በ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ችለናል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ችለናል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 350 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገቢ መሰረትን በማስፋትና የሚሰበሰብ ገቢ ፍትሀዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሰበሰብ በማድረግ በኩል ሰፊ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
በበጀት አመቱ የተሰበሰበው ገቢም ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ116.3 ቢሊየን ብር ወይም 50 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል።