ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል
May 20, 2026 223
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለዓለም ዋንጫ የመለያ ጨዋታ አልፏል። ቡድኑ ወደ መለያ ጨዋታው የተሸጋገረው ትናንት ቱኒዚያን 1 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ ነው። ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል። ሞዛምቢክ በምድብ ሶስት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በተያያዘም በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ከቱኒዚያው ጨዋታ በኋላ ዛሬ ልምምድ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በዴሞክራሲ ተቋማት የተፈጠረው አስቻይ ምኅዳር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት ያላቸው ተሳትፎ እያደገ እንዲመጣ አስችሏል
May 20, 2026 553
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ተቋማት የተፈጠረው አስቻይ ምኅዳር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሂደት ያላቸው ተሳትፎ እያደገ እንዲመጣ ማስቻሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አቶ መለሰ ዓለሙ ገለጹ። አቶ መለሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊነትን የሚያረጋግጡ ዝግጅቶችን በማድረግ ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን በሚካሄዱ የምርጫ ክርክር መድረኮች ላይ የፖሊሲ አማራጮችን በግልፅ ለህዝብ በማቅረብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑንም አብራርተዋል። ከምርጫ ቦርድ፣ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ መገናኛ ብዙኅንና የፀጥታና የፍትሕ ተቋማት ጋር በምርጫው ሂደት በመርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በማድረግ አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እየተሰራበት መሆኑን ጠቅሰዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚዛን የጠበቀ የፉክክርና የትብብር መርህን በመከተል የሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ምክር ቤቱ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በእስካሁኑ ሂደትም ከ50 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በመራጭነት መመዝገቡም የምርጫ ተሳትፎ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፉክክር ባለፈ ለሀገር ግንባታ መሳካት እንዲሰሩ ሀላፊነት የሚሰጥ ነው ብለዋል። የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስቻይነት የሚያረጋግጡ የማሻሻያ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ተቋማት የፈጠረችው አስቻይ ምኅዳርም የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ልምምድም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መምጣቱን አስረድተዋል። በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች በተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤቶች አማካኝነት ሁሉም ፓርቲ እየተሳተፈ ነው ብለዋል። በተቃራኒው አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ አይነቶች በማህበራዊ ሚዲያና መገናኛ ብዙኅን የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች ሚዛናዊነት የጎደላቸው ናቸው ብለዋል። እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው በመቆጠብ ለምርጫው ዴሞክራሲያዊነት ገንቢ ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል። መራጩ ህዝብም ድምፅ በሚሰጥበት ወቅት በንቃት በመሳተፍ ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምፅ በመስጠት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መገናኛ ብዙሃን ለዴሞክራሲ ስርዓት መዳበር ሚናቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል-ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ
May 20, 2026 349
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦መገናኛ ብዙሃን የህዝብን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ስራዎችን በመስራት ለዴሞክራሲ ስርዓት መዳበር ሚናቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ አስገነዘቡ። ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣መገናኛ ብዙሃን በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ በመንገድ ጠቋሚነት፣ በችግር ፈቺነትና በአጋዥነት ትልቅ ስፍራ አላቸው። ይህም መገናኛ ብዙሃን በማህበረሰቡ ውስጥ እጅግ የጎላ ስፍራ እና ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚያመላክት መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም እንደ ምርጫ ባሉ ወሳኝ ወቅቶች ህዝቡ የመወሰን አቅሙን የሚለማመድበት፣ የስልጣን ገደቡን የሚያውቅበት እንዲሁም እሱን ተከትሎ ስርዓት የሚያሰፍንበት ምህዳር መሆኑን የማሳወቅ ትልቅ ኃላፊነት በመገናኛ ብዙሃን ላይ ይወድቃል ብለዋል። መገናኛ ብዙሃን እውነታን የመፈተሽ፣ ህዝብን ወደ እውነታው የማምጣት፣ የደፈረሰ ሀሳብን የማጥራትና የተዛነፈ አካሄድን የመግራት ግዴታ እንዳለባቸውም ሚኒስትሯ አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ስራ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለዓለም ህዝብ ትልቅ ትርጉምና መልዕክት ያስቀመጠ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም ከ50 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የምርጫ ካርዳቸውን ወስደው ድምፅ ለመስጠት በከፍተኛ ተነሳሽነት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን በአብነት አንስተዋል። ይህ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የመራጮች ቁጥር እና የህዝቡ ዝግጁነት ደግሞ ዴሞክራሲ የእኛ እና ለእኛ ብቻ ነው ብለው ለሚያስቡ የውጭ ሀገራት ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል። በመሆኑም በተቀሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘውን ህዝብ ይበልጥ የሚያተጋ እና የሚያነቃቃ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ምርጫው ነጻ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊነቱን ጠብቆ እንዲካሄድ ሚናችንን እናጠናክራለን
May 20, 2026 278
አዳማ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ ረገድ ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የመገናኛ ብዙሃንና ሲቪክ ማህበራት የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ገለጹ። ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ከተሳተፉት የመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎች መካከል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ፣ በምርጫ ወቅት የመገናኛ ብዙሃን ሚና ትልቅ መሆኑን አንስተዋል። በተለይም መገናኛ ብዙሃን ምርጫው ዴሞክራሲያዊነቱን በጠበቀ መልኩ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም በኢትዮጵያ ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሰረት የሚጥል እንዲሆን መገናኛ ብዙሃን ሙያዊ ስነ-ምግባርን ባከበረ መልኩ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቁመው ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ሌሎች የምርጫ ተዋንያን የሚያደርጉት ጥረት በመገናኛ ብዙሃን ከተደገፈ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊነቱን የጠበቀ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል አንስተው ለዚሁ ስኬት ሚዲያቸው ሚናውን እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መገናኛ ብዙሃን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ሰንበታ በበኩላቸው፤ መገናኛ ብዙሃን መርህን መሰረት አድርገው መስራታቸው ምርጫውን ስኬታማ ያደርገዋል ብለዋል። የዘንድሮ ምርጫ ነጻና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ ረገድ መገናኛ ብዙሀን ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቁመው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች በበኩላቸው፤ የዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ሂደቱ ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ነጻ፣ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊነቱን የጠበቀ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም የሲቪክ ማህበራትና የመገናኛ ብዙሀን ድርሻ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል። የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በተለይም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ነጻ ሆነው በምርጫ ዙሪያ ስራ እንዲሰሩ እድል የፈጠረላቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
May 20, 2026 220
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሩዋንዳዊው ፓትሪክ ሲቦማና በ16ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪ ሆኗል። አስቻለው ታመነ በ63ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ድሬዳዋ ከተማን አቻ ያደረገውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ46 ነጥብ ከነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም። ድሬዳዋ ከተማ በ35 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ33ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 1 ሲረታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን፣ መቀሌ 70 እንደርታ ሸገር ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ፖለቲካ

የምርጫው ሂደት የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረትን ከማፅናት ባለፈ የዴሞክራሲ ልምምድ ሁነኛ ማሳያ ነው
May 20, 2026 509
አዳማ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረትን ከማፅናት ባለፈ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ልምምድ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን የመንግስት ኮሙንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለፁ። ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የምርጫ ሂደት ብሄራዊ ጥቅምን ለማሳካት የሚደረግ ጥረትና የዴሞክራሲ ልምምድ ነው። በዚሁ መሰረት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን በስኬት መቀጠሉን አንስተዋል። የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ልማትና ብልፅግና ማሳካት የሚቻለው በተደመረ አቅም መትጋት ሲቻል መሆኑን ገልፀው ምርጫው አንዱ የብሄራዊ ጥቅም መገለጫ መሆኑን አንስተዋል። የብሄራዊ ጥቅምና የሀገር ሉአላዊነት ጉዳይ ያለ ልዩነት የምንሰራበት የጋራ አጀንዳችን ነው ያሉት አቶ ተስፋሁን ለዚህም የሚዲያ ሚና ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ በምርጫ የዴሞክራሲ ባህልን ለመገንባት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑን ገልፀዋል። በዚሁ መሰረትም የሲቪል ማህበራት ለዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት በላቀ ቁርጠኝነት እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል። አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በገለልተኝነት በማገልገልና ማህበረሰብን በማንቃት ጠንካራ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ ሲሉም አክለዋል ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ግዛው ተስፋዬ፣ መገናኛ ብዙሃን ህግና አሰራርን ተከትለው እንዲያገለግሉ ባለስልጣኑ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በእስካሁኑ የምርጫ ሂደትም መገናኛ ብዙሃኑ ገንቢ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል። በመድረኩ አስተያየታቸውን የሰጡ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮች በምርጫ ሂደቱ የህዝቡ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው ሚዲያውም በዚሁ ልክ ለመስራት እየጣረ መሆኑን አመልክተዋል። የመገናኛ ብዙሃን ለምርጫው ስኬታማነት በብቃት መስራት እንዳለባቸው አንስተው ሚዛናዊና ጥልቅ እይታ ያለው ዘገባ ተደራሽ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመገንባት ሂደት የድርሻውን እየተወጣ ነው
May 20, 2026 300
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመገንባት ሂደት ውስጥ ድርሻውን በላቀ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። የጋራ ምክር ቤቱ 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ የበጀት ዓመቱ የ10 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ፤ ምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን የሚያፋጥኑ እና የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል። ባለፉት አሥር ወራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ከማዘጋጀት ባለፈ፣ የፓርቲዎችን የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያሳድጉ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል። በዚህም በሀገር ጉዳይ ላይ በጋራ የመምከር ባህል፣ ተቀራራቢ አቋም መያዝ፣ እርስ በርስ መደማመጥ እና ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት መሠረት የሆኑ ተግባራትን ጨምሮ ቀደም ሲል ያልነበሩ ለውጦች ተመዝግበዋል ነው ያሉት። አባል ፓርቲዎች የምክር ቤቱን የሥራ ጥንካሬ ለማስቀጠልና የሚታዩ ድክመቶችን ለመቅረፍ፣ እንዲሁም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል። የዛሬው ውይይት አስፈላጊነትም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲዳብር የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ነው ብለዋል። የምክር ቤቱ ጸሐፊ አቶ ታሪኩ ድንበሩ በበኩላቸው፤ የጋራ ምክር ቤቱ በተለይም የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና የተረጋጋ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ቆይቷል ብለዋል። ከዚህም ባለፈ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረት እንዲጣል ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል። ከዚህ ጎን ለጎን በፓርቲዎች መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር እና ችግሮች ሲያጋጥሙም በውይይትና በንግግር እንዲፈቱ ምክር ቤቱ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችም መድረኩ በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ያለው የእርስ በርስ መተማመን መንፈስ እንዲጎለብት ያደርጋል ብለዋል። የጋራ ምክር ቤቱም ባለፉት 10 ወራት ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲገነባ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰው፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ነፃና የዴሞክራሲ ተምሳሌት በሆነ መንገድ እንዲከናወን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስረድተዋል።
ለሀገርና ለሕዝብ ይበጃል ያልነውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል-የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች
May 20, 2026 284
ባህርዳር፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር እድገት ይሰራል ያልነውን ፓርቲ ወደ ስልጣን ለማምጣት የድምጽ መስጫውን ቀን በጉጉት እየጠበቅን ነው ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ሀብታሙ ጥላሁን ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የዜግነት ድርሻቸውን እየተወጡ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን ከሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር በቂ እውቀት በማግኘት ለሀገርና ለሕዝብ የሚበጀውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቼያለሁ ነው ያሉት። ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ በለጠ ደረበ በበኩላቸው፤ ከጎረቤቶቻቸው እና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በመሆን የአካባቢውን ሰላም ነቅተው በመጠበቅ መጪው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን አመልክተዋል። ህገ-መንግስቱ ያጎናፀፈኝን መብት በመጠቀምም በወሰድኩት የመራጭነት ካርድ የሀገርን አንድነት፣ ልማትና ዕድገት ያፋጥናል ብዬ ላመንኩበት ፓርቲ ድምጼን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ብለዋል። በምርጫ ካርዱ አገርን ያሻግራል ብሎ ላመነበት ፓርቲ በነፃነት ድምጹን ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለጸው ደግሞ ወጣት ትልቅሰው አንሙት ነው። ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን ለመወጣት መዘጋጀቱን ነው የገለጸው፡፡
ፓርቲው የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ተግባራት አከናውኗል
May 20, 2026 313
አምቦ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎትና በሌሎችም ዘርፎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ተግባራት ማከናወኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ። የብልፅግና ፓርቲ በምዕራብ ሸዋ ዞን እና በአምቦ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ። በቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሕዝቡን ሕይወት የሚያሻሽሉ የልማት ሥራዎች አከናውኗል። በተጨማሪም የዜጎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሠራው ሥራ ሁሉን አቀፍ ውጤት እየተገኘ መሆኑንም ተናግረዋል። በተለይም በኦሮሚያ ክልል በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎትና በሌሎችም ዘርፎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚችሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ፓርቲው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን በማረጋገጥ፣ ፍትሕ፣ እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲጎለብት እንዲሁም አብሮነት እንዲጠናከር እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ እንደገለጹት፤ ብልፅግና ሀገር በቀል የሆኑ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን አንግቦ የተነሳ ፓርቲ ነው። በዞኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የክልሉ መንግሥት በቀረጻቸው የልማት ኢኒሼቲቮች አማካኝነት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰፋፊ ሥራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት አምቦን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ብዙ መሠራቱን የገለጹት ደግሞ የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሐጫሉ ገመቹ ናቸው። ፓርቲው ተጨባጭ የልማት ሥራዎችን በከተማ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች በጥራት መሥራቱን አብራርተዋል።
ለዘላቂ ሰላምና ልማት ይሰራል ያልነውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል - የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች
May 20, 2026 305
ወልቂጤ፣ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፡-በወሰድነው የመራጭነት ካርድ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ይሰራል ያልነውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ሲሉ የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በመገናኛ ብዙሃን የተመቻቸላቸውን የዓየር ሰዓት በመጠቀም ማኒፌስቷቸውን እና አማራጭ ሃሳቦቻቸውን ለመራጩ ህዘብ በማስተዋወቅና ላይ ናቸው፡፡ በምርጫው ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጉራጌ ዞን ነዋሪዎችም በጠቅላላ ምርጫው ለሃገር እና ለህዝብ ዘላቂ ሰላምና ልማትን የሚያስቀጥል ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በዞኑ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ማርታ ሽበሺ እንዳሉት በጠቅላላ ምርጫው በንቃት መሳተፍ የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደው የድምጽ መስጫ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ፓርቲዎች በብዙሀን መገናኛ እና በተለያዩ አማራጮች እያደረጉት ያለውን የምረጡኝ ቅስቀሳና የሚያቀርቧቸውን የፖሊሲ አማራጮች ሲከታተሉ መቆየታቸውን ጠቅሰው፣ ይህም ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመለየት እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ወጣት ሙባሪክ ጀማል እንዳለው፣ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ድምጹን ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ለመስጠት ተዘጋጅቷል። በዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ ለፓርቲዎች ምቹ መህዳር መፈጠሩ በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ማድረጉን ገልጾ፣ እሱም ድምጹን ከመሰጠት ባለፈ ለምርጫው ሰላማዊና ፍትሀዊነት የበኩሉን እንደሚወጣም አረጋግጧል። የአካባቢው ወጣቶችም በወሰዱት ካርድ ድምጻቸውን ለሚፈልጉት ፓርቲ በነጻነት በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተግባር እንዲያረጋግጡ የማስገንዘብ ሥራ እየሰራ መሆኑንም ተናግሯል። በዞኑ የቸሃ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሙደሲር የሲሩ እንደገለጹት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሀገርን መፃኢ ዕድል ለመወሰንና የተረጋጋ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት ተግቶ ይሰራል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። በምርጫው ቀን የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ሀገርን በልማት ያሻግራል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ የተናገሩት ደግሞ በጉራጌ ዞን የምሁር አክሊል ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ዙርያሽ ደሴ ናቸው። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስጠብቃል፤ ህዝብንም በሰላምና ልማት ተጠቃሚ ያደርጋል ያልነውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ ያሉት ደግሞ በእኖር ወረዳ የመራጭነት ካርድ የወሰዱት ተናኜ ባድገባ ናቸው፡፡ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ የሚሰጥበት ቀን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን የጉራጌ ዞን ነዋሪዎችም ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ለሚሉት ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት ዕለቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ማህበራዊ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቁጥር 3 የበጎነት መንደር የተገነባውን ባለ አምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላለፉ
May 20, 2026 337
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገብስ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ቁጥር 3 የበጎነት መንደር የተገነባውን 44 የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች ያሉት ባለ አምስት ወለል ህንጻ ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ገብስ ተራ ቀደም ብሎ እጅግ የተጎሳቆለ እና ለመኖር ምቹ ያልሆነና ባረጁ እና በደቀቁ ቤቶች የተሞላ ነበር ብለዋል፡፡ እንዲሁም በተደጋጋሚ በእሳት አደጋ የሚጠቃ ፣ ለአቅመ ደካሞች እናቶች የማብሰያና የመጸዳጃ አገልግሎት አስቸጋሪ የነበረበት መንደር እንደነበርም አስታውሰዋል። በዚህ መንደር የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 377 የመኖሪያ ቤቶች ያላቸው 5 ህንጻዎችን መገንባት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡ ነዋሪዎቻችንም ከዛ አስከፊ አኗኗር ተላቀው ክብራቸውን በሚመጥን ፅዱ፥ ዘመናዊ አኗኗር የሚፈጥር፥ ልጆች ቦርቀዉ የሚጫወቱበት እና ደረጃውን በጠበቀ መኖሪያ መንደር እንዲኖሩ በማድረጋችን በጣም ደስ ብሎናል ሲሉም ገልጸዋል። በዚህ የበጎነት መንደር ግንባታ ላይ በክትትል እና ድጋፍ አስተዋጽኦ ላደረጉ አመራሮች እንዲሁም ልበ ቀና ባለሀብቶች በገንዘባቸው ላደረጉት ድጋፍ ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል።
ክትባትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ በማድረግ የበሽታ ወረርሽኞችን የመከላከል አቅምን ማሳደግ ተችሏል
May 20, 2026 272
አሶሳ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ ሀገር አቀፍ የክትባት ሽፋንን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ በማድረግ፣ የተለያዩ ተላላፊ በሽታዎችንና ወረርሽኞችን የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የጤና ሚኒስቴር "ለእያንዳንዱ ትውልድ ክትባቶች ይሰራሉ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የአፍሪካ ክትባት ሳምንት ንቅናቄ መድረክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ ከተማ አካሄደ። በመድረኩ ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ አጋር አካላት ተገኝተዋል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ስለሺ ጋሮማ በወቅቱ እንደገለፁት፤ በኢትዮጵያ መከላከልን መሠረት አድርጎ የተቀረጸው የጤና ፖሊሲ ክትባትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ በማድረግ፣ የበሽታ ወረርሽኞችን አስቀድሞ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል። በተለይም ህጻናት መደበኛ ክትባቶችን በተሟላ ሁኔታ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ከተለያዩ ለህልፈትና ለሕመም ከሚዳርጉ በሽታዎች ለመታደግ ትልቅ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል። የአፍሪካ ክትባት ሳምንት መከበር ዋና ዓላማም ክትባት ለሁሉም ትውልድ ተደራሽ የሚሆንበትን ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ስለ ክትባት የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለማረም መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የክትባት ተደራሽነት እንዲያድግ የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ መንግስት ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት አዎንታዊ ለውጥ መታየቱንም ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች እየተከናወነ ያለው የክትባት ስርጭትና ተደራሽነት ከአፍሪካ አገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስና አርአያ የሚሆን መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዩኒሴፍ የክትባት ስፔሻሊስት አልማዝ መርደኪዮስ ናቸው። ቀደም ሲል በክትባት ብቻ በቀላሉ መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች የበርካታ ሕጻናትን ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ ይቀጥፉ እንደነበር ያስታወሱት ስፔሻሊስቷ፤ በአሁኑ ወቅት ግን እንደ ኩፍኝ፣ ፖሊዮ እና ሳንባ ምች ያሉ አስከፊ በሽታዎችን በተደራጀ መልኩ መከላከል የሚያስችል አገራዊ አቅም መፈጠሩን አስታውቋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልሙኒዬም አልበሽር በበኩላቸው በክልሉ የእናቶችና ህፃናትን ጤና ለመጠበቅ ክትባት የመጀመሪያ አማራጭ ተደርጎ እየተሰራበት ነው ብለዋል። በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ክትባት ያመለጣቸው ህፃናት ክትባት እንዲወስዱ ለማድረግ በየጊዜው ሰፊ የንቅናቄ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አክለዋል።
የቱሪስት መስህብ መዳረሻዎችን የማልማት ስራ ላይ ትኩረት መሰጠቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እያበረከተ ነው
May 20, 2026 184
ጎንደር ፤ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፡-በለውጡ ዓመታት በጎንደር ከተማ የተከናወኑ የቱሪስት መስህብ ልማቶች የዘርፉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ እያሳደጉ መሆኑን የዘርፉ ምሁራንና የስራ ኃላፊዎች ገለጹ፡፡ የጎንደር አብያተ መንግስት ጥገናና እድሳት ጨምሮ የጎርጎራ የኢኮ ሪዞርት ግንባታ የዘርፉን አቅም አልምቶ መጠቀም እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ መሆኑም ተገልጿል። በጎንደር ዩንቨርሲቲ የቱሪዝምና ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ኃላፊና የዘርፉ ተመራማሪ የሺዋስ አቡኔ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሃብት በተገቢው በማልማት ጥቅም ላይ የማዋል ተግባር ተዘንግቶ እንደነበር ያስታውሳሉ። ከለውጡ አመታት ወዲህ ግን መንግስት የቱሪዝም ጸጋዎችን በማልማትና በማስተዋቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን የማጉላት ስራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ለአብነትም የፋሲል አብያተ መንግስትን ጥንታዊና ታሪካዊ ገጽታውን በጠበቀ መልኩ ታድሶና ተጠግኖ ለጎብኚዎች ክፍት መደረጉንና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት በአዲስ መልክ ማልማት መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል። በተለይም የጣና ሀይቅን ጨምሮ የተለያዮ የተፈጥሮ ጸጋዎች በጎንደርና ሰሜን ተራሮች ከሚገኙ ቅርሶች ጋር እንዲተሳሰሩ መደረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን እድልን ያሰፋ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የቱሪዝም ዘርፉን በእውቀትና በሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲመራ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ውስጥም በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በርካታ ባለሙያዎች በማፍራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ የጎንደርን የቀደመ ስምና ታሪክን የሚዘክሩ ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦችን በማልማትና በማስተዋወቅ የዘርፉን ሀገራዊ እድገት ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ መሰራቱን ያነሱት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥበቃና ልማት ቡድን መሪ አቶ አይቸው አዲሱ ናቸው። ለአብነትም የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት ዛሬ ላይ ታሪኩንና ገናና ስሙን በሚመጥን መንገድ እንደጠገን መደረጉ ታላቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሰጠው ልዩ ትኩረት እድሳትና ጥገናው የተጠናቀቀው ቤተ መንግስቱ ባለፉት 10 ወራትም አካባቢውን የሚገበኙ ቱሪስቶች ቁጥር ወደ 5ሺህ ከፍ እንዲል ማድረጉን ተናግረዋል። የቱሪስቶቹ ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር በ3 ሺ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁመው ይህም የቱሪስት መዳረሻዎችን በመጠበቅና በማልማት የተመዘገበ ለውጥ መሆኑን አረጋግጠዋል። የቅርስ ጥበቃና ልማት ስራው ማህበረሰቡ በዘርፉ ለጎብኝዎች አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘው ገቢ እንዲጨምር አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አመልክተዋል።
የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለጥያቄያችን ምላሽ የሰጠ ነው-የወረዳዎቹ ነዋሪዎች
May 20, 2026 280
ሠመራ፣ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፡- በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን የዱለቻና አሚበራ ወረዳዎች ነዋሪዎች፤ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት በመጓዝ ያባክኑት የነበረውን ጊዜና ጉልበት እንዳስቀረላቸው ገለጹ። በወረዳዎቹ የተለያዩ ቀበሌዎች በ109 ሚሊዮን 600 ሺህ ብር ወጪ በመሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት የተገነቡት የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቹ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብረሃም በላይ(ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ይታወሳል። የፕሮጀክቶቹን ምረቃ ተከትሎ አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል አቶ ያሲን መሐመድ በአካባቢው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማግኘት አራት ሰዓት የደርሶ መልስ ጉዞ የሚወስድ መሆኑን አስታውሰዋል። በተለይም ሴቶች የችግሩ ሰለባ ሆነው መቆየታቸውን ገልፀው፤ በፕሮጀክቶቹ አማካኝነት የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄያቸው ተመልሶ በደጃቸው እየተጠቀሙ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላኛዋ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወይዘሮ አባሂና ሁመድም የፕሮጀክቶቹ መመረቅ በቅርባችን ውሃ ማግኘት አስችሎናል፤ በዚህም ደስተኞች ሁነናል ብለዋል። ቀድሞ ያልጠራ የጎድጓድ ውሃ ከሩቅ ስፍራ በጀርባችን አዝለን ነበር የምናመጣው፤ አሁን ላይ ውሃ ፍለጋ ረጅም ርቀት ጉዞና ድካም አስቀርቶልናል ብለዋል። የዱለቻ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ኢነሃባ በበኩላቸው፤ የተገነቡት ፕሮጀክቶች እናቶች ንጹህ ውሃ ለማግኘት ያባክኑት የነበረውን ረጅም ሰዓትና እንግልት ያስቀሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ቀደም ሲል የነበረው የውሃ እጥረት ችግር በመቀረፉ ለሰውም ሆነ ለእንስሳት አስተማማኝ መፍትሄ መገኘቱን የገለጹት ሃላፊው፤ በአሁኑ ወቅት የንጹህ መጠጥ ውሃን በደጃቸው ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል። የአሚበራ ወረዳ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኢብራሂም መሐመድ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ለውሃ ፍለጋ የሚያደርገውን ረጅም ጉዞ በማስቀረት፣ በአቅራቢያው ንጹህ ውሃ አግኝቶ ተረጋግቶ እንዲኖር ማስቻሉን ገልጸዋል። የዱለቻ ወረዳ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ሷሊህ ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ ይጠይቀው የነበረ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጥያቄ ከነእንሳሳቶቻቸው ጭምር ፕሮጀክቱ መመለስ መቻሉንና የነበረውን ዕጦት ማስወገዱን ተናግረዋል።
ኢኮኖሚ
በመዲናዋ የተገነቡ ግዙፍ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ሕይወት እያሻሻሉ ነው
May 20, 2026 305
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የተገነቡ ግዙፍ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ሕይወት እያሻሻሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ ሱቆችና የህጻናት መጫወቻ ፓርኮችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ከንቲባዋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፓስተር አካባቢ የተገነባ ባለአምስት ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበዋል። እንዲሁም በክፍለ ከተማው 40/60 ብርጭቆ ኮንደሚኒየም አካባቢ የተገነቡ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ አዲስ አበባ ከስም በዘለለ በተግባር ውብ እና አበባ እየሆነች ትገኛለች ብለዋል። በከተማዋ የተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን እንዳስቻሏት ገልጸዋል። የከተማዋ ልማት ከዜጎች ህይወት መለወጥ እና መዘመን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑን አመላክተዋል። በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ፣ ምቹ የመኖሪያና የመዝናኛ አማራጭ የሚፈጥሩ እና የቱሪስት መስህብ መሆን የሚችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ነዋሪዎች የተገነቡትን ውብ የልማት ፕሮጀክቶች በአግባቡ በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የልማት ፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው፤ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የህፃናት መጫወቻ ፓርኮች ወደ ዘመናዊና ምቹ አኗኗር የሚያሸጋግሩ ናቸው ብለዋል።
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረጉ ስምምነቶች የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና ገቢ ለማስፋት ጉልህ ሚና ይጫወታሉ
May 20, 2026 156
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረጉ የአየር አገልግሎት ስምምነቶች የአየር መንገዱን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና ገቢ በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳላቸው የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በተደረጉ የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጆች ላይ የአስረጂዎች መድረክ አካሂዷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባንግላዲሽ፣ አንጎላ፣ ኢስዋቲኒና ሴራሊዮን በሚያደርጋቸው በረራዎች የተፈረሙ የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያና ቬትናም መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል አገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመው ስምምነት ረቂቅ አዋጆች ላይ በዝርዝር ውይይት ተደርጓል። የቋሚ ኮሚቴው አባላትና የምክር ቤቱ የህግ ማእከል በስምምነቶቹ ፋይዳ፣ የበረራ ደህንነት መጠበቅ፣ በኢሚግሬሽን ቁጥጥር፣ የአየር መንገዶች ገንዘብ የመታገድ ችግር፣ የአየር መንገዶች የመሬት ላይ አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተዋል። ከሀገራቱ ጋር የተደረገው ስምምነት ከኢትዮጵያ ህገ-መንግስት፣ ከሌሎች ህጎች እንዲሁም ሀገሪቱ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጋር እንዳይጋጭ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ነጎ (ዶ/ር)፥ ረቂቅ አዋጆቹን የሀገራትን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ የሀገሪቱን ደህንነት በማስጠበቅና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በማጠናከር በተለያዩ አማራጮች ሀገሪቱን ተጠቃሚ ለማድረግ ማዳበር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠውን አገልግሎት ተወዳዳሪነት ለማላቅና የሀገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ከተለያዩ ህጎችና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጳውሎስ ኃይሌ፤ ከሀገራቱ ጋር የተደረጉ ስምምነቶች የአቪዬሽን ደህንነት፣ ዓለም አቀፍ ስምምነትና ብሔራዊ ጥቅምን መሰረት ያደረጉ ናቸው ብለዋል። ስምምነቶቹ ለቱሪዝም፣ ንግድና ኢንዱስትሪዎች እድገት ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ መሆኑን አንስተዋል። የአየር መንገዶች ገንዘብ የመታገድ ችግር ከባለድርሻ አካላት ጋር በዲፕሎማቲክ መንገድ እየተፈታ መሆኑን ገልጸዋል። አየር መንገዶች በተለያዩ ሀገራት የሚጠቀሟቸው የመሬት ላይ አገልግሎቶች የአየር መንገዶች አገልግሎት ብቃት ማሳያ መሆኑንና ከዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች ጋር በተጣጣመ መልኩ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢኮኖሚና ሬጉሌሽን ዳይሬክተር ናርዶስ በድሉ፤ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተደረጉት ስምምነቶች የአየር መንገዱን ተደራሽነትና የትራፊክ መብቶችን የሚያሳድጉ እንዲሁም ተደራራቢ ቀረጥና ወጪን ለመቀነስ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ይበቃል ግዛው፤ ከቬትናም ጋር የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል አገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የመወሰን ነጻነት የጠበቀ ነው ብለዋል።
በዞኑ የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታን ከማስፋፋት ጎን ለጎን አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ትኩረት ተደርጓል
May 20, 2026 159
መቱ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ በኢሉባቦር ዞን የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታን ከማስፋፋት ጎን ለጎን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ማሻሻል ትኩረት መደረጉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። በኢሉባቦር ዞን በበጀት ዓመቱ የተገነቡ 831 የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት የማድረግ መርሃ ግብር በሀሉ ወረዳ ተጀምሯል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ አስተዳደሩ ለሕብረተሰቡ ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆኑን በተጨባጭ ስራዎች እያሳየ ነው። በዞኑ በትልቅ በጀት የሚሰሩ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን በብዛትና በጥራት ለአገልግሎት በማብቃት ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል። በዚህም ዓመት በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሕብረተሰቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታዎችን የሚፈቱ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረግ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ከመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ ጎን ለጎን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች የሚጠናከሩ መሆኑን አስረድተዋል። ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶችም የአስተዳደር ሕንጻዎች፣ ድልድዮች፣ የጤና ተቋማት፣ መንገዶች፣ የሶላር ኃይል ማመንጫ፣ የመጠጥ ውሃና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ፣ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የበርካታ ፕሮጀክቶች ግንባታ መካሄዱን አስታውሰዋል። ፕሮጀክቶቹ የልማትና የአገልግሎት ተደራሽነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የሀሉ ወረዳ ነዋሪዎች ለአገልግሎት እየበቁ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያለውን አቅም የሚያሳድጉ፤ የሕብረተሰቡንም ማሕበራዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የአስተዳደር ሕንጻው ብዙ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በአንድ ሕንጻ ውስጥ የሚሰበስብ እንደመሆኑ አገልግሎት ለማግኘት የሚጠይቀውን ድካም የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል።
ክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም ይገባል
May 20, 2026 220
ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ፣ ዳሞት ፑላሳ ወረዳዎች እና ሻንቶ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በምረቃው ላይ እንደገለጹት፤ ክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም ይገባል። የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል። ዛሬ በወላይታ ዞን በዳሞት ጋሌና በዳሞት ፑላሳ ወረዳዎች እንዲሁም በሻንቶ ከተማ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የዚሁ አካል መሆናቸውን አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ ባለፉት 9 ወራት 275 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ተስፋዬ ናቸው። ዛሬ የተመረቀው የ15 ኪሎ ሜትር መንገድ በሻንቶ ከተማ፣ በዳሞት ፑላሳና በዳሞት ጋሌ ወረዳዎች የሚገኙ ቀበሌያትን የሚያገናኝ ነው ብለዋል፡፡ የሀርቶ ቆንጦላ ጫራቄ ተንጠልጣይ ድልድይ ደግሞ የዳሞት ጋሌና የዱጉና ፋንጎ ወረዳዎች ከ22 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አስረድተዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ በዞኑ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለአገልግሎት ክፍት በመደረጋቸው የህዝቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። ለአብነትም የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ግንባታ ህዝቡ በቅርበትና በተመጣጣኝ ዋጋ መድኃኒት እንዲያገኝ ማገዙን ጠቁመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ በመንገድና ድልድይ ማጣት ሁለቱ ወረዳዎች ተለያይተው እንደቆዩ ተናግረዋል። አሁን መንግስት ችግሩ እንዲፈታ በማድረጉ የጤና አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ በቀላሉ ወደ ገበያ ሄዶ ለመገበያየት እንደቻሉም ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም መድኃኒት ለመግዛት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ርቀው ይጓዙ እንደነበርም ተናግረዋል። መድኃኒት ቤት በአቅራቢያቸው በመገንባቱ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እና በቅርበት ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በቅመማ ቅመም ምርት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር እየተስፋፋ ነው
May 20, 2026 265
ቴፒ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ በቅመማ ቅመም ምርት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ዝግጅት ሂደትን የማስፋፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ። ማዕከሉ የእርድ ምርትን ለገበያ ለማቅረብ የሚደረገውን ልማዳዊ አሰራር የሚያስቀር አዲስ ቴክኖሎጂ ለአርሶ አደሮች አስተዋውቋል። የእርድ ምርትን በባህላዊ መንገድ ለማዘጋጀት የሚደረገው የመቀቀል ሂደት ከፍተኛ የእንጨት፣ የውሃ፣ የጊዜና የጉልበት ብክነትን የሚያስከትል እንደሆነ ተገልጿል። የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ደረጀ ቱሉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ማዕከሉ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባደረገው የምርምር ሥራ ያስተዋወቀው አዲስ ቴክኖሎጂ የምርቱን ጥራት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያስጠብቅ ነው። በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ምርት ለማቅረብ ጥራት ትልቅ ትርጉም እንዳለው የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ አዲሱ የእርድ ማዘጋጃ ማሽን ጊዜና ጉልበትን በእጅጉ የሚቆጥብ መሆኑን አስረድተዋል። የቅመማ ቅመም ምርቶችን በብሔራዊ ደረጃ የሚያስተባብረው ይህ ማዕከል፤ የእርድ ሰብልን በክልሉ በስፋት ማስተዋወቁን ገልጾ፣ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የማሰራጨት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በማዕከሉ የቅመማ ቅመም ምርት ብሔራዊ አስተባባሪና ተመራማሪ የሆኑት አቡኪያ ጌቱ በበኩላቸው፤ አዲሱ የእርድ መክተፊያ ማሽን ከዚህ ቀደም ሦስት ሳምንታት ይፈጅ የነበረውን የምርት ዝግጅት ጊዜ ወደ 5 ቀናት ዝቅ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። በላብራቶሪ በተደረገ ፍተሻ በማሽኑ የተዘጋጀው ምርት የተሻለ የጥራት ደረጃ መያዙ መረጋገጡንና ይህም ለሀገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ከባዕድ ነገሮች የጸዳ ምርት ለማቅረብ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል። የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አዳምሰገድ ኃይለኢየሱስ ፤ በዞኑ ካለው ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ የእርድ ማሳ፣ በዓመት ከ20 ሺህ ቶን በላይ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል። ማዕከሉ የተሻሻሉ ዝርያዎችን ከማቅረብ ባለፈ፣ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቁ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ፤ አርሶ አደሮች ተደራጅተው ማሽኑን መጠቀም የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮችም፤ ነባሩ የእርድ ዝግጅት ሂደት የማገዶ፣ የውሃ እና የጉልበት ብክነት ስለሚያስከትል እስካሁን ከምርቱ ተገቢውን ጥቅም እንዳላገኙ ገልጸዋል። በተጨማሪም የተቀቀለው እርድ ደርቆ ለገበያ እስኪበቃ ረጅም ጊዜ ይወስድ እንደነበር አስታውሰው፤ ማዕከሉ ያስተዋወቀውን ማሽን በመጠቀም ምርታቸውን በቀላሉ አዘጋጅተው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለገበያ ለማቅረብ ትልቅ ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የእርድ ምርት ለምግብ ዝግጅት፣ ለአልባሳት ማቅለሚያና ለፊት መዋቢያዎች ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ያለው የቅመማ ቅመም ዓይነት መሆኑ ይታወቃል።
ስማርት ቆጣሪዎች ዘመናዊና ግልጽ አሰራርን በማስፈን የኃይል ብክነትን መቀነስ አስችለዋል
May 20, 2026 308
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ) ፡-በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የስማርት ቆጣሪዎች ትግበራ ዘመናዊና ግልጽ አሰራርን በማስፈን የኃይል ብክነትን መቀነስ ማስቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በአገልግሎቱ የፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት የዲስትሪዩብሽንና አውቶሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ተስፋዬ ሂርጳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አገልግሎቱ አስተማማኝ፣ቀልጣፋ እና ተደራሽ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት የስማርት ቆጣሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው፡፡ ለዚህም 500 ሺህ ስማርት ቆጣሪዎችን በመግዛት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 160 ሺህ ቆጣሪዎች ተገጥመው ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ ከተገጠሙት ስማርት ቆጣሪዎች መካከል 140 ሺህ ባለ ነጠላ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ባለ ሶስት ፌዝ መሆናቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋት በቀጣይ 300 ሺህ የደረሱ ስማርት ቆጣሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ ስማርት ቆጣሪዎች ደንበኞች ያለ አንዳች እንግልት ባሉበት ሆነው ክፍያ መፈጸም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠቃሚዎች ምን ያህል ኃይል እየተጠቀሙ እንደሆነ እንዲረዱ ከማገዙም በላይ የኃይል አጠቃቀማቸውን ተረድተው አላስፈላጊ አጠቃቀምን በመቀነስ ኃይልን መቆጠብ ያስችላል ነው ያሉት። ከቆጣሪና ከኃይል አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የደንበኞችን ቅሬታ ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር መሆኑን ገልጸው፤ በኃይል አጠቃቀም የመረጃ ንባብ መዘግየትና መሳሳት ተቋሙ ሊያጣ የሚችለውን ገንዘብ ያስቀራል ብለዋል፡፡ ስማርት ቆጣሪዎች ማናቸውንም አይነት የቆጣሪ ማጭበርበር ወይም ያልተፈቀደ ንክኪ በቀጥታ ወደ ማዕከላዊ ቁጥጥር ክፍሉ የማሳወቅ ብቃት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ የኃይል ሥርቆትን ለመከላከል የጀመረውን ሥራ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከፍተኛ የኃይል ሥርጭት በሚያጋጥምበት ወቅት አደጋዎች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ቆጣሪው ኃይል ማገድ የሚያስችል ስርዓት እንዳለው ጠቁመዋል። በምሥራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቁጥር ስምንት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ስራ አስኪያጅ ድሪባ አብዲሳ በበኩላቸው፤ማዕከሉ የነጠላና የባለሶስት ፌዝ ስማርት ቆጣሪዎችን ለነዋሪዎችና ለደንበኞች እየገጠመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የስማርት ቆጣሪዎች ቴክኖሎጂ አዲስ መሆኑን በመግለጽ፤ አገልግሎቱን በተመለከተ ለኅብረተሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን ስኬታማ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራ ተሞክሮ ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል
May 20, 2026 216
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12 /2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን ስኬታማ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ትግበራ ተሞክሮ ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ገለጹ። በኮትዲቩዋር መዲና አቢጃን በተካሄደው የ"ID4Africa 2026" የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ተሞክርን በማካፈል የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ብቃትና ዕድገት በተግባር ማሳየት ተችሏል፡፡ የ"ID4Africa 2026" ዓመታዊ የአፍሪካ የዲጂታል መታወቂያ ጉባኤ "ከዲጂታል መሠረተ ልማት ወደ ዲጂታል የሕዝብ ሥነ-ምህዳር" በሚል መሪ ሃሳብ በኮትዲቩዋር መዲና አቢጃን እ.ኤ.አ ከግንቦት 12 እስከ 15 ቀን 2026 ተካሂዷል። በዚህም በሀገር በቀል አቅም የተገነባው የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ጉባኤው ላይ አድናቆት እንደተቸረውም ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመዘገበችውን ውጤታማ ጉዞና ተሞክሮ አቅርባለች። የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ጉባኤውን አስመልክተው ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ መድረኩ ኢትዮጵያ የራሷን ተሞክሮ ከማቅረብ ባለፈ ሌሎች ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ስራዎቿ አዎንታዊ ምስክርነት የሰጡበት ነው። ጉባኤው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ብቃትና ዕድገት በተግባር ማሳየት የተቻለበት መሆኑንም ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ከተካሄደው የ“ID4Africa 2025” መድረክ ወዲህ በሀገሪቱ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ረገድ አስደናቂ ለውጥ መመዝገቡን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት የብሔራዊ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ43 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ጠቅሰዋል። ይህም በየሳምንቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የመመዝገብ ከፍተኛ ብሔራዊ አቅም መፈጠሩን የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነቱን ከማስፋት ጎን ለጎን፣ ከተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የማቀናጀት ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በባንክና ፋይናንስ፣ በትምህርት እንዲሁም በጤና መድህን ዘርፎች በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማካተት የቻሉ ወደ 132 የሚጠጉ የአገልግሎት ሥርዓቶች ትስስር መፈጠሩን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት በራሷ ወጣቶች፣ መሐንዲሶች እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቁርጠኝነትና በሀገር በቀል ዕውቀት መገንባቷ በጉባኤው ላይ ትልቅ አድናቆት እንዳስገኘላት አስታውቀዋል። ይህ በራስ አቅም የተመዘገበው ስኬት ከኢትዮጵያ አልፎ እንደ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክ ያሉ የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለመውሰድና አጋርነት ለመመሥረት ከፍተኛ ፍላጎት እንዲያሳዩ በር ከፍቷልም ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የቢሊዮን ሕዝብ መለያ ሥርዓት ባለው የሕንዱ አድሃር (Aadhaar) ከፍተኛ ኃላፊዎች ጭምር የሕንድን ሥርዓት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር በማቀናጀት፣ የሁለቱን አገራት የቴክኖሎጂ ትብብር ለማሳየት ፍላጎት ማቅረባቸውን አክለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ገጽታ በራስ ስታቲስቲክስና እይታ መግለጽ የመረጃ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ ነው
