በአርሲ ዞን ከ300 ሺህ በላይ የወተት ላሞችን በሰው ሰራሽ ስነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ የማዳቀል ስራ እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአርሲ ዞን ከ300 ሺህ በላይ የወተት ላሞችን በሰው ሰራሽ ስነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ የማዳቀል ስራ እየተከናወነ ነው
አዳማ ፤ ጥቅምት 28/2018 (ኢዜአ):-በአርሲ ዞን በበጀት ዓመቱ ከ300 ሺህ በላይ የወተት ላሞችን በሰው ሰራሽ ስነ ዘዴ እና በመደበኛ የማዳቀል ስራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለፀ።
የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ቃሶ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ የእንስሳት ሀብት ልማትን ለማዘመንና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በበጀት ዓመቱም በሰው ስራሽ ስነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ 300 ሺህ የወተት ላሞችን ዝሪያ ለማሻሻል በዘመቻ መልክ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በእስከ አሁኑ ሂደትም ከ130 ሺህ በላይ የወተት ላሞችን ማዳቀል መቻሉን ጠቅሰው እቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከማዳቀል ስራው ጎን ለጎን የተሻለ የወተትና የስጋ ምርት መስጠት የሚችሉ ዝሪያቸው የተሻሻለ ጥጃዎች ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።
የተጀመረው እንቅስቃሴ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን አንስተው አርሶ አደሩም በእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያ ዘዴዎች ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።