ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማት የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤት እያስገኘ ነው
Jul 13, 2026 21
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማት የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤት እያስገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት የአህጉር-አቀፍ የእንስሳት ሃብት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ፎረሙ በአፍሪካ የእንስሳት ሃብት ልማትን በማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል፣ አርብቶ አደሮች የተሻለ ገበያ እንዲያገኙና የሀገራትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማትን በማሳደግ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ እየሰራችበት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም አርሶና አርብቶ አደሮች የሚያጋጥሟቸውን የውሃና የመኖ እጥረት በዘላቂነት የሚቀርፉ እንዲሁም የእንስሳት ሕክምና መስጫ ተቋማትን የማስፋፋት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከአርብቶ አደሮች ጋር የሚሰሩ ተቋማትን፣ የእንስሳት ገበያ ማእከላትን ለአርብቶ አደር አካባቢዎች ተደራሸነት የማጠናከር ስራዎችንም እየተሰራበት እንደሆነም አብራርተዋል። በአፍሪካ ህብረት የእንስሳት ሀብት ቢሮ ዳይሬክተር ሁያም ሳሊህ (ዶ/ር) አፍሪካ የዓለምን የእንስሳት ሃብት ከፍተኛ ድርሻ ብትይዝም፣ ከእሴቱ ግን የምታገኘው በጣም አነስተኛ ነው ብለዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን ግዙፍ የእንስሳት ሃብት በማልማት የአርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሻሻል በሁሉም ዘርፍ የኢንቨስተመንት አማራጮችን ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የአፍሪካን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የሚያሳልጥ የዲጂታል አቅም መገንባት ያስፈልጋል
Jul 13, 2026 73
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የሚያሳልጥ የዲጂታል ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ገለጸ። የአፍሪካ የትምህርት ፈጠራ ኤክስፖ 2026 በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። ''የትምህርት ዲጂታል ሽግግርና የፈጠራ መፍትሔዎችን ማሳደግ'' በሚል መሪ ሃሳብ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ኤክስፖ የፈጠራ ባለቤቶች፣ የጥናትና ምርምር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባንያን ክምቢና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በአፍሪካ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ብቁ የሰው ሃይል መገንባት ያስፈልጋል። ለዚህም በአፍሪካ ሕብረት በተገባው የፖለቲካ ቁርጠኝነት መሰረት አፍሪካዊያን በተለወጠ ዓለም ውስጥ የትውልዱን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካን ትምህርት ወደ ዲጂታል ማሸጋገር ወቅታዊ እና የሀገራትን ትኩረት የሚፈልግ ነው ብለዋል። በአፍሪካ አካታች የዲጂታል ትምህርት ስርአት በመዘርጋት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፣ የዲጂታል የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት ላይም ይበልጥ መስራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። ትምህርትን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቃኘ ማድረግ እና የአስተማሪዎችን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ትምህርትን ለማሸጋገር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አክለዋል። የጥናትና ምርምር ተቋማትን አቅም ማሳደግም የሀገራት የትኩረት ማዕከል ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ ህብረትም በአህጉሪቱ ትምህርትን ለማዘመን የሚሰሩ ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
በኦሮሚያ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ የተተገበሩ አሰራሮች ውጤት አስገኝተዋል
Jul 13, 2026 89
አዳማ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ በግብርና ዘርፍ የተተገበሩ አሰራሮች ውጤት ማስገኘታቸውን የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዲ ያዩ (ዶ/ር) ገለፁ። የክልሉ የመንግሥትና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዘርፍ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል። በግምገማው መድረክ ላይ ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽነር አብዲ ያዩ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ የተተገበሩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተደረጉ ሁለንተናዊ ድጋፎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች የወተት ላሞች እርባታ በዘመናዊ መንገድ መተግበሩና ምርጥ የእርባታ ዶሮዎች ለአርሶ አደሩ መሰራጨታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በዓሣ እርባታ ዘርፍ ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ የዓሣ ጫጩቶች ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ ተሰራጭተው ወደ እርባታ ኩሬዎች መግባታቸውን ገልጸዋል። የአርሶ አደሩን የሰብል ልማት ውጤታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና በቅርበት የገበያ ትስስር የሚያገኝበት ምቹ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል። ይህም የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደጉ ባለፈ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ትልቅ እገዛ ማድረጉን አስረድተዋል። በክልሉ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ሰፊ ጥረትም በበጀት ዓመቱ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል። የክልሉን ሁለንተናዊ ልማት በራስ አቅም ለመሸፈን በተደረገው የውስጥ ገቢ ማሰባሰብ ጥረትም የተሻለ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት 13 ሺህ 147 አዳዲስ አልሚ ባለሀብቶችን መሳብ ተችሏል ነው ያሉት። ይህንን ተግባር ይበልጥ ለማስቀጠልም አርሶ አደሮችና የአገር ውስጥ አንቀሳቃሾችን በመደገፍ፣ ሀብት አፍርተው ከእርሻ ሥራ ወደ ኢንቨስትመንት ባለቤትነት እንዲሻገሩ መደረጉን ጠቅሰዋል። የሕዝቡን የማኅበራዊ አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረትም በትምህርት፣ በጤና፣ በንጹህ መጠጥ ውኃና በመንገድ ልማት ዘርፎች እጅግ የተሻለና አበረታች አፈጻጸም መመዝገቡን አንስተዋል። በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ያለው ይህ የመንግሥትና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቀጣዮቹ ቀናትም እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ተወያዩ
Jul 13, 2026 68
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከቤኒን ፕሬዝዳንት ጋር በወል ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ እድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት አለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በክልሉ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል
Jul 13, 2026 61
ሳውላ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ "ትምህርት ለልጄ" በሚል መሪ ሃሳብ የ2018 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ንቅናቄ መድረክ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፣ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ግብአት በማሟላት ተማሪዎች ብቁ ሆነው እንዲወጡ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል። የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተደረገ ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸው፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ምቹ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልጸው፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ ትምህርት በመስጠት የትምህርት ውጤት ማሻሻል ለነገ የሚባል አይደለም ብለዋል። የዛሬው የ"ትምህርት ለልጄ" ንቅናቄም ተማሪዎች የክረምት ወራትን ካላስፈላጊ ቦታ ይልቅ ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያሳልፉ ስለሚያግዝ ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ቢሮው ትውልድ የመቅረጽ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሁሉም አካባቢዎች በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በየአመቱ የሚካሄደው የትምህርት ንቅናቄ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የተስተዋለውን የውጤት ማሽቆልቆልና የጥራት ችግር ለመፍታት በተሰራው ሥራ የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል በቀጣይም በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣት መምህራንን እና የማህበረሰቡን አቅም በመጠቀም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና ግብዓት ለማሟላት በቅንጅት እንደሚሰራም አስታውቀዋል። በዞኑ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን በብቃት ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት መረጋገጡን አንስተው፣ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ተወያዩ
Jul 13, 2026 68
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከቤኒን ፕሬዝዳንት ጋር በወል ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ እድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት አለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
Jul 13, 2026 220
አዳማ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በዚህ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንና የነበሩ ድክመቶችን በመመርመር፣ የ2019 የሥራ ዕቅድ አቅጣጫን የሚያመላክት ውሳኔ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
Jul 13, 2026 238
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ አቀባበል አድርገዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል። በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
አዲስ አበባ ከተማ የወል ትርክት ግንባታን በማጎልበት የሰላምና የልማት ማዕከል እየሆነች ነው
Jul 12, 2026 1077
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦አዲስ አበባ ከተማ አሰባሳቢና የወል ትርክት ግንባታን በማጎልበት የሰላምና የልማት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሪፖርታቸው፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋታለን ብለን በገባነው ቃል መሠረት ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ መሠረታዊና ሥር ነቀል ለውጦችን ማከናወናን ችለናል። በተጨማሪም ሥር የሰደዱ ኋላቀር አስተሳሰቦችንና ችግሮችን በጽናት በመጋፈጥ፣ አዲስ አበባን ከማይጠቅም የመሳሳብና የመገፋፋት ፖለቲካ የተላቀቀች የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ለአብነትም የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመገንባት አሰባሳቢና የወል ትርክት ለማስረጽ የሚያስችሉ መሠረቶች መገንባታቸውን ጠቅሰዋል። በአዲስ አበባ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ ውብ፣ አረንጓዴና ጽዱ በመሆን ለኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን የሚያስችሉ መሠረቶችን እየጣለች እንደምትገኝ አስረድተዋል። የመዲናዋን ጎስቋላ ገጽታ በመቀየር ከተማዋ ከአፍሪካ አስር ጽዱ ከተሞች አንዷ በመሆን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቷን አንስተዋል። የመዲናዋ የአረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ ማለቱም ሌላው የመሠረታዊ ለውጥ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። አዲስ አበባ መንገዶቿ ሰፊ፣ የነበረችበት የጨለማ ገጽታም ወደ ብርሃን መቀየሩን የገለጹት ከንቲባዋ፤ ይህም ከተማዋ በርካታ ኮንፈረንሶችንና ጎብኝዎችን የማስተናገድ ብቃቷን እንዳሳደገው አብራርተዋል። የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷም ይበልጥ ጎልብቶ፣ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካውያን ዋና ከተማችን ብለው የሚጠሯትና የሁላችንም ኩራት መሆኗን ገልጸዋል።
ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የልዩነቶቻችን ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች በምክክር ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበት ይሆናል-ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Jul 12, 2026 821
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ የልዩነቶች ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች በሰለጠነ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበት እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ይህን የገለጹት ኮሚሽኑ ያዘጋጀውና "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ የሩጫ ውድድር ላይ ነው። በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዳሉት፤ ዋናውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ ተጠናቋል። ለዚህም በዋናው ምክክር ላይ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች ከሁሉም ወረዳዎች፣ ክልሎች እንዲሁም ከሀገር ውጭ ጭምር አዲስ አበባ መግባታቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። በዋናው የምክክር ጉባኤ በዜጎች መካከል የልዩነት መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች መክረውና ዘክረው ዘላቂ መፍትሔ በሚሰጡ ሐሳቦች ላይ መግባባት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል። ምክክሩ ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ ተቋማት፣ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት አካላት፣ ለሲቪል ማኅበራትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ በጉባኤው ላይ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ይመከርባቸዋል። የዋናው ጉባኤ የምክክር ዐበይት አጀንዳዎች የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች (የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይን ጨምሮ)፣ ሙስና፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ የሚሉት ናቸው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
Jul 12, 2026 1090
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል። "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅትም የውድድሩ ተሳታፊዎች ከሩጫው አስቀድሞ በተዘጋጀው የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዋናው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሕዝብ ወኪሎችም ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው። በዚህ ዋና የምክክር ጉባኤ ላይ፡ • የሀገር ግንባታ፣ • የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ • የፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ • የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ • የሃይማኖት ጉዳዮች፣ • የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች (የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይን ጨምሮ)፣ • እንዲሁም ሙስና፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታን ያካተቱ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ላይ የሕዝብ ወኪሎች የሚመክሩባቸው ይሆናል። በመስቀል አደባባይ በተሰናዳው በዚህ የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መርሃ ግብር ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራው አንደሞ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዲሁም የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።
ምክክር ኮሚሽኑ የለያቸው አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው
Jul 11, 2026 1466
ቦንጋ ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በምክክር ኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ መሆናቸውን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። በጉዳዩ ላይ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መምህር ፍቅረየሱስ ሀብተጊዮርጊስ፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ጉባኤው በሚመች መልኩ አደራጅቶ ያቀረባቸው ስምንቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች እጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህ አጀንዳዎች ላለመግባባት መንስኤ በመሆን ልዩነትን ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት፣ ሀገራዊ መግባባትንና አንድነትን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ወንድሙ ካኪሎ በበኩላቸው፤ አጀንዳዎቹ አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት ሀገራዊ እሳቤዎችን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። አጀንዳዎቹ የግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የሚከፍቱ መሆናቸውንም አክለዋል። ለሀገራዊ ጉባኤው የቀረቡ አጀንዳዎች ስር ሰደው የቆዩ ችግሮችን ከመሠረቱ ለመፍታት የሚያስችሉና ሲያጋጥሙ ለነበሩ ችግሮች ውይይትን አማራጭ በማድረግ መፍትሄ ለመሻት አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ አዳሙ እሼቱ ናቸው።
ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው
Jul 11, 2026 1187
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡ ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት የሀገር ሰላምና አንድነትን ያጸናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ወደ ተግባራዊ ውይይት ለመግባት መወሰኗ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ አካሄድ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረውም አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ ከወረዳ ጀምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት ስምንት ወሳኝና አንኳር አጀንዳዎችን መለየቱ ለምክክሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ጠቁመዋል። እነዚህ የተመረጡ አጀንዳዎች ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ሀገረ መንግስት ግንባታና ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸውም አክለዋል። የምክክር ሂደቱ በሕግና በአዋጅ በተቋቋመ ኮሚሽን የሚመራና ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ በመሆኑ፤ አፍሪካና የተቀረው ዓለም ተሞክሮ ሊወስድበት የሚችል አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ምሁሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ ስልጡን አካሄድ ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ በዓለም መድረክ የሚያሳዩበት እንደሚሆንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አመራር ትምህርት ክፍል መምህር ኡጁሉ ኡኮክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። ምክክሩ ዜጎች በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አለመግባባቶች እንዲቀረፉና በጋራ ልማት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ዕድል እንደሚፈጥርም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የልማታዊ ተግባቦትና የሚዲያ ጥናት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዘለቀ ተሾመ (ዶ/ር)፤ ሀገራዊ ምክክሩ አንድነቷ የተጠናከረና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚጣል ታሪካዊ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ስኬታማነትም እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን ንቁ ተሳትፎና ጥረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
ፖለቲካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ተወያዩ
Jul 13, 2026 68
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከቤኒን ፕሬዝዳንት ጋር በወል ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ እድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት አለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
Jul 13, 2026 220
አዳማ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በዚህ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንና የነበሩ ድክመቶችን በመመርመር፣ የ2019 የሥራ ዕቅድ አቅጣጫን የሚያመላክት ውሳኔ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
Jul 13, 2026 238
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ አቀባበል አድርገዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል። በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
አዲስ አበባ ከተማ የወል ትርክት ግንባታን በማጎልበት የሰላምና የልማት ማዕከል እየሆነች ነው
Jul 12, 2026 1077
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦አዲስ አበባ ከተማ አሰባሳቢና የወል ትርክት ግንባታን በማጎልበት የሰላምና የልማት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሪፖርታቸው፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እናደርጋታለን ብለን በገባነው ቃል መሠረት ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ መሠረታዊና ሥር ነቀል ለውጦችን ማከናወናን ችለናል። በተጨማሪም ሥር የሰደዱ ኋላቀር አስተሳሰቦችንና ችግሮችን በጽናት በመጋፈጥ፣ አዲስ አበባን ከማይጠቅም የመሳሳብና የመገፋፋት ፖለቲካ የተላቀቀች የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። ለአብነትም የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመገንባት አሰባሳቢና የወል ትርክት ለማስረጽ የሚያስችሉ መሠረቶች መገንባታቸውን ጠቅሰዋል። በአዲስ አበባ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ ውብ፣ አረንጓዴና ጽዱ በመሆን ለኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን የሚያስችሉ መሠረቶችን እየጣለች እንደምትገኝ አስረድተዋል። የመዲናዋን ጎስቋላ ገጽታ በመቀየር ከተማዋ ከአፍሪካ አስር ጽዱ ከተሞች አንዷ በመሆን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቷን አንስተዋል። የመዲናዋ የአረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ ማለቱም ሌላው የመሠረታዊ ለውጥ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። አዲስ አበባ መንገዶቿ ሰፊ፣ የነበረችበት የጨለማ ገጽታም ወደ ብርሃን መቀየሩን የገለጹት ከንቲባዋ፤ ይህም ከተማዋ በርካታ ኮንፈረንሶችንና ጎብኝዎችን የማስተናገድ ብቃቷን እንዳሳደገው አብራርተዋል። የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷም ይበልጥ ጎልብቶ፣ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካውያን ዋና ከተማችን ብለው የሚጠሯትና የሁላችንም ኩራት መሆኗን ገልጸዋል።
ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የልዩነቶቻችን ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች በምክክር ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበት ይሆናል-ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Jul 12, 2026 821
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ የልዩነቶች ምንጭ የሆኑ ጉዳዮች በሰለጠነ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙበት እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ። ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ይህን የገለጹት ኮሚሽኑ ያዘጋጀውና "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ የሩጫ ውድድር ላይ ነው። በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዳሉት፤ ዋናውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ ተጠናቋል። ለዚህም በዋናው ምክክር ላይ የሚሳተፉ ተመካካሪዎች ከሁሉም ወረዳዎች፣ ክልሎች እንዲሁም ከሀገር ውጭ ጭምር አዲስ አበባ መግባታቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። በዋናው የምክክር ጉባኤ በዜጎች መካከል የልዩነት መንስኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች መክረውና ዘክረው ዘላቂ መፍትሔ በሚሰጡ ሐሳቦች ላይ መግባባት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል። ምክክሩ ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጸጥታ ተቋማት፣ በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት አካላት፣ ለሲቪል ማኅበራትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ በጉባኤው ላይ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ይመከርባቸዋል። የዋናው ጉባኤ የምክክር ዐበይት አጀንዳዎች የሀገር ግንባታ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች (የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይን ጨምሮ)፣ ሙስና፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ የሚሉት ናቸው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
Jul 12, 2026 1090
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል። "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅትም የውድድሩ ተሳታፊዎች ከሩጫው አስቀድሞ በተዘጋጀው የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዋናው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሕዝብ ወኪሎችም ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው። በዚህ ዋና የምክክር ጉባኤ ላይ፡ • የሀገር ግንባታ፣ • የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ • የፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ • የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ • የሃይማኖት ጉዳዮች፣ • የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች (የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይን ጨምሮ)፣ • እንዲሁም ሙስና፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታን ያካተቱ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ላይ የሕዝብ ወኪሎች የሚመክሩባቸው ይሆናል። በመስቀል አደባባይ በተሰናዳው በዚህ የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መርሃ ግብር ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራው አንደሞ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዲሁም የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።
ምክክር ኮሚሽኑ የለያቸው አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው
Jul 11, 2026 1466
ቦንጋ ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦በምክክር ኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ መሆናቸውን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። በጉዳዩ ላይ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በኮሚሽኑ የተለዩት አጀንዳዎች አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል የሚወስኑ ናቸው። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መምህር ፍቅረየሱስ ሀብተጊዮርጊስ፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ጉባኤው በሚመች መልኩ አደራጅቶ ያቀረባቸው ስምንቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች እጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህ አጀንዳዎች ላለመግባባት መንስኤ በመሆን ልዩነትን ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት፣ ሀገራዊ መግባባትንና አንድነትን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ወንድሙ ካኪሎ በበኩላቸው፤ አጀንዳዎቹ አለመግባባቶችን በዘላቂነት በመፍታት ሀገራዊ እሳቤዎችን የሚያጎለብቱ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። አጀንዳዎቹ የግጭት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የሚከፍቱ መሆናቸውንም አክለዋል። ለሀገራዊ ጉባኤው የቀረቡ አጀንዳዎች ስር ሰደው የቆዩ ችግሮችን ከመሠረቱ ለመፍታት የሚያስችሉና ሲያጋጥሙ ለነበሩ ችግሮች ውይይትን አማራጭ በማድረግ መፍትሄ ለመሻት አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ አቶ አዳሙ እሼቱ ናቸው።
ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው
Jul 11, 2026 1187
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ስር የሰደዱ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሀገራዊ መግባባት ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡ ለዓመታት ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ታሪካዊ ጉባኤ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚጀመረው በዚህ ወሳኝ ጉባኤ ላይ ለመመካከር ከመላው ሀገሪቱ የተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደውን ዋናው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት አስመልክቶ ለተመካካሪዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ የቅድመ ምክክር ማብራሪያና ገለፃ አድርጓል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በውይይት በመፍታት የሀገር ሰላምና አንድነትን ያጸናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን አቋቁማ ወደ ተግባራዊ ውይይት ለመግባት መወሰኗ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ አካሄድ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረውም አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ ከወረዳ ጀምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት ስምንት ወሳኝና አንኳር አጀንዳዎችን መለየቱ ለምክክሩ ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ጠቁመዋል። እነዚህ የተመረጡ አጀንዳዎች ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ሀገረ መንግስት ግንባታና ልማት ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸውም አክለዋል። የምክክር ሂደቱ በሕግና በአዋጅ በተቋቋመ ኮሚሽን የሚመራና ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ በመሆኑ፤ አፍሪካና የተቀረው ዓለም ተሞክሮ ሊወስድበት የሚችል አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ምሁሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ ስልጡን አካሄድ ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ በዓለም መድረክ የሚያሳዩበት እንደሚሆንም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አመራር ትምህርት ክፍል መምህር ኡጁሉ ኡኮክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አመልክተዋል። ምክክሩ ዜጎች በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አለመግባባቶች እንዲቀረፉና በጋራ ልማት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ዕድል እንደሚፈጥርም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የልማታዊ ተግባቦትና የሚዲያ ጥናት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዘለቀ ተሾመ (ዶ/ር)፤ ሀገራዊ ምክክሩ አንድነቷ የተጠናከረና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚጣል ታሪካዊ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል። ለዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ስኬታማነትም እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን ንቁ ተሳትፎና ጥረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
ማህበራዊ
በክልሉ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል
Jul 13, 2026 61
ሳውላ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል የመማር ማስተማር ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። የክልሉ ትምህርት ቢሮ "ትምህርት ለልጄ" በሚል መሪ ሃሳብ የ2018 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ንቅናቄ መድረክ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፣ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ግብአት በማሟላት ተማሪዎች ብቁ ሆነው እንዲወጡ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል። የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተደረገ ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸው፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና ምቹ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ይጠናከራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልጸው፣ ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ ትምህርት በመስጠት የትምህርት ውጤት ማሻሻል ለነገ የሚባል አይደለም ብለዋል። የዛሬው የ"ትምህርት ለልጄ" ንቅናቄም ተማሪዎች የክረምት ወራትን ካላስፈላጊ ቦታ ይልቅ ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያሳልፉ ስለሚያግዝ ባለድርሻ አካላት ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ቢሮው ትውልድ የመቅረጽ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሁሉም አካባቢዎች በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በየአመቱ የሚካሄደው የትምህርት ንቅናቄ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የተስተዋለውን የውጤት ማሽቆልቆልና የጥራት ችግር ለመፍታት በተሰራው ሥራ የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠል በቀጣይም በትኩረት ይሰራል ብለዋል። በክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣት መምህራንን እና የማህበረሰቡን አቅም በመጠቀም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና ግብዓት ለማሟላት በቅንጅት እንደሚሰራም አስታውቀዋል። በዞኑ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን በብቃት ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ናቸው። ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት መረጋገጡን አንስተው፣ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በሐረሪ ክልል በትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል
Jul 13, 2026 57
ሐረር፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወነ የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር ውጤታማ ስራ መሰራቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ በትምህርት ዘርፍ በተሰሩ ሥራዎች ከፍተኛ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ትምህርት ከታች መሠረት ካልተሠራለት የላይኛው ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለመዋዕለ ሕፃናት ማስፋፊያ በተሰጠው ልዩ ትኩረት 35 ሺህ መዋዕለ ሕፃናትን መገንባት መቻሉን ጠቅሰዋል። ጉዳዩን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አርሰላን አብዲ፤ በሐረሪ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወነ የትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል። በዚህም በሕዝብ ንቅናቄና በትምህርት ባለሙያዎች የተቀናጀ ሥራ የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ፣ ተሳትፎን ከማጎልበትና የተማሪዎችን ውጤት ከማሻሻል አኳያ የተሻለ ሥራ መሰራቱን ጠቅሰዋል። በተለይም በክልሉ በበጀት ዓመቱ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ልማት ላይ በተከናወነው ሥራ በሁሉም የከተማና የገጠር አካባቢዎች በሚገኙ 69 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የቅድመ መደበኛ ትምህርት መስጠት መቻሉን ገልጸዋል። በትምህርት ቤቶቹም የትምህርት ማቋረጥ እንዳይከሰት ለማድረግ፣ በሁሉም ቅድመ መደበኛ እና ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም መከናወኑን አስታውቀዋል። በ2019 የትምህርት ዘመን ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲከታተሉ ዕቅድ መያዙን ጠቁመው፤ ለዚህም በክልሉ ገጠር ወረዳዎች 6 አዳዲስ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በክልሉ በ“ትምህርት ለትውልድ” መርሃ ግብር የሚከናወኑ ሥራዎች የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል ባለፈ፣ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ በማስቻል ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። ባለፈው በጀት ዓመት በገንዘብ፣ በዓይነትና በዕውቀት 38 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሥራ መሰራቱን ገልጸው፤ በዘንድሮው የክረምት ወቅት ደግሞ ከ 42 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል። በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አረጋግጠዋል።
ዜጎችን ከሰቀቀን ኑሮ ወደ አዲስ ህይወት እያመጣ ያለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት
Jul 13, 2026 96
ሰቆጣ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በጎነት የራስን፣ የቤተሰብንና የማኅበረሰብን አቅምና ዕውቀት አስተባብሮ በችግር ውስጥ የሚኖሩ ወገኖችን በመደገፍ ወደ አዲስ ሕይወት ማሸጋገር ነው። ማኅበረሰቡ ለዘመናት በአካባቢው የሚኖሩ አቅመ ደካሞችን በማብላት፣ በማጠጣትና የፈረሱ ቤቶቻቸውን በማደስ ተደስተው እንዲኖሩ የሚያደርገውን ይህንን መልካም እሴት በትውልድ ቅብብሎሽ አጠናክሮ ያስቀጥልበታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይህ ልዩ ትኩረት የተሰጠው የበጎነት ተግባር በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ ሁሉም ዜጋ የሚሳተፍበትና ወገኖችን ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ ንቅናቄ ሆኗል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአስ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ ብርሃኔ ወንድማገኝ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑና ቤት ተከራይቶ ለመኖር አቅም በማጣታቸው፣ ከጎዳና ሕይወት ባልተናነሰ ሁኔታ በፈራረሰ ጎጆ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ይናገራሉ። "መኖሪያ ቤቴ ክረምት በመጣ ቁጥር ስለሚያፈስ ከሁለት ልጆቼ ጋር በዝናብ፣ በውርጭና በቁር እየተሰቃየን እናሳልፍ ነበር፤ በተለይ ዝናብ ሲዘንብ ወደ አንድ ጥግ ተሰብስበን በመጠለል ነበር የምናሳልፈው" ይላሉ። ችግሩን የተገነዘቡት የከተማዋ በጎ ፈቃደኞች ለአቅመ ደካሞች አዲስ መኖሪያ ቤት ገንብተው ሲያስረክቡ የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። ወይዘሮ ብርሃኔ አሁን ላይ ክረምት ቢመጣ ቢሄድ ምንም ዓይነት ሰቀቀን እንደሌለባቸውና ከነቤተሰቦቻቸው በሰላም ተኝተው፣ ጠዋት በደስታ በመንቃት ወደ ዕለት ተግባራቸው እንደሚሰማሩ ተናግረዋል። የዚሁ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ አድና ደሴ በበኩላቸው፤ የአይን ብርሃናቸውን በተፈጥሮ በማጣታቸው ተንቀሳቅሰው ለመስራትና ሀብት ለማፍራት ባለመቻላቸው ለተደራራቢ ችግሮች ተጋልጠው መኖራቸውን አውስተዋል። በደሳሳ ጎጆዋቸው ከልጆቻቸው ጋር በመኖር በክረምት በዝናብ፣ በውርጭና በቁር፤ በበጋ ደግሞ በፀሐይና በነፋስ ይሰቃዩ እንደነበር አስታውሰው፣ በዘንድሮው ዓመት በበጎ ፈቃደኞች በተደረገላቸው ድጋፍ አሁን ላይ የተሻለ ሕይወት መምራት እንደቻሉ ገልጸዋል። በአስ ከተማ በበጎ ፈቃድ ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት ሀብቱ ሰለሞን፤ የከተማዋን ነዋሪ በማስተባበር በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን አኗኗር ለመቀየር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጿል። በከተማዋ የሚገኙ በጎ ፈቃደኞች ባለፉት ዓመታት የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤቶች በመገንባትና በማደስ የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ ማድረጋቸውንም አመልክቷል። በአስተዳደሩ የጋዝጊብላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው ደሳለኝ እንዳሉት፤ በወረዳው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር 14 አዳዲስ ቤቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች ለማስረከብ ተችሏል። ከተገነቡት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሦስቱ በበጋው ወቅት በተካሄደው የበጎ ፈቃድ ሥራ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ለአቅመ ደካሞች ማስተላለፍ መቻሉን ገልጸዋል። በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎትና የወጣቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ ሙሉጌታ ስኳር እንዳሉት፤ በዘንድሮው የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 197 ሺህ 250 ወጣቶች ይሳተፋሉ። በዚህ መርሐግብር 584 ሺህ 860 የሚሆኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በትጋት እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Jul 13, 2026 110