May 20, 2026 226
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12 /2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ በራስ ስታቲስቲክስና እይታ መግለጽ መቻሉ የመረጃ ሉዓላዊነትን የማረጋገጫ ዋነኛ መንገድ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) ገለጹ። ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት'' በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉባኤውን በይፋ በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ መሆኑን አስገንዝበዋል። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ተቋማቸው የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታዎችን በትክክል የሚያንጸባርቁ ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን በስፋት በማመንጨት ላይ ይገኛል። ተቋሙ በዋናነት ለውሳኔ ሰጪዎች፣ለእቅድና ለልማት ስትራቴጂዎች መንደፊያ የሚሆኑ ኦፊሴላዊ የስታቲስቲክስ መረጃዎችን በማመንጨት እንደሚታወቅም ጠቁመዋል። በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በገንዘብና በባለሙያ ድጋፍ ስም መረጃዎቻቸው እንዳይቀለበሱና የራሳቸውን እውነታ በሌሎች እይታ እንዳያዩ የመረጃ ሉዓላዊነትን ማስከበር ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል። ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡት የኢኮኖሚ ሪፎርሞች እንዲሁም የሀገሪቱ የዲጂታላይዜሽን ፍጥነት እጅግ አስገራሚ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ እያሳየች ያለው ሁለንተናዊ እድገት የሰው ሀብት ልማት አቅሟንና የባለሙያዎቿን ክህሎት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገው እንደሚገኝ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር መጥተው የሚማሩበትና የሚደመሙበት ደረጃ ላይ ደርሷል ነው ያሉት። ይህንን የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት በመጠቀም የሀገሪቱን ትክክለኛ ገጽታ በራስ ስታቲስቲክስና እይታ መግለጽ መቻሉ የመረጃ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ተቋሙ ለውሳኔ ሰጪነትና ለትንበያ ስራዎች የሚጠቅመውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስና የሮቦቲክስ እድገትን በማጣጣም የዚህ ዲጂታል ለውጥ ተጠቃሚ መሆን መቻሉ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ትልቅ አቅም ያለው የሰርቨር መሠረተ ልማት መገንባት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ስጋቶችን ለመቀነስና መረጃዎችን በአንድ ቋት ብቻ ከመያዝ ለመውጣት በቴሌ ክላውድና በተለያዩ አማራጮች መረጃዎችን የማባዛት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህ የክላውድ አማራጮች መረጃዎችን በተለያዩ አስተማማኝ ስፍራዎች አስቀምጦ ከመጠበቅ ባሻገር፣ ለአጠቃቀማቸው ጥብቅ የሆነ የደህንነት ጥበቃ እንደሚደረግላቸውም አረጋግጠዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል
May 20, 2026 223
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ በአራት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለዓለም ዋንጫ የመለያ ጨዋታ አልፏል። ቡድኑ ወደ መለያ ጨዋታው የተሸጋገረው ትናንት ቱኒዚያን 1 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ ነው። ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከሞዛምቢክ ጋር ይጫወታል። ሞዛምቢክ በምድብ ሶስት ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በተያያዘም በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ከቱኒዚያው ጨዋታ በኋላ ዛሬ ልምምድ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋሩ
May 20, 2026 220
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሩዋንዳዊው ፓትሪክ ሲቦማና በ16ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪ ሆኗል። አስቻለው ታመነ በ63ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ድሬዳዋ ከተማን አቻ ያደረገውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ46 ነጥብ ከነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም። ድሬዳዋ ከተማ በ35 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ33ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 1 ሲረታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን፣ መቀሌ 70 እንደርታ ሸገር ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ሶስተኛው ዙር የክለቦች ቦክስ ሻምፒዮና መካሄድ ጀመረ
May 20, 2026 161
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው ሶስተኛው ዙር የክለቦች ቦክስ ሻምፒዮና በራስ ኃይሉ ስፖርትና ስልጠና ማዕከል ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። በውድድሩ ላይ በሁለቱም ጾታዎች ከ12 ክለቦች የተወጣጡ 126 ቦክሰኞች ተሳታፊ ሆነዋል። ሻምፒዮናው ለስፖርተኞች ተከታታይነት ያለው የውድድር እድልን ለማመቻቸት፣ በብሔራዊ ደረጃ ሀገርን ወክለው የሚወዳደሩ ብቁ ስፖርተኞችን ለመመልመልና ለመምረጥ ዓላማ ያደረገ ነው። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ መነቃቃት እየታየበት ላለው የካራቴ፣ ማርሻል አርት እና ኤምኤምኤ (MMA) ስፖርት ዘርፎች፤ ብቁ ስፖርተኞችን ከሻምፒዮናው በመመልመል ተጠቃሚ ማድረጉ የውድድሩ ሌላኛው ግብ ነው። የሶስተኛው ዙር የክለቦች ቦክስ ሻምፒዮና ውድድር ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ሻምፒዮናው በዓመት አራት ጊዜ የሚካሄድ ነው። ሁለት ሻምፒዮናዎች አስቀድመው በአዲስ አበባ ተደርገዋል። የመጨረሻው ውድድር ከአንድ ወር በኋላ ይከናወናል። የአራቱ ውድድሮች አጠቃላይ ውጤት ተደምሮ በሁለቱም ጾታዎች አጠቃላይ አሸናፊ ክለቦች ይለያሉ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ
May 20, 2026 155
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ አለማየሁ በስምንተኛው ደቂቃ ግቡን ከመረብ ጋር አገናኝቷል። በሊጉ 11ኛ ድሉን ያገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ45 ነጥብ ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ ዝቅ ብሏል። ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሃዋሳ ከተማ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።
አካባቢ ጥበቃ
በክልሉ ከ261 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ ተጀምሯል
May 20, 2026 319
ባህርዳር ፤ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ከ261 ሺህ ሔክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ችግኞችን ለመትከል የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር እስመለዓለም ምህረት ለኢዜአ እንደገለፁት የክልሉን የደን ሽፋን ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው። በመጭው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን በላይ የዋንዛ፣ ወይራ ፣ ዝግባ ፣ ፅድ ፣ አኬሺያ ዲከረንስ፣ ባህር ዛፍ፣ የፍራፍሬና ሌሎች ችግኞችን ለመትከል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የችግኝ ተከላውን በስኬት ለማከናወን እስካሁን 401 ሚሊዮን በላይ ጉድጓዶችን በማስቆፈር ለተከላ ዝግጁ ማድረግ መቻሉን አረጋግጠዋል። በቀጣይም የአረንጓዴ አሻራ ግብን ለማሳካት ተጨማሪ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶችን የማስቆፈር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። ባጠቃላይ በክረምቱ ለሚካሄደው ችግኝ ተከላ 261 ሺህ 297 ሄክታር መሬት ከወዲሁ ተለይቶ የጉድጓድ መቆፈር ስራው እየተካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ አርሶ አደር መኮነን ልንገር እንደገለጹት ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጀመሩ ተራቁተው የነበሩ አካባቢዎችን መልሰው በደን እንዲሸፈኑ ለማድረግ አስችሏል። መርሃ ግብሩ ለመኖ ፣ በንብ ማነብና እንስሳት እርባታ እያስገኝ ያለውን ተጠቃሚነት ለማስፋት በመጭው ክረምት በሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በግልና በወል ቦታዎች ችግኝ ለመትከል ጉድጓዶችን እያዘጋጀን ነው ብለዋል። የሚተከሉት ችግኞች አያስገኙ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት በየዓመቱ ችግኞችን እያለማሁ ነው ያሉት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን የደራ ወረዳ አርሶ አደር ካሴ መንግስት ናቸው። በመጭው ክረምት የሚተከሉ ችግኞች ተንከባክበን በማሳደግ ለውጤት ለማብቃት ከወዲሁ ዝግጅት ጀምረናል ነው ያሉት። ባለፈው ክረምት በነቃ የህዝብ ተሳትፎ ከተተከለው ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው መጽደቁን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአፍሪካ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ሀገራት ቅንጅታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል
May 19, 2026 550
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በአፍሪካ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ሀገራት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ፀባይ ትንበያ ማዕከል ጋር በመተባበር ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየውን 73ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የአየር ፀባይ አዝማሚያ ትንተናና ትንበያ ፎረም ተጠናቋል። በፎረሙ የቀጣናው ሀገራት ተወካዮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅት ተወካዮች እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዚዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በአፍሪካ ቀንድ ዙርያ ያሉ የኢጋድ አባል ሀገራት ያለፈው የበልግና መጪው ክረምት ወቅት የሚጠበቀውን የአየር ጠባይ ትንበያን አስመልክቶ ተወያይተዋል። በዚህም ሁሉም ሀገራት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የራሳቸውን የሜቲዎሮሎጂ መረጃዎችንና ከአካባቢያቸው አየር ሁኔታ በማገናዘብ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቅያ የሚሰጡበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸው አንስተዋል። ከአየር ትንበያው በመነሳትም የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርና፣በውሃ፣በጤና ላይ ሊያደርሰ የሚችለው አሉታዊና አዎንታዊ ተፅእኖ በመገምገም ለቀጣይ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑ ተናግረዋል። እንዲሁም በህይወትና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን የአደጋ ተጋላጭነትን ከመቀነስ አንፃር ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ መሰል መድረክ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው የላቀ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ አደጋዎች በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ይህን ለመከላከል ሀገራት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና የመተግበሪያ ማዕከል(ICPAC) ዋና ዳይሬክተር አብዲ ፊዳር (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የኢጋድ አባላት ሀገራት መረጃን መሰረት ያደረገ መረጃ በመለዋወጥ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል።
ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ እስካሁን ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል-ግብርና ሚኒስቴር
May 19, 2026 454
