ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሰልጣኞች በኦሮሚያ ክልል በግብርና ምርታማነት የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ):- የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሰልጣኞች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በግብርና ምርታማነት የተከናወኑ ስራዎችን እና ሌሎች  የልማት ተግባራትን  ጎብኝተዋል። 

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና የአመራር አባላቱን አቅም በሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን በአዳማ ከተማ  እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።  

"በመደመር መንግሥት ዕይታ፥ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሐሳብ በተሰጠው ስልጠና ላይ ከ2ሺህ በላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። 

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ ከፍተኛ አመራሮችም ከስልጠናው በተጓዳኝ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የግብርና ክላስተር የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።   


 

የስልጠናው ተሳታፊ ከፍተኛ አመራሮችም  በቱሪዝም፣ በግብርና በቴክኖሎጂና መሰል የልማት መስኮች ለቀጣይ ስራ ስንቅ የሚሆን ዕውቀትና ክህሎት የቀሰሙበትን ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል። 

በስልጠናው ያገኙትን የንድፈ ሀሳብ ትምህርትም በቀጣይ ስራቸው ወደተግባር ለመለወጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። 

ከሁሉም ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች በስልጠናው መሳተፋቸውም ሕብረብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። 

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ያደረጉት የመስክ ምልከታም የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ የሚያመላክት ተጨባጭ ስኬት መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም