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዓይነተኛ ሚና እንዳለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። ምክክሩ የውስጥ አቅምን በማጠናከር ለሀገራዊ እድገት መፋጠን ተጨማሪ አቅም እንደሚሆንም ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ በኢትዮጵያ የማያግባቡ ጉዳዮችን በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት ቁልፍ ሚና አለው። የሀገራትን ልምድና ተሞክሮ በመቅሰም፣ ባህላዊና ትውፊታዊ የምክክር እሴቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲሁም አጀንዳ በማሰባሰብ ሒደት አካታች የሆነ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረጉ የሚበረታታ ነው ብለዋል። ምክክሩ የሀገር ጉዳይ የጋራ ጉዳይ መሆኑን በሁሉም ዜጎች ዘንድ ማስረጽ ከማስቻሉ ባሻገር ልዩነትን አሉታዊ በሆኑ አካሄዶች የመፍታት ባህል እንዲከስም ያደርጋል ነው ያሉት። በሀገራዊ ምክክር ሒደት ከሚገኙ ጥቅሞች መካከል ልዩነትን ሲፈጥሩ የቆዩ አጀንዳዎች ወደ አንድ የሚመጡበትና የጋራ አቋም መፍጠር የሚቻልበት እድል አንዱና ዋነኛው መሆኑንም አስረድተዋል። እንደ አምባሳደር ዲና ገለጻ ሀገራዊ ምክክሩ በልማት፣ በእድገት፣ በዲሞክራሲ፣ በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በደህንነት፣ በሰላምና በሌሎችም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ዜጎች የጋራ ስሜትና ፍላጎት እንዲኖራቸው መሰረት የሚጥል ነው። ይህም በዜጎች መካከል ትልቅ ብሔራዊ ጉልበትን በመፍጠር ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዓይነተኛ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የውስጥ አቅምን በማጠናከር በኩል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፤ ይህም በሁሉም ዘርፎች ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ከፍ ያለ ፋይዳ አለው ብለዋል። በተለይም በሀገር ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና እድገት ላይ ዜጎች የሚያደርጉት ተሳትፎ እንዲጠናከር እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ዘርፎች የሚከናወኑ ተግባራት እንዲሁ በጋራ ትብብርና በአንድነት መንፈስ እንዲከናወኑ ሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ሁኔታን በመፍጠር የተጀመረውን ሀገራዊ እድገት ለማፋጠን ተጨማሪ አቅም ይሆናል ብለዋል፡፡
በብሄረሰብ አስተዳደሩ ሰላምን በማጽናትና የልማት ሥራዎችን በማፋጠን ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል
Feb 20, 2026 72
ሰቆጣ ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰላምን በማጽናትና የልማት ሥራዎችን በማፋጠን ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መቻሉ ተገለጸ። የብሄረሰብ አስተዳደሩ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሰቆጣ ከተማ ተካሂዷል። የአስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪ ሹመት ጥላሁን እንደገለፁት፤ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተካሄደው የሰላም ግንባታና የልማት ስራ ውጤት አስገኝቷል። ምርታማነት ለማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂና ግብዓት በመጠቀም በመኸር ምርት ዘመን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። በበጋ መስኖ ልማት ለአርሶ አደሩ የግብርና ግብዓትና የውሃ መሳቢያ ሞተር በማቅረብ ከራሱ አልፎ ለገበያ የሚተርፍ ምርት እንዲያመርት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። የሕብረተሰቡን የማሕበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት በተደረገ ጥረትም ውጤት መምጣቱን አንስተዋል። ባለፉት ስድስት ወራት የ142 ፕሮጀክቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ጠቁመው፣ ቀሪዎቹን በተቀመጠላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል። የሰቆጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እሚያምረው ጌጤ፤በወረዳው የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የመስኖና የእንስሳት ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ገልጸዋል። ሕብረተሰቡ ቅሬታ ያነሳባቸው የነበሩ የማህበራዊ አገልግሎቶች መሰረተ ልማትን ለማሟላት ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር ሰፊ ጥረት መደረጉን አብራርተዋል። የጋዝጊብላ ወረዳ አስተዳዳሪ አበባው ደሳለኝ በበኩላቸው፣ ባለፉት 6 ወራት በሕብረተሰቡና በጸጥታ ሃይሉ ትብብር ሰላምን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስጠበቅ መቻሉን ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራን በነቃ የህዝብ ተሳትፎ ማሳካት መቻሉን ጠቁመው፣ በቀጣይም የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የሰላምና የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ የጋራ ትርክትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባትና ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው
Feb 20, 2026 69
መቱ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ገዢ ትርክትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባትና ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ዓይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የመቱ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ተናገሩ። ሀገራዊ ምክክሩ ያሉ ልዩነቶችን ለማጥበብ፣ የቆዩ አለመግባባቶችን በዘላቂነት ለማስወገድና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ወሳኝ ነው። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በመቱ ዩኒቨርሲቲ የሚሰሩ መምህርና ተመራማሪ በዳሳ አምሳሉ እንደተናገሩት ምክክሩ የጋራ ሀገራዊ ትርክትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባትና ዘላቂ መፍትሔን ለመሻት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው። ሀገራዊ ፍላጎትና ጥቅምን ያስቀደመ ቋሚ አጀንዳ ለማንገብና ለተፈጻሚነቱ በጋራ ለመረባረብ ሁሉንም የማነሳሳት አቅም እንዳለውም አስረድተዋል። ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በሀገራዊ ምክክሩ ሁሉም ሂደቶች በንቃት በመሳተፍ ለሰላም ግንባታ ይበጃል ያለውን ሃሳብ በባለቤትነት ስሜት ማበርከት እንዳለበትም መክረዋል። ሌላኛው በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩት መምህር ሳቢት ዜይኑ በበኩላቸው ሀገራዊ ምክክሩ ለጋራ ሀገራዊ ትርክት ግንባታ የሚበጅ አዲስ እሳቤና ጠቃሚ እሴትን ያመጣል ብለዋል። በዓለም ላይ በምጣኔ ሀብት ያደጉና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሀገራት መሰረታቸውን በወል ትርክት ላይ በመገንባትና ለሀገራዊ ጥቅምና ፍላጎት ቅድሚያ በመስጠት መሆኑንም ተናግረዋል። በምክከሩ ጠንካራ የወል ትርክትን በመገንባቱ ሂደት ሁሉም ዜጋ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አስገንዝበው ከዚህም ተጠቃሚ የሚሆነው ህዝቡ ራሱ መሆኑን አብራርተዋል። በወል ትርክት የተገነባ ሀገር በትናንሽ ችግሮች እንዳይበገር ትልቅ ድርሻ አለው ያሉት መምህሩ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ቀዳሚ እንድትሆን በወል ትርክት ላይ የምትሰራው ስራ ትልቅ ሚና እንዳለውም አውስተዋል።

ማህበራዊ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዓላማ ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ማጠናከር ነው
Feb 20, 2026 75
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዓላማ የዘመናት ሥብራትን ለመጠገንና ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ማጠናከር ነው። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የምትታተመው "ነጋሪ" መጽሔት፤ "ምክክር ለሀገር ክብር" በሚል ርዕስ የሀገራዊ ምክክሩን የዘመናት ሥብራትን ለመጠገን፣ የኮሚሽኑ አራት የክዋኔ ምዕራፎች፣ አካታችነትና ተሳትፎ እንዲሁም ተግዳሮቶችና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ዳሥሣለች። በዚህም ኢትዮጵያ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮችንና ጫፍ የረገጡ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት እና ለትውልድ የምትመች ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ምክክር መጀመሯ ተብራርቷል። እንዲሁም የታሪክ አረዳድ ልዩነትን በተመለከተ በሀገር ግንባታ ታሪክ፣ በሰንደቅ ዓላማና በሕገ-መንግሥት ላይ ያሉ አለመግባባቶችን በምክክር ለመፍታት መታቀዱም ተጠቁሟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጡትን ማብራሪያ በመጥቀስ፤ ምክክሩ የዘመናት ሥብራትን ለመጠገንና ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን ለማጠናከር ማለሙን መግለጻቸውን ነጋሪ አብራርታለች። መንግሥት ለውጤታማነቱ ቁርጠኛ መሆኑንም ማረጋገጣቸውን ነጋሪ ተመልክታለች። በዐዋጅ ቁጥር 1265/2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራዎቹን በአራት ዋና ዋና ምዕራፎች ከፋፍሎ እያከናወነ እንደሚገኝም በመጽሔቱ ተመላክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት 80 በመቶ የሚሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል። በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ዜጎችም ሐሳባቸው እንዲደመጥ የማረሚያ ቤት ታራሚዎችን የማሳተፍ እንቅስቃሴ መከናወኑ ተመላክቷል። ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ውስብስብ ችግር ወጥታ የጋራ መግባባትና ዘላቂ ሰላም የምታሰፍንበት "ወርቃማ ዕድል" መሆኑን መጽሔቷ አፅንኦት ሰጥታለች ።
አስቻይ ፖሊሲና ህጎችን በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
Feb 20, 2026 43
ሀዋሳ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- አስቻይ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊስና ህጎችን በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ። "ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፣የሚዲያ አስተዳደርና ቁጥጥር በኢትዮጵያ" በሚል ርእስ ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ውይይት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተካሄዷል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ በወቅቱ እንደገለጹት የሃሳብ ነጻነት በአለም አቀፍ ህጎችና ህገ-መንግስቱ ውስጥ የተካተተ መረጃ የማግኘትና ለሌሎች መብቶች ጥበቃ የሚያደርግ መብት ነው። በዚህም እንደ ሀገር አስቻይ ፖሊሲዎችና ህጎችን በማውጣትና በመተግበር ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የ2012ቱ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲና እሱን ተከትለው የወጡ አዋጆችና ህጎች ከዚህ ቀደም የነበሩ አሳሪ ህጎችን በመሻር ለሚዲያ አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓቱ ምቹ መደላድል መፍጠሩን ገልጸዋል። በተለይም ግልጽና ቀላል የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የሚዲያውን ምህዳር በቁጥርና በዓይነት ማስፋት መቻሉን ጠቅሰው በሀገሪቱ 310 የሚደርሱ መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። የጋራ የቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋትም በርካታ ተቋማትና የሙያ ማህበራትን ያሳተፉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የሀሳብ ነጻነትን የሚገድቡ ሀሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች እንዲወገዱ የሚያደርግ አዋጅ በማውጣት ችግሩን የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በውይይቱ የጸደቁ ህጎች ተግባራዊነት፣ በወጡ ዝርዝር ህጎችና በመገናኛ ብዙሃን አገልግሎት አሰጣጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መነሳታቸውን ገልጸዋል። በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናትና የጋዜጠኝነት ተባባሪ ፕሮፌሰር መልሰው ደጀኔ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ለማንኛውም እድገትና ልማት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ሃገር የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲን ተከትለው የወጡ ህጎችና አዋጆችን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ምህዳሩን እንዲያሰፉ መጠቀም ይገባል ብለዋል። መገናኛ ብዙሃንም ራሳቸውን በራሳቸው መቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተቋማዊ አንድነት በመፍጠር አቅማቸውን ማጎልበትና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንዲረጋገጥ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ተናግረዋል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊና ቀጠናዊ ፋይዳ ባላቸውና የፖሊሲ ግብዓት በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዘለቀ አርፍጮ (ፕ/ር) ናቸው የዛሬው የፖሊሲ ውይይት ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ስድስት ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀት የሃሳብ የበላይነትን የማረጋገጥና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የማጎልበት ተግባር እንደሚጠናከርም ገልጸዋል። በመድረኩ ሁለት የመወያያ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
የእንስሳት በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት ሊጠናከሩ ይገባል
Feb 20, 2026 45
አዳማ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- የእንስሳት በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል ምርታማነትን የሚያሳድጉ ሥራዎች የበለጠ ሊጠናከሩ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የዶሮ፣ የወተት ላሞችና ጥጆች እንዲሁም የዓሣ ሀብት አያያዝ፣ ሥነ-ሕይወት ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በአዳማ ተካሂዷል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሣ (ዶ/ር) በመደረኩ ላይ እንዳሉት፣የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የእንሰሳት ምርታማነትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው። የእንሰሳት ዝርያዎችን በማሻሻል በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱንም አንስተዋል። የእንሰሳት ተዋጽኦ ምርቶች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ሥርዓተ-ምግብን ከማሻሻል አኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው አንስተዋል። ከእንሰሳት ሀብት በዘላቂነት ለመጠቀምና ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ የአንሰሳት ደህንነትና ጤንነት ላይ በበለጠ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ዘመናዊ የእንሰሳት እርባታ በመከተልና ለእንሰሳት ደህነነትና ጤንነት ቅድሚያ በመስጠት ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ መሆን አንደሚገባም አመልክተዋል። በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤናና ቬተርነሪ ፐብሊክ ሄልዝ መሪ ስራ አስፈፃሚ ሲሳይ ጌታቸው (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀገር ደረጃ የእንስሳት በሽታን ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል የዘርፉን የጤና ሙያተኞችና የኤክስቴሽን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። የእንሰሳት በሽታዎችን ዕውቀት ተኮር በሆነ መልኩ መከላከል እንዲቻል ክትባት መስጠትን ጨምሮ አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ብለዋል። የጋምቤላ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሞክ ያንግ ጋትሏክ እንደገለጹት፣ የእንስሳት ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ የእንስሳት ጤና ኬላዎችና ኪሊኒኮችን በህክምና ቁሳቁስ ከማጠናከር ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወኑ ነው። አርብቶ አደሩ የእንስሳት ሀብት ምርትና ምርታማነትን የሚቀንሱ በሽታዎችን አስቀድሞ እንዲከላከል ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።
"ነጋሪ" መጽሔት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በዝርዝር የዳሰሰ አዲስ ዕትሟን ይዛ ወጥታለች