አዲስ አበባ፤ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን ከ8 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኝ የማዘጋጀት ስራ መከናወኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአየር ንብረት ተፅዕኖን በመቀነስና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎችን እያስገኘ ይገኛል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገር በቀል እጽዋቶችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን ከመጠበቅ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከልና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን ከማከናወን አንጻር ግንባር ቀደም ለውጥ አስገኝቷል፡፡ ባለፉት ሰባት ዓመታት በተሰሩት ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በመርሃ-ግብሩ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልማት ከተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ባለፈ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን የሰነቀ ሲሆን የአየር ንብረት ተጽዕኖን በመቀነስ ለኢትዮጵያ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ መስኮች ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል፡፡ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ ለሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ላይ የተከናወኑ ሥራዎችና የተመዘገቡት አበረታች ውጤቶች ትልቅ ምስክር ናቸው፡፡ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የሁለተኛው ምዕራፍ ማጠናቀቂያ መሆኑን የገለጹት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ ቀደም ሲል ከነበሩ የአረንጓዴ አሻራ አፈጻጸሞች የተወሰዱ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ የዘንድሮው ዕቅድ በቁጥር ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህም መሠረት 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ሰፊ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንና አሁን ላይ ለተከላው የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ጠቁመው የስነ-ምህዳር ሁኔታን መሠረት ያደረገ የችግኝ ዝርያዎች መረጣ መከናወኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ችግኝ የሚተከሉባቸው ጉድጓዶችን የማዘጋጀት ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አሁን ላይ በበርካታ ዜጎች ዘንድ ባህል እየሆነ መምጣቱንና የተሳታፊዎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አንድነት በተግባር የሚረጋገጥበት ትልቅ አገራዊ ኩነት በመሆኑ፣ መላው ሕዝብ በኃላፊነት ስሜትና በቀዳሚነት እየተሳተፈበት ይገኛል ብለዋል። ለዘንድሮው የችግኝ ዝግጅት ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል 40 በመቶው ሀገር በቀል የደን ዛፎች ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቅሰው፣ 60 በመቶው ደግሞ ለምግብ ዋስትናና ለሌሎች ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች የሚውሉ የፍራፍሬና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን አስረድተዋል።
ትውልዱ የአካባቢውን ልምላሜ ጠብቆ በማቆየት የማህበረሰቡን የደን ልማት ባህል ማስቀጠል አለበት-የሀገር ሽማግሌዎች
May 19, 2026 393
ጂንካ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ትውልዱ የአካባቢውን ልምላሜ ጠብቆ በማቆየት የማህበረሰቡን የደን ልማት ባህል ለማስቀጠል ግንዛቤን እየፈጠሩ መሆኑን የአሪ የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአሪ ማህበረሰብ ደኖችን ጠብቆ የማቆየትና የመንከባከብ ጠንካራ ባህል አለው። በዞኑ ሰሜን አሪ ወረዳ የጎዛ ቀበሌ የሀገር ሽማግሌዎችም ትውልዱ የአካባቢውን ልምላሜ ጠብቆ በማቆየት ለመጪው ትውልድ እንዲያሻግር ግንዛቤ በመፍጠር ደኖችን የመንከባከብ ባህሉን ለማስቀጠል እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የሃገር ሽማግሌ አቶ ተክሌ ተረፈ እንደገለፁት፤ በአካባቢው ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር የቆየ ደኖችን የመንከባከብ እና ጠብቆ የማቆየት ባህል አለ፡፡ ባህሉ ሳይሸራረፍ እንዲቀጥል በደን ተከላና እንክብካቤ ከማሳተፍ ባለፈ የደኖች መኖር ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ግንዛቤ የመስጠትና የማስተማር ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በእርሻ ስራ ውጤታማ ለመሆን ደኖችን ጠብቆ ማቆየት ተገቢ መሆኑን ጠቁመው ደን ከሰው ልጅ ህይወት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ስላለው እንክብካቤ እንደሚያስፈልገውም አስረድተዋል። ደኖች የተራቆቱባቸው አካባቢዎች በተፈጥሮ አደጋዎች በተደጋጋሚ ሲፈተኑ አስተውለናል ያሉት ደግሞ የሀገር ሽማግሌው ብላታ ቶዳ ናቸው። አዲሱ ትውልድ ይህን በመገንዘብ ደኖችን እንዲንከባከብ፣ በተራቆቱ አካባቢዎች ችግኞችን እንዲተክሉ ግንዛቤ በመፍጠር ትውልዱን የማነፅ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙም ገልጸዋል። የአሪ ባህላዊ የዕርቅ ስነ-ስርዓት፣ አፈ-ታሪኮች፣ የመጪው ዘመን ትንበያ እና ሌሎች ባህላዊ ስነ-ስርዓቶች የሚፈፀሙት በደኖች አካባቢ በሚገኝ ትልቅ ዋርካ ስር እንደሆነ የገለፁት ደግሞ አቶ አለማየሁ ታጋ ናቸው። በደኖች አካባቢ የሚፈፀሙ ባህላዊ ስርዓቶች የደኖችን ጥቅም ለአዲሱ ትውልድ ለማስተማር ታስቦ እንደሆነም አመልክተዋል። ደኖች ከሰው ልጅ ህልውና ጋር የተቆራኙ በመሆናቸው አዲሱ ትውልድ ይህን ተገንዝቦ የአካባቢውን ለምላሜ ጠብቆ እንዲያቆይ የማስተማር ስራ እየሰራን ነው ብለዋል። በአሪ ዞን የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ጽህፈት ቤት የደን ጥበቃና ቁጥጥር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ክንዴ ፍሰሃ በዞኑ ደኖችን ጠብቆ ለትውልድ የማሻገር ጠንካራ ባህል እንዳለ ገልፀዋል። በዞኑ ከ21 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት በደን መሸፈኑን ጠቁመው በዚህም 41 ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች እንደሚገኙ ተናግረዋል። በአካባቢው በሚገኘው ደን ውስጥም ለመድኃኒትነት የሚያገለግሉ በርካታ የዕፅዋት ዓይነቶች እንዳሉም አስረድተዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዞኑ ከ12 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በተራቆቱ አካባቢዎች የሚተከሉ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም የአካባቢው የደን ሽፋን እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 1536
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 946
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 869
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 13, 2026 910
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በሕብረቱ ዋና መቀመጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል። በውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ውይይቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል በአፍሪካ ልማት እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅት፣ የጋራ ተጠያቂነት እና ትብብርን በልማት፣ በአስተዳደር፣ በሰብአዊ ድጋፍ እና በሰላም ግንባታ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ያላቸውን ትስስር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ በርካታ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ሲሆን፣ በተለይም የአጀንዳ 2063 እና የሁለተኛው የአስር ዓመት ምዕራፍ የትግበራ ዕቅድ አፈፃፀምን ማፋጠን እንዲሁም አፍሪካን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ እና አስተዳደር ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና መጠበቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም "ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት" የተሸጋገረ የልማት ፋይናንስ፣ የ2026 የአፍሪካ ሕብረት የዓመቱ መሪ ቃል የሆነው ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፎርም እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና የተመለከቱ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል። መድረኩ ለአህጉራዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ማምጣት፣ የአገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብን ማሳደግ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲሁም በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የልማት የቅድሚያ ትኩረቶች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት የሚሰጥበት እንደሆነ ተመላክቷል። ከውይይቱ ከሚጠበቁ ውጤቶች መካከል የተሻለ ስትራቴጂካዊ ቅንጅት፣ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ፣ በአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ቃል ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር እና በተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ውስጥ ፍትሐዊ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር የቀረቡ ጥሪዎችን ማጠናከር እንደሚገኙበት ህብረቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የውይይቱን ውጤቶች አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
May 17, 2026 855
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፦ የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን። 👉የግንቦት - ታላቁ ሁነት የምርጫ ጉዳይ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ በሁሉም አካባቢዎች የዜጎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ሳምንት ነው። መራጮች ካርዳችንን ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተመቻቸላቸው ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ የፖሊሲ አማራጮቻቸውንና ማኒፌስቷቸውን እያስተዋወቁ ቀጥለዋል። የተለያዩ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ። ለዘንደሮው ጠቅላላ ምርጫ በመራጮች ትምህርት ላይ ለሚሰማሩ 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና መስጠቱ ይታወቃል። 👉የመጠጥ ውሃ ችግሮችን የመፍታት ጥረት ማሳያዎች በሳምንቱ በወላይታ ዞን ከ150 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሆቢቻ ወረዳ ብዝሃ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) መርቀዋል። የፕሮጀክቶቹ ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የላቀ ትርጉም እንዳለው ተነስቷል። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ በቀብሪደሃር ከተማ በ407 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚካሄድ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ከለውጡ በኋላ በክልሉ ከ370 በላይ የጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች ተቆፍረው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዚህም የመጠጥ ውሃ ሽፋኑ ከ19 ወደ 52 በመቶ ማሳደግ መቻሉ ታውቋል። በምስራቅ ሐረርጌ ዞንም የደደር ከተማንና የአካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክትም ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው በዚሁ ሳምንት ነበር። የፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ የኦሮሚያ ክልል መሬት ቢሮ ሃላፊ መሰረት አሰፋ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር እና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ደደር ከተማን ጨምሮ ሌሎች በወረዳው ሶስት ቀበሌዎች የሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል። 👉የጤና ጉዳይ የጤና ሚኒስቴር የተቀናጀ የህክምና እና የምርመራ ዘመቻ ከግንቦት 3 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በስምንት ክልሎች በሚገኙ 154 ወረዳዎች የሚያካሄድ መሆኑ የተገለጸውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ይሄው መርሃ ግብር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩ በተለይም ትምህርት ቤቶችን ማዕከል በማድረግ የሚከናወን ሲሆን ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል። 👉ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የውይይት መድረክም የሳምንቱ አበይት ጉዳይ ነበር። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጂነት የመውጣት ጥረት ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። በግብርና ልማት በተለይም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተመዘገበውን የላቀ ስኬት ለአብነት ጠቅሰዋል። በሌሎች የተለያዩ የግብርና የልማት ስራዎችንም በተጠናከረ መልኩ በማከናወን ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተረጂነት የመውጣት ጉዳይ የብሔራዊ ጥቅም አካል ሆኖ የመንግስት ስትራቴጂክ አጀንዳ ተደርጎ በፖሊሲ አቅጣጫ እየተመራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ብልጽግና እውን በማድረግ የኢትዮጵያን የድህነት ታሪክ መቀየር ይኖርብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሠይፈ ደርቤ በበኩላቸው፤ እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረው ግብ እንዲሳካ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም ሚዲያ የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸው ኢዜአ ይህንን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የይዘት ስራዎችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። 👉የምግብ ስርዓት ሽግግር በጋምቤላ ክልል ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚተገበረው የምግብ ስርዓት ሽግግር እና የኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጋምቤላ ከተማ በይፋ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን(ዶ/ር)፤ በክልሉ የተሟላ ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። 👉ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በአሶሳ በአሶሳ ከተማ ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የተጀመረው በዚሁ ሳምንት ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የትምህርት ቤቱን ግንባታ አስጀምረዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን 34 ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተገነቡ መሆኑን ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በአሶሳ ከተማ የሚገነባው ትምህርት ቤትም በአንድ ዓመት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል። 