ቀጥታ፡

ወይዘሮ ህይወት መሀመድ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን ወይዘሮ ህይወት መሀመድን የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል። 

ኮንፌዴሬሽኑ ዓመታዊ ጉባኤውን በዚምባብዌ ሃራሬ እያካሄደ ይገኛል። 


 

በጉባኤው ላይ እየተሳተፉት የሚገኙት የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ህይወት መሀመድ የኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። 

የወይዘሮ ህይወት መሀመድ የኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጥ በአፍሪካ መደረክ የኢትዮጵያን የባህል ስፖርቶች ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን መፍጠሩን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። 


 

የባህል ስፖርት በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነት ለማሳደግ እንደሚያግዝም ገልጿል። 

የኢትዮጵያ 11 ባህል ስፖርቶች የውድድር ህግና ደንብ ወጥቶላቸው ዓመታዊ ውድድሮች እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም