የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን ተበሠረ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን ተበሠረ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ):- የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን ተበሠረ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ የፋሲል ግንብ ለአራት መቶ ዓመታት ያህል የሚንከባከበው አጥቶ የእርጅና እድሜው ላይ ደርሶ ሞቱን ነበር የሚጠብቀው ሲሉ አስፍረዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አመራርና ክትትል እንደ ንሥር ታድሶ ተነሣ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዘዞ እስከ ፒያሳ ያለው የጎንደር መንገድ ግራና ቀኙ እየተስተካከለ እና እያማረ ዳግም እየተወለደ ነው ያውም ውበት፣ ጥቅምና ምቾት ጨምሮ ብለዋል።
ተጀምሮ ያለማለቅና ቆሞ የመቅረት መተረቻ የሆነው መገጭ ዛሬ ታሪኩ ተቀየረ፤ ወድቆ የመነሣት፣ ደክሞ የመበርታት ምሳሌ ሆነ ሲሉም ገልጸዋል።
ወንዙ ተቀለበሰ፤አንዱን ወሳኝ ምእራፍ ተሻገረ፤እነሆ የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን በዚህ ሰሞን ተበሠረ ሲሉም ነው የገለጹት።