👉የሰላምና አብሮነት እሴት ግንባታ የሐረሪ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞንና የማያ ከተማ አስተዳደር "የህዝቦች ሰላምና አብሮነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የህዝብ ለህዝብ የሰላምና አብሮነት ኮንፍረንስ የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፤ የሐረርጌ ህዝቦች ትስስር በሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠውና ለታላቅ ማህበራዊ ውህደት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል። የኮንፈረንሱም ዓላማ የሰላም እሴት ግንባታና የልማት ትስስርን ይበልጥ ማጠናከር ስለመሆኑ አንስተዋል። 👉የግብርና ልማትና ምርታማነት በአማራ ክልል ለዘንድሮው የመኸር እርሻ ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ያስታወቀው በዚሁ ሳምንት ነው። የአፈር ለምነትን በዘላቂነት ለማሻሻል ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ76 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ እስካሁን ከ81 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ኮምፖስት መዘጋጀቱ ታውቋል። 👉በኦሮሚያ ክልልም ለዘንደሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካል የሆነው ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአቮካዶ ተክል እንደሚሸፈን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ኃላፊ ሙሐመድሳኒ አሚን፤ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም አቮካዶን ጨምሮ አስር አይነት የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ስለመዘጋጀታቸውም ተናግረዋል። በተለይም አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ዘይቱን፣ ፓፓያ፣ ግሽጣ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሎሚና ሌሎች የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። በክልሉ የአቮካዶ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን በማዳቀል የችግኝ ዝግጅት ላይ በስፋት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት። በክልሉ እስካሁን ከ80 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመደበኛና በተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞች መሸፈኑንም ገልጸዋል። 👉የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ ሎካ አባያና ደራራ ወረዳዎች በበልግ ወቅት በኩታ ገጠም እየለማ ያለውን የበቆሎ ማሳ በመስክ የተመለከቱትም በዚሁ ሳምንት ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ የሰብል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገበያን የሚያረጋጋ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች ውጤት እየተገኘ ነው። በዚህም በበልግ ወቅትም ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር በማድረግና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እየተከናወነ ባለው የእርሻ ስራ የምርት ቁመናው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል። በበልጉ ያለውን አመቺ የዝናብ ስርጭት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመጠቀም የተሻለ ምርት ለማግኘት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት አሁን ላይ ለማሳ እንክብካቤ ስራ ትኩረት መሰጠቱን አመልክተዋል። 👉የኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው የመረቋቸው የምግብ ዘይት እና የቆርቆሮ ማምረቻ ፋብሪካዎች ሥራ የጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሙሄ፤ በኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ልማት ይበልጥ እያንሰራራ ስለመሆኑ አንስተዋል። በኢንዱስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በድምሩ 69 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ገልጸው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረትና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን በመተካት ከፍተኛ የሃብት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 1496
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል። በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 1319
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 1389
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
ትንታኔዎች
እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት
May 17, 2026 3195
በኢዜአ ዐይን …! በዮሐንስ ደርበው እንግልትንና ብልሹ አሠራርን መቅረፊያ ብልኀት - መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለእንግልትና ብልሹ አሠራር አጋላጭ ሁኔታዎች ይስተካከሉን የሚሉ እሮሮዎች በተለያዩ ሕዝባዊ ውይይቶች ሲነሱ ቆይተዋል። በተለይም በአንዳንድ ተቋማት መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት እዚያም እዚህም መንከራተት፤ደግሞም ወረፋ በመጠበቅ መጉላላት ብሎም ለጊዜና ገንዘብ ወጪ መዳረግ ይስተዋላል የሚሉ ሐሳቦች ተስተጋብተዋል። ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ባሳለፍነው ሳምንት … መንግሥትም የተነሱ ቅሬታዎችን ማረቅ የሚያስችል አሠራር በመንደፍ ሚያዝያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንድ ብሎ አስጀመረ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማዕከሉ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅትም ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሠራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ብለው ነበር። አሁን ላይም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሁን በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋ ነው።መስፋፋቱም በማዕከላት ብዛት፣በአገልግሎት መስጫ መስኮቶች ቁጥር እና በአገልግሎት ዐይነቶች እየተገለጠ ነው። በዚህም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 2 ሺህ 260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት የተደራጁ ሲሆን ይህ አሃዝም ለዘርፉ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና ያለውን ፈጣን እድገት ያመላክታል። ጉዳዩ የዜጎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ማላቅ፤ ብልሹ አሠራርንም መቅረፍ ነውና መንግሥት በልዩ ትኩረት ይዞታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ አሥተዳደርና በሐረሪ ክልል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅትም፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የምልከታቸው አካል ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ከፍያለ ትኩረት ያሳያል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሶብ የሞባይል አገልግሎትን በመረቁበት ወቅት ደግሞ፤ ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል። አክለውም፤በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች ዕርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል፤ ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፤ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ መሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት፤ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው ብሏል። የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሔ ይሰጣል ማለቱም ይታወቃል። የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ደግሞ፤ ዘመናዊና ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ ያስቻለ ስኬት ተገኝቷል ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አገልግሎቶችም ዜጋ ተኮር፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍልና የተገልጋዮችን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዲጂታል 2030 የአገልግሎት አሰጣጥ አመላካች ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ 50 ሀገራት መካከል አንዷ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዜጎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦንላይን በየትኛውም ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ስለመሆኑም እንዲሁ። አገልገሎቱን ያገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ እንግልትን ያስቀረ፣ ጊዜና ወጭን የቀነሰ ነውና ይስፋፋ፤ ተጠናክሮም ይቀጥል። #መሶብ_የአንድ_ማዕከል_አገልግሎት #የዜጎችን_እንግልትና_ብልሹአሠራርን_መቅረፍ #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #በኢዜአ_ዐይን
ባሳለፍነው ሳምንት …
May 17, 2026 1595
በዮሐንስ ደርበው ከግንቦት 2 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ጋር መምከራቸው ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ ጋር መክረዋል። በዚሁ ወቅትም በኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በአጋርነት እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ለነበረን ጠቃሚ የሐሳብ ልውውጥና ቀጣይነት ላለው አጋርነትም ምስጋናዬ የላቀ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ በኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል። በዚሁ ወቅትም በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሐሳቦች ተነስተዋል ብለዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ሥራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን ደህና መጡ ስል ሁልጊዜም በልዩ ኩራትና ደስታ ነው ሲሉ ተቀብለዋቸዋል። ከአቀባበሉ በኋላም፤ መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በዚህም መሠረት፤ በታዳሽ፣ የተቀናጀ እና ዘላቂ ኃይል እንዲሁም የዲጂታላይዜሽን ፕሮግራምን ለመተግበር የሚውል የ54 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ብድርን ጨምሮ የ150 ሜጋ ዋት የጂኦተርማል የመንግሥትና የግል አጋርነት አዲስ የማዕቀፍ እና የፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈርሟል። · ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስምንት አስርት ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርገዋል። እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፤ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል። በዓለም የፖስታ ኅብረት በኩል ለ192 ሀገራት የተሰራጩት እነዚህ ቴምብሮች፤ ለአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ሁሉ የሚተርፍ የታሪክ ዐሻራ ማሳያ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በተያያያዘም፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለቡድናቸው፣ በዘመናዊው ታሪክ ውስጥ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር ጥልቅ አድናቆታችንን እንገልጻለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግሥታት የጸናው ሀገራት ከመከፋፈል ይልቅ ውይይትን ስለመረጡ መሆኑን አስገንዝበው፤ ኢትዮጵያም ይህንኑ የሁልጊዜ ምርጫዋን ታጸናለች ሲሉ አረጋግጠዋል። · የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም የምክክር ባህል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው፤ ጠንካራ የሲቪክ ማኅበረሰብ ባህል ግንባታ ደግሞ ያላሰለሰ የመነጋገር ልምምድ እና የሰከነ የወል መደማመጥን ግድ ይላል ብለዋል። የእስካሁን ሂደቱም በማኅበረሰባችን በየደረጃው የመደማመጥን ከፍ ያለ ጠቀሜታ አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል። ሂደቱ በሀገራችን ሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ከ90 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያንን አመለካከቶች እና የውይይት ውጤቶች ያንፀባረቀ ሆኗልም ነው ያሉት። ለሀገር ወሳኝ ፋይዳ የያዘው የምክክሩ ምዕራፍ ተጨባጭ ውጤት ወደሚያስገኘው ቀጣይ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያረጋግጥ የጋራ ፅኑ አቋም እና ገንቢ በሆነ መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። · የገላን ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመረቁበት ወቅት፤ ፓርኩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በጀመርነው የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ እመርታ ነው ብለዋል። ለመካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች ምቹ የንግድ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል ይከፍታል ሲሉም ገልፀዋል። ፓርኩ የሀገራችን አምራቾች አቅማቸውን በማጎልበት፣ ምርታማነታቸውን ማሳደግና ተወዳዳሪነታቸውን በመጨመር ለከተማችን፣ ለሀገራችንና ለቀጣናው የሚተርፉበት ታላቅ እድልን ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት በአምራቾችና በሸማቾች መካከል ቀጥተኛና ቀልጣፋ የንግድ ትስስር ይፈጥራል፤ ምርቶችን ደግሞ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል። · ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ መጀመር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት ዓለም አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔን ባስጀመሩበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ቆራጥ ጥረት ውስጥ የሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዋና ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል በማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በመላ ሀገሪቱ ከ35 ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት የነጻና አስገዳጅ ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን እያደረግን ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር ላይ መሥራት በመሆኑ ተባብረን፣ በጊዜ የለንም መንፈስና በትጋት እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። · የፖሊሲ ቀን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት፤ ባሳላፍነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የፖሊሲ ቀን ተከብሯል። በዚሁ ወቅትም፤ ውጤታማ ፖሊሲ ለሀገራዊ ዕድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስገንዝበው፤ መንግሥት በግልፅ፣ ተተግባሪና ጥራት ባላቸው ፖሊሲዎቹ ለሕዝብ የገባውን ቃል እየተገበረ ስኬትም እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። ሀገራችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጂኦ-ፖለቲካዊና በቴክኖሎጂ ለውጦች ላይ ቀድሞ ምላሽ የሚሰጡ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በዕውቀት ላይ ኢንቨስት በማድረግ እና ለማስረጃዎች ዋጋ በመስጠት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የፖሊሲ ሥነ-ምኅዳር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ለዚህ ስኬት ሁላችንም በጋራ እንሥራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የጤና ነገር
