ቀጥታ፡

የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ

አዳማ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

በዚህ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንና የነበሩ ድክመቶችን በመመርመር፣ የ2019 የሥራ ዕቅድ አቅጣጫን የሚያመላክት ውሳኔ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም