የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት - ኢዜአ አማርኛ
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦የዘንድሮ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።
ክለቡ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ከማለዳው ጀምሮ በተዘጋጀ ስነ ስርአት በተሽከርካሪ የታገዘ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በአቀባበል ስነ ስርአቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ በመሆን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።