Feb 20, 2026 57
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ "ነጋሪ" መጽሔት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በዝርዝር የዳሰሰ አዲስ ዕትሟን ይዛ ለንባብ በቅታለች። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ታትማ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የምትዳስሰው "ነጋሪ" መጽሔት ወቅታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ዐበይት ጉዳዮችን ይዛ ለንባብ በቅታለች። መጽሔቷ በ8ኛ ዓመት ቁጥር-32 ዕትሟም የባሕር በር እና የታሪክ ምስክርነት፣ ሀገራዊ ምክክር-ለዘላቂ መፍትሔ፣ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ሩሲያና ሕንድ እንዲሁም የልማትና ኢኮኖሚ ዐበይት ጉዳዮችን ዳሳለች። ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ የነበራት ጥንታዊ የባሕር ላይ ገናናነት እና የታሪክ ዑደትም መጽሔቷ በዐበይት ጉዳይነት ከዳሰሰቻቸው መካከል አንዱ ሆኗል። የኢትዮጵያ የንግድና የጦር መርከቦች ከቀይ ባሕር እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ድረስ የነበራቸውን እንቅስቃሴና የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው ያውለበለቡበትን የታሪክ ምስክርነት በዝርዝር አቅርባለች። ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ ለማከናወን እንደ ሁነኛ መፍትሔ የያዘችውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት መጽሔቷ በዐቢይ ርዕስነት ተመልክታዋለች። መጽሔቷ የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት አስመልክቶ ሁለት ታላላቅ ሀገራትን ትኩረት ሰጥታለች፡፡ ኢትዮጵያና ሩሲያ ከአድዋ ጦርነት ጀምሮ እስከ ዛሬ የዘለቀውንና በተለያዩ የሥርዓተ መንግሥት ለውጦች ያልተናወጠውን የሁለቱን ሀገራት ጥልቅ ወዳጅነት ታስቃኛለች። የኢትዮጵያና ሕንድ ግንኙነትን በተመለከተም የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የታየውን "የመኪና እና የቡና ዲፕሎማሲ" እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የፈጠሩትን ጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እንዴት እንደዘገቡት በትንታኔ አቅርባለች። በተጨማሪም በኢኮኖሚው ዘርፍ መጽሔቷ በኢትዮጵያ እየተከናወነ ያለው የመስኖ ልማት ያስገኛቸው ስኬቶች እና በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ባንኮች መከፈታቸው ለፋይናንስ ዘርፉና ለኢንቨስትመንት እድገት የሚኖራቸው ቁልፍ ጠቀሜታም ዳሳለች። እንዲሁም "ነጋሪ" መጽሔት በጤና ዙሪያ ያተኮሩ ጠቃሚ ጽሁፎችን በማካተት ሁለገብ መረጃዎችን ለንባብ አብቅታለች።
ኢኮኖሚ
የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የመስኖ አውታሮችን በመጠቀም ምርታማነትና ተጠቃሚነታቸውን አሳድገዋል
Feb 20, 2026 30
ሀዋሳ፣ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡-በመንግስት የተዘረጉ የመስኖ አውታሮች ዓመቱን ሙሉ በማልማት ምርታማነታቸውን በማሳደግ የተሻለ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የወረዳው አርሶ አደሮች መንግስት በአካባቢያቸው የዘረጋላቸውን የመስኖ ልማት አውታር በመጠቀም ገቢያቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው የገላልቻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሲራቴ ገላ አካባቢያቸው ቆላማ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከዚህ በፊት የክረምት ዝናብን ብቻ ጠብቀው በቆሎ ያመርቱ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ በዓመት አንዴ የሚያመርቱት የበቆሎ ምርት ከቤት ውስጥ ፍጆታና አነስተኛ ገቢ ከማስገኘት ባለፈ የተሻለ ተጠቃሚ ሳያደርጋቸው መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት መንግስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በመቆፈሩና የመስኖ አውታር በመዘርጋቱ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ ማምረት በመቻላቸው በኑሯቸው ላይ ትልቅ ለውጥ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡ የጃራ ሂእኔሳ ቀበሌ አርሶ አደር እንዳለ እንግዳ በበኩላቸው አነስተኛ የውሃ ጉድጓድ መሳቢያ ሞተር ተጠቅመው በሚያወጡት ውሃ በዓመት ሦስት ጊዜ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ መስኖ በመጀመሩ እሳቸውን ጨምሮ የአካባቢው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ዓመቱን ሙሉ ማምረት መጀመራቸውን ገልጸው፣ መንግስትም የውሃ መሳቢያ ሞተርን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችን ማድረጉን ተናግረዋል። በዓመት ሦስት ጊዜ ጥቅል ጎመንና ሌሎች አትክልቶችን እንደሚያመርቱ ገልፀው በአንድ ዙር እስከ 300 ሺህ ብር ገቢ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በክልሉ የመስኖ ልማት ሥራ በአብዛኛው ከወንዞች፣ ጅረቶችና አነስተኛ ጉድጓዶች ውሃ በሞተር በመሳብ እንደሚከናወን ጠቅሰዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በቆላማና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች በቅርብ ጊዜያት ብቻ 6ሺህ ሄክታር መሬት የሚያለሙ የተለያዩ የመስኖ ፕሮጀክቶች ዕውን መደረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡ እንደ ሀዋሳ ዙሪያና ሎካ አባያ ያሉ ወረዳዎች ከዚህ በፊት በዓመት አንድ ጊዜ በቆሎ ከማምረት ወጥተው ዓመቱን ሙሉ ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይህም አርሶ አደሩን የተሻለ ተጠቃሚ አድርጓል ያሉት ኃላፊው ልማቱ የአካባቢውን ገበያ በማረጋጋትም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አመልክተዋል። በዘንድሮው በጋ በመስኖ ለማልማት ከታቀደው 80 ሺህ ሄክታር መሬት እስካሁን ድረስ 73 ሺህ ሄክታሩ መልማቱንም ተናግረዋል፡፡
የቡና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Feb 20, 2026 54
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ የቡና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ዘርፉን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማህበር 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ሀገሪቱ በዘርፉ የጀመረችው የጥራትና የብዛት ምርት የማሳደግ ባህል ለውጭ ምንዛሬ ግኝት መጠናከር ትልቅ አቅም እየሆነ ነው። ለዚህም እንደ ማሳያ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የቡና ምርት የሶስት እጥፍ እድገት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። ቀደም ሲል በሄክታር ስድስት ኩንታል የነበረው የቡና ምርት በአሁኑ ወቅት ወደ አሥር ኩንታልና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማህበር ከባለስልጣኑ ጋር በመቀናጀት የዘርፉን ተዋንያን በማሰልጠንና የስራ እንቅስቃሴው በእውቀትና በክህሎት እንዲመራ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በያዝነው በጀት ዓመት ከቡና ሽያጭ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት የታቀደውን ግብ ለማሳካት ማህበሩ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቡና ንግድ ስርአቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ ባለድርሻ አካላት ምርታቸውን በወቅቱ ለገበያ ማቅረብ እንዳለባቸውና ዋጋ ሲተምኑም ዓለም አቀፍ ገበያን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል፡፡ ጉባኤው የኢትዮጵያን አረንጓዴ ወርቅ ይበልጥ ለማዘመንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ማህበሩ ባካሄደው 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፣ ባለፉት ጊዜያት የቡና አመራረት ዘዴን በቴክኖሎጂና በምርምር ለማገዝ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ ስራ ተከናውኗል ብለዋል። አርሶ አደሮች የተሻሻሉና ምርታማ የቡና ዝርያዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰው፤ በቡናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አቅራቢዎችና ላኪዎች በንግድ ሂደቱ ውስጥ በቀላሉ የሚገናኙበትና መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ የቡና ልማት ስራው በዘመናዊ የእርሻ ዘዴዎች እንዲደገፍ በማድረግ ረገድ ማህበሩ ጉልህ ሚና መጫወቱ ጠቅሰዋል፡፡ 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤው በዋናነት እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም፣ በቀጣይም የቡና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የማህበሩ አባላት አቶ ፈጠነ የኋላሸት እና አቶ ደግፌ ኢድሉ በበኩላቸው የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት በጋራ በመሆን የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በመትከል ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ ለዘርፉ እድገት የሚያደረጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ጠቁመዋል፡፡
በወለጋ ዞኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ትልቅ ተስፋን የሰነቅንባቸው ናቸው
Feb 20, 2026 45
ነቀምት፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- በወለጋ ዞኖች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ትልቅ ተስፋን የሰነቅንባቸው ናቸው ሲሉ የነቀምት ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ሰሞኑን በወለጋ ዞኖች የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል። ጉብኝት ከተካሄደባቸው የልማት ስራዎች መካከልም በማዕድን ዘርፍ የወርቅና የድንጋይ ከሰል ማምረቻዎች፣ በኢንዱስትሪው ረገድ የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ የግብርና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች የልማት ስራዎች ይጠቀሳሉ። ይህንንም አስመልክቶ ኢዜአ ያነጋገራቸው የነቀምት ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ አካባቢያችው መጥተው ጉብኝት በማድረጋቸውና ፕሮጀክቶችን በማስጀመራቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ እንደገለፁት፤ በዞኖቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ትልቅ ተስፋን የሰነቁባቸው ናቸው። በነቀምት ከተማ የ04 ቀበሌ ነዋሪ ሼህ ሰዒድ አርጋው ከለውጡ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወለጋ ዞኖች በሰጡት ትኩረት የልማት ጥያቄዎቻችን በተጨባጭ ምላሽ እያገኙ ነው ብለዋል። ከልማት ስራዎቹ መካከልም የነቀምቴ ከተማ ኮሪደር ልማት ትልቅ ለውጥ የታየበትና የከተማዋን ገጽታ የቀየረ መሆኑን አመልክተዋል። ከዚህ ቀደም አካባቢያቸው የፀጥታ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ወድቆ እንደነበር ያነሱት አስተያየት ሰጪው በመንግስት ጥረት ዛሬ ላይ ይህ ሁኔታ ተቀይሮ ማህበረሰቡ ያለ ስጋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል። በአካባቢው ግንባታው የተጀመረው አዲስ የምግብ ማቀነባበሪያ ግዙፍ ፕሮጀክት ለልጆቻችን ሰፊ የስራ እድል ከማመቻቸት ባለፈ የሀገሪቱን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት አጋዥ እንደሚሆንም ያላቸውን እምነት ገልፀዋዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት መደሰታቸውን በመግለፅ በነቀምት ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ እንድትነቃቃ ማድረጉን የገለፁት ደግሞ ሌላኛዋ የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ ምትኬ ዋሲሁን ናቸው። በየደረጃው ጠንካራ ስራ በመሰራቱም የጤና፣ የመልካም አስተዳደር፣ የስላምና ፀጥታ እንዲሁም የፍትሕ አገልግሎቶች መሻሻል ማሳየታቸውን አክለዋል። አቶ በቀለ ወያ የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካባቢያችንን ከመጎብኘት ባለፈ የዓመታት ጥያቄያችን የነበረን የግዙፍ ኢንዱስትሪ ግንባታን በማስጀመራቸው ድርብ ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በስፋት ማየት እንዳልተለመደ ገልፀው ዛሬ ላይ ግን ትልቅ ተስፋን የሚሰጡ አዳዲስ የልማት ስራዎችን ማስተዋል ችለናል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥቂት ዓመታት በፊት የነቀምቴ ከተማ እና አካባቢውን ነዋሪዎች ባወያዩበት ወቅት በዞኑ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ቃል መግባታቸውን አስታውሰው ዛሬ ላይ ቃላቸውን ጠብቀው ዳግም በመገናኘታችን ተደስቻለሁ ያሉት ደግሞ አቶ ፈዬራ ፉፋ የተባሉ ነዋሪ ናቸው። ለህዝብ የገባነውን ቃል እንተገብራለን ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩም ዝም ብለው ሳይሆን ሰርተው እያሳዩ መሆኑንም አቶ ፈዬራ መስክረዋል። ግንባታቸው ተጓቶ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ፕሮጀክቶች በጥቂት ዓመታት ተጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተጀምረው በፍጥነት እየተገነቡ መሆናቸው አስደሳችና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ነው ብለዋል። መንግስት ቀን ከሌሊት በመስራት ሀገሩን እየቀየረ ስለመሆኑን በየጊዜው እየታየ ያለ ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች ስኬት ከመንግስት ጎን በመሆን ያለማሰለስ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በምስራቅ ቦረና ዞን በዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ178 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዷል
Feb 20, 2026 51
ነገሌ ቦረና፣ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡-በምስራቅ ቦረና ዞን በዘንድሮ የበልግ ወቅት በተሻሻለ የግብርና አሰራር ከ178 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት መታቀዱንም የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በዞኑ ለበልግ አዝመራው እስካሁን ከ37 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መቅረቡም ተመልክቷል። ከመጋቢት 15 እስከ ሚያዝያ 30 አካባቢው የበልግ ዝናብ የሚያገኝበት ወቅት በመሆኑ የእርሻ ስራ የሚጧጧፍበት የአዝመራ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅትም ለሚከናወነው የእርሻ ስራ የዞኑ አርሶ አደሮች የምርታማነት ማሳደጊያ ግብዓቶችን በመጠቀም የማሳ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ኩልሌ ሸና እንደገለፁት፤ በዞኑ በዘንድሮ የበልግ ወቅት በተሻሻለ የግብርና አሰራር ከ178 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዷል። በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች እስካሁን ከ50 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለሁለተኛ ጊዜ ታርሶ ለዘር መዘጋጀቱን ገልፀው የማሳ ዝግጅቱም በኩታ ገጠም የእርሻ ስነ-ዘዴ እንደሚከናወንም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከበልግ አዝመራው ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ አጠቃላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱንና በማሳ ዝግጅት ምዕራፉ ከ78 ሺህ በላይ ከፊል አርብቶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በጽህፈት ቤቱ የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ቡድን መሪ አቶ አብዱረሂም አብዱራህማን በበኩላቸው በዞኑ ለበልግ አዝመራው ከ120 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም 50 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ከመሀል አገር ወደ ዞኑ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ አሳውቀው ከዚህ ውስጥ 37 ሺህ 600 ኩንታል ወደ ዞኑ ገብቶ ለተለያዩ ወረዳዎች እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የግብዓት አቅርቦቱ የተከናወነው በቆላማ ወረዳዎች ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ታሳቢ በማድረግ መሆኑንም አመልክተዋል። በዞኑ ሊበን ወረዳ የሜኤሳ ዳሎሬ ቀበሌ ነዋሪ አቶ እስማኤል ማሊማ ሁለት ሄክታር መሬታቸውን ደጋግመው በማረስ ለዘር ያዘጋጁ ሲሆን በመኸር አዝመራ ያጡትን ምርት የማካካስ እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ አርሶ አደሩ በበልግ ወቅት አዳዲስ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ የምርት ማሳደጊያዎችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለመጨመር ማቀዳቸውንም ተናግረዋል። ለበልግ አዝመራው 8 ሄክታር መሬትን በኩታ ገጠም የእርሻ ስነዘዴ ደጋግመው በማረስ ለዘር ማዘጋጀታቸውን የገለፁት ደግሞ በሊበን ወረዳ የጎቢቻ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ወርቁ አለባቸው ናቸው። ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግም ማዳበሪያ በወቅቱ እንዲቀርብላቸው ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበው እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የመረጃና የመዝናኛ ይዘቶችን መመልከት የሚያስችላቸውን ቴሌስትሪም የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ
Feb 20, 2026 33
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች የመረጃና የመዝናኛ ይዘቶችን መመልከት የሚያስችላቸውን ቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት አስተዋወቀ። በዚህ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ቴሌስትሪም በመዝናኛ፣ ትምህርት፣ ጤና እና በተለያዩ ዘርፎች ይዘትን በማዘጋጀትና ለሚሊዮኖች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎቱም ሃሳብ ያላቸው አካላት ይዘት በመፍጠር የሚያስተላልፉበት "ብሔራዊ የዲጂታል ይዘት መድረክ" መሆኑን አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ 98 በመቶ መረጃ የሚተላለፈው በሳተላይት መሆኑን በመጥቀስ፤ የዲጂታል መረጃ ተጠቃሚዎች ሁለት በመቶ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በዲጂታል አማራጭ የቀረበው የቴሌስትሪም አገልግሎት ምስሎችን በ4k፣ 8k እና በHD ጥራት በማሳየት የሚያድግና የሚሰፋ የቴሌኮም አገልግሎት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በየጊዜው የሁሉንም ዜጎች የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እያሰፋ እንደሚገኝ አንስተዋል። የቴሌስትሪም (TeleStream) የዲጂታል አማራጭ አገልግሎት ደንበኞችም የአገልግሎት ክፍያዎችን ባሉበት ቦታ በቴሌ ብር መፈጸም እንደሚችሉ አስረድተዋል። ኢትዮ ቴሌኮም 108 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ፈጥሯል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ከ87 ሚሊዮን ደንበኞች 50 ሚለዮን የሚሆኑት የብሮድባንድ ተጠቃሚ በመሆናቸው የቴሌስትሪም አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ለሳተላይት ክፍያ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ከማዳን ባለፈ ያልተቆራረጠ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል። የቴሌስትሪም ምርቶችን በዘመን ገበያ በማዘዝ በኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከላት ማግኘት እንደሚቻል ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂ ልማት የታዳሽ ኃይል ብዝኅነትን በማስፋት የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን ወሳኝ እርምጃ ነው
Feb 20, 2026 82
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂ ልማት የታዳሽ ኃይል ብዝኅነትን በማስፋት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያፋጥን ወሳኝ የልማት እርምጃ መሆኑን ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ወቅት የ30 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማብሰራቸው ይታወሳል። ከብሔራዊ ፕሮጀክቶቹ መካከል ሰላማዊ የኒውክሊየር ልማት መርሃ ግብር፣ የዩሪያ ማዳበሪያ፣ ግዙፍ የአየር ማረፊያ፣ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ቤቶችና የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂ ልማት መርሃ ግብር የምታካሂደው ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ እንደሚውል መንግስት ማሳወቁ ይታወሳል። ይህ መርሃ ግብር የሀገሪቷ የኃይል አቅርቦት ፍላጎትን በማሟላት ፈጣን የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዕድገቷን ለማሳለጥ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑ ይገለጻል። በዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የቴክኒክ ትብብር መምሪያ የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጋሻው ገበየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኒውክሊየር ኃይል ከታዳሽ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም ኢትዮጵያ ከሰላማዊ የኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር ለመጠቀም የሚያስፈልጉ የፖሊሲና የመሠረተ ልማት እርምጃዎችን እየወሰደች እንደሚገኝ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብርም ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያስቀጥል የታዳሽ ኃይል አማራጭ ብዝኅነትን ማስፋት የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል። የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት የኢትዮጵያን ሰላማዊ የኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር የመጠቀም ጥረት ለማገዝ በአጋርነት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል። በቀጣይም ለኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር ፕሮጀክት ስኬታማነት የሚያስፈልጉ ሙያዊና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የኒውክሊየር ኃይል አነስተኛና ነፃ የካርበን ልቀት የኃይል አማራጭ በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የማይበገር አረንጓዴ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በሌላ መልኩም አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት አማራጭ በመገንባት የኢኮኖሚ ዕድገትን ማሳለጥ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዲጂታል ሉዓላዊነትን በተሟላ መልኩ የሚያረጋግጥ ነው
Feb 20, 2026 64
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚያፋጥንና ዲጂታል ሉዓላዊነትን በተሟላ መልኩ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጅ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይና በኢትዮጵያ የክፍለ አህጉር ቢሮ ዳይሬክተር ስቴፈን ባይኖስ፤ ዲጂታላይዜሽን የእድገት አቀጣጣይ መሣሪያ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ በልጽገው የምናያቸው የዓለም ሀገራት የደረሱበት የእድገት ደረጃ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በሰጡት ትኩረት ልክ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማሳደግ እና ዘመናዊ አሠራሮችን ለመተግበር ያስቀመጠችው አቅጣጫ ይበል የሚያሰኝ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ተከትሎ የሚታዩ እና ትርጉም ያላቸው ሁለንተናዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ለአብነት አንስተዋል፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚያፋጥንና ዲጂታል ሉዓላዊነትን በተሟላ መልኩ የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ በምታከናውነው ተግባር አብረው እየሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በቀጣይም ትብብሩን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲን በሰው ሃይልና ግብዓት ለማሟላት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል
Feb 19, 2026 73
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲን በሰው ሃይልና ግብዓት ለማሟላት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2018 የግማሽ ዓመት የመንግስት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም እየተሰራ ነው ብለዋል። በዓለማችን 2ኛው የኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲም ለመጪዉ ትዉልድ ምቹ የቴክኖሎጂ ምህዳር በመፍጠር ለዲጂታል ኢትዮጵያ ስኬት አስቻይ ሁኔታን እንደሚፈጥር አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታላይዜሽን መሠረተ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ወንደሰን ሙሉጌታ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በዲጂታል ክህሎት ልማት ላይ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የኢትዮጵያን የዲጂታል ልማት ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ተወዳዳሪ የሰው ሃብት በማፍራት፣ ጥናትና ምርምር የሚጠበቅበትን ገንቢ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የወሰዱት ተነሳሽነትም መጪውን ጊዜ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም ሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንዲወጡ አቅጣጫ መሰጠቱን አብራርተዋል። በዚህም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም በሰው ሃብት ልማትና ግብዓት የማሟላት ሂደት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመጪው ዘመን የኢትዮጵያና የዓለም ተስፋ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ በቀጣይም ብቁ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የሰው ሃይል ለማፍራት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይህኑ ታሳቢ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ የተካኑ ምሁራንን በማዘጋጀት በጥናትና ምርምር ዘርፍ ውጤታማ ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።
ስፖርት
ቅድሚያ ለሴቶች የሩጫ ውድድር በመጋቢት ወር ይካሄዳል
Feb 20, 2026 44
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018 (ኢዜአ)፡- 23ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድር መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ይደረጋል። ይህ በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ የሚዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መነሻ እና መድረሻው ቦሌ አትላስ ሆቴል መሆኑ ተገልጿል። የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ ውድድሩን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ በውድድሩ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። 23ኛው ዓመት ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር ነገ ምዝገባ እንደሚጀመር ገልጸው፤ ለሶስት ሳምንታት እንደሚቆይ አመላክተዋል። በውድድሩ ላይ 16 ሺህ ሴቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል። የሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር፤ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ እና በሌሎች የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት ትብብር የተዘጋጀ ነው። ውድድሩ የተጀመረው በ1996 ዓ.ም ነው።
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር በ3000 ሜትር የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸፈች
Feb 20, 2026 85
አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2018(ኢዜአ)፦ በፈረንሳይ ላይቪን የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ተካሄዷል። በሴቶች 3000 ሜትር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ8 ደቂቃ ከ24 ሴኮንድ ከ59 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች። በርቀቱም የ2026 ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች። አለሺኝ ባወቀ ሁለተኛ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስትጨርስ ጣልያናዊቷ ናዲያ ባቶክሌቲ ሶስተኛ ወጥታለች። በውድድሩ ሂሩት ማስረሻ አምስተኛ፣ ሃዊ አበራ ስድስተኛ፣ የኔዋ ንብረት ዘጠነኛ፣ ብርቱካን ሞላ 10ኛ፣ ሺቶ ጉሚ 11ኛ፣ ፋንታዬ በላይነህ 13ኛ እና አስቴር አረሪ 14ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በወንዶች የ3000 ሜትር ውድድር አትሌት አዲሱ ይሁኔ 7 ደቂቃ ከ33 ሴኮንድ ከ58 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አንደኛ ወጥቷል። ኬንያዊው ጃኮብ ኪሮፕ ሁለተኛ እና ጌትነት ዋለ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በ1500 ሜትር ሴቶች ብርቄ ኃየሎም እና ሳሮን በርሄ ሁለተኛና ሶስተኛ ወጥተዋል። የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ጆርጂያ ሃንተር ቤል ውድድሩን አሸንፋለች። ወርቅነሽ መሰለ እና ሐረገወይን ካላዩ 9ኛ እና 10ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል። በሴቶች 2000 ሜትር ኬና ቱፋ አምስተኛ፣ ባይሴ ቶሎሳ 10ኛ እና ገላ ሐምበሴ 11ኛ ወጥተዋል። አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሁል፣ ፖርቹጋላዊቷ ሳሎሜ አልፎንሶ እና ፈረንሳያዊቷ አጋት ጉሌሞት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ፅጌ ዱጉሞ ሶስተኛ ወጥታለች። ንግስት ጌታቸው አራተኛ ደረጃን ይዛለች። የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ኬሊ ሆድኪንሰን አንደኛ ስትወጣ ስዊዘርላንዳዊቷ ኦውድሬይ ዌሮ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። የዓለም አትሌቲክስ እ.አ.አ በ2026 ባወጣው መርሐ-ግብር አማካኝነት በተለያዩ ሀገራተ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በሻምፒዮንስ ሊጉ ቦዶ ግሊምት እና ባየር ሌቨርኩሰን ድል ቀናቸው
Feb 19, 2026 91
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11 /2018(ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ማምሻውን ሶስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል። በአስፕማይራ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቦዶ ግሊምት ኢንተር ሚላንን ባልተጠበቀ ሁኔታ 3 ለ 1 አሸንፏል። ሶንድሬ ብሩንስታድ ፌት፣ ጄንስ ፒተር ሃውግ እና ካስፐር ዋርትስ ሆግ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ፍራንቼስኮ ፒዮ ኤስፖዚቶ ለኢንተር ሚላን ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በሌላኛው መርሐ-ግብር ባየር ሌቨርኩሰን ከሜዳው ውጭ በፓትሪክ ሺክ ግቦች ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0 ረቷል። ክለብ ብሩዥ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ሶስት አቻ ተለያይተዋል። በጃን ብሬይዴል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ክሪስቶስ ዞሊስ፣ ኒኮሎ ትሪሶልዲ እና ራፋኤል ኦንዬዲካ ለብሩዥ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ጁሊያን አልቫሬዝ፣ አዴሞላ ሉክማን እና የክለብ ብሩዡ ጆኤል ኦርዶኔዝ በራሱ ላይ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ክለብ ብሩዥ ሁለት ጊዜ ተመርቶ አቻ ወጥቷል። ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ካራባግን 6 ለ 1 ረቷል። የመልስ ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳሉ።
የሊጉ መሪ አርሰናል ከዎልቭስ ጋር አቻ ተለያየ
Feb 19, 2026 99
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዎልቭስ እና አርሰናል ሁለት አቻ ተለያይተዋል። ማምሻውን በሞልኒው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ እና ፒዬሮ ሂንካፒዬ ለአርሰናል ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሁጎ ቡዌኖ እና የአርሰናሉ ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በራሱ ላይ ለዎልቭስ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ከ2 ለ 0 መምራት አቻ የወጣው አርሰናል በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ ጥሏል። በጨዋታው አርሰናል የተሻለ ብልጫ ነበረው። የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 58 ነጥብ ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ አምስት ከፍ አድርጓል። ዎልቭስ በ10 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል። ዎልቭስ በውድድር ዓመቱ ያሸነፈው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። የሁለቱ ቡድኖች የ31ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛር የተደረገው አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያለበት የካራባኦ ዋንጫ ከመርሐ-ግብሩ ጋር በመገጣጠሙ ምክንያት ማስተካከያ ተደርጎበት ነው።
