የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
በውድድሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለዓለም ዋንጫ የመለያ ጨዋታ አልፏል።
ቡድኑ ወደ መለያ ጨዋታው የተሸጋገረው ትናንት ቱኒዚያን 1 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ ነው።
ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል።
ሞዛምቢክ በምድብ ሶስት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በተያያዘም በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ከቱኒዚያው ጨዋታ በኋላ ዛሬ ልምምድ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።