ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዝዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከቤኒን ፕሬዝዳንት ጋር በወል ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።




‎የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ እድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት አለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም