የመንግሥታቱ ድርጅት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የመንግሥታቱ ድርጅት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የተነደፉ ስትራቴጂዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበች።
በትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፥ የተመራ ልዑክ በኡዝቤኪስታን በተካሄደው 43ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባዔ ላይ መሳተፉን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ሴክሬታሪ ጄኔራል ዓለሙ ጌታሁን ለኢዜአ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በትምህርት፣ባህል፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና ከብዝኃ-ሕይወት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ያከናወነቻቸውን እና እየሠራቻቸው ያሉ ተግባራትን ማብራራታቸውንም ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግሥታት የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የተነደፉ ስትራቴጂዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል ነው ያሉት።
ከጉባዔው ጎን ለጎንም ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶች ማድረጋቸውንም ሴክሬታሪ ጀኔራሉ ተናግረዋል።