በፕሪሚየር ሊጉ መቀሌ 70 እንደርታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከነጌሌ አርሲ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቋል - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ መቀሌ 70 እንደርታ ወላይታ ድቻ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከነጌሌ አርሲ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአምስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ እና ወላይታ ድቻ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ኪቲካ ጅማ በጨዋታ እና ቦና ዓሊ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ምንተስኖት ተስፋዬ በጨዋታ እና ካርሎስ ዳምጠው ለወላይታ ድቻ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ወላይታ ድቻ በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን አግኝቷል። በሊጉ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
መቀሌ 70 እንደርታ በሁለት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከነጌሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ11 ነጥብ የሊጉን መሪነት በጊዜያዊነት ከመቻል ተረክቧል።
ነጌሌ አርሲ በሶስት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።