May 15, 2026 1419
በዮሐንስ ደርበው ሾተላይ ምንድነው? እንዴትስ ይከሰታል? ቀድሞ መከላከልስ ይቻላል? ሾተላይ የሚከሰተው RH-Negative የሆነች እናት RH-Positive የሆነ ፅንስ በምታረግዝበት ወቅት የእናትየው በሽታ የመከላከል ሥርዓት የፅንሱን ደም እንደ ባዕድ ነገር በመቁጠር በሚያመነጨው ንጥረ-ነገር (Antibodies) አማካኝነት መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ዶክተር ዳንኤል ኃብተማርያም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከወሊድ ጋር በተያያዘው አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ወይም ሾተላይ እየተባለ በሚጠራው በጽንስ ላይ የሚያጋጥም ችግር ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሾተላይ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ምንድን ነው? እንደ ዶክተር ዳንኤል ማብራሪያ፤ ሰዎች ከሚታወቁበት አራቱ የደም ዓይነቶች ምደባ (ኤ፣ ቢ፣ ኤቢ እና ኦ) በተጨማሪ በቀይ ደም ኅዋስ ሰርፌስ ላይ በፕሮቲን መኖርና አለመኖር ይለያሉ። በዚህም መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ (RH+) እና አር ኤች ኔጌቲቭ (RH-) ተብለው እንደሚከፈሉ ያስረዳሉ። በዚህ ምደባ መሠረት ከአጠቃላይ ሕዝቡ 85 በመቶው አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ማለት በቀይ ደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን አላቸው ማለት ነው ይላሉ። 15 በመቶው ደግሞ አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም በቀይ የደም ኅዋሳቸው ሰርፌስ ላይ ፕሮቲን የሌላቸው ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። አክለውም አር ኤች ኔጌቲቭ ወይም ፖዘቲቭ መሆን በሽታ እንዳልሆነ በአጽንኦት ገልጸው፤ ከወላጆች የሚወረስ መሆኑን አስገንዝበዋል። ስለዚህ አንድ ልጅ ሲወለድ እንደ ወላጆቹ አር ኤች ፋክተር መሠረት አር ኤች ፖዘቲቭ ወይም አር ኤች ኔጌቲቭ ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። ይህን በምሳሌ ሲያስረዱም፤ አንዲት ሴት አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ ሆኖ ጽንሷ ደግሞ አር ኤች ፖዘቲቭ ቢሆን ተገቢው የሕክምና ክትትል ካልተደረገ ብሎም የእናትና ልጅ ደም ንክኪ ከተፈጠረ የበሽታ መከላከል ሥርዓቷ የሚያመነጨው አንቲ ቦዲ ጽንሱን እንደ ባዕድ ነገር ስለሚቆጥረው ጉዳት (ሾተላይ) ያስከትላል ይላሉ። የአንቲ ቦዲ ሥራ ሴቷ ለአር ኤች ፖዘቲቭ የምትጋለጥበት ሁኔታ ከተፈጠረ ጽንሱን (አር ኤች ፋክተሩ ከእሷ ተቃራኒ ሲሆን) እንደ ባዕድ ነገር ቆጥሮ ሴትዮዋን ለመከላከል በጽንሱ ላይ ጥቃት ማድረስ መሆኑንም አመላክተዋል። መፍትሔው ምንድን ነው? ለማንኛውም ጤናማ የእርግዝና ሂደት የሕክምና ክትትል ማድረግ ቀዳሚ መፍትሔ መሆኑን መክረዋል። ከሾተላይ ጋር በተያያዘ ደግሞ በእርግዝና ወቅት የሚስትና ባልን አር ኤች ፋክተር መለየት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። ይህን ተከትሎም አር ኤች ፋክተራቸው ተመሳሳይ ከሆነ ጽንሱም ከእነሱ ጋር ስለሚመሳሰል ጤናማ እንደሚሆን ገልጸዋል። በአንጻሩ ግን፤ አር ኤች ፋክተሯ ኔጌቲቭ የሆነች ሴት የባለቤቷ አር ኤች ፋክተር ፖዘቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አምርቷል ወይስ አላመረተም የሚለው በሕክምና ምርመራ እንደሚታወቅ አስረድተዋል። ይህ ምርመራ ሲሠራ ውጤቱ ኔጌቲቭ ከሆነ ወይም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ ሰውነቷ መከላከያ አላመረተም የሚል ከሆነ በዚህኛው እርግዝናም ለአር ኤች ፖዘቲቭ ተጋልጣ፣ የእናትና የጽንስ ደም ንክኪ ኖሮ መከላከያ እንዳታመርት የሚሰጥ ሕክምና እንዳለ አረጋግጠዋል። ይህ ሕክምናም 28ኛ ሳምንት ላይ በመርፌ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሰጣል ብለዋል። ከወለደች በኋላ ደግሞ የተወለደው ልጅ አር ኤች ፋክተር ታይቶ እንደእናቱ ከሆነ ተጨማሪ መድኃኒት እንደማያስፈልግና ከአባቱ ጋር ከተመሳሰለ ግን (አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ) በመርፌ ተጨማሪ መድኃኒት በወለደች በ72 ሠዓት ውስጥ በመስጠት ለቀጣይ እርግዝናዎች ሰውነቷ መከላከያ እንዳያመነጭ ማድረግ እንደሚቻል አብራርተዋል። በሌላ በኩል ከሾተላይ ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ሳይንሳዊ ያልሆኑ ልማዳዊ ድርጊቶችን ኮንነው፤ ትክክለኛው መፍትሔ ያለው የሕክምና ክትትል በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል። እንዲሁም፤ በተለይም የጎንዮሽ ህመም ያለባቸው ሴቶች (የኩላሊት፣ የደም ግፊት፣ ስኳር እና ሌሎችም) ቀድመው ሐኪም አማክረው ወደ እርግዝና ቢገቡ እንደሚመከር ገልጸው፤ የቅድመ እርግዝና ክትትል ማድረግ ካልተቻለ እንኳን በእርግዝና ወቅት በአግባቡ ክትትል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል። ለመከላከያ ትልቅ ትኩረት መስጠት ችግሩ ተፈጥሮ ከመታከም የተሻለና ተመራጭ መፍትሔ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። #የጤና_ነገር #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት
ለተቃና ነገ የኢትዮጵያ ትጋት አንዱ መገለጫ
May 11, 2026 2072
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ ከምትከውናቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል ሰው ተኮር ተግባራት ቀዳሚው ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ጥረት ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል። መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል አድርጎ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ ስለመሆኑም አስረድተዋል። በዚህም መሠረት፤ የልጆች ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የምገባ ሥርዓትን ማሳደግ፣ የሕጻናት መጫወቻ ሥፍራዎች ግንባታ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መምጣታቸውንም ነበር የጠቀሱት። ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማትና ትምህርት ፖሊሲ የዘላቂ ብልጽግና መንገዳችን ከሆነው የመደመር ዕሳቤ ጋር በተናበበ መልኩ እየተተገበረ በስኬት ቀጥሏልም ብለዋል። ኢትዮጵያ ለነገ የተዘጋጀ ትውልድ ለመገንባት በሕግና በፖሊሲ የተደገፉ የቀዳማይ ልጅነት ኢኒሼቲቮችን እየተገበረች እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ለአብነትም፤ በ2015 ተሻሽሎ የፀደቀው ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና ትምህርት የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም በ2017 የፀደቀውን አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ መሠረት በማድረግ ከ35ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ሀገሪቱ እየተተገበረ መሆኑን አንስተዋል። በመንግሥት ተቋማት የሕጻናት ማቆያ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በመጠቆምም፤ ኢትዮጵያ የሕጻናትን ደኅንነት ማሻሻል የሚያስችል ጉልኅ ብሔራዊ መርሐ-ግብር መጀመሯን አንስተዋል። በሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካኝነት የ15 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን መቀንጨር በ2022ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። የሌማት ትሩፋትና የአልሚ ምግቦች ምርታማነት የሕጻናትን ጉዳት ለመቀነስና የልጆችን ጤናማነት መጨመር እያስቻሉ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሕጻናት መብቶች ጥበቃ የገባቻቸውን ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር እየለወጠች መሆኑን በማንሳት፤ ይህንንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የቀዳማይ ልጅነት ልማትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አመላክተዋል። በዚህም መሠረት፤ በጀት በመመደብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ በማስፋፋት ውጤት ማምጣቱን ነው የሚያብራሩት። ልጆች በአካልና በመንፈስ የሚጎለብቱባቸው የስፖርትና የመዝናኛ ቦታዎች በየአካባቢው በመገንባት፣ በኮሪደር ልማት ለልጆች ምቹ ሥፍራ እየተፈጠረ መሆኑንም በመጥቀስ። ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር፣ አኅጉር እና ዓለም ላይ መሥራት በመሆኑ በትጋት ማስቀጠል እንደሚገባም በአጽንኦት ይናገራሉ። አፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት የራሷን መፍትሔዎች በማፍለቅ፣ በብሔራዊ የልማት አጀንዳዋ እያካተተች መሆኑን የሚገልጹት ደግሞ የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ ናቸው። በሕጻናት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማንኛውም ሀገር በመጪው ትውልድ ላይ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው እጅግ አስፈላጊ ኢንቨስትመንቶች አንዱ መሆኑንም ያነሳሉ። አፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ ያሉባትን ተግዳሮቶች ከመጋፈጥ ባለፈ፤ የራሷን መፍትሔዎች እያመነጨች መሆኑንና ጉዳዩን የብሔራዊ ልማት አጀንዳዋ አካል እያደረገችው እንደምትገኝም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ይህን ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ እንድታስተናግድ የተመረጠችበት ዋና ምክንያትም፤ በዘርፉ እያከናወነች ያለው ተግባር አርዓያነት ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል። ከተማዋ የጤና እና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶችን ያካተተ የተቀናጀ ዘርፈ-ብዙ አሠራር መዘርጋቷን ጠቅሰው፤ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት እና የቀን የሕጻናት እንክብካቤ ማዕከላትን በከተማ አቀፍ ስትራቴጂ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝም ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ መዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት ያመጣችው ተጨባጭ ውጤት በአርዓያነት እንድትጠቀስ እንዳደረጋት አንስተዋል። በሕጻናት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች፤ በትምህርት፣ በሰው ሃብት ልማትና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። በዚህም በአዲስ አበባ ፍትሐዊና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሐ-ግብርን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የትውልድ ግንባታ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። "ሕጻናት የአዲስ አበባ የነገ ተስፋዎች" የሚል ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ከስድስት ዓመት በታች ሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት መረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብርም ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ዩኒፎርምና በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ በማቅረብ በሕጻናት ክብካቤ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ነው ያሉት። የሕጻናት ማቆያና መጫወቻ የመሠረተ-ልማት ግንባታ፤ ሕጻናት ነፃ የሕክምና፣ የምገባና የሥነ-ልቦና አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር በ2015 ዓ.ም ሲጀመር በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩ የሕጻናት መጠን ከነበሩበት 13 በመቶ አሁን ላይ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ከንቲባዋ አመላክተዋል። አክለውም፤ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጁነታቸው ከነበረበት 49 በመቶ አሁን ወደ 90 በመቶ ማደጉንም ተናግረዋል። ሀገር በሁሉም ዘርፍ የበቃ መጪ ትውልድ እንዲኖራት መንግስት የያዘው ጥረት በሚፈለገው መጠን ለውጤት እንዲበቃ የሁሉንም ትኩረትና ተሳትፎ ይሻል። ለነገ በሁሉም ዘርፍ የዳበረ ትውልድና የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን ዛሬ ላይ እየተደረገ ያለው ርብርብ የሀገራችንን መፃኢ ብሩህ ተስፋ ይበልጥ የሚያለመልም ነውና ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 6432
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 3969
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 9759
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 8240
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 1197
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 2097
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።