አካባቢ ጥበቃ
ነፋሻማው የጎዴ ፓርክ በወጣቶች ተመራጭ የመዝናኛ ሥፍራ ሆኗል
Feb 19, 2026 75
ጎዴ፤ የካቲት 12/2018 (ኢዜአ) ፡-ነፋሻማው የጎዴ ፓርክ በወጣቶች ተመራጭ የመዝናኛ ሥፍራ ሆኗል። በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል። የከተማዋን ውበት የሚገልጡና የክልሉን እድገት የሚያፋጥኑ የወጣቶች መዝናኛና መናፈሻ ስፍራዎች መገንባታቸው ደግሞ የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው። በሞቃታማዋ ጎዴ ከተማ የተገነባው የክፍለ ዘመን መዝናኛ ፓርክ የዚሁ አካል ሲሆን በፓርኩ የሚገኙ እጽዋት አካባቢውን ነፋሻማ በማድረግ ለወጣቶች አማራጭና ተመራጭ መዝናኛ ሥፍራ ሆኗል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ወጣቶች ፓርኩ ውብና አረንጓዴ በመሆኑ ሞቃታማውን የአካበቢውን አየር ጸባይ ነፋሻማና ምቹ አድርጎታል ይላሉ። የከተማዋ ወጣቶች ለመዝናናትም ሆነ ለንባብ የሚመርጡት ቦታ መሆኑንም ተናግረዋል። ወጣት ሀምዛ አብዱልዋሃብ እንደሚለው ፓርኩ ወጣቶች ጊዜያቸውን በአልባሌ ስፍራ እንዳያሳልፉ አማራጭ መዝናኛ ሆኗል። ወደ ፓርኩ በተደጋጋሚ በመምጣት አንደሚያነብና እንደሚዝናናም ገልጿል። ለተለያዩ ዝግጅቶች ፓርኩን ተመራጭ መዳረሻ እንደሚያደርግ የገለጸው ደግሞ ወጣት ሳዳም ሁሴን ነው። ፓርኩ ከአካባቢው ወጣቶች ባለፈ ወደ ጎዴ ለሚመጡ እንግዶች ተመራጭ የመዝናኛ ቦታ መሆኑን ተናግሯል። ወጣት ዴቃ መሀመድ በበኩሏ የፓርኩ መገንባት ውብና አረንጓዴ አካባቢ በመፍጠር በነፋሻማ አየር ጊዜዋን አንድታሳልፍ ዕድል መፍጠሩን ገልጻለች። የጎዴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አሊ፣ ከተማዋን አረንጓዴና ዉብ የማድረግ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ፓርኩ ለወጣቶች አማራጭ የመዝናኛ ቦታ ከመሆን ባለፈ ለአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ በንፅህና አጠባበቅ ረገድ እያከናወነች ያለው ሥራ በአርዓያነት ይጠቀሳል
Feb 19, 2026 76
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2018 (ኢዜአ)፡- አዲስ አበባ በውኃና በንፅህና አጠባበቅ ላይ እያከናወነች ያለው ሥራ በአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ገለጹ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት ግንባታ እያከናወነች ያለውን ተግባርም አድንቀዋል አምባሳደሩ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ። በተጨማሪም ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ እየወሰደቻቸው ያሉ እርምጃዎች ለእድገቷ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል። በሌላ በኩል በተለያዩ ከተሞች የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆናቸውን ነው ያስረዱት። እንዲሁም አዲስ አበባ ከውኃና ንፅህና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ እያከናወነቻቸው ያሉ ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም እንደ ትልቅ ማሳያ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። ለአብነትም በርካታ የሕዝባዊ መገልገያ ስፍራዎች እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ መገንባትን ጨምሮ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ እየተሠራ ያለውን ሥራ አድንቀዋል።
በምስራቅ ቦረና ዞን በመጪው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች እየተዘጋጁ ነው
Feb 16, 2026 154
ነገሌ ቦረና፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ቦረና ዞን በመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ ነው። ምስራቅ ቦረና በአብዛኛው የእንስሳት እርባታ የሚካሄድበት ቆላማ፣ ዝናብ አጠር እና ደረቃማ ዞን እንደሆነ ይታወቃል። የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን መትከል፣ የውሃ አማራጮችን ለይቶ መጠቀምና ከእንስሳት እርባታ ጎን ለጎን መስኖን ማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መንግስት እያከናወናቸው ካሉ ተግባራት መካከል ይጠቀሳል። የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ኩልሌ ሸና ፤በዞኑ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አዳጋዎች ሳቢያ የተራቆቱ አካባቢዎችን መልሶ ለማልማት እያስቻለ ነው ብለዋል። በዘንድሮው ዓመትም በ6 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለመጪው ክረምት በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች የደን፣ የጥላ ዛፍ ፣ የእንስሳት መኖና የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት ምክትል ኃላፊው በዚህም አብዛኛው ችግኝ መጽደቁን ጠቅሰዋል፡፡ በተለይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተተከሉ የጽድ፣ ግራቪሊያ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ የእንስሳት መኖ እና የደንና የጥላ ዛፎች በተሻለ ሁኔታ መጽደቃቸውንም ለአብነት አንስተዋል። በዞኑ ሊበን ወረዳ የጎቢቻ ነዋሪ ሀጂ ቀራርሳ ጉራቻ፤ ባለፉት አመታት በደኖች ላይ በደረሰ ጉዳት ድርቅና የአካባቢ መራቆት ሲያስከትል መቆየቱን ያስታውሳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተለያዩ ችግኞችን በመትከል የተፈጥሮ ሀብቱን መልሶ ለመተካት እየተደረገ ካለው ጥረት ባሻገር ችግኞቹን መትከልና መንከባከብ ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ ነው የጠቀሱት። አቶ አብዲ ሮባ የዚሁ ወረዳና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በየአመቱ በአካባቢው በሚከሰተው ድርቅ የወንዞችና ምንጮች መድረቅ፤ የእንስሳት መኖና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ችግር እንደሚያጋጥም ገልጸዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ በተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማህበረሰቡ የተሻለ ግንዛቤ ለመያዝ መቻሉንና ለውጥ መመዝገቡን ነው የገለጹት። በዚህም ማሕበረሰቡ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንክብካቤም እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተያዘው ዓመትም በተመሳሳይ መልኩ በመርሃ ግብሩ በመሳተፍ ዘላቂ ልማትና የምግብ ዋስትናን በሚያረጋግጡ ስራዎች ላይ የማተኮር እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ በምስራቅ ቦረና ዞን በ9 ወረዳዎች ባለፈው አመት በአረንጓዴ አሻራ ከተተከለው ችግኝ ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ መጽደቁን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች
Feb 15, 2026 139
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያስመዘገበችውን ስኬት አዲስ አበባ በራሷ ትናገራለች ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ የ39ኛው የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ አሻራ ለተመዘገበው ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያሳዩት ቁርጠኝነት በተግባር የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ የተመዘገበውን ውጤት የአዲስ አበባ ከተማ በራሷ ትናገራለች ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በማዘጋጀት የአፍሪካ አቋም ለማሳወቅ ማጣቀሻ የሚሆን ሰነድ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡ ጉባኤው በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ተጽዕኖን በመቋቋምና በሀይል ሽግግር የአፍሪካን ድምጽ የሚያንጸባርቅ አቋም የተያዘበት መሆኑን አንስተዋል፡፡ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ የበካይ ጋዝ ልቀት ተጽዕኖ ከ4 በመቶ እንደማይበልጥ በማንሳት፤ በብክለት የምትጎዳው ግን የላቀ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራትን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የሚያስችል የማገገሚያ ዕቅድ እንዲያወጡ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ታሪካዊ አጋርነት
Feb 16, 2026 294
የኢትዮጵያ እና ቱርኪዬ ግንኙነት ክፍለ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው። የአፍሪካ ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ኦቶማን ኢምፓየርን ጨምሮ በታሪክ ከመካከለኛው ምስራቅ እና አውሮፓ ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ነበራት። ኦቶማን ኢምፓየር ለዘመናዊቷ ቱርክዬ መሰረት ጥሎ አልፏል። በ20ኛ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ የተጀመረው የሀገራቱ ወዳጅነት በዲፕሎማሲ እና ንግድ ልውውጥ ላይ የተመረኮዘ ነው። ቱርክዬ አፍሪካን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር የምትቆጥር ሲሆን አፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ቁልፍ አህጉራዊ ተቋማት የሚገኙባት እና የአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ የዚህ ትብብር አካል ናት። ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ 1896 መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የመጀመሪያ የኦቶማን-ቱርክዬ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እ.አ.አ በ1912 በሐረር ከተማ ተከፍቷል። ቱርክዬ ከሰሃራ በታች የመጀመሪያውን ኤምባሲ የከፈተችው በኢትዮጵያ ሲሆን ወቅቱም እ.አ.አ በ1926 ነበር። ኢትዮጵያ በቱርክዬ ኤምባሲዋን የከፈተችው እ.አ.አ በ1933 ነው። ያለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ ግንኙነት ከፍተኛ እድገት ያሳየበት ነው። ኢኮኖሚ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት ምሰሶ እንደሆነ ይጠቀሳል። የቱርክዬ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በግንባታ እና በግብርና ማቀነባበሪያ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ። ቱርክዬ በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። የሀገራቱ የንግድ ግንኙነትም እየዳበረ መጥቷል። ከኢኮኖሚ ባሻገር ፖለቲካ፣ ደህንነት፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪ እና ባህል ሌሎች የትብብር መስኮች ናቸው። ባለፉት 10 ዓመታት በሁለቱ ሀገራት መካከል የከፍተኛ ባለስልጣናት የጉብኝት ልውውጦች ተደርገዋል። የቱርክዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ጉብኝቱ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር ማጠናከርን ያለመ ነው። እ.አ.አ በ2017 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቱርክዬ ጉብኝት በማድረግ ኢትዮጵያን በመወከል በቱርክዬ-አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2021 በቱርክዬ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ስምምነቶች መፈራረማቸው ይታወሳል። ውሃ፣ ወታደራዊ ትብብር እና ፋይናንስ ከስምምነቶቹ ትኩረቶች መካከልም ይገኙበታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የተደረገው ኢትዮጵያና ቱርክዬ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 125ኛ ዓመት ላይ መሆኑ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈረሙት ስምምነቶች የግንኙነቱን መጠናከር እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። ለኢትዮጵያ የልማት እና መረጋጋት ጉዞ ቱርክዬ የምታደርገውን ድጋፍም አድንቀዋል። የቱርክዬ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን ኢትዮጵያ መቼም አትረሳውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በነበራቸው ቆይታ። የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እ.ኤ.አ በ2021 በቱርክዬ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በወቅቱ አዲስ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲም መርቀዋል። የቱርክዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እ.አ.አ በ2024 ኢትዮጵያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የከፍተኛ ባለስልጣናቱ ጉብኝት የሀገራቱን የግንኙነት መጠናከር የበለጠ የሚያጎለብቱም ናቸው። ኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ፣ መሰረተ ልማት፣ የንግድ ብዝሃነትን ማስፋት፣ መከላከያ እና ደህንነት፣ ቱሪዝም እና ባህል ሀገራቱ ትብብራቸውን ሊያሰፉባቸው እየሰሩባቸው ከሚገኙ መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ። የኢትዮጵያ እና የቱርክዬ አጋርነት በጋራ ፍላጎቶች፣ ተራማጅ በሆኑ ሀሳቦች፣ በጋራ ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና እየተለወጡ ያሉ የዓለም እውነታዎችን ባማከለ ሁኔታ የበለጠ እየተጠናከረ መጥቷል። በልማት ጎዳና ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ ከአፍሪካ ጋር ያላት ትስስር የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ጥልቀት የሚሰጥ ነው። ሁለቱ ሀገራት በፍጥነት እየተለዋወጠ በሚገኘው ቀጣናዊ እና የዓለም ምህዳር ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር እየሰሩም ይገኛሉ።
የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን ለማደስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ
Feb 16, 2026 123
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018(ኢዜአ):- የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የአህጉሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ማጠናከርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት በአዲስ መልክ ለማደስ እንደሚሰሩ አስታወቁ። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሲዲ ኡልድ ታህ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ባንኩ ለአፍሪካ ቁልፍ የትኩረት መስኮች እያደረገ ያለውን ጠንካራ ድጋፍ ያደነቁ ሲሆን ለአፍሪካ ልማት ፈንድ 11 ቢሊን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን መልካም የሚባል እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል። ሊቀመንበሩ እና የባንኩ ፕሬዝዳንት ከእዳ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የደህንነት ፈተናዎች ባለፈ የፋይናንስ አቅርቦት የአፍሪካ አበይት ፈተና መሆኑን በምክክራቸው ወቅት ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች የፕሮጀክት ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር፣ የአንድ ትሪሊን የአሜሪካን ዶላር የአፍሪካ ካፒታል ማሰባሰብ፣ የአፍሪካ የብድር ምዘና ኤጀንሲን ማጎልበትና ጠንካራ የአፍሪካ የፋይናንስ ስርዓት መገንባት ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ አጋርነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ ተሠማመተዋለ። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመወያያት እና በአፍሪካ ፋይናንስ ላይ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ለማካሄድ እቅድ መያዛቸውንም ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል
Feb 16, 2026 177