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ) ፦ በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተግባራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት በሰጡት መግለጫ መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። ጽሕፈት ቤቱ በክልሉ በ2018 የበጀት ዓመት ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናወን መቻሉንም ገልጸዋል። የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጠናከር እንዲሁሞ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የተጠናከረ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል። የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችም በትኩረት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማህበራዊ ሚዲያና በአካባቢው የሚገኙ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል። አቶ ሔኖክ አክለውም በተለይም በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማጎልበት ያስቻሉ ስራዎችም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን ጠቁመዋል። የጋራ መግባባት በመፍጠር ረገድም የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት ስለመደረጉም አስረድተዋል። በአዲሱ የበጀት አመትም ጽሕፈት ቤቱ የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰራ ነው ኃላፊው የተናገሩት።
ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማት የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤት እያስገኘ ነው
Jul 13, 2026 21
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማት የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሻሻል ውጤት እያስገኘ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት የአህጉር-አቀፍ የእንስሳት ሃብት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ፎረሙ በአፍሪካ የእንስሳት ሃብት ልማትን በማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል፣ አርብቶ አደሮች የተሻለ ገበያ እንዲያገኙና የሀገራትን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የፖሊሲ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብት ልማትን በማሳደግ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ እየሰራችበት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም አርሶና አርብቶ አደሮች የሚያጋጥሟቸውን የውሃና የመኖ እጥረት በዘላቂነት የሚቀርፉ እንዲሁም የእንስሳት ሕክምና መስጫ ተቋማትን የማስፋፋት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከአርብቶ አደሮች ጋር የሚሰሩ ተቋማትን፣ የእንስሳት ገበያ ማእከላትን ለአርብቶ አደር አካባቢዎች ተደራሸነት የማጠናከር ስራዎችንም እየተሰራበት እንደሆነም አብራርተዋል። በአፍሪካ ህብረት የእንስሳት ሀብት ቢሮ ዳይሬክተር ሁያም ሳሊህ (ዶ/ር) አፍሪካ የዓለምን የእንስሳት ሃብት ከፍተኛ ድርሻ ብትይዝም፣ ከእሴቱ ግን የምታገኘው በጣም አነስተኛ ነው ብለዋል። በቀጣይም የአህጉሪቷን ግዙፍ የእንስሳት ሃብት በማልማት የአርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሻሻል በሁሉም ዘርፍ የኢንቨስተመንት አማራጮችን ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ የተተገበሩ አሰራሮች ውጤት አስገኝተዋል
Jul 13, 2026 89
አዳማ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ በግብርና ዘርፍ የተተገበሩ አሰራሮች ውጤት ማስገኘታቸውን የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዲ ያዩ (ዶ/ር) ገለፁ። የክልሉ የመንግሥትና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዘርፍ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል። በግምገማው መድረክ ላይ ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽነር አብዲ ያዩ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ የተተገበሩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተደረጉ ሁለንተናዊ ድጋፎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች የወተት ላሞች እርባታ በዘመናዊ መንገድ መተግበሩና ምርጥ የእርባታ ዶሮዎች ለአርሶ አደሩ መሰራጨታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም በዓሣ እርባታ ዘርፍ ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ የዓሣ ጫጩቶች ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ ተሰራጭተው ወደ እርባታ ኩሬዎች መግባታቸውን ገልጸዋል። የአርሶ አደሩን የሰብል ልማት ውጤታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና በቅርበት የገበያ ትስስር የሚያገኝበት ምቹ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል። ይህም የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደጉ ባለፈ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ትልቅ እገዛ ማድረጉን አስረድተዋል። በክልሉ የሚታየውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ሰፊ ጥረትም በበጀት ዓመቱ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል። የክልሉን ሁለንተናዊ ልማት በራስ አቅም ለመሸፈን በተደረገው የውስጥ ገቢ ማሰባሰብ ጥረትም የተሻለ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በተደረገው የተቀናጀ ጥረት 13 ሺህ 147 አዳዲስ አልሚ ባለሀብቶችን መሳብ ተችሏል ነው ያሉት። ይህንን ተግባር ይበልጥ ለማስቀጠልም አርሶ አደሮችና የአገር ውስጥ አንቀሳቃሾችን በመደገፍ፣ ሀብት አፍርተው ከእርሻ ሥራ ወደ ኢንቨስትመንት ባለቤትነት እንዲሻገሩ መደረጉን ጠቅሰዋል። የሕዝቡን የማኅበራዊ አገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረትም በትምህርት፣ በጤና፣ በንጹህ መጠጥ ውኃና በመንገድ ልማት ዘርፎች እጅግ የተሻለና አበረታች አፈጻጸም መመዝገቡን አንስተዋል። በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ያለው ይህ የመንግሥትና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቀጣዮቹ ቀናትም እንደሚቀጥል ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል
Jul 13, 2026 99
ባህር ዳር ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ስራ መከናወኑን የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ። በክልሉ ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ ፀጋዎችን በመለየት ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ አቅማቸውን የማሳደግ ስራ እየተሰራ ይገኛል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዳርጋቸው ጎፋ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ለመፍጠር ተችሏል። በዚሁ ወቅት የስራ እድል ፈጠራዉን ስኬታማ ለማድረግ በቅንጅት የሚመራ ግብረ ኃይል በማቋቋም እና አጋር ተቋማትን በማቀናጀት ሰፊ ስራ መከናወኑን ጠቅሰዋል። በዚህም ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል። ከተፈጠረው የስራ እድል ውስጥም 75 በመቶ በቋሚነት የተፈጠረ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ነው የተናገሩት። የስራ ዕድሉ በመስኖ እና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በእንስሳት እርባታና ማድለብ፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም በእንጨትና ብረታብረት ስራዎች የተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። በዚሁ ወቅት በስራ እድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥማቸው ለማድረግ በተከናወኑት ተግባራትም 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት እንዲያገኙ ተደርጓል ነው ያሉት። በተጨማሪም 21 ሺህ 400 ሄክታር የሚጠጋ መሬትና ከ 2 ሺህ 200 የሚበልጡ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶች ተገንብተው የስራ እድል ለተፈጠረላቸው ዜጎች ማስተላለፍ መቻሉን ገልፀዋል። ኢንተርፕራይዞቹ የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተከናወኑት ተግባራትም የ8 ነጥብ 3 ቢሊዮን የሀገር ውስጥ፤ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ሃገራት የገበያ ትስስር መፈጠሩንም አብራርተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት ያስቻሉ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል
Jul 13, 2026 177
አዳማ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች መፍታት ያስቻሉ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። የኦሮሚያ ክልል የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ ሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። በዚሁ ወቅት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በክልሉ ሕዝብ ሲነሱ የነበሩ የልማት ጥያቄዎች በተጨባጭ ምላሽ አግኝተዋል ብለዋል። በተለይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች ስኬታማ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ በዚህ ሂደት አመራሩ የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እንዲሳለጡ አድርጓል ነው ያሉት። የመንግሥትን በጀት እና የሕዝብ ተሳትፎን በማቀናጀት የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ የተደረገው ርብርብ ውጤታማ እንደነበርም አንስተዋል። ይህም በመሆኑ የክልሉ አመራር የተገኙ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ስልቶችን መፈተሽና የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ቀጣይ ሥራዎች መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል። በቀጣዩ በጀት ዓመትም በክልሉ ካለው እምቅ አቅምና የልማት ፍላጎት ጋር የሚጣጣም የተለጠጠ ዕቅድ በማዘጋጀት፣ ያሉትን አማራጮች አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በተለይም የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በቁጠባ ላይ በትኩረት መሥራት የሚገባ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳለጥ በዞኖች፣ በወረዳዎችና በከተሞች ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፈተሽና ሥራ ላይ ማዋል እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ክልል ያለው የአመራርነት አቅምና ብቃት በግምገማው በመፈተሽ በተገኙ ውስን ድሎች ሳይዘናጉ አሁንም በሙሉ አቅም መረባረብ ይገባልም ብለዋል። በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው፣ በበጀት ዓመቱ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሪፎርሞችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ተስፋ ሰጪ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ 21 ሺህ የሚጠጉ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲበቁ መደረጉን አንስተው፤ ይህም የዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማ ቢያደርገውም፣ አፈጻጸሙ በሁሉም ዞኖችና ከተሞች ወጥነት ያለው አለመሆኑን ጠቅሰዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ለዴሞክራሲ ያለውን ፅኑ ፍላጎት ያሳየበትና ትልቅ የፖለቲካ ድል የተመዘገበበት መሆኑን የጠቀሱት አመራሮቹ፤ በተያዘው አዲሱ የበጀት ዓመት አመራሩ በሙሉ አቅሙና ቁርጠኝነት መረባረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የአፍሪካን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የሚያሳልጥ የዲጂታል አቅም መገንባት ያስፈልጋል
Jul 13, 2026 73
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት የሚያሳልጥ የዲጂታል ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ገለጸ። የአፍሪካ የትምህርት ፈጠራ ኤክስፖ 2026 በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው። ''የትምህርት ዲጂታል ሽግግርና የፈጠራ መፍትሔዎችን ማሳደግ'' በሚል መሪ ሃሳብ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ኤክስፖ የፈጠራ ባለቤቶች፣ የጥናትና ምርምር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የትምህርት፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ጋስፓርድ ባንያን ክምቢና በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በአፍሪካ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ብቁ የሰው ሃይል መገንባት ያስፈልጋል። ለዚህም በአፍሪካ ሕብረት በተገባው የፖለቲካ ቁርጠኝነት መሰረት አፍሪካዊያን በተለወጠ ዓለም ውስጥ የትውልዱን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካን ትምህርት ወደ ዲጂታል ማሸጋገር ወቅታዊ እና የሀገራትን ትኩረት የሚፈልግ ነው ብለዋል። በአፍሪካ አካታች የዲጂታል ትምህርት ስርአት በመዘርጋት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ፣ የዲጂታል የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት ላይም ይበልጥ መስራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። ትምህርትን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቃኘ ማድረግ እና የአስተማሪዎችን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ትምህርትን ለማሸጋገር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አክለዋል። የጥናትና ምርምር ተቋማትን አቅም ማሳደግም የሀገራት የትኩረት ማዕከል ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የአፍሪካ ህብረትም በአህጉሪቱ ትምህርትን ለማዘመን የሚሰሩ ተግባራትን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።
በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኘን ነው
Jul 12, 2026 470
ሚዛን አማን፣ ሐምሌ 5/2018 (ኢዜአ)-:-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ተገልጋዮች ገለጹ፡፡ በክልሉ በሁለተኛ ዙር የተገነቡ አምስት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በቅርቡ ወደሥራ የገቡ ሲሆን በሦስተኛ ዙርም 15 አዳዲስ ማዕከላት ለመገንባት መታቀዱ ተመላክቷል። በክልሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሚዛን አማን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋዮች እንደገለጹት በማዕከሉ ቀልጣፋ፣ ከብልሹ አሰራር የጸዳና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እያገኙ ነው፡፡ ከተገልጋዮች መካከል አቶ ከረጋ ወልደማርያም በማዕከሉ የባንክ እና ዲጂታል መታወቂያን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መስተንግዶ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። የጤና ሙያ ፍቃድ ለማሳደስ ወደማዕከሉ እንደመጡ የገለጹት ወይዘሮ ቤዛዊት ጠና በበኩላቸው በማዕከሉ ባገኙት ቀልጣፋ መስተንግዶ በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ማዕከሉ ከመከፈቱ በፊት የጤና ሙያ ፍቃዳቸውን ለማደስ ረጅም ኪሎ ሜትር ይጓዙ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን በአቅራቢያቸው ማግኘት መቻላቸው ትልቅ ለውጥ እንደሆነና ገንዘብና ወጪንም እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል። መንግስት ለሕዝብ የቀረበና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰራርን ከማዘመን ባለፈ የጊዜና ጉልበት ብክነት ማስቀረቱን የገለጹት ደግሞ አቶ ስማቸው መኮንን እና ወጣት ሀፊዝ ሁሴን ናቸው። ዲጂታል መታወቂያ ለማውጣት በማዕከሉ መገኘታቸውን ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም ሲገጥማቸው የነበረ የቀጠሮ ምልልስና ሌሎች ችግሮች ተፈተው ፈጣንና ከሙስና የጸዳ አገልግሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመዲን አወል በበኩላቸው መንግሥት የሕዝብ አገልግሎትን ከእንግልትና አድሏዊ አሠራር ነጻ ለማድረግ የዘረጋው ዘመናዊ አሠራር ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከ35 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች አገልግሎት መስጠቱን ጠቅሰው የተገልጋይ ቁጥርና እርካታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል። በክልሉ የዲጂታል አሠራሩን በማስፋፋት ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በማለም በሁለተኛ ዙር 5 ተጨማሪ ማዕከላት ተገንብተው ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በማዕከላቱ እየተገኘ ያለውን ውጤት ለማስቀጠል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በሦስተኛ ዙር 15 አዳዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በተለያዩ የክልሉ ከተሞች በቅርቡ እንደሚገነቡም አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የአሰራርና የቴክኖሎጂ አቅም ገንብታለች
Jul 11, 2026 881
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የህግ፣ የአሰራርና የቴክኖሎጂ አቅም መገንባቷን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ። ከትናንት ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፉ የፓርላማ የመረጃ ደኅንነት ፎረም ተጠናቋል። በመድረኩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም፣ የሳይበር ደኅንነት፣ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መሰል ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ በስፋት ምክክር ተደርጎበታል። በዚህ ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ እንዳሉት፤ የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ድንበር የለሽ በመሆናቸው ስጋቶችን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ህጎችን የማጣጣምና የቅንጅት ስራ ወሳኝ ነው። ሃገራት የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅና የሚቃጡ ጥቃቶችን ለመከላከል ተናባቢ ህጎች ሊኖራቸው እንደሚገባ አንስተው፣ ኢትዮጵያም በዚህ አግባብ እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል የህግ፣ አሰራርና ቴክኖሎጂ አቅምን ገንብታለች ብለዋል። ፎረሙ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ መድረኮችን ለማዘጋጀት ያላትን አቅም ለማሳየትና ለገጽታ ግንባታ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑንም ተናግረዋል። የናይጄሪያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፎረሙ አባል አግበዲ ዬቲዬኔ ፍሬድሪክ (ዶ/ር) ፤ በኢትዮጵያ በተዘጋጀው ፎረም መሳተፋቸው ከተለያዩ ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። በህንድ በሚገኘው የካሊንጋ የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ቫሩን ሱትራ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ፎረሙን ሙያዊ በሆነ አግባብ መምራቷ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
Jul 11, 2026 627
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ኤክስፖ፤ “በትምህርት ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠንና ለአፍሪካ የክህሎት ዘመን የአዳዲስ መፍትሔዎችን ተደራሽነት ማስፋት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል። ይህ አህጉራዊ ኤክስፖ በአፍሪካ የትምህርትና ክህሎት ሥርዓት ውስጥ ያሉ የጥራት፣ የተደራሽነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመፍታት ያለመ ነው። መድረኩ በተለይም አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማስተዋወቅ የአፍሪካን የትምህርት ዘርፍ ማዘመን በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራል። በኤክስፖው በትምህርት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሮቦቲክስ ዘርፎች ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት የቻሉ ከ20 በላይ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። በተጨማሪም በዲጂታል ትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአረንጓዴ ክህሎቶች፣ በምርምርና በኢንዱስትሪ አጋርነት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ውይይቶቹም ከአህጉራዊ የትምህርትና የሳይንስ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተገልጿል። በኤክስፖው ከ300 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ የፈጠራ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል እንደሚገኙ ይጠበቃል። ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ታዳሚዎችም በበይነ መረብ አማካኝነት በሁነቱ ላይ እንደሚሳተፉ ኢዜአ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘው መረጃ ያሳያል። ኤክስፖው በአጠቃላይ በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የዲጂታልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል። ይህም አፍሪካ ለቀጣይ የኢኮኖሚ ሽግግር ብቁና ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲሁም የአህጉሪቱን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላት ታምኖበታል።
ስፖርት
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
Jul 13, 2026 98
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦የዘንድሮ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። ክለቡ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከማለዳው ጀምሮ በተዘጋጀ ስነ ስርአት በተሽከርካሪ የታገዘ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በአቀባበል ስነ ስርአቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ በመሆን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫው ያልፍ ይሆን?
