ቀጥታ፡

አስቶንቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ አስቶንቪላ ፍራይበርግን 3 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሚገኘው ቲውፕራሽ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩሪ ቲሊማንስ፣ ኢሚሊያኖ ቡንዲያ እና ሞርጋን ሮጀርስ የማሸነፊያ ጎሎቹን አሳርፈዋል።

በጨዋታው አስቶንቪላ የተሻለ ብልጫ የወሰደ ሲሆን ተጨማሪ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን መጠቀም አልቻለም።

የአስቶንቪላ ደጋፊ የሆኑት የዌልስ ልዑል ዊሊያምስ ጨዋታውን በስታዲየም በመገኘት ተከታትለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ አስቶንቪላ የዘንድሮው የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

ቪላ እ.አ.አ በ1982 የዩሮፓ ካፕ (የአሁኑ ሻምፒዮንስ ሊግ) ካነሳ 44 ዓመታት በኋላ ሌላኛውን የአውሮፓ ክብር ተቀዳጅቷል።

ቡድኑ እ.አ.አ በ1996 የሊግ ካፕ ዋንጫውን ካነሳ በኋላ የመጀመሪያ ዋንጫውን አሳክቷል።

ስፔናዊው የአስቶንቪላ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ዩሮፓ ሊግ ዋንጫን አምስት ጊዜ በማንሳት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል።

ኤምሬ "የዩሮፓ ሊግ ንጉስ" የሚል የክብር ስም ተሰጥቷቸዋል።

የዩሮፓ ሊግ አሸናፊው አስቶንቪላ በሊጉ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀ በቀጣዩ ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፉ የእንግሊዝ ክለቦች ብዛት ወደ ስድስት ያድጋል።

ፍራይበርግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ የማንሳት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም