ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በድሬዳዋ የወባ በሽታን ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ውጤቶች ተመዝግበዋል
May 3, 2026 5
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ አስተዳደር ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት በሽታውን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ አመራሮች ገለጹ። ድሬዳዋ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧና በሞቃታማ የአየር ንብረቷ ምክንያት ለወባ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዷ መሆኗ ይታወቃል። ይህንን ተጋላጭነት ለመቀነስና የህዝቡን ጤና ለመጠበቅም የተለያዩ የመከላከያ ስራዎች ሲከናወኑ የቆዩ ሲሆን በዚህም ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። በሳቢያን ወረዳ የጎሮ ጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጅ የጤና መኮንን እንዳለማው እርቅይሁን እንዳሉት፤ ለወባ በሽታ መንስኤ የሆኑ የትንኝ መራቢያ አካባቢዎች በተቀናጀ መንገድ በማዳረቅና ኬሚካል በመርጨት ወባን በተጨባጭ መከላከል ተችሏል።   በተለይም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ተገቢውን የመከላከያ ትምህርት በመስጠት በመከላከሉ ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራት ፍሬያማ ሆነዋል ብለዋል። ነዋሪው ጊቢውንና አካባቢውን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ አካባቢዎችን በማፋሰስና በማዳረቅ እያከናወነ የሚገኘው ስራ በአብነት የሚጠቀስ መሆኑን በመግለፅ። ከመከላከሉ ጎን ለጎን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በወባ በሽታ ለተያዙ 2ሺህ 900 ሰዎች ተገቢውን ህክምና በመስጠት የማዳን ስራ መሰራቱን አንስተዋል። አምናና ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተሰሩ ስራዎች በወባ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ማስቻሉንም ገልጸዋል። የመልካ ጀብዱ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሙያ ቤተልሄም እንዳለ በበኩላቸው፤ ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተከናወኑ ተግባራት የበሽታውን ስርጭት እንዲገታ አስችሏል። በተለይም የትንኝ መራቢያ ወንዞችና የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ላይ ኬሚካል ርጭት በማካሄድ አካባቢዎችን ከስጋት ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ለታመሙትም አስፈላጊው ህክምና እየተሰጠ መሆኑን በማስታወስ አንድም በወባ የተያዘ ሰው በጤና ጣቢያው እንደሌለ በመግለፅ። ወባን ለመከላከል በተሰሩ ስራዎች የመጡ ለውጦችን ይበልጥ በማሳደግ ከወባ ነፃ የሆነ መልካጀብዱን ዕውን ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው የወባ በሽታን በመከላከልም ሆነ በየጤና ተቋማት በወባ ለተያዘ ሰው እየተሰጠ የሚገኘው ህክምና አበረታች ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል እያደረገ የሚገኘው ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ እና በሁሉም ጤና ተቋማት የፀረ ወባ መድኃኒት እና ፈጣን መመርመሪያ ኪት እንዲሟላ መደረጉ የበሽታውን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ አስችሏል ብለዋል። በወባ በሽታ ህይወቱ ያለፈ አንድም ነዋሪ አለመኖሩን ጠቅሰው ይህን ውጤታማ ጉዞ በማስቀጠልና ድሬዳዋን ከወባ ነፃ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 15
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ‎ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
በጠቅላላ ምርጫው የፖሊሲ አማራጮቻችንን በተለያዩ ሚዲያዎች ሳንገደብ ማቅረብ ችለናል 
May 3, 2026 53
ሰመራ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በዘንድሮው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ያለ ምንም ገደብ ለህዝብ ማቅረብ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) ሊቀ መንበርና የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ ገለጹ። ለዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦቻቸውንና ማኒፌስቶዋቸውን ለህዝብ እንዲያስተዋውቁ የመገናኛ ብዙኃን እኩል የአየር ሰዓትና ሰፊ መድረክ መመደባቸው ይታወቃል። ይህም ሚዲያዎች ብዝሃነትን በማስተናገድ ረገድ ያላቸውን ሚና በተግባር እያሳዩ መሆኑን አመላካች ሆኗል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ(አነግፓ) ሊቀ መንበር አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ፤ በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ምህዳሩ ከቀደምት የምርጫ ዘመናት የተለየና የተሻሻለ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ለክልል ተወዳዳሪዎች አምብዛም ሽፋን ያልሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ጊዜ ግን አማራጭ ሐሳቦቻቸውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ አውታሮች እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፓርቲያቸው ከሰባት በላይ መድረኮችን በመጠቀም የመወዳደሪያ ሐሳቡን ማቅረቡን ገልጸው፤ በዚህም የመወዳደሪያ ምህዳሩ የሰፋ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ ወቅት በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች በነፃነት ቅሰቀሳ በማድረግና በማሰተዋወቅ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል። የአፋር ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫውን ሂደት በመገምገም አስፈላጊ የሆኑ የእርማት እርምጃዎችን የሚጠቁም ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ኮሚቴ ያዋቀረው ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያለውን ድርሻ ለመወጣት እንደሆነም አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
May 3, 2026 47
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከመቻል ጋር ይጫወታል። ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ451 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ23ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ባህር ዳር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ እና ከወራጅ ቀጠና ስፍራ ለመራቅ ይጫወታል። ተጋጣሚው መቻል በበኩሉ ካሸነፈ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። በሌላኛው መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻው 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሸገር ከተማ በ44 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት 16 የሊግ ጨዋታዎች ያላሸነፈው አርባምንጭ ከተማ ዛሬ ከተሸነፈ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ይረጋገጣል። በ23ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 የረታው ሸገር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከልደታ ክፍለ ከተማ ይጫወታሉ። ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ልደታ ክፍለ ከተማ በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በ23ኛ ሳምንት በሸገር ከተማ የተሸነፈው ሲዳማ ቡና ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይጫወታል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያላሸነፈው ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እና ከወራጅነት ስጋት ለመላቀቅ ይጫወታል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ60 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ 60 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በ23 ግቦች ቀዳሚ ስትሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በ18 ግቦች ትከተላለች።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
May 3, 2026 50
ጅማ ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስና ተጨባጭ መሆኑ ተመላከተ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመከተል ላይ ትገኛለች። ስትራቴጂው በዋናነት ዘላቂነት ባለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና በፈጠራ የታገዙ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልምዶችን በማስፋፋት ላይ ያተኩራል። ለአብነትም የአፈር እና ውሃ ጥበቃን ማጠናከር፣ ድርቅ የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መጠቀም እና ከበካይ ጋዝ ነፃ የሆኑ የኃይል ምንጮችን ማስፋፋት የስትራቴጂው አካላት ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጉዞ ከበካይ ጋዝ ልቀት የጸዳ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የያዘችው ግብ አካል ነው። ለተግባራዊነቱም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ ዘመናዊና አረንጓዴ ትራንስፖርት እንዲሁም የግብርና እና ተፋሰስ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በኢትዮጵያ የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት (GGGI) ዳይሬክተር እና በኢትዩጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ጋር ቆይታ አድርጓል። የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ሁሉን አቀፍና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ ኢኮኖሚን እንዲገነቡ እገዛ ያደርጋል።   በኢትዮጵያ የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ተቋቁማ ያስመዘገበችው እድገት ቀጠናውን በልማት ለማስተሳሰር ተጨማሪ እቅም እየፈጠረ ነው። የአረንጓዴ የኢኮኖሚ ልማቱም የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የስራ እድል እንዲስፋፋና ኢንቨስትመንትን ለመሳብም ተደማሪ አቅም በመፍጠሩ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ በታዳሽ ኃይል ልማት በውሃ፣ በነፋስና ጸሐይ ላይ የሚደረጉት ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችም በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚያስችላት ተናግረዋል።   በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ከፈለኝ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ እድገትን መገንባት እንደሚያስችላት ጠቁመዋል። ለዚህም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ተከላና የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ምርታማነት እንዲጨምር ማገዛቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የሰሃራ በረሀ መስፋፋትን ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተደቀነውን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አየገነባች መሆኗን አስተባባሪው ገልጸዋል። አትዮጵያ ቀጣናውን በጋራ ልማት ለማስተሳሰር የጀመረችው ተግባርም የሚበረታታ መሆኑንም አክለዋል።
የሚታይ
ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ስብዕና እና የስራ ባህል እየገነባ ነው
May 3, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ታምርት ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ስብዕና እና የላቀ የሥራ ባህል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ስራ በማስገባት፣ 4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በመተካት እና 433 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት በማስገኘት አስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ውጤት ማስመዝገቡንም አመልክቷል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት ንቅናቄውን ሲጀምር ግቡ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን መታደግ ብቻ እንዳልነበረ አገልግሎቱ ገልጿል። ከኢኮኖሚያዊ ስሌቶች ባሻገር፣ ትልቁና ስትራቴጂካዊው ስኬት የተመዘገበው ኢትዮጵያን የዕውቀትና የክህሎት ምንጭ በሚያደርገው የሰው ሀብት ልማት ላይ መሆኑ ተመላክቷል። ዛሬ ላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የፋብሪካዎች ስብስብ መሆኑ ቀርቶ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነቡ ብቁ ባለሙያዎችና መሪዎች የሚፈሩበት ታላቅ የተግባር ትምህርት ቤት መሆን ችሏል። ይህ ሽግግር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተወዳዳሪነት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቴክኖሎጂ ላኪነትና ክህሎት አቅራቢነት ከፍ የሚያደርግ ለነገዋ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሚጥል የታሪካችን እጥፋት መሆኑን ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው። በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በግዙፍ ፋብሪካዎች ውስጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ የመንግሥትን የፖሊሲ ጥንካሬ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ክፍያ በሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ ዘመናዊ የምርት መስመሮችና የሶፍትዌር መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ወጣት መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች እየተመሩ ይገኛሉ። ይህ ስኬታማ የዕውቀት ሽግግር፣ መንግሥት ጥራት ያለው ፖሊሲ የመቅረጽ ብቻ ሳይሆን ፖሊሲን በተጨባጭ ወደ ተግባር የመለወጥና የማስፈጸም አቅም እንዳለው ትልቅ ማሳያ መሆኑ በመረጃው ላይ ተብራርቷል። በዘርፉ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም የተፈጠረላቸውን ምቹ ዐውድ ተጠቅመው ቴክኖሎጂን የመቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የመግራትና የማላመድ ብቃታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ። በዚህም ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበረባትን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በፈጠራ አቅማቸው እያስቀሩና አዳዲስ የሥራ ባሕልና የታሪክ ምዕራፍ እየጻፉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ይገኛል። በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው። ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ መሆኑ ተጠቁሟል። መንግሥት የኢንዱስትሪ ሽግግሩን ትክክለኛ ፍሬ የሚለካው በወጪ ንግድ ስሌቶች ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የደረጀና በዕውቀት የበለጸገ አምራች ዜጋ መፈጠሩ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል። በመሆኑም ይህን የክህሎት አብዮት ይበልጥ በማፋጠንና ዘርፉን የቴክኖሎጂ ምንጭ በማድረግ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች በቁርጠኝነት እንደሚቀጥሉም ገልጿል።
የመምህራንን የኢኮኖሚ አቅም ለማጎልበት የክልሉ መንግስት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ያደርጋል
May 2, 2026 228
ሀዋሳ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ የመምህራንን የኢኮኖሚ አቅም ለማጎልበት የክልሉ መንግስት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያደርግ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለፁ፡፡ ‎አቶ ደስታ ሌዳሞ የክልሉ መምህራን ማህበር ለሚያስገነባቸው የመምህራን ሆስፒታል እና ሁለገብ ሕንጻዎች ግንባታ ሥራ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡   ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት መምህራን በክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑንና በተለይ ከማህበሩ ጋር በመቀራረብ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ የትምህርት ሥብራትን ለመጠገንና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ እየታየ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ለግንባታ ሥራው ማስጀመሪያ የሚሆን 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉንና ሕንፃው ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡   የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) በበኩላቸው መምህራን በትውልድ ግንባታ ውስጥ ተሳትፏቸው ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ የመምህራን ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዲሻሻል፣ ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲኖራቸውና ጤናቸው በአግባቡ ተጠብቆ በበለጠ ትጋት እንዲሰሩ ለማስቻል ማህበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡   የሲዳማ ክልል መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ኢያሱ ፍቅሬ የክልሉ መምህራን ጠንካራ የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከመንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል። ማህበሩ ከ46 ሺህ በላይ አባላትን በሥሩ መያዙን ጠቁመው የመምህራን መታከሚያ ሆስፒታልና ሁለገብ ሕንጻዎቹ የረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆነው መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ በክልሉ በየደረጃው በመንግስት እየተደረገላቸው ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስግነው የማህበሩ አባላት ትውልድ የመቅረጽ ሀላፊነታቸውን በበለጠ ተናሳሽነትና ትጋት አጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ለመምህራን ሆስፒታል የሚገነባው ሕንጻ ባለ 6 ወለል መሆኑን ገልጸው፣ ሁለገብ ሕንጻው ባለ 12 ፎቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሕንጻዎቹ በ1ሺህ 200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እንደሚያርፉ ገልጸው ለግንባታቸውም በአጠቃላይ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል።
የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ስጋቱን ወደ መልካም አጋጣሚ ቀይሯል -የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ
May 2, 2026 197
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ያስገነባቸውን ዘመናዊ ሕንፃዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።   የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ይህንኑ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ የነበረበትን ዘመናት ያስቆጠረ ስጋት በማስወገድ ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል። አፈ ጉባኤው እንደገለጹት ተቋሙ ላለፉት ሰባት ዐሥርተ ዓመታት የመንግሥት ሠራተኛው ዋስትና ሆኖ ቢቆይም፣ የጡረታ ፈንዱን በአግባቡ የማንቀሳቀስ እና ወደ ኢንቨስትመንት የመቀየር አቅም ማጣቱ ለረጅም ጊዜ ስጋት ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት እና በወሰዳቸው የሪፎርም እርምጃዎች አዳዲስ አዋጆች እና የአስተዳደር ደንቦች እንዲጸድቁ ተደርጓል። ይህም ተቋሙ የነበረበትን ስጋት ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ፈንዱን ከማስጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማራ እና በሀገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል። አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አክለውም፣ ዛሬ የተመረቁት ዘመናዊ ሕንፃዎች ከግዙፍ ቁሳዊ ሀብትነታቸው ባሻገር ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ፍሬ እና የነገው ብሩህ ተስፋ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። "ሕንፃዎቹ የተገነቡት ከድንጋይ እና ከብረት ብቻ አይደለም፤ በእያንዳንዱ ጡብ ውስጥ የጡረታ ባለመብቶች ክብር፣ የሠራተኞች ላብ እና የሀገራችን ተስፋ ታትሞባቸዋል" ሲሉ የምረቃው ዋና ዓላማ የባለመብቶችን ክብር እና እርካታ ማረጋገጥ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ለወደፊቱም የፈንዱን ዘላቂነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋፋት እና አገልግሎቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል። አፈ-ጉባኤው መንግሥት ለተቋሙ የሚያደርገው ድጋፍ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት ለስኬቱ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
May 2, 2026 190