Jul 12, 2026 386
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 5/2018 (ኢዜአ)፦ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን፣ ወሳኙንና የመጨረሻውን የዙር መልስ ጨዋታ ዛሬ ከዛምቢያ ጋር ያካሂዳል። ጨዋታው ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል። ሁለቱ ሀገራት ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በንዶላ ሌቪ ምዋናዋሳ ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ዛምቢያ 2 ለ 1 አሸንፋለች። ፍሪዳ ንዳሼ እና ፒዳ ሙዙዋ የዛምቢያን ጎሎች አስቆጥረዋል። ምኅረት አየለ የኢትዮጵያን ብቸኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ጨዋታው በዛምቢያ የተደረገ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ከሜዳቸው ውጪ ያስቆጠሯት ወሳኝ ጎል በአዲስ አበባው የመልስ ጨዋታ የማለፍ ዕድላቸው እንዲለመልም አድርጎታል። በአሰልጣኝ ራውዳ አሊ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከመጀመሪያው ጨዋታ መልስ ዝግጅቱን በአዲስ አበባ ሲያደርግ ቆይቷል። ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያከናወነ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት እና የስነ ልቦና ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በልምምዱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ኘሬዝዳንት ዳኛቸው ንግሩ (ዶ/ር)፣ የፌዴሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሪት ብዙዓየሁ ጀምበሩ እና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በመገኘት ቡድኑን አበረታተዋል። ኢትዮጵያ በድምር ውጤት ካሸነፈች በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፊፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማለፏን ታረጋግጣለች። በአንጻሩ ዛምቢያ ማሸነፍ ወይም አቻ መውጣት ከቻለች ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ በዓለም ዋንጫው መሳተፏን ታረጋግጣለች። በርካታ ደጋፊ በስታዲየሙ በመገኘት ለታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሞሮኮ አስተናጋጅነት በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም ለሚካሄደው 10ኛው የፊፋ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ 24 አገራት ይሳተፋሉ። የአፍሪካ አህጉር በውድድሩ ላይ በአምስት አገራት የምትወከል ሲሆን፣ ከአስተናጋጇ ሞሮኮ ውጪ አህጉሪቱን ወክለው ወደ ዓለም ዋንጫው የሚጓዙት ቀሪዎቹ አራት አገራት በመጨረሻው ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ተለይተው ይታወቃሉ።
የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለስፖርቱ ዘርፍ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል - ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
Jul 12, 2026 380
አሶሳ፤ ሐምሌ 5/2018 (ኢዜአ)፡- የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለስፖርቱ ዘርፍ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። የአሶሳ ከተማ የመጀመሪያው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ "ለኮሪደር ልማትና ለከተማ ውበት እሮጣለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ ማለዳ ተካሂዷል። በመርሃግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገፅታ በመቀየር የተለያዩ አገልግሎቶች ለነዋሪዎች ተደራሽ እንዲሆኑ አድርጓል። የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማትም ከተማዋን በማዘመን ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ከማድረግ ባለፈ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ በታዎችን በመገንባት ለዘርፉ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን ገልጸዋል። በዚህም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተለዬ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፥ የዛሬው የጎዳና ላይ ሩጫም የኮሪደር ልማቱ ለስፖርቱ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ይበልጥ የሚያመላክት ነው ብለዋል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢብራሂም መንሱር በበኩላቸው፤ መንግስት ለስፖርቱ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት በርካታ የስፖርት መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆኑን አንስተዋል። እንደዚህ ዓይነት የጎዳና ላይ ሩጫ የአትሌቲክስ ስፖርትን ከማነቃቃት ባለፈ በህዝቦች መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር እንደሚያግዝም ጠቁመዋል። በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ሯጮችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
Jul 12, 2026 1090
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር ታላቁ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል። "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" በሚል መሪ ሃሳብ በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው በዚህ መርሃ ግብር ላይ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅትም የውድድሩ ተሳታፊዎች ከሩጫው አስቀድሞ በተዘጋጀው የጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዋናው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የሕዝብ ወኪሎችም ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው። በዚህ ዋና የምክክር ጉባኤ ላይ፡ • የሀገር ግንባታ፣ • የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ • የፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና እና የምርጫ ሥርዓት፣ • የፌዴራል ከተሞች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) ጉዳይ፣ • የሃይማኖት ጉዳዮች፣ • የተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች፣ • ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች (የአርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ጉዳይን ጨምሮ)፣ • እንዲሁም ሙስና፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታን ያካተቱ ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ላይ የሕዝብ ወኪሎች የሚመክሩባቸው ይሆናል። በመስቀል አደባባይ በተሰናዳው በዚህ የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር መርሃ ግብር ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራው አንደሞ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ እንዲሁም የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።
አካባቢ ጥበቃ
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ እና የስነ-ምህዳር መታደስ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል
Jul 11, 2026 707
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተራቆቱ አከባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ በማድረግና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ለዘላቂ አካባቢ ጥበቃና ለስነ-ምህዳር መታደስ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቋቋም፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተገበረች ይገኛል። በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ እስከ አሁን ባሉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ የደን፣ የፍራፍሬና የጥላ ችግኞችን ማልማት ተችሏል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ወደ ትግበራ ተገብቷል። የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካባቢን ከብክለትና ከዕፅዋት መራቆት የምንጠብቅበት፣ እንዲሁም የተዛባውን የተፈጥሮ ሚዛን የምናስተካክልበት ዋነኛና ውጤታማ መንገድ መሆኑን አንስተዋል። በአገሪቱ እየተተገበረ ያለው ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማገገም፣ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጠራቀም በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃና ለሥነ-ምህዳር መታደስ የጎላ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታውቀዋል። ከዚህም ባሻገር ዘላቂ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የአየር ብክለትን ለመቀነስና ለቀጣዩ ትውልድ ምቹና አረንጓዴ ሀገርን ለማስረከብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የሀገሪቱን የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህም ለሀገር ውስጥ የአየር ንብረት መረጋጋት ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ጥበቃም ጭምር ትልቅ በረከት መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራና ሰው ሠራሽ ደን ሥራ አስፈጻሚ አበሩ ጠና በበኩላቸው፤ ከመርሀ ግብሩ ጅምር ጀምሮ የተተከሉት ችግኞች ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። የፍራፍሬና ሌሎች ምግብ ነክ ችግኞች የምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባለፈ ለውጭ ገበያ ቀርበው የውጭ ምንዛሬ ማስገኘትንና የሥራ ዕድል ፈጠራን እየደገፉ እንደሚገኙ አመልክተዋል። መርሀ ግብሩ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ያላትን ዓለም አቀፍ አስተዋጽኦ እያጠናከረ ሲሆን ለካርቦን ገበያ ተጠቃሚነትም ምቹ መሠረት እየፈጠረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። የጉለሌ እፅዋት ማዕከል የምርምርና ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደበላ ብሩ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተለይ ሀገር በቀል ዕፅዋትን በማስፋፋት የሥነ-ምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ሀገር በቀል ዕፅዋት ከአካባቢው የአፈርና የአየር ንብረት ጋር ተስማሚ በመሆናቸው በቀላሉ የሚለሙ መሆናቸውን አንስተው፤ የመሬት ለምነትን፣ የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትንና የአፈር ጥበቃን በማጠናከር የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ኢዜአ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያለውን ተግባራዊ ተሳትፎ አጠናክሮ ይቀጥላል
Jul 11, 2026 434
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሕብረተሰቡን ከማንቃት ባለፈ በተግባር በመሳተፍ ግንባር ቀደም ሚናውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሰይፈ ደርቤ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) አመራሮችና ሰራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለአረንጓዴ ዐሻራ ልዩ ትኩረት ሰጥታ የችግኝ ተከላን ባህል አድርጋዋለች። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ለማስቀጠል እንዲሁም ለዓለም ስጋት የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የምትጫወተውን ሚና ለዓለም በማሳወቅ በኩል ኢዜአ የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግረዋል። ሀገር ያስቀመጠችውን ግብ እንዲሳካ ኢዜአ ማኅበረሰቡን ከማንቃትና መረጃ ከማስተላለፍ ባሻገር፣ በግንባር ቀደምነት በተግባር የመሳተፍ ሚናውን እንደሚያጠናክርም አስታውቀዋል። በተለይም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ማዕከል እንድትሆን የሚከናወኑ ተግባራትን በማስተዋወቅና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። በመርሐ ግብሩ የተሳተፉ የኢዜአ አመራሮችና ሠራተኞች በበኩላቸው፣ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ ዐሻራቸውን በማኖራቸው መደሰታቸውን ጠቅሰዋል። በኢዜአ የይዘት ፕሮግራም ዳይሬክተር ራሄል አበበ፣ መርሐ ግብሩ የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከመጨመር ባለፈ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ እንድትታወቅ ትልቅ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የነጋሪ መጽሄት ምክትል ዋና አዘጋጅ የሺመቤት ደመቀ በበኩላቸው፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መረጃ ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን በተግባር በመሳተፍ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ለፍሬያማነታቸው መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የውጭ ቋንቋ ዴስክ ከፍተኛ አዘጋጅ ሄኖክ ታደለ በሰጠው አስተያየት፣ ኢትዮጵያ የደን ሽፋንን ለማሳደግ የምትሠራው ሥራ ለዓለም ሀገራት አርዓያ እየሆነ መሆኑን ጠቁሟል። ሌሎች የኢዜአ ባለሙያ የሆኑት ሬድዋን ሸምደስር እና ሰርካለም ዘለቀ በበኩላቸው፣ የለመለመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ዐሻራቸውን በማሳረፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ ነው
Jul 11, 2026 430
ባህርዳር ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ገለጹ። የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን በጥበበ ግዮን ህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ አኑረዋል። የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር)፤ የአረንጓዴ አሻራ ኢንሸቲቭ እንደ ሀገር ለውጥና ስኬት እየተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በጥበበ ግዮን ህክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ችግኞችን በመትከል ጀምረዋል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በስሩ በሚገኙ ዘጠኝ ካምፓሶች ችግኞችን በመትከል ፅዱ፣ ውብና ምቹ የመማሪያ አካባቢ ከመፍጠር ባለፈ ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የድርሻውን እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። እንዲሁም ከመማር ማስተማር ስራው በተጓዳኝ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት የላቀ ሚናውን እየተወጣ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። በእለቱ አሻራቸውን ካኖሩት መካከል በዩኒቨርሲቲው የምድረ ግቢ ውበት ዳይሬክተር አማረ ቢተው(ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በተያዘው ዓመትም 15 ሺህ 200 ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መደረጉንና ለዚህም 37 ሄክታር የመካነ እፅዋት መሬት መዘጋጀቱን ጠቁመው ስራው በዛሬው እለት የተጀመረ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ጥረትም ዩኒቨርሲቲው 54 ሄክታር መሬት በአረንጓዴ ልማት መሸፈኑን አስረድተዋል። በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ግንባር ቀደም ማሳያ ነው
Jul 11, 2026 600
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ግንባር ቀደም ማሳያ ነው ሲሉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለፁ። ዓለምን እየፈተኑ ከሚገኙ ተፈጥሯዊ አደጋዎች መካከል የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ይህንን ተጽዕኖ ለመከላከልም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጨባጭ ለውጥ እያስገኘ ዘንድሮ ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል። በእነዚህ ዓመታት በተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮች የሃገሪቱ የደን ሽፋን እንዲጨምርና ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲፈጠር ከማድረጉም በላይ ለግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ዕድገት ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸመች ሲሆን በዘንድሮው ዓመትም ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሐሳብ ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር እያከናወነችው ያለው ተግባር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ አርአያ የሚሆን እጅግ አስደናቂ ስኬት መሆኑን አድንቀዋል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብርሃም ንጉሴ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲና የችግኝ ተከላ ሂደት እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። የአየር ንብረት ጉዳይ መላውን ዓለም የሚያሳስብ ዓለም አቀፋዊ ክስተት በመሆኑ ኢትዮጵያ ይህንን ሂደት በተለይም ከአፍሪካ አህጉር በግንባር ቀደምትነት እየመራችው እንደምትገኝ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የስሪላንካ አምባሳደር ኒርማላ ፓራናቪታ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነቱን የአረንጓዴ ልማት መርሐግብር መተግበሯ እጅግ ብልህነት የተሞላበት አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለሀገር የኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አበርክቶ ያለው መሆኑን በመግለጽ፣ ስሪላንካ በዚህ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያላትን ፍላጎት ተግባራዊ የምታደርግበትን መንገድ እያጠናች መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የፓኪስታን የንግድና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ተወካይ ባሲት ሳሊም ሻህ በበኩላቸው፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ለኢትዮጵያ የተለየ ውበትና መስህብ ከመለገሱም በላይ፣ ከአየር ብክለት የጸዳ አካባቢን ለማስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብና መሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለዚህ ከፍተኛ ደረጃ መብቃት መቻላቸው ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 18838
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 12340
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 11134
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 11032
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የሌማት ትሩፋት ሀገራዊ ስኬት- ከአመጋገብ ለውጥ እስከ ገቢ ምንጭ
Jul 13, 2026 79
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ለብዙ ኢትዮጵያውያን ወተት፣ እንቁላል፣ ማርና ሥጋ በምግብ ገበታ የማይገኙ፣ ለረጅም ዓመታት የቅንጦት ያህል የሚታዩና በቂ ምርት ባለመኖሩም በገበያ ላይ በስፋት የማይገኙ ነበሩ። ይህንን እውነታ ለመቀየርና የዜጎችን የሥርዓተ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ሀገራዊ መርሃ ግብር ዛሬ ላይ ትልቅ ተስፋና ተጨባጭ ውጤት እያሳየ ይገኛል። ቀደም ሲል ትኩረት አጥቶ የነበረውን የእንስሳት ተዋጽኦ ልማት በቅንጅትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ረገድ በአካባቢው ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። በግብርና ሚኒስቴር መረጃ መሠረት መርሃ ግብሩ ከመጀመሩ በፊት የነበረው 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ዘንድሮ 15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር መድረሱ፣ በዓመት የሚሰራጨው የዶሮ ጫጩት ከ26 ሚሊዮን ወደ 184 ሚሊዮን ማደጉ እንዲሁም የእንቁላል ምርት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ከፍ ማለቱ የዚሁ ሀገራዊ ስኬት ማሳያዎች ናቸው። ይህ የተጀመረው አበረታች ሂደት እንደ ወተት፣ ማር፣ ሥጋ፣ አሳ እና እንቁላል ያሉ ምርቶች የቅንጦት ሳይሆኑ የዜጎች የዕለት ተዕለት የሥርዓተ ምግብ አካል እንዲሆኑ በማስቻል ረገድም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። መርሐግብሩ በቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ ለሚኖሩ በርካታ ዜጎችም የአመጋገብ ሥርዓትን ከመቀየር ባለፈ፣ የኢኮኖሚ አቅማቸውን የለወጠ የሕይወት ጉዞን ፈጥሮላቸዋል። አቶ ከፈለኝ ጫላ ቀደም ሲል በመንግሥት ሥራ በደመወዝ ነበር የሚተዳደሩት። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ላይ ዜጎች እንዲሳተፉ ጥሪ ሲቀርብ ግን የቀደማቸው አልነበረም። ገንዘብ በብድር በማመቻቸት በአንድ የወተት ላም ሥራቸውን ጀመሩ። በአሁኑ ወቅት የወተት ላሞቻቸውን ቁጥር 15 ማድረስ ችለዋል። የአካባቢው አስተዳደርና ባለሙያዎች ያደረጉላቸው ተከታታይ ድጋፍና ክትትል አሁን ለደረሱበት ውጤት እንዲበቁ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተላቸው ያነሳሉ አቶ ከፈለኝ። የራሳቸውን ኑሮ ከመቀየር ባለፈ፣ የሚያመርቱትን ወተት ለአካባቢው ማኅበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የተመጣጠነ አመጋገብን እንድንከተል የሌማት ትሩፋት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል የሚሉት አቶ ከፈለኝ፥ በተጨማሪም በመስኩ ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል። ሌላኛው በዚሁ መርሃ ግብር ሕይወታቸው የተቀየረው ሥራ ፈጣሪ አቶ ጌቱ ብሩ ናቸው። እሳቸው ደግሞ በተቀናጀ የዶሮና የዓሣ ልማት ዘርፍ ላይ ነው የተሰማሩት። የሌማት ትሩፋት ያመጣላቸው በረከት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከመጥቀም አልፎ የንግድ አድማሳቸውን አስፍቶላቸዋል። ከልማቱ በሚያገኙት የምርት ውጤት የራሳቸውን ሆቴል መክፈት የቻሉ ሲሆን፣ ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። "ለሆቴላችን የምግብ ግብዓት የሚሆነውን ምርት የምናቀርበው ከራሳችን የዶሮና የዓሣ እርባታ ማዕከል ነው" የሚሉት አቶ ጌቱ፣ ዘርፉ ሰፊና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት መሆኑን ይመሰክራሉ። አቶ ጌቱ እቅዳቸው እዚህ ላይ ብቻ አያበቃም፤ በቀጣይ የሌማት ትሩፋት ምርቶችን እሴት ጨምረው ለከተሞች ከማቅረብ ባለፈ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክና ለሀገር የውጭ ምንዛሬ የማስገኘት ውጥን አላቸው። ሌሎችም በዚህ ሥራ ላይ ቢሰማሩ ከራሳቸው አልፈው ሀገርንና ወገንን መለወጥ እንደሚችሉም ነው የጠቆሙት። በተመሳሳይ በዶሮ እርባታ ሥራ ላይ የተሰማሩት አቶ ደረጄ አበበ መርሃ ግብሩ ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ይናገራሉ። የዶሮ እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለአካባቢው ማኅበረሰብ በስፋት በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰዋል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፥ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበትና የዜጎችን የምግብና ሥርዓተ ምግብ አቅም እያሳደገ የሚገኝ ኢኒሼቲቭ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሀገራዊ ጥረት ለማሳካት የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ጠቅሰዋል። አክለውም፤ ኢኒሼቲቩ በቤተሰብ ደረጃ የዶሮ እርባታ ባህል እንዲሆን በማድረግ፣ በተለይም ሕፃናትና እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ መሠረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑንና ምርቶች በስፋት ለገበያ እንዲቀርቡ በማስቻል ረገድ ትርጉም ያለው ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Jul 12, 2026 366
አዲስ አበባ፤ ሀምሌ 5/2018 (ኢዜአ) ፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የኢትዮጵያ እመርታ በምሁራን እይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና፣ ቱሪዝም፣ በመሠረተ-ልማትና በማህበራዊ ዘርፎች በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ እመርታ እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል። የእርሳቸውን ማብራሪያ ተከትሎ ኢዜአ ያነጋገራቸው በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲንና የአግሪካልቸራል ኢኮኖሚክስ ባለሙያ ከዲር ጀማል (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የብዝሃ ኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫን በመከተል አቅምን አካብቶ በተደመረ አቅም በማልማት ባለፉት አምስት አመታት የተመዘገበው ስኬት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ሙሐመድ ኢብራሂም በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በብዝሃ ዘርፍ ላይ ያተኮረ መሆኑ በሁሉም ዘርፎች ተመጣጣኝ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ አግዟል ብለዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊና ስነሰብ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር)፤ መንግስት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስመዝገብ የነደፋቸው ፖሊሲዎች ሀገር ያላትን ጸጋዎች አልምቶ ለመጠቀም ወሳኝ ናቸው ብለዋል። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማስፋፋትና ለማዘመን ከተያዙ ቁልፍ ዘርፎች መካከል የኢንዱስትሪው ክፍለ-ኢኮኖሚ ዋነኛውና የትኩረት ማዕከል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጥቀሳቸውም ይታወሳል። ከለውጡ በፊት በሀገሪቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ በታች እንደነበር ጠቅሰው፤ ለዚህም እንደ ፋይናንስ፣ መሬትና የኃይል አቅርቦት ችግሮች በምክንያትነት ይጠቀሱ እንደነበር ገልጸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም እያንዳንዱን ኢንዱስትሪ በመጎብኘትና ችግሮቻቸውን በየደረጃው ለመፍታት ባደረገው የተቀናጀ ጥረት፣ ቀድሞ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው ዛሬ ላይ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር መስፍን መኮንን (ዶ/ር)፤ ባለፉት ዓመታት የውጭ ምንዛሬ እጥረት በትልቅ ተግዳሮትነት የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ችግሩ በፍጥነት እየተቀረፈ ይገኛል ብለዋል። በጅማ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ምጣኔ ባለሙያ እና ተመራማሪ አደባ ገመቹ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ እንደ ስንዴ እና ሩዝ ያሉ ሰብሎችን በስፋት በማምረት ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመቀነስና ለማስቀረት ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኗን ገልጸዋል። የወላይታ ሶዶ እና የወሎ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የተከማቹ ችግሮችን ለመፍታት ያለውን ዕድል መጠቀም እንደሚገባ የገለጹትን ሃሳብ በመጋራት፤ ለኢዜአ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ምሁራኑ በኮሚሽኑ የተለዩት የምክክር አጀንዳዎች ሁሉንም አካታች አድርገው የተመረጡና ለቆዩ ሀገራዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንደሚያስችሉ ተናግረዋል። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት መምህርና ተመራማሪ ተሻለ ተገኔ (ዶ/ር) እንዳሉት በኮሚሽኑ የተለዩ ስምንት የምክክር አጀንዳዎች ለቅራኔ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ሀገራዊ ምክክሩ የዜጎችን አንድነት በማጠናከር ለሀገራቸው በጋራ እንዲቆሙ በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ጣሰው ታደሰ ናቸው። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ካሴ በበኩላቸው፤ የምክክር ኮሚሽኑ የለያቸው የመወያያ አጀንዳዎች ስር የሰደዱ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል። ለሰላም ለተዘረጉ እጆች ምላሽ የሰጡ ወጣቶች ስኬት የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከጥፋታችን ተምረን ለልማትና ለሰላም ግንባታ አርአያ በመሆን እየሰራን ነው ሲሉ የአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች የገለጹት በዚህ ሳምንት ነው። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተሃዲሶ ስልጠና ወስደው ህብረተሰቡን ተቀላቅለው በልማት ስራ ላይ የተሰማሩ የቀድሞ ታጣቂዎችን የኢዜአ ሪፖርተር አነጋግሯቸዋል። የቀድሞ ታጣቂዎቹ፤ በተሳሳተ መንገድ ጫካ በመግባት ማህበረሰባቸውንም ይሁን ቤተሰባቸውን የጎዱበት አጋጣሚ ሲያስታውሱ ከፍተኛ ጸጸት የሚሰማቸው መሆኑን ገልጸዋል። በጫካ እንዲሰባሰቡ ያደረጓቸው አካላት ለዘረፋና ሃብት ማካበት እንጂ ለአላማ የተሰለፉ እንዳልሆኑ በመረዳታቸውም የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሃዲሶ ስልጠና ወስደው ማህበረሰቡን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል። ለሰላም ለተዘረጉ እጆች ምላሽ የሰጡት ወጣቶቹ የልማት አርበኛ እና የሰላም አምባሳደር ሆነው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እየመከረች ነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "ሀገራዊ የምክክር ጉባኤውን" ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ማካሄድ ይጀምራል። በምክክር ኮሚሽኑ በተለዩት ስምንት አንኳር አጀንዳዎች ላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ተመካክረው የሚያቀርቧቸው ምክረ ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው ዘላቂ መፍትሄ ይገኝባቸዋል ተብሎም ታስቧል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል ሴቶች ማህበራት ፌዴሬሽን ለምክክሩ የተለዩ አጀንዳዎች የቆዩ ሀገራዊ ችግሮችን በመፍታት በአሰባሳቢ ትርክት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችሉ ነጥቦች መሆናቸውን ገልጿል። የፌዴሬሽኑ ዳይሬክተር ወይዘሮ እንየ ገነቱ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ ታሪካዊ እድል መሆኑን አንስተዋል። የአማራ ክልል ሴቶች ማህበራት ፌዴሬሽን በምክክር ሂደቱ እስካሁንም በንቃት መሳተፉን አውስተው በቀጣይም ለምክክር ጉባኤው መሳካት የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል። የዲጅታል አገልገሎት ለዘመናዊ የንግድ ስርአት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ''የተደራጀ የዲጂታል አገልግሎት ለዘመናዊ የንግድ አገልግሎት'' በሚል መርህ የሴክተር ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ አካሄዷል። በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በበጀት ዓመቱ የንግድ ዘርፉን ከማዘመን በተጨማሪ ዲጂታል አገልግሎቱን በማጠናከር ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የተገልጋዩን ጊዜና ጉልበት ለሚቆጥቡ አገልግሎቶች ተደራሽነት የተደረጉ ጥረቶች ስኬታማ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም ከ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የንግድ ፈቃድና መሠል አገልግሎቶችን በኦን ላይን በመፈጸም የንግዱን ማህበረሰብ የአገልግሎት እርካታ 96 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል። በበጀት ዓመቱ 805 ተጨማሪ የቅዳሜ እና ዕሁድ ገበያዎች መከፈታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በዚህም በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ለማህበረሰቡ በቀጥታ ማቅረብ በመቻሉ ገበያው እየተረጋጋ መምጣቱን አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከተላኩ የተለያዩ ምርቶች ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ማንሳታቸው ይታወሳል። ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሳምንቱ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በስፋት የተተገበረበትም ነው። የዘንድሮው ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው በዚህ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመደጋገፍና የመረዳዳት እሴቶችን በማጎልበት ማህበራዊ ሃላፊነት በጋራ መወጣት የሚያስችል ነው። በመርሃ ግብሩ ወጣቶች የሚያከናውኗቸው የልማት ተግባራት ህዝቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ በበኩላቸው በጎነትና አብሮነት የማህበረሰቡ መልካም እሴት በመሆኑ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች እርስ በርስ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ባከናወኗቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 25 ሚሊዮን ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች በመሳተፍ ከ53 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ተግባራትን እንደሚያከናውኑም ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትም የክልሉ እና የዞኑ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ እንደገለፁት፤ የህዝቡን የነበረውን የቆየውን የመረዳዳት እሴትና ባህል ወደነበረበት ለመመለስ የክልሉ መንግስት እየሰራ ይገኛል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በበጎ ፍቃድ አገለግሎት በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶቾ፣ የአረጋውያን እንክብካቤን ጨምሮ በአቅመ ደካማ ቤት እድሳትና ግንባታ፣ በደም ልገሳ፣ በፅዳት፣ በውበትና በአረንጓዴ አሻራ ህዝቡ የነበረው ተሳትፎ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን አመላክተዋል። ተስፋን እንትከል ሳምንቱ የክረምቱ ዝናብ ያየለበትና የእርሻውና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላው መርሃግብር በስፋት የተካሄደበት ሆኖ አልፏል። በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጋር በፓርላማ ጊቢ ከተከሉት ችግኝ ጀምሮ በመላ ሀገሪቷ በስፋት የተተከለበት ሳምንት ነው። በሳምንቱ የክልል አመራሮች፣ የተቋማት ተወካዮች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም ነዋሪዎች ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በስፋት ተክለዋል። 8 ቢሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ ሀይቅ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ቦሎቄን በኩታ ገጠም በኦሮሚያ ክልል የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሳደግ የሚረዱ እና ለወጪ ንግድ የሚውሉ ምርቶችን በስፋት የማምረት ስራ ትኩረት ማግኘቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገለጹ። በክልሉ ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ቦሎቄን በኩታ ገጠም የመዝራት ሥራ የክልሉ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል። በዚሁ ወቅት የቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ አዱኛ በክልሉ የግብርና ምርታማነትን በእጥፍ ከመጨመር ጎን ለጎን፣ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሳደግ በወጪ ንግድ ምርቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል። በዞኑ ቦሰት ወረዳ የዶንጎሬ ጪዮስ ቀበሌ የተጀመረው ቦሎቄን በኩታ ገጠም የመዝራት ሥራ ለዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው መሰል መልካም ተሞክሮዎች እንዲሰፉ ይደረጋል ነው ያሉት። በደቡብ ወሎ ዞኑ 15 የእርሻ ትራክተሮች ለአርሶ አደሩ የተከፋፈሉትም በዚሁ ሳምንት ነው። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮነን በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ በዞኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ግብርናውን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ የተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ተመዘግቦበታል። ዞኑ በሜካናይዜሽን ለሚካሄድ የሰብል ልማት ምቹ መሆኑን ጠቁመው፣ በዚህም በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ጥራትና ብዛት ያለው ምርት በማምረት ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የማዳበሪያ ስርጭት በአማራ ክልል ለመጪው መኸር ሰብል ልማት የሚውል ከአራት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ለዘንድሮው የመኸር ሰብል ልማት 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል። እስካሁን ባለው ሒደትም ከ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደ አካባቢው የገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነውን ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል። የማዳበሪያ ስርጭቱ ቀድመው ለሚዘሩ አካባቢዎችንና በክረምት ለተሽከርካሪ አስቸጋሪ ለሆኑ አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት የተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን በጎንደር ከተማ ገጠር ቀበሌዎች የተጀመረው ሞዴል የአርሶ አደሮች መንደር ግንባታ በአዲሱ በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ከተማ አስተዳደሩ በ2019 በጀት ዓመት አሻጋሪ የእድገትና የዘላቂ የልማት እቅድ ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር የትውውቅ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ፕላንና ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ፋሲል አብዩ እንደተናገሩት የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ ከመቀየር ባለፈ ሁለንተናዊ አገልግሎትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት መሰረተ ልማትን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እና የግብርናውን ኢኮኖሚ ለማዘመንም ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሳይ እና በሳቢያ የገጠር ቀበሌዎች በገጠር ኮሪደር የተገነባውን ሞዴል የአርሶ አደሮች መንደር በአዲሱ በጀት ዓመትም በሌሎች ቀበሌዎች ለማስፋት የቅድመ ዝግጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በአስተዳደሩ ስር በሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች 20 ሞዴል የገጠር መንድሮችን ለመገንባት ዝግጅት መጀመሩንም አቶ ፋሲል ጠቅስዋል። የማዕድን ሀብት ልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፥ ሀገሪቱ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከወርቅ ማዕድን ዘርፍ 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ ገቢ ማስመዝገቧን ይፋ አድርገዋል። በማዕድን ዘርፍ የተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ እና ድጋፍ ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማስቻሉንም አስታውሰዋል። የማዕድን ሀብት ክምችት ከሚገኝባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የማዕድን ምርት ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ናስር ሙሐመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ወርቅን ጨምሮ በርካታ ማዕድናትን በማልማት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ከመቻሉ በላይ ክልሉ ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱን አስታውቀዋል። ለአብነትም በ2018 በጀት ዓመት 8 ሺሕ 961 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መግባቱን ገልጸዋል። ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልም በበጀት ዓመቱ 348 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ማዕድን እና ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ወልያብ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 350 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ ታቅዶ 348 ኪሎ ግራም ምርት ቀርቧል። በጥራትና በፍጥነት የፕሮጀክቶች ግንባታ በሶማሌ ክልል የተጠናቀቀውን የ2018 በጀት ዓመት የሴክተር ቢሮዎች የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት ተጠናቀው ለአገልገሎት እንዲበቁ ተገቢ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል። የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የክልሉ እና የሀገሪቱን ልማት ማፋጠን የሚችል ብቁ የሰው ሀይል እንዲያፈሩ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችም ይጠናከራሉ ሲሉ ተናግረዋል። መሰረተ ልማት ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 ሺህ አዳዲስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ይህን የተናገሩት የሞጆ-አዳማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረበት ወቅት ነው። ፕሮጀክቱ ለ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አዳማ የንግድ፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ማዕከል እንደመሆኗ፣ ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል። ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 ሺህ አዳዲስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅትም ከእነዚሁ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የጎዴና ቢቸና ከተሞች የውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን አንስተዋል። ማጠቃለያ ሳምንቱ በሁሉም ክልሎቻችን መደበኛ የልማት፣ የማህብራዊ እና የሰላም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው የቀጠሉበትም ነበር። በሁሉም ክልሎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በተመሳሳይ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላና የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በሁሉም ክልሎች እየተከናወነ ይገኛል።
ላሊበላ፦ ከዓለም አቀፍ ቅርስነት እስከ ባህል ዲፕሎማሲ ማዕከልነት
Jul 9, 2026 1260
በሙሴ መለሰ ከ40 በላይ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተወከሉ ከ70 በላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና የልማት አጋሮች ከአፍሪካ እጅግ አስደናቂ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶች መገኛ በሆነችው በታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ ከሰሞኑ ጉብኝት አድርገዋል። ይህ ታሪካዊ ጉብኝት በዓለም አቀፍ ደረጃ የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የመንከባከብና የመጠበቅ የጋራ ቃልኪዳንን በድጋሚ ለማደስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህን ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት ያዘጋጀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ ከአማራ ክልል መንግሥት፣ ከላሊበላ ከተማ አስተዳደር እና በፈረንሳይ መንግሥት ድጋፍ ከሚንቀሳቀሰው “ዘላቂ ላሊበላ” ፕሮጀክት (Sustainable Lalibela Project) ጋር በመሆን ነው። ላሊበላ እ.አ.አ በ1978 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የሰፈሩት ድንቅ አብያተ ክርስቲያናትን ይዛለች። ከስምንት መቶ ዓመታት በፊት (በ13ኛው ክፍለ ዘመን) ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለው የታነጹት 11ዱ ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናት፤ ዛሬም ድረስ መላውን ዓለም በአድናቆት የሚጎበኛቸው፣ የጥንታዊ ምህንድስና እና የመንፈሳዊነት ጥልቅ መገለጫዎች መሆናቸውን ዩኔስኮ ጉብኝቱን አስመልክቶ ባወጣው ጽሁፍ ላይ አመልክቷል። በጉብኝቱ የተሳተፉት ዲፕሎማቶች እንደ ቤተ መድኃኔዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ አማኑኤል እና ቤተ ቅዱስ መርቆሬዎስ ያሉትን አብያተ ክርስትያናት ተመልክተዋል። ዲፕሎማቶቹ ላሊበላን “ከዚህ ዓለም ስሪት የላቀ እፁብ ድንቅ ጥበብ” ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ቅርሶቹ የጥንታውያኑን አባቶች ድንቅ የምህንድስና ጥበብና የስነ-ህንጻ ልህቀት ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መሆናቸውን በአድናቆት ተናግረዋል። ዲፕሎማቶቹ ከአብያተ ክርስቲያናቱ ጉብኝት ባሻገር ከነዋሪው፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አድርገዋል። ይህ ውይይት ልዑካኑ የላሊበላን ህያው ቅርስ ለመጠበቅ የሚደረጉ ጥረቶችን እና ይህንን ታሪካዊ ስፍራ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት እየገጠሙ ያሉ ወቅታዊ ተግዳሮቶችን መፍታት ስለሚቻልበት ሁኔታ በተሻለ መልኩ ለመረዳት አስችሏቸዋል። ጉብኝቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በቅርቡ በአካባቢው ከተከሰቱ ፈተናዎች በኋላ፣ የላሊበላን የቱሪዝም እንቅስቃሴ መልሶ ለማገገም እና ለማነቃቃት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። ጎብኚዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባህል ሰዎችን በማቀራረብና የእርስ በርስ መግባባትን በማጠናከር ረገድ ስላለው የማይተካ ሚና አጽንኦት ሰጥተዋል። ዩኔስኮ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ለፈረንሳይ መንግሥት እና ለጉብኝቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል። ጉብኝቱ የላሊበላን ባህላዊ፣ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶች እና እሴቶች ባሉበት ለተተኪው ትውልድ ለማሻገር ያለውን ዓለም አቀፍ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል። ዩኔስኮ በቅርሱ አያያዝ፣ ጥበቃ እና ቀጣይነት ላለው አስተዳደር ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ቴክኒካዊ ትብብር እና በአቅም ግንባታ ለበርካታ አስርት አመታት በቅርበት ሲሰራ መቆየቱንና የቅርሱን ዓለም አቀፍ ሀብትነት ጠብቆ ለማቆየት ይህንኑ ተግባሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በጽሁፉ አረጋግጧል።
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
Jul 5, 2026 1933
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28/2018(ኢዜአ):- የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው የገጠር ትራንስፎርሜሽን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው የከተሞች ኮሪደር ልማት ወደ ገጠሩም ተስፋፍቶ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗርና አመጋገብ እንዲሁም ጤናን መሰረት በማድረግ የገጠር ኮሪደር ልማት በመከናወን ላይ ይገኛል። ለጤናም ይሁን ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ለዘመናት በተመሳሳይ ሁኔታ የኖረው አርሶና አርብቶ አደሩ አሁን ላይ መሰረታዊ የአኗኗር ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በገጠር የኮሪደር ልማት የሰዎችና እንስሳት መኖሪያ እየተለየ፤ በባዮ ጋዝ እና በፀሃይ ብርሃን በሚሰራ የሃይል ምንጭ መብራት ማግኘትና ምግብ መስራት የተቻለበት፤ በጓሮ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን መመገብ የሚቻልበት ዘመናዊ አኗኗር ጀምረዋል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት እንቅስቃሴው በጅምር ላይ ቢሆንም በብዙ አካባቢዎች እየተስፋፋ ሞደል መንደሮች እየተበራከቱ መጥተዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ሀማሳ በ79 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ የተሰራው ሞዴል መንደር የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቆ ለነዋሪዎች የተላለፈው የሀማሳ ሞዴል መንደር በአንድ ግቢ ውስጥ የንጽህና መጠበቂያ፣ የተደራጀ የቤት እንስሳት ማቆያ፣ በባዮ ጋዝ የሚሰራ የሃይል አቅርቦትን እንዲሁም የተሟላ የጓሮ ግብርናን ማእከል አድርጎ የተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም መንግሥት በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች ሞዴል ቤቶችን መስራቱን አስታውሰው ከዚህ በመነሳት ነዋሪዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት የራሳቸውን መኖሪያዎች መገንባት ጀምረዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ''ንጽህና ካለ ጤና አለ፤ ምግብ ካለ ጤና አለ፤ የተስተካከለ ኮሪደር ካለ ሰላም አለ። እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ግምት ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል። የዜጎቻችንን ሕይወት ይቀይራሉ፤ የአኗኗር ዘዬአችንን ያሻሽላሉ፤ ኢትዮጵያን ወደ ምናስበው ከፍታ ወደ ምናስበው መሻሻል የመውሰድ አቅም አላቸው'' ሲሉም ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ቀጥሎ በጋሞ ዞን የ'ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆን የድንጋይ ከሰል ከውጭ ሀገር ለማስገባት እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ውጪ የሚደረግ መሆኑን አንስተዋል። አሁን ላይ በኢትዮጵያ የተለያዩ የከሰል ማምረቻ ፋብሪካዎች ተመርቀው ወደ አገልግሎት መግባታቸውንና ይህም የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ከመሙላት ባለፈ ለውጭ ገበያ የማቅረብ እድል ይፈጥራል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአርባምንጭ ዘመናዊ የኮንፈረንስ ሪዞርት መርቀው ስራ ያስጀመሩ ሲሆን በዶርዜ ሎጅ እና አካባቢው መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም የአርባ ምንጭ ከተማን የኮሪደር ልማት፤ በከተማዋ የሚገኘውን ኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓንም ጎብኝተዋል። በሁሉም ዘርፎች ኢትዮጵያ ማከናወኗን አጠናክራ ቀጥላለች፤ እድገትና ማንሰራራቷ ላይቀለበስ ጉዞውን ቀጥሏል። ከዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች አንዱ የቱሪዝም ሚኒስቴር በዚህ ሳምንት እንዳስታወቀው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኗል። በዩሮኒውስ የዜና አውታር በተደረገ ጥናት፤ ሁሉንም የዓለም ክፍሎች ያዩ አንጋፋ ተጓዦች ካስቀመጧቸው ተወዳጅ የዩኔስኮ የዓለም ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በግንባር ቀደምትነት ተቀምጧል። በዚሁ ሳምንትም ከአርባ በላይ ሀገራት እና ከአሥር በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወከሉ ዲፕሎማቶች የላሊበላ ከተማና ውቅር አብያተክርስቲያናትን ጎብኝተዋል። ይህ ከፍተኛ የዲፕሎማቶች ልዑክ በቆይታው ከ800 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩትን፣ የሕንጻ ጥበብ እና የኢንጂነሪንግ ጥበብ ማስተርፒስ እንዲሁም የሃይማኖትና የታሪክ ሕያው ምስክር የሆኑትን የዓለም ቅርስ የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ አስተማማኝ መከታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በመከላከያና ስትራቴጂክ የደህንነት ጥናት መስክ ያሰለጠናቸውን ተመራቂዎች በዚሁ ሳምንት አስመርቋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ሰራዊቱ የውስጥ ባንዳና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችን ከንቱ ህልም በማምከን የሀገርን ሉዓላዊነት በአስተማማኝ መልኩ እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል። የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄና ቀጣናዊ የትብብር መርህ ለማደናቀፍ ታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ግንባር ፈጥረው እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያን ከባሕር ለማስወጣት የተጠቀሙበት የረጅም ዘመናት ሴራም ዛሬ ላይ “ፅምዶ” በሚል የተሰለፉ አካላት ስለመኖራቸው ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአደረጃጀት ልዩ እና በዘመናዊ ትጥቅ ተጠናክሮ በማንኛውም ሁኔታ ለሀገሩ ክብርና ሉአላዊነት መጠበቅ አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና በሳምንቱ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ስኬታማ በሆነ መልኩ ተከናውኗል። በሁሉም አካባቢዎች ተፈታኞች በበይነመረብ (ኦንላይን) እንዲሁም በወረቀት እንደየ ዝግጅቱና ምቹ ሁኔታውን መሰረት በማድረግ ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። በገጠር ኮሪደር አዲስ የህይወት ምእራፍ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ በተገነባው ሞዴል የገጠር መንደር የሚኖሩ አርሶ አደሮች አዲስ የህይወት ምእራፍ መጀመራቸውን ገልጸዋል። የኤሌክትሪክና ሌሎች አገልግሎቶች የተሟላለት የገጠር ሞዴል መኖሪያ መንደር የአኗኗር ዘይቤያችንን ምቹና ዘመናዊ አድርጎታል ያሉት ነዋሪዎቹ ይህንን ላደረጉ ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ የተገነባውን የገጠር ሞዴል መኖሪያ መንደር መመረቃቸው ይታወሳል፡፡ የግብርናና ገጠር ሽግግርን እውን በማድረግ የአርሶ አደሩን አኗኗር ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የመብራት፣ የውሃ፣ የመንገድን ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን አርሶ አደሩ በአቅራቢያው ማግኘት የሚያስችልና የኢኮኖሚ አቅሙን የሚያሳድጉ መሆናቸውን በወቅቱ ተናግረዋል። በቀጣይም ተግባሩን በማስፋት ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግን ፍልሰት ለማስቀረት በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አኔ ዲማ ወረዳ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰኣዳ አብዱረህማንና የከተማው ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የአከባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሄዷል። የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን በወቅቱ፤ ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ የሚሰጡ ናቸው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለትውልድ ቀጣይነት አስተማማኝ ዋስትና ጭምር መሆኑን ተናግረዋል። የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ በሸገር ከተማ የአካባቢውን አረንጓዴነት ለማረጋገጥና ኢኮኖሚውን ለመደገፍ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን የተለያዩ ዝርያ ያላቸውና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር ገብተናልም ብለዋል። የባቡር መስመር ጥገና የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ባቡር መስመር ፕሮጀክት ጥገናን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በቅርቡ የጥገና ስራው የተጀመረውን የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት የጥገና ሂደት በዚሁ ሳምንት ጎብኝተዋል። ከአዋሽ -ኮምቦልቻ -ሃራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ፕሮጀክት በአራት አቅጣጫ የጥገና ሥራው እየተከናወነ መሆኑም ታውቋል። ለልማት ተነሽዎች የተገነቡ ቤቶች በዚሁ ሳምንት የጅማ ከተማ አስተዳደር ለልማት ተነሺዎች ያስገነባውን 300 መኖሪያ ቤቶች መርቆ ማስረከቡን እንመለከታለን። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ጌቱ ገመቹ፤ በክልሉ በገጠርም ይሁን በከተሞች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ ጠሃ ቀመር፤ በከተማው በርካታ ፕሮጀክቶች በመንግስት እየተከናወኑ እንደሆኑና የተጠናቀቁትም ለአገልግሎት ክፍት እየተደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በከተማዋ በዚህ አመት 80 የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ጠቅሰው ዛሬ ለልማት ተነሺዎች ተገንብተው የተላለፉ መኖሪያ ቤቶች የዚሁ ጥረት አንድ አካል ናቸው ብለዋል። እነዚህ መኖሪያ ቤቶች ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው ግንባታቸው ተጠናቆ ለ300 አባወራና እማወራዎች ተላልፈዋል ብለዋል።
ትንታኔዎች
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 3096
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 2688
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ትላንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሳሰር - የመደመር መንግስት እይታ በቱሪዝም
Jul 1, 2026 2712
በዮሐንስ ደርበው ቱሪዝም ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመላው ዓለም ከፍተኛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ነው። ይህ ዘርፍ በአህጉራችን አፍሪካም ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙበት ሃገራት እንዳሉ ይታወቃል። ቱሪዝም ከገቢነት ከኢኮኖሚያዊ እቅምነት ባለፈ ትውልድን ያስተሳስራል ብሄራዊ ትርክትን ለመገንባትም ያግዛል ። ትላንትን ከዛሬ ዛሬንም ከነገ ጋር የሚያስተሳስር ነው። “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግስት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ በማድረግም ይጠበቅባቸዋል።
ምክክር - ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ!
Jun 24, 2026 6457
በዮሐንስ ደርበው በአመለካከት መለያየት ሥሪቱ ተፈጥሯዊ ነው። ሰዎች ልክ በመልክ፣ ቁመት ውፍረት ወይም ቅጥነት ሥብጥር፤ ምድርም በተፈጥሮ አቀማመጥ እና በዓየር ጠባይዋ ወጥ እንዳልሆኑት ሁሉ ማለት ነው። ለአንድ ሕዝብ እና ሀገር ብልጽግና ሲባል ከተበተነ ይልቅ የተደመረ ሐሳብ በእጅጉ ይጠቅማል። ሀገርኛ ብኂላችን “ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ” ብሎ መሰባሰብን እንደሚሰብከው። የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ይካሄዳል - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ትውልዱ ዛሬንም ነገንም በሚጠቅመው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ንቁ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ከሥሪታቸው አንጻር ዕሳቤዎች የግድ ተጨፍልቀው አንድ እንዲሆኑ ባይጠበቅም፤ ሀገርና ሕዝብን ወዳስቀደመው በይበልጥ ገዥ ሐሳብ መቅረብ ግን ተገቢ ይሆናል። በአንጻሩ በተለያዩ ዋልታዎች ቆሞ መጓተት ለማን ይጠቅማል? በምክክር ሁሉንም አሸናፊ አድርጎ መቋጨት እየተቻለ ለበርካታ ዓመታት የሐሳብ ልዩነቶች የወለዷቸው ግጭቶች፤ እንደ ሀገር አያሌ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ-ልቡናዊ እና ማኅበራዊ ክስረቶች ማስከተላቸውን ታሪክ ይነግረናል። የለውጡ መንግሥት ለኢትዮጵያ ከቸራቸው ትልልቅ ጉዳዮች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ አንዱ ነው። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ሀገር ውስጥ የምንኖር ሕዝቦች ራሳችንን በታማኝነት ፈትሸን በሐሳብ ልዩነቶች ላይ ለመነጋገር መፍቀዳችንን የሚጠይቅ ሂደት እንደመሆኑ፤ በቁጥር የማይተመኑ ረቂቅ የሆኑ ዋጋዎች አሉት። ይህም ፍላጎትን በኃይል ለመተግበር ሕይወትና ንብረት ከሚያወድመው ጦርነት ይልቅ አዋጭ የመግባቢያ መንገድ መሆኑን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። እዚህ ደረጃ ከመደረሱ በፊት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ኮሚሽኑ በየጊዜው ማሳወቁም ይታወሳል። ሀገራዊ ምክክር በአካታችና አሳታፊ ውይይት ወደ የጋራ መግባባት መድረሻ አትራፊ መንገድ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ኃላፊነቱን ለመወጣት ለምክክር በሩን ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ክፍት አድርጓል። በዚህም መሠረት ከዳያስፖራው፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በተለያዩ ክልሎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩና ሰላምን ከመረጡ ብሎም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ፤ አጀንዳዎችንም ተቀብሏል። ኮሚሽኑ የመጨሻው የምክክር ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት ዋና ኮሚሽነሩ፤ አካታች የምክክር ጉባዔ ለማካሄድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሩ ክፍት መሆኑንም አረጋግጠዋል። የኪንታሮት ህመም እንዴት ይከሰታል? እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ብልኀትስ አለ? 👉 ሀገራዊ ምክክር ምን ይጠግናል? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥራ በሆነው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 384 ላይ እንደተቀመጠው፤ በሀገረ-መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ተመካክሮ፣ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ፣ የተግባባባቸውን በሕግና በሥርዓት አጽንቶ፤ ያልተግባባባቸውን ለወደፊት ምክክሮች አቆይቶ አልተጓዘም። በዚህ የተነሣ በየጊዜው ቅሬታ፣ ኩርፊያ፣ አብዮት፣ ዐመጽ ይፈጠራል። ነገሮች በተናጠል እየቀረቡ ለፖለቲካ ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታ ይመቻቻል። ሁለንተናዊ ዕይታ ይጠፋል። ሀገራዊ ምክክር ይህን የዘመናት ስብራት ይጠግናል። 👉 ሀገሬው ለበለጸገችና ጠንካራ ሀገሩ ምን ይጠበቅበታል? መንግሥት በኢትዮጵያ የሐሳብ ገበያን ባሕል ለማድረግ እየተከተላቸው ካሉ መንገዶች አንዱ ሀገራዊ ምክክር ነው። በመደመር መንግሥት መጽሐፍ (ገጽ 383) ላይ እንደሰፈረው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሐሳቦች በአንድ መድረክ ቀርበው፤ በምክክርና ውይይት ጎልብተው አሰባሳቢና አስማሚ ሆነው የሚወጡበት መድረክ ነው። ስለሀገር የሚያገባው ሁሉም አካል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ አዋጥቶና ተነጋግሮ መግባባት የሚፈጥርበት ምኅዳር መሆኑም ተገልጿል። ስለዚህ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሚከናወነው ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ኢትዮጵያውያን ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል። በሀገራዊ የምክክር ጉባዔው ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ጉባዔ ማካሄድ የሚችሉበትን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ በኩል፤ አንድነትና ኅብረትን በማጠናከር ልሂቃንና ሕዝብ ለአንድ ከፍ ላለ ዓላማ በአንድ ላይ እንዲቆሙ ያደርጋል። በዚህም ጥረቶች ሁሉ በአንድ አቅጣጫ እንዲፈስሱ ያደርጋል። በሌላ በኩል ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሰላምን በመፍጠር የመንግሥት ትኩረት፣ ሀብትና ጊዜ ሳይበታተን ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብቻ እንዲውል ያደርጋል (የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 403)። #እንመካከር! #በምክክር_ከሰፈር_እስከ_ሀገር_የተሻለ_ነገን_እንገንባ! #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 9302
