ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ አቀባበል አድርገዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የቤኒን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።
በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።