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ በርትተን ከሰራን፣ ጀምረን ከጨረስንና ክፍተቶችን እያየን መሙላት ከቻልን፣ ዘላቂና ተከታታይነት ያለው ዕድገት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ብልፅግና በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻንና ሌሎች ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በግል ባለሀብት የተገነባው ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከጅማና ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፣ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር ደግሞ በመጠን የሚስተካከል ነው። የሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሠላሳ ሼዶች ያሉት መሆኑን ጠቅሰው፤ ስፋት ያለው፣ በርካታ ሰዎችን የሚይዝና ለከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የግል ዘርፉ በኢንቨስትመንት መስክ ያለውን ሚና አጎልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በጨርቃጨርቅ ላይ ተመስርቶ የነበረው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርት አሁን ላይ እንዲሰፋ በተከናወነው ተግባር፤ ሶላር፣ የኤሌክትሪክ ባጃጅ፣ ጫማና አልባሳትን የመሳሰሉ ምርቶች በኢኮኖሚ ዞኑ እንደሚመረቱ ተናግረዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ባሉ ሼዶች የተለያዩ ምርቶች መመረታቸው የገበያ ዕድልን የሚያሰፋ መሆኑንም አንስተዋል። በኢኮኖሚ ዞኑ ያለው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ አሁን ላይ ሁለት ጊጋ ዋት እያመረተ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ዓመት ተጨማሪ ሁለት ጊጋ ዋት ማምረት ይጀምራል ብለዋል። የሶላር ሴል ምርት በአጭር ጊዜ ውስጥ መመረት የጀመረና አሁን ላይ እየሰፋ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል። ሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ የሚገኝና በርካታ ሼዶች ያሉት በመሆኑ፣ በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ዕድል ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ኢንዱስትሪ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢነርጂና ለአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት የሚውል በመሆኑ፣ በበርካታ መንገዶች በኢኮኖሚው ላይ አስተዋፅኦ የሚያበረክት እንደሆነም ገልፀዋል። ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለእውቀት ሽግግርና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የሚውል በመሆኑ፣ ጥቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የተሳካውንና የሚቀረውን በመለየት በትኩረት መሥራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ ለውጥ እያስመዘገበና የኢንዱስትሪ ሽግሽግን እያመጣ ያለ መሆኑን ገልፀዋል። ይህን ማጠናከር ከተቻለ በቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ ራሷን የመቻል ዕድል እንዳላት የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም የመጣውን ውጤት በማስፋትና በማሳደግ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ከሁሉም የሚጠበቅ ዐቢይ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት ጥሏል
May 2, 2026 242
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት መሰረት መጣሉን የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶሳይቲው የበላይ ጠባቂ ደመቀ መኮንን ገለጹ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2004 የተመሰረተው የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ትውልድ ትገነባለች የሚለውን መርህ ገቢራዊ ለማድረግ በምታደረገው እንቅስቃሴ ሶሳይቲው ጉልህ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲና በመንግስት ቁርጠኝነት ለሳይንስ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ እንደ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያሉ ተቋማት በተደራጀ መንገድ እንዲቋቋሙ ተደርጓል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ወጣት የሳይንስ ተመራማሪዎችና አስትሮኖመሮችን ማፍራቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በርካታ ወጣቶችን በማፍራትና በምርምር ተስፋ ሰጪ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ ከዚህ በላይ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ ሳይንስ ለግብርና የዲጂታል አብዮት እድገትና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር እኩል ለመራመድ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ዘመኑን የሚዋጅ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። ወጣቶችን በሳይንስና አስትሮኖሚ ለማብቃት የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር በዘርፉ ከመጠቁ ሀገራት ጋር ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በተወሰኑ ስራዎችና ውጤቶች መርካት የለብንም ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለዚህ ደግሞ የወጣቶች ተሳትፎ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን አስረድተዋል።   የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለስፔስ ሳይንስ ዕድገት ትልቅ ባለውለታ መሆኑን አስታውቀዋል። ስፔስ ሳይንስ የሉዓላዊነት፣ የምግብ ዋስትና፣ የዲፕሎማሲ፣ የጤና፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፤ ያለ ስፔስ ሳይንስ መቆም እንደማይቻል ገልጸዋል። የሀገርን ኢኮኖሚና ኅልውና ለማስቀጠል ስፔስ ሳይንስ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ሶሳይቲው ወጣቶችን ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት የተለያዩ ተቋማት መደገፍና በትብብር መስራት አለባቸው ብለዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
በጠቅላላ ምርጫው የፖሊሲ አማራጮቻችንን በተለያዩ ሚዲያዎች ሳንገደብ ማቅረብ ችለናል 
May 3, 2026 53
ሰመራ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በዘንድሮው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ያለ ምንም ገደብ ለህዝብ ማቅረብ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ (አነግፓ) ሊቀ መንበርና የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ ገለጹ። ለዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦቻቸውንና ማኒፌስቶዋቸውን ለህዝብ እንዲያስተዋውቁ የመገናኛ ብዙኃን እኩል የአየር ሰዓትና ሰፊ መድረክ መመደባቸው ይታወቃል። ይህም ሚዲያዎች ብዝሃነትን በማስተናገድ ረገድ ያላቸውን ሚና በተግባር እያሳዩ መሆኑን አመላካች ሆኗል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ(አነግፓ) ሊቀ መንበር አቶ ሃንፈሬ አሊሚራህ፤ በዘንድሮው ምርጫ የመወዳደሪያ ምህዳሩ ከቀደምት የምርጫ ዘመናት የተለየና የተሻሻለ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ለክልል ተወዳዳሪዎች አምብዛም ሽፋን ያልሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ጊዜ ግን አማራጭ ሐሳቦቻቸውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያ አውታሮች እያቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ፓርቲያቸው ከሰባት በላይ መድረኮችን በመጠቀም የመወዳደሪያ ሐሳቡን ማቅረቡን ገልጸው፤ በዚህም የመወዳደሪያ ምህዳሩ የሰፋ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ ወቅት በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች በነፃነት ቅሰቀሳ በማድረግና በማሰተዋወቅ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል። የአፋር ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የምርጫውን ሂደት በመገምገም አስፈላጊ የሆኑ የእርማት እርምጃዎችን የሚጠቁም ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ኮሚቴ ያዋቀረው ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ያለውን ድርሻ ለመወጣት እንደሆነም አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ  ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትንና ፌዴራላዊ ሥርዓትን የማፅናት አዲስ አቅጣጫ
May 2, 2026 285
ከለውጡ በፊት ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በተሟላ ሁኔታ አለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መዋቅሮች ላይ ጥልቅ ጠባሳ ጥሎ አልፏል ፡፡ ቀደምት ግጭቶች፣ የመሠረተ ልማት ውድመትና የማኅበራዊ ትስስር መላላት የዚሁ አንድነት አለመረጋገጥ ውጤቶች ናቸው ፡፡ የመደመር መንግስት እየገነባ ያለው ሥርዓት ልዩነቶችን እንደ ጌጥ፣ አንድነትን ደግሞ እንደ መሠረት የሚቀበል "ባለ ሚዛን" ሥርዓት ነው ። ይህ አዲስ ጉዞ የቡድን መብትንና የግለሰብ ነፃነትን ሳያጋጭ በማጣጣም፣ የሀገረ መንግሥቱን ፅናት ለማረጋገጥ ያለመ ነው። ይህ ዕሳቤ ኅብረ-ብሔራዊነትን እንደ ነባር ሀገራዊ እውነታ የሚቀበል እንጂ ከአንድነት ጋር የሚጋጭ አድርጎ አይመለከተውም። በዚህም መሠረት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰቡ የሚገነባው በወል ትርክትና ለብዝኃነት እውቅና በሚሰጡ እሴቶች ላይ ይሆናል። መንግሥት "በኅብረት ሆነን እንበለጽጋለን" በሚል መርሕ፣ በቀጣይ ዓመታት የብዝኃ ቋንቋ ፖሊሲን ወደ ተግባር በማስገባትና የፌዴራል ሥርዓቱን ዋና ምሶሶ የሆነውን ብዝኃነትን በማስተናገድ ረገድ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ። ባለፉት የለውጥ አመታት ከተከናወኑት መካከል ቀደም ሲል "አጋር" ተብለው ከውሳኔ ሰጪነት ተገልለው የነበሩ የዳር አካባቢ ሕዝቦችን እንደ ሀገር ግንባታ ዋና ምሰሶ በማየት ማካተቱ ትልቅ እርምጃ ነው ፡፡ በተጨማሪም፣ በፌዴራልና በክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት በሕግ ለመምራት የወጣው አዋጅ (1231/2013) እና ለዘመናት ታፍነው የነበሩ የማንነት ጥያቄዎች በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ምላሽ ማግኘታቸው እንደ ስኬት ይጠቀሳሉ ። እነዚህ እርምጃዎች በዜጎች መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲጎለብትና ክልሎች እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉበት የ"እህትማማችነት" ፖለቲካ እንዲሰፍን አድርገዋል ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳን በተመለከተ፣ መንግሥት የፌዴራል ሥርዓቱን የክልሎችን ጸጋ ለጋራ ብልጽግና ማዋያ መሣሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት ይገኛል። ለዚህም እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ የሕዝብ ትስስር ምልክቶች፣ የ"ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክቶች እና በቆላማ አካባቢዎች የተመዘገበው የስንዴ ልማት ተሞክሮዎች በዋቢነት ቀርበዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች ክልሎች ያላቸውን አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከመቀየር ባለፈ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ አንድነትን አፅንተዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የሚከናወኑ የኮሪደር ልማቶችና የታሪክ መዘክሮች ግንባታም የኢትዮጵያን ብዝኃነትና የጋራ ማንነት የሚያንፀባርቁ ናቸው። መንግሥት ተቋማዊ ሪፎርሞችን በማጠናከር ሲቪል ሰርቪሱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ እንዲያገለግል ለማድረግ እሰራ ይገኛል ። የብዝኃ-ልሳን ፖሊሲን ማስፋፋት፣ የክልሎችን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርና በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል የሚመጡ የመፍትሔ ሀሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። በተጨማሪም፣ ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ቀመርን በማሻሻል አነስተኛ አቅም ያላቸውን አካባቢዎች የሚደግፍ አሠራር ይዘረጋል ። የመደመር መንግሥት የሚከተለው የፌዴራሊዝም አቅጣጫ ኢትዮጵያን ጠንካራ ተቋማት ያሏት፣ ብዝኃነቷ ለልማት የሚውልባትና እያንዳንዱ ዜጋ በነፃነት የሚኖርባት ሀገር ለማድረግ ያለመ ነው ። ብልፅግና ፓርቲ
የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ ግንቦት 24ን እየጠበቅን ነው - የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 212
ጂንካ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በተመቻቸልን ዕድል ተጠቅመን የምንፈልገውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ በመውሰዳችን ግንቦት 24ን በጉጉት እየጠበቅን ነው ሲሉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለፁ።   ተማሪ በቀለ ባሪሶ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ምርጫው የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በንቃት ተሳትፎ ለማድረግ መቻል ልዩ ስሜት አለው። ምርጫው የዴሞክራሲ ልምምድ ሥርዓት አካል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መሳተፍ አለበት ያለው ደግሞ ተማሪ አምሳሉ ዓባይነህ ነው።   በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያበቃውን የድምፅ መስጫ ካርድ በመውሰዱ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምጹን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አንስቷል።   የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት መቅደስ አድማሱ በበኩሏ አብዛኛው ተማሪ በምርጫው ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው በመግለጽ፤ ይህም ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስረድታለች።   ዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽ ኮሙኒኬሽን እና የቤተ ሙከራ ማዕከላትን በበይነ መረብ በማስተሳሰር ተማሪዎች ዲጂታል የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ ዘሮ (ዶ/ር ) ተናግረዋል።
የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ ወስደናል - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
May 2, 2026 314
አሶሳ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ። ቦርዱ የምርጫ ካርድ ላልወሰዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በካምፕ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በልዩ ሁኔታ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የመራጮች ምዝገባ እያካሄደ ነው። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ባገኙት የመራጭነት ዕድል ድምጽ ለመስጠት የሚያበቃቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት ተማሪ መልካሙ መላኩ እንደገለጸው፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላም እና ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ፓርቲ እንዲመርጡ ዕድል መመቻቸቱ የሚበረታታ ነው። ተማሪዎች ባሉበት ሆነው በቴክኖሎጂ ታግዘው መመዝገብ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የታየ ትልቅ መሻሻል መሆኑን ጠቁሟል። ተማሪ አበባ የኛነው በበኩሏ፤ ተማሪዎች በምርጫው እንድንሳተፍ መደረጉ የመምረጥ መብታችንን ተጠቅመን ሀገርን በልማትና በሰላም ግንባታ ወደፊት የሚያራምድ ፓርቲ ለመምረጥ ዕድል ይሰጠናል ብላለች። ለተማሪዎች የተመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የምርጫ ካርድ መውሰዱን የገለጸው ተማሪ አቢያን ኩኩ፤ ባሉበት ሆነው ካርድ ማውጣት መቻላቸው ጊዜና ጉልበት በመቆጠቡ ሊበረታታ ይገባል ብሏል። ግንቦት 24 ቀን 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጹን ለሚፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት መዘጋጀቱንም አረጋግጧል።
የሚበጀንን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫውን ዕለት እየጠበቅን ነው - የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች
May 2, 2026 260
ሰመራ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ በሆነው ምርጫ ላይ በንቃት በመሳተፍ ለሀገር ግንባታ የሚበጅ ፖሊሲ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ኢዜአ በሰመራ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት፤ በምርጫ ካርዳቸው የተሻለ ሐሳብ አለው፣ ሀገርና ሕዝብንም ወደፊት ያራምዳል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል።   አቶ ዘይኑ ሙሳ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ምርጫ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው፤ ለሕዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትና ዘላቂ ሰላም አበክሮ ይሠራል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።   ፓርቲዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮችና ቋንቋዎች ሐሳባቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ መደረጉ እንደ መራጭ በቂ ግንዛቤ ለመያዝ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል። ምርጫ ይበጀኛል ብለን ድምጻችንን ለምንፈልገው የፖለቲካ ፓርቲ የምንሰጥበት በመሆኑ ሁሉም ሰው ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም መዘጋጀት አለበት ያሉት ደግሞ አቶ ሙሳ አብዱ ናቸው። የምርጫውን ቀን እየጠበቁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ለሰላምና ልማት መቀጠል የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። አቶ መሐመድ ይመር በበኩላቸው፤ የፓርቲዎችን አማራጭ ሐሳቦች ሕብረተሰቡ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲያገኝ መደረጉ የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። የምርጫ ካርዳቸውን በወቅቱ ወስደው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን ለመስጠት መጪውን ግንቦት 24 እየጠበቁ መሆናቸውን አመላክተዋል።
በተከናወኑ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል
May 2, 2026 239
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ ስታድየም በመካሄድ ላይ ነው።   አቶ ሞገስ ባልቻ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ግዙፍ የልማት ሥራዎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ መሠረት መጣሉን አስገንዝበዋል። የሰው ተኮር ሥራዎች የበርካታ ሰዎችን ኑሮ ከመሠረቱ በመቀየር ረገድ ውጤት ማስገኘታቸውን ጠቅሰው፤ የብልጽግና ፓርቲ ለቃሉ የታመነ ለተልዕኮውም የፈጠነ ፓርቲ መሆኑን አስታውቀዋል። አዲስ አበባን ውብ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ሥራዎችም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ እነዚህን የልማት ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ለብልጽግና ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን የበለጠ ያከናውናል
May 2, 2026 208
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራትን የበለጠ እንደሚያከናውን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ በአዲስ አበባ ስታድየም በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባል አዳነች አቤቤ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ህዝብ ብቸኛው የስልጣን ባለቤት ነው። ያለ ህዝብ ተሳትፎና አጋርነት ብልፅግናን እውን ማድረግ እንደማይቻልም ተናግረዋል።   የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራት ማከናወናቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያቆመው አንዳች ምድራዊ ሀይል እንደሌለ ገልጸዋል። በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ማንንም ያልዘነጉ አካታች መሆናቸውን ጠቁመው፤ እነዚህ ተግባራት የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። ብልፅግና ቃሉን የሚጠብቅ ፓርቲ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ የከተማዋን ገጽታም ቃል በገባው መሰረት መገንባቱን ተናግረዋል። በቀጣይም ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ቃል በመግባት "ብልፅግናን ምረጡ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA

ማህበራዊ
በድሬዳዋ የወባ በሽታን ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ውጤቶች ተመዝግበዋል
May 3, 2026 5
ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ አስተዳደር ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ የተቀናጁ ተግባራት በሽታውን በመቀነስ ረገድ ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ አመራሮች ገለጹ። ድሬዳዋ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧና በሞቃታማ የአየር ንብረቷ ምክንያት ለወባ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዷ መሆኗ ይታወቃል። ይህንን ተጋላጭነት ለመቀነስና የህዝቡን ጤና ለመጠበቅም የተለያዩ የመከላከያ ስራዎች ሲከናወኑ የቆዩ ሲሆን በዚህም ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። በሳቢያን ወረዳ የጎሮ ጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጅ የጤና መኮንን እንዳለማው እርቅይሁን እንዳሉት፤ ለወባ በሽታ መንስኤ የሆኑ የትንኝ መራቢያ አካባቢዎች በተቀናጀ መንገድ በማዳረቅና ኬሚካል በመርጨት ወባን በተጨባጭ መከላከል ተችሏል።   በተለይም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ተገቢውን የመከላከያ ትምህርት በመስጠት በመከላከሉ ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ የተከናወኑት ተግባራት ፍሬያማ ሆነዋል ብለዋል። ነዋሪው ጊቢውንና አካባቢውን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ አካባቢዎችን በማፋሰስና በማዳረቅ እያከናወነ የሚገኘው ስራ በአብነት የሚጠቀስ መሆኑን በመግለፅ። ከመከላከሉ ጎን ለጎን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በወባ በሽታ ለተያዙ 2ሺህ 900 ሰዎች ተገቢውን ህክምና በመስጠት የማዳን ስራ መሰራቱን አንስተዋል። አምናና ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተሰሩ ስራዎች በወባ የሚያዙ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ማስቻሉንም ገልጸዋል። የመልካ ጀብዱ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሙያ ቤተልሄም እንዳለ በበኩላቸው፤ ዘንድሮ ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት የተከናወኑ ተግባራት የበሽታውን ስርጭት እንዲገታ አስችሏል። በተለይም የትንኝ መራቢያ ወንዞችና የኢንዱስትሪ አካባቢዎች ላይ ኬሚካል ርጭት በማካሄድ አካባቢዎችን ከስጋት ነፃ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ለታመሙትም አስፈላጊው ህክምና እየተሰጠ መሆኑን በማስታወስ አንድም በወባ የተያዘ ሰው በጤና ጣቢያው እንደሌለ በመግለፅ። ወባን ለመከላከል በተሰሩ ስራዎች የመጡ ለውጦችን ይበልጥ በማሳደግ ከወባ ነፃ የሆነ መልካጀብዱን ዕውን ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው የወባ በሽታን በመከላከልም ሆነ በየጤና ተቋማት በወባ ለተያዘ ሰው እየተሰጠ የሚገኘው ህክምና አበረታች ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል። ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል እያደረገ የሚገኘው ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱ እና በሁሉም ጤና ተቋማት የፀረ ወባ መድኃኒት እና ፈጣን መመርመሪያ ኪት እንዲሟላ መደረጉ የበሽታውን ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ አስችሏል ብለዋል። በወባ በሽታ ህይወቱ ያለፈ አንድም ነዋሪ አለመኖሩን ጠቅሰው ይህን ውጤታማ ጉዞ በማስቀጠልና ድሬዳዋን ከወባ ነፃ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 267
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። ‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። ‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ‎ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። ‎በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። ‎የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በክልሉ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት የማረጋገጥ ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል
May 2, 2026 115
ሚዛን አማን፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የጤና ተቋማትን ተደራሽነት የማረጋገጥ ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማን ገለጹ። በክልሉ ሚዛን አማን ከተማ በግሉ ባለሀበት ከ250 ሚሊዮን በሚበልጥ ብር የተገነባው "ኒቆ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል" ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። አቶ ፍቅሬ አማን ሆስፒታሉን መርቀው ሲከፍቱ እንዳሉት የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት ሕይወት የመታደግ ተግባር በመሆኑ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ማሳካት ለመንግስት ብቻ የሚተው አለመሆኑንና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል። የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉን ዘርፍ አጋርነት የማጠናከር ሥራ ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸው፣ ዛሬ የተመረቀው የኒቆ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የዚሁ አካል ነው ብለዋል። በመደመር መንግሥት እሳቤ የግሉን ዘርፍ እና የሕዝብ ተሳትፎ ከመንግሥት ተግባር ጋር በማቀናጀት የሚሰሩ ልማቶች ውጤታማ በመሆናቸው ጎልብተው እንዲቀጥሉ ይሰራል ነው ያሉት። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው በዞኑ የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ማስፋፋትና ግብዓት የማሟላት ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል። በተለይ የግሉ ባለሀብት በጤናው ዘርፍ እያደረገው ያለው ተሳትፎ በመንግስት የጤና ተቋማት የሚፈጠርን የአገልግሎት ጫና እንደሚያቃልል አንስተዋል። የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ሰሎሞን ሌዊ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በከተማዋ ሦስት የግል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተመርቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸዋል። ይህም መንግስት ለዘርፉ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ያሳያል ያሉት ከንቲባው፣ ሕዝቡ ጤናው ተጠብቆ ልማትን እንዲያፋጥን ከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ ኢንቨስትመንት የሚያደርገውን እገዛ ይቀጥላል ብለዋል። የሆስፒታሉ ባለቤት ኒቆዲሞስ ዓለሙ ለሆስፒታሉ ግንባታ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸውንና ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሉን በዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁስ ማደራጀታቸውን ገልጸዋል።
አገልግሎት ለዜጎች፣ ክብር ለሕዝብ
May 2, 2026 121
በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ውስጥ የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ቁልፍ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል። መንግስት የአገልጋይነት መርህን መሰረት በማድረግ፣ በአስተዳደራዊ መዋቅሮችና በማህበረሰቡ መካከል ጠንካራ ድልድይ ለመገንባት የተለያዩ የሪፎርም እርምጃዎችን እየወሰደ ነው ። ከዚህ አንፃር ማንኛውም የመንግስት አመራር እና ሰራተኛ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለበት ፡፡ የመደመር መንግስት እንደሚለው፣ የአንድ አስተዳደር መኖር ትርጉም የሚሰጠው ዜጎች በሚፈልጉት ቦታና ሰዓት ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ከሌብነት የጸዳ አገልግሎት ማግኘት ሲችሉ ብቻ ነው። አገልግሎት አሰጣጥ እንደ ተራ የመንግስት ግዴታ ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝብና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመን የሚገነባ ዋነኛ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል። ለዚህም ሲባል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ውሃና ፍትህ ያሉ ዘርፎች የዜጎች ሰብዓዊና ዜግነታዊ መብት እንጂ ከመንግስት የሚሰጡ ችሮታዎች አይደሉም ። በዚህም መሰረት የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በጸዳ መልኩ፣ በሙያዊ ብቃትና በገለልተኝነት ዜጎችን እኩል የሚያስተናግዱበትን ስርአት መገንባት ለሀገረ-መንግስቱ ፅናት ወሳኝ መሆኑ ይታመናል ። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ መንግስት ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ሰፋፊ የህግና የመዋቅር ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከእነዚህም መካከል በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ውስጥ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ እንደ አንዱ አብይ ምሶሶ ተቀርጾ እየተተገበረ ይገኛል። ዜጎች ለአንድ አገልግሎት ብዙ መስሪያ ቤት በመመላለስ እንዳይጉላሉ "መሶብ" የተሰኘ ዘመናዊ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በማስጀመር የሌብነት ዕድልን መቀነስ ተችሏል። በተጨማሪም በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ አማካኝነት የንግድ ፍቃድ፣ የፓስፖርት አገልግሎትና የታክስ ክፍያ መሰል አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል ተቀይረዋል። ይህም ለዜጎች ከፍተኛ የጊዜና የጉልበት ብክነትን ከማስቀረቱም በላይ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት በስራ ሂደት ውስጥ እንዲሰፍን አድርጓል። በተለይም በፍትህ ዘርፍ የዳኝነት ነፃነትን ለማረጋገጥና ተቋማቱን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያሳዩ ነው። በጤናው ዘርፍ የጤና መድህን ስርአት በመስፋፋቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል። በትምህርት ዘርፍም የብሄራዊ ፈተና አሰጣጥ ስርአት በማሻሻልና የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን በመተግበር የትውልድ ግንባታ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። እነዚህ ውጤቶች በዜጎች ዘንድ የመንግስት ተቋማት ቅቡልነት እንዲጨምርና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ስሜት እንዲጎለብት በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ወደፊትም መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማዘመን ታላላቅ እቅዶችን ነድፏል። የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በማስፋፋት ቢያንስ 80 በመቶ የሚሆኑ የመንግስት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲሰጡ የማድረግ ግብ ተቀምጧል። ይህ "የሙሉ ዲጂታላይዜሽን" እቅድ የተወሳሰበ ቢሮክራሲንና ሙስናን ለዘላቂው ለመቅረፍ እንደ ዋና መፍትሄ ታይቷል። በተጨማሪም በብቃት ላይ የተመሰረተ የሲቪል ሰርቪስ ስርአት በመገንባት፣ የዜጎችን ግብረ-መልስ በቀጥታ የሚቀበል የክትትል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል። ይህም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ተቋማትና አመራሮች ተጠያቂ የሚሆኑበትን ስርአት ይፈጥራል። በአጠቃላይ መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ ስብራትን በመጠገን፣ ዜጎች በሀገራቸው ተከብረውና ተደስተው የሚኖሩባትን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ፡፡ ብልፅግና ፓርቲ
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ስብዕና እና የስራ ባህል እየገነባ ነው
May 3, 2026 75
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ታምርት ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ስብዕና እና የላቀ የሥራ ባህል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ 830 ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ስራ በማስገባት፣ 4 ነጥብ 85 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በመተካት እና 433 ሚሊየን ዶላር ከኤክስፖርት በማስገኘት አስደናቂ የኢንዱስትሪ ሽግግር ውጤት ማስመዝገቡንም አመልክቷል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት ንቅናቄውን ሲጀምር ግቡ ምርትን ማሳደግና የውጭ ምንዛሬን መታደግ ብቻ እንዳልነበረ አገልግሎቱ ገልጿል። ከኢኮኖሚያዊ ስሌቶች ባሻገር፣ ትልቁና ስትራቴጂካዊው ስኬት የተመዘገበው ኢትዮጵያን የዕውቀትና የክህሎት ምንጭ በሚያደርገው የሰው ሀብት ልማት ላይ መሆኑ ተመላክቷል። ዛሬ ላይ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የፋብሪካዎች ስብስብ መሆኑ ቀርቶ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነቡ ብቁ ባለሙያዎችና መሪዎች የሚፈሩበት ታላቅ የተግባር ትምህርት ቤት መሆን ችሏል። ይህ ሽግግር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተወዳዳሪነት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ቴክኖሎጂ ላኪነትና ክህሎት አቅራቢነት ከፍ የሚያደርግ ለነገዋ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሚጥል የታሪካችን እጥፋት መሆኑን ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው። በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በግዙፍ ፋብሪካዎች ውስጥ የታየው ተጨባጭ ለውጥ የመንግሥትን የፖሊሲ ጥንካሬ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ክፍያ በሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች ብቻ ይተዳደሩ የነበሩ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ ዘመናዊ የምርት መስመሮችና የሶፍትዌር መሠረተ-ልማቶች ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ወጣት መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች እየተመሩ ይገኛሉ። ይህ ስኬታማ የዕውቀት ሽግግር፣ መንግሥት ጥራት ያለው ፖሊሲ የመቅረጽ ብቻ ሳይሆን ፖሊሲን በተጨባጭ ወደ ተግባር የመለወጥና የማስፈጸም አቅም እንዳለው ትልቅ ማሳያ መሆኑ በመረጃው ላይ ተብራርቷል። በዘርፉ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም የተፈጠረላቸውን ምቹ ዐውድ ተጠቅመው ቴክኖሎጂን የመቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የመግራትና የማላመድ ብቃታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ። በዚህም ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበረባትን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት በፈጠራ አቅማቸው እያስቀሩና አዳዲስ የሥራ ባሕልና የታሪክ ምዕራፍ እየጻፉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከቴክኒካዊ ብቃት ባሻገር፣ አዲስ ኢንዱስትሪያዊ ሰብዕና እና የሥራ ባህል እየገነባ ይገኛል። በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ዓለም አቀፍ የጥራት ቁጥጥር ስታንዳርዶችን፣ ጥብቅ የጊዜ አጠቃቀምንና ስልታዊ የአመራር ክህሎትን በመላበስ ላይ ናቸው። ከታችኛው የሥራ እርከን ተነስተው በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ውስጥ እስከ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ደረጃ የደረሱ ወጣቶች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው "ምርጥ ምርት" የሰው ሀብቷ መሆኑን እያስመሰከሩ መሆኑ ተጠቁሟል። መንግሥት የኢንዱስትሪ ሽግግሩን ትክክለኛ ፍሬ የሚለካው በወጪ ንግድ ስሌቶች ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የደረጀና በዕውቀት የበለጸገ አምራች ዜጋ መፈጠሩ መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል። በመሆኑም ይህን የክህሎት አብዮት ይበልጥ በማፋጠንና ዘርፉን የቴክኖሎጂ ምንጭ በማድረግ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች በቁርጠኝነት እንደሚቀጥሉም ገልጿል።
ተፈጥሯዊና የባህል ሀብቶችን ለቱሪዝም ልማት ለማዋል የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው 
May 2, 2026 197
ሀዋሳ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ የተፈጥሯዊና የባህል ሀብቶችን ለቱሪዝም ልማት ለማዋል የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተመላከተ። "በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራና ዘላቂነት" በሚል መሪ ሀሳብ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 15ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ተካሂዷል።   በኮንፈረንሱ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ የትምህርት መስክ ተማሪዎችን ከማሰልጠን ባለፈ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማድረግ ዘርፉ ለሀገር እድገት ያለውን ፋይዳ ለማሳደግ የበኩሉን እየተወጣ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ በተጀመረው ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትወልድ መርሀ ግብር በርካታ የመስህብ ስፍራዎች መልማታቸውን የማልማት ሥራ መሰራቱን ለማሳያነት ጠቅሰዋል። በቀጣይም ተፈጥሯዊና የባህል ሀብቶችን ለቱሪዝም ልማት ለማዋል የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አክለዋል።   የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው እንዳሉት፣ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ ነው። በአትዮጵያ በርካታ የመስህብ ሥፍራዎች ቢኖሩም አልምቶ ከመጠቀም እንጻር ተግዳሮቶች እንደነበሩ አስታውሰው፣ በለውጡ መንግስት የመዳረሻ ስፍራዎችን በማስፋፋት ኢትዮጵያ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን ተሰርቷል ብለዋል።   የኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና በኮንፈረንሱ ጥናት ያቀረቡት ይታሰብ ስዩም፣ በዘመናዊ የቱሪዝም ልማት ውስጥ አዳዲስ ፈጠራና ዘላቂነትን መሰረት ያደረገ የማልማትና ማስተዋወቅ ሥራ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የቱሪዝም መሰረተ ልማትን ከቴክኖሎጂ ጋር የማስተሳሰርና አገልግሎቱን ማዘመን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳውን ከማሳደግ ባለፈ ሀብቱ ለትውልድ እንዲተላለፍ ያግዛል ብለዋል።   በስነምህዳር ቱሪዝም (ኢኮ ቱሪዝም) ዙሪያ የምርምር ሥራቸውን ያቀረቡት በቦረና ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ጸለፎ ጫካ፣ በሀገራችን ቱሪዝምን ከስነምህዳር ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ ያለው ሥራ በርካታ ጎብኚዎችን እየሳበ መሆኑን ገልጸዋል። የመዳረሻ ልማት ሥራዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ባህል፣ አኗኗር እና አረንጓዴ አሻራን ያስተሳሰረ በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውና በከተሞች የተጀመረውን የቱሪዝም መሰረተ ልማት ተደራሽነት ወደ ሌሎች ማስፋፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል። በመድረኩ ከቱሪዝም ጋር የተያያዙ ጥናታዊ የምርምር ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን ከሀዋሳና ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ ምሁራን፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት መምህራንና በቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በዞኑ በመኸር እርሻ በዘር ከሚሸፈነው መሬት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በኩታ ገጠም የሚለማ ነው
May 2, 2026 118
ደሴ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ወሎ ዞን በመጪው የመኸር እርሻ በዘር ከሚሸፈነው 432 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በኩታ ገጠም እንደሚለማ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። አስተዳደሩ የ2018/19 መኸር ምርት ዘመን የሰብል ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በደሴ ከተማ አካሂዷል።   የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አሊ ይማም በመድረኩ እንደገለጹት፣ የመኸር እርሻ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት የተያዘውን ግብ የሚሳካበት ነው። በመኸር እርሻ ከሚለማው 432 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ249 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው በኩታገጠም እንደሚለማ ገልጸዋል። በአጠቃላይ ለመሰብሰብ ከታቀደው ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ከ10 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው በኩታ ገጠም ከሚለማው ሰብል እንደሚሰበሰብ አስታውቀዋል። በልማቱ ምርታማነትን ለማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂና አዳዲስ አሰራሮችን እንዲሁም ግብዓትን በአግባቡ መጠቀም ላይ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።   የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው በመኸሩ የታቀደውን ምርት ለማግኘት ለአርሶ አደሩ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል። በተለይም የሜካናይዜሽን እርሻ ላይ በማተኮርና የተሻሻሉ የግብርና አሰራርና ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር የምርት ዕድገትን ለማረጋገጥ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
በክልሉ የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ልማትን ለማስቀጠል ያላቸውን እቅም እንዲያጠናክሩ እየተሰራ ነው
May 2, 2026 116
ባህርዳር፤ ሚያዚያ 24/2018 (ኢዜአ)፦ የልማት ድርጅቶች በክልሉ እድገት ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ እንዲያጠናክሩ እየተሰራ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) ገለጹ። በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የተቋቋመው አልማኮን የህንጻ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ማምሻውን አዲስ ብራንዱ ይፋ ተደርጓል። የአማራ ክልል ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ለማሳደግ የአጋር አካላት ተሳትፎ የጎላ ሚና እያበረከተ ነው። በመሰረተ ልማት ግንባታና ማህበራዊ ልማት ላይ በመሳተፍም የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አጋር አካላቱ እገዛ እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል። የዚሁ ማሳያ የሆነው አልማኮን በአዲስ ብራንድ መምጣቱ የተሰጠውን ተልእኮ በብቃት በመፈጸም የክልሉን እድገት ለማፋጠንና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ይብልጥ እንዲያጠናክር ያደርገዋል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በክልል የሚገኙ የልማት ድርጅቶች በክልሉ እድገት ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ እንዲያጠናክሩም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ነው የገለጹት። የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋና ስራ አስፈጻሚና የአልማኮን ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ በበኩላቸው ፤ ማህበሩ ሀብት የሚያመነጩ ተቋማትን በማቋቋም ከእርዳታ ጠባቂነት ለመውጣት እየሰራ ይገኛል። አልማኮን የተሰኝው ተቋምም በኮንስትራክሽን፣ በሪል እስቴት ልማትና በግንባታ ግብዓት አቅርቦት ላይ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያመለከቱት። ኩባንያው በአዲስ ብራንድ መምጣቱም በኮንስታራክሽንና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተወዳዳሪ ምርቶችን ይዞ ወደ ገበያ በመግባት የክልሉን እድገት ለፋጠን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት እንደሚያስችለው አስረድተዋል። የአልማኮን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰጥቷል ደሳለኝ እንደገለጹት፤ ኩባንያው በ2005 ጀምሮ በኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሰማራት ለክልሉ እድገትና ለህዝቡ ተጠቃሚነት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ኩባንያው አዲስ ብራንድ ይዞ መምጣቱም በአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅዱ መሰረት አዲስ አደረጃጀትና አሰራር በመፍጠር የገበያ አድማሱን ለማስፋት እንደሚያስችለው አስገንዝበዋል። በመደረኩ ላይም በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረሥ ሳህሉ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።    
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አገልግሎቱ ከአላስፈላጊ የገንዘብ ወጪ እና እንግልት ታድጎናል - ተገልጋዮች
May 3, 2026 103
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ከአላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት ታድጎናል ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው ተገልጋዮች ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት ተንቀሳቃሽ አገልግሎትን በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎችና ወደ ንግድ ተቋማት በመንቀሳቀስ ለዜጎች ቀልጣፋና እንግልት የሌለው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ኢዜአ አገልግሎቱ በሚሰጥባቸው የከተማዋ ስፍራዎች በመዘዋወር ያነጋገራቸው ተገልጋዮች፤ አሠራሩ ከአላስፈላጊ የገንዘብ ወጪና እንግልት እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡ ከተገልጋዮች መካከል መንጃ ፈቃድ ሲያሳድስ ያገኘነው ወጣት ታምራት መንግሥቱ፤ አገልግሎቱ ደጃፉ ድረስ በመምጣት ተገቢውን ምላሽ እንደሰጠው ተናግሯል፡፡ ቀደም ሲል መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በርካታ ቀናትን ይፈጅ እንደነበር አስታውሶ፣ አሁን በፍጥነትና በጥራት ማግኘት መቻሉን ገልጿል።   ይህም ጊዜና ገንዘብ ሳይባክን፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሳይገታ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት እንዳስቻለው አስረድቷል። ሌላኛው መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ የመጡት አቶ ክፍሌ ዳባ በበኩላቸው፤ "አገልግሎቱ ጊዜ ቆጣቢና እንግልትን ያስቀረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብለዋል።   መስተንግዶው እጅግ ትሕትና የተሞላበት፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና እንከን የማይወጣለት መሆኑንም መስክረዋል፡፡ የልደት ምስክር ወረቀት ሲያወጣ ያገኘነው ወጣት መኮንን ይማም በበኩሉ፤ ከአገልግሎት አሰጣጡ ፍጥነትና ጥራት ባሻገር፣ ሠራተኞቹ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጹ መሆናቸውን በአካል መታዘቡን ገልጿል።   "የመንግሥት አገልግሎት በዚህ ልክ ይዘምናል፣ ወደ ደጃፍም ይቀርባል ብዬ አስቤም አልሜም አላውቅም" ያሉት ደግሞ የንግድ ፈቃድ ለማደስ የተገኙት አካል ጉዳተኛው አቶ መኮንን ወርቁ ናቸው።   የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት በተለይ ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ በረከት መሆኑንም ተናግረዋል። ሌላኛው መታወቂያ ሲያሳድስ ያገኘነው ወጣት ሚኪያስ ወንድማገኝ፤ አዲስ መሶብ ቢሮክራሲንና የተገልጋዮችን እንግልት ሙሉ በሙሉ ያስቀረ መሆኑን ገልጿል።   የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ፤ በመዲናዋ እስካሁን የ25 ተቋማት 150 አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ባለጉዳይ የሚበዛባቸው የስምንት የተለያዩ ተቋማት አገልግሎቶችን በተንቀሳቃሽ መልክ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።   ተንቀሳቃሽ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎቱ ዜጎች ጊዜና ገንዘባቸውን ሳያባክኑ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን እያከናወኑ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁን በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉንና በደንበኞች ግብረ-መልስ መሠረት የእርካታ ደረጃቸው እያደገ መምጣቱን አረጋግጠዋል። ይህም ቀደም ሲል በመንግሥት ተቋማት ይስተዋል የነበረውን የአገልግሎት ስብራት ሙሉ በሙሉ ያስቀረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይም የአገልግሎቱን አድማስ ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረዋል
May 2, 2026 192
ድሬደዋ፤ ሚያዚያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወዳዳሪ ትውልድ በመገንባት ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ተናገሩ። በአስተዳደሩ ለሶስት ቀናት የተካሄደው የትምህርት ቤቶች የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች አውደ ርዕይ ዛሬ ተጠናቋል። የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ፤በአውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት የፈጠራ ውጤቶች ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩ አበረታች ጉዞዎችን ለማሳካት የጎለ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል። በትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክህሎትና ጥበብ ያላቸውን ታዳጊ ተማሪዎችን ለማፍራት የሚከናወኑ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በአውደ ርዕዩ የቀረቡ ችግር ፈቺ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በበኩላቸው፤ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕውቀት፣ ክህሎትና ጥበብ የተላበሱ ታዳጊዎችን ለማፍራት የተጀመሩ ጥረቶች ፍሬያማ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል። በአውደ ርዕዩ በየዘርፉ የቀረቡ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች የዚሁ መገለጫ መሆናቸውን በመግለፅ ። በቀጣይም የፈጠራና የምርምር ስራዎችን በጥራት፣ በስፋት እና በተሻለ ከፍታ ለማሳደግ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ምሁራን ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ። የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን የፈጠራ ውጤቶቹን በመገምገም በየዘርፉ የተሻሉትን የፈጠራ ውጤቶች ደረጃ መለየቻቸውም ታውቋል። በአውደ ርዕዩ ላይ በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ የ1ኛ እና 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው የቀረቡት። በአውደ ርዕዩ በየዘርፉ የተሻለ የፈጠራ ሃሳቦችን እና ውጤቶችን ይዘው ለቀረቡት ተማሪዎች ሽልማት ተሰጥቷል።    
ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በምርምር በማዳበር የመድኃኒት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት እየተሠራ ነው
May 2, 2026 119
ደብረ ብርሃን፤ ሚያዝያ 24/2018 (ኢዜአ)፡- ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በምርምር በማዳበር የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው 5ኛውን ሀገር አቀፍ የጤና ምርምር ሲምፖዚየም አካሂዷል። በዩኒቨርሲቲው የአሥራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ በዚሁ ወቅት፤ ዩኒቨርሲቲው ሀገር በቀል ዕውቀቶች ላይ ተግባር ተኮር ምርም እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። በአንኮበር የዕጽዋት የምርምር ጣቢያ በማቋቋም የመድኃኒት አቅርቦትና ሌሎች ዘርፎች ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ሥራ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። በጣቢያው ዕጽዋት ለመድኃኒት ቅመማና ክትባት ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ዐቅም ለመፍጠር ከአርማወር ሐሰን የምርምር ኢንስቲትዩትና ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በምርምር የተገኙ ውጤቶችን በማዳበር ወደ ተግባር የሚሸጋገሩበትን ሂደት ለማሳካት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።   በአርማወር ሐሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የዕውቀት አስተዳደርና ሥርፀት ዳይሬክተር ዶክተር አክሊሉ ዓለሙ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በመድኃኒትና ክትባት ላይ በማተኮር እየሠራ ይገኛል። በሀገር በቀል ዕውቀቶች ላይ የተመሰረተ የመድኃኒት አቅርቦት ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የጀመረው ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።   የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር እያሱ መስፍን ደግሞ፤ በዘርፉ የምርምር ኮንፈረንስ መዘጋጀቱ የዕውቅትና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ችግር ፈች የምርምር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥልሉ ያደርጋል ነው ያሉት። ይህም በጤናው ዘርፍ እየተካሄደ የሚገኘውን በሽታን የመከላከልና አክሞ የማዳን አቅጣጫ በሳይንሳዊ ምርምር በማገዝ ውጤማ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል።
በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ ነው
May 2, 2026 109
ጋምቤላ፤ ሚያዝያ 24/2018(ኢዜአ)፦ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትል ለማረጋገጥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ። ’’አርብቶ አደሮችና ትምህርት’’ በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ዛሬ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው።   በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በኮንፍረንሱ እንደገለጹት፣ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማስፋፋት በሰራቸው ተግባራት ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይም የተጀመሩ ኢንሼቲቮችና ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በማህበራዊ ልማት በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል። በዚህ ረገድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማውጣት ለፖሊሲ ግብዓት እንዲውሉ ሲያከናውኑ የቆዩትን ስራዎች ማጎልበት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይም በአርብቶ አደሮች አካባቢ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ለልማት እንዲውል በምርምር በማገዝ የአርብቶ አደሩ ሕይወት እንዲለወጥ በማድረግ በኩል የላቀ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል። በተለይም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማሳደግ የሚያግዙ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል።   የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሰለጠነ የሰው ኃይል ከማፍራት ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ወደ ልማት የሚቀየርበትን አቅም በምርምር እንዲያግዙ ጠይቀዋል። ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስም በቀጣይ ለሚወጡ ሀገራዊ የልማት ፖሊሲዎች ጠቃሚ ግብዓቶች ለማፍለቅ ያግዛል ብለዋል።   የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ጎን ለጎን የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የአካባቢው ማህበረሰብ ሕይወት እንዲለወጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመድረኩ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ተጨማሪ ግብዓቶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያገኝም ተናግረዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
May 3, 2026 47
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋሉ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከመቻል ጋር ይጫወታል። ባህር ዳር ከተማ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ451 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ23ኛ ሳምንት አዳማ ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ባህር ዳር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ እና ከወራጅ ቀጠና ስፍራ ለመራቅ ይጫወታል። ተጋጣሚው መቻል በበኩሉ ካሸነፈ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘግባል። በሌላኛው መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከሸገር ከተማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። አርባምንጭ ከተማ በ10 ነጥብ የመጨረሻው 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሸገር ከተማ በ44 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ባለፉት 16 የሊግ ጨዋታዎች ያላሸነፈው አርባምንጭ ከተማ ዛሬ ከተሸነፈ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ይረጋገጣል። በ23ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 የረታው ሸገር ከተማ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል። ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከልደታ ክፍለ ከተማ ይጫወታሉ። ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ልደታ ክፍለ ከተማ በ19 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በ23ኛ ሳምንት በሸገር ከተማ የተሸነፈው ሲዳማ ቡና ወደ ድል መንገድ ለመመለስ ይጫወታል። ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያላሸነፈው ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ እና ከወራጅነት ስጋት ለመላቀቅ ይጫወታል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ60 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ 60 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃ የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በ23 ግቦች ቀዳሚ ስትሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በ18 ግቦች ትከተላለች።
ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 3, 2026 70
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ ከመላው ዓለም የተውጣጡ የብስክሌት ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኢሊሚኔተር (UCI City Mountain Bike Eliminator) ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል። የዓለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፈው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ፣ በኢትዮጵያ የሚካሄድ ይሆናል። ውድድሩ የሚካሄደው በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ነው። በዓለም አቀፉ ውድድር ላይ ከ24 የአውሮፓ እና ከ10 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ብስክሌተኞች እንደሚሳተፉ ተገልጿል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያን በዓመታዊው የዓለም አቀፍ የከተማ ማውንቴንባይክ ካሌንደር ውስጥ ከባርሴሎና በመቀጠል ሁለተኛዋ መዳረሻ ያደርጋታል። የኤሊት ተወዳዳሪዎች (ወንድና ሴት) የጊዜ ሙከራ፣ የግማሽ ፍጻሜ እና የፍጻሜ ውድድሮች ይከናወናሉ። ውድድሩ በዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዋናው ውድድር አስቀድሞ ትናንት ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች የመሳተፍ እድል አግኝተዋል። በዕለቱ የአማተር ብስክሌተኞች፣ የልጆች እና የሰዓት ሙከራ ውድድሮች ተደርገዋል። የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ ዓለም አቀፍ ውድድሩን ለኢትዮጵያ ስፖርት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጿል። ውድድሩ ኢትዮጵያን ለዓለም ከማስተዋወቁ ባሻገር፣ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ውድድሮች የማዘጋጀት አቅም እንዳላት በተግባር እንደሚያሳይ አመልክቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በሀገራቸው ከዓለም ኮከቦች ጋር የመወዳደር እድል እንዲያገኙና ወደ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ እንዲሸጋገሩ ትልቅ ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግል ነው ፌዴሬሽኑ ያስታወቀው። ለኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎም ይታመናል። በአዲስ አበባ የስፖርት መሰረተ ልማቶች መስፋፋት ከተማዋ ዓለምአቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማካሄድ ተመራጭ አድርጓታል። በቅርቡ የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን ውድድር በመዲናዋ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
የእንግሊዝ እግር ኳስ ኃያላን ፍልሚያ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል
May 3, 2026 63
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛው ሳምንት መርሐ-ግብር፤ በታሪካዊ ባላንጣነታቸው የሚታወቁት ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ በብዙዎች ዘንድ ተጠባቂ ሆኗል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይካሄዳል። ማንችስተር ዩናይትድ በ61 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በ58 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁለቱ ክለቦች እስከ አሁን በሁሉም ውድድሮች 244 ጊዜ ተገናኝተው ማንችስተር ዩናይትድ 92 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ ሊቨርፑል 82 ጊዜ አሸንፏል። 70 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ሁለቱ ክለቦች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባደረጓቸው 67 ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ 30 ጊዜ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል 20 ጊዜ አሸንፎ 17 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ባለፉት አምስት የሊግ ግንኙነታቸው ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ አንድ ጊዜ ሲያሸንፉ በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። ለ131 ዓመታት የዘለቀ ታሪካዊ ተቀናቃኝነት ያላቸው ሁለቱ ክለቦች በተመሳሳይ የሊጉን ዋንጫ 20 ጊዜ በማንሳት ስኬታማ ክለቦች ናቸው። ማንችስተር ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ እየተመራ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጥሩ ግስጋሴ እያደረገ ይገኛል። ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ወይም አቻ ከወጣ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋግጣል። የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርገው ፉክክር የዛሬው ጨዋታ ወሳኝ ነው። የ40 ዓመቱ ዳረን ኢንግላንድ ተጠባቂውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል። በሌላኛው የሊጉ መርሐ ግብር አስቶንቪላ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ በቪላ ፓርክ ስታዲየም ይጫወታሉ። አስቶንቪላ በ58 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ሲይዝ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ34 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ጨዋታው አስቶን ቪላ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነቱን ለማረጋገጥ፣ ቶተንሃም ደግሞ በሊጉ የመቆየት ህልውናውን ለመታደግ በሚያደርጉት ፉክክር ውስጥ ወሳኝ ትርጉም አለው። ዌስትሃም ትናንት መሸነፉን ተከትሎ ቶተንሃም ዛሬ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠና ይወጣል። ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ከቀኑ 10 ሰዓት በቫይታላቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ባለፉት 14 የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልቀመሰው ቦርንማውዝ በ49 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። ክሪስታል ፓላስ በ43 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሀረር ከተማ የኮሪደር ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ
May 2, 2026 211
ሐረር፤ ሚያዚያ 24/2018 (ኢዜአ)፦ በሀረር ከተማ የምሽት የአምስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ። የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ናቸው።   በክልሉ ስፖርት ኮሚሽንና ላንድ አፍሪክ በጋራ አዘጋጅነት የተካሄደው የሩጫ ውድድር "ለብልፅግና እሮጣለሁ ድምፄንም እሰጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ነው። በውድድሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከሐረር ከተማና ገጠር አካባቢ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አትሌቶች ተሳትፈዋል። የሩጫው ውድድሩ ዓላማ በከተማው የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማስተዋወቅና ስራውን ስኬታማ ያደረጉ እጆችን ለማመስገን ታስቦ የተዘጋጀ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በውድድሩ ማጠቃላያ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። በክልሉ ከተማና ገጠር የተጀመሩ የልማት፣ የቅርስ ጥበቃና ሌሎች ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የሜዳልያና የገንዘብ ሽልማት ከዕለቱ ክብር እንግዳ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና ከሌሎች እንግዶች እጅ ተበርክቶላቸዋል።  
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው
May 3, 2026 50
ጅማ ፤ ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት አተገባበር በምሳሌነት የሚጠቀስና ተጨባጭ መሆኑ ተመላከተ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን በመከተል ላይ ትገኛለች። ስትራቴጂው በዋናነት ዘላቂነት ባለው የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና በፈጠራ የታገዙ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልምዶችን በማስፋፋት ላይ ያተኩራል። ለአብነትም የአፈር እና ውሃ ጥበቃን ማጠናከር፣ ድርቅ የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መጠቀም እና ከበካይ ጋዝ ነፃ የሆኑ የኃይል ምንጮችን ማስፋፋት የስትራቴጂው አካላት ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው ጉዞ ከበካይ ጋዝ ልቀት የጸዳ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የያዘችው ግብ አካል ነው። ለተግባራዊነቱም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ ዘመናዊና አረንጓዴ ትራንስፖርት እንዲሁም የግብርና እና ተፋሰስ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራች ትገኛለች። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ በኢትዮጵያ የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት (GGGI) ዳይሬክተር እና በኢትዩጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ጋር ቆይታ አድርጓል። የግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲቲዩት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ሁሉን አቀፍና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ ኢኮኖሚን እንዲገነቡ እገዛ ያደርጋል።   በኢትዮጵያ የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ኦኬቹኩ ዳንኤል ኦግቦናያ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ተቋቁማ ያስመዘገበችው እድገት ቀጠናውን በልማት ለማስተሳሰር ተጨማሪ እቅም እየፈጠረ ነው። የአረንጓዴ የኢኮኖሚ ልማቱም የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የስራ እድል እንዲስፋፋና ኢንቨስትመንትን ለመሳብም ተደማሪ አቅም በመፍጠሩ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገሪቱ በታዳሽ ኃይል ልማት በውሃ፣ በነፋስና ጸሐይ ላይ የሚደረጉት ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችም በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚያስችላት ተናግረዋል።   በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት አስተባባሪ ከፈለኝ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ታሳቢ ያደረገ እድገትን መገንባት እንደሚያስችላት ጠቁመዋል። ለዚህም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች ተከላና የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ምርታማነት እንዲጨምር ማገዛቸውን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የሰሃራ በረሀ መስፋፋትን ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተደቀነውን ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አየገነባች መሆኗን አስተባባሪው ገልጸዋል። አትዮጵያ ቀጣናውን በጋራ ልማት ለማስተሳሰር የጀመረችው ተግባርም የሚበረታታ መሆኑንም አክለዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች ነው - አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ
May 1, 2026 321
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 23/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችል አስደናቂ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ እየገነባች መሆኑን በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ገለጹ። የኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በአረንጓዴ አሻራ፣ የውሃ፣ የንፋስና የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ምንጮችን በማስፋፋት ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ያስገኘ ዕድገት እያመጣ ይገኛል። የበካይ ጋዝ ልቀትን የሚቀንሱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አማራጮችን ማበረታታትና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ዘላቂ ግብርናን የሚያሳልጡ ስትራቴጂክ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። ይህ የተቀናጀ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ዕድገትን በማፋጠን ለቀጣዩ ትውልድ አስተማማኝ መሰረት እየጣለ ይገኛል። በኢትዮጵያ የአየርለንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ የትብብር መስኮችን በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ እየሰራች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ተምሳሌትና ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ስኬቶችን እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል። በተለይም በታዳሽ ኃይልና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተመዘገቡ ውጤቶች የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን መቋቋም የሚያስችሉ መሠረቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም አየርላንድ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎችን ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። የኢትዮ-አየርላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባላቸው የልማት መስኮች በአጋርነት እየተሰራ አንደሚገኝም አምባሳደሯ ገልጸዋል። ኢትዮጵያና አየርላንድ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር የበለጠ በማጠናከር በተለያዩ የልማት መስኮች የሚደረጉ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር እንደምታጠናክርም አምባሳደሯ አረጋግጠዋል።
ዘንድሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ ይተከላል
Apr 30, 2026 333
ደብረ ብርሃን፤ ሚያዝያ 22/ 2018 (ኢዜአ)፡- በመጪው ክረምት በሚካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ከ36 ሺህ ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኝ እንደሚተከል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል። ለመጪው ክረምት አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሚተከሉ 294 ሚሊየን ችግኞች እስካሁን መዘጋጀታቸውን በመምሪያው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ቡድን መሪ ጌታነህ ተ/ማርያም ገልጸዋል።   በቀሪ ወራትም ፈጥነው የሚደርሱ ችግኞች ላይ በማተኮር የማዘጋጀት ሥራው እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። በአጠቃላይም በመጪው ክረምት ከ36 ሺህ 260 ሔክታር በሚልቅ መሬት ላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ለኢዜአ ተናግረዋል። ከአሁን በፊት የተተከሉ ችግኞች አርሶ አደሩን በእንስሳት ዕርባታና ማድለብ፣ በንብ ማነብ፣ በመኖ አቅርቦትና በሌሎች የሥራ ዘርፎች በማሰማራት ጥምር ግብርናን ለማስፋፋት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ብለዋል። በዞኑ ባለፉት ዓመታት የለሙ 1 ሺህ 163 ተፋሰሶች የአፈር ለምነትን በማሻሻል፣ የገጸና ከርሰ ምድር ውኃን በማበልጸግና ለመስኖ ልማት በማዋል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውንም አክለዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ባለማነው የፍራፍሬ ችግኝ ተጠቃሚነታችን አድጓል-አርሶ አደሮች
Apr 29, 2026 281
ሃዋሳ ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኝ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገላቸው በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በሲዳማ ክልል የሸበዲኖ ወረዳ አርሶ አደሮች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ያለሙት የፍራፍሬ ችግኞች አድገው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እያስቻሉ ነው፡፡ በወረዳው የፉራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር መሃመድ ቦጋለ እና አርሶ አደር ሄርቲሞ ሬቢሶ የቡና ችግኝ በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡   ችግኞቹን በኩታ ገጠም በመትከል፣ የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀትና ለጥላ የሚሆን እንሰት በመትከል ተገቢውን እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አቮካዶን ጨምሮ ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ በአቮካዶ ልማት የተሳተፉት አርሶ አደር ሙሴ በቴሾ ናቸው፡፡   ላለፉት ስምንት ዓመታት ሁለት ሄክታር በሚጠጋ ማሳቸው ላይ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው የአቮካዶ ችግኞችን ተክለው በማልማት ምርቱን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚሸጡም አክለዋል። የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ጽህፈት ቤት የቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለሙያ አቶ ደሞዜ ሌዳሞ እንዳሉት በወረዳው በዘንድሮው ዓመት ከ726 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።   በተለይም ቡና በክላስተር በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ቡናን ጨምሮ ለፍራፍሬና ለምግብት ለሚውሉ ችግኞች ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት ደግሞ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ናቸው፡፡   በመርሃ ግብሩ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በመርሃ ግብሩም አቮካዶ፣ አፕልና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ለእንስሳት መኖም ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በክልሉ ለዘንድሮ ዓመት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ322 ሚሊዮን በላይ ችግኖች የተዘጋጁ ሲሆን በቡና ችግኝ ተከላ የተጀመረው መርሃ ግብር እስከ መጪው ሃምሌ ወር እንደሚከናወንም አስረድተዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት ይገባል 
Apr 28, 2026 586
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የአህጉሪቷን የልማት ግቦች ለማሳካት የአፍሪካ ሕብረትና አባል ሀገራትን የፖሊሲ አቅጣጫ አሰናስሎ መምራት እንደሚገባ የሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃጸም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 ጎን ለጎን የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው።   የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድን ሀገር በቀል በማድረግ አካታች ዕድገትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ሽግግርን የሚያፋጥን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራትም ብሔራዊ የልማት ዕቅዶችን ከአጀንዳው ጋር በማጣጣም የበጀት ድልድልና የፖሊሲ እርምጃዎችን ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦች የበለጸገች አህጉርን እውን ለማድረግም የአባል ሀገራት ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። የአጀንዳ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን በማሳካት የተሳለጠ የለውጥ ሽግግርን ለመፍጠርም ጠንካራና የተሰናሰለ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ የፖሊሲ ፍሰት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የመንግሥታት፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች በወሳኝ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚኖራቸውን ትብብርና ቅንጅት የሚያበረታታ ምኅዳር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።   የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትርና ተሰናባቿ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ ቢሮ ሊቀ-መንበር ሮቢናህ ናባንጃ በበኩላቸው፤ የአፍሪካውያን ድምፅ በወሳኝ የዓለም መድረኮች ላይ መንፀባረቅ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች በከፍተኛ ደረጃ ከሚደረግ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ባለፈ በወሳኝ ስትራቴጂክ ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ብለዋል። የአፍሪካ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካትም ሎጂስቲክስ፣ ትራንስፖርትና መሰል የትኩረት ዘርፎች ላይ በስፋት በመሰማራት ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች ነው
Apr 28, 2026 322
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የአጀንዳ 2030 እና 2063 ዘላቂ የልማት ዕቅዶችን በመተግበር ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየች መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ ገለጹ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር "የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀና አሻጋሪ አካሄድ መከተል" በሚል መሪ ሐሳብ ያዘጋጀው 12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ጉባኤ የአፍሪካ ሕብረትን የአጀንዳ 2030 እና 2063 የዘላቂ የልማት ግቦችን አፈፃፀም ይገመግማል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊክ ሀዳዲ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳ 2030 እና 2063 በትይዩ የሚሄዱ ሳይሆን እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው። በአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ሽግግር ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት የሁለተኛውን የአሥር ዓመት የአጀንዳ 2063 የትግበራ ዕቅድ ሀገር በቀል እንዲሆን መሠረታዊ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። የሕብረቱ አባል ሀገራት ብሔራዊ የልማት ዕቅዶቻቸው ከአጀንዳው ጋር እየተጣጣመ መምጣቱን በማንሳት፤ የበጀት ድልድልና ፖሊሲዎቻቸው ለአፍሪካ የትኩረት መስኮች ቅድሚያ የሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአጀንዳ 2030 እና 2063 ግቦችን በማሳካት የበለጸገች አፍሪካን እውን ለማድረግ በሀገራት መካከል ያለው ቅንጅትና ትብብር ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸውን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ አለባቸው
Apr 27, 2026 348
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2018 (ኢዜአ)፦‎ አፍሪካውያን የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የማዕድን ሀብታቸው ላይ እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታንዛኒያ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የአፍሪካ ወሳኝ ማዕድናትን ለአረንጓዴ የኢንዱስትሪ አብዮትና ዘላቂ ልማት ማዋል" በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁት የ12ኛው የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ቀጣናዊ ቅድመ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ ክላቨር ጋቴቴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ እንደ ኮባልት፣ ሊቲየም፣ ግራናይት እና ሌሎች የከርሰ ምድር ሀብቶችን ጨምሮ የዓለምን 30 በመቶ ማዕድናትን ይዛለች፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብቻዋን የዓለምን ከፍተኛ የኮባልት ማዕድን የያዘች መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም አፍሪካን የዓለም አቀፍ የኃይል ሽግግር /Energy Transition/ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል፡፡ አፍሪካ ዩራኒዬምና ሌሎች የከርሰ ምድር የከበሩ ማዕድናት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ፤ ለዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል አቅርቦት አስተዋጽኦ ከማድረግ ባለፈ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ኃይል ልማት እያመሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አፍሪካ የከበሩ ማዕድናት ባለቤት ብትሆንም አብዛኛው በጥሬ እቃ መልክ ወደ ውጭ የሚላክ በመሆኑ የአህጉሪቱ የእርስ በእርስ ግብይት ከሁለት በመቶ እንዳማይዘል ተናግረዋል፡፡ በአህጉሪቱ የማዕድናት ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን መገንባት ቢቻል በየዓመቱ ከ24 ቢሊየን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘትና ለ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማዕድን ፖሊሲ ለእሴት መጨመር፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ሁሉን አቀፍ ልማት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በአህጉሪቱ የተቀናጀ ቀጣናዊ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለውን ፍላጎት በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አህጉራዊ የማዕድን ሀብቶችን ወደ ዘላቂ ብልጽግና መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህም የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጣናዊ እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር የማዕድን ጸጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን ማጠናከሩን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዘላቂ ልማት አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ካዳሪ ሲንጎ በአፍሪካ ሁሉን አቀፍና አካታች ዕድገት ለማስመዝገብ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አፍሪካውያን በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ የሚኖረን ትብብርና ተሳትፎ ስትራቴጂያዊና መዳረሻ ግብ ያለው መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ አብዮት ሽግግርን ለመፈጠር በአቅም ግንባታ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ተምሳሌት ነበሩ
Apr 7, 2026 725
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ እሴት በተግባር ያሳዩ ታላቅ ዲፕሎማት ነበሩ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ስመጥር በሆኑት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደሯን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ፈር ቀዳጅ፣ ታላቅ ዲፕሎማት እና ህይወታቸውን ለሀገራቸውና ለአህጉሪቱ እድገት የሰጡ ጽኑ አፍሪካዊት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ለበርካታ አስርተ አመታት የዘለቀ አርአያነት ያለው ሙያዊ ስኬት ማስመዝገባቸውንና ከኢትዮጵያ ቀዳሚ ሴት አምባሳደሮች አንዷ በመሆንም ለአፍሪካውያን ሴት ዲፕሎማቶች የብርሃን ፋና መሆናቸውን አመልክተዋል። የአፍሪካን ጥቅም ለማስከበርና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የነበራቸው የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለአህጉራዊ የጋራ ግቦች መሳካት የጎላ ሚና እንደነበረውም አውስተዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ቆንጂት በታማኝነት፣ በልዩ ብቃት እና ለጋራ የወደፊት እጣ ፈንታ የነበራቸው ጽኑ ቁርጠኝነት የአፍሪካ ዲፕሎማሲ እሴቶች ያላቸውን ጽኑ አቋም ያሳየ መሆኑንም ነው ያነሱት። የአምባሳደሯ የዲፕሎማሲ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ዲፕሎማቶች፣በተለይም ለሴቶች፣በድፍረትና በዓላማ እንዲያገለግሉ ዘላቂ መነሳሳት ሆኖ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ስም ለአምባሳደር ቆንጂት ቤተሰቦች፣ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ፣ እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 15
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ‎ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Apr 26, 2026 464
ክልሎች፤ሚያዝያ 18 /2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር የምንቃኝበት ነው። በዚህ ሳምንትም አንኳር የክልሎች ክንውኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ቀርበዋል። የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተም! ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማት ስራ መደባኛ ስራዋ ካደረገች ወዲህ አያሌ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ባለፉት ዓመታት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእቅድ እና በቁርጠኝነት በመከናወኑ ከውጪ የሚገባ ስንዴ ቀርቷል፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረቱም ቀጥሏል። ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ሽግግርም ዓመቱን ሙሉ በማልማት እየታጀበ ሲሆን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ ነው። በዚህ ውስጥ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አበረታች ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል። በተያዘው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊማ፣ በጂዳ ወረዳ ሲባ ሲርቲ እና ቂምቢቢት ወረዳ ሰገሌና ደርማሙሳ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ እና በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ የስንዴ ቡቃያ አስቃኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፎቶ ጋር ያያዙት መልዕክትም ''ይህ የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጫ ማህተማችን ነው'' ይላል። ብሪክስ -- ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በባህር ዳር ከተማ ''የብሪክስ አሁናዊ አቅሞች እና የኢትዮጵያ የልማት ትብብር ትኩረቶች'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ጉባኤ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ከተሳትፎ ባለፈ መፍትሄ አቅራቢ በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑ ይታወቃል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር መሐመድራፊዕ አባራያ በመድረኩ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሳትፎዋን በማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረቱ የተደራጁ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የሚጠቅሙ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች። መድረኩም ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችላት የሁለትዮሽ ትብብር ጭምር የተካሄደበት፤ በብሪክስ ማዕቀፋ በተለይም በግብርና እና ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና መሰል ዘርፎች ልምድ የተሰጠበትም መሆኑ ተመላክቷል። ማረም እና ማነጽ የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል እንዲሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት መሰጠቱ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነው። የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ “የማረሚያ ተቋማት ለሀገር ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የማረሚያ ተቋማት የሰብዕና እና የክህሎት ግንባታ ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት፣ ከማረሚያ ቤት የሪፎርም ሥራዎች እንዲሁም ከማረም የማነጽ ተሃድሶ ልማት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ጉባኤው በልዩ ሁኔታ የመከረበት ነው። ኢትዮጵያ ማምረቷን ቀጥላለች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ እንደቀጠለ ነው። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤክሲፖ ላይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ ነው ብለዋል። ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት። ዘንድሮ ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል። ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል በኢትዮጵያ ቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ውኃ የህልውና ጉዳይ ነው። በእርግጥ ለፍጡራን ሁሉ ውኃ ህይወት ቢሆንም በእነዚህ አካባቢዎች ግን ውኃ ይበላል፤ ውኃ ይጠጣል። በሳምነቱም በአፋር ክልል ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአይሳኢታ አፋምቦ የብዙሃን መንደር እና የአይሳኢታ ከተማ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተከናወነው ልማት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተግባር ከመመለሱ በላይ፣ በየደረጃው ያለውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፤ መንግስት የውሃ ሽፋን አነስተኛ ለሆነባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ በፕሮጀክቶች ታግዞ መስራት እንደሚገባ በጽኑ ያምናል፤ በተለይም የለውጡ መንግስት ለቆላማ እና አርብቶ አደር አካባቢዎች በሰራው ስራ የውኃ ተደራሽነት በእጅጉ ማደጉን አንስተዋል። ልምድ ልውውጥ እና ተሞክሮ -ለምክር ቤቶች ሌላው ቅኝታችን በዚህ በተጠናቀቀው ሳምንት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤትና የዞን ምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱን የዳሰሰ ነው። የጋራ የምክክር መድረኩ ዓለማ የልምድ ልውውጥና የልማት ሥራዎችን በመመልከት ተሞክሮ መለዋወጫ ነው።የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ መንግስት ሕዝቡ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የምክር ቤቶችን አደረጃጀት ማጠናከርና የክልሉ ሕገ መንግስት ያስቀመጣቸውን ኃላፊነቶች መፈጸም ይገባል ብለዋል።የመንግስት የልማት ኢኒሼቲቮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ በመሆናቸው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው መተግበር እንዲችሉ ምክር ቤቶች ያለሰለሰ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተመልክቷል። የጤና ልማት ስራ እስከ አክሞ ማዳን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ በሚደረግ ጥረት የአጋር ድርጅቶች አስተዋጾ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም የተመለከተው በዚህ ሳምንት ነው። ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጋር በመሆን በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ መሰል የጤና ዘርፍ የልማት ስራዎች መንግስት በዘርፉ የያዘውን ውጥን ከማሳካት አንጻር እገዛቸው ትልቅ መሆኑን አንስተዋል።ማዕከሉ ማህበረሰቡ በቅርበት ሕክምና እንዲያገኝ ከማስቻል ባለፈ ወደ ሌላ አካባቢ ሄዶ ሲታከም ሊያወጣ የሚችለውን ወጪ ያስቀራል። ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ማሽኖች፣ የመድሃኒት ቤት፣ መኝታ አልጋዎችና የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሟልቶ የተገነባ መሆኑም ታውቋል። የከተሞች ኮሪደር- ከቱሪዝም እስክ ኮንፍረንስ ማዕከልነት በኮሪደር ልማት እጅግ ከተዋቡ እና ከደመቁ የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ሀዋሳ አንዷ ናት። በሳምንቱ የከተማዋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ማጠናቀቂያ የምስጋናና ዕውቅና እንዲሁም የአራተኛ ዙር የኮሪደር ልማትና የሐይቅ ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡ የሲዳማ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ‎ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርቡ ቀጥሏል ብለዋል። በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሪደር እና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ስራዎች እንደሚቀጥሉ አንስተው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከልነት ለማጠናከር ሥራዎች በላቀ ፍጥነትና ጥራት መከናወናቸውን እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ምርጫ -የዴሞክራሲ መሰረት ሳምንቱ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት መራጮች የምርጫ ካርድ ወስደው ለምርጫው ዝግጁ መሆናቸውን የገለጹበትም ነበር። ኢትዮጵያዊያን መጪውን ጊዜ የተሻለ የሚያደርግላቸውን መንግስት ለመመረጥ ዝግጅታቸውን በተግባር እያረጋገጡ ነው።
ከአፍሪካ አቪዬሽን መሪነት እስከ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር
Apr 23, 2026 466
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና በአህጉሪቱ ትልቁ የሆነውን የ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ መጀመሯን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል። ጋዜጠኛ ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ይህ ሜጋ ፕሮጀክት አፍሪካውያን ተጓዦች ከአህጉሩ ውጭ ባሉ እንደ ዱባይ፣ ፓሪስና ለንደን ባሉ ማዕከላት በኩል የሚያደርጉትን አድካሚ ጉዞ በማስቀረት፣ አዲስ አበባን የአህጉሪቱ ቀዳሚ የመገናኛ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ግንባታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአቪዬሽን መሰረተ ልማት ተብሎ መጠቀሱን ጋዜጠኛው በዚሁ ጽሁፉ አመልክቷል።   ስራው በይፋ የተጀመረው ባለፈው ጥር ወር ሲሆን፣ አውሮፕላን ማረፊያው በ2023 ዓ.ም (2030 እ.ኤ.አ) የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል። ይህም አውሮፕላን ማረፊያውን በዓለም ላይ በርካታ ተጓዦችን ከሚያስተናግደው የአትላንታው ሀርትስፊልድ-ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ካለው አቅም በላይ እንደሚያደርገው ዳንኤል ኦሊቫሬስ ጋሌጎ ባሰፈረው ጽሁፍ አብራርቷል። አውሮፕላን ማረፊያው ከመንገደኞች አገልግሎት ባለፈ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን (AfCFTA) በላቀ ሁኔታ ለመደገፍ ታቅዶ የተገነባ መሆኑን ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ በዝርዝር አስቀምጧል።   በዓመት 3 ነጥብ 73 ሚሊዮን ቶን ጭነት የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ መሠረተ ልማት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የአፍሪካን የጭነት በረራ ፍላጎት በሚገባ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆኑን ተጠቁሟል። የአውሮፕላን ማረፊያው የተርሚናል ዲዛይን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ በሆነው ዛሃ ሃዲድ አርክቴክትስ የቀረበ መሆኑን የጠቀሰው ጋዜጠኛው፣ዲዛይኑ የኢትዮጵያን ታላቁ ስምጥ ሸለቆና የተለያየ መልክዓ ምድራዊ ውበትን የሚያንፀባርቅ መሆኑን በጽሁፉ አካቷል። ተጓዦች በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ ሲዘዋወሩ የኢትዮጵያን ባህልና ተፈጥሮ እንዲመለከቱ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ለዘላቂነት ቅድሚያ በመስጠት የፀሐይ ብርሃን ኃይልንና የዝናብ ውሃ አሰባሰብ ስርዓትን እንዲጠቀም ተደርጎ ተቀርጿል።   በአጠቃላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መጠናቀቅ፣ኢትዮጵያ በአፍሪካ አቪዬሽን ያላትን መሪነት ከማረጋገጡ ባለፈ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ጋዜጠኛው በሲኤንኤን የጉዞ ገጽ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ ደምድሟል። ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች ጋር በመተባበር የነጠላ የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያን (SAATM) ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝም ተመልክቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
በኢዜአ ዐይን …!
Apr 19, 2026 530
የምግብ ሉዓላዊነት - ከተረጂነት መላቀቂያው መንገድ በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ ከተረጂነትና ጠባቂነት መፋቻ መንገዶች መካከል የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንዱ ብልኀት አድርጋ እየታተረች ነው። ይህን ተከትሎም የዜጎችን የምግብ ፍላጎት በራስ የምርት ዐቅም የመሸፈን ሥራ በመከወን ከጠባቂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ስኬታማ ናቸው። ለዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ከልመና ወጥታ ወደ ውጭ ገበያ መላክ መጀመሯ አሥረጅ ነው። በመሆኑም ከውጭ የኢኮኖሚ ጥገኝነት በመላቀቅ የዜጎችን የምግብ ሉዓላዊነት ለማስከበር በስንዴ ልማት የተመዘገበውን ስኬት በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለመድገም ርብርብ እየተደረገ ነው። በዚህም መሠረት በሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ሻይ ቅጠል እና ሌሎች የተለያዩ ሰብሎች ላይ እየተከናወነ ያለው ሥራ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምግብ ዋስትናና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ የአመራር ቁርጠኝነት የአግሪኮላ ሜዳሊያ በ2016 ዓ.ም ማበርከቱ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረት የተሰጠ ዕውቅና ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ረሃብን ከማስቀረት ባለፈ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ብሔራዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ ጥሬ ሃብቶች፣ተስማሚ የዓየር ንብረት፣ ለሥራ ትጉ የሆነ ወጣት እንዳላት እና እነዚህን ሃብቶች ታሳቢ በማድረግ የታሪክ ዐውራ የሆነችውን ሀገር ልማት ወደፊት ለማራመድ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ እንደከፈልን ሁሉ፤ ከምግብ ጥገኝነት ለመላቀቅ በትጋት መሥራት ይገባል ሲሉ ማስገንዘባቸው ይታወሳል። የምግብ ሉዓላዊነት፣የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፣ የበጀት ሉዓላዊነት ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ መሆናቸውንም አብራርተዋል። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበርም ብሔራዊ ዐርበኝነት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። ሀገራዊ ትልሙ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያሸጋግር መልካም ጅማሮ ነው።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 2, 2026 267
ከሚያዝያ 18 እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም (Invest in Ethiopia Forum) አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው ብለዋል። ‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው "ጎበዝ ሶላር ሴል" ማምረቻ ዘመናዊ ማሽኖች እና በቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ገልጸው፣ ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድልም ፈጥሯል ነው ያሉት። ‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጌጋዋት ዓመታዊ የማምረት ዐቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ ዐቅም ፈጥሯል ሲሉም ተናግረዋል። በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የጫማ ማምረቻ እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ጣቢያን ተመልክቻለው ብለዋል በመልዕክታቸው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራዳ ፓርክን መመረቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት አራዳ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አዲስ አበባን ለመለወጥ ያለንን ርዕይ በተግባር ያሳየንበት አንዱ ሥራችን ነው ብለዋል። ቀደም ሲል ተዘንግቶና ለአደጋ ተጋልጦ የነበረው የአራዳ አካባቢ፤ ዛሬ ተመልሶ ተገንብቶ አስደናቂ የከተማ አካል መሆን ችሏል ሲሉም ገልጸዋል። ‎ኢትዮጵያ ለእኛ በምናብ የምትሳል ህልም ብቻ ሳትሆን በተግባር የምትገነባ እውነታ ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጤናማ፣ ጽኑ፣ ለመጭው ትውልድ ተስፋን ከተጨባጭ ሀብት ጋር የምትሰጥ፣ በአፍሪካ መሪ፣ በዓለም መድረክ ደግሞ ተወዳዳሪ የሆነች ሀገር እየገነባን እንገኛለን ብለዋል። በየቀኑም ተስፋን ወደ እውነታ የመለወጥ ተግባራችንን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል። • ‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተው ሐሳባቸውን ያጋሩበት “የማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀውና በማኅበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‎የማኅበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፤ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች መሆኗን ገልጸው፤ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማኅበራዊ ዘርፍ የለም ሲሉም አስረድተዋል። ‎በየዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ እንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማኅበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም እንዳለበት አስገንዝበዋል። • የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በክብር ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ልማትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጡ የሚችሉ ተጨባጭ ሥራዎችን ቅድሚያ የሰጠ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለእውነተኛ አፍሪካዊ አጋርነት ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ከዚያም ባደረጉት ቆይታ ዘላቂ እና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሠነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ብለዋል። • የበጋ መስኖ እርሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የበጋ መስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሠረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። ‎የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘውን ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ተከትሎም፤ ፍቃዱ ነመራ የተቀናጀ የእርሻ ልማት በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ያሳተፈ የግብርና ሥራ እንዲስፋፋ ለሚደረገው ሥራ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህ በግል ባለሀብት እየለማ ያለው የግብርና ሥራ እንደ ሶላር ያሉ የኃይል አማራጮችን እና የከርሰ ምድር ውኃን በመጠቀም በመስኖ በማልማት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የግብርና ልማት እና የገጠር ሽግግር ሰፊ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉም ገልጸዋል። በተመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግራናይት የሚያመርተውን የኦርላመንት (3ኤም) ማርብልና ቴራዞ ማኑፋክቸሪንግ የሥራ እንቅስቃሴ የጎበኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ፣ ማበረታቻና ድጋፍ እንዲህ ያሉ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ ነው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከወርቅ እስከ ግራናይት በተፈጥሮ የታደለ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ፀጋ ለሀገር ብልጽግና ለማዋል የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት …
Apr 25, 2026 514
ከሚያዝያ 11 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። በሁለቱ ሀገሮች በላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ የተለዋወጥን ሲሆን፤ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን የምናሰፋባቸውን የቀጣይ ስራዎች የተመለከተ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ሲሉም ገልፀዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች አንዱ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲከላ ጋር መምከራቸው ነው። በዚሁ ወቅትም፤ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ስላለን የረጅም ጊዜ ትብብር መክረናል ብለዋል። በተመሳሳይም ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት ይዘው ከመጡት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም በሀገሮቻችን መካከል ስላለው ትብብር ተወያይተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። እንዲሁም የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) በመሆን የተሰጠኝን አዲስ ኃላፊነት በሚመለከት በስፋት ተነጋግረናል ብለዋል። በጤናው ዘርፍ የሚገጥመንን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች ለመወጣት የሰው ሠራሽ አስተውሎትንና የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ዐቅም መጠቀም የጤና ሥርዓታችንን ለማጠናከር፣ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እና ለሕዝባችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ልምድ ለአህጉሩ ለማካፈል እንዲሁም በፍጥነት ከሚለዋወጠው የቴክኖሎጂው ዓለም ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመራመድ የሚያስችሉ ጠንካራ አጋርነቶችን ለመመሥረት ያላትን ቁርጠኝነት ዳግም ታረጋግጣለች ሲሉም አስታውቀዋል። • በኢትዮጵያ የበቆሎ መስኖ ውጤታማነት ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትኩረት ሰጥተን እየሠራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ፤ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል ማለታቸው ይታወሳል። የተገኘው ጅምር ውጤትም፤ ኢትዮጵያ የምግብ ዕርዳታ ከመቀበል ወጥታ ራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ህልማችን ዕውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል። • መሶብ የሞባይል አገልግሎት መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመሶብ አገልግሎት የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የስራውን ውጤታማነት ያረጋገጠ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሰራሩን ይበልጥ መስፋፋት አስፈላጊነትም ገልጸዋል።ዜጎች ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የተቀናጁ አገልግሎቶችን ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ ዛሬ ሥራ የጀመረው የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሠራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ሥርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን ገልጿል። ‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ሥርዓት እንዳለውና የተለያዩ የክፍያ አማራጮች ማካተቱንም አመላክቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል። በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደኅንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል፤ መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ፣ ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የሕክምና ምርመራ ማድረግ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ፣ የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን፣ የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ‎በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል። • የ100 ቀናትና የ9 ወራት የመንግሥት ሥራ አፈጻጸም ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት የሥራ ዘመኑ 3ኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በዚሁ ወቅትም፤ ‎የቀየስነው አዲሱ የኢኮኖሚ አካሄድ በአጭር ጊዜ ትግበራ ጠንካራ ባለሁለት አሃዝ የዕድገት ሂደትን አስመዝግቧል ብለዋል። ጥረቶቻችን የበለጠ ጽኑ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለንን አቋም እና የመተግበር ዐቅም ያሳያሉ ሲሉም አስገንዝበዋል። • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ስለ 3ኛው 100 ቀን አፈጻጸም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛው የ100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ተገምግሟል። በዚሁ ወቅትም አቶ ተመስገን፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ናት፤ የሚገባትም ትልቅ ሥፍራ ነው፤ እኛ ደግሞ የዚህ ታሪክ ሠሪዎች የመሆን ዕድል በእጃችን ላይ ነው ሲሉ አዝገንዝበዋል። በኮሪደር ልማት፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችና በዲጂታል ኢትዮጵያ ዘርፍ የተካሄደው የመሠረተ-ልማት አብዮት የሀገራችንን እንዲሁም የከተሞቻችንን ገጽታና አገልግሎት ቀይሯል ብለዋል። በስንዴ ልማትና በሌማት ትሩፋት አማካኝነት የተረጅነትን ቀንበር ሰብረን ወደ ምግብ ሉዓላዊነት እየተጓዝን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዲፕሎማሲው መስክም ኢትዮጵያ ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት በመሸጋገር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነቷን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሳድጋለች ብለዋል። • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች ባሳለፍነው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 54ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት ምክር ቤቱ፤ በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች፣ በሀገራችን የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን የሚመለከት የኢንቨስትመንት ማበረታቻና ጥበቃ ስምምነት፣ የቁልፍ መሠረተ-ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ፣ በሥድስት ዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ ስምምነቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ እሳት እና ሌሎች ቅጽበታዊ አደጋዎች አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ መክሮ በማጽደቅ ውሳኔዎችን አሳልፏል። • ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች ብሎ ባጋራው መረጃ፤ በመሠረተ-ልማት (የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት)፣ በዲጂታል መሳሪያዎች (ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም)፣ በዲጂታል መንግሥት (በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትሕ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ) የሚሉትን አንስቷል። በተጨማሪም በዲጂታል ክኅሎት (‎5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በዕውቀትና በፈጠራ ማብቃት፣ በተቋማት ግንባታ (‎ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር)፣ በሕግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት (በፋይዳ መታወቂያ ከ40 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት) የሚሉት ጉዳዮችን ጠቅሷል። • የልማት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ኢንሼቲቮችን በመለየት መተግበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባሳለፍነው ሳምንት ባጋራው መረጃ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ሀገራዊ የስንዴ ልማትን በተመለከተም ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን እያረጋገጠች ትገኛለች ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ አዳዲስ የግብርና ዕውቀቶች እየተስፋፉ፣ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ግብዓቶችን እያገኙ፣ ውድ የሆኑ የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የሥራ ዕድሎች እየሰፉና የአርሶ አደሮች ገቢ እየጨመረ ይገኛል ብሏል። ‎‎ከሌማት ትሩፋት አንጻርም፤ የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት እና ምርታማነት እየጨመረ ነው፤ የተመጣጠነ ምግብ በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኝ ከማድረግ ባለፈ፣ አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡና አካባቢው ይበልጥ እንዲጠበቅ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል። ዲጂታል ኢትዮጵያን አስመልክቶም፤ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የማንነት መታወቂያ (ID) ሥርዓቶች ወደ ዲጂታል እየተቀየሩ ነው። የኢንተርኔት ተደራሽነትና የኦንላይን አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የሞባይል ክፍያ ሥርዓት እየተጠናከረ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ ንግድ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ እያተረፈ ነው ብሏል። ‎‎የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማትም፤ የከተሞች መሠረተ-ልማት በአረንጓዴ ትራንስፖርት እየዘመነ ነው ያለው ጽሕፈት ቤቱ፤ ይህም የዜጎችን የኑሮ ጥራት እያሻሻለ፣ የአካባቢ ንግድን እያነቃቃ እንዲሁም በከተማና በገጠር መካከል ያለውን ትስስር እያጠናከረ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት አኳያም፤ የማምረት ዐቅምና የምርቶች እሴት የመጨመር ሂደት እየተሻሻለ ነው ብሏል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እየተተኩ፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እያደገ፣ የግብዓት አቅርቦት እየተጠናከረና አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እየተፈጠሩ ስለመሆኑም አመላክቷል። እያንዳንዱ ምሰሶ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር፣ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው ሲልም በአጽንዖት ገልጿል።
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ጤና ከሀገር በቀል ስኬት ወደ አህጉራዊ መሪነት
Apr 23, 2026 458
(በሙሴ መለሰ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ስራ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂካዊ የሆኑ ተቋማዊና የፖሊሲ መሰረቶች ተጥለዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም ለሀገራዊ ችግሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሄ ለማግኘት ትልቅ አቅም የፈጠረ ሲሆን፣ ብሄራዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተቀርጾ መጽደቁ ደግሞ የዘርፉን ልማትና አጠቃቀም በተደራጀ መንገድ ለመምራት አስችሏል። እነዚህ እርምጃዎች ሀገሪቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና 2030 ስትራቴጂ ውስጥ ቴክኖሎጂውን እንደ ቁልፍ የለውጥ አቅጣጫ እንድትጠቀም በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ዘላቂ ለማድረግም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። በአሁኑ ወቅት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በኮዲንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በክህሎት ለማሰልጠን የተጀመረው ግዙፍ ፕሮግራም የለውጡ አንቀሳቃሽ ኃይል እየሆነ ነው። ከዚህም ባለፈ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የኤአይ ዩኒቨርሲቲ እንዲገነባ መታቀዱና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልነት ውስጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት እንዲሳተፍ መወሰኑ፣ ሀገሪቱ ቴክኖሎጂውን ለውሳኔ ጥራትና ለምርምር በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቀመችበት መሆኑን ያሳያል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች ላለው የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው። በሹመት ደብዳቤው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ AI ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አክሎ እንደገለጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የAI አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል እና በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሀገራዊ ለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ በዝርዝር አስፍሯል። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የAI ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የተያዘው ሥራ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ይህ አህጉራዊ እውቅና በተለይ በጤናው ዘርፍ የታዩ ውጤቶችን ያካትታል። ኢትዮጵያ በኤአይ የታገዘ ዲጂታል ኤክስሬይን ለሳንባ ነቀርሳ ምርመራ ካዋሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ትጠቀሳለች። በተጨማሪም የ"HEP Assist" መተግበሪያን በሙከራ ደረጃ በማስጀመር፣ በገጠር የሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ውስብስብ ምልክቶችን ሲያዩ ሙያዊ የሕክምና ውሳኔ እንዲሰጡ ድጋፍ እየተደረገ ነው። እነዚህ የዲጂታል ጤና ስራዎች በ7 ክልሎችና በ15 ወረዳዎች ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸው፣ ቴክኖሎጂው በገጠርና በከተማ መካከል ያለውን የአገልግሎት ልዩነት ለማጥበብ ያለውን ፋይዳ ያሳያል።   በአጠቃላይ፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ከሚሰጠው የጡት ካንሰር፣ የአንጎል እብጠትና የቆዳ በሽታዎች ምርመራ ባለፈ፣ በግብርና፣ በፋይናንስና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥም በስፋት እየገባ ይገኛል። በ2030 በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት ለመቀየር የተቀመጠው ግብ፣ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት የጀመረችውን የቴክኖሎጂ ነጻነትና የመሪነት ጉዞ ይበልጥ የሚያጠናክር ነው። በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሥርዓት በጤና፣ በግብርና እና በመንግስታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለውጥ እያመጣ ይገኛል። በጤናው ዘርፍ እንደ ካንሰር እና ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመለየት የህክምና ጥራትን ሲያሻሽል፣ በግብርናው ደግሞ የሰብል ተባዮችንና የቡና በሽታዎችን በመለየት ምርታማነትን እያሳደገ ነው። ከዚህ ባለፈም ቴክኖሎጂው በመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ እና በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ሰፊ የመረጃ ትንታኔዎችን በፍጥነት በማከናወን፣ የሥራ ፍጥነትን እና የውሳኔ አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገረ ይገኛል። የዘርፉ ፋይዳ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባለፈ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት እና የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ላይ ያተኩራል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ በማሰልጠን እንዲሁም የፈጠራ ማዕከላትን (Startups) በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በሌሎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ወጥታ የራሷን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ይህም በአህጉር ደረጃ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች እንደ አርአያ በመሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለኢኮኖሚ እድገትና ለማህበራዊ ፍትሃዊነት የመጠቀም ጥቅል ፋይዳው የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ይበልጥ ያጎላል። በተጨማሪም ሹመቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ማግኘቱንና አፍሪካ በኃላፊነትና በፍትሐዊነት በታጀበ የኤአይ አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣም ያደርጋታል።
ኢትዮጵያ በአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ መንገድ
Apr 21, 2026 1683