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20077
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 13124
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 18875
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 5660
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ
Jun 26, 2026 4032
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት - የሕዝብ ድምጽ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ፍኖቷ ለአፍሪካ አርአያ ሆና አሳይታለች... የአፍሪካውያን ቀንዲል ናት። የክፉ ቀን መሸሸጊያቸው፣ የመከራ ጊዜ መጽናኛቸው፣ የነጻነት ተምሳሌትና የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በረጅም ዘመናት ታሪካዊ መስተጋብር የተፈጠረ የሀገረ መንግሥት መዋቅር ባለቤት ናት። በተፈጥሮ ጸጋዎች፣ ምድሯን ሰንጥቀው በሚያልፉ ወንዞቿ የምትታወቅ አገር ናት። የተለያዩ ማዕድናት በብዛት የሚገኙባት ከመሆኗም በላይ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህልና እሴቶች ሕብር ሠርተው፣ ተስማምተው የሚኖሩባት የታሪክ ማህደር ናት። ይሁን እንጂ ይህ ታሪካዊ ግርማ ሞገስና የነጻነት አርማነት፣ በውስጣዊ የፖለቲካ ጉዞዋ ውስጥ ካጋጠሟት መዋቅራዊ ስብራቶችና የሥልጣን ፍትጊያዎች ሊታደጋት አልቻለም። ለዘመናት በሀገሪቷ የሰፈነው የሥልጣን ሥርዓት የሰፊውን ሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ፣ በጥቂት የሕብረተሰብ ክፍሎችና ልሂቃን ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር። ይህ አካሄድ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አንዱን ሥርዓት በሌላው እየተካ፣ የተተካው አገዛዝ ደግሞ የባሰ ጭቆናን ይዞ የሚመጣበትን አዙሪት ፈጥሯል። ከብዙ መቶ ዓመታት የዘውድ አገዛዝ በኋላ የመጣው ወታደራዊ ሥርዓት፣ በመቀጠልም ለ30 ዓመታት ገደማ የዘለቀው የአንድ ወገን የበላይነት የሰፈነበት አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሀገሪቱንና ዜጎቿን ለከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርገው አልፈዋል። ይህ ዓይነቱ የመከራና የጭቆና ሰንሰለት ግን በ2010 ዓ.ም በተቀጣጠለው ሀገራዊ ለውጥ ተገርስሶ ወደ አዲስ የፖለቲካና የዴሞክራሲ ምሕዳር ተሸጋግሯል። ያለፉትን ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ጉዞ ስንመረምር፣ ሀገሪቷ ከአሮጌውና ከተለመደው የአፈና ሥርዓት ወጥታ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ አቅም ይዛለች። ይህ ወቅት የዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ መብት በተግባር የተረጋገጠበትና የሐሳብ ብዝኃነት የተስተናገደበት ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም የሥልጣን ማራዘሚያ ሆነው ያገለግሉ የነበሩ ዋና ዋና ተቋማት ገለልተኛና ነፃ ሆነው እንዲደራጁ መደረጉ የለውጡ ትልቁ ስኬት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት ውስጥ የለውጡ የመጀመሪያ ፍሬ የታየው በ2013 ዓ.ም የተካሄደው ስድስተኛው ምርጫ ነበር። በወቅቱ የነበሩትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተቆቁሞ ሕዝቡ ያሳየው የባለቤትነት ስሜት የዴሞክራሲ ናፍቆቱን በግልጽ ያሳየ ነው። ይህንን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ፣ በዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጥ የነቃ አስደናቂ የፖለቲካ ተሳትፎ አሳይቷል። ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ታሪካዊ መድረክ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን የማይናወጥ አቋም አሳይተውበታል። ከንጋት እስከ እኩለ ሌሊት ረጅም ሰዓታትን ተሰልፈው የተፈጥሮ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችንና ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በሙሉ በትዕግሥት በመሻገር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይህ ሂደት የሚያሳየው ሕዝቡ የሥልጣን ምንጭነቱን በተግባር የተረዳበትና ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነበት ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ነው። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞና የውስጥ መረጋጋት ሁልጊዜም በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተሉት ጉዳይ ነው። ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሚነሱ ሥጋቶችና የጂኦፖለቲካ ጫናዎች ቢኖሩም፣ ይህ በስኬት የተጠናቀቀው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቷን የውስጥ ጥንካሬና ሉዓላዊነት በተግባር ያስመሰከረ ሆኗል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነፃነትና በሰላም ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት፣ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ጉዳይ በራሷ ዜጎች ፍላጎት የመወሰን ሙሉ አቅም እንዳላት ለዓለም አሳይቷል። ምርጫው ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው። ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን በመስጠት የሀገሩን ሉዓላዊነትና አንድነት አስከብሯል። የፖለቲካ ሥልጣን የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ወይም በሁከት ሳይሆን በሕዝብ የላቀ ውሳኔ ብቻ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካለፈችባቸው የፖለቲካ ስብራቶች በላይ ከፍ ብላ እንድትቆም አድርጓታል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ተደማጭነትና የድርድር አቅም ከፍ የሚያደርግ ነው። የምርጫው ዝርዝር ስኬቶች ምን ምን ናቸው የሚለውን ስንመለከት፦ 👉የአፈሙዝ ድምፅንና የጽንፈኛ ዛቻን ያሸነፈው የሕዝብ ጽናት ግንቦት 24 ታሪካዊ ቀን ናት። በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ በየምርጫ ጣቢያው በነቂስ ወጥቶ ድምፁን የሰጠው ሕዝብ ያሳየው የነጻነት፣ የሉዓላዊነት እና የጽናት ማረጋገጫ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍና ሕዝቡን ለማስፈራራት የተቃጡ የአፈሙዞች ድምፆችና የሁከት ዛቻዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ሕዝብ ከመምረጥ አላፈገፈገም። መራጮች የጽንፈኛ ኃይሎችን ዛቻ ወደ ጎን ትተው፣ የአካላቸውን ሕመም፣ የበሽታን ሥቃይ፣ አልፎ ተርፎም የወሊድ ምጥንና የቅርብ ዘመድ ሞት ያመጣውን ጥልቅ ሐዘን በሕሊናቸውና በሥጋቸው ተሸክመው ነበር ረጅሙን ሰልፍ ተሰልፈው ይበጀኛል ያሉትን በካርዳቸው የመረጡት። ይህ የሚያሳየው እውነት ለኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ሰላማቸውን የሚገዙበት፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበትና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን በገዛ እጃቸው የሚወስኑበት ብቸኛ የነጻነት አዋጃቸው መሆኑን ነው። ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ በሆነ መንገድ፣ በኃይል ወይም በሁከት ሥልጣን ለመያዝ ምኞትና የቆየ የሥልጣን ናፍቆት ላላቸው ወገኖች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግልጽና የማያሻማ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የኃይልና የሁከት አካሄድን እንደማይቀበል፣ በድምፅ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሕጋዊ ሥርዓትን ለማፅናት እንደሚታገል አረጋግጧል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በአፅንኦት ሲያነሱ፤ "የዘመናችን ዲሞክራሲ አስተምህሮቱ ሰላምና ዕድገት፣ ቋንቋው ደግሞ መምረጥና መመረጥ ብቻ በመሆኑ የፖለቲካ ቅኝታችሁንና አካሄዳችሁን ከዚሁ ስልጡን መስመር ጋር ማስተካከል ይበጃችኋል። ካሁን በኋላ የሕዝብ ድምፅ ያልጎበኘው፣ የምርጫ ካርድ ያልዳሰሰው የፖለቲካ ሥልጣን መያዣ መንገድ በኢትዮጵያ ዝግ መሆኑን እነሆ እንዳየነው መሠረት የጣለ ስለሆነ ይህኑ ስልጡን መንገድ ለመቀበል የማትፈቅዱ ሁሉ ግን ግፋ ቢል የዘመናችን የፖለቲካ ድርሳን ሲጻፍ ልትሆኑ የምትችሉት የግርጌ ማስታወሻ ብቻ ነው።" ብለዋል። ስለሆነም ከዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕጋዊ አካሄድ ውጭ የሚደረግ ሙከራ የጥፋት ተዋናይ ከመሆን ባሻገር ለሀገር የሚያተርፈው አንዳች ነገር እንደሌለ በዚህ ስሑት መንገድ ላይ የሚገኙ አካላት ሊገነዘቡ ይገባል። 1. ምርጫው በቁጥሮች ሲገለጽ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጉልህ የሚጠቀሱ አኃዛዊ መረጃዎች አሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ እንደገለጹት፤ ቦርዱ ከ120 ሚሊዮን በላይ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በውጭ ሀገር አሳትሞ ካስመጣ በኋላ፣ ከምርጫው 4 ቀናት በፊት በሀገሪቱ ባሉት ከ52 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች በታማኝነትና በጥንቃቄ ማድረስ ተችሏል። ይህንን እጅግ ግዙፍና ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሥራ ሙሉ በሙሉ ያከናወኑት የቦርዱ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ብቻ መሆናቸው ተቋማዊ አቅሙ ምን ያህል እንደጎለበተ ማሳያ ነው። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ እንደተናገሩት፤ የቦርዱ ሠራተኞችና የምርጫ አስፈጻሚዎች በዕረፍት ቀናትና በሌሊት በመጋዘን ውስጥ ጭምር እያደሩ የቁሳቁስ ማሸግ ሥራዎችን በትጋት አከናውነዋል። ሩቅና ተደራሽነታቸው አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳቁሶችን በእግር፣ በእንስሳት ጀርባና በጀልባ ጭምር በማጓጓዝ፣ ወንዞችን ለመሻገር የራሳቸውን የፕላስቲክ ጀልባ ሠርተው ሀገራዊ አደራቸውን ተወጥተዋል። በድምፅ መስጫ ቀን ሥራቸውን ከንጋት እስከ ንጋት በልዩ ብርታት ፈጽመዋል። ይህ ልብ የሚነካ እውነታ የሚያሳየው፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር የሚደረገው ጥረት ከፍተኛ ዋጋ ያለው የተናጥልና የጋራ ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን ነው። ሰፊ ተሳትፎ፦ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 80 የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል። 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲና የግል ዕጩዎች ተወዳድረዋል። ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲዎች ፖሊሲዎቻቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበት የክርክር መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ፓርቲዎች ከምርጫው ውጭም ራሳቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበትን ባህል ያዳብራል። የመራጮችና አስፈጻሚዎች ቁጥር፦ በአጠቃላይ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ምርጫውን ለማስፈጸም ከ350 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ታዛቢዎችና ወኪሎች፦ ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያሰማሯቸው ከ60 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ እንዲሁም 63 የአፍሪካ ኅብረት እና 26 የኢጋድ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል። ለመራጩ ሕዝብ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት መስፈርቱን ላሟሉ 169 ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። እንዲሁም 21 ሚሲዮኖችና አንድ የውጭ ሀገር የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ምርጫውን ተመልክተዋል። የአየር ሰዓት አጠቃቀም፦ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ነፃ የአየር ሰዓት የማግኘት መብት ስለነበራቸው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 752.5 ነፃ የሬዲዮ ሰዓት፣ 57.5 ነፃ የቴሌቪዥን ሰዓትና 576 የጋዜጣ ኮለምን በዘመናዊ የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ተደልድሎ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። መገናኛ ብዙኃን፦ 73 የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃንን የወከሉ 1 ሺህ 827 የሀገር ውስጥና 45 የውጭ ጋዜጠኞች ለዘገባ ሥራ ተሰማርተዋል። የሕግ ማሻሻያ እና ዲጂታላይዜሽን፦ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ተሻሽሎ በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 ተተክቷል። ቦርዱ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር፦ ለመጀመሪያ ጊዜ በገለልተኛ ባለሙያዎች የሚመራ፣ እያንዳንዳቸው 2 ሰዓት የሚወስዱ 19 የክርክር መድረኮች በቦርዱ ተዘጋጅተዋል። 14ቱ በአማርኛ፣ 5ቱ በክልል ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ አፋርኛ) ተካሂደው በሰባት መገናኛ ብዙኃን በፕራይም ታይም ተላልፈዋል። አካታችነት፦ 28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ከ20 ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ተደርጓል። የቅሬታ አፈታትና ክትትል፦ የቅድመ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት (Early Warning System) ተዘርግቷል። 663 የምርጫ ክልል ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎችና ልዩ የአጣሪ ጉባኤ ተደራጅተው 129 አቤቱታዎችን መርምረዋል። የሕግ ጥሰት በተገኘባቸው ጣቢያዎች ውጤት እንዲሰረዝ እና በፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊና የወንጀል ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል። 2. ጠንካራና ገለልተኛ ተቋም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የሀገር ውስጥ አቅም ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠነ ሰፊ ተቋማዊና ሕጋዊ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ከመሆኑም በላይ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድ ሀገራዊ አቅምን በተግባር ያሳየ ነበር። የዚህ ምርጫ ትልቁ ትርፍ ጠንካራና የማይናወጡ ብሔራዊ ተቋማትን መገንባት መቻላችን ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳየው ፍጹም ገለልተኝነት፣ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ብቃት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተግበር አቅም፣ ተቋማት ከግለሰቦችና ከፖለቲካ ጫና በላይ መሆናቸውን ያስመሰከረ ነው። ይህም ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር አስተማማኝ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ነው። ለምርጫው ስኬት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮችን በትዕግሥት በማስተናገድ፣ ብቁ አስፈጻሚዎችን በማሰማራትና ሂደቱን በታማኝነት በመምራት ረገድ ቦርዱ አድናቆት የተቸረው ሥራን ፈጽሟል። የሠራተኞቹ ቀንና ሌሊት መትጋት እንዲሁም በግንባር ቀደምትነት የሚመሩት አመራር አባላት ያሳዩት ቁርጠኝነት የላቀና ለሀገር ኩራት የሆነ ተግባር ነው። በዚህ ምርጫ ውስጥ ትልቁን ትኩረት የሳበውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ላይ የዋለው የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት ነው። ይህ ዘመናዊ አሠራር ለምርጫው ከተመዘገቡ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መካከል ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በአካል መጓዝ ሳይጠበቅባቸው፣ ባሉበት ቦታ ሆነው በነፃነት እንዲመዘገቡ ዕድል ፈጥሯል። ቴክኖሎጂው የመራጮችን ማንነት በፎቶግራፍ ጭምር በማረጋገጡ በድምፅ መስጫ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ ግድፈቶችንና ማጭበርበሮችን በከፍተኛ ደረጃ መከላከል ተችሏል። የዚህ ሥርዓት ዋነኛውና ትልቁ ድል ደግሞ ሙሉ በሙሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለጸገ መሆኑ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የዚህን የቴክኖሎጂ ስኬት አስፈላጊነት ሲያብራሩ፤ "እነዚህ የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓቶች በውጭ ሀገር አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች የለሙ ሳይሆን በራሳችን ወጣት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተገነቡ ናቸው። ይህም ተቋሙን ከውጭ አቅራቢዎች ጥገኝነት ነፃ በማድረግ በራሱ አቅም እንዲቆምና ለወደፊቱ ማሻሻያዎችን በራሱ እንዲያከናውን መሠረት ጥሏል።" ይህ እርምጃ ቦርዱ የውጭ የቴክኒክ ጥገኝነትን በመቀነስ የሀገር ውስጥ አቅምን ለመገንባትና የሉዓላዊነትና የደኅንነት ዋስትናን በራስ ቴክኖሎጂ ለማረጋገጥ የቻለበትን ስትራቴጂካዊ አካሄድ በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም በስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በውጭ ዜጎች ይሠራ የነበረው የቴክኒክ ድጋፍ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መተካቱ የተሳካ የእውቀት ሽግግር መኖሩን አሳይቷል። 3. ሕጋዊ ማሻሻያዎች፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ዴሞክራሲ እውነተኛ ትርጉም የሚኖረው ዜጎች፣ በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ያለ ፍርሃትና ጫና፣ ደኅንነታቸው ተጠብቆ በፖለቲካዊ ሂደቶች እኩል መሳተፍ ሲችሉ ነው። ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በታዛቢነት በመሳተፍ፣ ሴቶች የዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዲጠቀሙና በሂደቱ በንቃት እንዲሳተፉ አስችሏል። ቦርዱ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ ጾታዊ ጥቃትና ትንኮሳን ለመከላከል የሚያስችል ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። ከዚህም በላይ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግብረ ኃይል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አቋቁሟል። በተጨማሪም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ቀድሞ የነበረው አዋጅ ቁጥር 1162/2011 በአዋጅ ቁጥር 1394/2017 እንዲተካ የተደረገ ሲሆን፣ ቦርዱ ይህንን መነሻ በማድረግ 10 አዳዲስ መመሪያዎችን አጽድቋል። በነዚህ ማሻሻያዎች ውስጥ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደ ዋና መርህ የተወሰደ ነው። 4. ፈተናዎችን መጋፈጥና ገለልተኝነትን ማስከበር ይህ ሁሉ ስኬት ግን ያለ ፈተና አልመጣም። ምርጫው በተያዘለት ጊዜ አይካሄድም የሚሉ ጥርጣሬዎችና የተሳሳቱ መረጃዎች ተቋሙን ፈትነውት ነበር። ሆኖም ቦርዱ ጫናዎችን በመቋቋም ሕግና መርህን ብቻ ተከትሎ በመሥራት ምርጫውን ለስኬት ማብቃቱን ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ያረጋግጣሉ። ቦርዱ በምርጫው ወቅት የተቋሙን ነፃነት ከማንኛውም ዓይነት ጫናና ጣልቃገብነት በመጠበቅ በሕግና በመርህ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ ቆይቷል። በምርጫ አፈጻጸም የአሠራር ግድፈቶች እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች በድምፅ መስጫው ቀን ጭምር አስፈጻሚዎችን አሰናብቷል፤ በምርጫ ውጤቶች ላይም ውሳኔ ሰጥቷል። ይህም ቦርዱ ለሕግ የበላይነትና ለምርጫ ታማኝነት ያለውን ጽኑ አቋም ያሳያል። የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአንድ ተቋም ወይም በጥቂት ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች በፀሐይና በዝናብ ሳይበገሩ በትዕግሥት የሰጡት ድምፅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች (እንደ አፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ) እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው። 5. የምርጫው ግልጽነትና ዓለም አቀፍ እውቅና የምርጫውን ታሪካዊ ሂደትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥና የውጭ አካላት በሰፊው ተሳትፈዋል። ሂደቱን ለመዘገብ 73 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1 ሺህ 827 ጋዜጠኞች የዘገባ ሥራቸውን አከናውነዋል። ከ260 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እና ከ64 ሺህ በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች በሂደቱ ላይ ተሳትፈዋል። በተለይም በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 60 ሺህ 277 ታዛቢዎችን በማሰማራት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን፤ 169 ድርጅቶች ደግሞ ለመራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል። በአህጉር ደረጃም የኬንያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እና 26 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ታዛቢዎች ሂደቱን በታዛቢነት ተከታትለዋል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫው ግልጽ፣ አሳታፊና ተዓማኒ ሆኖ በስኬት መካሄዱንም አረጋግጠዋል። 👉የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች ምስክርነት የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ፣ የምርጫው ዕለት ሰላማዊ፣ ሥነ ሥርዓት የሰፈነበት እና ግልፅነት የታየበት መሆኑን ነው ያረጋገጡት። በቴክኖሎጂ የታገዘ የመራጮች ምዝገባ መተግበሩ ወጣቶችን መሳቡን፣ ዜጎች በትዕግሥት ሰልፍ በመያዝ ጥልቅ ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን፣ የሎጂስቲክስ ዝግጅቱ የተሟላ መሆኑንና የምርጫ ሰዓት መራዘሙ የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል። በመስተንግዶ ረገድም ወንበሮችና የምግብ አቅርቦቶች መኖራቸው ረጅሙን ሰልፍ ታጋሽ እንዳደረገውና ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱን አረጋግጠዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት "ቅኝ ግዛትን በአንድነት የተከላከለች Couch፣ ለአፍሪካ ነፃነት የቆመች እና የአህጉሪቱ ዋና ከተማ በሆነች ሀገር ውስጥ የተደረገው ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ሊኮሩ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድም በሕዝቦች መካከል ያለውን የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ውይይት ይበልጥ ማሳደግ፣ ወደ ኋላ የተተዉ የሚሰማቸውን አካላት ወደ መድረኩ በማምጣት እና አካታችና የተባበረች ኢትዮጵያን መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል። በሌላ በኩል፣ የኡጋንዳ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ (IGAD) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በሰባት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 28 ጣቢያዎችን በመጎብኘት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አውጥቷል። ቡድኑ ጣቢያዎቹ በሰዓታቸው መከፈታቸውን፣ በቂ ቁሳቁስና አስፈጻሚዎች እንደነበሩ፣ የሳጥኖች አስተሻሸግ የድምፅ ምስጢራዊነትን ያረጋገጠ መሆኑንና የድምፅ አሰጣጡ ያለምንም መሰናክል በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመታዘብ ምስክርነቱን ሰጥቷል። ለአረጋውያን፣ ሕፃናት ለያዙ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ መሰጠቱንና መራጮች የሚቀመጡባቸው ወንበሮች መኖራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን በማዘጋጀትና በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዳደራዊና ኦፕሬሽናል አቅም ማሳየቱን አጉልቷል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ለሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት ያደነቀ ሲሆን፣ "ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ በተለይም የምርጫ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ አካታችነትን እና ተዓማኒነትን ለማሳደግ የተነደፉ ዋና ዋና ቴክኖሎጂያዊ እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተስተዋሉበት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲል ቡድኑ ምስክርነታቸውን በአፅንኦት የገለጹት። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ "ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ይበልጥ እንዲጠናከርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲመዘገብ አብረን ለመሥራት ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።" ሲሉ ነው የተደመጡት። 6. የምርጫው ውጤት፣ የሕዝቡ ጽናትና የአሸናፊው ፓርቲ ከባድ ሸክም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎችም በምክር ቤቶቹ ወንበሮችን ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) 13፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ስድስት፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሦስት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሦስት፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሦስት፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ሁለት ወንበሮችን አሸንፈዋል። በሌላ በኩል ኦብነግ፣ ጉህዴን፣ አርጎባ አንድነት ጀበርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ፣ ኅብረት ለዴሞክራሲና ለነጻነት፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ የጌዴዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እያንዳንዳቸው አንድ ወንበር ሲያገኙ 8 የግል ተወዳዳሪዎችም ምክር ቤት ለመግባት አሸንፈዋል። ይህን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች ጊዜያት ለየት የሚያደርገው ታላቅ ክስተት፣ መራጩ ሕዝብ በታጋሽነት ተሰልፎ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ወደር የለሽ ጽናት ነው። በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ይህንን የሕብረተሰብ አደራ "አሸናፊው ፓርቲ ትልቅ ሀገራዊ ሸክም የተጣለበት መሆኑን ብልፅግና ፓርቲ በሚገባ ይረዳል። ፓርቲያችን በማኒፌስቷችንና በአጠቃላይ በምርጫ ቅስቀሳችን ወቅት ለሕዝብ ቃል የገባናቸውን በተግባር ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል" ብለዋል፡፡ 👉የፉክክርና የትብብር ሚዛን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር በቀጣይነት ሊመራበት የሚገባው ስልጡን መስመር በፉክክርና በትብብር መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ነው። ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሀገር ግንባታ ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር በብሔራዊ ጥቅም ላይ በትብብር ለመሥራት ያለው አቋም የጸና መሆኑን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በሰጡት አስተያየት፤ "ባለፉት ዓመታት የጀመርነውን በፉክክርና በትብብር መካከል ሚዛን ጠብቆ የሚሄድ ጥረታችንን በቀጣይ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ሕዝቡን በማሳተፍ፣ በየጊዜው የሕዝቡን ግብረ መልስ በመስማት፣ ያንን እንደ ግብዓት ተጠቅመን የእቅድ አካል አድርገን ወደ ተግባር ለመተርጎም በቁርጠኝነት እንንቀሳቀሳለን።" ብለዋል። ይህ ዕይታ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሕዝብን ድምፅና ግብረ መልስ በየጊዜው የሚያዳምጥ፣ እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሀገር ጥቅም በጋራ የመሥራትን ስልጡንና አካታች የአሠራር ሥርዓት መከተል መጀመሩን ያሳያል። 7. ዴሞክራሲና ምርጫው የሚገለጽባቸው አራቱ ምሰሶዎች ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ማለት አማራጭ የሌለው የህልውና ጉዳይና የሁለንተናዊ ብልጽግናችን መሠረት ነው። ብዝኃነትን በአግባቡ ማስተናገድ፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና ጠንካራ ሀገር መገንባት የሚቻለው በዴሞክራሲያዊ ምሰሶዎች ላይ በመመሥረት ብቻ ነው። መንግሥት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሠራ ቆይቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ የሲቪል ማኅበራት ሚና የማይተካና አዎንታዊ ሚና አላቸው። መራጩን ሕዝብ ከማስተማር፣ ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም ከማስቻል፣ እስከ ሰላም እሴት ግንባታና በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የዜጎችን ባለቤትነት ከማረጋገጥ አኳያ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ እንደገለጹት፣ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነው። አንደኛው ምሰሶ፦ ምርጫ የሰላም ዋስትና መሆኑን መረዳት ነው። ሕዝቡ ልዩነቶችን በፀብና በአምባጓሮ ከመፍታት አዙሪት ተላቆ፣ በሰላማዊ መንገድ የመሻገር ባህልን መርጧል። በነቂስ ድምፁን መስጠቱ ኋላ ቀር የአመፃ መንገድን ለሚከተሉ ሁሉ "በቃችሁ" የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ሲሆን፣ የሰፊው ሕዝብ ማዕበላዊ ድምፅ ከአሮጌው የብጥብጥ ባህል መላቀቅ እንደሚፈልግ ማረጋገጫ ነው። ሁለተኛው ምሰሶ፦ የምርጫ ውግንና ከሕዝብ ጋር መሆኑን ማወቅ ነው። የምርጫ ተዓማኒነትና ክብሩ የሚገለጠው ሥልጣን ከሚመነጭበት ከሰፊው ሕዝብ ሉዓላዊ መብትና ፍላጎት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ነው። ምርጫ ከሚሰጠው ኃላፊነት በላይ ለእያንዳንዱ ዜጋ የዕለት ተዕለት ሕይወት መሻሻልና ከሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ሕዝቡ በትክክል ተገንዝቧል። ሦስተኛው ምሰሶ፦ የምርጫው የፖሊሲ ሐሳቦችና አማራጮች ከፍታ የታየበት ነው። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የክርክር መድረኮች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያነሷቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሕዝቡ በጥንቃቄ አዳምጧል። እነዚህ ሐሳቦች ለሀገር ዕድገት፣ ለጠንካራ መንግሥትና ለሰከነ የፖለቲካ ባህል ግንባታ መሠረት እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕሊና ማስረፅ፣ በሰነድ በማዘጋጀትም መተግበር ይገባል። አራተኛው ምሰሶ፦ ምርጫ እንደ ማኅበራዊ ሀብት፤ ምርጫ ፖለቲካዊ ኩነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማኅበራዊ ሀብት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የዚህን ማኅበራዊ እሴት አንድምታ ሲያብራሩም "ሕዝባችን ስለ ኢትዮጵያዊ ቀናነቱና ፍቅሩ ጩኸቱን ሳይሆን የምርጫ ካርድ ድምፁን፣ ስላቅና ሃኬትን ሳይሆን ትሑትነቱን፣ የትኛውንም የፖለቲካ ሐሳብ ቢያራምድ እንኳን ማኅበራዊና ሀገራዊ ፍቅሩን ከጎኑ ላለው ወገኑ አለመንፈጉን ያየንበት እጅግ የተዋበ መድረክ ነበር። ስለዚህ የኢትዮጵያ ምርጫ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ባልተናነሰ ሁኔታ ማኅበራዊ ፋይዳውም ከፍ ያለ ትልቅ የማኅበራዊ መሠረትን የሰጠው ነው።" ብለዋል። 8. የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ታሪካዊ ሚና፦ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስብራቶች የመፈወስ ዕድል ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትና የፖለቲካ ሥርዓት ጉዞዋ ውስጥ በርካታ አኩሪ ታሪኮችን ብታስመዘግብም፣ በሂደቱ ውስጥ የተፈጠሩና ዛሬም ድረስ ሀገራዊ አንድነቷን፣ ሰላሟንና የዴሞክራሲ ግንባታዋን እየተፈታተኑ ያሉ ሥር የሰደዱ የፖለቲካ ስብራቶች መኖራቸው አይካድም። እነዚህን ለዘመናት የዘለቁ ስብራቶች በመጠገን ረገድ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሻግር የሚችል ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ ዕድል ይዞ መጥቷል። ምርጫው በበሰለና አካታች መንገድ በመመራቱ በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ጉልህና አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ የሚችልባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች አሉት። እነዚህም፦ የቅቡልነት ስብራትን ማከም፦ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመንግሥታት ሥልጣን አመጣጥ አብዛኛውን ጊዜ ከኃይል ፖለቲካ ወይም ሙሉ በሙሉ ነፃ ካልሆኑ ምርጫዎች ጋር የተያያዘ በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕዝባዊ ቅቡልነት ማጣት ለግጭቶች መነሻ ሲሆን ቆይቷል። ይህ ምርጫ ነፃና ታማኝ ሆኖ መካሄዱ አሸናፊው አካል ከሕዝብ የሚሰጠው እውነተኛ የሥልጣን አደራ እንዲኖረው ያደርጋል፤ ይህም በገዥው አካልና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን በማደስ ረገድ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የሰላማዊ ሥልጣን ሽግግር ባህልን መገንባት፦ ሥልጣንን በአፈሙዝ የመያዝ ልምድ ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ለድቀት የዳረጋት መሆኑ ብዙ ትምህርት ሰጥቷል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሁሉም ወገኖች የሕዝብን ድምፅ አክብረው የሚቀበሉበት ድባብ መፈጠሩ ምርጫን ብቸኛ የሥልጣን መያዣና መልቀቂያ መንገድ የማድረግ አዲስና ጤናማ የፖለቲካ ባህል በሀገሪቷ ውስጥ እንዲለመድ ያደርጋል። በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ ማደስ፦ ሕዝቡ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤቶችና የዴሞክራሲ ተቋማት ባሉ ገለልተኛ መሆን በሚገባቸው ተቋማት ላይ ያለው እምነት መሸርሸሩ ሌላው ስብራት ሲሆን፣ ይህንንም ምርጫ በስኬትና በገለልተኝነት ማካሄድ መቻሉ የተቋማቱን ነፃነትና ብቃት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ ዜጎች በሀገሪቷ የሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት መልሶ እንዲያገግም ያደርጋል። ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፦ አካታች የሆነ ምርጫ ማካሄድ መሣሪያ ያነሱ ወይም በሰላማዊ መንገድ የሚያምፁ የፖለቲካ ኃይሎች ቅሬታቸውን በሕዝብ ድምፅ እንዲፈትሹ በር ይከፍታል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶች ለመፈወስ የራሱ አሻራ ሊያኖር የሚችለው ሂደቱ ፍትሐዊ፣ ግልጽና በርካታ የፖለቲካ ኃይሎችን ያሳተፈ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በንቃት የተሳተፈበት በመሆኑ ነው። በዚህም ምርጫው በተሳካ ሁኔታ መካሄዱ በራሱ ወደ ሰፊው ብሔራዊ ምክክር ለመሻገር እንደ ትልቅ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ማጠቃለያ፦ ምርጫው ለአፍሪካ ዴሞክራሲ የብርሃን ፍኖት አፍሪካ በፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፣ በወታደራዊ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትና ኢ-ሕገመንግሥታዊ መንገድ መምራት፣ የመንግሥት ግልበጣዎች እየተፈተነች ባለችበት በዚህ የታሪክ ምዕራፍ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊና ስልጡን መንገድ ምርጫዋን ማጠናቀቋ ለአህጉሪቱ አዲስ ፍኖተ ዴሞክራሲ ሆና እንድትወጣ አድርጓታል። 'የአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካውያን መፍትሔዎች' የሚለውን መርህ በተግባር በማሳየት፣ የራሳችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በራሳችን አቅም መቅረጽ እንደምንችል ለዓለም አሳይተናል። በዚህ አስቸጋሪ አህጉራዊ ድባብ ውስጥ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከልና የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና ፍትሐዊ መንገድ በስኬት ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ለጫናዎች ሳትበገር፣ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ መድረክ ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል። የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ አህጉሪቱ ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዲሞክራሲ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ገልጸው፤ ሰላምና ልማት ሊመጡ የሚችሉት በጠመንጃ ኃይል ሳይሆን ሕዝብ በነፃነት የራሱን መሪ በሚመርጥበት ስልጡን መንገድ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም፦ "አህጉራችን ከዲሞክራሲ ውጭ ሌላ ምርጫ የላትም። ወደፊት ለመራመድ፣ ዕድገትን ለማረጋገጥና በተለይም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ዴሞክራሲ ብቻ ነው" ሲሉ በአፅንኦት ጠቅሰዋል። በአጠቃላይ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ኢትዮጵያ ተቋማዊ አቅሟንና ሕጋዊ መሠረቷን በማጠናከር ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የተሻገረችበት እና የጋራ የትብብር አቅምን ያሳየችበት አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል። ለዚህም ስኬት በየሚናቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች፣ ሲቪል ማኅበራት፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአፍሪካ ኅብረትና የኢጋድ ታዛቢ ቡድኖች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዲሁም ሀገር በቀል ታዛቢ ድርጅቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል። በምርጫው ወቅት የተሰጠው የሕዝብ አመኔታና ድምፅ ለተመራጮች ትልቅ አደራና ኃላፊነትን ጥሏል። ያሸነፉ ፓርቲዎችና ዕጩዎች ይህንን ታሪካዊ አደራ በመሸከም ለሕዝብ ፍላጎት ቅርብ የሆነ አገልግሎት በመስጠት፣ በታማኝነት፣ በቅንነትና ንጹሕ በሆነ ሕሊና በመሥራት የሕዝቡን ተስፋ ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ግዴታ አለባቸው። የምርጫው ትልቁና የመጨረሻው ስኬት የሚለካው በተመራጮችና በሕዝብ መካከል በሚገነባው መተማመን፣ በሚረጋገጠው ዘላቂ ሰላምና ለሁሉም ተጠቃሚነትን በሚያሰፍነው ሀገራዊ ዕድገትና ብልጽግና ብቻ ነው።