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2018 (ኢዜአ):- ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል። “የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ሥራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አኅጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አኅጉራዊው መድረክ የአፍሪካ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያንና የልማት አጋሮችን በአንድ መድረክ ያገናኛል። ፎረሙ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግሥት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል። የሥራ ዕድል፣ ምቹ የኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳር እና የአፍሪካን የፈጠራ ዐቅም አሟጦ መጠቀም በፎረሙ ላይ ምክክር ከሚካሄድባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። በተለይም የዲጂታል ኢንዱስትሪዎች፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም እየሰፋ ያለው የአፍሪካ የፈጠራ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶታል። በፎረሙ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችና ማዕቀፎች ይተዋወቃሉ። የወጣቶችን የኢኖቬሽን ሥራ ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር የሚያስተሣሥር የአፍሪካ የወጣቶች አይበገሬነትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፍ ይፋ ይሆናል። በኢሲኤ የበለጸገውና የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ቃል ኪዳኖችን ትግበራ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ሥርዓትም በፎረሙ ይፋ ሆኖ ወደ ትግበራ ይገባል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ። አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ ዐውደ-ርዕይም ይካሄዳል። ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽዖ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል። የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በዘላቂ ልማት ግቦችና በአጀንዳ 2063 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ስትራቴጂካዊ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም በመረጃው ተመላክቷል። የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች https://linktr.ee/ENADigitalክቷል።
አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸመባት በደል የታሪክ ዕውቅና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የምትጠይቅበት ነው - የጋና ፕሬዚዳንት
Feb 15, 2026 166
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፦አፍሪካ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸመባት በደል የታሪክ ዕውቅና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የምትጠይቅበት መሆኑን የጋና ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ሻምፒዮን ጆን ድራማኒ ማሃማ ገለጹ። ”ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። ከሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የጋና ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ሻምፒዮን ጆን ድራማኒ ማሃማ "የቅድመ አያቶች ዕዳ፣ ዘመናዊ ፍትሕና የአፍሪካውያን ምክንያታዊ የአንድነት ውክልና" በሚል መሪ ሃሳብ መነሻ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው፤ በአፍሪካ ለተፈጸመው በደል ስርዓታዊ ማካካሻና በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ላይ ለምታቀርበው ፍትሀዊ የውክልና ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአፍሪካውያን ላይ የተፈጸመው ግፍ በሰው ልጅ ታሪክ የታየ ከፍተኛው ኢ-ፍትሀዊ በደል መሆኑን አስታውሰዋል። ይህ ኢ-ፍትሀዊ በደል ዓለም አቀፍ ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ዕውቅና መስጠት መከፋፈል ሳይሆን የሞራል ድፍረትና ፍትሕን የማረጋገጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው ብለዋል። የአክራ ዳግም ማስጀመር የተሰኘው አሕጉራዊ ንቅናቄ አፍሪካ በውጭ ያላትን የእርዳታ ጥገኝነት ለማስቆም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በኮቪድ-19 ወቅት አፍሪካ ክትባት በማግኘት ረገድ የመጨረሻ ተሰላፊ የነበረችበትን አሳዛኝ ሁኔታ በማስታወስ፣ አህጉሪቱ የራሷን የጤና እና የፋይናንስ ተቋማት በራሷ አቅም መገንባት እንዳለባት ገልጸዋል። የማካካሻ ፍትህን ጥያቄን በተመለከተም ጥያቄው ከገንዘብ ክፍያ ባለፈ የታሪክ መዝገብን የማስተካከልና የተዘረፉ ቅርሶችን የመመለስ ጉዳይ እንደሚጨምር ጠቁመዋል። አፍሪካ እና የካሪቢያን ሀገራት በዚህ ጉዳይ ላይ በአንድ ድምፅ ለመቆም መስማማታቸውን ገልጸዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኩል የባሪያ ንግድ በሰው ልጅ ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል እውቅና እንዲያገኝ ግፊት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ሐተታዎች
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 126
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች
Jan 25, 2026 582
የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ ፍላጎት በመገንዘብ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያልዘነጉ የቦረና ቅን ልቦች። ዶክተር አብዱራህማን ሮኔ ይባላሉ። ትውልድና ዕድገታቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልተሌ በተሰኘ አካባቢ ነው። የቀለም ትምህርት በሀገር ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል። ለበርካታ ዓመታት ሕይወታቸውን በአሜሪካን ሀገር እየመሩ የሚገኙት ዶክተር አብዱራህማን ከሁለት ዓመታት በፊት ለቤተሰብ ጥየቃ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ቦረና አቀኑ። የጉዟቸው ዓላማ ለዓመታት የናፈቋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ብቻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በቤተሰብ ጥየቃ ቆይታቸውም በቦረና ዞን ተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የሚጎበኙበት አጋጣሚ ተፈጠረ። ጉብኝታቸውም ሆስፒታሉ በኪነ-ሕንፃ የተዋበ መሆኑን ነገር ግን የህክምና ግብዓት እጥረት ያለበት ሆኖ ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በተልተሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምልከታቸው በሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ሲቸገሩ ማየታቸው የወቅቱ አሳዛኝ ትውስታ እንደነበርና ይህን እጥረት ወደ አሜሪካን ሀገር ሲመለሱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መወሰናቸውን አስታውሰዋል። ዶክተር አብዱረሃማን በተልተሌ አካባቢ ተወልደውና አድገው ለሕክምና ባለሙያነት ያበቃቸውን ትምህርት የቀሰሙ ሰው በመሆናቸው በሆስፒታሉ የተመለከቱት የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት የሺዎችን ሕይወት የሚታደግ ሰብዓዊ ፕሮጀክት የሚቀረጽበት ሃሳብ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። ከዚያም የራሳቸውን የሕክምና ሙያ ዕውቀትና በውጭ ያካበቱትን ግንኙነት በመጠቀም መነሻቸውን ባለፈው ዓመት ለተልተሌ እና ሜጋ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ በድጋፍ ማበርከታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ዓመትም የሞያሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሶስት ትላልቅ የጤና ተቋማት ዘመናዊ ሕክምና መሳሪያዎችን አበርክተዋል። እነኚህ የሕክምና መሳሪያዎች አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ያስታወሱበት በጎ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል። በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ያስተማራቸውን ማህበረሰብ በማስታወስ መንግስት የዜጎችን የሕክምና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። ሌላኛው በአሜሪካን ሀገር በሕክምና ሙያ የሚያገለግሉት ዶክተር ዋቆ ዳደቻ በበኩላቸው፤ ሁሉም ዜጋ በትብብር መስራት ከቻለ የማህበረሰብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል ይላሉ። ይህ የሆስፒታሎችን የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ለማሟላት የሚደረገውን ተሳትፎ ሁሉም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች ሊማሩበት የሚገባ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት የሕክምና ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሻሻል የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ አሳድጎ ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ማሰብ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ፤ በውጭ የሚኖሩ የሕክምና ሙያተኞች የሚያደርጉት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በአርዓያነት የሚወሰድ ነው ብለዋል። በዶክተር አብዱራህማን መሪነት ለቦረና አካባቢ ሆስፒታሎች የተደረገው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የተቋማቱን የጤና አገልግሎት ጥራት በማስጠበቅ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በመግለጽ። በቀጣይም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የህዝባቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በማገዝ በኩል የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።
እኩል አጋርነትን መፍጠር፤ አዲሱ የአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር ምዕራፍ
Dec 30, 2025 921
የአፍሪካ እና ጣልያን ግንኙነት የጀመረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ጣልያን እ.አ.አ በ1947 የተፈራረመቻቸው የሰላም ስምምነቶች ቅኝት ግዛት እና የአንድ አካል የፖለቲካ የበላይነት እንዲያከትም አድርጓል። በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ከቅኝ አገዛዝ የሁለትዮሽ ትስስር ወደ የኢኮኖሚ ትብብር ተሸጋግሯል። ወቅቱ አፍሪካውያን ሉዓላዊነታቸውን የበለጠ ያረጋገጡበትና ጣልያን ከአፍሪካ ጋር በአዲስ መልክ አጋርነቷን ያደሰችበት ነበር። ከቅኝ ግዛት በኋላ የአፍሪካ እና የጣልያን ትብብር በባህል መስክ ላይ ብቻ የተገደበ ነው። የንግድ እና የቴክኒክ ትብብሩ ውስን ነበር። እ.አ.አ ከ1990ዎቹ መግቢያ አንስቶ የአፍሪካ እና ጣልያን ስትራቴጂክ አጋርነት እያበበ የመጣበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል። የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖች እና የንግድ ቢሮዎች መጨመር እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብር አድማስ መስፋት የትብብሩ መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊው የአፍሪካ እና ጣልያን አጋርነት ከእርዳታ ወደ የጋራ እድገት ምዕራፍ መሸጋገር ችሏል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው የሁለቱን ወገኖች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብር አጠናክሯል። የልማት ትብብሩ እርዳታን ከመለገስ ወጥቶ እድገት ተኮር ሆኗል። ከደህንነት ጋር በተያያዘም የፍልሰት አስተዳደር እና ሽብርተኝነት መዋጋት አንዱ የትብብር መገለጫ ነው። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የአፍሪካ እና ጣልያን የባለፈው ጊዜ የነበሩ ፈተናዎች እውቅና በመስጠት አሁን ላይ የሁለቱን ወገኖች የጋራ ፍላጎት ማስጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። የፖሊሲው ሰነድ “ ዋጋ እና ክብርን ማዕከል ያደረገ” ዲፕሎማሲ በሚልው እሳቤው ከአፍሪካ ጋር ላለው ወዳጅነት ከፍተኛ ግምት እንደሚሰጥ አስቀምጧል። እ.አ.አ በ2024 በሮም የተካሄደው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ በቅርብ ጊዜያት ከነበሩ ከፍተኛ መድረኮች መካከል ይጠቀሳል። በጉባኤው ላይ የ45 የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የልማት አጋሮች ተሳትፈዋል። ጉባኤው የተካሄደበት ዓመት ጣልያን የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ሊቀ መንበር የነበረችበት ወቅት ሲሆን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ አንኳር ትኩረት ሆኗል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በወቅቱ ጉባኤውን የአፍሪካ እና ጣልያን ትብብርን በአዲስ መልክ የበየነና ትብብሩ እኩል በቆሙ ወገኖች መካከል ያለ ትስስር እንደሆነ አንስተዋል። ሜሎኒ የሰጪ እና ተቀባይ ዘመን እንዳበቃና የጋራ እድገት እና የጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ ግንኙነት አዲሱ የትብብር ምዕራፍ እንደሆነም ተናግረዋል። በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋቂ ማህማት የጣልያንን አዲሱን የፖሊሲ ለውጥ ያደነቁ ሲሆን አፍሪካ ከቃል ባለፈ እውነተኛ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የፖሊሲ ሽግግሩ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ እና እኩልነትን መሰረት ያደረገ ዓለም መፍጠርን ያማከለ መሆን እንዳለበትም አንስተዋል። ጣልያን የገባቻቸውን ቃሎች ወደ ተግባር መቀየር አለባት ሲሉም ማህማት ተናግረው ነበር። በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉ ቁልፍ ማዕቀፎች አንዱ የማቴይ እቅድ (The Mattei Plan) ይገኝበታል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ ያደረጉት የማቴይ ፕላን ጣልያን ከአፍሪካ ጋር ያላት የኢኮኖሚ እና የልማት ትብብር ማጠናክርን ያለመ ነው። የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ የስትራቴጂክ ማዕቀፉ በጣልያኑ የብሄራዊ የዘይት እና ነዳጅ ኩባንያ መስራች ኤነሪኮ ማቴይ የተሰየመ ነው። ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር ከአጭር ጊዜ እርዳታ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ ትብብርን በማስቀደም እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት መደገፍ፣ የስራ እድሎችን ማስፋት፣ አፍሪካን የአውሮፓ የኢነርጂ አቅራቢ አጋር የማድረግ ስራን ማስተዋወቅ፣ ለአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ኢ-መደበኛ ፍልሰትን ከምንጩ ማድረቅ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት የተላቀቀ የጋራ ተጠቃሚነት እና ትብብርን መፍጠር የእቅዱ አበይት አላማዎች ናቸው ። ለአራት ዓመታት የሚቆየው የማቴይ እቅድ በአፍሪካውያን በበጎ መልኩ የታየ ሲሆን እቅዱ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተነስቷል። እ.አ.አ በ2023 የአፍሪካ እና የጣልያን የንግድ ልውውጥ 59 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዩሮ መድረሱን ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። የንግድ ልውውጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። የአፍሪካ ሀገራት በዋናነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ድፍድፍ ነዳጅ፣ የብረታ ብረት እና ማዕድናት ምርቶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርቶች የሆኑ ጥሬ እቃዎችን ወደ ጣልያን ይልካሉ። ጣልያን የኢንዱስትሪ ማሽን እና መሳሪያ፣ እሴት የተጨመረባቸው እቃዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃዎች ወደ አፍሪካ ከምትላካቸው ምርቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አጠቃላይ የንግድ ምጣኔው ሲታይ ጣልያን በገቢ አብዛኛውን ድርሻ ትይዛለች። ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ ኢነርጂ፣ መሰረተ ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ምርምር፣ ጤና፣ ቴክኖሎጂ፣ የፍልሰት አስተዳደር፣ ደህንነት እና አስተዳደር ከአፍሪካ እና ጣልያን የትብብር መስኮች መካከል ይገኙበታል። የ2026 የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በየካቲት ወር አጋማሽ 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ እና የአህጉሪቷ መዲና ናት። ይህም ጉባኤውን የአፍሪካ ዋንኛ የዲፕሎማሲ አጀንዳ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ በፓን አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ያላት ሀገር ናት። በአሁኑ ሰዓትም በርካታ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን እያዘጋጀች ትገኛለች። የሁለቱን ወገኖች አጋርነት የበለጠ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የማቴይ እቅድ ትግበራ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር፣ የአፍሪካን ተሰሚነት መጨመር፣ ፍልሰትን ጨምሮ በጋራ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አቋም መያዝ፣ የአጋርነት እና የመግባቢያ ስምምነቶች የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤው ውጤቶች ናቸው። የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ካለፈው ታሪካዊ ግንኙነቶች ፣ እያደገ ከመጣው የኢኮኖሚ ትብብር እና የጋራ ፈተናዎችን የመፍታት ቁርጠኝነት አኳያ በአፍሪካ እና በጣልያን መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ታምኖበታል። የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበባ የሚደረገው ጉባኤ አፍሪካ መር አጋርነት ለመፍጠር እና የአፍሪካን ተሰማኒነት ለመጨመር መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው።
አፍሪካውያን ሀገር በቀል አሰልጣኞች ጎልተው የታዩበት የአፍሪካ ዋንጫ !
Dec 28, 2025 849
35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።24 ሀገራት በስድስት ምድቦች ተከፍለው ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው። በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ 24 ሀገራት 12ቱ በአፍሪካውያን የሚሰለጥኑ ናቸው። የአዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ከዛው ከሀገራቸው ናቸው። የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሞሮኮን ለግማሽ ፍጻሜ አድርሰዋል።ሀገሪቷ በዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ከእ.አ.አ 2022 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እየመሩት የሚገኙት ሬግራጉዊ ሞሮኮን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቭዋር አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ኤመርሰን ፋኤ ነው። ፋኤ እ.አ.አ በ2023 በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በተካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል። በውድድሩ መሐል በውጤት ማጣት የተሰናበቱትን ፈረንሳዊውን አሰልጣኝ ጂን-ሉዊስ ጋሴት በመተካት በጊዜያዊነት አሰልጣኝ የተሾመው ፋኤ ቡድኑን ለዋንጫ ማብቃቱ አስወድሶታል። በዘንድሮው ውድድር ዋንጫውን ለማንሳት የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት ተርታ የተመደበችው ሴኔጋል አሰልጣኝ የ41 ዓመቱ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ፓፔ ታው ነው። ፓፔ ታው በተጫዋችነት ዘመኑ ለሴኔጋል ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። አሰልጣኙ ሴኔጋል ለ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እንድታልፍ አድርጓል። ከሶስት ዓመት በፊት በአልጄሪያ በተካሄደው የሰባተኛው የአፍሪካ አገራት ሻምፒዮና(ቻን) ሴኔጋል ዋንጫውን ስታነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ መርቷል። የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ግብጽ የምትሰለጥነው በቀድሞ ኮከቧ ሆሳም ሀሰን ነው። በተጫዋችነት ዘመኑ በአፍሪካ ዋንጫ 11 ግቦችን አስቆጥሯል። በ177 ጨዋታዎች 69 ግቦችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ የብሄራዊ ቡድኑ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። ሆሳም ሀሰን የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ በተጫዋችነት በማንሳት ስኬታማ አሰልጣኝ ነው። ሌላኛው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሮን አሰልጣኝ የ56 ዓመቱ ዴቪድ ፓጉ ነው። ካሜሮናዊው አሰልጣኝ የተሾሙት ከሰሞኑ ነው። ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን በመተካት ቡድኑን እንዲመሩ ኃላፊነት ተጠሎባቸዋል። በካሜሮን እግር ኳስ ባላቸው የታክቲክ መረዳት እና ብቃት የሚሞካሹት ፓጉ ቡድኑን አንድ በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት ተጥሎባቸዋል። ሌላኛው የውድድሩ ተሳታፊ ሀገር ዛምቢያ ናት።የ48 ዓመቱ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ ተከላካይ ሞሰስ ሲቾኔ የቡድኑ የወቅቱ ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2022 እስከ 2024 በጊዜያዊነት እና በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት ሲቾኔ በ2025 ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። ምስራቅ አፍሪካን በውድድሩ ከሚወክሉ ሶስት ሀገራት መካከል አንዷ ሱዳና ናት። ጋናዊው ጀምስ ክዌሲ አፒያ የቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። አፒያ ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የጋቦን አሰልጣኝ ቲዬሪ ሞዩማ የብሄራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነበር። ለ11 ዓመታት ለጋቦን ተጫውተዋል። ከእ.አ.አ 2023 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ይገኛል። የ44 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊ ሞሬና ራሞሬቦሊ የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ናቸው። ከእ.አ.አ 2025 አንስቶ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛል። ሞሬና ከዚህ ቀደም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ነበሩ። የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪናፋሶ አሰልጣኝ የቀድሞ የብሄራዊ ቡድን የአማካይ ተጫዋች ብራማ ትራኦሬ ነው። አሰልጣኙ ከእ.አ.አ ማርች 2024 አንስቶ ቡርኪናፋሶን እየመራ ይገኛል። ትራኦሬ ቡድኑ የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። የአንድ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ቱኒዚያ አሰልጣኝ የቀድሞ የቡድኑ የተከላከይ መስመር ተጫዋች ሳሚ ትራቤልሲ ናቸው። የ57 ዓመቱ አሰልጣኝ ለቱኒዚያ ብሄራዊ ቡድን ለ10 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግሏል። ብሄራዊ ቡድኑን ከእ.አ.አ 2025 ቱኒዚያን እየመራ ይገኛል። በአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ሞዛምቢክ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ፍራንቺስኮ ኩዌሪዮል ኮንዴ ጁኒየር (ቺኩዊኒዮ ኩንዴ) የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ናቸው። የ60 ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሞዛምቢክ ለ15 ዓመታት በተጫዋችነት አገልግለዋል። ለሀገራቸው በ43 ጨዋታዎች 12 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ኩንዴ ከእ.አ.አ 2021 አንስቶ ብሄራዊ ቡድኑን እያሰለጠኑ ይገኛሉ። የናይጄሪያ አሰልጣኝ የሆነው ኤሪክ ቼሌ የኮትዲቭዋር፣ ማሊ እና ፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኝ ናቸው። ይሁንና ቼሌ የአፍሪካ የዘር ግንድ ቢኖራቸውም በፈረንሳይ መወለዳቸው የውጭ ሀገር ዜጋ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። የአፍሪካውያን አሰልጣኞች በአፍሪካ ዋንጫ የማሰልጠን ምጣኔ ከሌሎቹ ወቅቶች አንጻር የአሁኑ የተሻለ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ሀገር በቀል አሰልጣኞች እየተሰጣቸው ያለውን ትኩረት ያሳያል። 12 ሀገራት በውጭ ሀገር ዜጎች ይሰለጥናሉ። በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ አፍሪካውያን የሚያሰለጥኗቸው ወይስ የውጭ ሀገር ዜጋዎች የሚመሯቸው ሀገራት ዋንጫውን ያነሳሉ? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
ትንታኔዎች
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 978
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
የአፍሪካ እግር ኳስ ፈር ቀዳጇ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 1, 2026 932
ክፍል አንድ እንደ መነሻ እ.አ.አ የካቲት 8 ቀን 1957 በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። በካርቱም ግራንድ ሆቴል ሱዳን፣ኢትዮጵያ፣ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካን እግር ኳስ በበላይነት የሚመራውን ተቋም ለመመስረት ምክክር ላይ ናቸው። አህጉሪቷን የሚወክለው ኮንፌዴሬሽን ለማቋቋም መነሻ የሆነው ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) እ.አ.አ በ1956 በፖርቹጋል ሊዝበን ባካሄደው ዓመታዊ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች ከሌሎች አህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት ጋር ያደረጓቸው መደበኛ ምክክሮች ናቸው። በካርቱም የተሰበሰቡት አራት አገራት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በይፋ መሰረቱ። ግብጻዊውን አብደል አዚዝ አብደላ ሳሌምን በሙሉ ድምጽ የካፍ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አድርገው መረጡ። ካፍን ያቋቋሙት አገራት እ.አ.አ በ1957 የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን እንዲካሄድ ወሰኑ። የመጀመሪያውን የካፍ መተዳደሪያና የውድድር ደንቦች ያዘጋጁት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ናቸው። የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና የፎርፌ ውጤት የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ከየካቲት 10 እስከ 16 1957 በሱዳን ካርቱም ተካሄዷል። በውድድሩ ላይ ሱዳን፣ኢትዮጵያና ግብጽ ተሳታፊ ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው አስቀድሞ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ትሳተፋለች ተብሎ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ከአገሪቷ በነበረው የአፓርታይድ የዘር መድሎ ምክንያት ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ደቡብ አፍሪካ ከውድድሩ ውጪ የሆነቸው በአፓርታይድ ሕግ ነጮች ሙሉ በሙሉ በነጭ ወይም በሙሉ የተገነባ ብሔራዊ ቡድን እንጂ መቀላቀል አንችልም በማለታቸው ምክንያት ነው። በዚህም ምክንያት ከደቡብ አፍሪካ ጋራ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋን ልታደርግ የነበረችው ኢትዮጵያ 2 ለ 0 በፎርፌ በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፋለች። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ አለፈች። እ.አ.አ የካቲት 16 1957 በካርቱም ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ኢትዮጵያን 4 ለ 0 በማሸነፍ ታሪካዊውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች። አራቱንም ግቦች ያስቆጠረው የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ዲያብ አል-አታር ሲሆን በአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ አራት ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋችና በአምስት ግቦች የመጀመሪያው የውድድሩ ኮከብ ግቢ አግቢ በመሆን ድርብ ታሪክ ጽፏል። ኢትዮጵያ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች። በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምንም የማጣሪያ ውድድር አልተደረገም። በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ግብ ጠባቂ ሚካኤል ጊላ ተከላካዮች አየለ ተሰማ፣መኩሪያ ከበደ አስፋው፣አዳሙ ዓለሙ፣አዳል ተክለስላሴ አማካዮች ናስር በርሄና ሳሙኤል ዘውዴ አጥቂዎች አብርሃም ባይሩ፣አምደስላሴ ነጸረ፣አስፋው ብርሃኔና ከበደ መታፈሪያ ናቸው። በአፍሪካ ዋንጫና እግር ኳስ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን በሱዳን አሀዱ ብላ ጀመረች። የኢትዮጵያ ሁለተኛ ተሳትፎ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1959 በግብጽ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ አድርጋለች። ሱዳን ሌላዋ በውድድሩ ላይ የተሳተፈች አገር ናት። የውድድሩ ፎርማት በአገራቱ መካከል እርስ በእርስ በሚደረጉ ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያነሳበት ነበር። በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች በግብጽ 4 ለ 0፤ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ግብጽ ሱዳንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ብቸኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያነሳችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተካሄደው በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እ.አ.አ በ1962 ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች ለየት የሚያደርገው አራት አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉበት ነው። ኢትዮጵያ የውድድሩ አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራችን በቀጥታ ለውድድሩ ስታልፍ ፤ በተመሳሳይ የግብፅ ቡድንም የ1959 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዋንጫ አሸናፊ ቡድን ስለነበር በቀጥታ ለ3ኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፉ ዩጋንዳና ቱኒዚያ የማጣሪያ ጨዋታ አድርገው ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈዋል። በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ሲሆኑ ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዋ ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። አጥቂው ሉቺያኖ ቫሳሎ በ32ኛው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ያስቆጠረችው የመጀመሪያ ግቧ ሆኖ ተመዝግቧል። ቫሳሎ በ75ኛው ደቂቃ በጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ እና ግርማ ተክሌ ቀሪዎችን ግቦች ለኢትዮጵያ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ግብጽ ዩጋንዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ከኢትዮጵያ ጋር ደረሰች። በፍጻሜው ጨዋታ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በ35ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት በግብ ግብጽን መሪ ማድረግ ችላ ነበር። ከእረፍት መልስ ግርማ ተክሌ በ74ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጋለች። በ75ኛው ደቂቃ አሊ መሐመድ ባዳዊ አብደል ፋታህ በድጋሚ ግብጽን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ። አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን በድጋሚ አቻ አደረገ። ጨዋታው በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሬ ሰዓት አምርቷል። በጭማሬ 30 ደቂቃው ኢታሎ ቫሳሎ በ101ኛው እና መንግስቱ ወርቁ በ118ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ኢትዮጵያ 4 ለ 2 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉራዊውን ዋንጫ ከፍ አድርጋለች። በፍጻሜው ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው አጥቂው መንግስቱ ወርቁ በአጠቃላይ በውድድሩ ላይ ሶስት ጎሎችን ከመረብ ላይ በማሳረፍ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ጨርሷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት አገራት የተሳተፉበት የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እ.አ.አ በ1963 በጋና አስተናጋጅነት በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው። በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች የተሳተፉ ሲሆን በሁለት ምድብ እያንዳንዳቸው ሶስት አገራት ተደልድለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። የውድድሩ ፎርማት በየምድቡ አንደኛ ሆኖ የጨረሰ አገር ወደ ፍጻሜው እንዲሁም ሁለተኛ የወጡ አገራት ለደረጃው ያለፉበት ነበር። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ጋና ቱኒዚያ ጋር ተደልድላች። በአክራ ስፖርት ስታዲየም ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁ ሁለት እንዲሁም ግርማ ተክሌና ግርማ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው አንድ አንድ ግቦች ቱኒዚያን 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ከምድቡ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቋ ለደረጃ ጨዋታ የቀረበች ሲሆን በግብጽ 3 ለ 0 ተሸንፋለች። በፍጻሜው ጋና ሱዳንን 3 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አነሳች። ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1965 በቱኒዚያ አስተናጋጅነት በተካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስድስት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከቱኒዚያና ሴኔጋል ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በቱኒዚያ 4 ለ 0 ተሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ በሴኔጋል 5 ለ 1 ተሸንፋለች። በጨዋታው ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር። በፍጻሜው ጋና ቱኒዚያን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ 1968 የተካሄደውን ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ኢትዮጵያ ነበረች። ውድድሩን ያስተናገደው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ስታዲየም(የአሁኑ አዲስ አበባ ስታዲየም) ነበር። በሻምፒዮናው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣አልጄሪያና ዩጋንዳ ጋር የተደለደለች ሲሆን ሶስቱንም የምድብ ጨዋታዎቿን አሸንፋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ግርማ አስመሮም ተስፋይ በጨዋታና ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በሁለተኛ ጨዋታዋ በኩረጽዮን ገብረሕይወት ባስቆጠራት ግብ ኮትዲቭዋርን 1 ለ 0 ረታለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ አጥቂው መንግስቱ ወርቁና ሸዋንግዛው አጎናፍር በጨዋታ እንዲሁም ሉቺያኖ ቫሳሎ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ግቦች አልጄሪያን 3 ለ 1 በማሸነፍ ከምድቧ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜው አልፋለች። ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታዋን ያደረገችው ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ነበር። ራውል አልበርት ኪዱሙ ማንታንቱ በሶስተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጎል። ሊኦን ሙንጋሙኒ በ16ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ የኮንጎን መሪነት ወደ 2 ለ 0 ከፍ አድርጓል። ሉቺያኖ ቫሳሎ በ25ኛው ደቂያ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን ወደ ጨዋታው እንድትመለስ አድርጓል። መንግስቱ ወርቁ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ አመራ። በጭማሬ ሰዓቱ ሊኦን ሙንጋሙኒ በ100ኛው ደቂቃ ያስቆጠራትን ግብ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን አሸናፊ በማድረግ ወደ ፍጻሜው እንድታልፍ አድርጎታል። ኢትዮጵያ ለደረጃው ባደረገችው ጨዋታ ላውረን ፖኩ ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ተሸንፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው ውድድር አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግብ ያስተገደችበት ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሱዳን እ.አ.አ 1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ በአህጉራዊው የውድድር መድረክ ተሳትፋለች። በውድድሩ ላይ ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከኮትዲቭዋር፣ካሜሮንና ሱዳን ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ በምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በሱዳን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተረታለች። በሁለተኛው ጨዋታም በካሜሮን 3 ለ 2 የተሸነፈች ሲሆን መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፋለች። መንግስቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ ያሳረፈ ተጫዋች ነበር። በዚህ ጨዋታ አጥቂው ላውረን ፖኩ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በውድድሩ 12 ግቦችን ተቆጥረውባታል። በፍጻሜው ሱዳን ጋናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ለማድረግ ስድስት ዓመት መጠበቅ ነበረባት። እ.አ.አ በ1976 ራሷ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ በድጋሚ ወደ ውድድር ተሳትፎ ተመልሳለች። በውድድሩ ላይ አሁንም የተሳተፉ አገራት ቁጥር ስምንት ነበር። ኢትዮጵያ በውድድሩ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ዩጋንዳና ጊኒ ጋር ተደልድላለች። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሰለሞን ሽፈራውና ተስፋዬ ስዩም ግቦች ዩጋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች። በሁለተኛ ጨዋታዋ ኢትዮጵያን በጊኒ የ2 ለ 1 ሽንፈት አጋጥሟታል። ሰለሞን ሽፈራው ኢትዮጵያን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። መሐመድ አሊ ለኢትዮጵያ ግቧን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአራት ነጥብ ከምድቧ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ሳትችል ቀርታለች። በፍጻሜው ሞሮኮ ጊኒን በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ማንሳት ቻለች። ይቀጥላል ….
ብክነትን መቀነስ የኃይል አቅርቦትን ማሳደግ፤ የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳ
Dec 8, 2025 1489
አፍሪካ በዓለማችን በታዳሽ ኃይል እምቅ ሀብቶችን የያዘች አህጉር ናት። የዓለም 60 በመቶ የፀሐይ ኃይል ሀብት የሚገኘው በአፍሪካ ነው። አህጉሪቱ ከፀሐይ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቴራዋት ሰዓት ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አላት። ይሁንና በፀሐይ የምታመነጨው ኃይል ድርሻ አነስተኛ መሆነን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የእ.አ.አ 2023 ጥናት ያመለክታል። የዓለም ባንክ ተቋም የሆነው ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በበኩሉ አፍሪካ 25 በመቶ የዓለም የንፋስ ኃይል አቅም ያላት ሲሆን 180 ሺህ ቴራ ዋት ሰዓት ማመንጨት እንደምትችል ይገልጻል። ይሁንና በዓለም ላይ በዘርፉ ያላት ድርሻ ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን ያነሳል። ሃይድሮ ፓወር የአፍሪካ ሌላኛው የኢነርጂ ሀብት ማሳያ ነው። የአህጉሪቷ ወንዞች እና ተፋሰሶች በየዓመቱ 1 ሺህ 500 ቴራ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም ቢኖራም ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶውን ብቻ ነው። የናይል ተፋሰስ፣ የኮንጎ ተፋሰስ እና የዛምቤዚ ተፋሰሶችን የያዘችው አፍሪካ ከፍተኛ የሃይድሮ ፓወር አቅሟን መጠቀም አልቻለችም ይላል የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥናት። ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ያለው የእንፋሎት ኃይል ሌላኛው ትልቅ እድል ነው። የአፍሪካ የእንፋሎት (ጂኦተርማል) አቅም ከ15 እስከ 20 ጊጋዋት መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መረጃ ያሳያል። አፍሪካ ከዓለም የኢነርጂ ምርት ውስጥ ከአራት በመቶ በታች እንዲሁም በታዳሽ ኃይል ደግሞ ከ1 ነጥብ 6 በመቶ ያነሰ ድርሻ እንዳላት መረጃዎች ያመለክታሉ። የአፍሪካ የኢነርጂ ምህዳር ሁለት ተጻራሪ እውነታዎችን የያዘ ነው። አህጉሪቷ የዓለምን 17 በመቶ ህዝብ ብትይዝም በዓለም የኢነርጂ አጠቃቀም ያላት ድርሻ ከአራት በመቶ በታች ነው። በአሁኑ ሰዓት 600 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን የአፍሪካ ህዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። 21 በመቶ አፍሪካውያን ብቻ ንጹህ የማብሰያ ነዳጅ እና ቴክኖሎጂዎችን ያገኛሉ። ባህላዊ የምግብ ማብሰያ አማራጮች ለጤና አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ናቸው። በአፍሪካ ከከተሜነት መስፋፋት እና ከፈጣን የህዝብ እድገት ጋር በተያያዘ የኢነርጂ ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል። እ.አ.አ በ2040 የአፍሪካ ህዝብ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ህዝብ እንደሚያልፍ ትንበያዎች ያሳያሉ። በተለይም የህዝብ ብዛት መጨመሩ በኢነርጂ አቅርቦት ላይ ጫና ያሳድራል። ከእ.አ.አ 2014 እስከ 2023 የአፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ በእጥፍ አድጎ ከ32 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ወደ 62 ነጥብ 1 ጊጋ ዋት ማደጉ መልካም የሚባል እምርታ መሆኑን የዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኢነርጂ ኤጀንሲ ይገልጻል። የአፍሪካ ሌላኛው ፈተና የምትጠቀመውን ኢነርጂ የብክነት ምጣኔ ነው። በበቂ ሁኔታ ባልተደራጀው የኢነርጂ ስርዓት ምክንያት አፍሪካ በየዓመቱ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ገንዘብ ታጣለች። እንደ ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ከሆነ አፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀሟን የምታሻሽል ከሆነ 30 በመቶ የኢነርጂ ወጪዋን መቀነስ ትችላለች። ይህም የአፍሪካ መንግስታት ለማህበራዊ ልማት የሚያወጡትን በጀት እንደሚያሳድግ እና አዲስ የኃይል ማመንጫዎችን ሳትገነባ የካርቦን ልቀትን መቀነስ የምትችልበትን እድል ይፈጥርላታል። ኢትዮጵያ ከወራጅ ወንዞች በአመት 124 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያላት ሲሆን ከ36 እስከ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የከርሰ ምድር የውሃ ሃብት እንዳላት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከገፀ ምድር የውሃ ሃብቷ 83 በመቶ የሚገኘው ከተከዜ፣ ባሮ፣ አባይና ጊቤ ኦሞ ወንዞች ነው። አንዱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚመነጨው ካላት የውሃ ሀብት ነው። ኢትዮጵያ በውሃ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና በጂኦ-ተርማል የኃይል አማራጮች በአጠቃላይ ከ300 እስከ 400 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላት መረጃዎች ያሳያሉ። በ10 ዓመት መሪ ልማት እቅዱ ኢትዮጵያ አሁን እያመነጨች ያለውን 4 ሺህ 818 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማሳደግ አቅዳለች። ከለውጡ በኋላ በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም የተለያዩ የማሻሻያ ስራዎች ተከናውነዋል። ከስራዎቹ መካከል ለሶስት አስርት ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የኢነርጂ ፖሊሲ ማሻሻል ይገኝበታል። ፖሊሲው ከ2013 ዓ.ም አንስቶ የማሻሻያ ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቷል። የፖሊሲ ማሻሻያው የተዘጋጀው አሁን ያለውን ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ነባራዊ እውነታ መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ለኢነርጂ ፖሊሲው ማሻሻል ምክንያቶች ከሆኑት መካከልም ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ፣ ከአረንጓዴ ልማት፣ ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ማጣጣም በማስፈለጉ እንደሆነም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በአፍሪካ ግዙፉ የኢነርጂ ፕሮጀክት ሲሆን ለቀጣናው እና ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አቅምን ይዞ መጥቷል። ከፖሊሲው ትኩረት አንዱ ከአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ለጎረቤት አገራት ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሆነም በሰነዱ ላይ ሰፍሯል። በ10 ዓመቱ የመሪ ልማት እቅዱም ዜጎችን በስፋት የአሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የማድረግ ግብ ተይዟል። ከዚህ ባሻገር በእቅዱ ኢትዮጵያ የቀጣናው ሀገራትን በኃይል የማስተሳሰር ዕቅድ ሰንቃ እየሰራች ትገኛለች። በእቅዱ ለጎረቤት አገራት እየቀረበ ያለውን 2 ሺህ 803 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ወደ 7 ሺህ 184 ጊጋ ዋት ሰዓት የማሳደግ ውጥን ተይዟል። የአፍሪካ የኢነርጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመቀነስ የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ነው። የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ ይደረጋል። ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው። የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል። “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው። አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው። ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል። የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋንኛ ሀብት ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢነርጂ ውጤማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልህቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው። ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ከፍተኛ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ያልዋለ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም በቀጣይ የዓለም የኢነርጂ ሽግግር እና አቅርቦት ውስጥ ትልቅ ሚና የሚጫወት ነው። የኢነርጂ አቅሙን ትሩፋቶች የመጠቀም ጉዳይ አነስተኛ ነው ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያላቸውን የታዳሽ ኃይል ምንጭን ለመጠቀም እየወሰዷቸው የሚገኟቸው እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው። የኢነርጂ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የተቀናጁ ፖሊሲዎች፣ የተቀናጀ ቀጣናዊ የኃይል ቋቶችን መፍጠር፣ የኢነርጂ ፋይናንስን ማሳደግ እና የመንግስታት የፖለቲካ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ኢነርጂ አቅሞች ወደ ዘላቂ ልማት፣ የኢነርጂ ደህንነት የማረጋገጥ፣ የአየር ንብረትን የሚቋቋም ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ይዞ ይመጣል።
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 3805
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3458
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2292
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8083
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6570
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ ዐሻራ ከዓድዋ - እስከ አፍሪካ ኅብረት
Feb 14, 2026 221
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የፖለቲካ፣ የታሪክ እና ዲፕሎማሲ ምኅዳር ውስጥ ልዩ ስፍራ እና ተጽዕኖ ያላት ሀገር ናት። የጥንታዊ ሥልጣኔዎች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ፤ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ የአፍሪካ ሀገር ከመሆኗ ባሻገር ለፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ መስፋፋት ትልቅ ሚና ተጫውታለች። ይህንም ታሪክ ይዘክራል። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀመራል አይበገሬነት፣ ሉዓላዊነት እና የፓን አፍሪካ መንፈስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ካሳረፈቻቸው ዐሻራዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በዘመናዊው ዓለምም በአፍሪካ አጀንዳዎች ላይ ወሳኝ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት እና ማንነት ተምሳሌት ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ1896 በዓድዋ ጦርነት በጣሊያን ኃይሎች ላይ የተቀዳጀችው ድል በአፍሪካ እና በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው። አብዛኛው የአፍሪካ አኅጉር በቅኝ ግዛት ውስጥ በነበረበት ወቅት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ድል ሉዓላዊነቷን ከማስጠበቅ ባለፈ በአፍሪካ እና በአፍሪካ ዳያስፖራ የነጻነት ትግሎች እንዲቀጣጠሉ አድርጓል። በተለይም ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ይህ ታሪካዊ ዐሻራ ኢትዮጵያን የጥቁሮች ኩራት፣ ትግል እና ራስን የመቻል ምልክት እንድትሆን አስችሏታል። የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ ኢትዮጵያ የአኅጉሪቷ የዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል አስችሏል። እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት) ታሪካዊ ምሥረታ የተካሄደው በኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ ከድርጅቱ መሥራች ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ይህም የአፍሪካ የጋራ የፖለቲካ ድምጽ እንድትሆን ምክንያት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሴኤ) እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት የሚገኙባት ኢትዮጵያ፤ በዲፕሎማሲው ምክክር እና ውሳኔ ሰጪነት ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና የበለጠ የሚያጠናክር ነው። የፓን አፍሪካኒዝም ድምጽ ኢትዮጵያ በቅኝ አለመገዛቷ ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ ሥር መስደድ ወሳኝ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ ለአፍሪካ አንድነት እና የጋራ ምላሽ አጥብቃ ስትሞግትም ቆይታለች። በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ መድረኮች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፈታት አለባቸው የሚለውን እሳቤ ለማስረጽ አበክራ እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተኮር መፍትሔዎች ከቃላት ባለፈ በአኅጉራዊ የትሥሥር አጀንዳዎች፣ ሰላም እና ደኅንነት ማዕቀፎች እንዲሁም የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ፈተናዎች እንዲፈቱ ድጋፏን በመስጠት ቁርጠኝነቷን አሳይታለች። የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትንም በፍጥነት አጽድቃ ወደ ሥራ ማስገባቷ የዚሁ አንድ ማሳያ ነው። ሰላም ማስከበር እና ቀጣናዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ በቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ስትራቴጂካዊ ሚና እየተወጣች ነው። በዚህም መሠረት ለተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ድርሻ ትይዛለች። ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ግጭት ባለባቸው የአፍሪካ ሀገራት ወታደሮቿን በመላክ ለሰላም እና ደኅንነት ያላትን ሚና በተግባር ገልጣ አሳይታለች። የተባበሩት መንግሥታትም ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር እየተወጣች ላለው ሚና ምሥጋናውን ማቅረቡ ይታወቃል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሀገራት ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተወጣችው የእርቅ እና የዲፕሎማሲ ሚናም ተጠቃሽ ነው። የኢኮኖሚ እድገት እና ቀጣናዊ ትሥሥር ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች። በ2017 ዓ.ም ማብቂያ የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በግንባታ ላይ የሚገኘው ኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከግዙፍ መሠረተ ልማትነታቸው ባለፈ ቀጣናዊ ትሥሥር በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና አላቸው። ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢነርጂ የስኅበት ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምትሸጠው ኢነርጂ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትብብርን የሚያሳልጥ ነው። የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድን ጨምሮ የመንገድ መሠረተ ልማቶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢትዮጵያን የቀጣናዊ ትሥሥር ማዕከል እንድትሆን እያደረጓት ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እየተከናወነ ያለው አረንጓዴ ዐሻራም፤ ኢትዮጵያን የአረንጓዴ ትብብር እና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተምሳሌት ማድረግ ችሏል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ትገኛለች። የባህል እና የሥልጣኔ አስተዋጽዖ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ፣ ቱባ ባህል እና ብዝኃነት መገለጫዋ ናቸው። የቋንቋ ብዝኃነት በአፍሪካ ውስጥ ገራገር የዲፕሎማሲ ኃይል (Soft Power) እንዲኖራት አስተዋጽዖ አድርጓል። የኢትዮጵያ የሀገርነት ታሪክ እና የሥልጣኔ ትርክት አፍሪካ ያሏትን ጥልቅ የታሪክ ሥሮች ይበልጥ አጉልቶ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነቶች፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች እና አስደማሚ የሥነ-ሕንጻ ሥራዎች በአፍሪካ ባህል እና ሥልጣኔ ውስጥ ያላቸው ሚና ትልቅ ነው። ኢትዮጵያ አሁንም በአፍሪካ አንድነት እና መረጋጋት ውስጥ እንደ ቁልፍ ምሰሶ ትታያለች። በአኅጉሪቱ ውስጥ ያላት ድርሻ በታሪክ ሥር የሰደደ እና አሁን ባለው ዘመን በዲፕሎማሲ፣ በሰላም ግንባታ እና ልማት ሥራ በግልጽ ጎልቶ ይታያል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና እንዲሁም የአይበገሬነት እና የነጻነት ምልክት ናት። አፍሪካ አንድነቷን ለማረጋገጥ፣ የተረጋጋ አኅጉር ለመፍጠር እና በራስ ዐቅም ነገሮችን የመከወን ጉዞ ትልም ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ ቁልፍ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ ኑረትና ንጽህና ሥርዓት፤ ለአጀንዳ 2063 ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬና ነገ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። ጉባዔው ኢትዮጵያ አኅጉራዊ የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲያዊ መድረክ መሆኗን ዳግም የምታሳይበት ነው።
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!!
Feb 6, 2026 304
"ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በያንተስራ ወጋየሁ -ዲላ ቀን ቀንን እየወለደ ጊዜ ሳያቋርጥ እንደ ዥረት መፍሰሱን አያቆምም። ትናንት አዲስ የነበረው አሮጌው የሚባልበት፣ ዛሬ አዲስ ሆኖ ነገ አሮጌ ለመባል ይሮጣል። ወቅቶች ይፈራረቃሉ፣ ይመሻል፣ ይነጋል፣ ትናንት ለዛሬ፣ ዛሬ ለነገ እንዲህ እንዲህ እየተቀባበሉ ዘመን ዘመንን እየተካ ዛሬ ላይ ተደርሷል። በጥምር ግብርናውና በቡናው የሚታወቀው ጌዴኦ ትናንትን ሸኝቶ ዛሬን እንደ አዲስ ለመቀበል ሽር ጉድ እያለ ነው። በክረምቱ የተዘራው ሰብል ተሰብስቦ ወደ ጎተራ እንዳስገባ ጌዴኦ አዲስ ዓመቱን ‹‹ዳራሮ››ን ይቀበላል። ዳራሮ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ቂም የያዘ ቂምና ቁርሾውን የሚተውበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ አዛውንቶች ወደ ሽምግልና የሚሸጋገሩበት እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው የጌዴኦ አርሶ አደር ካመረተው ምርት ለመሪው፣ ልጆች ለወላጆችና ለአሳዳጊዎቻቸው፣ አዲስ ተጋቢዎች ለአማቾቻቸው፣ ቂም የያዘ ሰው እንዲሁ የተቀየመውን ሰው ይቅርታ ለመጠየቅ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። "ጉማታ" በጌዴኦ ዘመን መለወጫ ወቅት የሚፈጸም ስጦታ ነው። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማኅበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ነው። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። በዳራሮ በዓል አከባበር ውስጥ "ጉማታ" እጅግ አስፈላጊና ትልቅ ትርጉም ያለው ባህላዊ የክብር ስጦታ የመስጠት ሥርዓት ነው። "ጉማታ" ማለት በቀጥታ ትርጉሙ "ስጦታ" ማለት ቢሆንም፣ በጌዴኦ ባህል ግን ከስጦታ በላይ ነው። ምስጋናን፣ ፍቅርን፣ አክብሮትንና በረከትን የመጋራት መገለጫ ነው። የጌዴአ ባህላዊ የባሌ ስርዓት መሪ ሆነው የሚሰየሙት አባ ገዳ ለህዝብ ከመጸለይ፣ ከማስታረቅና ክፉን በማውገዝ ህዝቡ ተፈጥሮን እንዲንከባከብ ከማስተማር ውጭ አይዘሩም፣ አይነግዱም፣ አልፎም እንሳስትን አያረቡም፡፡ የዳራሮ በዓልን ተከትሎ ህዝቡ የሚያቀርብላቸውን "ጉማታ" በመቀበል ባህላዊ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት ውጪ። ኑሮው ከጥምር እርሻ ጋር የተቆራኘው የጌዴኦ ሕዝብ ዘርቶ ካጨደው፣ አርብቶ ካገኘው ከብት፣ አንቦ ከቆረጠው ማር፣ ከሁሉም በአይነት በአይነቱ ሸክፎ ዳራሮ ወደ ሚከበርበት ሶንጎ (አደባባይ) ይተማል። ለጉማታ ከሚቀርቡ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች አንዱ ማር ነው። ማር በጌዴኦ ዘንድ የጣፋጭ ዘመንና የጤና ምልክት ተደርጎ ይወሰዳልና ዋናው ስጦታ ነው። ጌዶኦዎች ቡና፣ ቅቤና ባህላዊ ምግቦች፣ የቁም እንስሳት በግና ስንጋ እንዲሁም ገንዘብ በመያዝ በበዓሉ ውስጥ የጉማታ ስርዓት ሲደርስ ተሽቀዳድመው ለአባ ገዳው በመስጠት ምርቃት ይቀበላሉ። "ጉማታ" የተቀበለው ሰው የሚመርቀው ምርቃት በሰጪው ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይታመናልና ከስጦታው ይልቅ ምርቃቱ ትልቅ ዋጋ አለው። "ያገኘሁትን ምርት ብቻዬን አልበላም" ብሎ የሚያምነው ጌዴኦ በረከትን ማካፈል ለቀጣዩ ዓመት ተጨማሪ በረከት እንደሚያገኝ ስለሚያውቅ ጉማታ መስጠት የዘመናት ቅርሱ ነው። ጉማታ ከአባ ገዳና ከባህል ሽማግሌዎች ባለፈ አርሶ አደሩ ከማጋኖ (ከፈጣሪ) ያገኘውን በረከት ለሚወዳቸውና ለሚያከብራቸው ሰዎች የሚያቀርብበት መንገድ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ልጆች ለወላጆቻቸውና ለቤተሰብ አባላት ላሳደጓቸውና ለሰጧቸው ምርቃት ምስጋናቸውን ለመግለጽ ጉማታ ይዘው ይሄዳሉ። በቅርቡ ጋብቻ የመሠረቱ ወጣቶች ወደ አማቾቻቸው ቤት ጉማታ ይዞ በመሄድ ዝምድናቸውን ያጠናክራሉ። በዓመቱ ውስጥ ቅሬታ ወይም ቂም ካለ፣ በዳራሮ ወቅት ጉማታ ይዞ በመሄድ ይቅርታ ይጠየቃል። ጉማታ የሰውን ልብ ለማለስለስና አዲስ ዓመትን በሰላም ለመጀመር ያገለግላል ተብሎ ስለሚታመን። ጉማታ በቤት ውስጥ ተዘጋጅቶ ወደ ታላላቆች ቤት ወይም ወደ ማህበረሰቡ አደባባይ የሚወሰድ በመሆኑ፣ የግለሰብን ደስታ ወደ ማህበረሰባዊ ደስታ የሚቀይር ድልድይ ስለመሆኑም ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠቆሙት። በአጠቃላይ ጉማታ ከሌለ የዳራሮ በዓል ሙሉ አይሆንም። ጉማታ የጌዴኦን ሕዝብ አንድነት የሚያጸና፣ ትውልድን ከትውልድ የሚያስተሳስር ሀገር በቀል እሴት ነው። ይህም የመደጋገፍ እሴትን ከማጠናከር በተጓዳኝ ህዝቡ የመንግስት ገቢን እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን መሰረት የጣለ ነው ይላሉ። የዘንድሮው ዳራሮ ከቤት በተለይም ከአባ ገዳው መኖሪያ አንስቶ በሶንጎዎችና በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ጭምር እየተከበረ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ጉማታም ዋናው የበዓሉ እሴት ሆኖ እየተከበረ ነው ብለዋል። ባህልና ማንነትን በማስጠበቅና በማዳበር፣ ባህሉ ወደ ወጣቶች እንዲተላለፍ በማበረታታት እንዲሁም የጌዴኦ ባህልን ለሌሎች ህዝቦች ለማስተዋወቅና የማህበረሰብ አንድነትና ባህላዊ እሴትን ለማጠናከር እያገለገለ ያለው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ ጥር 29 እና 30 በዲላ ከተማ ይከበራል። የዳራሮ በዓል የጌዴኦን ሕዝብ የሥራ ባህል፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ዕውቀትና የሰላም እሴት ለዓለም የሚያሳይ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህ በዓል በተለይ የጌዴኦ የባህላዊ መልክዓ ምድር (Cultural Landscape) በዩኔስኮ (UNESCO) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ፣ አሁን ላይ ከቤትና ከአደባባይ አልፎ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እያገኘ ያለ ታላቅ እሴት ሆኗል። የዓመት ሰው ይበለን!!