(በዮሐንስ ደርበው) ታሪክ እንደሚነግረን፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥቅም ለመጀመሪያ ጊዜ ዕውቅና ያገኘው የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን በሚመለከተው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1883 በተፈረመው የፓሪስ ስምምነት እንዲሁም፤ በ1886 የተፈረመውን የሥነ-ጽሑፍና ሥነ-ጥበብ ሥራዎች ጥበቃን የተመለከተውን የበርን(ስዊዘርላንድ) ስምምነት ተከትሎ ነው። እነዚህ ስምምነቶችም በዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት የሚተዳደሩ መሆናቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣንን፤ በ2022 ዓ.ም ፈጠራንና ኢኖቬሽንን በማበረታታት የፈጠራ ሐሳቦችን ወደ ዕሴት በመለወጥ ሂደት ለሀገራዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና የሚጫወት በአፍሪካ ተምሳሌት የአዕምሯዊ ንብረት ተቋም ለማድረግ እየታተረች ነው። ለዚህ ርዕይ መሳካትም፤ ተቋሙ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለሀገራዊ ፈጠራ መጎልበት፣ የኢኖቬሽን፣ ቴክኖሊጂ ሽግግር እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማደግ ጥቅም ላይ የሚውልበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀገራዊ የመዋቅር ሽግግርን መደገፍ የሚል ተልዕኮ አንግቦ እየሠራ ይገኛል። የእስካሁኑ የንግድ ምልክት፣ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና የፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) ምዝገባ   የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ወርቅነህ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2015 ዓ.ም እስከ ያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት ዘጠኝ ወራት ድረስ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እና በፈጠራ ባለቤትነት (ፓተንት) 20 ሺህ 476 ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል። በዚህም መሠረት ይላሉ፤ 14 ሺህ 729 የንግድ ምልክቶች፣ 5 ሺህ 254 የቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም 1 ሺህ 781 የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት ምዝገባ በተቋማችን አማካኝነት ተከናውኗል። የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ምንድን ናቸው? አዕምሯዊ ንብረት ማለት በሰው ልጅ አዕምሮ የሚፈጠሩ የፈጠራ ሥራዎችን የሚመለከት መሆኑን የገለፁት አቶ ብሩክ፤ እነዚህ የፈጠራ ሥራዎች እንደማንኛውም ቁሳዊ ሀብት በንብረትነት የሚታወቁበትን አግባብ የያዘው ሥርዓት ደግሞ የአዕምሯዊ ንብረት መብት እንደሚሰኝ ያስረዳሉ። በዚህ አግባብ፤ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እንደማንኛውም ቁሳዊ ንብረት ሁሉ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ባለመብቶች የሚሰጡ የባለቤትነት መብቶች መሆናቸውን እንረዳለን። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቀርበው እንደ አቶ ዳንኤል ገለጻ፤ ወጥ ሥራዎችን ለማመንጨት የፈጠራ ባለመብቶች ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ከብዙ ድካም በኋላ ያገኟቸው የፈጠራ ውጤቶች በመሆናቸው ነው። ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ ለምን አስፈለገ? አንድም፤ የሰው ልጅ ቀጣይ ዕድገትና የኑሮ ደኅንነት ዋስትና መሠረት የሚያርፈው በቴክኖሎጂና ባሕል ዘርፎች በሚያሳርፋቸው ፈጠራዊ ብቃቶቹ በመሆኑ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን ለማካሄድ ተጨማሪ ሀብት የሚያስገኝ በመሆኑና ይህም የኢኖቬሽን ሥርዓቱን ስለሚያሳድግ ነው ይላሉ አቶ ብሩክ። እንዲሁም፤ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃና ዘርፉን ለሕዝብ የማስተዋወቅ ተግባር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ የድርሻውን ስለሚወጣና የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት በአጠቃላይ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ደረጃ ላይ እንዲቆም ስለሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ሀገራት ጠንካራ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠሩ ቁጥር ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ የልማት መሣሪያ መሆኑን ይገነዘባሉ። ጠንካራና ፍትሐዊ የአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት በፈጠራ ባለቤቶችና በተጠቃሚው ሕዝብ ዘንድ ሚዛናዊ ነው ያሉት አቶ ብሩክ። በአጠቃላይ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ማድረግ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን በአጽነዖት አንስተዋል። ዜጎች በአዕምሯዊ ንብረት ሥርዓት እንዴት ተጠቃሚ ይሆናሉ? ባለብዙ ቢሊየን ዶላር የፊልምና ድምጽ ሪከርድስ አሳታሚዎችና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎች ለብዙ ሚሊየኖች የመዝናኛ ሥራዎች የሚያበረክቱት የቅጅ መብት ጥበቃ በመኖሩ መሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አቶ ብሩክ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን ምርቶችና አገልግሎቶችን መለየት የሚያስችላቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ምልክቶች ጥበቃና የመብት ማስከበር ሥርዓቶች ባይኖሩ ኖሮ ተመሳስለው በሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች መታለልና ሌሎችም ችግሮች ያጋጥማቸው እንደነበርም ጠቁመዋል። ስለዚህ ምርቶችን በመሸመት ሂደትም በምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያለምንም ግራ መጋባት ግብይቱን ማከናወን እንደሚያስችላቸው መገንዘብ ይቻላል። እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ፤ ለፓተንት የፈጠራ ሥራዎች ጥበቃ በመደረጉ መሰጠት የሚገባቸው ማበረታቻዎች የማይሰጡ ከሆነ፤ የፈጠራ ባለሙያዎች ቀጣይ የምርምር ሥራዎችን ማሳደግና ማስፋት እንደማይችሉ ይገመታል። በቀጣይነት የሚገኙ የተሻሻሉ የፈጠራ ሥራዎች አለመኖራቸው ደግሞ፤ በምርቶች ተጠቃሚና አጠቃላይ የኑሮ መሻሻል ሂደት ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። የአዕምሯዊ ንብረት ዓይነቶች እንዴት ይመደባሉ? የአዕምሯዊ ንብረት፤ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት (Industrial Property) እና የቅጅና ተዛማጅ መብቶች (Copyright and Related Rights) በሚሉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚመደብ ያስረዳሉ። አክለውም፤ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት በውስጡ፤ የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ እና የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች የተሰኙ አራት ክፍሎችን እንደሚይዝ ያብራራሉ። ፓተንት ምንድን ነው?፡- ፓተንት ማለት በአንድ ቴክኒካዊ ባሕርይ ባለው የፈጠራ ሥራ ላይ የሚኖር የፈጠራ ባለቤትነት ብቸኛ መብት መሆኑን አቶ ብሩክ አስረድተዋል። የፓተንት መብት በአንድ ምርት (ለምሳሌ ማሽን ወይም የአመራረት ሂደት (Process) ሊሰጥ የሚችል ሲሆን፤ ፈጠራውም ለአንድ ቴክኒካዊ ችግር መፍትሔ የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል ይላሉ። ከፈጠራ ሥራው አመንጪ ይሁንታ ውጭ ሥራውን ገበያ ላይ ማዋል፣ መጠቀም፣ ማሰራጨት፣ መሸጥ ወዘተ… እንደማይቻልም አክለዋል። ፓተንት ለባለ መብቱ የጥበቃ መብት የሚያስገኝ ሲሆን፤ የጥበቃው ዘመንም በአጠቃላይ እስከ 20 ዓመት ሊደርስ ይችላል። ፓተንት የሚያስገኛቸው ሕጋዊ (የጥበቃ) መብቶች፡- የፈጠራ ሥራውን መጠቀም የሚችሉና የማይችሉ ሰዎችን መወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ሥራውን እንዲጠቀሙ የመፍቀድ ወይም የፈቃድ ውል ስምምነት የመስጠት እንዲሁም የፈጠራ ሥራውን የመሸጥ (ለአዲስ የፓተንት ባለመብት) የሚሉት ይገኙበታል ብለዋል ሥራ አስፈጻሚው። የፓተንት ሥራዎች ለምን ያስፈልጋሉ?፡- ይህን ሲያብራሩም፤ ፓተንት ለፈጠራ ባለመብቶች ዕውቅናንና ሽልማቶችን (ማበረታቻዎችን) የሚሰጥ በመሆኑ፣ ፈጠራዎቹ የኢኖቬሽን ሥራዎችን ስለሚያጠናክሩና በዚህም ቀጣይነት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት መሻሻልን የሚያረጋግጥ በመሆኑ እና በሌሎችም በጎ አስተዋጽዖዎች ፓተንት በዕጅጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የንግድ ምልክት ምንድን ነው?፡- የንግድ ምልክት ማለት አንድን ምርት ወይም አገልግሎት ከሌላው ምርትና አገልግሎት እንዲለይ ለማስቻል በንግድ ምልክት ባለቤቶች ለምርታቸውና አገልግሎታቸው መለያ እንዲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ልዩ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል። የንግድ ምልክት ሸማቹ ሕብረተሰብ የሚፈልገውን ምርትና አገልግሎት በቀላሉ ለይቶ እንዲገዛ ከማስቻሉም በላይ በሚገዛው ምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ በመተማመን ፍላጎቱን እንዲያሟላ ያደርጋል። የንግድ ምልክት ለባለመብቱ ምን ጥቅም ያስገኛል?፡- ምርቶቹ (አገልግሎቶቹ) በተጠቃሚዎች እንዲለዩለት ወይም እንዲታወቁለት ያደርጋል፣ ክፍያን መሠረት አድርጎ ሦስተኛ ወገን እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የንግድ ምልክቶች በራሳቸው ዋጋ አላቸው (የአዕምሯዊ ንብረት ዋጋ ትመና (IP Valuation) ለምሳሌ በፈረንጆቹ በ2026 የመጀመሪያ ወራት አፕል (Apple) 600 ቢሊየን ዶላር፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft) 565 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር፣ ጉግል (Google) 433 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ግምት እንደነበራቸው ተብራርቷል። በተጨማሪም፤ የንግድ ምልክት በሕግ በሚቀመጥ የጊዜ ገደብ መሠረት እየታደሠ ለዘላለም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤ የንግድ ምልክት ባለቤቱን በማስተዋወቅ ዕውቅናና የገንዘብ ትርፍን ያስገኛል፤ የንግድ ምልክት ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል (ተመሳስለው የሚሠሩና ለገበያ የሚቀርቡ ሥራዎችን (Counterfieited Products) ለመዋጋት ዓይነተኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ ምልክት ሰዎች ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ሚዛናዊ በሆነ አግባብ እንዲያቀርቡ በማድረግና በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳለጠ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አስተዋጽዖው የላቀ ነው ብለዋል። ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ምንድን ነው?፡- ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ በምርቶች ሥነ-ውበት (Esthetics) ላይ ተመስርቶ ቅርጽን፣ መስመሮችን ወይም ቀለምን በመጠቀም ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የገዥዎችን (ሸማቾችን) ቀልብ ለመሳብ እንዲችሉ በምርቶች ላይ የሚገለጽ የንድፍ ጥበብ ዘርፍ ነው ያሉት አቶ ብሩክ፤ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች በኢንዱስትሪና ዕደ-ጥበብ ምርቶች ላይ ተዘጋጅተው ሊወጡና ለገበያ ሊቀርቡ ይችላሉ ይላሉ። ዘርፉ ከቴክኒካልና ሕክምና መሣሪያዎች አንስቶ እንደ ሠዓት፣ ጌጣጌጦችና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ዕቃዎችን ሊያካትት ይችላልም ብለዋል። የቤት ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን፣ ተሽከርካሪዎችና የሕንጻ ንድፎችን እንዲሁም የጨርቃጨርቅ ንድፍ ውጤቶች በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ሥር የሚወድቁ ይሆናሉ ይላሉ። ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች ጥበቃ የሚደረግላቸው አዲስ ወይም ወጥ ከሆኑ ብቻ መሆኑን ገልጸው፤ በዲዛይኑ ውስጥ ከሚገለጸው ምርት ጋር ተያያዥ የሆኑ የቴክኒክ ጉዳዮች ጥበቃ እንደማይደረግላቸው አስታውቀዋል። ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?፡- በምርቶች ውበት ላይ የሚገለጽ በመሆኑ የተጠቃሚውን ዐይን ይስባል፣ የምርቶችን ዋጋ ይጨምራል፣ ፈጠራንና ውድድርን ያበረታታል፣ ለባለመብቱ ብቸኛ መብትን ያጎናጽፋል፣ በኢንዱስትሪዎች፣ ባሕላዊ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ ፈጠራ በማሻሻል ኢኮኖሚ እንዲያድግ ያደርጋል፣ የወጭ ንግድን (Export Trade) ያሳድጋል በማለት የኢንዱስትሪ ንድፍ ጥበቃ አስፈላጊነትን ያብራራሉ። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካች ምንድን ነው?፡- የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች በምርቶች ላይ የሚቀርቡ ምልክቶች ሆነው እነዚህ ምልክቶች አንድ የተወሰነ አካባቢን በምርቱ ምንጭነት የሚያመላክቱና ጥራትንና ዝናን ከቦታው ጋር አስተሳስረው የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን አቶ ብሩክ ያስረዳሉ። በአብዛኛው የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾች ልዩ ምርቱ የሚገኝበትን የቦታ ስም (Specific Local Geographyical Factors – Climate, Soil) ይይዛሉ። ለምሳሌ፡- Roquefort for Cheese -France፣ የማረቆ በርበሬ፣ የሸኖ ቅቤ፣ የዓድኣ ጤፍ … የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሾች ናቸው። የጂኦግራፊያዊ ምንጭ አመላካቾችን መጠበቅ ለምን ያስፈልጋል?፡- ተጠቃሚዎች ምርቶች የሚገኙበትን ሀገር ወይም አካባቢ በቀላሉ ለመለየት፣ ሕጋዊነት በሌላቸው ወገኖች የምርቱ መገኛ አካባቢ እና የምርቱ ዝና በተሳሳተ መልኩ ለሌላ ምርት መጠሪያ እንዳይውል ለመከላከል ይረዳል ይላሉ። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምንድን ናቸው?፡- የቅጅ መብት በሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ ወጥ የፈጠራ ሥራዎችን ለሚያመነጩ ደራስያን፣ አርቲስቶች ወዘተ… የባለቤትነት መብት የሚሰጥ የሕግ ማዕቀፍ መሆኑንም ነው ሥራ አስፈጻሚው የሚያስረዱት። በአንጻሩ ተዛማጅ የቅጅ መብት ማለት ይላሉ አቶ ብሩክ፤ በወጥ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተመስርተው የሚሠሩ ተዛማጅ (Related) የፈጠራ ሥራዎችን ያካትታል። ለምሳሌ፡- ከዋኞቹ (ተዋንያን እና ዘፋኞች)፣ ድምጽ ሪከርዲንግስ፣ አሳታሚዎች (ኮምፓክት ዲስኮች)፣ የብሮድካስት ተቋማት፣ (ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ ሲሉ ዘርዝረዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ምን ዓይነት መብቶች ያስገኛሉ?፡- ባለመብቶች ሥራዎቻቸውን ለመጠቀም ወይም ሦስተኛ ወገኖች እንዲጠቀሙባቸው የመፍቀድ፣ ሥራዎች እንዲባዙ፣ ለሕዝብ እንዲዳረሱ፣ እንዲሠራጩ፣ እንዲተረጎሙ ወይም ወደሌላ ሥራ እንዲቀየሩ የመፍቀድ ወይም የመከልከል፣ የደራሲነት (የአመንጭነት) መብት ዕውቅና እንዲያገኙ፣ በብዕር ስም የመጠቀም መብት፣ ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጎድፍ የሥራ መዛባት እንዳይኖር የመጠበቅ ወይም የሥራው ወደሌላ መቀየር የሚያስከትለውን ጉዳት የመቃወም ወዘተ መብቶችን ያስገኛሉ ብለዋል። የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?፡- የሰውን ልጅ የፈጠራና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ያሳድጋል፣ ለፈጠራ አመንጭዎች መበረታታትን ይፈጥራል፣ የሕጋዊ ተፈጻሚነትን በማረጋገጥ አመንጭዎችና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈሱ የፈጠራ ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን የሥርጭት ሽፋን ያሳድጋል ነው ያሉት አቶ ብሩክ። የፓሪስ ስምምነት አባል ኢትዮጵያ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር ለመሆን ለዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) ያስገባችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስምምነቱን ነሐሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በማጽደቁ ከዚሁ ዕለት ጀምሮ ለስምምነቱ ተገዢ ሆናለች። አቶ ብሩክ እንዳብራሩት፤ የፓሪስ ስምምነት በጥቅሉ የኢንዱስትሪያዊ ንብረቶችን ጥበቃ የሚመለከት ነው። የፓተንት፣ የንግድ ምልክት፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ፣ የግልጋሎት ሞዴል (በአንዳንድ ሀገራት ሕግ ኢትዮጵያን ጨምሮ “የአነስተኛ ፈጠራ የባለቤትነት መብት” በመባል የተደነገገ)፣ የአገልግሎት ምልክት፣ የንግድ ስም (የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ስያሜዎች)፣ ጂኦግራፊያዊ አመላካች እና ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድርን መከላከል ያካተተ ነው። የስምምነቱ መሠረታዊ ድንጋጌዎች በሦስት ዋና ዋና መርሆዎች እንደሚከፈሉ ጠቁመው፤ እነሱም፡- የፓሪስ ስምምነት አባል ሀገር መሆን በሌሎች አባል ሀገራት ውስጥ እንደ ዜጋ የመስተናገድ መብት፣ የቀዳሚነት መብት የማግኘት፣ በቀላሉ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የማግኘት አሠራር እና መሰል ጉልህ ጥቅሞችን የማግኘት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ይገልጻሉ። በመሠረቱ የፓሪስ ስምምነት የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃን በማቀላጠፍ አዳዲስ ግኝቶችንና ፈጠራዎችን እንዲሁም የንግድ ሥራዎች ድንበር ሳይገድባቸው የፓተንትና የንግድ ምልክት መብቶች በቀላሉ እንዲጠበቁ በማድረግ ፈጠራን፣ ንግድን እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን እውን ያደርጋል ብለዋል። የዘንድሮው የአዕምሯዊ ንብረት ቀን የፊታችን ሚያዝያ 17 ቀን 2018 ዓ.ም “አዕምሯዊ ንብረትና ስፖርት፤ እንዘጋጅ፣ እንጀምር፣ እንፍጠር!” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፉ የአዕምሯዊ ንብረት ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በስፖርት ዓለም ውስጥ የሚከሰቱ ተወዳዳሪዎች የግልና የጋራ ፈጠራዎች፣ ንድፎች፣ ብራንዶችና የመልካም ዝና ታሪኮችን ለመጠበቅና ሀገራትን ጭምር ለማስተዋወቅ የአዕምሯዊ ንብረት መብት ጥበቃ ሥርዓት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል። ምክንያቱም ስፖርት በባሕርይው በውድድር ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፤ ከሀገራት ዝና፣ ከፋሽን ዲዛይን፣ ከመዝናኛ፣ ከሚዲያ ሥርጭት፣ ከጤናና ከዕለት ተዕለት መገልገያ ቁሶች ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ነው።  
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 4254
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2878
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8667
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7150
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 61519
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 55304
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35792
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 33392
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 28202
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 27504
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 26997
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 26496
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 61519
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 55304
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 35792
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 33392
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 559
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው።   በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል።   የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል።   የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል።   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል።   ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።
ፋሲካ -አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል
Apr 12, 2026 767
በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው። የትንሳኤ በዓል የሚከበረው ከ55 ቀናት የጾም ወቅት በኋላ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እነዚህን ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና ጸሎት ከመለመን ባለፈ ከሥጋ፣ ከወተትና መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ታቅበው ነው የሚያሳልፉት። የትንሣኤ በዓል ከመድረሱ በፊት ያለው አንድ ሳምንት "ሰሞነ ሕማማት" በመባል ይታወቃል። የእምነቱ ተከታዮች በሰሞነ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳለፈውን መከራና ስቃይ በማሰብ በቤተ ክርስቲያን በስግደት፣ በጸሎትና በጾም በተለየ ሁኔታ ያሳልፋሉ። ምእመናን በእለተ አርብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን ብሎ በቀራኒዮ አደባባይ የከፈለውን መከራ፣ ግርፋትና ስቅላት በማሰብ በስግደት፣ በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ያሳልፋሉ። የትንሳኤ (የፋሲካ) በዓልም ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትል ድል አድርጎ መነሳቱን ተከትሎ የሚከበር ነው። ትንሳኤው ይቅርታ፣ ለሰው ለጆች መዳን የተከፈለ ፍቅርና መስዋዕትነት ጎልቶ የሚታይበት ነው። በመሆኑም ፋሲካ ሞትን ድል በመንሳት በትንሳኤ የምስራች የተበሰረበት ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን በትንሳኤ የለወጠበት ለሰው ልጅም ፍቅርን በቤዛነት ተክቶ ያሳየበት ዕለት ነው። ዕለቱ ትንሳኤ ብርሀን የታየበት በመሆኑ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ምሽት ምዕመናን ነጭ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በጸሎትና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶች ያሳልፋሉ። የሌሊቱ ቅዳሴና ስርአተ ፀሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ምዕመናን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ጾም ይፈታሉ። ከቅባት ምግቦች ለሁለት ወራት በመቆጠብ ያሳለፉበት ወቅት በመሆኑም በትንሳኤ ሌሊት ዶሮ በመብላት ጾማቸውን ይፈስካሉ። በበዓሉ ቀንም በነጭ የሀበሻ ልብስ ደምቀው ይታያሉ። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርአቱ ባለፈ የአብሮነት፣ የፍቅርንና የመተሳሰብ እሴት ያለው ነው። ዘመድ አዝማድ በመጠራራትና ከጎረቤት ጋር አብሮ በመብላትና በመጠጣት የሚያሳልፉት ነው። ቤት ያፈራውን በመቋደስ በዓሉን በአብሮነት በደስታ ያሳልፋሉ። የፋሲካ በዓል ማህበራዊ ትስስር የሚገለጥበትና አብሮነት የሚደምቅበት የደስታ በዓል ነው። በተለይ በፋሲካ በዓል ለዶሮ ወጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፋሲካና ዶሮ ወጥ ጥብቅ የሆነ ባህላዊ ቁርኝት ያላቸው በመሆኑ አንዱ የበዓሉ ማድመቂያ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዚህ በተጨማሪ የበሬ ቅርጫ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዳቦና ጠላ እንደየ አቅም በማዘጋጀት ይከበራል። በአንዳንዶች ዘንድም ከገብስ ብቻ የሚዘጋጅ "ኬኔቶ" የተሰኘ (ከአልኮል ነፃ የሆነ መጠጥ) በማዘጋጀት በአማራጭነት ይቀርባል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም