ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መሪነቱን ያጠናከረበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳግማዊት ሰለሞን እና ማህሌት ምትኩ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥቡን ወደ 15 ከፍ በማድረግ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።
በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
የኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ ዳግማዊት ሰለሞን በሊጉ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ ዘጠኝ ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን መሪነቷን አጠናክራለች።
ዛሬ በተደረገው ሌላኛው መርሃ ግብር ሸገር ከተማ አዲስ አበባ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ህይወት ራጉ፣ ሰናይት ኡራጎ እና ማርታ ወልዴ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ሸገር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ሲያደርግ በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በሶስት ነጥብ 13ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛል።
ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።